en
Feedback
Kolfe P.P - ብልፅግና

Kolfe P.P - ብልፅግና

Open in Telegram
1 671
Subscribers
No data24 hours
-177 days
-8030 days
Posts Archive
ዛሬ የተሰሩ ስራዎች ነገ መሠረቶች ናቸው። የነገውን ታሪክ ለመፃፍ ብዕሩም ወረቀቱም የተሰጠው ለዚህ ትውልድ ነው። የነገውን ታሪክ የመፃፍ እድል የተሰጠው ደግሞ ታሪኩን በሚፈልገው መንገድ መፃፍ ይችላ
ዛሬ የተሰሩ ስራዎች ነገ መሠረቶች ናቸው። የነገውን ታሪክ ለመፃፍ ብዕሩም ወረቀቱም የተሰጠው ለዚህ ትውልድ ነው። የነገውን ታሪክ የመፃፍ እድል የተሰጠው ደግሞ ታሪኩን በሚፈልገው መንገድ መፃፍ ይችላል። አንድም ኢትዮጵያን አበልፅጎ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ያደረገ ትውልድ ተብሎ ይወሳል። ኢትዮጵያ በሁሉም ረገድ ታላቅ እና አሸናፊ አድርጎ በመስራት ይህንኑ መፃፍ ይችላል። ይህንን እድል ካበላሸ በአግባቡ ካልሰራ ደግሞ በተቃራኒው ሊያፅፍ ይችላል። እናም በነገው ትውልድ በልጆቻችን በልጅ ልጆቻችን በየትኛው እንድንታወስ እንፈልጋለን ነው ቁም ነገሩ። የነገው ትውልድ ልጅ የልጅ ልጆቻችን ታሪክ ሰሪው ትውልድ ብለው እንዳወሱን ወይስ ታሪክ አበላሽቶው የፃፍልን ትውልድ። መምረጥ የትውልዱ ድርሻ ነው። በርግጥ በልጆቹ ታሪክ ያበላሸ ትውልድ ተብሎ መታወስን የሚሻ አይኖርም። መሻቱ ብቻው ግን ውጤት አይሆንም እና በያዝነው የብልፅግና ጉዞ ውስጥ 7/24 በመስራት ሁለንተናዊ ብልፅግናን እውን ማድረግ ይገባል። ዛሬ ወደድንም ጠላን ለእኛ ተሰጥቶናል። ትናንት እኛ አልነበርንም አባቶቻችን አያቶቻችን የሰሩት ታሪክ ነው። ነገም የእኛ አይደለም የመጭው ትውልድ ነው። ዛሬ ግን የእኛ ነው። ዛሬያችንን የእኛን ጊዜ ታሪክ እንስራበት ታሪክ እንፃፍበት። ያልተፃፈበትን የእኛ ወረቀት፣ የተሰጠንን የመፃፊያ ብዕር በአግባቡ ተጠቅመን የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ያደረገው ትውልድ የሚል እንፃፍበት። ሁላችንም ስንተጋ በተሰማራንበት ሁሉ ኃላፊነታችንን በብቃት ስንወጣ የበለፀገች ኢትዮጵያ እውን ማድረግ ይቻለናል። በእውቀት፣ በትጋት፣ በእውነት፣ በውጤት ወደ ብልፅግና። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ኢትዮጵያ በለውጥ ጉዞ ውስጥ በርኬታ ስኬቶችን እያስመዘገበች ያለች ሀገር ነች። በርካታ ድሎች ስኬቶች ከተመዘገቡት አንዱ የስንዴ አምራችነት ነው። ኢትዮጵያ ትናንቷን ስናይ አቅሙ እያላት አቅሙን ሳትቀ
ኢትዮጵያ በለውጥ ጉዞ ውስጥ በርኬታ ስኬቶችን እያስመዘገበች ያለች ሀገር ነች። በርካታ ድሎች ስኬቶች ከተመዘገቡት አንዱ የስንዴ አምራችነት ነው። ኢትዮጵያ ትናንቷን ስናይ አቅሙ እያላት አቅሙን ሳትቀመጥበት ቆይታለች። ከለውጡ መምጣት በኋላ ግን በበርካታ ዘርፍ በርካታ ስኬቶች አስመዝግባለች። በግብርናው ዘርፍ የስንዴ ምርት የላቀ ደረጃ ላይ ማድረስ ችላለች። የሩዝ ምርት በማምረት ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ነው። የስንዴ ምርት የሀገር ውስጥ ፍላጎት ሸፍኖ ለውጭ ገበያ መትረፍ የተቻለበት ትልቅ ድል የመዘገበበት ነው። ተግተን ከሰራን ያለንን አቅም አሟጠን ከተጠቀምን የበለፀገች ኢትዮጵያን በአጭር ጊዜውስጥ እውን ማድረግ እንችላለን።ሁላችንም ያለንን አቅም በመጠቀም የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናድርግ! መልካም ቀን ይሁንለዎ! #kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት የጀግንነት ማሳያ ለባንድራው የሚዋደቅ ለሀገር ዳር ድንበር ህይወቱን የሚሰጥ ነው። የእኛ እንደ ዜጋ የተከበረ ዜጋ መሆን መከላከያ ሰራዊታችን በሚከፍለው ዋጋ ነው።
የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት የጀግንነት ማሳያ ለባንድራው የሚዋደቅ ለሀገር ዳር ድንበር ህይወቱን የሚሰጥ ነው። የእኛ እንደ ዜጋ የተከበረ ዜጋ መሆን መከላከያ ሰራዊታችን በሚከፍለው ዋጋ ነው። የመከላከያ ጀግንነት የእኛ መከበር ነው። የእኛ መከላከያን መበርታት መጠናከር ከጎኑ መቆም የበለጠ የጀግንነቱ ምንጭ መሆን ነው። መልካም ቀን ይሁንሐዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

አርበኝነት ከራስ የተሻገረ ሰዋዊ ማንነት የተላበሰ ለሰው ሁሉ የሚራራ፣ የሚከፈል ፣የሚሰጥ፣ የሚያንፅ የሚያቆም ማለት ነው። -ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ #Kolfe Prosperity Part
አርበኝነት ከራስ የተሻገረ ሰዋዊ ማንነት የተላበሰ ለሰው ሁሉ የሚራራ፣ የሚከፈል ፣የሚሰጥ፣ የሚያንፅ የሚያቆም ማለት ነው። -ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ኢትዮጵያ የፀናችው በልጆቾ መስዋትነት ነው። ጀግና ህዝብ ያላት ሀገር ጀግና የመከላከያ ሰራዊት ታፈራለች። ኢትዮጵያ ጀግኖች ልጆችን ወልዳ የምታሳድግ ልጆቿ በእሷ ለመጣ መስዕዋትነት ለመክፈል ያማያቅማ
ኢትዮጵያ የፀናችው በልጆቾ መስዋትነት ነው። ጀግና ህዝብ ያላት ሀገር ጀግና የመከላከያ ሰራዊት ታፈራለች። ኢትዮጵያ ጀግኖች ልጆችን ወልዳ የምታሳድግ ልጆቿ በእሷ ለመጣ መስዕዋትነት ለመክፈል ያማያቅማሙ ሰራዊቶችን ትፈጥራለች። ዘመን ተሻግረን ታሪክ ብናነብ አሁን ላይ ሆነን ቆመን ብንታዘብ የኢትዮዊያንን ጀግንነት ዘመን አይሽረውም፤ ጊዜ አይቀይረውም። ዘመኑን የሚመጥን ዘመኑን የመሰረ ጀግንነት በኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ አለ። ኢትዮጵያ የሚለውን ስም የያዘ ሁሉ ለኢትዮጵያ የተሰለፈ ሁሉ አሸናፊ ይሆናል ተብሎ እንደተፃፈ ሁሉ በኢትዮጵያ የመጣ ነገር ሁሉ ተሸንፎ ይሄዳል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የመላው ኢትዮጵያዊያን የጀግንነት ምልክት ነው። የአሸናፊነት ምሳሌ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ነው። የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት በየትኛውም ስፍራ በማንኛውም ሁኔታ በምንም ውስጥ ሆኖ በሀገር ለመጣ በህዝብ ላይ ለተነሳ ጠላት ህይወት ሰጥቶ ሀገር የሚያፀና ጀግና ነው። ሁላችንም በተሰማራንበት ኃላፊነታችንን በአግባቡ በመወጣት የጀግና ተግባር ለሀገራችን ኢትዮጵያ እንወጣ። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ግዴታችንንና ኃላፊነታችንን በአግባቡ መወጣት መቻል የምናልመውን ለማሳካት ወሳኝ ነው። አሁን ያለው ትውልድ የሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ ለመጪው ትውልድ መሠረት ነው። መጪው ትውልድ ግዴታና ኃላፊነቱን ጠንቅ
ግዴታችንንና ኃላፊነታችንን በአግባቡ መወጣት መቻል የምናልመውን ለማሳካት ወሳኝ ነው። አሁን ያለው ትውልድ የሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ ለመጪው ትውልድ መሠረት ነው። መጪው ትውልድ ግዴታና ኃላፊነቱን ጠንቅቆ የሚያውቅ እንዲሆን አሁን መስራት አማራጭ የለውም። ትውልድ ተገልጋይ ብቻ ሳይሆን አገልጋይ መሆን እንዳለበት ከመረዳት እስከ በተግባር መግለፅ ይኖርበታል። ትውልዱ በሀገሩና በህዝብ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ስሜት እንዲፈጠርበት ከመገልገሉ ተጨማሪ ለሀገሩና ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጥባቸውን መንገዶች መቀየስ አስፈላጊ ነው። መገልገል ብቻ ሳይሆን ማገልገልን፣ መቀበል ብቻ ሳይሆን መስጠትን፣ መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታንንና፣ ኃላፊነትን፣ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ማበርከት እንዲያውቅ፤ አገልግሎትን መለማመድ ይኖርበታል። ሁላችንም ኃላፊነታችንን በሁሉም መስክ በመወጣት ለእኛ እንዲሆኑልን የምንሻቸውን ለሌሎች በማድረግ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናድርግ። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ከትልምነት ወደ ተግባራዊ እውነታነት የተቀየረ ስራ በሌማት ትሩፋት! የሌማት ትሩፋት በተጀመረ አጭር ጊዜ ውስጥ እውን ይሆናሉ ብለን ያላሰብናቸው እውን ሆነዋል። ከሰራን ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ዶሮ
ከትልምነት ወደ ተግባራዊ እውነታነት የተቀየረ ስራ በሌማት ትሩፋት! የሌማት ትሩፋት በተጀመረ አጭር ጊዜ ውስጥ እውን ይሆናሉ ብለን ያላሰብናቸው እውን ሆነዋል። ከሰራን ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ዶሮ አርብተው እንቁላል ከራስ ፍጆታ አልፎ ለገበያ ቀርቧል። የጓሮ አትክልት የአካባቢው ነዋሪን የመመገብ የቻሉ አምራቾች ተፈጥረዋል። ራዕያችንን እንተልማለን፤ ተግባራዊ ስራ እንጀምራለን የመጡ ውጤቶችን ወረት አድርገን የበለጠ እንተጋለን። በትብብር የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሁላችንም እንትጋ!

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ መጠናከር እና አንድነት በርካታ ኃላፊነቶችን ተወጥታለች። ከሰራቻቸው ትልልቅ ስራዎች አንዱ የቅኝ አገዛዝ እንዲያከትም ኢትዮጵያ የሰራችው ትልቅ ስራ የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያዊያን ፍ
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ መጠናከር እና አንድነት በርካታ ኃላፊነቶችን ተወጥታለች። ከሰራቻቸው ትልልቅ ስራዎች አንዱ የቅኝ አገዛዝ እንዲያከትም ኢትዮጵያ የሰራችው ትልቅ ስራ የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያዊያን ፍትህ አዋቂ ጀግና ህዝብ አላት። ይህንንም ደጋግማ በተለያዩ ኩነቶች አስመስክራለች። አሁን ላይ ደግሞ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የራስን ተፈጥሮ ሀብት በራስ አቅም ተጠቀሞ መልማትን እውን እያደረገች ነው። አፍሪካ ትልቅ የመልማት አቅም ያላት አህጉር ነች። የራሷን ተፈጥሯዊ ሀብት በራስ አቅም አልምቶ በፍትሃዊነት መጠቀም የማንንም ይሁንታ የሚያስጠይቅ አይደለም። ኢትዮጵያ በሁለንተናዊ ረገድ የአፍሪካ ተምሳሌት በመሆን የበለፀገች አህጉርን እውን ለማድረግ ትተጋለች። ትብብርና አብሮ መስራት አብሮ ማደግን ያመጣል። ከአፍሪካ ወንድም እህት ጋር በጋራ በትብብር በመስራት የበለፀገች አፍሪካን እውን እናድርግ! መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ጥበብ ምናባዊ እይታችንን ወይም ያለፉ እውነታዎችን ህይወት ዘርቶባቸው ስጋ አልብሷቸው ለአሁናዊ አለሙ የሚያሳይ ልብን የመያዝ ሀይል ያለው ነው። ጥበብ ትናንትን ያልኖረባት ከመስማት ያለፈ ምንነቷን በቅጡ ያልተረዳትን ትውልድ ጥበብ እና ጥበበኞች ዛሬ እየተካሄደ ያለ የምንዳስሰው የምናየው የምናሸተው እውነታ አድርገው ይስሉልናል። በጥበብ የማይሸነፍ የለም። ነገን በምናባዊ ትልም ምን መምሰል እንዳለበት ወይ ምን ሊመስል እንደሚችል የገመቱትን ዛሬ ላይ ስጋ አልብሰው ነፍስ ዘርተው በጥበብ አዋዝተው እንካችሁ ይሉናል። ጥበብ ማህበረሰብን ትቀርፃለች። አንዳንድ ሀያላን ሀገራት የተሸነፉበትን ጦርነት ሳይቀር በፊልማቸው ላይ በጥበበኞቻቸው አማካኝነት ራሳቸውን አሸናፊ አድርገው ይሰራሉ። ውስብስብ ችግር ነው አይፈታም አይችሉትም ብለህ የምታስበውን ችግር ችለውና ፈትተውት ተዓምር ፈጥረው አልፈውት ያሳዩሃል። ይህንን የሚያይ ትውልዳቸው የነገን ውስብስብ ችግር ማለፍ የሚችል አእምሮ እንዳላቸው እንድረዱ በማድረግ የአእምሮን ጉልበት ሀይል ይጠቀማሉ። ከዜጎቻቸው ባሻገር ያሉ ህዝቦች ሳይቀሩ አይበገሬ አዲስ ነገር የመፍጠር ብቃት ያላቸው ልዩ ፍጡር አድርገው ይስሏቸዋል። ይህንን ስዕል የሰጡን ደግሞ በጥበበኞቻቸው በጥበብ ላይ ተራቀው ነው። ትናንትን ሁሉ የአሸናፊነት ታሪክ እንዳላቸው እስክሪብት ላይ ፅፈው በትወና ውስጥ ደምና ስጋ ለብሶ ህይወት ዘርተቶ አሸናፊነታቸውን ያሳዩናል። በጥበባቸው አማካኝነት ለሁሉ ነገር በእርግጥ መፍትሔ አለው የሚል ትውልድን ይፈጥራል። አንዳንድ ሀገራት ደግሞ እድሜ ጠገብ ታሪክ ይዘው፣ ተነግሮ፣ ተፅፎና ተሰርቶ የማያልቅ ታሪክ ሰሪ ትውልድ ታሪክ ሰርቶ አውርሷቸው የጥበቡ ውል ጠፍቶ ጥበብን ሳንጠቀምባት ነገን ማየት ቀርቶ የነበረውን ትናንት ሰርቶ ማሳየት ሲሳናቸው ታያለህ። አመት ሰርተህ ያላስተማርከውን ትምህርት ጥበብ በደቂቃ በቅፅበት ሰው ልብ ውስጥ ታትማለች። ጥበብን ለሀገር ግንባታ፣ ለሀገር ብልፅግና፣ ለህዝብ አንድነት፣ ለህዝብ ወንድማማችነት/ እህትማማችነት መሠረት የሚሆን ነው። ትናንት የነበሩንን የጀግንነት፣ አይበገሬነት፣ አሸናፊነት፣ የግዛት ስፋትና ሀገራዊ አንድነት በጥብ አዋዝቶን ለትውልዱ የመስጠት ኃላፊነት የጥበብ ሰዎች ላይ ነው። ነገ መሆን የምንፈልገውንና የተለምነውን መዳረሻ ማሳየት የፖለቲከኛው ስራ ብቻ አይደለም ጥበብን የተቸሩ ሰዎችም ዋና ድርሻ እንጂ። ጥበብን ለሀገር ብልፅግና ለህዝብ አንድነት ወንድማማችነት እንጠቀመው። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ያለንን አቅም እና ሀብት መረዳት የምንችለው ባለን የማየት እና የመትለም አቅም ልክ ነው። አለም ከሰፈራችን ጀምሮ በርካታ የተትረፈረፈ ሀብት አላት። የመበልፀግ አቅም የትኛውም አካባቢ ላይ ይገኛል። ከተፈጥሯዊ ስጦታ በላይ ብልፅግና ያለው የሰው ልጅ አእምሮ ውስጥ ነው። አእምሯቸውን የተጠቀሙ  ለማየት የሚከብድ በርሃ ላይ የተንቆጠቆጠ የመናፈሻ ቦታ ሰርተው የሚያስደምም ህንፃ አንፀው አለም ለጉብኝት እንድተም አቅም ያለው መኖሪያ ቅንጡ ቤት እንድገዛ ያደርጉታል። አእምሯቸውን መጠቀም ያቃታቸው ዘርተውት ሳይሆን ወድቆ ምርት የሚሰጥ አፈር ይዘው የሚራቡ፣ ትንሽ ቢጥሩ ዳይመንድ የሚያመርቱ ሆነው እርስ በእራስ የሚዋጉ፣ ያላቸውን እና የተሰጣቸውን ማየት ተስኗቸው የሚሰደዱ፣ ጠንካራ ሀገር መንግስት፣ ፅኑ ብሔረ መንግስት መገንባት ተስኗቸው ጦር የሚማዘዙ፣ ጠረጴዛ ላይ መነጋገርን ንቀው በጫካ የሚሸፍቱ 'ሙህር' ነን የሚሉ ማህበረሰቦች እዛም እዚህም ማየት የአለም ነባራዊ ሀቅ ነው። ቁም ነገሩ አለምን የምናይበት መነፀር፣ አለምን የምንረዳበት አእምሮ፣ ለአለም የምንሻበት ልባችን ላይ ነው። አለምን የተትረፈረፈ ሀብት እንዳላት በቅጡ የተረዳ ለአለም ተዝቆ የማያልቅ ሀብትን በአእምሮው አስቦ በልቦናው መክሮ ዘክሮ በክሱትነት አለምን የሚጠቅም ነገር ያበስራል። በተቃራኒው የአተያይ መነፀር ሲንሸዋረር በቅርባችን ያለንን ሀብትና አቅም ማየት ሲሳነን መሰደድን እንደ አማራጭ፣ መሸፈትን እንደ ጀግንነት አኩራፊነትን እንደ አዋቂ እንቆጥራለን። እኛ ኢትዮጵያዊያን በአካባቢያችን ካየን ተነግሮ የማያልቅ የአባቶቻችን፣ የታላላቆቻችን ገድል አለ። ተዝቆ የማያልቅ ሀብት ሰርቶ ያልጠገበ ጉልበት አለን። የሚያስኬድ የሚያራምድ ውጤት እያመጣ ያለ የምንመራበት ሀገር በቀል እሳቤ እውን ሆኗል። የሚጠበቅብን ቅሬታዎቻችንን በንግግር የምንፈታ፣ ያለንን ሀብት በፍትሃዊነት የምንጠቀም፣ ኢትዮጵያን በትብብር የምናበለፅግ፣ አካባቢያችንን በኃላፊነት ወደ ተሻለ ደረጃ የምናሻግር፣ አእምሯችንን ለአለም የሚጠቅም ሀሳብ በማመንጨት የምናተጋ፣ ልባችንን በወንድማማችነት እህትማማችነት ገመድ የምናስተሳስር ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን የምናጠናክር መሆን ይገባናል። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ህዝብን በተገቢው ሁኔታ ማገልገል ብልፅግናን እውን ለማድረግ ወሳኝ ነው። አገልጋይነት ከአስተሳሰብ የመነጨ ለሀገር እና ለህዝብ ያለ ቀና እይታ የመነጨ ተግባር ነው። በአስተሳሰብ ደረጃ በውስጣችን ለሀ
ህዝብን በተገቢው ሁኔታ ማገልገል ብልፅግናን እውን ለማድረግ ወሳኝ ነው። አገልጋይነት ከአስተሳሰብ የመነጨ ለሀገር እና ለህዝብ ያለ ቀና እይታ የመነጨ ተግባር ነው። በአስተሳሰብ ደረጃ በውስጣችን ለሀገር እና ለህዝባችን ያለንን ቀናዕይነት የምንገልጠው በአገልጋይነት ነው። የመደመር ትውልድ አገልጋይ ትውልድን ለመፍጠር በርካታ ተግባራትን እየከወነ ይገኛል። አገልጋይ ትውልድ ሀገራዊ አገልግሎት፣ ማኅበራዊ ኃላፊነትና በጎ ፍቃደኝነትን በተገቢው ይወጣል። ለሀገር ብልፅግና ሀገራዊ አገልግሎት፣ ማኅበራዊ ኃላፊነትና በጎ ፍቃደኝነትን ማስፋፋት በትውልዱ ውስጥ ማስረፅ አስፈላጊ ነው። ሁላችንም ቅንና ታማኝ አገልጋይ በመሆን ሀገር ለማበልፀግ በሚደረገው ሩጫ ውስጥ የድርሻችንን አሻራ እናሳርፍ! መልካም ቀን ይሁንለዎ! #kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ዘመኑ አለምን ከፍተኛ በሆነ የቴክኖሎጂ ምጥቀት ፍክክር ውስጥ እንዲትሆን ያደረገበት ዘመን ነው። በቴክኖሎጂ ምጥቀት አሸናፊ እና ሀያላን የሚፎካከሩበት አሸናፊውም የተሻለ ቴክኖሎጂ ያበለፀገ የሆነበት
ዘመኑ አለምን ከፍተኛ በሆነ የቴክኖሎጂ ምጥቀት ፍክክር ውስጥ እንዲትሆን ያደረገበት ዘመን ነው። በቴክኖሎጂ ምጥቀት አሸናፊ እና ሀያላን የሚፎካከሩበት አሸናፊውም የተሻለ ቴክኖሎጂ ያበለፀገ የሆነበት ዘመን ነው። ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና በተጠቀምነው ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ ይወሰናል። የሰዎችን ማህበራዊ ግንኙነት ሳይቀር ቴክኖሎጂ እየወሰነው ይገኛል። ማህበራዊ ሚዲያ አንዱ በቴክኖሎጂ ምጥቀት በኢንተርኔት የመጠቀም ሂደት ውስጥ የአለምን ህዝብ እያንዳንዱን ዜጋ መረጃ ሰጭም ተቀባይም ተጠቃሚም ተጎጂም አድርጎታል። ፈጣን የሆነን የፓለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ስርዓት ልውውጥን እየፈጠሩ ካሉ ጠንካራ ምክንያቶች አንዱ የዜጋ ጋዜጠኝነት እድል መፈጠሩ መረጃ በሰፊው ማገኘትና መስጠት መቻሉ ነው። በእርግጥ ያገኘውን መረጃ ሳያላምጥ በመዋጥ ሀገርን የሚንጥ በጉዳት መንገድ የሚነዳ የበሬ ወለደ መረጃ የሚያሰራጭ ከፍተኛ ነው። በብስለት የሚያይ እውነቱን ከውሸቱ ፍሬው ከገለባው ለሚለይ ደግሞ ጠቀሜታው የጎላ ሆኖ አይተነዋል። በአዳዲስ የአለም እይታ ውስጥ አዳዲስ ቴክኖሎጂን ማበልፀግ ለጥቅም ማዋል፣ ቀድመው የበለፀጉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በአግባቡ ለሀገራዊ ብልፅግና መጠቀም ይጠይቃል። ቴክኖሎጂ የማበልፀግ፣ የበለፀጉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በኃላፊነት መጠቀም የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ያግዛል። በለፀጉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በኃላፊነት በመጠቀም የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናድርግ። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ሀብት ከቁሳዊነት በእጅጉ ይሻገራል። ቁሳዊ ሀብት አንዱ ሀብት ሆኖ ሳለ የስሜትና የሀሳብ ረቂቅ ሀብት አስፈላጊ ሀብት ነው። የመደመር ትውልድ ቁሳዊ ሀብትን ብቻ ሳይሆን፣ የስሜትና የሐሳብ ረቂቅ ሀብቱ
ሀብት ከቁሳዊነት በእጅጉ ይሻገራል። ቁሳዊ ሀብት አንዱ ሀብት ሆኖ ሳለ የስሜትና የሀሳብ ረቂቅ ሀብት አስፈላጊ ሀብት ነው። የመደመር ትውልድ ቁሳዊ ሀብትን ብቻ ሳይሆን፣ የስሜትና የሐሳብ ረቂቅ ሀብቱን የሚያገናዝብና የሚያሳልጥም ነው። ሁሉንም ሀብታችንን በእኩል በማሳደግ በሁለንተናዊ ረገድ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናድርግ! መልካም ቀን ይሁንለዎ! #kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

“የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረብሔራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው!” ሰንደቅ ዓላማ የሀገር መገለጫ አርማ ነው። ሰንደቅዓላማ በዓለም ላይ የዜግነት መወከያ ነው። ሰንደቅዓላማ ከፍ ሲል
“የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረብሔራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው!” ሰንደቅ ዓላማ የሀገር መገለጫ አርማ ነው። ሰንደቅዓላማ በዓለም ላይ የዜግነት መወከያ ነው። ሰንደቅዓላማ ከፍ ሲል የሀገር እና የህዝቧን ከፍታ ያሳያል። እኛ ኢትዮጵያዊያን ለሰንደቅ ዓላማችን አስፈላጊውን ዋጋ ከፍለን በክብር ከፍ እንድል የምናደርግ ህዝብ ነን። ኢትዮጵያ ልጆቿ ሰንደቅዓላማዋን ከፍ አድርገው ሲያውለበልቡ የደስታ እንባ ይተናነቃቸዋል። የሀገር ፍቅር ስሜታችንን በሰንደቅዓላማችን ከፍታ ክብር ፍቅር እንገልፃለን። በሀገር ሉዓላዊነት መደፈር ለመጣ የማይተካውን ህይወት ገብሮ የሉዓላዊነቷ መገለጫ የሆነውን ሰንደቅ ከፍ አድርጎ ማውለብለብ የእኛ መገለጫ ነው። ኢትዮጵያ የመደፈር አደጋ ሲያጋጥማት ልጆቿ በፍፁም ለህይወታቸው አይሳሱም። የክብሯ መገለጫ የሆነውን ሰንደቅዓላማቸውን ከፍ አድርገው ያውለበልባሉ። ሰንደቅዓላማ የሀገር መለያ ምልክት ነው። የዜግነት ክብር መግለጫ የሀገር ፍቅር ስሜት ማሳያ የሀገር ምልክት አርማ ሰንደቅ ዓላማ ነው። ኢትዮጵያዊያን በሉዓላዊነቷ ለመጣ እንደሚዋደቁት ሁሉ ሀገር ለሰላም ማስከበር ወደ ሌላው አለም በላከቻቸው ጊዜ ገድል ፈፅመፈው ኃላፊነታቸውን ተወጥተው ሰንደቅዓላማቸውን ከፍ ያደርጋሉ። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

ሚዲያ ማህበረሰብን በሚፈለገው መንገድ ይቀርፃል። ሚዲያ የትርክት የበላይነት እንዲኖ በማድረግ የሚያግባቡ ሀሳቦችን ይዘራል። ሚዲዲ የምንሰራቸውን ስራዎች በሙሉ በህዝብ ዘንድ በማስተዋወቅ ህዝብን የልማ
ሚዲያ ማህበረሰብን በሚፈለገው መንገድ ይቀርፃል። ሚዲያ የትርክት የበላይነት እንዲኖ በማድረግ የሚያግባቡ ሀሳቦችን ይዘራል። ሚዲዲ የምንሰራቸውን ስራዎች በሙሉ በህዝብ ዘንድ በማስተዋወቅ ህዝብን የልማት ባለቤት የማድረጊያ መንገድ ነው። በአሁኑ ጊዜ አዲሱ ሚዲያ ሁሉንም ዜጋ መረጃ ሰጭ፣ መረጃ ተቀባይ፣ ለመረጃው ግብረ መልስ ሰጭ፣ በግብረ መልሱ ማስተካከያ ሰርቶ መልሶ ተከታዩን የሚያገኝበትን እድል ሰጥቷል። በዚህ ፈጣን ለሁሉም የመረጃ ሰጭነት እድል የሰጠ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጭ ያለበት ዘመን ውስጥ የተሻለ ሀሳብ ያለው ሀሳቡ አሸናፊ እንድሆን በፍጥነት እኩል መስራት ይጠይቃል። በፈጣኑ የማህበራዊ ሚዲያ የሚዲያ አማራጭነት ዘመን ውስጥ ሁሉም ዜጋ በእኩል መንፈስ ወንድማማችነትን/ እህትማማችነትን የሚያጠናክሩ፣ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን መሠረት የሚያስይዙ ሀሳቦች ቦታ እንድኖራቸው ማድረግ ከሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ ይጠበቃል። የተገራ የሚዲያ አጠቃቀምን እውን በማድረግ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናድርግ። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና

በወንድማማችነትና እህትማማችነት የተገነባ ህብረ - ብሔራዊ አንድነት ለኢትዮጵያ ብልፅግና ፅኑ መሠረት ነው። በወንድማማችነት መሰረት ላይ የሚገነባ ህብረ ብሄራዊ አንድነት ከፍቅር፣ ፍትህ፣ መተሳሰብ እ
በወንድማማችነትና እህትማማችነት የተገነባ ህብረ - ብሔራዊ አንድነት ለኢትዮጵያ ብልፅግና ፅኑ መሠረት ነው። በወንድማማችነት መሰረት ላይ የሚገነባ ህብረ ብሄራዊ አንድነት ከፍቅር፣ ፍትህ፣ መተሳሰብ እና አብሮነት ሌላ አማራጭ ሊያደርግ አይችልም፡፡ የወንድማማችነት እና እህትማማችነት መሠረት ሲሆን ፅንፈኝነትን የሚፀየፍ አካታች፣ አቃፊ፣ በውይይት የሚያምን፣ ችግሮችን በጠረጴዛ ዙሪያ የሚፈታ ይሆናል። ከወንድማማችነት እና እህትማማችነት መርህ የሚያፈነግጥ ለፅንፈኝነት ይጋለጣል። ፅንፈኝነት አጥፊ አስተሳሰብ ነው፡፡ በፅንፈኝነት የሚመጣ ጥፋት ደግሞ ብዙ ጉዳት ያስከትላል፡፡ ፅንፈኝነት ከኔ ውጭ ላሳር ማለት ከመንገድ የሚያስቀር ወደ ኋላ የሚጎትት አስተሳሰብ ነው፡፡ የመደመር ትውልድ ከፅንፈኝነት ይልቅ ሚዛናዊነትን፣ ከዋልታ ረገጥነት ይልቅ መሀል ላይ ያለ መንገድን የመረጠ ነው፡፡ የመደመር ትዉልድ አሰባሳቢ አቃፊ አሳታፊ ነው፡፡ ፅንፈኝነትን የሚፀየፍ በምክንያታዊነት የሚያምን ችግሮችን በንግግር የሚፈታ ትውልድ ነው፡፡ የመደመር ትውልድ ቃል የገባውን በተግባር የሚኖር ትውልድ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ለማበልፀግ መንገዱን መደመር ያደረገ ትውልድ ቃል የገባቸውን በተግባር እየተረጎመ ኢትዮጵያን የከፍታ ማማ ላይ ለማድረስ በአጭር ጊዜ እያመጣቸው ያሉ ውጤቶች ማሳያ ናቸው፡፡ የመደመር ትውልድ የነገዋ ኢተዮጵያ ልዕለ ኃያል በሁለንተናዊ ረገድ የበለፀገች ልጆቿ በወንድማማችነት/ እህትማማችነት መሰረት ላይ ህብረ ብሄራዊ አንድነቷን ያፀናች ሀገር ለማድረግ እየሰሩ ያሉ ናቸው፡፡ መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe Prosperity Party - ብልፅግና