en
Feedback
ቢኒ የመጻሕፍት ግብዣ

ቢኒ የመጻሕፍት ግብዣ

Open in Telegram

👉 ሰሞነኛ ትኩስ መፅሐፍት ከነድስቱ እንገጮታለን። 👉 ዘርፈ ብዙ የሆነውን የኪነት ወሬ እስከነቃጭሉ ዱብ እናረጋለን። 👉 ነባርና አዳዲስ መፅሐፍትን መጠነኛ ዳሰሳ አድርገን እንጠቁሞታለን። ✴ ወሬ ጥሩ ስለሆነ በዚህ ቦይ ላኩልኝማ @a3b2ysm

Show more
1 955
Subscribers
-124 hours
-57 days
-2730 days
Posts Archive
ይሄን መገዘዝ ፊት በፋና ካሜራ አስመትተነዋል። ካላመናችሁኝ comment ላይ ያስቀመጥኩላችሁን link ጠይቁት ማለት አለብኝ እንዴ?
+1
ይሄን መገዘዝ ፊት በፋና ካሜራ አስመትተነዋል። ካላመናችሁኝ comment ላይ ያስቀመጥኩላችሁን link ጠይቁት ማለት አለብኝ እንዴ?

#ግጥም የሕያው ስሜቶች ምስክርነት እንደሆነ እናምናለን፤ ምናባዊ መገለጥ እንደ ሆነ እናምናለን፤ ለአያቶቻችን ከመለኮት ጋ የሚያገናኝ መሰላል፤ ለአባቶቻችን የአብዮትን ሰይፍ የሚስል ሞረድ፤ ለእኛ ፍለ
+2
#ግጥም የሕያው ስሜቶች ምስክርነት እንደሆነ እናምናለን፤ ምናባዊ መገለጥ እንደ ሆነ እናምናለን፤ ለአያቶቻችን ከመለኮት ጋ የሚያገናኝ መሰላል፤ ለአባቶቻችን የአብዮትን ሰይፍ የሚስል ሞረድ፤ ለእኛ ፍለጋ(ኀሠሣ) መሆኑን እናምናለን፤ ያልተንዛዛ ልቅሶ፣ ያልቆረፈደ ተረብ፣ ያልተዝረከረከ ፍልስፍና መሆኑን እናምናለን፡፡ ለገጣሚው ብቻ የተሰጠ መክሊት መሆኑን እናምናለን፡፡ #በዕውቀቱ ስዩም #ስብስብ ግጥሞች

ጓዳዊ ግንኙነታችን የተመሠረተው ለተመሳሳይ ግብ በነበረን ሟችነት ላይ ነበር። 367 ሕይወት ተፈራ ማማ በሰማይ
ጓዳዊ ግንኙነታችን የተመሠረተው ለተመሳሳይ ግብ በነበረን ሟችነት ላይ ነበር። 367 ሕይወት ተፈራ ማማ በሰማይ

ጠመንጃና ሙዚቃን ተጋበዙልኝ! ... ከአገሬው የኪን ፍልስፍና ተነስቶ፥ በ40ዎቹ አርመናውያን አመጣጥ ጎዳና ተምሞ፥ ማርሽ ኢትዮጵያ እና ማርሽ ተፈሪን ተዝቶ፥ የኬቦርክ ናልባንዲያን እና የየኔታ ዮፍታ
ጠመንጃና ሙዚቃን ተጋበዙልኝ! ... ከአገሬው የኪን ፍልስፍና ተነስቶ፥ በ40ዎቹ አርመናውያን አመጣጥ ጎዳና ተምሞ፥ ማርሽ ኢትዮጵያ እና ማርሽ ተፈሪን ተዝቶ፥ የኬቦርክ ናልባንዲያን እና የየኔታ ዮፍታሄ ንጉሴን ፍጥጫ አውስቶ፥ በፋቼታ ኔራ ኩርባ ታጥፎ፥ መሰንቆ እንደ ጦር መሣሪያ የተቆጠረበትን አውድ አውግቶን ይነጉዳል። የሀገር ፍቅር ማኅበርን ከአመሠራረቱ ጀምሮ የነበረውን ታሪክ ለመሰነድ የሄደበት ርቀት እሚደንቅ ነው። የቀብር ቀኑን በገዛ ሙዚቃው ከታጀበለት አሰፋ አባተ፥ እስከ ሙዚቃ የዋጠው ፖለቲካ (አሊ ቢራ)፥ ከሜሪ አርምዴ ታሪክ የአበበ ፍቅር እስካናወዛት አስናቀች ወርቁ ድረስ ያሉ  የሕይወት ታሪክ መድብል ብዙ የተለፋበት ሥራ መሆኑን ያሳብቃል። የተለያዩ የሙዚቃ ባንድ ታሪኮችን ማካተቱ ሲገርመን፥ ዓይነስውራን ሙዚቀኞችን ማውሳቱ ደግሞ እጅግ አስደንቆኛል። የ700 ሙዚቃዎች "ካታሎግ" ደግሞ ሌላ ታሪክ ነው። ደራሲውን እጅ ነስተናል! በንባብ ይለቅ ብለናል! በኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር፥ በሀገር ፍቅር ማኅበር፥ የሙዚቃ ባንዶች ማኅበር ... ተጋግዘው መሥራት የነበረባቸውን የቤት ሥራ በአንድ ሰው ትከሻ ብቻ መሞከሩ አጃኢብ እንድንል አሰኝቶናል። #ጠመንጃና_ሙዚቃ #ይነገር_ጌታቸው

#የፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ "አድዋ" የተሰኘው ፊልም ለጥቂት ቀናት በሲኒማ ቤቶች በመታየት ላይ ነው። #አርብ ቅዳሜ እሁድ ከግንቦት 18 - 20 #በሲኒማ ኢትዮጵያ፣ አምፒር እና አምባሳደር በ8፣ 10
#የፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ "አድዋ" የተሰኘው ፊልም ለጥቂት ቀናት በሲኒማ ቤቶች በመታየት ላይ ነው። #አርብ ቅዳሜ እሁድ ከግንቦት 18 - 20 #በሲኒማ ኢትዮጵያ፣ አምፒር እና አምባሳደር በ8፣ 10 እና 12 ሰዓት #መግቢያ ዋጋ 100 ብር #እንዳያመልጥዎ

#ጥቁር ነች አፍሪቃ ሥሯ ከሰል መሳይ ቆዳዋን ገልብጣ እሳት አቀጣጣይ ጥቁር ነች አፍሪቃ ነጻ ቀይ ነኝ ባይ ነጭ ትሆናለች አመድነቷ ላይ #ወደ መንገድ ሰዎች #መዘክር ግርማ
#ጥቁር ነች አፍሪቃ ሥሯ ከሰል መሳይ ቆዳዋን ገልብጣ እሳት አቀጣጣይ ጥቁር ነች አፍሪቃ ነጻ ቀይ ነኝ ባይ ነጭ ትሆናለች አመድነቷ ላይ #ወደ መንገድ ሰዎች #መዘክር ግርማ

#ሎሬት ጸጋዬ ሼክስፒርን ለማግኘት ጥሮ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ሼክስፒርን አልፎታል። ወፌ ላ አጋግም ብዬ ግግም ብዬ ከግዞተኛ ስጫወት ውዬ አላለም ሼክስፒር #ጋሽ ነብይ መኮንን በሸገር ኤፍኤም ከመዓዛ
#ሎሬት ጸጋዬ ሼክስፒርን ለማግኘት ጥሮ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ሼክስፒርን አልፎታል። ወፌ ላ አጋግም ብዬ ግግም ብዬ ከግዞተኛ ስጫወት ውዬ አላለም ሼክስፒር #ጋሽ ነብይ መኮንን በሸገር ኤፍኤም ከመዓዛ ብሩ ጋር ባደረገው ቃለመጠየቅ ከተናገረው።