cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሐሽማል ቤተ-መዘክር

👉Only for readers 👋መግቢያ👋 መግቢያ ለመግባቢያ ገታ አርገነዋል የቃላትን ግልቢያ እናም በዚህ ሀሳብ ከተስማማህበት ያንኳኳኸዉን በር የገለፅከዉን ገፅ ፈቅደናል ግባበት ምንጭ - ካልታወቀ ገጣሚ Join the group @amharicbooksforeadersgroup አድሚኑን በ ቀጥታ ለማናገር ይህንን ቦት ተጠቀሙ @Digitallibraryofhashmal_bot

Show more
Advertising posts
3 961
Subscribers
-224 hours
+637 days
+32030 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
አኮ መኖዬ ስትታወስ --- አፈንዲ ሙተቂ ------ በኦሮሞ ህዝብ አፈ-ታሪክ በስፋት ከሚታወቁ ገጸ-ባህሪዎች መካከል ናት -አኮ መኖዬ፡፡ ወደ የትኛውም የኦሮሚያ ዞን ብትሄዱ እርሷን የማያውቃት ሰው አታገኙም፡፡ በዚያ ላይ የእያንዳንዱ ዞን ነዋሪ “አኮ መኖዬ የኛ አካባቢ ሰው ናት” ይላችኋል፡፡ ቦረና ብትሄዱ “አኮ መኖዬ የዚህ አካባቢ ገዥ ነበረች፤ የኖረችበትን ሰፈርና የሞተችበትን ስፍራ ላሳይህ እችላለሁ” የሚል ሰው ይገጥማችኋል፡፡ ሸዋ ብትሄዱም “አኮ መኖዬ እዚሁ ነበረች እኮ” ትባላላችሁ፡፡ ወደ ሀረርጌ ብትመጡ ደግሞ “አኮ መኖዬ በጨርጨር አውራጃ ለገ-ቤራ በሚባለው አካባቢ ነው የኖረችው” የሚል የረዥም ጊዜ አፈ-ታሪክ አለ፡፡ ከዚህ እንደምንረዳው አኮ መኖዬ የኦሮሞ ህዝብ እንደ አሁኑ ተስፋፍቶ በሀይማኖትና በዘዬ ከመለያየቱ በፊት የነበረች ጥንታዊ ሴት ናት፡፡ የቅርብ ዘመን ሰው ብትሆን ኖሮ ታሪኳ በሁሉም የኦሮሚያ ዞን ሊታወቅ ባልቻለ ነበር፡፡ --- ያቺ በትውፊት በስፋት የምትታወቀው አኮ መኖዬ ጨካኝ ንግሥት ነበረች፡፡ በጭካኔ እርምጃዋ ብዙ ሰዎችን ፈጅታለች፡፡ ታዲያ ሰዎችን የምትገድለው እንዲሁ ከመሬት ተነስታ አይደለም፡፡ በቅድሚያ የሀገሬው ነዋሪዎች በጭራሽ ሊተግብሯቸው የማይችሏቸው ነገሮች እንዲደረጉላት ትጠይቃለች፡፡ ፍላጎቷ እርሷ በጠየቀችው መንገድ ካልተፈጸመላት በአንድ ቀን መቶ ሰዎችን ትጨርስና ታስቀብራለች (አፈ-ታሪኩ ከቦታ ቦታ ይለያያል፤ “በአንድ ጊዜ መቶ ሰው ትገድላለች”፤ “አንድ ሰው ትገድላለች”፤ “አስር ሰው ትገድላለች” እየተባለ ይነገራል)፡፡ አኮ መኖዬ ከጠየቀቻቸው ጥያቄዎች አንዱ “ከብቶች እንዳይሰማሩ፤ ከቤትም እንዳይውሉ” የሚለው ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ጥያቄ እንዴት ነው የሚመለሰው?… እርሷም የምትፈልገው ይህንኑ ነውና በአንድ ቀን መቶ ሰው ጨፈጨፈች፡፡ በሌላ ቀን ደግሞ “መሬትም ያልነካ ሰማይ ላይም ያልወጣ፤ አየር ላይ የተንሳፈፈ ቤት ስሩልኝ” አለች አሉ፡፡ ጥያቄዋ መላሽ ቢያጣ መቶ ሰው በአንድ ላይ ረሸነች፡፡ እንደገና ደግሞ “የቅቤ ተራራ ስሩልኝ፤ ይህ ተራራ ከተሰራ በኋላ ሳይናድ መቆየት አለበት” በማለት አዘዘች፡፡ በሰፈሩ ውስጥ ያለው ቅቤ ተሰብስቦ መለስተኛ ተራራ በጧት ተሰራ፡፡ ነገር ግን ጸሐይ እየጠነከረች ስትሄድ የቅቤ ተራራው ቀልጦ ፈሰሰ፡፡ አኮ መኖዬም እንደለመደችው መቶውን ሰው ፈጀች፡፡ አኮ መኖዬ እንዲህ እንዲህ እያደረገች ህዝቡን ስትጨርስ ሰነበተች፡፡ በመጨረሻም ሲያቀብጣት “በአየር ላይ የሚበር ፈረስ አምጡልኝ” የሚል ትዕዛዝ አወጣች፡፡ በዚህን ጊዜ የሰው እልቂት ያስመረራቸው የሀገሩ “ሀዩዎች” (አዋቂዎች) ተመካከሩ፡፡ ሴትዮዋን የሚያስወግዱበትን ብልሃት ለመፈለግ መላ መቱ፡፡ የአኮ መኖዬን ገመና የተረዳ አንዱ ውስጠ አዋቂ “ይህች ንግሥት የሜዳ አህያ አይታ አታውቅም፤ ስለዚህ ለምን በርሱ ላይ አስቀምጠናት ከገደል ገብታ እንድትሞት አናደርግም?” በማለት ተናገረ፡፡ ሌሎቹ ተሰብሳቢዎች ሰውዬው ባመጣው ዘዴ ተስማሙ፡፡ የሜዳ አህያ ተፈልጎ እንዲመጣም አዳኞች ወደ “ዲዳ” (የሳር ሜዳ) ተላኩ፡፡ የሜዳ አህያው ተይዞ መጣና ለአኮ መኖዬ ቀረበላት፡፡ ታዲያ አዋቂዎቹ የሜዳ አህያውን ሲያቀርቡላት እንዲህ የሚል ቃል አክለው ነገሯት፡፡ “ይህ ፈረስ በአየር ላይ ለመብረር የሚችለው ፊቱ በጨርቅ ከተሸፈነ ብቻ ነው”፡፡ አኮ መኖዬም ከሰዎቹ የተነገራትን ስትሰማ የእውነት መሰላት፡፡ በሃሳቡ መስማማቷን ገለጸችና የሜዳ አህያው በጨርቅ ተሸፈነ፡፡ እርሷም ተፈናጥራ ከጀርባው ላይ ወጣች፡፡ የሜዳ አህያው ከእስር ሲለቀቅ እንደ ጀት በረረ፡፡ ዳሩ ምን ያደርጋል?.. የአኮ መኖዬን ሰማይ ላይ የመውጣት ህልም ሳያሳካላት ከገደል ውስጥ ገባ፡፡ እርሷም ሆነ አህያው በአንድ ላይ ተሰባብረው ሞቱ፡፡ በዚህም መንገድ በጭቆናዋ የታፈነው ህዝብ ከስቃዩ ተገላገለ፡፡ -- አፈንዲ ሙተቂ መስከረም 4/2007 ----- ማስታወሻዎች 1. እንደ አኮ መኖዬ ስመ ገናና የሆኑ ሴቶች በሌሎች ህዝቦች አፈ-ታሪክ ውስጥ ይታወቃሉ። በዚህ ረገድ በሲዳማ ህዝብ የምትወሳው "ፉራ" እና በጉራጌ አካባቢ ታሪኳ የሚነገረው "ውርድውት" ይጠቀሳሉ። 2. ስለ አኮ መኖዬ አሟሟት የሚነገረው ታሪክ ከቦታ ቦታ ይለያያል፡፡ በሀረርጌና በቦረና ግን አሟሟቷ ከላይ በተገለጸው መንገድ እንደተፈጸመ ነው የሚነገረው፡፡ 3. አንዳንድ ምሁራን “የአኮ መኖዬ ታሪክ ሴቶች ወደ ስልጣን እንዳይመጡ ለመከላከል የተፈጠረ ሳይሆን አይቀርም” የሚል ግምት አላቸው፡፡ ነገር ግን ግምቱ ትክክል አይመስለኝም፡፡ በኦሮሞም ሆነ በሌሎች ህዝቦች አፈ-ታሪክ በከፍተኛ ተምሳሌትነታቸው የሚወሱ የሴት ነገሥታት አሉ፡፡ በአንጻሩ ደግሞ በጭካኔያቸው የሚኮነኑ የወንድ መሪዎች ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህ ለትውፊቱ ሌላ ግምት ከመስጠት ይልቅ የሞራል ዋጋን ለማስተማር የተፈጠረ ተረት አድርጎ መቀበሉ የተሻለ ይመስለኛል፡፡ ---- Afendi Muteki September 15/2014
620Loading...
02
So ልጅቷን እኛ መስሪያ ቤት ነው የማውቃት (this kinda storytelling ከticktock ነው ያየኹት። grammatically wrong ነው አይደል ?ደግሞ አብዛኛዎቹ ብዙ view አላቸው...ምን ያህል ወረኛ ብንሆን ነው በእመቤቴ ! ስራ የለንም እንዴ? ) እና ወደ ወሬዬ ስመለስ ልጅቷ እኛ መስሪያ ቤት አዲስ ገቢ ናት።ከቢሮአችን ጎን ነው ቢርዋ...በውበቷ ብዙ ሰው ስለሚያሸረግድላት...በቅርጿ ሴቶችም ሳይቀሩ መነጋገሪያ ስላደረጓት...እጅግ ጣሪያ የነካ መኮፈስ...መንጠባረር...መመፃደቅ...ይስተዋልባታል። ...አንድ ቀን እኛ ቢሮ ለጉዳይ መጥታ ፈገግ ብላ ሰላም አለቺኝ...ከደማቅ ፈገግታ ጋር አፀፋውን መለስኹ። ...ከዛ ሌላ ጊዜ በመንገድ ስንገናኝ ሰላም መባባል የለብንም ? በሁለተኛው ቀን ፊት ለፊት ስንገናኝ ከመተላለፋችን በፊት ሰላም ልበላት አልበላት እያልኹ ሳመነታ "ሰላም ነህ ?" አለቺኝ በዛ ድምጿ...አፀፋዋን መለስኹ። ከዛ በቀጣዩ ቀናቶች ፊት ለፊት ስንገጣጠም አንዴ ሰላም ትለኛለች ሌላ ጊዜ ትዘጋኛለች ። ብቻዬን "ሰላም ነው?" እያልኹ አልፋለሁ። አሁን አሁን እሷን ሳይ መሳቀቅ ጀመርኹ ሰላም ልበላት ወይስ አልበላት? ቆይ ማነኝ ብላ ነው የምታስበው? የእርሷ ሰላምታ ቀኔን የሚያበራው ፤ ምሽቴን የሚያደምቀው መሰላት ? ምናባቷ ነው የምታወዛግበኝ ፤ ስንት ሰው ሳቀብኝ ብቻዬን " ሰላም ነው? " እያልኹ እያለፍኹ ! ሰላም ነው? ©ሶፊ
3730Loading...
03
እወዳታለሁ ❤ መውደዴ ሰላማዊ ነው። ጥርጣሬ የሚፈጥር ጨዋታ አታመጣም ። ከሰዎች ጋ ያላት ጨዋታ ሁኔታ፣ ትውውቅ ጨዋነት የተሞላበት ስለሆነ አይረብሸኝም ። እወዳታለሁ ፦ እንከኔን ስታይ እንዴት እንደምታስተካክለው እያሰበች ነው አሁን ማክሰኞ ለ'ት ወረቀት ኪሴ ውስጥ ሲዝረከረክ ተመልክታ ሌዘር ቆንጆ ዋሌት አመጣችልኝ ። የተበሳጨሁበትን ነገር ደግማ አታደርግብኝም ። እማትወደውን ነገር "ማርዬ እንዲ አታድርግ" ትለኛለች ለስለስ ያለ ሁኔታ ውስጥ ግግር አቋሟን አየዋለሁ ። በተጣላንበት በተጨቃጨቅንበት ጉዳይ በሌላ ቀን አንስተን አንንዘባዘብም ። ፍቅራችንን እና ፀባችንንም እወቁልን ስሙልን አንልም ። እሷን የሚያሳጣኝ ሁኔታ ውስጥ አልሳተፍም ። እንደምወዳት ነግርያታለሁ እንደምወዳት አሳይቻታለሁ ። እንደምቶደኝ ነግራኛለች እንደምቶደኝ አይቻለሁ ። መዋደድ ደስስ ይላል ❤ ©Adhanom Mitiku
5425Loading...
04
https://t.me/gamee?start=ref_314556431 Participate in mining events, play games, and spin the Fortune Wheel to WIN. Welcome gift included!
5142Loading...
05
ሎላሼ ዲጂታል መጽሔት ሎላሼ¶ {የንጋት ጸሀይ} . . . መኖርን በብርሀኗ ጅራፍ ቋጨን! በሶስት ሳምንት አንድ ግዜ ከሚደርሶ መጽሔታችን ጎን ለጎን፥ የእለት ሞሶባችንም ሙሉ ነው። ዛሬ ማታ ሁለት ሰአት ሎላሼ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ አንድ ቁጥር አንድን ይጠብቁ የፌስቡክ ገጻችንንም ይቀላቀሉ። ይህን ስላደረጉ እናመሰግኖታለን https://www.facebook.com/profile.php?id=61556306424311&mibextid=ZbWKwL
4870Loading...
06
እዉነት እንዳይመስልሽ . . ዛሬ ......ምን ብትደምቂ፤ ከቆነጃጅቱ እጅጉን ብትልቂ፤ ኑሮ ተመችቶሽ ያ.... ፊትሽ ቢወዛ፤ ወደድኩሽ የሚለዉ አፍቃሪሽ ቢበዛ ፤ ሴትነትሽ ማለት... መልክ ከመሰለሽ፤ ፍፁም አትመኪ እዉነት እንዳይመስልሽ፤ አንቺን ሳያማክር........ የጠቆረዉ ፀጉርሽ.. በሽበት ይተካል፤ ጸአዳዉም መልክሽ በፍጥነት ይረግፋል፤ ሴትነትሽ ማለት መልክ ከመሰለሽ፤ ፍፁም አትመኪ እዉነት እንዳይመስልሽ። .......................................... በዔደን ታደሰ
4984Loading...
07
ሁሉም ነገር ለበጎ ነው! አንድ ሃብታም ጎብኚ ወደ አንዲት ሃገር ከተጓዘ በኋላ ከከተማ ራቅ ወዳለ ስፍራ ለጉብኝት ሄደ፡፡ በዚያም አንድን እጅግ በጣም ደሃ የሆነ አስጎብኚ ቀጠረውና አካባቢውን እያሳየው ሲጓዙ ሳለ ጎብኚው አንድ ከዚህ በፊት አይቶት የማያውቀው አይነት ዛፍ ተመለከተ፡፡ በነገሩ ተገረመና ውስጡ ምን እንደሆነ ለማወቅ ለጉዞ የያዘውን አነስተኛ መጥረቢያ አንስቶ ዛፉን እቆርጣለሁ ብሎ ተሳስቶ ጣቱን ቆርጦ ጣለው፡፡ ይህ ባለጠጋ ጎብኚ በስቃይ ሲጮህ አስጎብኚው፣ “አይዞህ ሁሉም ለበጎ ነው” እያለ በመደጋገም ሲነግረው እጅግ ተበሳጨና አጠገባቸው የሚገኝ ጉድጓድ ውስጥ ገፍትሮ ጥሎት ሄደ፡፡ ይህ ጎብኚ ትንሽ ከተጓዘ በኋላ ጸጉረ ልውጥ ሰው ሲያገኙ ቀቅለው የሚበሉ ጎሳዎች አገኙት፡፡ የሚበላ ሰው በማግኘታቸው የተደሰቱት እነዚህ ሰዎች ጥፍር ካሰሩት በኋላ እንደልማዳቸው እሳታቸውን አንድደውና መቀቀያውን ጥደው በዙሪያው ከጨፈሩ በኋላ ጎብኚውን መቀቀያው ውስጥ ሊጨምሩት ሲሉ በድንገት የተቆረጠውን ጣቱን ተመለከቱ፡፡ በእምነታቸው መሰረት እንደዚህ አይነት ሰው መብላት ክልክል ስለሆነ ሃሳባቸውን ቀይረው እንዲሄድ ለቀቁት፡፡ ይህ ጎብኚ የነበረበት የፍርሀት መንቀጥቀጥ ረገብ ሲልለት መጀመሪያ ትዝ ያለው በንዴት ገደል ውስጥ ገፍቶ የጣለው አስጎብኚው ነበረና ሄዶ ጎትቶ በማውጣት ይቅርታን ጠየቀው፡፡ የአስጎብኚው መልስ አሁንም እንደተለመደው፣ “ችግር የለውም፣ ሁሉም ነገር ለበጎ ነው” የሚል ነበር፡፡ ጎብኚው ይህንን መልስ በድጋሚ በመስማቱ፣ ምን ለማለት እንደፈለገ ጠየቀው፡፡ የአስጎብኚው መልስ እንደዚህ የሚል ነበር፡- “አንዱ ጣትህ በመቆረጡ ምክንያት በእነዚህ ሰዎች ከመበላት ዳንክ ስለዚህ አንዱ ጣትህ መቆረጡ ጥሩ ልምምድ ባይሆንም የኋላ ኋላ ግን ለበጎ ሆነ፡፡ አንተ ደግሞ እኔን በንዴት ገደል ውስጥ መክተትህ ምንም ጥሩ ነገር ባይሆንም፣ ያንን በማድረግህ ምክንያት እዚሁ ባልቀርና አብሬህ ብጓዝ ኖሮ አንተን ትተው እኔን ይበሉኝ ነበረ፡፡ ይህም ለበጎ ሆነ”፡፡ ካጠፋ በኋላ የሚመለስና ይቅርታ የሚጠይቅ ማንነት ላለው ሰው ሁሉም ነገር ለበጎ ነው! ይቅርታ ሲጠየቅ መለስ ብሎ ይቅር የሚል ጨዋ ማንነት ላለው ሰው ሁሉም ነገር ለበጎ ነው! በሁሉም ነገር በፈጣሪው ላይ ያለውን እምነት ለማይተው ሰው ሁሉም ነገር ለበጎ ነው! በአሁኑ ወቅት የምታልፉበት አስቸጋሪ ሁኔታ ለበጎ እንዲለወጥላችሁ ጸሎቴና ምኞቴ ነው፡፡ ✍ ዶክተር እዮብ
6015Loading...
08
መልካም የናቶች ቀን ❤ 😥❤ አምስተኛ ክፍል ማጥናት፤ ትምህርት በደንብ መማር፣ መከታተል ጀመርኩ ። ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለተኛ ወጣሁ ደስስ አለኝ። ለእናቴ ስበር ሄጄ ነገርኳት : ሎተሪ እንደደረሰው ሰው ፊቷ ፈካ። ትክ ብላ አይታኝ፤ "ስጋሃ?" አለችኝ (እውነት! እንደማለት ነው ) "ስጋሂ" አልኳት። ግንባሬን፣ አንገቴን ሳመችኝ ። "ጎበዝ ዝወደይ: ከማኻስ ዓሰርተ ዘይምወለድኩ " ( እንዳንተ አስር ልጅ በወለድኩ) ብላ አገላብጣ ደግማ ሳመችኝ። "ወሊድካ ተሓጎስ" (በልጅህ ደስ ይበልህ) "ተመስገን : ተመስገን: ምን ይሳንሃል ጌታዬ " ብቻዋን ከጌታዋ ጋር አጉተምትማ ስታበቃ ፤ "ምን ልግዛህል" አለችኝ ? "ኮካ ኮላ እና ጮርናቄ " አልኩ ከጉያዋ መሃረብ አውጥታ ጭምትር ያለች አምስት ብር ሰጠችኝ :ገዝቼ መጣሁ። "ብላ አባ ዘወደይ" "አንቺ አትበይም?" "ጠግቤያለሁ፤ ደግሞ እኔ ለስላሳ አልወድም አበሩ ጋር ጠላ ጠጥቻለሁ። በሚቀጥለው ደግሞ አንደኛ ትወጣለህ አይደል? " አለችኝ። "እንደዚህ ደስስ የሚልሽ ከሆነ እ'ማ እወጣልሻለሁ ። " "መጣሁ : ቤቱን ጠብቅ" ብላ የሆኑ ከቀበሌ የመጡ የእርዳታ ድርጅቶች የገዙልንን ትልቅ ድስት ይዛ ወጣች: ብዙ ቆይታ መጣች ። ስትመጣ ብረት ድስቱን አልያዘችውም። በብረት ድስቱ ፈንታ ጥቁር ፌስታል ይዛለች። ጥቁሩ ፌስታል የያዘውን ስታወጣው አመድማ ሸራ ጫማ እና ጥልፍልፍ ነጭ ክፍት ዘለበታም የባሊያችንን ቀለም የመሰለ ጫማ ገዛችልኝ ። ደስታ ሊገለኝ ደረሰ። ጋዴ ማድረግ አቆምኩ :ጋዴ ጫማዬ ተጣለ ። ቆይቶ በጣም ቆይቶ ነው በእርዳታ የተሰጠንን ድስቷን ሸጣ ጫማ እንደገዛችልኝ ያወኩት ። የዚህች እናት ልጅ ሆኜ እንዴት መስነፍ ይቻለኛል ?! © Adhanom Mitiku
6974Loading...
09
https://t.me/gamee?start=ref_314556431
7860Loading...
10
እናታችሁን በሶስት ቃላት ግለፁ ብትባሉ እንዴት ትገልጿታላችሁ ? How would you describe your mother in three words?
8501Loading...
11
Media files
8581Loading...
12
ይህን challenge ለሌሎችም በማጋራት የተቻለን ን እናድርግ። 📌ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነው። በተለያዩ የሶሻል ሚዲያ አማራጮች ላይ ፖስት በማድረግ የኝህን እናት ህይወት እንታደግ።
8970Loading...
13
Media files
8120Loading...
14
በሰርጓ ቀን ያማረባት ብቸኛዋ ሴት ናት ለኔ ­-የአጎቴ ልጅ ሜሪ። እንደሌሎቹ የሜካፕ ናዳ ፊቷ ላይ አዝንባ፤ አዲስ መልክ ይዛ አልመጣችም፤ ያው...እግዜር አንዴ ተጠብቦ ተጨንቆ ሰርቷት የለ? ከዚ ወዲያ የሜካፕ ባለሞያዎች ከማበላሸት በቀር ምን ይጨምራሉ?- ምንም። ንጥት ያለው ቬሎዋ መሬት ላይ፤ የተፈጥሮ ፀጉሯ ደሞ ጀርባዋ ላይ ተንፏሏል፤ ውብ ገጿ ላይም አንዳች ሚያክል ደስታ ድሩን ሰርቷል። ሁሌም ደስተኛ ነች የምትባል ሴት ብትሆንም፤ የዛሬው ግን የተለየ ነው፤ የደበዘዘ ሮዝ ቀለም የተቀባውን ከንፈሯን ከፈት እያደረገች፤ሀፍረት የቀላቀለ ፈገግታ ትጋብዘናለች። ፀጉሯ ላይ የሚያንፀባርቅ ነገር ይታያል፤ አክሊል ካናቴራ ነው፤ ሄዶባታል አጥገልፀውም ምክንያቱም... የምር ንግስት የሚያስመስል ግርማ ሞገስ አላት። በቀኝ እጅዋ እንደሷ የፈኩ ነጫጭ አበቦችን፤በግራ እጅዋ ደሞ የመጪው ባሏን ክንድ ቆልፋ ይዛለች፤ በኤሊ እርምጃ ወደ አዳራሹ በማዝገም ላይ ናቸው፤ ብዙዎች ከሁዋላ ሀይሎጋ እየጨፈሩ ያጅቧቸዋል። እኔ እና አጎቴ(የሙሽራዋ  አባት) አዳራሹ መግቢያ ላይ ተሰይመናል፤ በትንሹ እያጨበጨብን፤ በፍቅር አይን ሙሽሮቹን እናያቸዋለን። ሁለታችንም ተመሳሳይ ሱፍ ነው የለበስነው፤ እንደወጣትነቴም፤ እንደ ቁመና ባለቤትነቴም፤ እኔ ላይ ይበልጥ ሳያምርብኝ አይቀርም። በቃ ተውኩት፤ 'ስለ ራስ አይወራም!' ያለኝ ማን ነበር?...ብቻ ማንም ይሁን ማን ልክ ሳይሆን አይቀርም። በአሁኑ ሰአት ግን ሙሽሮቹን ማጀብ ሲገባኝ፤ እዚ ፈዝዤ የቆምኩበት ምክንያት አልገባኝም፤ በርግጥ ሜሪ ቀድማኝ በማግባቷ ትንሽ ደብሮኝ ነበር፤ «አትቀድመኝም!» «አትቀድሚኝም!» የሚል የፌዝ ውርርድ ስለነበረን፤ በመሸነፌ ትንሽ ቅር ብሎኛል። ግን የሷ ደስታ ደስታዬ አይደለም እንዴ?...ይሄን ያክል ፋራ ሆኛለሁ?...ሳምንቱን ሙሉ ጠብ እርገፍ ስል የነበር፤ ዛሬ እንዲ ለመሆን ነው? ራሴን ተቆጣሁት፤ደሞስ የሷ ሰርግ ያልጨፈርኩ የማን ልጨፍር ነው? ከሰመመኑ እንደ ነቃ ሰው ደንገጥ አልኩና ፤ወደ አጃቢዋች ሄጄ ተቀላቀልኩኣቸው። ሜሪ አስተውላኝ ነበር፤ ዲምፕሎቿን አስከትላ  ፈገግ አለችልኝ። ደስ ስላላት፤ ደስ አለኝ። ድምፄን አጠብድዬ እኔ እመራቸው ጀመር፤ የጭፈራውውን ዙር አከረርኩት...። * * * ልጅ እያለሁ ነው ፤ ወደ አስራዎቹ መግቢያ ላይ። ከእናቴጋ ለመጀመሪያ ጊዜ መነሀሪያ ሄድኩ፤ ተገድጄ ነው እንጂ፤ የመምጣቱ ፍላጎት አልነበረኝም። ቆይቶ ግን አብዛኛውን የማየው ነገር አዲስ ስለሆነብኝ፤በሆድ ማማረሬን አቆምኩ። ገና ከመግባታችን አንድ ሱቅ በደረቴ አዟሪ ልጅ መጥቶ እናቴን ይለማመጣት ጀመር፤ «እናት ሶፍት ይፈልጋሉ?..ማስቲካም አለ ጦር..ባናና..» ምንም እንደማትፈልግ ከይቅርታ ጋር ነግራው፤ መቀመጫ ወዳለበት ሄደን ተቀመጥን። ሲመስለኝ የምንቀበለው ሰውዬ ገና አልደረሰም። ከጥቂት ደቂቃዎች በሁዋላ፤ እናቴ ሁለት ባሶች ተከታትለው መግባታቸውን አስተውላ፤ ባለሁበት እንድጠብቃት አስጠንቅቃኝ ሄደች። የግቢው(የመነሃሪያው) ስፋትና የመኪኖቹ ብዛት አስገርሞኝ፤ አይኔን ወዲያና ወዲ እያቅበዘበዝኩ ትንሽ እንደቆየሁ፤ ውሃ ሰማያዊ ቀሚስ ያደረገች ሴት ወደ እኔ አቅጣጫ ስትመጣ ተመለከትኩ። ይሄኔ ነው እንግዲህ ጉዴ የሚጀምር። እድሜዋ ከኔ ጋ ተመጣጣኝ ይሆናል፤ አልያ ደሞ በትንሽ ትበልጠኛለች። ከሩቅ እንዳየኋት ቆንጆ መስላኝ ነበር፤ እየቀረበች ስትመጣ ግን እጅግ በጣም ቆንጆ ሆነችብኝ። ከላይ እስከ ታች ባይኔ አላመጥኩኣት፤ ስጋ እንዳየ ውሻ ምላሴን አውጥቼ ለሀጬን ማዝረክረክ ነው የቀረኝ። አፌን እንደከፈትኩ እርምጃዋን ስቆጥር ከአይኗጋ ገጠምኩኝ፤ በጣም ማፍጠጤ ታወቀኝና አይኔን ሰበርኩ፤ ዝቅ አልኩ። ወዲያው የየሆነ ሰው ጥላ እየቀረበኝ መጥቶ ካጠገቤ ሲቀመጥ ተሰማኝ። እሷ መሆኗን ላረጋግጥ ቀና ስል፤ በድጋሚ ካይኖቿጋ ተጋጨሁ፤ እዛው ስብር። ሆ! በምን ሃቅሜ፤ ልቋቋማቸው? ልቤ በፍጥነት እየመታ ነው፤ ሰውነቴም በላብ ተጠምቋል፤ ወደሷ መዞር አቃተኝ፤ የተሸከምኩኣት ያክል ከብዳኛለች። በእርግጥ በጣም የተቀራረብን መስሎ ተሰማኝ እንጂ በመሀከላችን ያለው ርቀት አምስት ሰው ያስቀምጥ ነበር። ከትንሽ መንቀጥቀጦች በኋላ አላስችለኝ ሲል፤ እንደምንም ሰረቅ አድርጌ አየሁአት፤ 'ተመስገን'! አልኩ ከአይኖቿ ጋ ስላልተጋጨሁ መሆኑ ነው ሂሂሂ!!። እንደዚህ አይቼ የደነገጥኩላቸው ሴቶች ጥቂት ነበሩ፤ ግን አንዳቸውንም አውርቼአቸው አላውቅም። ይህቺን ልዕልት መሳይ ግን ዝም ብሎ ያልፋት ዘንድ ልቤ አልቻለም፤ ውስጤ 'አናግራት!..አናግራት!' በሚል የድምፅ ማእበል ተናወጠ። እሷን የማናገር ፍላጎቴ ናረብኝ፤ ከዚህ የፍርሀት አዘቅት ወጥቼ እንዴት እንደማወራት ግራ ቢገባኝም፤ ውሳኔ ላይ ደረስኩ። ቀረብ ብዬ ልተዋወቃት፤ የተሰማኝን ሙሉውን ባልነግራትም፤ የመጣልኝን ብዬ ከበኋላ የህሊና ፀፀቴ ለመዳን ወሰንኩ። ራሴን በራሴ motivate ማድረግ ጀመርኩ፤ እንደሚችል ነገርኩት፤ ተቀበለኝ (ማለቴ ተቀበልኩት)። መመለሷን ስጠብቅ የነበረውን እናቴን ከነ እንግዳው በዛው እንዲቀሩ እየተመኘሁ ፤እግሬን አዘጋጀሁ፤ ጉሮሮዬን ጠረኩ፤ ልብሴን አስተካከልኩ በስተመጨረሻ ብድግ ስል፤ እናቴ ሻንጣ እየጎተተች ካንድ ሰውዬጋ ወደ እኔ ስትመጣ አየኋት። በእውነቱ ያን ጊዜ የተሰማኝን የመንፈስ ስብራት ልገልፅላችሁ አልችልም። ክው ነው ያልኩት፤ እዛው በቆምኩበት ክርር፤ ድርቅ፤ ዝም፤ ምንም። እንባዬን እየታገልኩ መለስኩት፤ ዋጥ!። ደረሱ። እናቴ አጎትህ ነው ብላኝ ከሰውየውጋ አስተቃቀፈችኝ። ሰላም ብዬው አብቅቼ ዞር ስል፤ « አልተዋወቃችሁም እንዴ? » እናቴ ነበረች። « ከማንጋ? » መቼም አጎትየውን እንደማይሆን አውቄ ጠየኳት። « ከ ሷ'ጋ ነዋ! » ጎኔ ተቀምጣ ስታስጨልለኝ ወደነበረችው እንስት በግንጭሏ እየጠቆመች። ይሄኔ ነበር ከቅድሙ በበለጠ በላብ የተዘፈቅሁት። ጉልበቴ ይርበተበት፤ ሰውነቴ ይንቀጠቀጥ ጀመር፤ እንዴት የልቤን አወቀችብኝ? ግራ ግብት አለኝ። የምለው ባጣ፤ አናቴን በአሉታ ግራ ቀኝ ወዘወዝኩላት «በፍፁም!» እንደማለት። ወዲያው ልጅቱን እጅዋን ይዛ አስነሳቻትና.. « እስከዛ ተዋወቂው ብለን ነበርኮ ወዳንተ የላክናት... ለማንኛውም ያጎትህ የሙሌ ልጁ ነች...በሉ ሰላም ተባባሉ » ፈዘዝኩ፤ ህልም ህልም መሰለኝ፤ ስሜቴ ድብልቅልቅ አለ፤ ልደሰት ወይስ ልዘን? እጇን ዘረጋችልኝ፤ ከበድን አካሌ በድን እጄን ልኬ ጨበጥኩዋት፤ እጇ ይለሰልሳል፤ « ሜሪ እባላለሁ! » ፈገግ ብላ ስሟን አከለችልኝ፤ ፈገግ ስትል ጉንጮቿ ሰርጎድ አሉ። ደስ የምትል ልጅ ደስ የሚል ስም አላት። እኔ ግን ስሜን የምናገርበት አቅም አጣሁ፤ ምላሴ ተሳስሯል፤ አንደበቴ ተዘግቷል፤ ዝም አልኩኝ ፤ ዝም። ምናልባት ብዬ ከህልሜ እስኪያባንነኝ፤ ሳምንታትን ጠበቅሁ...ልነቃ ግን አልቻልኩም...እውን ነበር። ∝ By BINIAM EJIGU
1 0834Loading...
15
"ሴቶች በምንም አይማልሉም አትድከሙ!" (አሌክስ አብርሃም) በነገራችን ላይ እንደምታስቡት ሴት"መጀንጀን" ላይ አሪፍ አይደለሁም! ስለመጨረሻ ጅንጀናየ ላውጋችሁ! የሆነ ጊዜ አምስት መንገዶች አስር ማሳለጫዎች ምናምን የሚል የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ሴት ልጅ በራሱ የሚተማመን ወንዳወንድ ወንድ ትወዳለች የሚል ነገር ሰማሁ! እና አንዲት በዛ ሰሞን የወደድኳትን ልጅ ማማለል ፈለኩ! ተቀጣጥረን ተገናኘን ምሳ አብረን በላን (በድሮሮሮሮሮሮሮ ጊዜ የዛሬ ስድስት ዓመት ሰዎች ምሳ ይገባበዙ ነበር) እና ከመሬት ተነስቸ ጀብዱ ነገር ማውራት ጀመርኩ! "ይገርምሻል የሆነ ጊዜ አንድ ዳይኖሰር የሚያክል በሬ ከቄራ አመለጠ ፤ እና ከቄራ ቡልጋሪያ ድረስ ሰባት ወንዶች ሶስት ሴቶች ሁለት መኪና በቀንዱ እየወጋ አተረማመሰው! ፖሊስ ሁሉ ማስቆም አልቻለም! እና እኔ ስደርስ ወደሆኑ አሮጊት ቀንዱን አሹሎ እየሮጠ ነበር ... በባልቴቷና በበሬው መካከል ሶስት የበሬ እርምጃ ሲቀር ተፈትልኬ ሮጥኩና መሀላቸው ገብቸ ስቆም ጫማየ እንደመኪና ጎማ ፉጭጭጭጭጭጭ አለ! በሬው ደንግጦ ቆመና ተፋጠን እንደቆምን በቀስታ ቀረብኩት .... በእግሩ አስፋልቱን እየቆፈረ ሊወጋኝ ሲሞክር ሸወድኩትና አንገቱ ላይ የታሰረውን ገመድ ቀጨም አድርጌ ለባለቤቱ አስረከብኩ! ይገርምሻል በተፈጥሮየ አልፈራም! ልጅቱ ስትሰማኝ ቆየችና የበሬውን ነገር እንዳልሰማ ሰው " ዳይኖሰር ስትል አስታወስከኝ! ለምን ዛሬ ኤድናሞል ሙቪ አናይም? አሪፍ የዳይኖሰር ሙቪ አላቸው" ብላ በሚያማምሩ አይኖቿ አየችኝ! ጀብዱየን ውሃ ቸለሰችበት! ቅር እንዳለኝ ወደኤድናሞል የሚወስደን ታክሲ ስንጠብቅ አስገራሚ ነገር ተፈጠረ .... በሬ! የፈረጠጠ በሬ መንገዱን እያመሰው ከፊት ለፊታችን መጣ ... በእርግጥ ነፍሴን ለማትረፍ ባደረኩት ሩጫ ከበሬው የበለጠ ብዙ ሰው እየገፋሁ ሳልጥል አልቀረሁም! ልጅቱ ጋር በተፈጠረው ግር ግር እንደተጠፋፋን ከዛ በኋላ አልተገናኘንም! በእርግጥ ትዝ ያለችኝም የሆነ ካፌ ገብቸ ሁለት ሊትሩን ውሃ ከጠጣሁ በኋላ ነው!
1 18212Loading...
16
ማህተብ ፈቶ ቀለበት ማሰር የለም! 'አጅሬ' የምለው...'ጊዜዬ' የሚለኝ አንድ ጌታን የተቀበለ የከንፈር ወዳጅ ነበረኝ።አብሮነታችን ዕድሜ ላይኖረው...ማህተቤን ላልፈታ...ማህተብ ላያስር ነገር...ከማይካደው እውነታ በላይ ብዙ ነገሩ ገዝቶኝ አብሬው መጓዝ ጀመርኩ።ተገኝቼ 'ማላውቅበት ቦታ ከሱ ጋር ተገኘሁ...ስጋ እየፆምኩ ስጋ የበላ እሱን ለመሳም አልግደረደርም ነበር።አንገቱ እስኪዥጎረጎር መጥጬው 'ከጠየቁህ ጊዜ ናት በል' ስል ግዳይ የጣልኩ ይመስለኝ ነበር።ያውም በሁዳዴ...ያውም በአቢዩ! ያወቅሁትኝ ሰሞን የሴት ግሳንግሴን ገፍፌ ጥዬ...እኔው ደዋይ...እኔው መልዕክት ላኪ...እኔው አጥብቆ ጠያቂ እየሆንኩ በእናትነት እና በሚስትነት መሃል የሚቀላውጥ ማንነቴን ጋትኩት።ሰከረ...ስካሩ ዕድሜ ገዛ። በሱ ካስተናገድኳቸው እብደቶቼ ሁሉ የማልረሳው የlipstickኬን ነገር ነው።አንድ ዕለት አክስቴን ልጎበኝ በሄድኩበት lipstickኬ ማለቁ ትዝ ብሎኝ የአክስቴን ልጅ ግዥልኝ ብዬ መላክ...ዘምናኒት ጁስ ጁስ የሚል lipstick ገዝታ መምጣት...ልቀባው ወደ አፌ ሳስጠጋው የጠረኑ ማማር...ተቀብቼ ስቀምሰው የጣዕሙ ነገር...ቴዲ "ሳሙኝ ሳሙኝ የሚል ከንፈር..."ያለው አምለሰት ይኸን መሳይ ተቀብታ ብትጠጋው ነው ብዬ እንድደመድም አደረገኝ። 'ቴዲ አንጋጦ ባየው ከንፈር እንዲህ አጉል ከሆነ አጅሬ ቁልቁል አይቶኝማ እንደምን አይስት!'የሚል ሔዋናዊ ሀሳብ ብልጭ አለብኝና ያንን እንጆሪ እንጆሪ የሚል lipstick አልጋዬ ላይ አስቀምጬ ኩሽና ገባሁ።ከኩሽና ስመለስ እማይበጃችሁ ይድረቅና ድርርርርርቅ ብዬ ቀረሁ...አንድ ከየት እንደመጣ የማላውቀው(በኋላ ሳጣራ የአክስቴ ሰራተኛ ልጅ) በግምት 3 አመት የሚሆነው ህፃን lipstickኬን ይዞ ይመጠምጣል።በድንጋጤ ነጥቄ ስመለከተው እንኳን የሚቀባ የሚታይ የለውም።ህፃኑን አየሁት...የጠባውን ያጣጥማል...'ደሜ ፈላ' ብል ደሜ ራሱ ይታዘበኛል...ተንተከተከ...ተፈናጥሮ ሰው እስኪጠብስ! የሆነ ስላችሁ የጨረሳችሁት ሁነት...በምናባችሁ እንዳማረ ተጀምሮ እንዳማረ የሚጠናቀቅ ሁነት...ሊሆን እንደማይችል ስታውቁት ልባችሁ ይወርድ የለ?እኔ ሁለመናዬ ነው የወረደው...ከእንጥሌ ጀምሮ... ልጁን በልቤ ረገምኩት... 'ከንፈርክን ስማ 'እንደ ወንድሜ ነው 'ማይህ ' ትበልህ'...'አልጋ አስይዛ ፔሬድ ላይ ነኝ ትበልህ!'... 'ፔሬዱ ሲሄድ 'ትንሽ ነው' ትበልህ' ብዬው ሳበቃ "ቤቢ አሜን በል" አልኩት። "አሜን"...ኤታባቱ! እናም እኔ ወለተ ማርያም...የአብማይቱ ማርያም ልጅ...የማርቆሷ ሎጋ...ጠላታችሁን የሎስ ያክንፈውና አስተካክሎ 'ነገ' እንኳን ማለት ከማይችል ደቡቤ ጋር ከነፍኩ።ዘረኛ ነበርኩ...እልልልም ያልኩ ዘረኛ!ወንድ ጎጃሜ ካልሆነ ወንድ የማይመስለኝ!'ሲያናድደኝ የምሰድበው ስድብ እንኳን ካልገባው ምን ላደርገው ነው?' ብዬ የምራቀቂቱ... ''መቼ ይመችሃል?'' ስለው "ነጌ" "እንዴት አርገህ አበጃጀኸው?" ስለው "እንደዚህ እንደዚህ 'አርግቼ' " "እኔ ኦርቶዶክስ...አንተ ጴንጤ...በምን ስሌት አብረን እንሁን?"ስለው " 'እምነት...ተስፋ...ፍቅር እነዚህ ሶስቱ ፀንተው ይኖራሉ፤ከሁሉም ግን ፍቅር ይበልጣል' ነው መፅሐፍ ቅዱስ 'የምለው' " ከሚለኝ አንድ ተላሰስ ጋር...ወደቅሁ። መላመዳችን ሲበረታ...ቅርርባችን ልክ ሲያጣ ጥያቄዎቻችንን ሽሽት ገባን።መሄድ ብቻ!እስከሆነ ቀይ መስመር ድረስ...በድፍረት ጥያቄዎቻችንን ስር ድረስ የማንጠያየቀው የማይቀረውን መለያየት ያራቅን መስሎን ነበር።ጠንካራ አማኝም ባልሆን ፈሪ ነኝ...ነፍስ አባቴ ዘንድ ስከንፍ ሄጄ 'መናፍቅ ወድጄ ልቤ ጠፋ' አልኳቸው። "ወለቴ" "ኧይ አባ" "እምን ድረስ ቀረብሽው?" "ሲሉኝ?" "ተመተቃቀፍ አለፋችሁ?" ሲሉኝ መሽኮርመም "ወለቴ...አደራሽን አረከሰኝ እንዳትይኝ" "ይፍቱኝ አባ" "አዪዪዪዪዪ....አይ ወለቴ...ምነው?ህጉን ስታውቂው?" አሉኝ...የምፈታበት መፅሐፍ ተነበበ...ለሶስት ተከታታይ ቀናት ጠመቁኝ። ህጉ 'ከአህዛብ አትጠጉ' ይላል...እንኳን አንሶላ መጋፈፍ...ማዕድ መካፈልን ያወግዛል...ግን ከህግ በላይ የሚገዛ፣ከውግዘት በላይ የሚያስር መሳሳብ ሲመጣስ?ምኔንም መሰሰት እስካልችል ከተሸነፍኩስ?አጅሬ አንዴ የሆነ መጣጥፍ ሲያነብልኝ "ሰው ከፍቅር የሚቆራረጠው ሰጥቶ መቀበልን ሲሻ ነው...የፍቅር ምክንያቱም ውጤቱም መስጠት ነው...ስለፍቅር የሚደረጉ ዝቅታዎች ሁሉ ከየትኛውም ከፍታ ይልቃሉ...ፍቅር ውስጥ መቀበልን የሚሻ እሱ ቀሽም ነው..." ብሎኝ ነበር።ያለስስት ስለሰጠሁት ሁሉ ደስተኛ ነኝ...አይደፈርን ደፍሬ፣አይተላለፉትን ተላልፌም...ይናፍቀኛል። በስተ መጨረሻ...ተመርቆ ከጊቢ ሊወጣ ሳምንት ሲቀረው "ተጠመቅና ከመሄድህ በፊት እንጋባ" ብዬ እስከምመረቅ ያሉትን ሶስት አመታት በዕምነት ልጠብቀው መዘጋጀቴን ነገርኩት...'ያዲያቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም' እንዲሉ "አንቺ ወደኔ እንዳትመጪ ምንድነው 'ሚያግድሽ? ቤተሰብ ነው?''አለኝ።እርግጥ ነው ቤተሰቦቼ የሚያማልደውን እየሱስ እየመገቡ አላሳደጉኝም...ከነሱ በላይ ግን...ነጌ ምጤ ሲመጣ ማን ሊያዋልደኝ?ማን ጭንቄን ሊያረግብ?የሱ ቀበቶ በቂ አልነበረምና ልቤን ዳር እስከዳር እየከረሰሰኝ...ዘለዓለም የሚመስል ፅልመት እየወረሰኝ...ሸኘሁት...ማህተብ ፈቶ ቀለበት ማሰር የለም። ዘማርቆስ 29/08/16
1 17911Loading...
17
⭕#Tapswap ከ #Notcoin ቀድሞ List ሊደረግ ነው እናም 23 ቀን አላችሁ ያልጀመራችሁ ዛሬውኑ ጀምሩ👇🏻👇🏻 https://t.me/tapswap_mirror_bot?start=r_314556431
1 0781Loading...
18
ባለፈው ከስራ እንደወጣው እቃ ልገዛ ወደ ፒያሳ ጎራ አልኹ...የምፈልገው ቤት ጋር ስደርስ ቆምኹ...ቤቱ የለም ፤ በቤቱ ፋንታ ፍርስራሽ ጠበቀኝ ፤ የአድራሻ ለውጥ ማድረጋቸውን የሚገልፅ ፅሁፍ ተንጠልጥሏል። በራሴ ተበሳጨው "ፒያሳ ፈርሷል" እያሉኝ ለማረጋገጥ ይሁን ለምን እንደመጣው አልውቅም ። ካላየው ስለማላምን ይሆን ? አረፍ የሚባልበት ካፌ እንኳ አላስቀሩም ። ፒያሳ ማረፊያ ቦታ የላትም ፤ ደግሞም ያለረፍት እየተቆፈረች ነው...ልሂድ ቢሉም አይቻልም። መጓጓዣም ሆነ መንገድ የለም ። ...ወደ ቤቴ መሄድ ፈለግኹ...ሰማዩ ጠቁሯል። ዝናቡ መጣው እያለ እየፎከረ ነው። አማራጭ ስላልነበረኝ ከፒያሳ ወደ አራት ኪሎ በእግሬ ተያያዝኹት ። ደክሞኛል...መሄድ ሳይሆን ጥቅልል ብሎ መተኛት ነበር ያማረኝ ።ሄድኹ ፤ ብዙ ስሄድ ተበሳጨው፤ስበሳጭ... ይሄን መንገድ ለመስራት ሃሳብ ያመጣውን ሰው ረገምኹ። ሃሳቡን ተቀብሎ መቆፈር የጀመረውን ሰው ረገምኹ...ሀገሬንም ረገምሁ፣ የተወለድኹበትንም ቀን ረገምኹት። ...አራት ኪሎ ጋር ስደርስ እዛም ታክሲ የለም...ባሶቹ ከመሙላት አልፈው ሰው እያንጠባጠቡ ያልፋሉ...ባስ አይሞከርም። ሜትር ታክሲ በስልኬ ጠርቼ ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጁ አካባቢ ከወዲያ ወዲህ እያልኹ ጠበቅኹ።የመጣም፤የደወለም የለም። እየፎከረ የነበረው ዝናብ በጥቂት በጥቂቱ ማንጠባጠብ ዠምሯል ። ሰው'ው ይተራመሳል። ከግራ ከቀኝ መንገዱ በዶዘር ይታረሳል። የእግረኛውም የመኪናውም መንገድ አንድ ላይ ነው ። የረባ ጃኬት አለበስኹም...በርዶኛል...ደክሞኛል...ግን አማራጭ ስለሌለኝ በእግሬ መሄድ ዠመርኹ...ካፊያው ቀስ ብሎ ወደ ዶፍ ዝናብ ተለወጠ...መንገድ ዳር የነበሩት ቤቶች፣ካፌዎች፣የንግድ ሱቆች ለኮሪደር ልማት ፈርሷል...ከፒያሳ-መገናኛ እየተቆፈረ ነው...በዶፍ ዝናብ ውስጥ እየተራገምኹ መረማመዴን ተያያዝሁት...የለስኹት ሸራ ጫማ የቻለውን ያህል ውሃ አስገብቷል ።(መብራት ነው የቀረው)...ያልበሰበሰ የሰውነት ክፍል የለኝም። ...ስልኬ ጮኽ በረጠበው እጄ፤ስልኬን ዝናብ እንዳይነካው አጎንብሼ ስሙን አነበብኹት እና ክው ብዬ ደነገጥኹ ! ክው አድርጎ ያስደነገጠኝ የደዋዩ ማንነት ሳይሆን Data እስካሁን አለማጥፋቴን ሳይ ነው። የተደወለው በቴሌግራም ነዉ ። Clare ናት የደወለቺው ። Clare አሜሪካዊት ናት። አንድ አሜሪካ የሚገኝ ጓደኛዬን አዲስ አበባ ኑሮ እጅግ እንደተወደደ በደወለልኝ ቁጥር ስለምነግረው ፤ ብር መላኩ ሲሰለቸው አንድ ስራ አገኘልኝ። ስራው ማዳመጥ ነው።አሁን የኔ ጆሮ የውጪ ምንዛሬ እንደሚያመጣ ማን ሰው ያምናል? Clare የ28 አመት ጎልማሳ ናት ፤ ጎልማሳ ያሰኛት እድሜዋ ሳይሆን ነገረ ስራዋ ነው። አረ እንደውም አዛውት ናት። ገና ህይወትን በቅጡ ሳታጣጥመው መኖር የደከማት ናት። በወጣት ጉልበቷ አልሮጠችበትም ፤ ቁጭ ብላ ታማርርበታለች። የትም መሄድ አትፈልግም...ሁሉንም ያየች ይመስል ሁሉም ነገር አስጠልቷታል ። ትገርመኛለች ሰው ሁሉም ነገር ተመቻችቶለት እንዴት ያማራል ? የምትኖርበት ቅንጡ አፓርታማ፣የምትነዳው መኪና፣የምትሰራው ስራ፣ስኬቷ ሰላምን አላመጣላትም ።የምትፈልገው ነገር ግራ ገብቷት ፤ የምትፈልገውን እየፈለገች ነው። ጓደኛዬ ሲያስቀጥረኝ ስራው የሚጠይቀው መስፈርት "A good listener" መሆን ነው። ገርሞኝ ነበር እዛ ሀገር የሚያዳምጥ የለም ማለት ነው ? አንድም ደስ ብሎኝ ነበር ። ስራ በዶላር በመቀጠሬ...Clare ታወራለች ያለማቋረጥ...የምትደውልልኝ ድባቴ ውስጥ ስትገባ ነው...ከምታወራኝ አብዛኛው ምሬት ነው። በቤተሰቧ ፣ በጓደኞቿ የደረሰባት በደል (አንዳንዴ እኔ ምናገባኝ ! ልላት አስብና መክፈሏ ትዝ ሲለኝ ዝም እላለሁ። ለካ እርቦኝ ጆሮዬን ሸጨዋለሁ ።) ድባቴ ውስጥ ስትገባ Clare ታወራለች ! እየጠጣች... ! አንዳንዴ በ Video ነው የምታወራኝ ። ቅንጡ ሶፋ ላይ በድብርት ተኮራምታ ስለልጅነቷ ታወራለች...የዛኔ ጆሮዬን ብቻ አይደለም...ፊቴንም ትገዛዋለች፤በምትነግረኝ ነገር ያዘንኹ ለመምሰል እየጣርኹ ...የረገበ አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ እሰማታለሁ። Clare አንድ እለት ቆንጆ ስልክ ላከቺልኝ።ከዛም በቪዲዮ ኮል ደውላ ቤቴን በጥራት ብታየው ጊዜ ልቧ በሐዘን ተነካ። ልታወራኝ የነበረውን ነገር ርግፍ አድርጋ ትታ..."i want you to tell me about yourself...your child hood...." በተሰባበረ ኢንጊሊዘኛ አወራት ዠመር። የዛኔ ይመስለኛል ኢንግሊዘኛዬን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማችው ።የዛኔ ይመስለኛል ያወራችውን ልሰማት እንደማልችል የጠረጠረችው...። ለClare አላነሳሁላትም ጠርቶ ሲጨርስ ዳታዬን አጠፋኹ። ከአራት ኪሎ፣ግንፍሌ፣ቀበና እንዳለፍኹ ወደቤቴ የሚወስደውን ቅያስ ያዝኹ።ቤቴ ስገባ ።መብራት ጠፍቷል።ውሀም የለም።እራትም አልሰራሁም።እጅግ ተበሳጭቼ።ልብሴን ቀያይሬ ጋደም አልኹና ዳታዬን አበራኹ።Clare ደወለች። Clare: What's wrong Sofi...i have been calling you the whole day...? Sofi: Come on Clare anything could happen,i live in Ethiopia...no electricity...no water...no food ልላት አሰብኹና የሀገሬን ገፅታ እንዳላጎድፍ ብዬ "I was at work the whole day" አልኋት።በባዶ ሆዴ ምሬቷን እንዳልሰማ እየተመኘው ጆሮዬን አዋስኋት። "ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው።" የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ©ሶፊ
1 2183Loading...
19
ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ የክብር የእንግዳ የሆነበት አንጋፋው የኪነጥበብ ምሽት ረቡዕ ይካሄዳል! በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነጥበብ መርሃግብር ረቡዕ ሚያዝያ 30 2016 ዓ.ም ይካሄዳል። በዕለቱ ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ "የአንድ ግጥም፣ የአንድ ወግ" የክብር እንግዳ ሆኖ  ይገኛል። እንዲሁም ግጥሞች፣ ወግ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ብለዋል አዘጋጆቹ ። ማስታወሻ :— ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው ። ✍Event Adiss
9751Loading...
20
ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ የክብር የእንግዳ የሆነበት አንጋፋው የኪነጥበብ ምሽት ረቡዕ ይካሄዳል! በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነጥበብ መርሃግብር ረቡዕ ሚያዝያ 30 2016 ዓ.ም ይካሄዳል። በዕለቱ ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ "የአንድ ግጥም፣ የአንድ ወግ" የክብር እንግዳ ሆኖ  ይገኛል። እንዲሁም ግጥሞች፣ ወግ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ብለዋል አዘጋጆቹ ። ማስታወሻ :— ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው ። ሼር ሼር ሼር ! ✍ event adiss
30Loading...
21
#አዛም_ጥናት በጂም ውስጥ ማልቀስ ለአእምሮ ጤንነት ጠቃሚ ነው እንደ ባለሙያዎች ገለጻ ከሆነ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወቅት ማልቀስ ጭንቀትን ለማስወገድ ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጋር በጥሩ ሁኔታ የሚሰሩትን ኢንዶርፊን እና ኦክሲቶሲንን በመልቀቅ ጭንቀትን ለመቋቋም ይረዳል።😂 ©new york post
1 1292Loading...
22
Invite your friends and get bonuses for each invited friend! 🎁 Your referral link:
10Loading...
23
https://t.me/getcapybot/now?startapp=MzE0NTU2NDMxfGViODA3OWY1LTdlY2QtNGZjNy1hMjg3LWU4OGZjZTFhZjRiNg==
1 1540Loading...
24
Media files
1 2871Loading...
25
Media files
1 5422Loading...
26
...ተመልሳ እንደማትመጣ ልቡ ያቃዋል…ብቻ ልፋ ቢለው እንደሆነም ይረዳዋል…ቀኑን ሙሉ ሲያማትር ቢውልም አንዳች አዲስ ነገር እንደማይፈጠር ከእሱ በላይ ማንም ሊያውቅ አይችልም…ማንም! …ግን እራሱን መሟገት አይፈልግም…ባትመጣም ትመጣለች ማለትን ይመርጣል…እራሱንም መሸወድ፣ ከራሱ ጋር ፀብ እንደሆነ ቅንጣት ታህል አይጠፋውም…ግን "አትመጣም" ከሚለው የእውነት ጩኽት ይልቅ "ትመጣለች" የሚለው ሹክሹክታ ለእሱ ሰላም አለው። …ከሰላም በላይ ደሞ ምን አለ?   ✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ
1 4725Loading...
27
Media files
1 5700Loading...
28
Media files
1 4361Loading...
29
Media files
1 46210Loading...
30
📙 ይድረስ ለውዷ ፊያሜታ ጊላይ... እንደምን አለሽልኝ..? እኔ በልጅነቴ ፍቅር እስከ መቃብር ነው ሲሉ ሰምቼ ዙቤይዳን እስከማገኝ ድረስ ኦሮማይን የሙጥኝ ብየ ነበር የቆየሁት። ሳድግ የፍርድ ቀን ዘመቻ ላይ ሆኜ በትኩሳት እየተንቀጠቀጥኩኝ... መልህቅ እንደሌለው መርከብ እየተናወጥኩኝ... ሌቱም አይነጋልኝ ስል ተገኘሁ። ሌላ ጊዜ ደግሞ ከአመጓ እስከ ዝጎራ እያካለልኩ መርበብትና ሰበዝን ይዤ በጠበኛ እውነቶች ስም አንፈርስም አንታደስም የሚል መፈክር ማሰማት ጀመርኩኝ። አይይይ... ይሄ ነገሬ እንኳን ለኔም አልገባኝም... ብቻ ሌላ ሰው ላይ ስፎክር እንደ ኢያሪኮ ግንብ በቅፅበት ለመፍረስ እንዳይሆንብኝ ሁሉቱ ጊዮርጊሶች ይጠብቁኝ። 📙 ይገርምሻል አንዳንድ ቀንና ህይወት ርዕስ የለውም ይባላል። ብዙ ሰው የሚስማማበት ሃሳብ ግን ያፍቃሪ ሰው ትንፋሽ ልክ እንደ መንደሪን ጣፋጭ መድሃኒት መሆኑን ነው። ከዕለታት ግማሽ ቀን ቤተልሄምን ተይው ፖለቲካን ዝም ብለሽ ሳሚኝ እያልኳት ሀገር ያጣ ሞት ድንገት በጠቢባን መንገድ በኩል ሲመጣብኝ ምንሽሮን ዋስ ጠርቼ አመለጥኩት። በሰሞነ ህማማት ደግሞ ገላና ገላዬ ሲታመሙብኝ ትዝታሽን ለኔ ትዝታየን ለአንቺ እያሰብኩኝ አሳለፍኩ። 📙 አንቺዬ ደግሞ ያልተነገረ ተረክና ያልተፃፈ ኑረት ታሪክ አይሆንምና አንድ ቀን ሜሎሪናን ህልምሽን አጫውችኝ ብያት ስታወጋኝ የአማኑኤል ሆስፒታል ታሪኮችን አስታወሰችኝ። እግረ መንገድ ይሁን እንጅ ዶክተር አሸብር የታካሚውንና የልብ ጠጋኙን ማስታወሻ እያገላበጠ ፊት ለፊቱ አሳንቲ የሰማይ ላይ ስዕል መስላ እንደተሰየመች በምናቤ ውል አለችብኝ። በመጨረሻም ከዚህ በላይ የነገርኩሽን ታሪክ ጨምሮ የአና ማስታወሻ፣ ዮቶርና ፖፒዮ የተሰኙትን ዜማዎች ከወንድም ሐሽማል ጋር ጋብዠሻለሁ። . . ያንቺው ጠኃ ባላደራ ...! የመፅሃፍት ስምና ገፀባህርያትን በመጠቀም የተፃፈ ታሪካዊ ደብዳቤ:: ✍️ መሳይ አርቀው ፊያሜታ ተናፍቀሻል🥰 ስንቶችን አንብበዋል?😊 ⛵️⛵️⛵️ "ማንበብ ፋሽን ነው።" Join us @noahbookdelivery
1 4779Loading...
31
Media files
1 2580Loading...
32
Media files
1 3530Loading...
33
Media files
510Loading...
34
ከርግቦች ትራስ ስር (አሌክስ አብርሃም) የላባን መከዳ አምነህ አትመቻች ቂም በቀል ነው ከታች! የመስዋዕት አንገት አግኝቶ እስኪመዘዝ አንዳች የሚወገር አንዳች የሚወገዝ "ከርግቦች" ትራስ ስር የዛገ ሰይፍ አለ በፍቅር እየማለ! ማነህ ባለሳምንት ማነህ ባለዝክር ተሰልፏል ከሳሽ ተሰብቋል ምስክር ብቻ እጣ ይውጣብህ ልክም ሁን ስህተት አንተን ሞረድ አርጎ የተረሳው ሁሉ ይነቃል ከዝገት!
1 3852Loading...
35
📕📚📓 #ባሎች_ሆይ_ተመከሩ 📕📚📓 🙏 ሚስትህን በምስጋና፣ በአክብሮትና በብዙ ፍቅር እንጂ ተራ በሆነ መንገድ ፈጽሞ አታናግራት 🙏 👉ሚስትህን በምስጋና፣ በአክብሮትና በብዙ ፍቅር እንጂ ተራ በሆነ መንገድ ፈጽሞ አታናግራት 👉ከራስህ ሕይወት ይልቅ እንደምትወዳት ንገራት፤ ምክንያቱም ይህ የአሁኑ ሕይወት ከንቱ ነውና፤ በሚመጣውም ዓለም በፍጹም ፍቅር አንድ እንድትኾኑ ይሁን 👉እሷን እንዲህ በላት፦ “በምድር ያለን ጊዜ አጭርና የሚያልፍ ነው፤ ነገር ግን በዚህች አጭር ጊዜ አምላክን የምናስደስት ከሆነ ይህን ሕይወት ለሚመጣው መንግሥት መለወጥ እንችላለን። ያን ጊዜ ከክርስቶስ ጋርም ሆነ እርስ በርሳችን ፍጹም አንድ እንሆናለን፣ እናም ደስታችን ወሰን አይኖረውም። ፍቅርሽንም ከኹሉም ነገር በላይ ከፍ አድርጌ እመለከታለሁ፣ አንዳችን ከአንዳችን ጋር ከመቃቃር በላይ፣ ምንም አይነት መከራ አያሰቃየንም። እርስ በእርሳችን ማር ከሆን የአለም መከራ አይመረንም፣ ኹሉንም መታገስ እንችላለን” 👉ከእርሷ ጋር አብሮ መዋልን የምትወድ መኾኑን አሳያት፣ በየገበያው ከመዞርም ከርሷ ጋር ቤት ውስጥ መሆንን እንደምትመርጥ አሳያት 👉በጓደኞችህና በልጆችህ ፊት አወድሳት 👉ስለ መልካም ተግባሯ አመስግናት፣ የሞኝነት ነገር ካደረገች በትዕግስት ምከራት። 👉በቤት ውስጥ አብራችሁ ጸልዩ፣ ወደ ቤተክርስቲያን አብራችሁ ሂዱ፣ ወደ ቤት ስትመለሱ አንደኛችሁ ሌላኛችሁን የንባብና የጸሎት ጥያቄዎችን ጠይቁ። ትዳራችሁ እንደዚህ ከሆነ ፍፁምናችሁ ከቅዱሳን መነኮሳት ጋር የሚወዳደር ይሆናል። 👉 የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አዲሱ #የነፍስ_ምግብ መጽሐፍ
1 58311Loading...
36
https://t.me/addexdrop_bot?start=9614879bbc05eb6b9c3b80474f09cf35
1 1571Loading...
37
Earn +50 Addex coins for inviting each person! Your invitation link: https://t.me/addexdrop_bot?start=9614879bbc05eb6b9c3b80474f09cf35 Total invited: 0 partners Earned: 0 Addex coins
10Loading...
38
https://t.me/getcapybot/now?startapp=MzE0NTU2NDMxfGViODA3OWY1LTdlY2QtNGZjNy1hMjg3LWU4OGZjZTFhZjRiNg==
1 2791Loading...
39
Media files
1 0490Loading...
40
ዛሬ ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቀን ነው! ስለ ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቀን አንዳንድ ነገሮች! የዓለም መጽሐፍ ቀን በየዓመቱ ሚያዝያ 15 ይከበራል። የመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅፅ የተገኘው በቻይናውያን በ3ኛው ክፍለዘመን ነበር። በ15ኛው ክፍለዘመን አጋማሽ የህትመት ማሽኖችን መፍጠር በመቻሉ የመጻህፍት አብዮት አሁን ወዳንበት ደረጃ ተሸጋገረ። ሚያዝያ 15 ለዓለምአቀፍ የመጽሐፍ ቀንነት የተመረጠበት ምክንያት የዊልያም ሼክስፒር እና ስፔናዊው የታሪክ ጸሐፊ ኢንካ ጋርሲላሶ ዴ ላ ቬጋ የሞቱበት ቀን በመሆኑ እንደመታሰቢያ እንዲሆን ነው። በእዚህ ቀን በዓለምአቀፍ ደረጃ በተለይ ወላጆች ለልጆቻቸው መጻሕፍትን በስጦታ መልክ በመስጠት ያከብሩታል። የቀኑም ትልቁ ዓላማ የንባብ በዓል ማዳበረ ነው። ✍ ኖህ book delivery
1 0941Loading...
አኮ መኖዬ ስትታወስ --- አፈንዲ ሙተቂ ------ በኦሮሞ ህዝብ አፈ-ታሪክ በስፋት ከሚታወቁ ገጸ-ባህሪዎች መካከል ናት -አኮ መኖዬ፡፡ ወደ የትኛውም የኦሮሚያ ዞን ብትሄዱ እርሷን የማያውቃት ሰው አታገኙም፡፡ በዚያ ላይ የእያንዳንዱ ዞን ነዋሪ “አኮ መኖዬ የኛ አካባቢ ሰው ናት” ይላችኋል፡፡ ቦረና ብትሄዱ “አኮ መኖዬ የዚህ አካባቢ ገዥ ነበረች፤ የኖረችበትን ሰፈርና የሞተችበትን ስፍራ ላሳይህ እችላለሁ” የሚል ሰው ይገጥማችኋል፡፡ ሸዋ ብትሄዱም “አኮ መኖዬ እዚሁ ነበረች እኮ” ትባላላችሁ፡፡ ወደ ሀረርጌ ብትመጡ ደግሞ “አኮ መኖዬ በጨርጨር አውራጃ ለገ-ቤራ በሚባለው አካባቢ ነው የኖረችው” የሚል የረዥም ጊዜ አፈ-ታሪክ አለ፡፡ ከዚህ እንደምንረዳው አኮ መኖዬ የኦሮሞ ህዝብ እንደ አሁኑ ተስፋፍቶ በሀይማኖትና በዘዬ ከመለያየቱ በፊት የነበረች ጥንታዊ ሴት ናት፡፡ የቅርብ ዘመን ሰው ብትሆን ኖሮ ታሪኳ በሁሉም የኦሮሚያ ዞን ሊታወቅ ባልቻለ ነበር፡፡ --- ያቺ በትውፊት በስፋት የምትታወቀው አኮ መኖዬ ጨካኝ ንግሥት ነበረች፡፡ በጭካኔ እርምጃዋ ብዙ ሰዎችን ፈጅታለች፡፡ ታዲያ ሰዎችን የምትገድለው እንዲሁ ከመሬት ተነስታ አይደለም፡፡ በቅድሚያ የሀገሬው ነዋሪዎች በጭራሽ ሊተግብሯቸው የማይችሏቸው ነገሮች እንዲደረጉላት ትጠይቃለች፡፡ ፍላጎቷ እርሷ በጠየቀችው መንገድ ካልተፈጸመላት በአንድ ቀን መቶ ሰዎችን ትጨርስና ታስቀብራለች (አፈ-ታሪኩ ከቦታ ቦታ ይለያያል፤ “በአንድ ጊዜ መቶ ሰው ትገድላለች”፤ “አንድ ሰው ትገድላለች”፤ “አስር ሰው ትገድላለች” እየተባለ ይነገራል)፡፡ አኮ መኖዬ ከጠየቀቻቸው ጥያቄዎች አንዱ “ከብቶች እንዳይሰማሩ፤ ከቤትም እንዳይውሉ” የሚለው ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ጥያቄ እንዴት ነው የሚመለሰው?… እርሷም የምትፈልገው ይህንኑ ነውና በአንድ ቀን መቶ ሰው ጨፈጨፈች፡፡ በሌላ ቀን ደግሞ “መሬትም ያልነካ ሰማይ ላይም ያልወጣ፤ አየር ላይ የተንሳፈፈ ቤት ስሩልኝ” አለች አሉ፡፡ ጥያቄዋ መላሽ ቢያጣ መቶ ሰው በአንድ ላይ ረሸነች፡፡ እንደገና ደግሞ “የቅቤ ተራራ ስሩልኝ፤ ይህ ተራራ ከተሰራ በኋላ ሳይናድ መቆየት አለበት” በማለት አዘዘች፡፡ በሰፈሩ ውስጥ ያለው ቅቤ ተሰብስቦ መለስተኛ ተራራ በጧት ተሰራ፡፡ ነገር ግን ጸሐይ እየጠነከረች ስትሄድ የቅቤ ተራራው ቀልጦ ፈሰሰ፡፡ አኮ መኖዬም እንደለመደችው መቶውን ሰው ፈጀች፡፡ አኮ መኖዬ እንዲህ እንዲህ እያደረገች ህዝቡን ስትጨርስ ሰነበተች፡፡ በመጨረሻም ሲያቀብጣት “በአየር ላይ የሚበር ፈረስ አምጡልኝ” የሚል ትዕዛዝ አወጣች፡፡ በዚህን ጊዜ የሰው እልቂት ያስመረራቸው የሀገሩ “ሀዩዎች” (አዋቂዎች) ተመካከሩ፡፡ ሴትዮዋን የሚያስወግዱበትን ብልሃት ለመፈለግ መላ መቱ፡፡ የአኮ መኖዬን ገመና የተረዳ አንዱ ውስጠ አዋቂ “ይህች ንግሥት የሜዳ አህያ አይታ አታውቅም፤ ስለዚህ ለምን በርሱ ላይ አስቀምጠናት ከገደል ገብታ እንድትሞት አናደርግም?” በማለት ተናገረ፡፡ ሌሎቹ ተሰብሳቢዎች ሰውዬው ባመጣው ዘዴ ተስማሙ፡፡ የሜዳ አህያ ተፈልጎ እንዲመጣም አዳኞች ወደ “ዲዳ” (የሳር ሜዳ) ተላኩ፡፡ የሜዳ አህያው ተይዞ መጣና ለአኮ መኖዬ ቀረበላት፡፡ ታዲያ አዋቂዎቹ የሜዳ አህያውን ሲያቀርቡላት እንዲህ የሚል ቃል አክለው ነገሯት፡፡ “ይህ ፈረስ በአየር ላይ ለመብረር የሚችለው ፊቱ በጨርቅ ከተሸፈነ ብቻ ነው”፡፡ አኮ መኖዬም ከሰዎቹ የተነገራትን ስትሰማ የእውነት መሰላት፡፡ በሃሳቡ መስማማቷን ገለጸችና የሜዳ አህያው በጨርቅ ተሸፈነ፡፡ እርሷም ተፈናጥራ ከጀርባው ላይ ወጣች፡፡ የሜዳ አህያው ከእስር ሲለቀቅ እንደ ጀት በረረ፡፡ ዳሩ ምን ያደርጋል?.. የአኮ መኖዬን ሰማይ ላይ የመውጣት ህልም ሳያሳካላት ከገደል ውስጥ ገባ፡፡ እርሷም ሆነ አህያው በአንድ ላይ ተሰባብረው ሞቱ፡፡ በዚህም መንገድ በጭቆናዋ የታፈነው ህዝብ ከስቃዩ ተገላገለ፡፡ -- አፈንዲ ሙተቂ መስከረም 4/2007 ----- ማስታወሻዎች 1. እንደ አኮ መኖዬ ስመ ገናና የሆኑ ሴቶች በሌሎች ህዝቦች አፈ-ታሪክ ውስጥ ይታወቃሉ። በዚህ ረገድ በሲዳማ ህዝብ የምትወሳው "ፉራ" እና በጉራጌ አካባቢ ታሪኳ የሚነገረው "ውርድውት" ይጠቀሳሉ። 2. ስለ አኮ መኖዬ አሟሟት የሚነገረው ታሪክ ከቦታ ቦታ ይለያያል፡፡ በሀረርጌና በቦረና ግን አሟሟቷ ከላይ በተገለጸው መንገድ እንደተፈጸመ ነው የሚነገረው፡፡ 3. አንዳንድ ምሁራን “የአኮ መኖዬ ታሪክ ሴቶች ወደ ስልጣን እንዳይመጡ ለመከላከል የተፈጠረ ሳይሆን አይቀርም” የሚል ግምት አላቸው፡፡ ነገር ግን ግምቱ ትክክል አይመስለኝም፡፡ በኦሮሞም ሆነ በሌሎች ህዝቦች አፈ-ታሪክ በከፍተኛ ተምሳሌትነታቸው የሚወሱ የሴት ነገሥታት አሉ፡፡ በአንጻሩ ደግሞ በጭካኔያቸው የሚኮነኑ የወንድ መሪዎች ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህ ለትውፊቱ ሌላ ግምት ከመስጠት ይልቅ የሞራል ዋጋን ለማስተማር የተፈጠረ ተረት አድርጎ መቀበሉ የተሻለ ይመስለኛል፡፡ ---- Afendi Muteki September 15/2014
Show all...
So ልጅቷን እኛ መስሪያ ቤት ነው የማውቃት (this kinda storytelling ከticktock ነው ያየኹት። grammatically wrong ነው አይደል ?ደግሞ አብዛኛዎቹ ብዙ view አላቸው...ምን ያህል ወረኛ ብንሆን ነው በእመቤቴ ! ስራ የለንም እንዴ? ) እና ወደ ወሬዬ ስመለስ ልጅቷ እኛ መስሪያ ቤት አዲስ ገቢ ናት።ከቢሮአችን ጎን ነው ቢርዋ...በውበቷ ብዙ ሰው ስለሚያሸረግድላት...በቅርጿ ሴቶችም ሳይቀሩ መነጋገሪያ ስላደረጓት...እጅግ ጣሪያ የነካ መኮፈስ...መንጠባረር...መመፃደቅ...ይስተዋልባታል። ...አንድ ቀን እኛ ቢሮ ለጉዳይ መጥታ ፈገግ ብላ ሰላም አለቺኝ...ከደማቅ ፈገግታ ጋር አፀፋውን መለስኹ። ...ከዛ ሌላ ጊዜ በመንገድ ስንገናኝ ሰላም መባባል የለብንም ? በሁለተኛው ቀን ፊት ለፊት ስንገናኝ ከመተላለፋችን በፊት ሰላም ልበላት አልበላት እያልኹ ሳመነታ "ሰላም ነህ ?" አለቺኝ በዛ ድምጿ...አፀፋዋን መለስኹ። ከዛ በቀጣዩ ቀናቶች ፊት ለፊት ስንገጣጠም አንዴ ሰላም ትለኛለች ሌላ ጊዜ ትዘጋኛለች ። ብቻዬን "ሰላም ነው?" እያልኹ አልፋለሁ። አሁን አሁን እሷን ሳይ መሳቀቅ ጀመርኹ ሰላም ልበላት ወይስ አልበላት? ቆይ ማነኝ ብላ ነው የምታስበው? የእርሷ ሰላምታ ቀኔን የሚያበራው ፤ ምሽቴን የሚያደምቀው መሰላት ? ምናባቷ ነው የምታወዛግበኝ ፤ ስንት ሰው ሳቀብኝ ብቻዬን " ሰላም ነው? " እያልኹ እያለፍኹ ! ሰላም ነው? ©ሶፊ
Show all...
10
እወዳታለሁ ❤ መውደዴ ሰላማዊ ነው። ጥርጣሬ የሚፈጥር ጨዋታ አታመጣም ። ከሰዎች ጋ ያላት ጨዋታ ሁኔታ፣ ትውውቅ ጨዋነት የተሞላበት ስለሆነ አይረብሸኝም ። እወዳታለሁ ፦ እንከኔን ስታይ እንዴት እንደምታስተካክለው እያሰበች ነው አሁን ማክሰኞ ለ'ት ወረቀት ኪሴ ውስጥ ሲዝረከረክ ተመልክታ ሌዘር ቆንጆ ዋሌት አመጣችልኝ ። የተበሳጨሁበትን ነገር ደግማ አታደርግብኝም ። እማትወደውን ነገር "ማርዬ እንዲ አታድርግ" ትለኛለች ለስለስ ያለ ሁኔታ ውስጥ ግግር አቋሟን አየዋለሁ ። በተጣላንበት በተጨቃጨቅንበት ጉዳይ በሌላ ቀን አንስተን አንንዘባዘብም ። ፍቅራችንን እና ፀባችንንም እወቁልን ስሙልን አንልም ። እሷን የሚያሳጣኝ ሁኔታ ውስጥ አልሳተፍም ። እንደምወዳት ነግርያታለሁ እንደምወዳት አሳይቻታለሁ ። እንደምቶደኝ ነግራኛለች እንደምቶደኝ አይቻለሁ ። መዋደድ ደስስ ይላል ❤ ©Adhanom Mitiku
Show all...
🔥 7 2
https://t.me/gamee?start=ref_314556431 Participate in mining events, play games, and spin the Fortune Wheel to WIN. Welcome gift included!
Show all...
Gamee

🎮 The biggest gaming platform on Telegram! 🔥 Join the community 👉 @gameechannel Perks, giveaways, airdrops & more 🎁 🎉💵

Photo unavailableShow in Telegram
ሎላሼ ዲጂታል መጽሔት ሎላሼ¶ {የንጋት ጸሀይ} . . . መኖርን በብርሀኗ ጅራፍ ቋጨን! በሶስት ሳምንት አንድ ግዜ ከሚደርሶ መጽሔታችን ጎን ለጎን፥ የእለት ሞሶባችንም ሙሉ ነው። ዛሬ ማታ ሁለት ሰአት ሎላሼ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ አንድ ቁጥር አንድን ይጠብቁ የፌስቡክ ገጻችንንም ይቀላቀሉ። ይህን ስላደረጉ እናመሰግኖታለን https://www.facebook.com/profile.php?id=61556306424311&mibextid=ZbWKwL
Show all...
👍 2
እዉነት እንዳይመስልሽ . . ዛሬ ......ምን ብትደምቂ፤ ከቆነጃጅቱ እጅጉን ብትልቂ፤ ኑሮ ተመችቶሽ ያ.... ፊትሽ ቢወዛ፤ ወደድኩሽ የሚለዉ አፍቃሪሽ ቢበዛ ፤ ሴትነትሽ ማለት... መልክ ከመሰለሽ፤ ፍፁም አትመኪ እዉነት እንዳይመስልሽ፤ አንቺን ሳያማክር........ የጠቆረዉ ፀጉርሽ.. በሽበት ይተካል፤ ጸአዳዉም መልክሽ በፍጥነት ይረግፋል፤ ሴትነትሽ ማለት መልክ ከመሰለሽ፤ ፍፁም አትመኪ እዉነት እንዳይመስልሽ። .......................................... በዔደን ታደሰ
Show all...
👍 11
ሁሉም ነገር ለበጎ ነው! አንድ ሃብታም ጎብኚ ወደ አንዲት ሃገር ከተጓዘ በኋላ ከከተማ ራቅ ወዳለ ስፍራ ለጉብኝት ሄደ፡፡ በዚያም አንድን እጅግ በጣም ደሃ የሆነ አስጎብኚ ቀጠረውና አካባቢውን እያሳየው ሲጓዙ ሳለ ጎብኚው አንድ ከዚህ በፊት አይቶት የማያውቀው አይነት ዛፍ ተመለከተ፡፡ በነገሩ ተገረመና ውስጡ ምን እንደሆነ ለማወቅ ለጉዞ የያዘውን አነስተኛ መጥረቢያ አንስቶ ዛፉን እቆርጣለሁ ብሎ ተሳስቶ ጣቱን ቆርጦ ጣለው፡፡ ይህ ባለጠጋ ጎብኚ በስቃይ ሲጮህ አስጎብኚው፣ “አይዞህ ሁሉም ለበጎ ነው” እያለ በመደጋገም ሲነግረው እጅግ ተበሳጨና አጠገባቸው የሚገኝ ጉድጓድ ውስጥ ገፍትሮ ጥሎት ሄደ፡፡ ይህ ጎብኚ ትንሽ ከተጓዘ በኋላ ጸጉረ ልውጥ ሰው ሲያገኙ ቀቅለው የሚበሉ ጎሳዎች አገኙት፡፡ የሚበላ ሰው በማግኘታቸው የተደሰቱት እነዚህ ሰዎች ጥፍር ካሰሩት በኋላ እንደልማዳቸው እሳታቸውን አንድደውና መቀቀያውን ጥደው በዙሪያው ከጨፈሩ በኋላ ጎብኚውን መቀቀያው ውስጥ ሊጨምሩት ሲሉ በድንገት የተቆረጠውን ጣቱን ተመለከቱ፡፡ በእምነታቸው መሰረት እንደዚህ አይነት ሰው መብላት ክልክል ስለሆነ ሃሳባቸውን ቀይረው እንዲሄድ ለቀቁት፡፡ ይህ ጎብኚ የነበረበት የፍርሀት መንቀጥቀጥ ረገብ ሲልለት መጀመሪያ ትዝ ያለው በንዴት ገደል ውስጥ ገፍቶ የጣለው አስጎብኚው ነበረና ሄዶ ጎትቶ በማውጣት ይቅርታን ጠየቀው፡፡ የአስጎብኚው መልስ አሁንም እንደተለመደው፣ “ችግር የለውም፣ ሁሉም ነገር ለበጎ ነው” የሚል ነበር፡፡ ጎብኚው ይህንን መልስ በድጋሚ በመስማቱ፣ ምን ለማለት እንደፈለገ ጠየቀው፡፡ የአስጎብኚው መልስ እንደዚህ የሚል ነበር፡- “አንዱ ጣትህ በመቆረጡ ምክንያት በእነዚህ ሰዎች ከመበላት ዳንክ ስለዚህ አንዱ ጣትህ መቆረጡ ጥሩ ልምምድ ባይሆንም የኋላ ኋላ ግን ለበጎ ሆነ፡፡ አንተ ደግሞ እኔን በንዴት ገደል ውስጥ መክተትህ ምንም ጥሩ ነገር ባይሆንም፣ ያንን በማድረግህ ምክንያት እዚሁ ባልቀርና አብሬህ ብጓዝ ኖሮ አንተን ትተው እኔን ይበሉኝ ነበረ፡፡ ይህም ለበጎ ሆነ”፡፡ ካጠፋ በኋላ የሚመለስና ይቅርታ የሚጠይቅ ማንነት ላለው ሰው ሁሉም ነገር ለበጎ ነው! ይቅርታ ሲጠየቅ መለስ ብሎ ይቅር የሚል ጨዋ ማንነት ላለው ሰው ሁሉም ነገር ለበጎ ነው! በሁሉም ነገር በፈጣሪው ላይ ያለውን እምነት ለማይተው ሰው ሁሉም ነገር ለበጎ ነው! በአሁኑ ወቅት የምታልፉበት አስቸጋሪ ሁኔታ ለበጎ እንዲለወጥላችሁ ጸሎቴና ምኞቴ ነው፡፡ ✍ ዶክተር እዮብ
Show all...
👍 12
መልካም የናቶች ቀን ❤ 😥❤ አምስተኛ ክፍል ማጥናት፤ ትምህርት በደንብ መማር፣ መከታተል ጀመርኩ ። ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለተኛ ወጣሁ ደስስ አለኝ። ለእናቴ ስበር ሄጄ ነገርኳት : ሎተሪ እንደደረሰው ሰው ፊቷ ፈካ። ትክ ብላ አይታኝ፤ "ስጋሃ?" አለችኝ (እውነት! እንደማለት ነው ) "ስጋሂ" አልኳት። ግንባሬን፣ አንገቴን ሳመችኝ ። "ጎበዝ ዝወደይ: ከማኻስ ዓሰርተ ዘይምወለድኩ " ( እንዳንተ አስር ልጅ በወለድኩ) ብላ አገላብጣ ደግማ ሳመችኝ። "ወሊድካ ተሓጎስ" (በልጅህ ደስ ይበልህ) "ተመስገን : ተመስገን: ምን ይሳንሃል ጌታዬ " ብቻዋን ከጌታዋ ጋር አጉተምትማ ስታበቃ ፤ "ምን ልግዛህል" አለችኝ ? "ኮካ ኮላ እና ጮርናቄ " አልኩ ከጉያዋ መሃረብ አውጥታ ጭምትር ያለች አምስት ብር ሰጠችኝ :ገዝቼ መጣሁ። "ብላ አባ ዘወደይ" "አንቺ አትበይም?" "ጠግቤያለሁ፤ ደግሞ እኔ ለስላሳ አልወድም አበሩ ጋር ጠላ ጠጥቻለሁ። በሚቀጥለው ደግሞ አንደኛ ትወጣለህ አይደል? " አለችኝ። "እንደዚህ ደስስ የሚልሽ ከሆነ እ'ማ እወጣልሻለሁ ። " "መጣሁ : ቤቱን ጠብቅ" ብላ የሆኑ ከቀበሌ የመጡ የእርዳታ ድርጅቶች የገዙልንን ትልቅ ድስት ይዛ ወጣች: ብዙ ቆይታ መጣች ። ስትመጣ ብረት ድስቱን አልያዘችውም። በብረት ድስቱ ፈንታ ጥቁር ፌስታል ይዛለች። ጥቁሩ ፌስታል የያዘውን ስታወጣው አመድማ ሸራ ጫማ እና ጥልፍልፍ ነጭ ክፍት ዘለበታም የባሊያችንን ቀለም የመሰለ ጫማ ገዛችልኝ ። ደስታ ሊገለኝ ደረሰ። ጋዴ ማድረግ አቆምኩ :ጋዴ ጫማዬ ተጣለ ። ቆይቶ በጣም ቆይቶ ነው በእርዳታ የተሰጠንን ድስቷን ሸጣ ጫማ እንደገዛችልኝ ያወኩት ። የዚህች እናት ልጅ ሆኜ እንዴት መስነፍ ይቻለኛል ?! © Adhanom Mitiku
Show all...
🥰 25👍 2

👍 4💔 2