1 671
Subscribers
No data24 hours
-177 days
-8030 days
Posts Archive
1 671
አንድነት ሀይል ነው። አንድ ሆነን በመንገዳችን ስንጓዝ የሚገጥመንን እንቅፋት እየጠረግን የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናደርጋለን።
መልካም ቀን ይሁንለዎ!
#Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና
1 671
"ኢትዮጵያ ለብዙ ሺህዎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል ያስገኙ 13 የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ገንብታ ወደ ስራ አስገብታለች። የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮችንም ገንብተን በስራ ላይ እንገኛለን።
ከአለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋ ጋር በመሆን ዛሬ ጠዋት በአንደኛው የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በምርት ስራ ላይ ካሉ ኢንዱስትሪዎቻችን ሁለቱን አብረን ጎብኝተናል። ኢትዮጵያ ትልቅ አቅም ያላት ሀገር ብቻ ሳትሆን በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች መዋእለ ነዋይ ለማፍሰስ ለሚሹ ሁሉ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረች ነው።"
ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ
1 671
ፓሪቲያችን ብልፅግና ልማትና ፍትሓዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ አካታች የኢኮኖሚ ስርዓት ለመገንባት ባደረገው ጥረት ውስጥ ስንዴን ለውጭ ገበያ ማቅረብ ያስቻለ አቅም ፈጥሯል። አፋር ላይ ስንዴን ማምረት እንደሚቻል አሳይቶ ችግራችን የአተያይ እንጂ የሀብት አለመሆኑን አስመስክሯል። ትናንት የተገፉ ክልሎች ዛሬ የኢትዮጵያ ያልተነኩ ሀብቶች መገኛ መሆናቸው ተመስክሯል። የተረሳው ዘርፍ ማዕድን ዛሬ አንዱ የኢኮኖሚው ምሰሶ ሆኗል። ጋንቤላን በማዕድን ዘርፍ ተጠቃሽ ማድረክ የተቻለው የአካታች ኢኮኖሚ ስርዓቱ እውን በመሆን ነው። የቱሪስት መስህብ ቦታዎች በጥንታዊነታቸው በታሪክ ተናጋሪነታቸው ይጎበኙ የነበሩት ዛሬ የዘመናችን አሻራ ተጨምሮባቸው ጥንታዊ ታሪኩን አይቶ ዘመኑን በሚመጥኑ መዝናኛዎች ከጥንት እስከ አሁን የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚያረጋግጡ ሀላላ ኬላ፣ ኮይሻ፣ ጎርጎራ፣ ወንጪ ተጠቃሾቹ ናቸው። ግብርናውን ከኢንዱስትሪው ማዛመድ፣ ቱሪዝሙን ከጥንት ታሪክ የዛሬ ምቾት ጋር ማገናኘት፣ የከተሜነት መስፋፋትና መዘመን፣ ማዕድን የራሱን ድርሻ እንድወጣ መደረጉና የአይሲቲ ዘመነኛው አንዱ የኢኮኖሚ መወዳደሪያ ዘርፍ እንዲሆን መደረጉ ፓርቲያችን ብልፅግና በፕሮግራሙ ላይ ያስቀመጣቸውን ብዝሃ ዘርፍ እውን የማድረግ ቃል ኪዳን በተግባር የተገለጠበት ናቸው። የተጀመረው የኢኮኖሚያዊ ግስጋሴ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን አድርጎ አይቀሬው የከፍታ ማማ ላይ የሚያስቀምጥ ነውና ሁላችንም በተሰማራንበት የድርሻችንን ኃላፊነት እንወጣ።
መልካም ቀን ይሁንለወሸ!
#Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና
1 671
ብልፅግና ማህበራዊ ፍትህን ለማረጋገጥ የሚሰራ ጠንካራ ፓርቲ ነው።
ብልፅግና ፓርቲ በማህበራዊ ዘርፍ የሰራቸው በርካታ ተግባራቶች አሉ። በፕሮግራሙ ላይ በዝርዝር አስቀምጦ በተግባር በርካታ ስራዎችን እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው።
ስራዎቻችን ትውልድ ላይና ለትውልድ የሚሰራ ፓርቲ መሆኑን የሚያረጋግጡ ስራዎች በስኬት ተሰርተዋል። ከተሰሩት መካከል የትምህርት ፍትሃዊ ተደራሽነትን ማረጋገጥ ሲሆን በዚህ ረገድ የሚመሰገን ስራ መስራት ተችሏል። አዲስ አበባ በ2015 በጀት አመት በ6 ወር ውስጥ ገንብታ በአንድ ጀንበር 72 የትምህርት መማሪያ ህንፃ መርቃ ስራ ማስጀመር መቻሉ አንዱ ማሳያ ነው።
ተደራሽነት ከጥራት ጋር የተቀናጀ መሆን አለበት። መፍጠር የሚችል ትውልድ ማፍራት የሚቻለው የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ ነው። የትምህርት ተደራሽነት ካላረጋገጥን መማር የማይችል ትውልድ ይኖረናል። የትምህርት ጥራት ካላስጠበቅን ብቃት የሌላቸው ተመራቂዎች ይኖሩናል። ለዚህም ነው ብልፅግና የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት የማይነጣጠሉ ናቸው በሚል ሁለቱም ላይ በስፋትና በብቃት እየሰራ የሚገኘው።
ከመዋለ ህፃናት እስከ ፕሪፓራቶሪ የትምህርት ደረጃ በርካታ የመማሪያ ክፍሎች ተሰርተዋል። ተማሪ ከትምህርቱ ውጭ ሊያሳስበው የሚገባ ጉዳይ አይኖርም በሚል ከመመገብ እስከ ማልበስ የደረሰው ተግባር ሌሎች በአርዓያነት ሊወስደው የሚገባ ለትውልድ የተሰራ ስራ ነው።
ተደራሽነት ብቻውን በራሱ በቂ እንዳልሆነ በማመን በቁርጠኝነት የተሰራው የትምህርት ጥራት ማስጠበቅ ላይ ነው። አንድ ተማሪ በብቁ መምህር ከተማረ፣ ስሚለብሰው ካላሰበ፣ ምግብ ካላሳሰበው፣ ምቹ ፅዱ እና ውብ መማሪያ ክፍሎች ካሉት፣ የመማሪያ ቁሳቁስ ከተሟላለት ለትምህርት ጥራት ዋናዎቹ ተሟሉለት ማለት ነው። ቀሪው ተማሪዎች አላማቸውን እንድረዱ ማስቻል፣ የትምህርት ካርኩለሙ ጥራትን የሚያስጠብቅ እንዳደርግ በሙህራን አስጠንቶ መተግበር በመሆኑ እነዚህን ሁሉ እውን ማድረግ ተችሏል። ውጤቱንም በጅማሮ እያየን እንገኛለን። አጠናክሮ በመቀጠል በተሰራው ስራ የሚመጡ ውጤቶችን ለሀገር ጥቅም እንድሆን ስቻል ብቻ ነው።
በቴክኒክና ሙያ ተቋማቶቻችን መፍጠር የሚችል የተቀያያሪውን አለም የተረዳ ከራሱ ያለፈ ለሀገረ የሚጠቅም ለትውልድ የሚተርፍ ስራ መስራት የሚችሉብቃት ያላቸው ወጣቶች አሰልጥኖ አስተምሮ እያስመረቀ ይገኛል። የትናንቱ በከተማችን አዲስ አበባ የቴክኒክ እና ሙያ የተማሪዎች ምረቀ አንዱ ነው።
ሀገር የምትበለፅገው የመፍጠር ችሎታ ባለው በተሰማራበት ፈጣን በሆነ ትውልድ ነው። አሁን እየተሰራ ያለውም ትውልዱ በፍጥነት የመፍጠር ችሎታውን የሚያዳብርበት ውድድር በበዛበት አለም ውስጥ አሸናፊ ሆኖ የሚወጣበት እንዲሆን ነው።
በጤና ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች፣ ከቅድመ መከላከል እስከ አክሞ ማዳን የሚችል ጥጤና ስርዓት፣ በስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ግንባታ፣ የወጣቶች እና የሴቶች ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በማህበራዊ ፕሮግራማችን ከሰራናቸው በጥቂቱ ነው።
ከዳረጎትነት ወደ መብት የተሻገረ ማህበራዊ ፍትህን ለማረጋገጥ የተሰራውን ስራ አጠናክረን ትውልድ ላይ በመስራት ብልፅግናን እናረጋግጥ።
መልካም ሳምንት ይሁንለዎ!
#Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና
1 671
ቃል የገባውን በተግባር እውን የሚያደርግ፣ ያቀደውን መተግበር የሚችል፣ ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ እየወሰደ ያለ ፓርቲ ብልፅግና ነው። ኢትዮጵያ በልጆቿ ብልፅግናዋን እያረጋገጠች ያለች ሀገር ነች። በምታደርገው ጉዞ እንቅፋት እንድሆን የሚሰሩ ጠላቶች ብዙዎች ናቸው። እኛ ኢትዮጵያዊያን ግን ጠላት አይበግረንም እንቅፋት ከጉዟችን አይገታንም። አንድ ስኬት ስታስመዘግብ ሺህ እንቅፋት ሊደረደርብን ይችላል። አንድ ሆነን በመንገዳችን ስንጓዝ የሚገጥመንን እንቅፋት እየጠረግን የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናደርጋለን።
#Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና
1 671
ፓርቲያችን ብልፅግና ሰርቶ ማሳካት ቃል የገባውን በተግባር የሚገልጥ ፓርቲ ነው። ብልፅግና የሚሰራው የነገውን ትውልድ ጥቅምና ፍላጎት ያገናዘበ ነው። ፕሮጀክትን የሚጀምረው ዜጎችን የሚጠቅም ስለመሆኑ፣ ለሀገር እድገት አስተዋፅኦው ከፍ ያለ ስለመሆኑ አረጋግጦ ነው። በእሳቤያችን ተመርተን በትክክለኛው መንገድ ተጉዘን የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የጀመርነው ውጥን ተዓምር የሚመስሉ ስኬቶችን እያስመዘገበ ቀጥሏል። ዛሬ ክ/ከተማችን ኮልፌ የገነባቸውን ፕሮጀክቶች አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ያደርጋል። አንድ ሆነን፣ ተደማምጠን፣ ጠንክረን፣ ተዋደን እና ተፋቅረን በወንድማማችነት/ እህትማማችነት መንፈስ ከሰራን ያሳብነውን ያቀድነውን ማሳካት ይቻለናል። ሁላችንም በተሰማራንበት ዘርፍ ውጤት በማስመዝገብ ኢትዮጵያን እናበልፅግ!
መልካም ቀን ይሁንለዎ!
#Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና
1 671
የሀገር ከፍታ የሚረጋገጠው በዜጎች በመስራትና በማምረት ብቃት ነው። ዜጎች አምራች ዜጋ ሲሆኑ የግል ፍላጎት አሟልተው ለሌላው መትረፍ ይችላሉ።
መልካም ቀን ይሁንለዎ!
@Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና
1 671
የጀግንነት መለኪያው ሀገር ወዳድነት ነው። የሀገር ወዳድነት መገለጫው ለሀገር ብሎ የሚከፈል ዋጋ ካለ እንኳን ለመክፈል መዘጋጀት መቻል ነው። የሀገር ወዳድነት መገለጫ ሀገር የሚያበለፅግ መንገድን መከተል ነው። ታሪክ ሀገር ወዳድ የሀገር ባለውለታ ጀግኖችን ከፍ አድርጋ ታወሳለች። አሰላለፍህ እኔ ካልሆንኩ ለአሳር በሚል የመጣውን ውጤት ሁሉ ጥላሸት ቀብተህ የምታቀርብ ከሆነ፣ ሀገርን የሚጎዳ ነገር ሁሉ ካደረክ ቅንጣት ታክል ሀገር ወዳድነት የለህም ማለት ነው። አንዳንዶች ሀገር የሚጎዳ ሀሳብ ላይ ተጠምደው ሀገር ወዳድ ነኝ ለማለት ይሞክራሉ። ሀገር የሚወድ ህይወት አሳልፎ እስከመስጠት ሆኖ ሳለ የፖለቲካ አተያይ ልዩነት ስላለ እኔ ካልሆንኩ ትፍረስ ካለ እንደት ሀገር ወዳድ ሊሆን ይችላል። ኢትዮጵያ ብዙ የሚወዷት ልጆች ያሏት ሀገር ነች። በሀገር አንድነት ክብር ሉዓላዊነት ሲመጣ መስዋዕትነት ከመጣ እንኳን ለመክፈል ዝግጁ ልጆች እንዳሏት አይተናል። እኛ ኢትዮጵያዊያን ሀገር ወዳድነታችንን ኢትዮጵያን በማበልፀግ ክብሯን በመጠበቅ እንግለፀው።
መልካም ቀን ይሁንለዎ!
@Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና
1 671
ሰላም ለሁሉ ነገር አስፈላጊ ነው። ሰላም ወጥቶ መግባትን፣ ሰርቶ መበልፀግን፣ አስተምሮ ማስመረቅን፣ በልጅ ወግ ማዕረግ ማየትን የምናገኘው በሰላም ነው። ሰላም ከሀገር መኖር ጋር ይያያዛል። የሰላም መስፈን የሀገርን ክብር ያስጠብቃል። የጎደለውን ለመጠየቅ ሰላም ያስፈልጋል። ለተመዘገበው ውጤት ለማመስገን እንኳን ሰላም ያስፈልጋል። የሀገርን ሰላም መጠበቅ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው። ሰላም ባልተረጋገጠበት ሀገር ውስጥ መብት አይኖርም። መብት በማይጠበቅበት ሀገር ውስጥ ተጠቃሚነት የለም። ተጠቃሚነት ከሌለ እድገትን ማምጣት አንችልም። የራስን ግደታ ስንወጣ ሰላማችንን ስንጠብቅ ሀገር ማበልፀግ እንችላለን። በሀገር መበልፀግ ውስጥ ተጠቃሚነት አለ። በተጠቃሚነት ውስጥ ፍትሃዊነትን ማረጋገጥ እንችላለን። ፍትሃዊ ስንሆን መብት እናከብራለን ግደታ እንወጣለን። ሁላችንም የግል ኃላፊነታችንን በመወጣት ኢትዮጵያን እናበልፅጋት!
መልካም ቀን ይሁንለዎ!
@Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና
1 671
ፓርቲያችን ብልፅግና የትናንት ወረቶችን የበለጠ የሚያበለፅግ፣ ጠብቆ እና ተንከባክቦ በወረትነት ከመያዝ ባለፈ ለማካበት የሚሰራ ፓርቲ ነው።
መልካም ቀን ይሁንለዎ!
@Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና
1 671
ብልፅግና ቃሉን በተግባር የሚያውል ሰው ተኮር ፓርቲ ነው!
ፓርቲያችን ብልፅግና ከሁሉም ነገር በፊት ሰው ይቀድማል የሚል ፓርቲ ነው። ሰው ይቀድማል የሚለው ፓርቲያችን ብልፅግና በሀሳብ ብቻ አይደለም በተግባሩ ጭምር እንጂ።
በሰው ተኮር ስራችን በርካታ ተግባራት ተፈፅመዋል። በተለይ በ90 ቀናት የስራ እቅድ ፕሮጀክቶቻችን በሙሉ ሰው ተኮር ናቸው። ማንም ሰው በቀን አንድ ጊዜ መመገብ አቅቶት እንዳይውል ምንም ረዳት ከሌላቸው በቀን አንድ ጊዜ መመገብ ካቃተቸው ዜጎች መራብ ስሌለባቸው 18 የመመገቢያ ፕሮጀክቶች ተሰርተው ተመርቀው ዜጎችን በማገልገል ላይ ናቸው።
በዝቅተኛ ገቢ ላይያሉ ዜጎቻችን አቅመ ደካማ እና አረጋዊያን የቤት ችግራቸው ይቀረፍ ዘንድ በ90 ቀናት ቤት ተገንብቶ ብዙ ዜጎችን የቤት ባለቤት ማድረግ ተችሏል።
ኢትዮጵያ ከልጆቿ አልፎ ለሌሎች የሚተርፍ ሀብት ያላት ሀገር ነች። ከእኛ የሚጠበቀው ያላትን ሀብት በአግባቡ እና በፍትሀዊነት ጥቅም ላይ ማዋል ነው። ለእንደዚህ አይነት ስራ ደግሞ መሪ በአግባቡ አስተባብሮና መርቶ ውጤት ማምጣት ግድ ይለዋል።
የአዲስ አበባ አስተዳደርም ይህንኑ በፓርቲያችን እሳቤ፣ በጠንካራ እና አርቆ አሳቢ መሪዎች እውን እየሆነ ይገኛል።
ከዚህ ቀደም 90 ቀናት ማለት ፕሮጀክት ለመስራት ታቅዶ እቅዱ የማይጠናቀቅበት ለመሠረት ድንጋይ ማስቀመጥ እንኳን የሚያጥርበት ነበር። አሁን ግን ብልፅግና ፓርቲ አሻራ አስቀምጦ የማለፍ ውጥን ይዞ ይህንን ማሳካት የሚችሉ መሪዎችን አሰማርቶ ህዝብን የልማት ባለቤት በማድረጉ 90 ቀናት ማለት ህንፃ ተገንብቶ ለነዋሪዎች የሚተላለፍበት ሆናል።
ሰው ተኮር ተግባሬችን የዝቅተኛ ገቢ እና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉ ዜጎች የሚጠቀሙበትን በርካታ ዳቦ ፋብሪካዎች እውን አድርጓል። እያንዳንዱ ፕሮጀክት ሲታይ የስራ እድል በመፍጠር ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል።
ከተባበርን አንድ ሆነን ከሰራን አርቀን ካለምን ዛሬውኑ ያለምነውን ለማሳካት ከጀመርን የማይሳካ አላማ አይኖረንም። ሁላችንም በወንድማማችነት/ እህትማማችነት አንድ ላይ ሆነን እጅ ለእጅ በመያያዝ ኢትዮጵያን ለማበልፀግ እንትጋ!
መልካም ሳምንት ይሁንለዎ!
@Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና
1 671
በየዘመናቱ የምንኮራባቸው ታሪኮች ተሰርተዋል። ያለፍ ጠቃሚ ታሪኮቹን ጠብቆ፣ በደረሱበት ዘመን የራስን አኩሪ ታሪክ መስራት ግድ ይላል።
መልካም ቀን ይሁንለዎ!
@Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና
1 671
አንድ ስንሆን ስንደመር ለጠላት አስፈሪ፣ ለወዳጅ የኩራት ምንጭ ለኢትዮጵያ መከበሪያዋ ሰርተው የሚያበለፅጓት ልጆቿ እንሆናለን።
መልካም ቀን ይሁንለዎ!
@Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና
1 671
ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ነች። አሁን ሀያል ከሚባሉት ብዙዎቹ ሀገር ሳይሆኑ ሀገር የሆነች። የመንግስት ትርጉም ሳይገባቸው መንግስት ያዋቀረች የጥንተ ስልጣኔ ባለቤት ነች ኢትዮጵያ። ትናንት ትልቅ የነበረች ሀገር ካለችን ደግሞ ዛሬም ወደ ታላቅነቷ የፊት መሪነቷ ለመመለስ ሀብቱም ልጆቿም አለን። የሚጠበቅብን ትናንትን አስበን መሠረቱን ማሳመር ነገን አስበን ዛሬን መስራት ነው። ዛሬ በሰራነው ነገን ማሳመር ይቻለናል። ዛሬን በትብብር ሁላችንም ሀገራችንን ለማበልፀግ ከሰራን ነገ ብሩህ ሆኖ ማየታችን አይቀሬ ነው። ዛሬን በመትጋት ነገን እናሳምር!
መልካም ቀን ይሁንለዎ!
@Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና
1 671
ኢትዮጵያ በጋራ የምንገነባት የጋራ ቤታችን ነች። ኢትዮጵያ ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ ጫፍ ከምዕራብ ጫፍ እስከ ምስራቅ ጫፍ በህብረ ብሔራዊነት ተውባ፣ በተለያዩ የተፈጥሮ ሀብቶችና ፀጋ የተንቆጠቆጠች ሀገር ነች። ከእኛ ከልጆቿ የሚጠበቀው ወንድማማችነትን/ እህትማማችነትን አጠናክረን በፍቅር በመከባበር ሀሳብ አዋጥተን በጋራ ሰርተን ማበልፀግ ነው። አንድ ስንሆን ስንደመር ለጠላት አስፈሪ፣ ለወዳጅ የኩራት ምንጭ ለኢትዮጵያ መከበሪያዋ ሰርተው የሚያበለፅጓት ልጆቿ እንሆናለን። አንድነታችንን አጠናክረን የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናድርግ!
መልካም ቀን ይሁንለዎ!
@Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና
1 671
የወል እውነታችንን ጠንካራ ማድረግ የተሻለ ነገን ለመገንባት ይጠቅማል። ሀገር የወል እውነታችን ነች የወል እውነታ የሆነችውን ሁላችንም ተባብረን ለልጆቻችን ምቹ እናድርግ። ዛሬን ብሩህ ማድረግ የምንችለው እኛው ነን የዛሬን ብሩህነት ለነገ የበለጠ ብሩህ እንድሆን እንስራ!
መልካም ቀን ይሁንለዎ!
@Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና
1 671
ዛሬ ኢትዮጵያ ጥሪ ያቀረበችበት ቀን ነው። ልጆቿ የራሳቸውን ሪከርድ እንድሰብሩ ጥሪ አስተላልፋለች። ጥሪዋን ተቀብለን አረንጓዴ እናልብሳት። የልጆቻችንን የነገ ተስፋ አለምልመን አይናቸው በተስፋ ተሞልቶ ነጋቸው ብሩህ መሆኑን የሚረጋገጥበት አረንጓዴ አሻራችንን ሐምሌ 10/2015 ዛሬ በስራ መጀመሪያው እለት እናሳርፍ።
መልካም ቀን ይሁንለዎ!
@Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና
