cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አለማመኔን እርዳው ጌታዬ #ማር 9፥24

#አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት #ኤፌ 4፥5 #ንቁ በሃይማኖት ቁሙ ጎልምሱ ጠንክሩ (1ኛ ቆሮንቶስ 16፥13) በዚህ ቻናል የተለያዩ #ያባቶች ትምህርት እና #መፅሐፍ #መዝሙራት እንዲሁም #የቅድሳን ታሪክ #ፊልም አስተማሬ ፅሑፍ ወቅታዊ መልዕቶችን ታገኛላችሁ #ኑ ተዋህዶን እንወቅ #ማንኛውም አሳብ #አስተያየት #ካለችሁ @soliyanae በዚህ ልታደርሱን ትትላላትሁ

Show more
Advertising posts
544
Subscribers
+124 hours
+17 days
-430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ግንቦት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ +"+ +ባለንበት ዘመን አሳዛኝ ከሆኑ ነገሮች አንዱ የቅዱሳኑ ስማቸው ከነሥራቸው መዘንጋቱ ነው:: ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ደማቸው እንዳልፈሰሰ: አጥንታቸውም እንዳልተከሰከሰ ይሔው አስታዋሽ አጥተው ስማቸውም ተዘንግቶ ይኖራል:: +አንዳንድ ንፉቃን ደግሞ ከዚሁ ብሶ ጭራሹኑ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስለ ክርስቶስ ትታ ስለ ቅዱሳኑ ብቻ ትሰብካለች ይሉናል:: +በእጅጉ ከሚያሳዝኑኝ ነገሮች አንዱ የቅዱሳን ሐዋርያት (የ120ው ቤተሰብ) መዘንጋት ነው:: ከ120ው ቤተሰብ የአብዛኞቹ ስም በመዘንጋቱ: ሊቃውንቱም ዝምታን በመምረጣቸው "ያሶን: አርስጦስ: አፍሮዲጡ: ቆሮስ . . . እያልን የ72ቱን አርድእት ስም ስንጠራ ግር የሚለው ዓይነት ትውልድ ተፈጥሯል:: +እስኪ እንዲያው ቢያንስ ሐዋርያትንና ዐበይት ቅዱሳንን እናስባቸው:: አስበናቸው የሚጨመረልን እንጂ የሚጨመርላቸው የለምና:: +ዛሬ የምናስበው ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው:: ጌታችንን ከጥምቀቱ በኋላ ተከትሎ ለ3 ዓመታት ከእግሩ ሥር ቁጭ ብሎ ተምሯል:: ከጌታችን ዕርገት በኋላ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል:: +ለብዙ ጊዜ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ተመላልሶ ሰብኳል:: በመከራውም ተካፍሎታል:: ታላላቆቹ ሐዋርያት ሰማዕትነትን ከተቀበሉ በኋላ ለመጣው አዲስ ክርስቲያን ትውልድ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በቃል የሰማውን አስተላልፏል:: +ወንጌልን ስለ ሰበከላቸው አሕዛብ ብዙ ጊዜ አስረው ይደበድቡት: ያንገላቱት ነበር:: አንዳንድ ጊዜም እሳት እያነደዱ ያቃጥሉት ነበር:: ፈጣሪው ግን በተአምራት እያዳነው ከርሱ ጋር አልተለየም:: +ከከተማ ወጥቶ በዱርና በእስር ቤቶች ብዙ ነፍሳትን: ሽፍቶችንም ሳይቀር ወደ ክርስትና ማርኳል:: ቅዱስ ያሶን ለረዥም ዓመታት ሰብኮ በመልካም ሽምግልና አርፏል:: ❖ ንግሥት ወለተ ማርያም ❖ +ዳግመኛ በዚህ ቀን ኢትዮዽያዊቷ እናታችን ቡርክት ወለተ ማርያም ትታሰባለች:: +ወለተ ማርያም ማለት የደጉ አፄ ናኦድ ሚስት: የአፄ ልብነ ድንግልና የቅድስት ሮማነ ወርቅ እናት ናት:: በንግስትነት በቆየችባቸው ዘመናት (ከ1487-1500 ዓ/ም) የረሃብ ጊዜ በመሆኑ ብዙ ሕዝብ አልቆ ነበር:: +ቡርክት ወለተ ማርያም ከጾምና ከጸሎት ባሻገር የተራቡትን በማብላት ብዙዎችን ታድጋለች:: የንጉሡን ቤተሰብ ወደ መልካም ክርስትና በመምራትም የተመሰገነች ነበረች:: በዚህ ቀንም አርፋ ተቀብራለች:: ❖አምላካችን ከቅዱሳኑ በረከት አይለየን:: ❖ግንቦት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት አንዱ) 2.አባ ብሶይ ሰማዕት 3.ቅዱስ አውሳብዮስ ቀሲስ 4.ቡርክት ወለተ ማርያም ንግሥት (የዐፄ ልብነ ድንግል እናት) ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም 2፡ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3፡ ካህናት ዘካርያስ ወስምዖን 4፡ አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ 5፡ አባ ዜና ማርቆስ 6፡ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ 7፡ ቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሃይማኖት 8፡ ቅዱስ ስምዖን ዘዓምድ ++"+ ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው ጌታ ሆይ! አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት:: እንዲህም አላቸው . . . እነሆ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችሁአለሁ:: የሚጐዳችሁም ምንም የለም:: ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ:: ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ:: +"+ (ሉቃ.10:17) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdusn
Show all...
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠    /(ማቴ ፫:፫/) ✝እንኳን አደረሰን! 🛑 ዝክረ ቅዱሳንን ላልደረሳቸው  እናድርስ እናስፋ ስለ ሀገራችን እንጸልይ ንስሐ እንግባ!!🛑 ✝ 5 ነገሮችን በደንብ ያዙ።     1, 🛑አላማ     2 ,🛑እምነት     3,🛑ጥረት     4 🛑ጥንቃቄ      5🛑ጽናት =>እነዚህን ያዟቸው ተጠቀሙባቸዉ ኑሯቸው። ❇️9ኙ የቅድስና መንገዶች❇️ ፩👉ሃይማኖት ፪👉ጾም ፫👉ጸሎት ፬👉ስግደት ፭👉ምጽዋት ፮👉ፍቅር ፯👉ትህትና ፰👉ትዕግስት ፱👉የዋህነት ✝ንስሐ የተጣመመውን ያቀናል።በኃጥያት የቆሸሸውን ያነጻል፤ንስሐ ለሚገቡ ሁሉ የመላዕክት ንጹሕ ልብስ ይሰጣችኃል።         (ቅዱስ መቃርስ )   ንስሐ ግቡ።✝ ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት) " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::        አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ 🛑በዩቲብለመከታተል👉https://www.youtube.com/@ZikereKedusan 🛑በቴሌግራም👉https://t.me/zikirekdusn 👉 ግእዝ መማር የምትሹ https://t.me/lisanegeez5
Show all...
🔥 2👍 1
ግንቦት1 ✝✞✝ በረከቱ ይደርብና የቅዱስ #ገላውዴዎስና የቅድስት #እምነጽዮን ፍሬ አረጋዊው አቡነ #ቀውስጦስ ሰማዕተ ጽድቅ ዛሬ ተወለደ ✝✞✝ ✝️✞✝️Also on this day was born the Martyr of Righteousness Abune Qewestos the Elder who was the fruit of St. Gelawdios (Claudius) and St. Emene Tsion. May his blessing be with us all. ✝️✞✝️ ✝ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት✝ ' " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn
Show all...
💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠    /(ማቴ ፫:፫/) ✝እንኳን አደረሰን! 🛑 ዝክረ ቅዱሳንን ላልደረሳቸው  እናድርስ እናስፋ ስለ ሀገራችን እንጸልይ ንስሐ እንግባ!!🛑 ✝ 5 ነገሮችን በደንብ ያዙ።     1, 🛑አላማ     2 ,🛑እምነት     3,🛑ጥረት     4 🛑ጥንቃቄ      5🛑ጽናት =>እነዚህን ያዟቸው ተጠቀሙባቸዉ ኑሯቸው። ❇️9ኙ የቅድስና መንገዶች❇️ ፩👉ሃይማኖት ፪👉ጾም ፫👉ጸሎት ፬👉ስግደት ፭👉ምጽዋት ፮👉ፍቅር ፯👉ትህትና ፰👉ትዕግስት ፱👉የዋህነት ✝ንስሐ የተጣመመውን ያቀናል።በኃጥያት የቆሸሸውን ያነጻል፤ንስሐ ለሚገቡ ሁሉ የመላዕክት ንጹሕ ልብስ ይሰጣችኃል።         (ቅዱስ መቃርስ )   ንስሐ ግቡ።✝ ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት) " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::        አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ 🛑በዩቲብለመከታተል👉https://www.youtube.com/@ZikereKedusan 🛑በቴሌግራም👉https://t.me/zikirekdusn 👉 ግእዝ መማር የምትሹ https://t.me/lisanegeez5
Show all...
✝✝✝ እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝ +*" 🌷ልደታ ለማርያም ድንግል🌷 "*+ ✝ ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ: ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ:: ✝ " ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን: ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን) " =>የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን: ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል: ተመስግነዋል:: ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኩዋ መሆን የማይችል: የሰማይና የምድር ንግሥት: የእግዚአብሔርን እናት: እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን:: +ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ:: እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ፀልየዋል:: ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል:: +እመቤታችን ከአዳም ስሕተት በሁዋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች:: (ኢሳ. 1:9) +ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ቀን: በሊባኖስ ተራራ ከ2,022 ዓመታት በፊት ተወልዳለች:: "ሙሽራዬ ሆይ! ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ" (መኃልይ. 4:8) =>ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ (አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች ልጅ የላችሁም በሚል ይናቁ ነበር:: +ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም:: +የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች:: +ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለ40 ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በ40ኛው ቀን 2ቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ አየ:: +እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለ7 ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ:: +በ7ኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ:: +እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች:: "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ . . . ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: (ቅዳሴ ማርያም) +"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ . . ." "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው . . ." (መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9) +እመቤታችን ነሐሴ 7 ቀን ተጸንሳ ግንቦት አንድ ቀን ተወልዳለች:: =>የእመቤታችን የዘር ሐረግ:- *አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ= *በእናቷ:- -ሌዊ-ቀዓት-እንበረም-አሮን-ቴክታና በጥሪቃ-ሔኤሜን-ዴርዴን-ቶና-ሲካር-ሔርሜላና ማጣት-ሐና:: *በአባቷ በኩል:- -ይሁዳ-ፋሬስ-ሰልሞን-ቦኤዝ-እሴይ-ዳዊት-ሰሎሞን-ሕዝቅያስ-ዘሩባቤል-አልዓዛር-ቅስራ-ኢያቄም ይሆናል:: +ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም: በሊባኖስ ተራራ ከ2,026 ዓመታት በፊት ተወልዳለች:: =>የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን:: =>ግንቦት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም (ልደታ) 2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3.ቴክታና በጥሪቃ 4.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ (የእመቤታችንን ቅዳሴ የደረሰበት) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት 2.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ 3.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር =>+"+ መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው:: ከያዕቆብ ድንኩዋኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል:: የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! በአንቺ የተደረገው ድንቅ ነው . . . ሰው እናታችን ጽዮን ይላል:: በውስጧም ሰው ተወለደ:: እርሱም ራሱ ልዑል መሠረታት:: +"+ (መዝ. 86:1-6) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdusn
Show all...
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/