cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቅድስት በርባራ ዘኒቆመዲያ Saint BarBara Αγία Βαρβάρα

ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸዉ መገለጫና መመስገኛ ምድር ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ ◍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት የዓለም ሁሉ መዳኛ ናት ።

Show more
Advertising posts
508
Subscribers
+224 hours
+167 days
+6730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላምና በፍቅር አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝† ብርሃነ ትንሣኤ †✝† የዓለማት ሁሉ ፈጣሪ የዘለዓለም አምላክ ወልድ ዋሕድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ዕለት መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በባሕርይ ኃይሉና ሥልጣኑ ተነስቷልና እንኳን ደስ አለን። ††† ከዚህ በኋላ ለ50 ቀናት እንዲህ እያልን ሰላምታ እንለዋወጣለን:- ††† ክርስቶስ ተንስአ እሙታን! ¤በዐቢይ ኃይል ወስልጣን! ††† አሠሮ ለሰይጣን! ¤አግዐዞ ለአዳም! ††† ሰላም! ¤እምይእዜሰ! ††† ኮነ! ፍሥሐ ወሰላም! በእርግጥም አምላካችን በሞቱ ሞትን ገድሎ፣ በትንሣኤው ሕይወትን አድሎናልና ደስታ ይገባናል። መድኃኔ ዓለም በኅቱም ድንግልና እንደ ተወለደ በኅቱም መቃብር ተነሥቷል። ለደቀ መዛሙርቱም "ሰላም ለእናንተ ይሁን" ሲል በዝግ ደጅ ገብቷል። በዕለተ ትንሣኤው የመጀመሪያውን ደስታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተካፍላለች። የእርሷን ያህል በኃዘን የተጎዳ የለምና። ቀጥለው ቅዱሳት አንስት እነ ማርያም መግደላዊት ትንሣኤውን አይተዋል፤ ሰብከዋልም። ††† አምላካችን ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤው በረከት አይለየን:: በዓሉንም የበረከት ያድርግልን:: ††† "ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም:: 'የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል: በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው' እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደተናገረ አስቡ::" ††† (ሉቃ. ፳፬፥፭-፰) ††† "አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል:: ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኗልና:: ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና::" ††† (፩ቆሮ. ፲፭፥፳)
Show all...
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

◦ ቅድስት እስጢፋና ◦ (Blessed Stephana - Corona - Stephanie - Stefania) - ሚያዝያ 27 | ቅድስት እስጢፋና በመድኃኔዓለም በማመኗ፣ በመታመኗ ለሁለት ተሰንጥቃ ተገደለች። በዚህችም ቀን የሰማዕትነትን ክብር ተቀዳጀች።
Show all...
👍 1🙏 1
.    •❀• [ ስንክሳር ዘሚያዝያ ፳፯ ] •❀•                          •• ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት ••                         ๏-❀-๏ ሚያዝያ ሃያ ሰባት በዚች ቀን የከበረ ቅዱስ ፊቅጦር በሰማዕትነት አረፈ። ለዚህ ቅዱስ የአባቱ ስም ኀርማኖስ ነው። እርሱም ለዲዮቅልጥያኖስ የአማካሪዎቹና የሠራዊቱ አለቃ ነው። ስለ አምልኮ ጣዖት ሥራ ምክሩና ንግግሩ ሁሉ ከእርሱ ጋራ ነበር። የእናቱም ስም ማርታ ይባላል። በክርስትናዋ የጸናች ብፅዕት ናት። ቅዱስ ፊቅጦርም በአደገ ጊዜ አባቱ ወደ ንጉሥ አቀረበው። ንጉሡም በመንግሥቱ ውስጥ ሦስተኛ ማዕርግ አድርጎ ሾመው። በዚያን ጊዜ ዕድሜው ሃያ ዓመት ነበረ። እርሱም የዚህን ዓለም ክብር ናቀ፤ ሥጋ አይበላም፣ ወይን አይጠጣም። ዘወትርም ይጾማል። ጸሎትንም ባለማቋረጥ በቀንና በሌሊት ይጸልያል። በክብር ባለቤት ክርስቶስ ስም የታሠሩትን ይጎበኛቸዋል፣ ለድኆችና ለምስኪኖችም ይመጸውታል። የቅዱሳን ቆዝሞስና ድምያኖስ እናት ቅድስት ቴዎዳዳን በገደሉዋት ጊዜ ንጉሡን ስለ መፍራት ሊቀብራት ማንም አልደፈረም። ይህ ቅዱስ ፊቅጦርም መጥቶ ሥጋዋን ወሰደ። ከንጉሥ ስለሚመጣው ቅጣት ሳይፈራ ቀበራት። ጣዖት ስለ ማምለኩ አባቱን ዘወትር የሚገሥጸውና ብዙ ጊዜም የሚመክረው ሆነ። አባቱም ወደ ንጉሥ ከሰሰው እንጂ አልሰማውም። ተከሶም ወደ ንጉሥ በአቀረቡት ጊዜ "አማልክት ያልሆኑ ርኲሳን ጣዖታትን ለሚያመልክ ሰነፍ ዝንጉ ልብ የለሽ ለሆነ ንጉሥ አላገለግልም። ከዛሬ ጀምሮ ለሕያው ንጉሥ ክርስቶስ እገዛለሁ። የሰጠኸኝንም ገንዘብህን ንሣ" ብሎ ከፊቱ ትጥቁን ፈትቶ ጣለለት። አባቱ ኀርማኖስም ወደ እስክንድርያ እንዲልከውና በኄርሜኔዎስ መኰንን ዘንድ በዚያ ፊቅጦር እንዲቀጣ ንጉሡን መከረው። በዚያን ጊዜም ከአደባባይ አወጡት፤ እናቱም በብዙ ልቅሶ ልትሸኘው መጣች። እርሱም ሲመግባቸው ስለ ነበሩ የታሠሩ ምእመናን ስለ ድኆችና ምስኪኖች ስለ ሙት ልጆችና ስለ ባልቴቶች የሚሹትን በመስጠት እንድትጎበኛቸው አዘዛት። ከዚያም አፉን ለጉመው ወሰዱት። በእስክንድርያ አገር ወደ መኰንኑ ኄርሜኔዎስ ዘንድ በደረሰ ጊዜ ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት። የእግዚአብሔርም መልአክ ወደ ሰማያት አውጥቶ ስለ ክብራቸው ለመናገር የሚያስጨንቁ የብርሃን ማደሪያዎችን አሳይቶ ወደ መኖሪያው መለሰው። መኰንኑም በእሳት በአፈሉት በዝፍት በዲን ደግሞ አሠቃየው። ከዚያም በብረት አልጋ ላይ አስተኝተው ከበታቹ እሳትን አነደዱ። ደግመው ከውሽባ ማንደጃ ውስጥ ጨመሩት። በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም አሠቃዩት። የክብር ባለቤት ጌታችንም ያጸናውና ከሥቃዩ ያስታግሠው፣ መልአኩንም ልኮ ከቁስሉ ይፈውሰው ነበር። ከዚህም በኋላ ወደ እንዴናው ከተማ ላከው። በዚያም ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት፤ ምላሱን ቆረጡ። በእሳት ያጋሉዋቸውን ችንካሮች በጎኖቹ ውስጥ ጨመሩ። እግዚአብሔር ግን አጽንቶ አስታግሦ ያለ ጉዳት በደኀና ያነሣዋል። ከዚህም በኋላ በዚያ በረኃብ እንዲሞት ከዱር ባለ ግምብ ውስጥ አሠሩት። እርሱ ግን መጥረብ የሚያውቅ ስለሆነ ላይዳዎችን በመጥረብና በመሸጥ በየጥቂቱ እየተመገበ የቀረውን ለድኆች እየሰጠ ኖረ። አንድ መኰንንም መጥቶ በዚያ ግምብ አቅራቢያ አደረ። ስለ ቅዱስ ፊቅጦርም እርሱ የንጉሥ የሠራዊት አለቃ የሆነ የኀርማኖስ ልጅ እንደሆነ ነገሩት። መኰንኑም ወደርሱ አቅርቦ ብዙ ሸነገለው። ባልሰማውም ጊዜ ያሠቃዩት ዘንድ አዘዘ። ጅማቶቹን መዘዙ፤ አፉን መቱት፤ ቊልቊል ሰቅለው በእጆቹ ላይ ከባድ ደንጊያ አንጠለጠሉ። ከዚያም ከሚነድ እሳት ውስጥ ጨመሩት ሙጫ፣ አደሮ፣ ማርና ዘይትን አፍልተው በላዩ ደፉበት። በማበራያም አበራዩት። አፉንም በአሞትና በእሬት አመረሩት። ዐይኖቹንም አወለቁት። ደግመውም ዘቅዝቀው ሰቀሉት። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ተገልጾለት አጸናው አረጋጋው። ሥሮቹንና ሕዋሳቶቹን በቦታቸው መለሰለትና አዳነው። አንዲት ዓሥራ አምስት ዓመት የሆናት ብላቴና ነበረች። ቅዱስ ፊቅጦርን ሲአሠቃዩት በቤቷ መስኮት ታየው ነበር። መላእክትንም በእጆቻቸው አክሊሎችን ይዘው እነርሱም በቅዱስ ፊቅጦር ራስ ላይ ሲያኖሩአቸው አይታ እንዴት እንዳየች ለአሕዛብ ነገረቻቸው። እጅግም አደነቁ። ከእርሳቸውም ብዙዎች በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት አረፉ፡፡፡ ያቺም ብላቴና በጌታችን አመነች። መኰንኑም ራሷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። የሕይወት አክሊልንም ተቀበለች። ሁለተኛም የአመኑትን ሁሉ ራሳቸውን እንዲቆርጡአቸው አዘዘ። የሕይወትንም አክሊል ተቀበሉ። ከዚህም በኋላ የከበረች የቅዱስ ፊቅጦርን ራስ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። ተጋድሎውንም ፈጽሞ የሕይወትና የድል አክሊልን ተቀበለ። ምእመናን ሰዎችም ሥጋውን ወስደው። በከበሩ ልብሶች በድርብ በፍታ ገነዙት። እናቱ ማርታም ከአንጾኪያ እስክትመጣ በንጹሕ ቦታ አኖሩት። በመጣችም ጊዜ ከዚያ ወሰደችው። ውብ ቤተ ክርስቲያንም ሠርታ ሥጋውን በውስጥዋ አኖረች ከእርሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። ◦🌿◦🌿◦🌿◦
Show all...
◦●◦●◦ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም፨ ◦●◦●◦ ~❴ ሚያዝያ ፳፯/27 ❵~ በዚህች ቀን፦ ● የከሃዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ ባለሟል በነበረው በወላጅ አባቱ እጅግ ተሠቃይቶ ምስክርነቱን የፈጸመው ታላቁ ሰማዕት #ቅዱስ_ፊቅጦር ዕረፍቱ ነው። ◦◦●●◦◦
Show all...
👍 2
◦ መድኃኔዓለም ነፍሳትን ከሲዖል እንዳወጣ ◦
Show all...
🕊 2
✤ 🌿 ✤ 🌿 ✤ 🌿 ✤ 🌿 ✤ 🌿  ✤ 🌿 ✤ ✤ ••┈┈•• በመስቀሉ ሰላምን አደረገ ••┈┈•• ✤ #ቀዳሚት_ሥዑር (#ሥዑር_ቅዳሜ) እግዚአብሔር ሥነ ፈጥረትን ከመፍጠር ዕረፍት እንዳደረገባት ዅሉ፣ የፍጥረት ርእስ የኾነውን አዳምን ለማዳን ሕማምና ሞት የተቀበለው አምላካችን ክርስቶስ በከርሰ መቃብር አርፎባታል፡፡ (ማቴ. ፳፯፥፷፩)፡፡ ‹ሥዑር› የተባለችበት ምክንያትም በዓመት አንድ ቀን ስለምትጾም (በሰንበት አይጾምም ግን የጾም ቀን በመኾኗ) "የተሻረች - ሥዑር" ለማለት ነው። የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያትና ሌሌችም የጌታ ወዳጆች ጌታችን ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት ጀምሮ ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ፥ አምላካቸው በመቃብር ስላረፈ ዕለቷን ሞቱን በማሰብና ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም አክብረዋታል፡፡ #_ለምን_ቄጠማ_እናስራለን? ቅዳሜ የጠዋቱ ጸሎት ሲፈጸም ካህናቱ ‹‹ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፤ በመስቀሉ ሰላምን አደረገ፥ መሠረተ›› እያሉ በቤተ ክርስቲያን ለተሰበሰቡ ምእመናን የምሥራች ቄጠማ ያድላሉ፡፡ ቄጠማው በኖኅ ዘመን በንፍር ውኃ ምድር በተጠለቀለቀች ጊዜ፤ አባታችን ኖኅ የውኃውን መጉደል ለመረዳት ርግብን ልኮ እርሷም ቄጠማን እንደ የምሥራች ምልክት በአፏ ይዛ በመመለስ፥ የውኃውን መድረቅ እንደተነገረችውና እንደተደሰተ ሁሉ (ዘፍ. ፱፥፩-፳፱) ‹‹በክርስቶስ ሞት፤ ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ፤›› ስንል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅዳሜ ጠዋት ቄጠማ ታድላለች፡፡ የምሥራች ተምሳሌት የኾነውን ቄጠማም፤ ከሲኦል ቃጠሎ ወደ ጥንተ ማኅደራችን ገነት መመለሳችንን  ለመመስከር በግንባራችን እናስረዋለን፡፡ ▸ አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ | t.me/Ewnet1Nat ✤ 🌿 ✤ 🌿 ✤ 🌿 ✤ 🌿 ✤ 🌿 ✤ 🌿 ✤
Show all...
እግዚአብሔርን እናመስግነው።
Show all...
👍 2
11ሰዓት
Show all...
🕊 6🙏 4