en
Feedback
Kolfe P.P - ብልፅግና

Kolfe P.P - ብልፅግና

Open in Telegram
1 671
Subscribers
No data24 hours
-177 days
-8030 days
Posts Archive
የመደመር ትውልድ ሀገራዊ አገልግሎትን እንደ ግዴታውና ኃላፊነቱ የሚቆጥር፤ ከሀገር ፍቅር በመነጨ ትጋትና ታታሪነት፤ በስፋትና በጥራት ሀገሩን የሚያገለግል ትውልድ ነው። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kol
የመደመር ትውልድ ሀገራዊ አገልግሎትን እንደ ግዴታውና ኃላፊነቱ የሚቆጥር፤ ከሀገር ፍቅር በመነጨ ትጋትና ታታሪነት፤ በስፋትና በጥራት ሀገሩን የሚያገለግል ትውልድ ነው። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ኢትዮጵያ የዳበረና የደረጀ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ላይ ትልቅ እሴት ያላት ሀገር ነች። እኛ ኢትዮጵያዊያን የቆየ የመረዳዳት ባህል ያለን ህዝብ ነን። ኢትዮጵያ የዘመናዊ አለም ኢንሹራንስን ማሰብ ሳይጀምር በእድር አማካይነት የመረዳዳት ባህልን ያዳበረች እሴቷ ያደረገች ሀገር ናት። በዘመኑ ለንብረት፣ ለህይወት፣ ለአካል ኢንሹራንስ መግባት የስልጣኔ መገለጫ የችግር ጊዜ ደራሽ አጋር መኖሩን ማረጋገጥ መቻል ነው። እድር ሲነሳ ስለ ኢትዮጵያዊያን አርቆ አሳቢነት የፋይናንስ አሰራርን ጠንቅቆ ቀድሞ መጠቀምን እርስ በእራስ መተማመን፣ መተጋገዝን፣ መረዳዳትን እንማራለን። በቀላሉ የማይታይ ትልቅ የማህበራዊ ፋይዳ የነበረው መሆኑን በቅጡ እንረዳለን። ኢትዮጵያዊያን የአንዱን ልጅ ሌላኛው ጎረቤቱ በያገባኛል መንፈስ፣ አስተምሮ፣ ተንከባክቦ፣ ቅጣት ካስፈለገም ቀጥቶ እንደራሱ ልጅ የሚያሳድግ ነው። እቁብን ካየን የቁጠባ ባህላችን ምን ያክል የተራቀቀ እና ያደገ እሳቤ የነበረን ህዝብ እንደነበርን እንረዳለን። በእቁብ ህግ ለቸገረው ቀድሞ በመስጠት ችግሩን እንዳቃልል፣ ለንግድ መነሻ ወረት እንዳገኝ፣ የንግዱ ማስፋፊያ ወረት እንዳይቸገር በአንድ በኩል ሁነኛ መፍትሔ የነበረ ነው። በሌላ በኩል ቁጠባን ያስተማረ ካለው ላይ ቀንሶ በማስቀመጥ የካበተ ወረት ለመያዝ የሚያስችል ብልሃት ነው። ኢትዮጵያዊያን በማህበራዊ ህይወት ከፍ ያለ ስብዕና ያለን መሆናችንን ያረጋግጣል። ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ላይ ያለንን የቆየ እና የካበተ እሴት በወረትነት በመጠቀም የበለፀገች ኢትዮጵያን እንገንባ። ኢትዮጵያ በሁለንተናዊ ረገድ ለማበልፀግ የሚቻለን መነሻ ወረት ብቻ ሳይሆን አንዳንዱ ዘርፍ ላይ የካበተ ወረት ያለን መሆናችንን መረዳት ይገባል። ሁላችንም የኢትዮጵያን አቅም በተረዳ እና በተዘጋጀ መንገድ በመስራት ሁለንተናዊ ብልፅግናን እውን እናድርግ። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

የሁለንተናዊ ብልፅግና ስኬት ዘላቂ ሰላም መስፈን ነው። ሰላም ሁሉም ይዘምርላታል። ሁሉም ይፈልጋታል። ሰላምን የማይፈልጉ በጣም ጥቂቶች ናቸው። ሰላም በፍላጎት ብቻ የሚሳካ አይደለም ሰላም ስራ ይፈልጋ
የሁለንተናዊ ብልፅግና ስኬት ዘላቂ ሰላም መስፈን ነው። ሰላም ሁሉም ይዘምርላታል። ሁሉም ይፈልጋታል። ሰላምን የማይፈልጉ በጣም ጥቂቶች ናቸው። ሰላም በፍላጎት ብቻ የሚሳካ አይደለም ሰላም ስራ ይፈልጋል። ሁላችንም ለሰላም በመስራት፣ ስለ ሰላም በማስተማር፣ ሰላማዊ በመሆን ዘላቂ ሰላምን እውን እናድርግ። መልካም ቀን ይሁንለዎ! Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚሳካው በሁሉም ዘርፍ በምናደርገው ርብርብ ነው። ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማሳካት ሁሉንም ዘርፍ መዳሰስ ተገቢውን ትኩረት መስጠት ተገቢ ነው። ከተማ ላይ የከተማ ግብር
የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚሳካው በሁሉም ዘርፍ በምናደርገው ርብርብ ነው። ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማሳካት ሁሉንም ዘርፍ መዳሰስ ተገቢውን ትኩረት መስጠት ተገቢ ነው። ከተማ ላይ የከተማ ግብርናን ትኩረት በመስጠት ትኩስና ጤናማ የግብርና ምርቶች ማምረት እንደሚቻል ታይቷል። የሌማት ትሩፋት ተግባራችን በርካታ ጀግና አምራቾችን ፈጥሯል። ለብዙዎች አዲስ አበባ ላይ የከተማ ግብርና ይቻላል ወይ የሚለውን ጥያቄ ተግባራዊ ምላሽ የሰጡ ውጤቶች ተገኝተዋል። የከተማ ግብርና ስራዎቻችን የኢትዮጵያ የብልፅግናዋ ስኬት ማሳያ ውስጥ አንዱ ነው። በክ/ከተማችን በከተማ ግብርናው ዘርፍ እየመጣ ያለውን ውጤት የበለጠ በማስፋት የአቅርቦት ችግር የሚቀርፍ የኑሮ ውድነቱን የሚያቃልል ስራ ጅማሮ ሁሉም አቀናጅቶ አደራጅቶ መቀጠል ይገባዋል። በሁሉም ረገድ ውጤት በማስመዝገብ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናድግ። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብፅግና

እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አቶ ሙሉጌታ ጉሉማ የብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ! አለም ከኢትዮጵያ በርካታ ልምዶችን ባህሎችን ወስዷል። ኢትዮጵያ በርካታ ልጆቿ ተባብረው በሰሩ ጊዜ ዘመን የማይሽረውን ታሪክ ሰርተው አልፈዋል። ሀገራችን ኢትዮጵያ ከኦሮሞ ልጆቿ የገዳ ስርዓትን ለአለም እንካችሁ ብላለች። የገዳ ስርዓት ትልቅ የዴሞክራሲ ስርዓት ነው። በገዳ ስርዓት ውስጥ በርካታ የዴሞክራሲ ተግባራት ይከወናሉ። ዴሞክራሲን ፈጥረናል የሚሉት ሀገራት ሳይፈጠሩ ኢትዮጵያ ልጆቿ በባህላቸው ውስጥ ፅኑ የዴሞክራሲን ፈጥረዋል። ለዚህም ነው ኢትዮጵያ ለአለም የዴሞክራሲ ልምምድን ሰጥታለች የምንለው። ኢሬቻ ከገዳ ስርዓት ውስጥ አንዱ ፈጣሪን የማመስገኛ ስርዓት ነው። ኢሬቻ እየተቃረበ ሲመጣ አባገዳዎች ፀብ ካለ አስታርቀው፣ በደል ካለ አስክሰው፣ ቂምን በርቅና ይቅርታ፣ በደልን በካሳ፣ አለመግባባትን በወንድማማችነትና እህትማማችነትን ተክተው ወደ መልካ ይሄዳሉ። በኢሬቻ ክብረ በዓል ላይ እጁ ንፁህ ያልሆነ፣ በውስጡ ቂም የያዘ አይገኝም። ኢሬቻ የምስጋና፣ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ የአንድነት ነውና። ኢሬቻ በሚከበርበት ቦታ ቂም እና ቁርሾ የለም። ደስታና ፍቅር ቦታውን ተክተው ሁሉም በአደባባይ ለፈጣሪው ምስጋናውን የሚያደርስበት ነው። በኢሬቻ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከሁሉም አቅጣጫ ወደሚከበርበት መልካ ይጓዛል። በአደባባይ አንድ ላይ በመገኘት በወንድማማችነት/ በእህትማማችነት በድምቀትም ይከበራል። ይህ የይቅር ባይነት የሰላም እሴት የሆነው ኢሬቻ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ትልቅ እሴት ነው። በማህበራዊ ዘርፍ አንድነትና መተሳሰብን መሠረት የሚያስይዝ በዓላችን ነው። በኢኮኖሚውም ቢሆን ኢረቻ በርካታ ጥቅም አለው። የአለም በዓል ሆኖ በዩኒስኮ በመመዝገቡ ቱሪስቶች እንዲገቡ እያደረገ ይገኛል። አንዳንድ ሀገራት በቱሪዝም ዘርፍ ኢኮኖሚያዊ ሀያልነት ፈጥረዋል። ኢትዮጵያ ደግሞ በርካታ የቱሪዝም ሀብቶች የታደለች ናት። የታደልነውን ሀብታችንን ለመጠቀም ደግሞ ይቅር ባይነት፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ አብሮነትና አንድነት ያስፈልገናል። የኢሬቻ በዓልም ይህንኑ እሴት ያጎናፅፈናል። የ2016 ኢሬቻ በዓልን የምናከብረው በ2015 በርካታ ስኬቶችን አስመዝግበን በበርካታ ውጤቶች ታጅበን ነው። እንደ ሀገር የህዳሴ ግድብ 4ኛ ዙር ሙሌት በስኬት ባጠናቀቅንበት፤ ትልቅ ፋይዳ ባለው የብሪክስ አባልነት ተቀባይነት ባገኘንበት ወቅት የምናከብረው ነው። በርካታ ስኬቶች ድሎች በማስመዝገባችን ላስመዘገብነው ድል ምስጋና መቸር ይገባል። ኢሬቻ ከክረምቱ ከጨለማው ከአስፈሪው ወቅት አልፈን ብርሃን ለሰጠን ፈጣሪ የምናመሰግንበት ነው። እኛም እንደ ሀገር በመንገዳችን ለይ፣ በብልፅግና ጉዟችን ላይ ልክ እንደክረምቱ የዝናባማ አስቸጋሪ ወቅት በርካታ እንቅፋቶች ሊገጥሙን ይችላሉ። ግን ክረምቱ አልቆ የብርሃኑ ወቅት እንደተካው ሁሉ እንቅፋቶች ተነስተው ስኬት እንደምናስመዘግብ ጥርጥር የለውም። በኢሬቻ ክብረ በዓል ክረምቱ አልፎ ብርሃን እንደሚመጣ እርግጠኛ እንደሆን ሁሉ፤ የኢትዮጵያን በሁለንተናዊ ረገድ እንደምናበለፅጋት አንጠራጠርም። ክረምቱ አስቸጋሪ ቢሆንም በክረምቱ መጠናቀቅ እርጥብ፣ ለምለም ሳር ይበቅላል። አካባቢው በአረንጓዴው ውበት ያሸበርቃል። አዝመራ ከቡቃያነት ወደ ማፍራቱ ወደ ምርት መስጠቱ ይንደረደራል። ኢሬቻ ፈተና ካለ ፈተናውን ስናልፈው ምስጋና ልናቀርብለት የሚገባው ስኬት እንዳለ ያስተምረናል። የበደለ ካለ በካሳ ማዳንን ያሳየናል። ቂም ያለበት ካለ በይቅር ባይነት ማስተማርን ያስተምረናል። እኛ ኢትዮጵያዊያን ያሉንን ሀብቶች ወረቶች ጠብቀን ተንከባክበን፣ እሴቶቻችን ጠብቀን ለትውልድ ማሳለፍ፣ ችግሩን በመፍትሔ፣ እንቅፋቱን በምቾት፣ ጨለማውን በብርሃን መተካት ግድ ይለናል። ህብረ -ብሔራዊ አንድነትን ስናጠናክር ደግሞ ሁሉንም ጉዳይ ማሳካት ይቻለናል። የ2016 ኢሬቻ በዓል ጥላቻን በፍቅር፣ ቂምን በይቅርታ፣ በደልን በካሳ የምናልፍበት ለተደረገልን የምናመሰግንበት ለሚቀረን እንዲሳካልን የምንሰራበት መሆን ይገባዋል። በ2016 በከተማችን አዲስ አበባ ለሚከበረው የኢሬቻ ክብረ በዓል በክ/ከተማችን ለሚገቡ የበዓሉ ታዳሚዎች ለመቀበል ዝግጁ ሆነናል። እንግዶቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ እያልን የክ/ከተማችን ወጣቶች ሰላም ሊያስከብሩ፣ እናቶች በእንኳን ደህና መጣችሁ ሊቀበሉ፣ መላው ነዋሪዎቻችን በዓሉን አብረው ሊያከብሩ በሙሉ ዝግጁነት ላይ ናቸው። በዓሉ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የይቅርታ፣ የእርቅና የምስጋና እንዲሆንልን እመኛለሁ። መልካም የኢሬቻ በዓል ይሁንልን!

ብሔራዊ መግባባት ማለት ወሳኝ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የአብዛኛው ሕዝብ ጥቅል ስምምነት መኖር ማለት ነው። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና
ብሔራዊ መግባባት ማለት ወሳኝ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የአብዛኛው ሕዝብ ጥቅል ስምምነት መኖር ማለት ነው። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ኢትዮጵያዊያን የሰላም ተምሳሌት የወንድማማችነት የእህትማማችነት መገለጫ የመሆናቸው ማሳያ በዓል ኢሬቻ ነው። ኢሬቻ የኢትዮጵያን የሰላም ተምሳሌትነት ይቅር ባይነትና አመስጋኝነት ማሳያ በዓል ነው። የሰ
ኢትዮጵያዊያን የሰላም ተምሳሌት የወንድማማችነት የእህትማማችነት መገለጫ የመሆናቸው ማሳያ በዓል ኢሬቻ ነው። ኢሬቻ የኢትዮጵያን የሰላም ተምሳሌትነት ይቅር ባይነትና አመስጋኝነት ማሳያ በዓል ነው። የሰላም፣ የአብሮነት፣ የይቅርታ፣ የፍቅር፣ የምስጋና በዓል የሆነውን ኢሬቻን በወንድማማችነትን በእህትማማችነትን ማክበር የእኛ መገለጫ ነው። ወንድማማችነትን እህትማማችነትን በማጠናከር አንድነታችን ፅኑ መሠረት እናስይዝ! መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ሀገር በትውልድ ይገነባል። ትውልድ በታሪክ ይወሳል። ኢትዮጵያ አሁን ላይ በሁሉም አንግል ትውልድ የሚያወሳው ታሪክ የማይረሳው የነገዎቹን ጥቅምና ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ ስራ እየተሰራ ይገኛል። ኢትዮጵያ
ሀገር በትውልድ ይገነባል። ትውልድ በታሪክ ይወሳል። ኢትዮጵያ አሁን ላይ በሁሉም አንግል ትውልድ የሚያወሳው ታሪክ የማይረሳው የነገዎቹን ጥቅምና ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ ስራ እየተሰራ ይገኛል። ኢትዮጵያ ስሟ ገናና ተፈጥሮ አዳልቶ የሰጣት የነገ ጉዞዋ ብሩህ ነው። ኢትዮጵያ ልጆቿ ዳር ድንበሯ እንዳይደፈር ነፃ ሀገር ሆና እንድትቀጥል ያደረገው ተጋድሎ የሚዘነጋ አይደለም። የአባቶቻችን ወኔ ጀግንነት በልጆችም የቀጠለ ነው ለሀገር ሲባል አንገት የሚሰጡ ጀግና ልጆች አሏት። ኢትዮጵያ ጥንት ከጀግንነት ተጨማሪ ያነፃት ያበለፀጋት ሀያል ያደረጋት ትውልድም አላት። በአሁኑ በእኛ ዘመን ገናና ታላቅነቷን የሚመጥን ከፍታ ላይ ለማድረስ ቀን ሌት የሚሰራ በአስፈለጋት ቦታ ሁሉ የሚሰለፍ ውጤት የሚያመጣ ትውልድ አፍርታለች። አሁን ያለው ትውልድ ዛሬን ብቻ የሚሰራ አይደለም ነገን ታሳቢ ያደረገ የነገዎቹን ጥቅምና ፍላጎት የሚያስጠብቅ እንጂ። የትናንት ትናንትን በደንብ ሲሰሩ የዛሬውን ጥቅምና ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ ስራ ከመስራት አንፃር የጎደለ ካለ ዛሬ ሞልተን የነገው ትውልድ በዋና ጉዳይ ላይ ጉድለት እንዳይገጥም የማድረግ አደራና ኃላፊነት እኛ ላይ ነው ያለው። ዛሬ የምንሰራው ለሀገር፣ ለትውልድ፣ ለነገ መሠረት መሆኑን በመገንዘብ መስራት ይጠይቃል። ሁላችንም በተሰለፍንበት የስራ ዘርፍ ሁሉ ውጤት በማስመዝገብ በሁሉም የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናድርግ! መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ኢትዮጵያ የታላቅ ህዝብ እናት፣ የጥንተ ስልጣኔ ባለቤት፣ ባህል ወግ ጠባቂ ሀገር ናት። ኢትዮጵያ ተደጋግሞ እንደሚባለው ታላቅ ሀገር ነች። ታላቅነቷን የሚያሳዩ ትልልቅ ታሪኮችን ለአለም እንካችሁ ብላለች። አንዳንድ ሀገራት ሀገር ሆነው ሳይፈጠሩ ሀገር መንግስት መስርታ የሀገረ መንግስትና ብሔረ መንግስት ግንባታውን ጥንት በተግባር የጀመረች ሀገር ነች። የጥንተ ስልጣኔዎቿን ስናወሳ በርካታ የሀያልነቷ ማሳያ የሆኑ ጉዳዮችን እናነሳለን። ኢትዮጵያ ከነበራት የግዛቷ ስፋት ተነስቶ ስለ ቅድመ ስልጣኔዋ ታሪክን ማውሳት ይቻላል። ምንም እንኳን አንዳንድ ሀገራት ደሞክራሲን ፈጠርን የሚሉ ሀገራት ቢኖሩም ኢትዮጵያ ግን ከጥንት እስከዛሬ የአባገዳ ስርዓትን ጠንቅቀን ካየን የእውነት የደሞክራሲ ፈጣሪ ሀገር ማን ነው የሚለው ምላሽ ያገኝ ይሆናል። በአባገዳ ስርዓት ሁሉም የደሞክራሲያዊ ስርዓትን እናያለን። የስልጣን ሽግግሩን፣ የስልጣን ቆይታውን፣ የስልጣን እርከኑን፣ የሁሉም የእድሜ ክልልና ፆታን ማዕከል ባደረገ መንገድ የሚሰጠውን የስራ ኃላፊነት ስናይ የደሞክራሲ ፈጣሪው ባለቤቱ የት እንደሆነ በእርግጥ እንረዳለን። በአባ ገዳ ስርዓት ውስጥ ካሉ ትልልቅ ክዋኔዎች ውስጥ የኢሬቻ ክብረ በዓልን እናገኛለን። የኢሬቻ ክብረ በዓል ደግሞ የምስጋና በዓል ነው። ሁሉን ላደረገው ፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት በዓል ኢሬቻ በዓል ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው ክረምቱ ከፍተኛ ዝናብ አለበት፣ ከፍተኛ ወጀብ ያስተናግዳል፣ በመብረቅ ይታጀባል፣ ቀኑ በደመናና በጉም በዝናብና ጉርምርምታ ይጨልማል። ይህንን ሁሉ በፈጣሪ ፍቃድ እና እርዳታ በሰላም እናልፋለን። ክረምቱም ሲያልፍ በመስከረም አበቦች ይፈነድቃሉ መልካዎች በለምለም ሳር ይሞላሉ፤ ሰብል ምርት ለመያዝ ያዘረዝራል፣ ያሸታል፣ መድረስ ይጀምራል። አእምሮ በተስፋ፣ አይን በብርሃን፣ ልብ በደስታ ሀሴት የምታደርግበት የደስታ ወቅት ይገባል። ይህንን ተከትሎ በአባ ገዳ ስርዓት ክረምቱን በሰላም ላሳለፈን ፈጣሪ የጠራ ሰማይ ያማረ ምድር ለማየት የበቃንበት ወቅት ላሳየን ፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት ስርዓት ኢሬቻ ነው። ኢሬቻ በፍፁም ቂም ተይዞ አይኬድበትም፣ በፍፁም ጥላቻ የለም፣ ፍፁም ሰላም ይሰፍናል፣ ጥል ካለ በእርቅ፣ ቂምና ቅሬታ ካለ በይቅርታ፣ በደል ካለ በካሳ ቀድሞውኑ በዓሉ ከመድረሱ በፊት ይተካካሉ። የበዓሉ እለት ያለው ደስታ ምስጋና ሰላም መተሳሰብ ለቀጣዩ በተስፋ ፈጣሪን መለመን ላለፈው ምስጋና ማቅረብ ነው። ኢሬቻ ይህን የመሰለ እና ሌሎች ያልተጠቀሱ በርካታ ወርቃማ ስርዓቶችን የያዘ የምስጋና በዓል ነው። አባ ገዳዎች፣ ሀደ ስንቄዎች፣ ፎሌዎች በአባገዳ ስርዓት መሰረት የተጣለባቸውን ሀላፊነት እየተወጡ እርጥብ ሳር ተይዞ ከክረምት ድፍርስነት በጠራ ወንዝ አካባቢ በመገኘት ምስጋና ይቀርብበታል። ኢሬቻ የአብሮነታችን ማሳያ ወንድማማችነትን እህትማማችነትን የምናጠናክርበት የሰላም የምስጋና በዓል ነው። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ሀገር በልጆቿ ጥንካሬና ብርታት በትብብር እና በመደመር አቅማቸው ልክ ትበለፅጋለች። የሀገር ብልፅግና የሚወሰነው በዜጎች ጠንካራ የመበልፀግ ፍላጎተትና ተግባር ነው። ፍላጎት በራሱ የልብ መሻትን እውን
ሀገር በልጆቿ ጥንካሬና ብርታት በትብብር እና በመደመር አቅማቸው ልክ ትበለፅጋለች። የሀገር ብልፅግና የሚወሰነው በዜጎች ጠንካራ የመበልፀግ ፍላጎተትና ተግባር ነው። ፍላጎት በራሱ የልብ መሻትን እውን ሊያደርግ አይችልም። ይልቁንም ጠንካራ ፍላጎት እና መነሳሳት የሚያስከትለው ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንጂ። ኢትዮጵያ የበለፀገች ገናና ትልቅ ሀገር ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው። በዚህ የሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዞ ውስጥ ሁላችንም የመሚጠበቅብንን ኃላፊነት መወጣት ይገባል። ስኬት በብዙሃኑ ትግል አስተዋፅኦና ተግባር ድምር ውጤት ሲሆን በፍጥነት የሚሳካ ይሆናል። የተወሰኑ ሰዎች ልፋትና ጥረት ከሆነ ግን የጊዜ ገደቡ የተራዘመ ስኬቱም ዋጋ የሚያስከፍል ይሆናል። በአጭር ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ለማሳካት ግን የሁላችንንም ርብርብ ይጠይቃል። ሁችንም በተደመረ አቅም ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና በመስራት በአጭር ጊዜ የበለፀገች ከፍታ ማማ ላይ ያለች ሀገርን እውን እናድርግ። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ኢትዮጵያ ብዙ ማንነቶችን በፍቅር ያስተናገደች ሀገር። ኢትዮጵያ ብዙ ማንነቶች በፍቅር የውበት መገለጫ ለሌሎች ተምሳሌት ሆነው የሚታዩባት ሀገር ነች። ብዙዎች አንዳይነትነትን ለመፍጠር ሀገር አፍርሰዋል
ኢትዮጵያ ብዙ ማንነቶችን በፍቅር ያስተናገደች ሀገር። ኢትዮጵያ ብዙ ማንነቶች በፍቅር የውበት መገለጫ ለሌሎች ተምሳሌት ሆነው የሚታዩባት ሀገር ነች። ብዙዎች አንዳይነትነትን ለመፍጠር ሀገር አፍርሰዋል፤ ታሪክ አዛብተዋል፤ ተፈጥሮን ተቃርነው በመቆማቸው ተፈጥሮ ከድታቸዋለች። ኢትዮጵያ ግን በተፈጥሮ ፀጋ በፍቅር አንድ ሆና ፀንታ የቆመች ሀገር አለችን። ብዝሃነት ሀብት ነው። ብዝሃነት አንዱ ጋ ያለው ከሌላው ጋር በመደመር ሁሉንም የማገኘት እድል ነው። የኢትዮጵያ ብዝሃነት በማንነት ሊገለፅ ይችላል። ብዙ ማንነቶች ውብ ሆነው ተከባብረው የጥንካሬ ምንጭ ሆነው እናያለን። ከማንነት የመነጨ ብዙ ባህሎች አሉን በብዙ ባህሎች ምክንያተት የውስጥም ሆነ የውጭ የቱሪስት መስህብነት በተፈጥሮ ታድለናል ማለት ነው። ሌላው ብዝሃነት በእምነት የሚገለፅ ነው። ኢትዮጵያ የእምነት ብዝሃነት ያለባት ብዝሃነታቸው ትውልድ ለመገንባት ያገዟት ሀገር ነች። እምነት የትውልድ ስነ - ምግባርን ያንፃል። በስነ - ምግባር የታነፀ ትውልድ ሀገር ይገነባል። ኢትዮጵያ በመልካ ምድር አቀማመጥ ብዝሃነትን ታድላለች። የበረዶ ክምችት የምናይበት ከፍተኛ ቅዝቃዜ ያለበት አካባቢ ብንፈልግ ኢትዮጵያ ታድላዋለች። ለመተንፈስ የሚያቃቅት እልም ያለ በረሃ ብንፈልግ ይህም ኢትዮጵያ ውስጥ አለ። በአለም ላይ አሉ ተብለው ከተጠኑት 28 የአፈር አይነቶች 25ቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛሉ። ተፈጥሮ ለእኛ ኢትዮጵያዊያን ምንም ፈልገን እንዳናጣ ሁሉንም አሟልቶ ያደለን ነን። የታደልነውን የተፈጥሮ ፀጋ በአግባቡ መጠበቅ መንከባከብ ጥቅም ላይ ማዋል ከእኛ የጠበቅ ነው። ኢትዮጵያ ተፈጥሮ ያደላትን ሀብት ተረድተን በፍቅርና በአብሮነት ጥቅም ላይ ለማዋል መትጋት ከእኛ ይጠበቃል። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ትውልድ በትናንት መሠረት፣ በዛሬ ጥረት፣ ትጋት፣ ልፋት፣ በነገ ህልምና ተስፋ ይገነባል። ትናንቱ መሠረት መነሻ ወረት ይሆነዋል። ዛሬውን ተግቶ መስራት ይጠይቀዋል። ነገን ደግሞ በተስፋ እና በሚያልመው
ትውልድ በትናንት መሠረት፣ በዛሬ ጥረት፣ ትጋት፣ ልፋት፣ በነገ ህልምና ተስፋ ይገነባል። ትናንቱ መሠረት መነሻ ወረት ይሆነዋል። ዛሬውን ተግቶ መስራት ይጠይቀዋል። ነገን ደግሞ በተስፋ እና በሚያልመው ህልሙ እውን መሆን ይጠበቃል። ለዚህ ነው የትውልድ እሳቤው ዛሬ ላይ ብቻ የታጠረ መሆን የለበትም ትናንትን የሚማርበት፤ ዛሬን ለነገው ምናቡ የሚወጣበት፤ መሰላሉ ማድረግ አለበት የሚባለው። ከትናንት ትምህርትን በመውሰድ ዛሬን ለነገ ህልማችን ስኬት በመስራት በጋራ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናድርግ! መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

አፍሪካ ትልቅ የተፈጥሯዊ ሀብት አቅም ያላት አሀጉር ናት። አፍሪካ ቀደምት ስልጣኔዋ በቀድሞው ለአለም ባበረከተችው አስተዋፅኦ ገናና ብትሆንም የቅኝ ግዛት የወለደው ትርክት ታላቅነቷን አደብዝዞት አልፏ
አፍሪካ ትልቅ የተፈጥሯዊ ሀብት አቅም ያላት አሀጉር ናት። አፍሪካ ቀደምት ስልጣኔዋ በቀድሞው ለአለም ባበረከተችው አስተዋፅኦ ገናና ብትሆንም የቅኝ ግዛት የወለደው ትርክት ታላቅነቷን አደብዝዞት አልፏል። ምንም እንኳን በትግል እና በመስዋዕትነት ነፃ የወጣች አፍሪካ ብትሆንም አሁንም ነፃ ሆና በራሷ ጉዳይ እራሷ እንዳትወስን በርካታ ጣልቃ ገብነቶች ይስተዋላሉ። አፍሪካ ውስጥ ያሉ ሀገራት ጠንክረው የሚወጡ ሲመስላቸው የውስ አለመረጋጋት በመፍጠር፣ መፈንቅለ መንግስት በማካሄድ፣ ለውጥ ሲኖር ለውጡ እንዳይረጋ እና እንዳይሰክን የቻሉትን ሁሉ በማድረግ በዘመናዊ ቅኝ ግዛት ብዝበዛ ውስጥ ለማቆየት የቻሉትን ሁሉ ይሰራሉ። ለዚህ መፍትሔው ጠንካራ የውስጥ አንድነትን መፍጠር፣ የራስን ሀብት በራስ አልምቶ ለመጠቀም መስራት፣ አፍሪካዊያን እርስ በእራስ መተጋገዝን ይጠይቃል። አፍሪካዊ ወንድማማችነትን/ እህትማማችነትን በማጠንከር የራስን ተፈጥሯዊ ሀብት በራስ በመጠቀም የበለፀገች ሀያል አሀጉረ አፍሪካን እውን ማድረግ ይቻለናል። ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ የመሪነት ሚና መጫዎት ይገባታል። የመሪነት ሚና ለመወጣት በቅድሚያ የራስን ጥንካሬ ማረጋገጥ ይፈልጋል እና ሁላችንም የውስጥ አንድነትን በማጠንከር የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናድርግ። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

በመደመር እይታ መሠረት የሰው ልጅ የፉክክርም ሆነ የትብብር፣ የጠበኝነትም ሆነ የሰላማዊነት ዝንባሌ በእጅ ላይ ነው። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና
በመደመር እይታ መሠረት የሰው ልጅ የፉክክርም ሆነ የትብብር፣ የጠበኝነትም ሆነ የሰላማዊነት ዝንባሌ በእጅ ላይ ነው። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ። #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ። #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ለመላው የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳቹ። መልካም በዓል ይሁንለዎ!
ለመላው የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳቹ። መልካም በዓል ይሁንለዎ!

ለአንድ ሀገር ብልፅግና መሠረታዊ ከሚባሉት ጉዳዮች አንዱ፤ በዕውቀት ላይ የሚኖር የበላይነት ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ በዕውቀት ዘርፍ ተወዳዳሪ ሆና እንድትወጣና፤ በውጤቱም ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስኬት
ለአንድ ሀገር ብልፅግና መሠረታዊ ከሚባሉት ጉዳዮች አንዱ፤ በዕውቀት ላይ የሚኖር የበላይነት ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ በዕውቀት ዘርፍ ተወዳዳሪ ሆና እንድትወጣና፤ በውጤቱም ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስኬትን ለማስመዝገብ፤ ትውልዱ በዕውቀት ታንፆ እንዲያድግ ማድረግ ይኖርብናል። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና