en
Feedback
Kolfe P.P - ብልፅግና

Kolfe P.P - ብልፅግና

Open in Telegram
1 671
Subscribers
No data24 hours
-177 days
-8030 days
Posts Archive
የኢትዮጵያ ከፍታ ሚስጥር የህዝቦቿ አንድነት፣ የመሪዎቿ ጥበብ፣ የመሬቷ ምቹነት፣ ብዝሃነት በወንድማማችነት/ እህትማማችነት የታሰረ አንድነት በመያዙ ነው። ኢትዮጵያ ታላቅ ገድል ያላት ትልቅ ሀገር ነች
የኢትዮጵያ ከፍታ ሚስጥር የህዝቦቿ አንድነት፣ የመሪዎቿ ጥበብ፣ የመሬቷ ምቹነት፣ ብዝሃነት በወንድማማችነት/ እህትማማችነት የታሰረ አንድነት በመያዙ ነው። ኢትዮጵያ ታላቅ ገድል ያላት ትልቅ ሀገር ነች። ከለውጡ ወድህ እየመጣ ያለው ኢኮኖሚያዊ እድገት በችግርም ውስጥ ሆኖ አለም እየታመሠ ባለበት በመሆኑ አለምን አስደምሟል። አለም አቀፋዊ ሁኔታው የተረጋጋ ቢሆንና የገጠሙ ችግሮች ባያጋጥሙ ኖሮ አሁን የመጣው ውጤት በስንት እጥፍ ሊጨምር እንደሚችል ታሳቢ ማድረግ ያስችላል። ጥያቄዎቻችንን፣ ችግሮቻችንን መንግስት እያመቻቸ ባለው በንግግር፣ በመድረክ፣ በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር ያስፈልጋል። ካልሆነ የምንወዳት ሀገራችን ኢትዮጵያ ለመበልፀግ ተንደረደረች ስንላት እየተደናቀፈች ባለችበት ስሟ ከሚመጥናት በታች በድህነት እየተጠራች እንድትቆይ ያደርገጋል። ሁላችንም የግልም ሆነ የቡድን ኃላፊነታችንን በመወጣት የበለፀገች፣ ዘላቂ ሰላም ያረጋገጠች፣ ምቹ፣ ውብ፣ አረንጓዴ ኢትዮጵያን እውን እናድርግ! መልካም ቀን ይሁንለዎ! @Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና

እኛ ኢትዮጵያዊያን በመነጋገር በመወያየት በሀሳብ የበላይነት ማመን አለብን። ውይይት ሀሳብ የማዋጣት ጉዳይ ነው። እኔ በዚህ መንገድ አስቤ ነበር አንተ ምን ትላለህ። አንች የተሻለ አማራጭ ካለሽ አዋጭ
እኛ ኢትዮጵያዊያን በመነጋገር በመወያየት በሀሳብ የበላይነት ማመን አለብን። ውይይት ሀሳብ የማዋጣት ጉዳይ ነው። እኔ በዚህ መንገድ አስቤ ነበር አንተ ምን ትላለህ። አንች የተሻለ አማራጭ ካለሽ አዋጭ ማለት ነው። ከመወያየቱ በኋላ የተሻለው ሀሳብ ብዙዎቹን ገዝቶ የሚተገበርበት። የእኔ ብቻ ካልሆነ የሚለው ሀሳብ አይጠቅምም። ዘመኑን የዋጀ ከእኛ የተሻለውን ሀሳብ እንዳንቀበል ዝግ ያደርግና ወደ ኋላ ብቻ ተነጥለን የሀሳባችን እስረኛ ሆነን እንድንቀር ያደርጋል። ስለዚህ በመወያየት፣ በሀሳብ የበላይነት፣ በሀሳብ አሸናፊነት ማመን ይገባናል። በሀሳብ የበላይነት ኢትዮጵያን እናበልፅግ! መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና

እኛ ኢትዮጵያዊያን በተሰለፉበት ሁሉ አሸናፊዎች ነን። በቦዳፔስት እየተካሄደ ባለው የ19ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊያን በ10,000 ሜትር የሴቶች ውድድር ከ1 እስከ 3ኛ ደረጃ ይዘው
+2
እኛ ኢትዮጵያዊያን በተሰለፉበት ሁሉ አሸናፊዎች ነን። በቦዳፔስት እየተካሄደ ባለው የ19ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊያን በ10,000 ሜትር የሴቶች ውድድር ከ1 እስከ 3ኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። ጉዳፍ ፀጋዮ የወርቅ፣ ለተሰንበት ግደይ የብር፣ እጅጋየሁ ታዬ የነሃስ ሜዲያሊያ ለሀገራቸው አስገኝተዋል። በአንድ ሩጫ 3 ሜዲያሊያ ለኢትዮጵያ ! አረንጓዴው ጎርፍ ዛሬም ተደግሟል። እንኳን ደስ ያላችሁ! ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!

የዘላቂ ሰላም ግንባታ እንዲሳካ አብሮነታችንን የበለጠ ማጠናከር ይጠይቃል። ኢትዮጵያዊነት ብዙ ማንነቶች አንድ ላይ ሆነው በውብ ህብረ ብሔራዊነት የተገነባ ማንነት ነው። ውብ ህብረ ብሔራዊነታችን በኢት
የዘላቂ ሰላም ግንባታ እንዲሳካ አብሮነታችንን የበለጠ ማጠናከር ይጠይቃል። ኢትዮጵያዊነት ብዙ ማንነቶች አንድ ላይ ሆነው በውብ ህብረ ብሔራዊነት የተገነባ ማንነት ነው። ውብ ህብረ ብሔራዊነታችን በኢትዮጵያዊ አንድነት ውስጥ ገዝፎና በግርማ ሞገስ የተሞላ ማንነት ነው። ኢትዮጵያዊነት ሲነሳ አልገዛ ባይነት፣ አሸናፊነት፣ ተምሳሌትነት አብሮ ይነሳል። መልካም ቀን ይሁንለዎ! @Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና

ብልፅግና በሁላችንም ትጋት፣ ትብብር፣ ያለረፍት መስራት፣ ትክክለኛውን መንገድ መከተል የሚሳካ ነው። ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግናዋ መረጋገጥ አለበት። ሁለንተናዊ ብልፅግና ደግሞ በምኞት አይመጣም በተ
ብልፅግና በሁላችንም ትጋት፣ ትብብር፣ ያለረፍት መስራት፣ ትክክለኛውን መንገድ መከተል የሚሳካ ነው። ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግናዋ መረጋገጥ አለበት። ሁለንተናዊ ብልፅግና ደግሞ በምኞት አይመጣም በተግባር እንጂ። የተጀመሩ በርካታ የብልፅግና ስራዎች አሉን። ያሳካናቸው በርካታ ስራዎች አሉን። የተሳኩትን ወረት በማድረግ የቀሩንን ትኩረት እየሰጠን መስራተት ይጠይቃል። ሁላችንም ለሀገራችን ብልፅግና እንትጋ! መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party-በልፅግና

መሪነት መዳረሻውን ቀድሞ በማየት ህዝብን ለመዳረሻው እንድሰራ ማሰለፍ ነው። መሪነት ሰርቶ ዓርዓያ በመሆን ሌሎች እንድከተሉ ማድረግ ነው። መሪነት ትክክለኛውን ጉዳይ በትክክለኛው ጊዜ እና ሰዓት መተግ
መሪነት መዳረሻውን ቀድሞ በማየት ህዝብን ለመዳረሻው እንድሰራ ማሰለፍ ነው። መሪነት ሰርቶ ዓርዓያ በመሆን ሌሎች እንድከተሉ ማድረግ ነው። መሪነት ትክክለኛውን ጉዳይ በትክክለኛው ጊዜ እና ሰዓት መተግበር መቻል ነው። መንገዱን ያሳያል በመንገዱ ይጓዛል እንድከተሉትም ያደርጋል። የእኛ መንገድ መደመር ነው፤ ማግለል የሌለበት፣ ነገውን ቀድሞ ያየ፣ ሁሉንም የሚያሰልፍ፣ በሁሉም፣ ለሁሉም፣ ከሁሉም የሆነን የዲሞክራሲ ስርዓት እየገነባ ያለ፣ መዳረሻውን ሁለንተናዊ ሀገራዊ ብልፅግና ያደረገ ነው። ሁላችንም ጉዟችን በመንገዳችን መደመር ካደረግን ሁለንተናዊ ብልፅግና ስኬት አይቀሬ ነው። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና

መከላከያ ለኢትዮጵያ አንድነት ዋልታና ማገር! መከላከያ ብሔር የለውም የአንድ ብሔር ወይ የአንድ እምነት ጠበቃ ያልሆነ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃይልና ጉልበት ነው። መከላከያ ቤቱ እና መኖሪያው ዱር እና ገደሉ ነው። መኖሪያውን ዱር ገደል የሚያድረው ደግሞ የሚወዳት ኢትዮጵያ አንድነቷን ጠብቃ፣ ዳር ድንበሯ ተከብሮ፣ ሉዓላዊነቷ ሳይነካ፣ ታፍራ እና ተከብራ እንድትኖር ነው። የመከላከያ ክብሩ የኢትዮጵያ መከበር ነው። መከላከያ ከኢትዮጵያ በታች የሚመጥነው ምንም ሰፈር የለም ምንም ብሔር የለም ልኩ ኢትዮጵያ ነች። የጀግንነት መለኪያ፣ የኢትዮጵያዊያን ኩራት፣ የአንድነታችን ምሰሶ የመጨረሻው የሀገር ጋሻና መከታ ነው። በስነ - መግባሩ የተመሰከረለት፣ በጀግንነቱ የምንኮራበት፣ በህዝባዊነቱ ደህንነት ሰላም እንድሰማን የሚያደርግ፣ በግርማ ሞገሱ ጠላት የሚያርድ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ነው። መከላከያ የሚጠብቀው ሀገርን ነው። የሚዋደቀው የሚሞተው የሚንገላታው ለህዝብ አንድነት፣ ለህዝብ ሰላም ሲል ነው። ለመተቸት የማይመች ከኢትዮጵያ አልፎ በአሀጉረ አፍሪካም ሆነ በዓለም አደባባይ የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት በህዝባዊነት በጀግንነትና በልበ ሙሉነት መፈፀም የቻለ የኩሩ ጀግና ህዝብ ልጅ ነው። እኛ ኢትዮጵያዊያን በኩራት ከምንናገርላቸው ተቋማቶቻችን መካከል መከላከያችን ነው። የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያን ሰራዊት በሙሉ ልብ የምናመሰግነው ለእኔ ለግሌ የሚለው ነገር የማይፈልግ በዓለም ላይ ዳግም የማይገኘውን እጅግ ውዱን በምንም የማይተካውን ህይወቱን የሚሠዋላት ሀገሩ ብቻ ነች። ለሀገሩ ለኢትዮጵያ ሲል ግን በምንም ዋጋ ዳግም የማይተካውን ህይወቱን ይሰጣታል። መከላከያ ክብራችን፣ ኩራታችን፣ የመጨረሻው የሀገር ጠባቂ ሀይላችን ነው። ሁላችንም ለሀገር መከላከያ ሰራዊታችን የሚገባውን ክብር መስጠት ይኖርብናል። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና

ኢትዮጵያ በህብረ ብሔራዊነት የደመቀች ሀገር ነች። ህብረ - ብሔራዊ አንድነት በወንድማማችነት/ እህትማማችነት የተሳሰረ ማንነት ነው። አንዱ ለአንዱ ደጀን የሚሆንበት ጥላ ከለላው የሚሆንበት ወንድማማች
ኢትዮጵያ በህብረ ብሔራዊነት የደመቀች ሀገር ነች። ህብረ - ብሔራዊ አንድነት በወንድማማችነት/ እህትማማችነት የተሳሰረ ማንነት ነው። አንዱ ለአንዱ ደጀን የሚሆንበት ጥላ ከለላው የሚሆንበት ወንድማማችነት/ እህትማማችነት ነው። በወንድማማችነት እህትማማችነት መንፈስ አንድ ሆነን የሁላችንም ቤት ሀገራችንን ኢትዮጵያን እናበልፅጋት! መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና

እኛ ኢትዮጵያዊያን ህዝባችን ዘመናዊ የፍትህ የፀጥታ አካላት ከመኖራቸው በፊት ሰላሙን እና ፀጥታውን የማስከበር ባህል ነበረው። በዚህ መልኩ ሰላሙን የጠበቀ ፀጥታውን ያስከበረ መሆኑን ስናይ ህዝባችን
እኛ ኢትዮጵያዊያን ህዝባችን ዘመናዊ የፍትህ የፀጥታ አካላት ከመኖራቸው በፊት ሰላሙን እና ፀጥታውን የማስከበር ባህል ነበረው። በዚህ መልኩ ሰላሙን የጠበቀ ፀጥታውን ያስከበረ መሆኑን ስናይ ህዝባችን በሙሉ ኃይሉ እና ፍላጎቱ ከሰራ ከምንም በላይ የህግ የበላይነትን የሚያስከበር ይሆናል። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና

ሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ ኢትዮጵያን ለማበልፀግ ይፈልጋል። ከልቡ ማበልፀግን የፈለገ ደግሞ የፈለገው እንድሳካ ወደ ተግባር ይገባል። ሁላችንም ስራ ላይ በማተኮር ኢትዮጵያን ለማበልፀግ እንትጋ! መልካም
ሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ ኢትዮጵያን ለማበልፀግ ይፈልጋል። ከልቡ ማበልፀግን የፈለገ ደግሞ የፈለገው እንድሳካ ወደ ተግባር ይገባል። ሁላችንም ስራ ላይ በማተኮር ኢትዮጵያን ለማበልፀግ እንትጋ! መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና

የብዞች ቁጭት እልህ እና ተስፋ የነበረው የአባይ ወንዝ የተፈጠረለትን ምድር ባይታወርነት የቀየረው ይህ የእኛ ትውልድ ነው። ትውልዱ ታሪክ አንባቢ እና ነጋሪ ብቻ መሆን ሳይሆን የትናንት ታሪኩን ጠብቆ
የብዞች ቁጭት እልህ እና ተስፋ የነበረው የአባይ ወንዝ የተፈጠረለትን ምድር ባይታወርነት የቀየረው ይህ የእኛ ትውልድ ነው። ትውልዱ ታሪክ አንባቢ እና ነጋሪ ብቻ መሆን ሳይሆን የትናንት ታሪኩን ጠብቆ ዛሬም ታሪክ መስራትን የሚችል መሆኑን እያስመሰከረ ይገኛል። የፓርቲያችን ብልፅግና ዋና አላማ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው፤ ይህንንም ለማሳካት መላው ህዝብን አሳትፎ በመስራት ላይ ይገኛል። በወንድማማችነት መርህ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ጠብቀን የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በጋራ እንትጋ! መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና

ብልፅግና ኢትዮጵያን ከፍ ለማድረግ የሚሰራ፣ ኢትዮጵያዊያን ወንድማማችነታችንን/ እህትማማችነታችንን አጠናክረን ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ማጠናከር አማራጭ የሌለው ምርጫ እንደሆነ ያምናል። በተግባር
ብልፅግና ኢትዮጵያን ከፍ ለማድረግ የሚሰራ፣ ኢትዮጵያዊያን ወንድማማችነታችንን/ እህትማማችነታችንን አጠናክረን ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ማጠናከር አማራጭ የሌለው ምርጫ እንደሆነ ያምናል። በተግባር በወንድማማችነት መርህ የሚሰራ በርካታ ስኬቶችን እያስመዘገበ ያለ ፓርቲ ነው። አንድነታችንን አጠናክረን፣ ሰላማችንን በጋራ አስጠብቀን፣ ዘላቂ እና ፍትሃዊ ልማት እውን በማድረግ የኢትዮጵያን ከፍታ በጋራ እውን እናድርግ! መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና

ሁለንተናዊ ሀገራዊ ብልፅግናን ለማሳካት ሁሉም ድርሻ አለው። ሁሉም ድርሻውን ሲወጣ ሀገራዊ ብልፅግና ይሳካል። አፍሪካ ከራሷ የተረፈ አለምን ሀብታም የሚያደርግ ተፈጥሮ ሀብት ያላት አሀጉር ናት። ነገር ግን በድህነት፣ በጉስቁልና የምትታወቅ ሀብት ላይ ተኝታ ስንዴ የምትለምን አሀጉር ነች። ኢትዮጵያም ለብዙ አመታት ከዚህ የተለየ እጣ ፋንታ አልነበረንም። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ መውጣት የተጫወተችው ትልቅ ሚና አለ። አድዋ ላይ ድል አድርጋ አልገዛም ባይ የድል አድራጊነት በዓል የምታከብር ሀገር ነች። አፍሪካዊያን ማሸነፍ ይቻላል ለካ ብለው የተነሳሱበት የነፃነት ቀን እንዳከብሩ እድል ያገኙበት ምክንያት ሆነናል። አሁን ደግሞ ስንዴን አምርቶ ከራስ ፍጆታ ተሻግሮ ለውጭ ገበያ ለማትረፍ በቅተናል። ይህም ሀብት ላይ ተኝቶ ስንዴ ለሚለምነው የንቃ ይቻላል ጥሪ ነው። ሀብት ደጅህ አለ የሚጠበቀው ሀብቱን ከስንፍና እና እርስ በእራስ ግጭት ወጥተን ሰላምን አስፍነን ቀን ሌት በመስራት ሀብታችንን እንጠቀም ነው። የተትረፈረፈ ተፈጥሮ ሀብት፣ መስራት የሚችል፣ የተማረ፣ ወጣት የሰው ኃይል ያላት አሁጉራችን ከልመና ወጥቶ ለጋሽ ለመሆን አልሞ እና አቅዶ መስራት የተጠመደውን የጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ በንጅ ማምከን ነው። ኢትዮጵያ በብዙ ውስብስብ ችግሮች ውስጥ ሆና ለማመን የሚከብዱ ስኬቶችን አስመዝግባለች። የአፍሪካ ችግር በአፍሪካዊ መፍትሄ የምትለዋ ኢትዮጵያ ለመጡ ውጤቶች ትልቁ ምክንያት ሀገር በቀል እሳቤ በብልህ መሪዎቿ ውጤት አምጥታ አሳይታለች። አሁንም የሚገጥሟትን ውስብስብ ችግሮች እየፈታች ለአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት የሚሆኑ ስኬቶቿን ማስመዝገብ ትቀጥላለች። አፍሪካ ያላትን ሀብት በልጆቿ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በማድረግ ብልፅግናዋን እውን ታደርጋለች። ኢትዮጵያም ለአፍሪካ ተምሳሌትነቷን አጠናክራ እንደ ትናንቱ አልገዛም ባይነትን ለአፍሪካ እንደሰጠች ሁሉ ድህነት በቃ ብላ ብልፅግናን እውን የማድረግ የመሪነት ሚናዋን ትወጣለች። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና

በኢትዮጵያ ለመጣ ሁሉ የማንበረከክ የጀግንነት ማሳያ ልክ መከላከያ ሰራዊት ነው! የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገር ፍቅር መገለጫ ለሀገሩ ሟች በሀገር ለመጣበት ህይወቱን ለመስጠት የማይሰስት ኩሩ ጀ
በኢትዮጵያ ለመጣ ሁሉ የማንበረከክ የጀግንነት ማሳያ ልክ መከላከያ ሰራዊት ነው! የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገር ፍቅር መገለጫ ለሀገሩ ሟች በሀገር ለመጣበት ህይወቱን ለመስጠት የማይሰስት ኩሩ ጀግና ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከኢትዮጵያዊነት በታች ባሉ ትንንሽ ቦታዎች ላይ የማይገኝ ከፍ ያለ ስብዕና ባለቤት ነው። ከኢትዮጵያ ባለፈ በአፍሪካ ሰላም አስከባሪነቱ ስመ ጥር የተሰጠውን ሀገራዊ ሀላፊነት በላቀ ትጋትና ጀግንነት የሚፈፅም ነው። የኢትዮጵያ የመከበር ምንጭ የስርዓት አልበኛ እና ሰፈርተኛ መድሀኒት የሉዓላዊነታችን አስከባሪ መከላከያ ሰራዊታችን ነው። መከላከያ ሰራዊት ሀሩር አይበግረውም፣ ብርድና ቆፈኑ አያሸንፈውም ቤቱ የኢትዮጵያ መድር ተራራ ዳገቱ የኢትዮጵያ ክብር ነው። በኢትዮጵያ ለመጣ ህይወት አይሰስትም። ከጥንት እስከ ዛሬ የማይቀየር ጀግንነት፣ የማይቀየር የሀገር ፍቅር፣ የማይቀየር አሸናፊነት፣ የሰላም አስከባሪነት ገድል የተላበሰ ጀግና መከላከያ ሰራዊት ነው። መከላከያችን በብሔር አይጠብም፤ በሰፈር አይታሰርም፤ በአካባቢ አያንስም፤ የመከላከያ ልኩ ኢትዮጵያ ነች። ከኢትዮጵያዊነት የማይወርድ ማንነት የገነባ ስለ አፍሪካ ሀያልነት የሚሰራ ትልቅ ስብዕናን የገነባ ነው። መከላከያ የሀገር ፍቅሩን ለሀገሩ ሰላም ክብር ሲል ህይወቱን ሰውቶ ያፀናል። የጀግንነት ውሃ ልክ፣ በስነ - መግባር የታነፀ ለኢትዮጵያ ክብር ሁሉንም አይነት ዋጋ የሚከፍል ኢትዮጵያን የሆነ ተቋም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችን ነው። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና

ኢትዮጵያ ወደ ከፍታ እየገሰገሰች ብልፅግናዋን እያሳካች ያለች ሀገር ነች። ብልፅግናዋን ስታሳካ የህዝቧን ፍላጎት እያሟላች ሀገራዊ ጥንካሬዋን እያሳደገች ተሰሚነቷን እና ተፅኖ ፈጣሪነቷን እያሰፋች ትሔ
ኢትዮጵያ ወደ ከፍታ እየገሰገሰች ብልፅግናዋን እያሳካች ያለች ሀገር ነች። ብልፅግናዋን ስታሳካ የህዝቧን ፍላጎት እያሟላች ሀገራዊ ጥንካሬዋን እያሳደገች ተሰሚነቷን እና ተፅኖ ፈጣሪነቷን እያሰፋች ትሔዳለች። ሀገር በልጆቿ ትገነባለች። ዜጎች በሀገራቸው ይኮራሉ ይከበራሉም። በሀገር መከበር መኩራት እንዲኖር የውስጥ ሰላምን መጠበቅ ወሳኝ ነው። የውስጥ ሰላም ባልጠበቅን ቁጥር ደካማነት ይነግሳል፤ ለውጭ ጠላት መጋለጥ ይመጣል። ሁላችንም ሰላማችንን በመጠበቅ፣ ወንድማማችነትን/ እህትማማችነትን በማጠናከር ጠንካራ፣ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናድርግ! መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና

ኢትዮጵያ በህብረ ብሔራዊ ልጆቿ የደመቀች የታደለች ሀገር ነች። ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን በማጠናከር የኢትዮጵያን ከፍታ በጋራ እናረጋግጣለን። አንዱ ለአንዱ ጥላ ከለላ የሆነበት አንዱ ለአንዱ ኩራ
ኢትዮጵያ በህብረ ብሔራዊ ልጆቿ የደመቀች የታደለች ሀገር ነች። ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን በማጠናከር የኢትዮጵያን ከፍታ በጋራ እናረጋግጣለን። አንዱ ለአንዱ ጥላ ከለላ የሆነበት አንዱ ለአንዱ ኩራት የሚሆንበት ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት መጠንከር ሲችል ነው። ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን አጠናክረን ኢትዮጵያን እናበልፅጋት! መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና

ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ሁላችንም እንረባረብ! ዘላቂ ሰላም የሁሉንም ሰው ርብርብ ይፈልጋል። ለሀገር ዘላቂ ሰላም ሲባል ብዙ ዋጋ ይከፈላል። የሚያስከፍለውን የሰላም ዋጋ ከፍሎ ሰላሙን ዘላቂ ማድረግ የ
ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ሁላችንም እንረባረብ! ዘላቂ ሰላም የሁሉንም ሰው ርብርብ ይፈልጋል። ለሀገር ዘላቂ ሰላም ሲባል ብዙ ዋጋ ይከፈላል። የሚያስከፍለውን የሰላም ዋጋ ከፍሎ ሰላሙን ዘላቂ ማድረግ የሁሉንም ሰው ፍላጎት ተነሳሽነትና ተግባራዊ መልስ ይፈልጋል። እኛ ኢትዮጵያዊያን ዘላቂ ሰላም ለማስፈን አንድ ላይ ከቆምን ሁላችንም ስለሰላም አንድ አይነት አቋም ከያዝን ዘላቂ ሰላም ማስፈን ይቻለናል። ዘላቂ ሰላም ማስፈን ትርፉ ብዙ ነው። የሁሉም ኢትዮጵያዊ ህልም የሆነው ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚሳካው በዘላቂ ሰላም ውስጥ ነው። ሁላችንም ለዘላቂ ሰላም መስፈን ዘብ በመቆም የኢትዮጵያን ብልፅግና እውን እናድርግ! መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና

መሪነት አርዓያነት ነው። ራሱ ሰርቶ ሌሎች እንድሰሩት የሚያበረታታ ነው። መሪነት መዳረሻን አሳይቶ ለመዳረሻው ሁሉም ከጎኑ ቆሞ እንድሰራ ማስቻል ነው። አመራር በሁሉ ነገር ብቁ ሆኖ ህዝብ መምራት መቻ
መሪነት አርዓያነት ነው። ራሱ ሰርቶ ሌሎች እንድሰሩት የሚያበረታታ ነው። መሪነት መዳረሻን አሳይቶ ለመዳረሻው ሁሉም ከጎኑ ቆሞ እንድሰራ ማስቻል ነው። አመራር በሁሉ ነገር ብቁ ሆኖ ህዝብ መምራት መቻል አለበት። ሀገራዊ ብልፅናችንን ለማሳካት መሪ የሚወጣው ሚና ቀላል አይደለም። መሪ ሰርቶ የሚያሰራ፣ አሳክቶ አርዓያ የሚሆን፣ የሰነቀውን ራዕይ ህዝብ እንድጋራው የሚያደርግ ነው። መሪ ሚናውን ሲወጣ ሌላው ድርሻውን በመወጣት የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናድርግ! መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party-ብልፅግና