en
Feedback
መልህቅ

መልህቅ

Open in Telegram

"ይህም ተስፋ እንደነፍስ መልሕቅ አለን!" ዕብ 6:19 Youtube: https://www.youtube.com/@zanchorr Tiktok: https://www.tiktok.com/@zanchorr ቻነሉና ግሩፑ የሚመሩባቸውን የአዲስ ኪዳን መርሆች ከቀጣዮቹ ክፍሎች ማግኘት ትችላላችሁ። Titus 2 : 2, 6 - 8 1 Peter 3: 8 - 12 James 3: 13 - 18

Show more
4 524
Subscribers
-324 hours
-117 days
+5930 days
Posts Archive
እዚህ አመት መግቢያ ላይ እንዲህ አቅጄ ነበር። ያው ተስፋና መሻት አይከለከል። ከሁለቱ የሆነ ያህልንኳ አከክ ያረኩት የመጀመሪያውን ነው። እርሱንም ካነበብኩት ከጥቂቷ ተነሽቼ የደረስኩበት እውነት ገና ምኑንም እንዳልጀመርኩት ነው። ስፋቱና ጥልቀቱ ከፍታውና ርዝመቱ ከመታወቅ ከራቀ ሆኖብኛል። የሁለተኛው ደግሞ ምኞት ብቻ ሆኖ ወደቀጣይ አመታት ተዘዋውሯል። ያው እቅዴን ያላሳካሁት በጊዜ ማጣት እና በሁኔታዎች አለመመቻቸን ላይ ብቻ የሚሳበብ ሳይሆን ዙሪያዬን በከበበው ስንፍናዬም ጭምር መሆኑ ከፀሀይ ይልቅ የጠራ ነገር ነው። ያም ሆነ ይህ ግን ፈይሳ እንዳለው .. ‘ምንም መጸሃፍት ከማያነብ ሰው ዝርክርክ መጸሃፍት አንባቢ ይሻላል።’ @zanchor @zanchor

በነገራቹላይ ከላይ ካሉት ፎቶዎች በስተመጨረሻ የምታዩት ሙዚየም ነው። እና ውስጡ በጣም ብዙ መፅሀፎችን ይዟል። ከገድላቱና ከድርሳናቱ ይልቅ ልቤን የገዛው እጅግ ጥንታዊ የሆኑ በብራና የተፃፉ የአራቱ ወንጌላት መፅሀፍት እና የጥንት የኢትዮጲያ ነገስታት ቅርስ ማየቴ ነበር። ውስጡን ያነሳሁትን አጠር ያለ ቪድዮ ለቅላቹሀለው።

ዛሬ ይህን ገዳም የመጎብኘት እድል አግኝቼ ነበር እና ጥሩ ጊዜ ነበረኝ። ኦርቶዶክሳውያንእስኪ ምን ገዳም እንደሆነ ገምቱ ? 😁
+2
ዛሬ ይህን ገዳም የመጎብኘት እድል አግኝቼ ነበር እና ጥሩ ጊዜ ነበረኝ። ኦርቶዶክሳውያንእስኪ ምን ገዳም እንደሆነ ገምቱ ? 😁

Romans 4 ALONE can sufficiently dismantle every counter Argument against the Protestant doctrine of justification by faith alone.

Wait, what am I witnessing guys? Is this really true?
Wait, what am I witnessing guys? Is this really true?

Sola Scriptura: The Church has no binding authority that binds the conscience of believers in and of herself and such a divine charism is nowhere taught by Christ or His disciples. Church Indefectibility: The Church cannot fall into heresy as a whole. One denies an active authority as a rule of faith, the other denies the passive extinction of the whole Church based on the promises of Christ.

ዛሬ በአጋጣሚ እዚ ነበርኩ ምን ቤተክርሰቲያን እንደሆነ ገምቱ እስኪ ? አንድ Hint ብቻ ነው ያስቀረሁላቹ😁
ዛሬ በአጋጣሚ እዚ ነበርኩ ምን ቤተክርሰቲያን እንደሆነ ገምቱ እስኪ ? አንድ Hint ብቻ ነው ያስቀረሁላቹ😁

የምናምኑትን ነገር Infallible የሆነ አካል ካልነገራቹ እውነት መሆኑን ልታውቁ ትችላላችሁ እርግጠኛ ግን ልቶኑበት አትችሉም… ይህን አንተ የምትለውን እርግጠኛነት (which is absolute certainity) አንፈልገውም ፤ አያስፈልገንምም!

ኑሮ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ በሸለቆ ቢሆን በተራራ አመቺ ነው ደስ ያሰኛል እርካታን ይሰጣል

እግዚአብሄር እያለ ለምን እፈራለሁ ? አምናንም ካቻምናንም በእርሱ አልፊያለሁ!

ስለ ልሳን የማውቀው ነገር የለም። አለም የለምም የሚል የተደመደመ አቋም የለኝም። የነብይና ሐዋርያ ሹመት የለም። ትንቢት ፤ ፈውስ ፤ አጋንንት ማስወጣት በየትኛውም ጉዳይ ላይ በግልም ቢሆን በጋራ ፀ
ስለ ልሳን የማውቀው ነገር የለም። አለም የለምም የሚል የተደመደመ አቋም የለኝም። የነብይና ሐዋርያ ሹመት የለም። ትንቢት ፤ ፈውስ ፤ አጋንንት ማስወጣት በየትኛውም ጉዳይ ላይ በግልም ቢሆን በጋራ ፀልዮ መልስ ማግኘት አሉ። ነገር ግን እነዚህም በአይነትና ተከታታይነታቸው ከሐዋርያትና ነብያት ዘመን አንፃር ያነሱ ናቸው። የግድም መጠበቅ ያለባቸው አይደሉም።

ስንተቻችን ነን እግዚአብሄር ዛሬም በህይወታችን ጣልቃ ይገባል ፤ ፀሎትን ይሰማናል ደግሞም ይመልሳል ፤ Even ሳንጠይቀው በድካም ሳለንኳ በብዙ መልኩ መንገዳችንን ያቀናል ብለን የምናምን ?
Anonymous voting

አፕሮች ላይ እንለያያለን።
አፕሮች ላይ እንለያያለን።

መጠየቅ ያለበት እንደውም የተለየ ነገር ያረገው ወይም ልዩነቱን ያመጣው ነው እንጂ ባለበት የዘለቀው ሰው አይደለምኮ። ሁለቱም ተመሳሳይ status ላይ ከሆኑ ይህ state እንዲለወጥ የተለየ ነገር ያ
መጠየቅ ያለበት እንደውም የተለየ ነገር ያረገው ወይም ልዩነቱን ያመጣው ነው እንጂ ባለበት የዘለቀው ሰው አይደለምኮ። ሁለቱም ተመሳሳይ status ላይ ከሆኑ ይህ state እንዲለወጥ የተለየ ነገር ያደረገው የካደው ሰው ነው። ስለዚሀ እሱ ነው ምን ጎሎበት ነውና ነው የካደው ተብሎ መጠየቅ ያለበት። ምንም አይኖርምና የሱ በእግጥም ተአምር ይሆናል። ማብራሪያም አንሰጥም። ነገር ግን የጠፋው ሰውዬ በለወጠው status የፀናው ሰውዬ የሆነ የተለየ ነገር አድርጎ አልያ ሆኖለት ነው ማለት non sense ነው።

ከConversion በኋላ Synergy አለ ማለት ሰውየው እግዚአብሄርን ማድመጥ ፤ መረዳት ፤ መውደድ ፤ ማመን ፤ መከተል ይችላል ማለት ነው። ፎርሙላው እምነትህ የሚጠበቀው በመንፈስቅዱስ ብቻ ነው ሲ
ከConversion በኋላ Synergy አለ ማለት ሰውየው እግዚአብሄርን ማድመጥ ፤ መረዳት ፤ መውደድ ፤ ማመን ፤ መከተል ይችላል ማለት ነው። ፎርሙላው እምነትህ የሚጠበቀው በመንፈስቅዱስ ብቻ ነው ሲል እያነፃፀረ ያለው ከስራ ጋር ነው። በስራህ አይደለም የምትጠብቀው ይላል። ይህን ለመቃወም አያይ በስራዬ ጠብቀዋለሀው ብለህ ማለት አለብህ። ይህ ማለት በአጭሩ እምነትህ የሚጠበቀው እግዜር በሚያቀርብልህ ፀጋ እየጠነከረና እያደገ ሲሄድ ስለሆነ ሙሉ Efficient Cause-ኡ እግዜር ነው እየተባለ ነው። የአንተ ሀላፊነት ከላይ እንዳልኩት ይህንን ፀጋውን ባስቀመጠበትና በሚሰጥበት ቦታ መቅረብና መቀበል ብቻ ነው። ስራህ በእግዜር የማመንህና በእርሱም ፀጋን የመቀበልህ ውጤት (ፍሬ) እና ማስረጃ ከሆነ እንዴት ነው መልሶ የእምነትህ ማዝለቂያ Efficient Cause የሚሆነው ?

አዎ ይመስለኛል እና ይችላሉ ግን ቢያንስ ከዌስተርኑ አማራጭ ማብራሪያዎች የሚወጡ አይስለኝም። እስከማውቀው የኢስተርኑን EED መቀበል የሚችሉ አይመሰለኝም። ግን እርግጠኛ አይደለሁም።
አዎ ይመስለኛል እና ይችላሉ ግን ቢያንስ ከዌስተርኑ አማራጭ ማብራሪያዎች የሚወጡ አይስለኝም። እስከማውቀው የኢስተርኑን EED መቀበል የሚችሉ አይመሰለኝም። ግን እርግጠኛ አይደለሁም።

ተገቢ አይደለም። መደረግ የለበትም።
ተገቢ አይደለም። መደረግ የለበትም።

በጣም General የሆነው መልስ በተቻለ መጠን ፀጋውን ከማገኝበት ቦታ ራሴን ላለማራቅ መጣር ነው። በወንድሞች ህብረት ውሰጥ መገኘት እና ቅዱስ ቁርባንን ያለማቋረጥ መውሰድ የመጀመሪያው ትልቁ መንገድ
በጣም General የሆነው መልስ በተቻለ መጠን ፀጋውን ከማገኝበት ቦታ ራሴን ላለማራቅ መጣር ነው። በወንድሞች ህብረት ውሰጥ መገኘት እና ቅዱስ ቁርባንን ያለማቋረጥ መውሰድ የመጀመሪያው ትልቁ መንገድ ነው። ሰው የዋለበትን ስለሚስል በዛ ውስጥ በመገኘት ውስጥ ብቻ ሀይል አገኛለሁ። በግል ደግሞ ያው የምታውቃቸውን መፀለይ ፤ ቃል ማንበብ የሚባሉ ልጠቅስልህ እችላለሁ። ነገር ግን ችግሩ እነዚህን ራሱ ማረግ የምንደክምበትና ምንዝልበት ጊዜ አለ እና ያኔ የሚረዳኝ ሁለት ነገር ነው። አንደኛ በዛው ድካም ውሰጥንኳ ሆኜ የክርስቶስን ፍቅር ፤ የእግዚአብሄርን ምህረት በተደጋጋሚ ማሰብ ነው። ሁለተኛው ደግሞ መዝሙር ነው። መዝሙር ማዳመጥም ሆነ መዘመር የእግዚአብሄርን ምህረት እንዳስብ የሚረዳኝ ነው ፤ ይበልጡንም ደግሞ ወደፀሎት የሚስበኝም ነው። ብዙ መዝሙሮችን እከፍትና እሰክነካና እስኪያንበረክከኝ ድረስ እየቀያየርሁ አዳምጣለሁ። ይብዛም ይነስም የገባው ነውና የሚወጣው የሆነ ጊዜ ላይ ሲመልሰኝ አገኘዋለሁ። አንዴ ከተንበረኩ በኋላ ግን ብዙ ድካሜን ጠርጎልኝ ስለሚሄድና አቅም ስሚሰጠኝ በተቻለ አቅም ተመሳሳይ ሪትም ይዤ ለመቀጠል እጥራለሁ። ይህ እንግዲ በግል ላለ መንፈሳዊ ጉዞ ነው። እዚህ ላይ ከላይ ያልኩት ህብረት ሲታከልበት እና በዛም ህብረት ውስጥ በአገልግሎትና ሀላፊነቶች ራስህን ስታስጠምድ የተሻለ ለመመላለስ ይረዳሀል። ያው ነገሩን በጣም Mechanical ማረግም አልፈልግም ምክንያቱም ሁሌ ለሁሉም እንደዛ ይሰራል አይደለም። ቢያንስ ግን መጨረሻ ላይ የሚያቆመን የእግዚአብሔር ፀጋ መሆኑን አውቃለሁ። ፀጋው ለበሽተኞችንጂ ለፍፁማን የቀረበ አይደለምና በጣም በደከመን ሰአት ወደፀጋው ለመቅረብና ወደጌታ ለመሸሽ በጣም ትክክለኛው ሰአት ነው።

የወጀቡ አዛዥ የተራራው ሰሪ የሸለቆው ጌታ ለጨለማው መሪ የማዕበሉ አዝማች የመብረቁ ንጉስ አንተ ነህ የእኔ አባት የእስራኤል ቅዱስ https://youtu.be/FCGExvNywx0?si=C5844lAbY-jdvOwZ