cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

World Peacefully

ሰላም ኢስላማዊ ወንድማማችነት በአንድነት እስከ ጀነት። Peace of Islamic brotherhood together to heaven ━━━━━━━━━━🇪🇹 ━━━━━━━━━━ Selam Islamic Channel ሰላም ኢስላማዊ ቻናል https://m.facebook.com/WorldPeacefully ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━

Show more
Advertising posts
728
Subscribers
No data24 hours
-47 days
-2030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

እንኳን ለ 1,444ኛው የዒዱል አድሓ በዓል አላህ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!! ጌታ አላህ ዒዱን የተባረከ፣ የመደሰቻ፣ ምስኪኖችንም የማስደሰቻ ቀን ያድርግላችሁ። ዒዱኩም ሙባረክ፣ ተቀበለላሁ ሚንና ወሚንኩም
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ወሊይ እና አታላይ ይለያያል ~ በሱፊያው ዓለም ሶላት የማይሰግዱ፣ ፆም የማይፆሙ፣ ከአላህ ተእዛዝ ያፈነገጡ በርካታ ወሊዮች አሉ። ለወንጀላቸው ሽፋን ይሆን ዘንድ “ትልቅ ወሊይ ለሰዎች ሲታይ ይወነጅላል። እሱ ግን ወንጀለኛ አይደለም” በማለት ኪታብ እስከመፃፍ የደረሱ አሉ። [አልኢብሪዝ፡ 2/23] እነዚህ የአላህ ሳይሆን የሸይጧን ወሊዮች ናቸው። የአላህ ወሊዮች በኢማን የደመቁ፣ በተቅዋ ያሸበረቁ ናቸው። አላህ እንዲህ ይላል፦ {أَلَاۤ إِنَّ أَوۡلِیَاۤءَ ٱللَّهِ لَا خَوۡفٌ عَلَیۡهِمۡ وَلَا هُمۡ یَحۡزَنُونَ (62) ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ وَكَانُوا۟ یَتَّقُونَ (63)} {ንቁ! የአላህ ወሊዮች አይፈሩም አይተክዙም። እነሱም እነዚያ ያመኑትና የሚፈሩ የሆኑት ናቸው።} [ዩኑስ፡ 62-63] የአላህ ወሊይ ለመሆን የሚያስፈልገው ኢማንና አላህን መፍራት ነው። ኢማንና ተቅዋ ያለው ሁሉ ወንድ ይሁን ሴት፣ ነጋዴ ይሁን ገበሬ፣ ወታደር ይሁን ወዛደር፣ ሐኪምም ይሁን አስተማሪ፣ ሊስቲሮም ይሁን ተላላኪ ሁሉም የአላህ ወሊይ ነው። “አማኞች በሙሉ የአረሕማን ወሊዮች ናቸው። አላህ ዘንድ ይበልጥ የተከበሩት ይበልጥ ታዛዦቹና ይበልጥ ለቁርኣን ተከታዮቹ ናቸው” ይላሉ ጦሓዊይ ረሒመሁላህ። [አልዐቂደቱ ጦሓዊያህ፡ 64] የአላህ ወሊይ ለመሆን የወሊይ ዘር መሆን አያስፈልግም። ጋርዶ መቀመጥን አይጠይቅም። አጃቢ እንዲኖር አይጠበቅም። ትንቢት መናገር አይደለም መስፈርቱ። ወሊይ ሞቶ ቀርቶ በህይወት እያለም የሰው ልጅ ከሚያደርገው የተሻገረ ምንም ሊያደርግ አይቻለውም። እንዲያውም “ልጅ፣ ዝናብ፣ ሲሳይ፣ ጤና፣ ህይወት እሰጣለሁ፣ እነሳለሁ፣ ዱስቱር ያለን እጠቅማለሁ፣ እምቢ ያለን እጎዳለሁ” ብሎ የሚሞግት ካለ እራሱን ለአላህ ባላንጣ ያደረገ ሸይጧን የሸይጧን ወሊይ ነው። ጌታችን እንዲህ ይላል፡- {أَمَّن یُجِیبُ ٱلۡمُضۡطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَیَكۡشِفُ ٱلسُّوۤءَ وَیَجۡعَلُكُمۡ خُلَفَاۤءَ ٱلۡأَرۡضِۗ أَءِلَـٰهࣱ مَّعَ ٱللَّهِۚ قَلِیلࣰا مَّا تَذَكَّرُونَ} {ወይስ ያ ችግረኛ በለመነው ጊዜ መልስ የሚሰጥ፣ ክፉንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደርጋችሁ (ይበልጣል ወይስ የሚያጋሩት?) (ይህን የሚያደርግ) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን?! ጥቂትንም አትገሰፁም!} [ነምል፡ 62] እንኳን ወሊይና ነብይም ሌሎችን መጥቀም መጉዳት የሚችልበት ስልጣን የለውም። ሃያሉ ጌታ ነብዩን ﷺ ይህን አዋጅ እንዲያሰሙ አዟቸዋል፦ {قُلۡ إِنِّی لَاۤ أَمۡلِكُ لَكُمۡ ضَرࣰّا وَلَا رَشَدࣰا (21) قُلۡ إِنِّی لَن یُجِیرَنِی مِنَ ٱللَّهِ أَحَدࣱ وَلَنۡ أَجِدَ مِن دُونِهِۦ مُلۡتَحَدًا (22)} {“እኔ ለናንተ መጉዳትንም ማቃናትንም አልችልም” በላቸው። “እኔ ከአላህ ቅጣት ማንም አያድነኝም። ከርሱም ሌላ መጠጊያን አላገኝም” በላቸው።} [ጂን፡ 21-22] ወሊይነት በኢማንና በተቅዋ የሚገኝ እንጂ ከአባት፣ ከአያት የሚወረስ እቃ አይደለም። ማንም ቢሆን በስራው ያላገኘውን ማዕረግ በዘሩ አይቆናጠጠውም። ነብዩ ﷺ {ስራው ያስቀረውን ዘሩ አያስቀድመውም} ብለዋልና። [ሙስሊም፡ 2699] ወሊይ ፍፁም የሆነ፣ የተናገረው መሬት ጠብ የማይል የሚመስላቸው አሉ። ወሊይ ሰው ነው። እንደማንኛውም ሰው ይሳሳታል። ነብዩ ﷺ {የሰው ልጅ ባጠቃላይ ተሳሳች ነው። ከተሳሳቾች ሁሉ በላጩ መመለስን የሚያበዙት ናቸው} ብለዋል። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 4515] ወሊዮች ሰዎች አይደሉም እንዴ? ለነገሩ አንዳንዶቹ መላእክት ናቸው ብለው ነው የሚያምኑት። አባቱ! ሶሐቦቹም መላእክት አልነበሩም። የአላህ ወሊዮች የራሳቸው መጨረሻ የሚያስጨንቃቸው እንጂ “አብሽሩ እኛ አለንላችሁ”፣ “እኛን ያየ ጀነት ይገባል”፣ “ከቀብራችን የቆመ እሳት አይነካውም” የሚሉ አልነበሩም። “ሰላሳ የሚሆኑ የነብዩ ሶሓቦችን አግኝቻለሁ። ሁሉም በራሳቸው ላይ ንፍቅናን ይፈሩ ነበር” ይላሉ ታቢዒዩ ኢብኑ አቢ ሙለይካህ። [ፈትሑል ባሪ፡ 1/51] የትኛውም የአላህ ወሊይ ከሸሪዐ አጥር የመውጣት ፍቃድ የለውም። ከነብዩ ﷺ ሸሪዐ ከወጣ እንኳን ትልቅ ወሊይ ተራ ሙስሊምም መሆን አይቻልም። ኢስላም አንድ ነው። ስውር የሚባል ሌላ ሸሪዐ የለም። “ሸሪዐ ሁለት አይነት ነው። ግልፅና ስውር። ግልፁ የመሀይማን ነው። ስውሩ የወሊዮች ነው” የሚሉ ሰዎች ያለጥርጥር ከሃ*ዲዎች ናቸው። አላህ ሶላት የማይሰግድ አጭበርባሪ ወሊይ የለውም። {فَخَلَفَ مِنۢ بَعۡدِهِمۡ خَلۡفٌ أَضَاعُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَٱتَّبَعُوا۟ ٱلشَّهَوَ ٰ⁠تِۖ فَسَوۡفَ یَلۡقَوۡنَ غَیًّا}] {ከነሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ፣ ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የጀሀነምን ሸለቆ ያገኛሉ።} [መርየም፡ 59] ታላቁ የአላህ ወሊይ ዑመር ብኑል ኸጧብ ረዲየላሁ ዐንሁ “ሶላት የተው ሰው በኢስላም ውስጥ ምንም ድርሻ የለውም” ይላሉ። [አልሙወጦእ፡ 2/54] ስለዚህ “ዐርሽ ላይ ነው የምሰግደው”፣ “ሐረም በርሬ ሄጄ ነው የምሰግደው” የሚል ሰው አጭ *በርባሪ ማጅራት መቺ እንጂ የአላህ ወሊይ አይደለም። = ( Ibnu Munewor )
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
🔴 ትኩረት የነፈግነው ሐቅ "ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን ተምሮ ያስተማረ ነው" ብለዋል ነብያችን (ﷺ)። [ቡኻሪ] ይሁን እንጂ ብዙ ቁርኣን ያልቀራ ወገን እያለን ለጉዳዩ የሰጠነው ትኩረት ግን ለችግሩ የሚመጥን አይደለም። ስለሆነም ችግሩን በመቅረፍ ላይ ከራሳችን ልንጀምር ይገባል። * ቁርኣን ካልቀራን ለምን አንቀራም? * ያልቀራ ቤተሰብ ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት፣ ወዘተ. ካለ ለምን አናቀራም? * ይህም ካልሆነልን የሚያቀሩትን በምንችለው አቅም ለምን አናግዝም? ዛሬ ዛሬ ቁርዓን ማስተማር የሰነፎች ወይም እውቀታቸው የደከሙ ሰዎች ስራ እየመሰለ ነው። ቁርዓን ያልቀራህ ወገኔ ሆይ! የትኩረት ማነስ እንጂ እውነት ቁርኣን ማንበብ መቻል ይህን ያክል ከባድ ነገር ሆኖ ነው ወይ? እስከ መቼ ነው 28 የዐረብኛ ፊደላትን አገጣጥሞ ማንበብ ተራራ የሚሆንብህ? ተገቢ ትኩረት ብንሰጠው ቁርኣን ፈፅሞ ዛሬ በሃገራችን የሚወስደውን የጊዜ መጠን የሚጠይቅ አልነበረም። ከልብ ካለቀሱ እምባ አይገድም ይባላል። እና ወንድሜ ሆይ! በነፃ የሚያስተምርህ ካገኘህ እሰየው። ካልሆነ ግን በክፍያ የሚያስተምሩ ወንድም/እህቶች ካሉም ደስ እያለህ ከፍለህ ተማር። ለሚያሳንፉ ሰዎች ጆሮ አትስጥ። ቁርኣን መማር ዲግሪና ዲፕሎማ ከመማር በታች ነውንዴ? ቁርኣን መማር ቋንቋ፣ ኮምፒተር፣ ... ከመማር በታች ነውንዴ? እነዚህን ነገሮች ለመማር ስንትና ስንት እያወጣን ቁርኣን ለመማር የሚወጣው ላይ ለቅሶ ማብዛት ምንድነው? ይልቅ በጊዜ ቁርጠኛ ውሳኔ ወስን። ከዜሮም ብትነሳ እሩቅ አይደለም ትደርሳለህ። ማረም ማስተካከል ከሆነም በአጭር ጊዜ ትጋት ሁነኛ ለውጥ ታያለህ። አላህ ያግዘን። © ኢብኑ ሙነወር World Peacefully
Show all...
በረመዳን በብዛት የሚፈፀሙ ስህተቶች ~~~~ ① ሶላት ሳይሰግዱ መፆም፣ ② ሌሊቱን በጫት ካሳለፉ በኋላ ሱሑርን አስቀድሞ በመመገብ ፈጅር ሳይሰግዱ መተኛት፣ ③ ቀኑን በእንቅልፍ፣ ሌሊቱን በተከታታይ ፊልም/ ሙሰልሰላት ማሳለፍ፣ ④ ረመዳንን ጠብቆ መንዙማና ነሺዳ እየለቀቁ ሰዎችን ከቁርኣን ማዘናጋት፣ ⑤ ተራዊሕን በንቃት እየሰገዱ ፈጅር ሶላትን በእንቅልፍ ማሳለፍ፣ ⑥ ተራዊሕ ላይ በየ አራቱ ረከዐ መሐል የቢድዐና የሺርክ እንጉርጉሮዎችን ማስገባት፣ ⑦ የተራዊሕ ኢማሞች ከሶላቱ ይልቅ ለቁኑት ዱዓእ የበለጠ ትኩረትና ጊዜ መስጠት፣ ⑧ መግሪብ ሶላት ሲጠናቀቅ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ለፊጥራ መጣደፍ (ሰጋጆችን የሚያቋርጥ፣ የሰው ጫማ የሚያቀያይር፣…ብዙ ነው) ⑨ ሌሊት ላይ "ተሰሐሩ " እያሉ በእስፒከር መጮህ፣ (10) የሱሑር ጊዜ ሳያልቅ ለጥንቃቄ በሚል ቀድሞ አዛን ማድረግ፣ (11) ሱሑር ላይ "ነወይቱ ሰውመ ገዲን" እያሉ በቃል መነየት፣ (12) እያንቀላፉ ተራዊሕ መስገድ፣ (13) ልጆች "እንፁም" ሲሉ ማበረታታት ሲገባ መከልከል፣ "ውሃ አያፈጥርም፣ ተደብቀህ ብላና ትፆማለህ" እያሉ መዋሸትና ውሸት ማለማመድ፣ (14) ሴቶች በተጋነነ የምግብ ዝግጅት ሰፊ ጊዜያቸውን ማቃጠል፣ (15) ሴቶች ሽቶ ተቀባብቶ ለተራዊሕ መውጣት፣ (16) በተራዊሕ ወቅት የሴቶችና የወንዶች አላስፈላጊ መዝረክረክ፣ (17) ሃሜት፣ (18) ፊጥራ ላይ ከመጠን በላይ መመገብ፣ (19) ቀኑን በካርታ፣ በዳማ፣ ወዘተ ማሳለፍ፣ (20) ሙዚቃ ማዳመጥ፣ (21) የሰው ስራ የሚሰሩ ተቀጣሪዎች ጧት በሰዓት አለመግባት (አማና መጠበቅ፣ ቃልን ማክበር ግዴታ ነው። ግዴታ ያልሆኑ ዒባዳዎች ተፅእኖ የሚያሳድሩብን ከሆነ መተው ወይም መቀነስ ይገባል)፣ (22) በተለይ በስራ ቦታዎች ላይ በመንዙማና በነሺዳ ማሳለፍ (መሆን ያለበት ከተመቼ ቁርአን መቅራት፣ ካልሆነ ዚክር ማድረግ ወይም ደዕዋ ማዳመጥ፣ ካልሆነ ዝምታ ይሻላል።) (23) ለይለተል ቀድርን ለማየት ሰማይ ሰማይ እያንጋጠጡ መጠበቅ (የሚታይ ነገር የለም)፣ (24) አንዳንድ አካባቢዎች ዒሻን በጣም በማዘግየት ሰው ጀማዐ ላይ እንዳይካፈል እንቅፋት መሆን፣ (25) አንዳንድ አካባቢዎች መስጂድ ውስጥ ጫት ይዞ ገብቶ መቃም፣ (26) አንዳንድ አካባቢዎች "ተርቲብ" ብለው ንፍሮ፣ ቆሎና መሰል ምግቦችን ወደ መስጂድ እንዲያቀርቡ ህዝብን ማዘዝ፣ (27) የምግብ ብክነት፣ ወዘተ ( ኢብኑ ሙነወር ) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/WorldPeacefully
Show all...
World Peacefully

ሰላም ኢስላማዊ ወንድማማችነት በአንድነት እስከ ጀነት። Peace of Islamic brotherhood together to heaven ━━━━━━━━━━🇪🇹 ━━━━━━━━━━ Selam Islamic Channel ሰላም ኢስላማዊ ቻናል

https://m.facebook.com/WorldPeacefully

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━

الشمراني | البقزة.m4a1.89 MB
በእርግጥም ለጋሽ መሆን ይከፍላል!! ~ ደስታን በልግስና ውስጥ ያገኙት የአለማችን ቁጥር አንድ በጎ አድራጊ፣ #Ethiopia | ሼይኽ ሱለይማን አልራጅሂ ይባላሉ:: ሳዑዲ አረቢያ ካፈራቻቸው ቢኒየነሮች መካከል አንዱ ናቸው:: ከንጉሳውያን ቤተሰብ ሳይሆኑ ቢሊየነር መሆን የቻሉ ሰው ናቸው:: በአለም ግዙፉን አልራጅሂ ኢስላማዊ ባንክ መመስረት ችለዋል:: በህይወታቸው ያጋጠማቸውን አንድ አስተማሪ ክስትተት እንዲህ ሲሉ ያካፍሉናል - "በልጅነቴ እጅግ በድህነት ውስጥ ነው ያደኩት:: ቤተሰቦቼ ድሆች ነበሩ:: በአንድ ወቅት ትምህርት ቤት ተማሪ እያለው ትምህርት ቤቱ የመዝናኛ ጉዞ ስላዘጋጀ በዚህ የሽርሽር ጉዞ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ 1ሪያል ማዋጣት እንደሚጠበቅበት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አስታወቀ:: እኔም በዚህ ጉዞ ላይ ለመሳተፍ እጅግ ስለጓጓው ለወላጆቼ አንድ ሪያል እንዲሰጡኝ እያለቀስኩኝ ጠየኳቸው:: ነገር ግን ወላጆቼ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ህይወት የሚኖሩ ሚስኪኖች ስለነበሩ ይህን አንድ ሪያል ስለሌላቸው ሊሰጡኝ አልቻሉም:: የጉዞ ቀናት መቃረቡን ተከትሎ አንድ ሪያሉን የሚሰጠኝ በማጣቴ እጅግ በጣም አለቀስኩኝ ፤አዘንኩኝ:: ለጉዞ አንድ ቀን ሲቀረው በትምህርት ቤቱ የወሰድነው ፈተና ውጤት ደርሶ ስለነበር የፈተና ውጤታችንን ስንቀበል ከሌሎች ተማሪዎች የላቀ ውጤት በማምጣቴ ፍልስጤማዊ የሆነው መምህራችን ተደስቶብኝ በተማሪዎች ፊት አስጨብጭቦ ውጤቴን ሰጠኝ:: ለማበረታታም አንድ ሪያል በሽልማት መልኩ አበረከተልኝ:: ለጉዞ መዋጮ የሚያስፈልገኝን አንድ ሪያል በሽልማት መልኩ በማግኘቴ እጅግ በጣም ተደሰትኩኝ:: ያንን የተሸለምኩትን ኣንድ ሪያልም ለትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በፍጥነት ሄጄ በመስጠት ብዙ በጓጓሁለት ጉዞ ላይ መሳተፍ ቻልኩኝ:: ለቀናት ሳነባ የነበረው እንባ በደስታ ተቀየረልኝ:: የቀናት ለቅሶዬ በዛች አንድ ሪያል ሽልማት የተነሳ ለረጅም ጊዜያት ውስጤ በቀረ ደስታ ተለወጠልኝ:: ጊዜያት ነጎዱ:: እኔም ትምህርቴን አጠናቀኩኝ:: ጠንካራ እና ታታሪ ሆኜም በስራ ዘርፍ ላይ ተሰማራው:: የአላህ ፀጋ ብዙ ነውና ስራዬን በረካ አደረገልኝ:: ፀጋውንም በኔ ላይ አንቧቧልኝ:: ከትንሽ ስራ ተነስቼ በሳኡዲ አረቢያ የመጀመሪያው የሸሪዓ መር ባንክ በመመስረት በመላው ሳኡዲ አረቢያ ቅርንጫፎች በዙልኝ:: በአንድ ወቅት በልጅነቴ ተማሪ እያለው አንድ ሪያል የሰጠኝ መምህሬን በማስታወስ በወቅቱ የሰጠኝ አንድ ሪያል ሽልማት ነው ወይስ እርዳታ ? በሚል ከእራሴ ጋር ሙግት ውስጥ ገባው:: እራሴን ደጋግሜ ጠየኩኝ:: ግን ፈፅሞ መልስ ላገኝለት አልቻልኩም:: መምህሩ ያንን አንድ ሪያል የሰጠኝ ምንም አስቦ ቢሆን ለእኔ ግን በወቅቱ የነበረብኝን ትልቅ ችግሬን ቀርፎ አስደስቶኛል ፤ ያንን የደስታ ስሜት ደግሞ ከእኔ ውጪ ማንም ሊረዳው አይችልም ስል ለራሴ ነገርኩት:: ውስጤ ለሚመላለሰው ትዝታ እና ጥያቄ ምላሽ ሊሆነኝ የሚችለው ይህን መምህር ካለበት አፈላልጌ አግኝቼው ስጠይቀው ነው በሚል ወደ ቀድሞ ትምህርት ቤቴ በመሄድ ፍልስጤማዊ መምህሬን ማፈላለግ ጀመርኩኝ:: በአላህ እገዛ መምህሬ ያለበትን ቦታ አፈላልጌ ማግኘት ቻልኩኝ:: እሱን ለማግኘትም ቀድሜ ተዘጋጀሁና ወዳለበት ስፍራ አቀናው:: ፍልስጤማዊው መምህሬ በጡረታ ላይ ሆኖ፣ እጅግ በድህነት እና በችግር ላይ ሆኖ አገኘውት:: የእርሱ ተማሪ እንደነበርኩኝ በማብራራት እንዲያስታውሰኝ አደረኩት :: የተከበርከው ውዱ መምህሬ ሆይ ፣እኔ እኮ ለረጅም አመታት የቆየ ያንተ ባለእዳ ነኝ አልኩት:: አንድ ደሃ ሰው ምን የሚያበድረው ነገር ኖሮት ነው የማበድርህ ሲል ተገርሞ ጠየቀኝ:: እኔም ተማሪ እያለው በውጤቴ ምክንያት የሰጠኝን አንድ ሪያል አስታወስኩት:: መምህሬም :- ክስተቱን በማስታወስ እየሳቀ ባለእዳ ነኝ ያልከኝ ታዲያ አሁን ያቺን አንድ ሪያል ልትከፍለኝ ነው ? በማለት ተገርሞ እየሳቀ ጠየቀኝ:: እኔም አዎ ውዱ መምህሬ በማለት መለስኩለት:: ወደ መኪናዬ እንዲገባ በማድረግ እጅግ ዘመናዊ መኪና በግቢው ውስጥ የቆመበት ግዙፍ ዘመናዊ ቪላ ቤት ውስጥ ይዜው ገባው:: መምህሬ ሆይ ተማሪ እያለው ለሰጠኸኝ አንድ ሪያል ምላሽ ባይመጥንም፤ ይሄ ግዙፍ ቪላ እና መኪና ላንተ ይሆን ዘንድ ያዘጋጀሁት ነው፤ በህይወት ዘመንህም የሚበቃህን ያህል ገንዘብ እኔ ዘንድ ተዘጋጅቶልሀል ብዬ ነገርኩት:: መምህሬ እጅግ በመደንገጥ ይሄ ፈፅሞ ለእኔ አይገባም፣ ይህ በጣም ከልክ ያለፈ ብዙ ነው በማለት አይኑ በእንባ ተሞልቶ መቀበል እንደሚከብደው ነገረኝ::: መምህሬ ሆይ በወቅቱ አንድ ሪያል ስትሰጠኝ የነበረኝ ደስታ ዛሬ አንተ ይህን ቪላ እና መኪና ስታገኝ ከተሰማህ ደስታ በላይ ነው:: የዛኔ የነበረኝ የልጅነት ደስታ እና ሀሴት ዛሬም ድረስ አይረሳኝም በማለት ለመምህሬ ስጦታዬን አበረከትኩለት::ይላሉ በመጨረሻም ሼይኽ ሱለይማን አል ራጅሂ ምክር ሲመክሩ "ምን ጊዜም ለሌሎች ደስታን ፍጠር፣ የሌሎችን ጭንቀት አሶግድ ፣ ምንዳህን እጅግ ከሰጪው ፣ከለጋሹ እና ከደጉ ጌታ ጠብቅ ይላሉ' ለመረጃ ያህል ሼይኽ ሱለይማን አልራጅሂ ያላቸውን ሀብት ግማሹን ለልጆቻቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ግማሹን ደግሞ ለበጎ አድራጎት አበርክተዋል:: በአለማችን ታሪክ ግዙፉ የተባለለትን እና በአለም ድንቃ ድንቅ መዘገብ ላይ ሊሰፍር የቻለ ለበጎ አድራጎት አገልግሎት የሚውል በሳኡዲ አረቢያ በቀሲም ግዛት የሚገኘውን 5466 ሄክታር ስፋት ያለው የእርሻ ማሳቸውን፤ ይህም የእርሻ ማሳ በአመት 10ሺህ ቶን የቴምር ፍሬ የሚሰጥ እና በውስጡም 45 አይነት የተለያዩ የተምር ፍሬዎችን የያዘ፣ 200,000 የሚሆን የተምር ዛፍ ለበጎ አድራጎት ይውል ዘንድ ወቅፍ ማድረግ የቻሉ ሰው ናቸው:: ሸይኽ ሱለይማን አራጅሂ ለዳእዋና ለበጎ አድራጎት ፕሮጀክቶች ቋሚ ድጋፍ እንዲሆን ወቅፍ ያደረጉት ካፒታል አሁን ላይ 60 ቢሊዮን ሪያል ደርሷል። ይህ በአለማችን እስካሁን ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ወቅፍ ነው:: ሼይኹ ወቅፍ ካደረጉት የተምር እርሻ የሚገኘው የቴምር ምርት ተሽጦም ገቢው ለበጎ አድራጎት ማህበራት የሚከፋፈል ሲሆን ቀሪው ተምርም ለሁለቱ ቅዱሳን መስጂዶች መካ እና መዲና ለሚገኙት ሀረሞች የረመዳን ኢፍጣር ፕሮግራም አገልግሎት ይውል ዘንድ ለምዕመናን በነፃ ይከፋፈላል:: በሳዑዲ አረቢያ ባሉ ከተሞች ላይ በሼይኽ ሱለይማን አል ራጅሂ እና ቤተሰባቸው አማካኝነት መስጂድ እና መድረሳ ያልተገነባበት ከተማ ማግኘት ያዳግታል:: በሁሉም ቦታዎች ላይ መስጂዶችን አስገንብተዋል:: በስራቸው ላለው ሰራተኞቻቸውም ደሞዛቸውን ወሩ ከመጠናቀቁ በፊት በመክፈል ይታወቃሉ:: ሽይኽ ሱለይማን አል ራጅሂ በአንድ ወቅት ቃለመጠይቅ ሲደረግላቸው ግማሹን ሀብታችሁን ለቤተሰባችሁ፤ ግማሹን ደግሞ ለወቅፍ ለግሰውታል:: ለራስዎት የግል ወጪ የሚሆንስ ምን አስቀምጠዋል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ውብ በሆነ ፈገግታ ተሞልተው "ባጭሩ ምላሼ ምንም ነው!" የምለብሳቸው ልብሶች ብቻ እኔ ጋር አሉኝ:: እድሜዬ በሰማኒያዎቹ ውስጥ ነኝ! ከዚህ ቡኃላ ምን ልፈልግ እችላለሁ? የወቅፍ ፕሮጀክቴ ወጪዬን ይሸፍናል፣ መጠለያ፣ ምግብ፣ ህክምና እና መጓጓዣ አገኛለው::በትንሹ ለመኖር በደንብ የተብቃቃው ነኝ:: ሲሉ መልሰዋል:: ” ቢሊየነር ሆነው ግን ምንም ገንዘብ የሌለው ሰው በመሆኖት! "ምን ይሰማዎታል?" ሲባሉም
Show all...
"ፈገግ እያሉ በናፍቆት እይታ ውስጥ ሆነው ውስጤን ብርሃን ይሰማኛል! ነፃነት ይሰማኛል! የበራሪ ወፍ ያህል ነፃነት ይሰማኛል…በህይወት ዘመኔ ሁለት ጊዜ ምንም ገንዘብ የሌለው ሰው ሆኜ አውቃለው:: በፊት ላይ የድህነትን ስሜት እና ሁኔታ በደንብ በህይወቴ አውቀዋለው:: ያሁኑ ግን በፍላጎቴ እና በምርጫዬ ነው:: ምንም ለራሴ ባይኖረኝም እጅግ መረጋጋት፣ የዐዕምሮ ሰላም እና ደስታ ይሰማኛል::ሀብት ሁሉ የአላህ ነው:: የእሱን ሀብት እንድንጠብቅ ነው የተሰጠን:: አሁን ላይ ጌታዬ አላህ ሲጠራኝ ያለ ምንም እክል ጥሪውን መመለስ እችላለሁ! ይህ ታዲያ እንዴት ያለ እፎይታ እና እረፍት የሚሰጥ ነው!!በማለት አስደናቂ ምላሻቸውን ሰጥተዋል:: በእርግጥም ለጋሽ መሆን ይከፍላል!! አላህ ከችሮታው አሁንም ይጨምርላቸው ለኛም የመለገስን ልብ ይወፍቀን (ኡስታዝ አቡበከር አህመድ)
Show all...