cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ማኅቶተ-ኄራን✍

ህልም አልባ መሆን ካለመኖር በላይ…። ይህ የኛ ቻናል ነው። እኛ ማለት ደሞ እናንተ ነንና የናንተን ለናንተ እነሆ እንካችሁ…(በጥበብ ለመግባባት ያህል ረጅሙን በአጭሩ እንተርካለን። አብራችሁን ቆዩ)። ለአስተያየቶ @yhudaz

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
189
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ጠያቂ ለምን እንቀየማለን?። መላሽ መተው ስለማንችል። ጠያቂ "እሱማ ከመተው ባለፈ መርሳትም አለ" ሲል በምላሹ ሳቅ አለ። መላሽ አፍንጫውን አከክ አከክ አድርጎ "ልክ ነህ ጥያቄህ ለምን እንቀየማለን ነው አይደል?" ሲል ጠየቀ። ጠያቂ "እህ" ሲል አንገቱን ነቀነቀ። መላሽ ትንሽ ግር ያለው በመምሰል "እና ትንሽ ግዜ እንዳስብበት ትሰጠኛለህ?" ካለ በኋላ "ግን ይቅርት ጥያቄ አበዛው" ሲልም ከንፈሩን ነከሰ። ጠያቂ ፈገግ እያለ ቅድም ፈጥነህ መተው ስለማንችል ብለሀል አሁን ካሰብክበት ደሞ መርሳት ማለቴ ስላልተዋጠልህ ሁሉን አስታውሰህ ለምን አንቀየምም ማለትህ አይቀርም። ስለዚህ አታስብ አንተም ልክ ነህ እንቀየማለን ሲል ዞር ብሎ ተመለከተው፡፡ ባየው ነገር የረካም ይመስላል። . . . ደስ የሚል ንጹህ ፈገግታ። . . . ከመተው ባለፈ በመርሳት ውስጥ ሰናይ ቀን። #ማኅቶተ_ኄራን @mahtotzeherans @yhudaz
Show all...
ትላንት ጨለም ያለው ሰማይ ላይ ከዋክብት ተበትነዋል። በእጇ ወደ አንድ አቅጣጫ እያመለከተችኝ "እነዛን ሶስት ከዋክብት ተመልከት" አለችኝ። እጇን ተከትዬ በጣም እንደሚያምሩ ነገርኳት። "ሁሌም ልብ በላቸው ተለያይተው አያውቁም" ስትል አንገቷን ወደ ትከሻዬ አዘነበለች። ዛሬ? ጨለም ያለው ሰማይ ላይ ከዋክብት ተበትነዋል። በአንድ ወቅት ስለማይለያዩ ሶስት ከዋክብት አንስተን ያወራነውን አስታውሼም ከሰማዩ ቀና እንዳልኩ እነሱን ፍለጋ ትንሽ ቆየው። ግን ላገኛቸው አልቻልኩም። አንገቴን ሰብሬ መንገዴን ስቀጥል ትልቅ ዛፍ ከጣለው ጥላ ስር ቀጥሎ ካለ ብርሀን ጥላዬ እየጠለቀ ሲሄድ ተመልክቼ ትንሽ ፈገግ አልኩ። . . . ነገን ከትላንት ሚለየው ዛሬ ከዛሬ ሚለየው ደሞ ትላንት አለ። ይህም ማለት የነዛ ከዋክብት ጉዳይ ነገ ላይ ጥያቄ ነው። ይህን ሁሉ ግን በአንድ ነገር መጠቅለል ፈልጋለሁ። መለየት በሚል ክቡድ ቃል። ስለሶስቱ ከዋክብት እውነታን መነሻ ማድረጌ ሶስትነትን የቁጥር ጉዳይ አድርጋችሁ እንድትወስዱ እንደማያደርጋችሁ አምናለሁ። እናንተን በመለየቴ የከፋኝ ብዙዎች ናችሁ፡፡ #ማኅቶተ_ኄራን @mahtotzeherans @yhudaz
Show all...
ከጠረፍ እኛና እነሱን ከሚለያየው ድንበር ላይ ተገናኘን። መቼም መኖር ታምሯ አያልቅም። ያልሞተ ይገናኛል ሚሉት ነገር ለካ አብረው ሳሉ ላልተያዩም ይሰራል። ሳቅ ከደስታ ወይስ ደስታ ከሳቅ ይመነጫል?። መልሱን እኔም እንጃ። ብቻ ግን መጨረሻ ላይ ቢከፋንም ሳቃችን ግን ከኛ እንዳልተለየ ይታወቀኛል። ደሞ መጪውም አለ። በፍርሀት ምኞት መስሎ በናፍቆት ግን መሆኑ የሚጠበቅ ነገ። . . . ብቻችንን መቅረታችን ሲታወቀኝ ሳቅ እያለ አንተምኮ መሄድ ትችል ነበር አለኝ። ስለኔ የተጨነቀ ስለመሰኝ አታስብ በመሄድ ውስጥ ብዙ ስለደከመኝ የተከፋሁ መስላለሁ እንጂ…አላስጨረሰኝም ከት ብሎ ሳቀና በል እንሂድ እንቀላቀላቸው አለና ትከሻዬን ቸብ አድርጎኝ ተነሳ። እኔ ግን ከተቀመጥኩበት ፈዝዤ ቀረሁ። እነሱን እየተመለከትኩ አንዳንዴ ዞር ሲሉ ፈገግ እያልኩ እጄን አነሳላቸዋለሁ። ሄዋን እጄን ሳነሳላት መጥታ ሰው ብዙ ነገር ያጠፋል ከቻልክ አትሰልች ብላኝ ሳም አድርጋኝ ሄደች፡፡ እሱ ደሞ መጣና መኖር ውስጥ ምንም ይቅርታ የለም ሁሉም ለውሳኔው ተላልፎ ይሰጣል ሲል ጥርሱን አንቀጫቀጨብኝ። መጽሀፍ ደሞ ስለሁሉም በፍቃዱ አንዱ ሞተ ይላል። . . . እኔ ግን ሶስቱን ምርጫዎቼን አስቤ ሳበቃ ሊዱን ዞር ብዬ ተመለከትኳት፡፡ ሄዋኔ ልክ ናት። ግዜ እንዲህ አዙሮ ሊያገናኘን መኖር እንዴት ይሰለቻል?። #ማኅቶተ_ኄራን @mahtotzeherans @yhudaz
Show all...
ከዕለታት አንድ ቀን #ጋሼ ስብሃት በከተማ አውቶቢስ ይጓዛል። አንድ ሌባ ጠጋ አለና ኪሱ ገባ። ጋሼ ስብሃት ቀድሞ ነቅቶ ኖሮ "ምነው!" አለው። ሌባውም ደንገጥ ብሎ "ውይ የኔ ኪስ መስሎኝ ነው" ሲል መለሰለት። ጋሼ ስብሃት የሚወርድበት አከባቢ ሲደርስ እየተራመደ ሌባውን ጭው አደረገው። ሌባውም ምነው ሲለው "ውይ የኔ ፊት መስሎኝ ነው" አለው። • # ምንጭ :- "ማስታወሻ" በዘነበ ወላ ገጽ-21 @mahtotzeherans
Show all...
አይገርምሽም ውዴ?🤷‍♀ 🎤kiya @noc_7612 @mahtotzeherans
Show all...
ናፍቀሽኛል አትበል🙄 🎤kiya @noc_7612 @mahtotzeherans
Show all...
ዛሬ አንድን ደስታ አየው። ሌላ አይደለም የመጨረስ ደስታን ነው። ይህ ደስታ እኔን ብቻ የሚመለከት ይሁን አይሁን አላውቅም። ግን ሳስበው ልክ ነኝ። ይህ ደስታ ለሚያልቀው ወይስ ለሚጀምረው ሲል አይምሮዬ ትክክለኛውን ጥያቄ የጠየቀ ይመስለኛል። ብቻ ሁሉን ስናልፍ… . . . አንድ ልይት ያለ ሰው መድረኩ ላይ ነበር። ይህ ሰው ከአለባበሱ የተነሳ ከአይን ከመግባቱ በላይ ሁናቴው ጥያቄን ይጭራል(ወላጅ ልጁ ምን ብትሆንበት ማን አስተማረሽ አለ አሉ)። ለምሳሌ ያህል እኛ ክብ ስንሰራ እሱ መሀል ነበር። አናዳጅ ነደደ በለኮሰው እሳት አወይ አጉል ጥጋብ አወይ ድሮን መርሳት…ሲባልማ ፎክሮ ሲተኩስ ያመለጠ የታል እስኪ ድረስ ምነበር? ታሪኩ ያጓጓል። እሷ ነበር ያስተማረችው። አሁንም ሌላ አይደለም ያለፈን ስለመርሳት ነው ያወራሁት። . . . ካለንበት ስንነሳ ደመና ዝናብ መስሎ ቢያስፈራራንም እኛ ግን እጃችንን በኪሳችን ከተን ሳቃችን ላፍታ ወደላይ ዝናቡን ሳይፈራ ተራመድን። ምክንያቱም በመንገዳችን የተሳለምነው እንኳን ተራምደን ለምንደርሰው በረን እማናልፈው ለሚመስለን እንኳን እንደማያንስ እናውቃለን።…ደረስን። ከበሩ ቆመን አንዳችን ሌላኛችንን ተመለከትን። ሳቃችን ያለንበትን ግዜ በአግራሞት እንደታዘበው ገብቶኛል። ግዜውን በአመት በወር በሳምንትና በቀን አስልተን ብቻ አላበቃንም እንደገና በስልሳ አባዝተን ሰአታቱን አስታወስናቸው፡፡ ዛሬም ላይ አለንና ግዜ ካይናችን ስር ሰለቀለለ ሌላ አይደለም እንደቀልድ አልን። . . . አሁን ትላንት እና ሰው የሚሉ ቃላት ትርጉም ተለየ። ምክንያቱም አሁን ላይ ሰው እንጂ ትላንት ሚባል ቃል በማያልፍ ዛሬ ስለተጋረደ አይስተዋልም። ነገ ግን አለ። ወደ ነገ መሄድና ነገ ላይ ሰውን መለየት ግን ይከብዳል፡፡ ምን አልባት እንደቀልድ እስካልተለያየን ድረስ፡፡ #ማኅቶተ_ኄራን #mahtotzeherans #yhudaz . .
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
።...…ታወራዋለች።...…አይመልስላትም።……ስትለው በጥያቄ ያስባል። ሀሳብህ የሚያስፈልገውን ሲፈጥር አካልህ...?።አሁንም አሁንም ደግሞ ያስበዋል። ሀሳብህ…...?። ከሀሳቡ መልስ እውነት ነው ሀሳቤ ሚፈልገውን ሲፈጥር አካሌ በፈጠርኩት ካልኖረ...…ሲል ወደግሮሰሪ ያመራል። በዚህም ሌላ ሀሳቡ ራሱን ለማጥፋት ከዘረጋው መረብ ራሱን ዘንግቶ ያመልጣል። ነገ ደሞ ሌላ ቀን ነው።…...ሲነጋ ራሱን የት እንደጣለ ባያውቅም ግን አዲስ ቀን ላይ ነው። አሁን ሀሳብህ...ሚሉ ቃሎቿን ሀሳቡ ሲያስታውሰው የተስፋ ፈገግታው ጽንፍ የለም።... #ማኅቶተ_ኄራን @mahtotzeherans @yhudaz
Show all...
#ፍትሃዊው_ዳኛ! አሜሪካ ውስጥ የ15 አመት ታዳጊ ሱቅ ሲሰርቅ ከዛም ሊያመልጥ ሲል አንዱን መደርደሪያ ሰበረ ይህ ፍትሃዊ ዳኛ የሰጠው ፍርድ!! ዳኛው የክስተቱን ዝርዝር ሁኔታ ከሰማ በኋላ ልጁን እንዲህ ሲል ጠየቀው። "በእርግጥ የሆነ ነገር ሰረቅክ? ዳቦና አይብ ሰርቀህ መደርደሪያ ሰባበርክ?" ልጁም አንገቱን ደፍቶ በአፍረት አዎ ሲል መለሰ፡፡ #ዳኛ፡ "ለምን ሰረቅክ?" #ታዲጊው_ልጅ: በጣም ፈልጌው ነው #ዳኛ፡ ከመስረቅ ይልቅ መግዛት አልቻልክም ነበር? #ልጅ፡ ምንም ገንዘብ አልነበረኝም። #ዳኛ፡ ወላጆችህን ገንዘብ ልትጠይቅ ትችላለህ። #ልጅ፡ እኔ ያለኝ፣ አልጋ ላይ የተኛች እና ስራ የሌላት የታመመች እናቴን ብቻ ነው... ለሷ ስል ዳቦና አይብ ሰርቄያለሁ። #ዳኛ፡ እና አንተ….. ምን እየሰራህ ነው? ሥራ የለህም? #ልጅ፡ የመኪና ማጠቢያ ሆኜ እሰራ ነበር። እናቴን ለመርዳት አንድ ቀን ዕረፍት ወሰድኩ፣ ለዚህም ነው ያባረሩኝ። ከልጁ ጋር የነበረው ውይይት ካለቀ በኋላ ዳኛው ፍርዱን አስታወቁ፡- “ሌብነት በተለይም ዳቦ መስረቅ በጣም አሳፋሪ ወንጀል ነው። ለዚህ የስርቆት ወንጀል ሁላችንም ተጠያቂ ነን። ለዚህ የስርቆት ወንጀል ዛሬ እኔ ራሴን ጨምሮ እዚህ ክፍል ውስጥ የተገኘ ሁሉ ተጠያቂ ነው” አለ። በመቀጠልም ሁሉም ተሰብሳቢዎች አሥር ዶላር ይቀጣሉ እና ማንም ሰው 1ዐ_ዶላር ሳይከፍል ከአዳራሹ አይወጣም። ዳኛው ከኪሱ የ1ዐ ዶላር ቢል አንሥቶ እስክሪብቶ አወጣና እንዲህ ብሎ መጻፍ ጀመረ። "በተጨማሪም የተራበውን ልጅ ለፖሊስ ያደረሰው ሱቅ ባለቤት 1,ዐዐዐ ዶላር እንዲቀጣ አዝዣለሁ እና ቅጣቱ በአንድ ሰዓት ውስጥ ካልተከፈለ ሱቁ ተዘግቶ ይቆያል።" በአዳራሹ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ለልጁ ይቅርታ ጠይቀው ሙሉ ገንዘቡን ሰጡት። ዳኛው እንባውን ለመደበቅ እየሞከረ ከችሎቱ ወጣ። ተሰብሳቢዎቹ የዳኛውን ውሳኔ ከሰሙ በኋላ ዓይናቸውበእንባ ተሞላ። ዳኛው አክለውም “አንድ ሰው ዳቦ ሲሰርቅ ከተያዘ መላው የዚች ሀገር ህዝብና ህብረተሰብ ሊያፍር ይገባል” ሲሉም አክለዋል። #ማኅቶተ_ኄራን @mahtotzeherans @yhudaz
Show all...