HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
Open in Telegram
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239
Show more2 280
Subscribers
-124 hours
+107 days
+3530 days
Posts Archive
"የእንባ ጸሎት"
◈ የእንባ ጸሎት መንፈሳዊ ኃይልን በማሳደግ በኩል ያለው ቦታ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ "የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ" ብሎ ጌታ ሲያስተምር፤ ካስተዋልን ቅዱስ መንፈስን የሚስብና ርኩስ መንፈስን የሚስብ ባሕሪይ፣ ጠባይ፣ ሁኔታና ጊዜ እንዳለ ለይቶ ሲነግረን ጭምር ነው፡፡ ከነዚህ ቅዱስ መንፈስን ከሚስቡ መንፈሳዊ ልምምዶች ውስጥ አንደኛው የእንባ ጸሎት ነው፡፡ ወደ ሰማይ አድራሻውን ያመራ የእንባ ቃል፦ የውስጥ ሕይወትን ኃጢአትና በደል ያጥባል፣ የልብ ንጹሕነትን በፈጣሪ ፊት ይገልጣል፣ የእግዚአብሔርን፣ መንፈስ የሚማርክ ትሕትናንና ታዣዥነትን ያስተምራል፣ መናፍስትን እንደ ጸበል ውሃ ያቃጥላል፣ አስረግጦ መልእክት ወደአርያም የመላክን እምነት ያበልጽጋል፡፡ ይህም ማለት ደብዳቤ በፖስታ አድራሽ ወደተፈለገው ቦታ እንደሚደርስ ሁሉ፤ ጸሎትም በእንባ በኩል ወደላይ ያርጋል።
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
◈ የትኛውም ሰባኪ (መምህርና መጽሐፍ) ስለ እግዚአብሔር ሲናገር ዲያቢሎስንም አይተወውም:: በቀጥታ ሰይጣን አሊያ አጋንንት ባይል እንኳ ስለ ክፉዎቹ ግብር ወዲያም አለ ወዲህ ያነሣል:: ስለ ውሸት፣ ክሕደት፣ ምቀኝነት፣ ዘርኝነት፣ አድመኝነት፣ ንፉግነት፣ ሌብነት፣ ግዴየለሽነት፣.. ሳይገሥጽ የሚሰብክ መንፈሳዊ ትምህርት አለ ይሁን? እንግዲያስ ዲያቢሎስ ማለት በነዚህ ክፉ ባሕሪያት የሚገለጽ ፍጡር ማለት እኮ ነው:: ችግር የሆነው ይህንን ክፉ ከነስሙና የውጊያ ስልቶቹ ስለተማማርነው ነው? እኔ ሐሰትን ለብቻ ሰይጣንን ለብቻ አድርገው የሚያዩና ይህን ዕይታቸውን የሚያስፋፉ ሰዎች ይደንቁኛል:: ብቻም ሳይሆን ወንጌል "[ዲያቢሎስ] ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል" ስለማለቷ ያነበቡ፥ ካነበቡም እንደሚገባ ያጤኑ አልመሰለኝም:: (ዮሐ. 8፥44)
◈ ቅድስናን ስናሞግስ ርኩሰትን በማውገዝ ነው፤ መልካምን መልካም ያልነው ከመጥፎው ለይተን ነው፤ ነግቷል እኮ ያስባለን የለሊቱ ማለፍ ነው፤ መጠንን ትንሽ ብለን የመዘንነው ከትልቁ አንጻር ነው:: .. [ከፀሐይ በታች ያለቺው] ዓለም እንደዚህ ናት:: አዳም ክፉና ደጉን የሚለይና የሚስማማ ባሕሪይ ይዞ ምድራዊ ኑሮውን ከጀመረ ወዲህ ሰውነት በሁለት መስተቃርን ዋልታዎች መካከል የሚባትት ሕልውና ሆኗል:: (ዘፍ. 3፥22) መጽሐፍ ቅዱስ ከመነሻው ታሪክ አንስቶ የሚነግረን ይህንን ነው:: ከእናንተ መካከል ከዚህ እውነት ውጪ የሆነ የመጽሐፍ ታሪክ የሚያነሣልኝ አለ?
◈ ስለ አዳም ስናወራ ስለ እባብ ተንኮል እናነሣለን:: ስለ አቤል ደግነት ስናነብ ድንጋይ ስለ ጨበጠው ቃየንም እናውቃለን:: ስለ ኖኅ መርከብ ለማውራት የኖኅ ጎረቤቶች ያስፈልጋሉ:: ስለ አብርሃም ጥሪ ስንማር ዙሪያውን ስለ ከበበው ባዕድ አምልኮት መገንዘብ ግድ ይላል:: ሙሴን ስንተርክ ፈርዖንን ማውጣት አንችልም:: ዳዊትን ከጎልያድና ከሳዖል ውጪ ማንሳት ታሪኩን አያሟላም:: ወደ ሐዲስ ኪዳንም አለፍ ብንል ያለው ይኸው ነገር ነው:: ሰብአ ሰገል ሲታሰቡ ሄሮድስ አይዘነጋም:: ለተቀበሉት የእግዚአብሔር ልጅነትን ሰጣቸው ያለው የገዛ ወገኖቹ እንዳልተቀበሉት ነግሮን ሲያበቃ ነው:: (ዮሐ.1፥11-12) በአጠቃላይ የጽድቅ ዕሴቶችን የሚያበረታታው መንፈሳዊው ዓለም ከኩኔው ጎራ ያሉትን በአንድም በሌላም መንገድ ሳይጠቅሳቸው አያልፍም:: ታዲያሳ ትሕትናን ለማስተልቅ ትዕቢትን ካላሳነሱ እንደምን ይሆናል?
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
እቆርባለሁ ግን መንፈሱ አልወጣልኝም በበዓለ ሃምሳ አይሰገድም ለምትሉ የመናፍስትን ጉዳት አቃለልን || ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ለምን ተባለ? #ንቁ 🔥💥
https://youtu.be/VwCdzFw6jGA
መካን በዘመን ሁሉ የማይከናወንለት ሰው የዕብደት መተት ሲላክብን ምልክቶቹ የዕብደት አጋንንት || ሰላማዊ ኑሮ ለመኖር | የሚጸጽተንን ሥራ አቁሙ 🚩💥
https://youtu.be/6B0okaNoiYw?si=c-NZz4vNsbcw9QuA
◈ ስትጸልይ በማክበር ውስጥ መሆንን ተለማመድ፣ የልብና የሥጋ ማክበር ይኑርህ፣ የስሜቶች ሰላምም እንዲሁ፤ ቀስ በቀስ መዝሙራትን፣ ወንጌላትንና የዘወትር ጸሎቶችን አጥና፤ በሁሉም ጊዜ ውስጥ ጸሎት መጸለይን ተለማመድ፣ ስትሠራ፣ ስትራመድና ከሌሎች ሰዎች ጋር ስትቀመጥ እንኳ፣ ዘወትር ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እኔ ኃጢአተኛውን ማረኝ እያልህ መጸለይን ተለማመድ፤ በማንኛውም ጊዜ ለሌሎች ሰዎች መጸለይን ተለማመድ፣ ለሁሉም ሰዎችም ፍቅር አሳይ፣ ለጠላቶችህና አንተን ለሚሰድቡህ ሰዎች እንድትጸልይ የሚያዝህን የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ተለማመድና ተግባራዊ አድርግ።
(አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ)
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
ስንጸልይ ስንሰግድ ፈተና ከበዛብን ጠቋርን ስናመልከው ኖረን ሰይጣንን አለማወቅ ጎዳን || የመኖራችን ትርጉም ምንድነው? #ethiopia #eotc 💥🚩
https://youtu.be/sRgmQ1QDPWY?si=LCg6dwaHiUPBxwKO
አጋንንት በመቁጠሪያ አይወጣም ከንስሐ በኋላ ከባድ ጸጸት ማህተብ የሌለው ሆዳም ነው ለቅዱሳን ስዕላት መስገድ ዮናታን እውነት ታሟል! 🔥💥🚩🙏
https://youtu.be/zvp4nbdaZvQ
"ዮሴፍ ጭንቀት አልነበረውም ብለህ ታስባለህ? ሙሴ ጭንቀት አልነበረውም ብለህ ታስባለህ? ዳዊት፥ ሐዋርያት፥ አባቶቻችን፥ ቅዱሳኑ? ሰማዕታቱ? ትጉሀኑ?"
◈ ሁሉም ጭንቀት ነበረባቸው፤ በእነርሱና በእኛ መካከል ያለው ልዩነት እኛ ጭንቀታችንን መፍታት የምንፈልገው በራሳችን፤ በገንዘባችን፣ በዘመዳችን፣ በጉልበታችን ወዘተ...ነው። እግዚአብሔር መፍትሔ አለው፤ ስለሆነም ራሳችንን ለእግዚአብሔር ሰጥተን እንዲህ እንላለን "እግዚአብሔር ሆይ ህይወቴን ምራው፤ አንተ በአስቀመጥክልኝ መንገድ መጓዝ እፈልጋለሁ፤ አንተ ለእኔ የተሻለውን መንገድ እንደምትመራኝ አውቃለሁ፤ ስለሆነም በእውነተኛው መንገድ ምራኝ፤ የሕይወቴን አቅጣጫ ወስንልኝ።
◈ እግዚአብሔር ሕይወታችን ሁሉ መቆጣጠር እንደሚችል ማመን ያስፈልጋል፤ እኛ ውጥረትና ጭንቀት እንደፈለገው የሚያደርገን ግዑዝ ወይም ቁስ ነገር አይደለንም ዕቃ ወስዳችሁ ክብደት ወይም ግፊት ያለውን ነገር ብትከቱበት ይሠበራል፤ እኛ ግን የእግዚአብሔር ልጆች ስለሆን ውጥረት፤ ጫና ወይም ጭንቀት ውስጥ ስንሆን ብንገላታም አንሰበርም እግዚአብሔር ያወጣናል፤ አንዳንድ ጊዜ ልንፈተን እንችላለን፤ እግዚአብሔር ሰይጣን እንዲፈትነን ሊፈቅድ ይችላል፤ ነገር ግን ብዙ መከራ ወይም ስቃይ እንዲያመጣብን አይፈቅድለትም፤ የእግዚአብሔር እጆች ሁል ጊዜ ይጠብቁናል፤ አይተወንም ችላም አይለንም፤ ጭንቀታችንን ሁሉ ያስወግድልናል፤ መልካም ህይወትን ይሰጠናል፤ ሠላምን ያጎናጽፈናል ዘላለማዊ በሆነ ፍቅሩ፤ ትምህርቱ መስዋዕትነቱ ማረጋገጫ ሰጥቶናል፤ ኃያላን እጆቹም ሁል ጊዜም ይጠብቀናል፤ በዕውነት ይህ እንዲሆን እንደ ቅዱሳኑ በእምነት ከፍ ልንል ያስፈልጋል።
(ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ)
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
«ፍቅር ቊስል ነው»
◈ እውነቱ ይህ ነው፣ ፍቅር የሚለካው በልባችን ላይ በተወው ቊስል ልክ ነው፤ እጅግ የምንወዳቸው ሰዎች አሳምመውን ይሆናል፤ እኛም እጅግ የሚወዱንን ሰዎች አሳምመን ይሆናል፤ ምክንያቱም ፍቅር የሚታየው በታገስነው ቊስል ውስጥ ነው።
◈ ፍቅር የሚታወቀው የተለዋወጥናቸውን ቃላት ሳይሆን በምንታገሠው ቊስል፣ በተሰማን የውስጥ ሕመም፣ በከፈልነውን መሥዋዕትነትና በተካፈልነውን ብርሃን ነው። ከትንሣኤው በኋላ በሐዋርያቱ ፊት የተገለጠው ክርስቶስ እርሱ የሚወዱት ጌታ እንደሆነ ለማስረዳት ያሳያቸው የትንሣኤው ድል ማብሠሪያ መለኮት አይደለም፣ የፍቅሩ ማስረጃ ቊስሉ ነበር። "ወደ እኔ ኑ ቊስሌን ዳስሱ፣ እጃችሁንም ስለ እናንተ ፍቅር በቆሰልሁት ቊስል አስገቡ" ነበር ያላቸው። "አታስታውሱኝም፤ አላወቃችሁኝም?"
◈ እስከ ሞት ድረስ የወደድኳችሁ እኔ ነኝ፤ ለፍቅሬ ማረስጃ እንዲሆናችሁ ደግሞ ቊስሌን ተመልከቱ ነው ያላቸው። ፍቅር ቊስል ነው፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ክብርና ምስጋና የምናገኘውም በምድር ሳለን በነበሩ ስኬቶቻችንና ባስገኘናቸው ውጤቶቻችን ሳይሆን በታገሥናቸው መከራዎችና በተሰቃየንባቸው ሕመሞች ልክ ነው። ለዚህም ነው በአበው መጽሐፍ አንድ ቅዱስ አባት ለረጅም ዓመት በሰውነትዋ ላይ ቆስሎ የምትሰቃይን ሴት ሊጠይቁ ሲሔዱ "እዩት ቊስሌን አጎንብሰው ቢያዩት አጥንቴ ይታይዎታል" አለቻቸው። እርሳቸውም ጎንበስ ብለው "ብዙ ዓመት በታገስሽው በቊስልሽ ውስጥ የሚታየኝ አጥንት ሳይሆን ገነት ነው" አሏት።
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
◈ ወዳጄ ሆይ! መንፈሳዊ ተጋድሎን አትፍራ፥ ከእርሱም አትሽሽ፤ ተጋድሎ ከሌለ ምግባር ትሩፋትም የለምና፤ እምነትና ፍቅርም ካልተፈተኑ በእውን ከአንተ ጋር ስለ መኖራቸው ርግጠኛ መኾን አይቻልም፤ እነዚህን በርግጥ አንተ ገንዘብ አድርገሃቸው እንደ ኾነ የሚታወቀው መከራ ሲገጥምህ ነውና፤ ስለዚህ ተጋድሎን አትፍራ ከእርሱም አትሽሽ''፡፡
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
ባታለብሰኝ ኖሮ ነውረን ሸፍነህ፤
ባታቆመኝ ኖሮ በደሌን ከድነህ፤
በጠፋ ነበር ስም አጠራሬ፤
ድካሜ ብዙ ነው እንደ ራስ ፀጉሬ፤
ጉዱፉን አልይ የወንድሜን በደል፤
አለ በእኔ ላይ ምሶሶን የሚያህል።
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
መንፈሳዊያን ለምን መስተፋቅርን ይፈልጋሉ?? የጓደኛን ኃጢአት፣ በደል መሸፈን መንፈሳዊ ለውጥ ሲኖርህ ዲያብሎስ ሥራውን ይጀምራል #ethiopia 🚩🔥💥
https://youtu.be/Y81BG3kmmKA
🌹🌹ዲያቆን ዘማርያም ዘለቀ ወንድማችን እንኳን ደስ አለህ፤ደስ አላችሁ። እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል። የቅዱሳን አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር ጋብቻችሁን ይቀድሰው፣ ይባርከው፣ ያጽናው በእውነት። 🌺🌹🌺
+++
+++
+++
+++
+++
+++
+++
+++
+++
+++
+++
+++
+++
+++
+++
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
🚩ድንግልና ለምን "ዓይን" እንደተባለ የሚያውቅ ማን ነው?
◈ ድንግልና የአንድን ሰው ማንነት እስከ መወሰን ወይም ገልጦ እስከ ማሳየት የሚደርስ መሠረታዊ ምሥጢር እንድትይዝ ሆና በመፈጠሯ አይደለምን? ዓይን ታያለች እርሷም ትታያለች፡፡
◈ አንቺ ሴት ከጋብቻሽ በፊት ድንግልናሽን ያጠፋሽው ከሆነ ስታገቢ ባልሽን በምን ታዪዋለሽ? ድንግልና "ዓይን" ተብላለችና፤ ባልም ድንግልናውን ጠብቆ ካልኖረ ረቂቅ መነጽር ድንግልና የለውምና ሚስቱን በምኑ ይመለከታታል? ዛሬ ዛሬ ብዙ ባልና ሚስቶች በጥቃቅን አለመግባባቶች ለአንድ ቀን እንኳን ተያይተው የማያውቁ ያህል የሚሆኑትና የሚኳረፉት ምናልባት ድንግልናን መጠበቅ ስለቀረ ሕገ እግዚአብሔርም እየፈረሰ ስለመጣ ይሆን? በማለት መጠየቅ አስተዋይነት ነው፡፡
◈ ድንግልና ሁሉን አርቆ የሚያሳይ ከፍተኛ ቦታ ነው፤ የኑሮ ደረጃቸውን በድንግልና ሆነው መርምረውና ተመልክተው ያገቡ ሰዎች አይጸጸቱም ማለትም አንድ ሰው ደረጃው ማግባትም ይሁን መመንኮስ በሚገባ ለይቶ ማወቅ የሚችለው ንጽሕናውን ጠብቆ ለመኖር ከቻለ ብቻ ነው፡፡
◈ መጽሐፍ ቅዱስ "የሰውነት መብራት ዓይን ናት፡፡ እንግዲህ ዓይንህ ጤናማ ብትሆን ሰውነትህ ብሩህ ይሆናል፤ ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል ይላል፡፡ (ማቴ 22፥23) እንደዚሁም ሁሉ በዓይን የተመሰለች ድንግልናም በሕገ ወጥነት በዝሙት ሥራ ከጠፋች አንደ ሰው ሰውነቱ ሁሉ እንደጨለመበት ሊያምን ይገባዋል፤ ምክንያቱም ድንግልና ሃይማኖትና ምግባር መሠረታቸውን ለቀው እንዳይናጉ የሚያደርግ ጽኑ መሠረት ነውና፤ ማለትም አመለካከት፣ አነጋገርና አሠራር ሚዛናቸውን እንዳልሳቱ ከድንግልና አጠባበቅ አንጻር መናገር ይቻላል፤ ስለዚህ ድንግልና "ዓይን" ቢባል ያንሰዋል እንጂ አይበዛበትም፡፡
◈ ብዙ ጊዜ ድንግልና ለሴቶች የሚነገረው በጉልህ ምልክት የሚታወቀው በእነርሱ ስለሆነ ነው፤ ነገር ግን ድንግልና ለወንዶችም የጸና ተጠቃሽ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ። "ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው፣ ድንግሎች ናቸው" በማለት ከትቦ ይዟል፡፡ (ራዕ 14፥4) ንስሀ ግን የወደቁትን ታነሳለች ቀማኛውን መጽዋች፣ ዘማዊውንም ድንግል ታደርጋለች።
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
ድንግል ሳትሆን ዲያቆኑ በመስተፋቅር አገባት ይቅርታ ማድረግ እንዴት ይከብዳል? ክርስትና እሩቅ መጓዝ ነው? || ጦርነቱ ከዲያብሎስ ጋር ነው! 🚩💥🔥🙏
https://youtu.be/0b99pWKW3NI
ቆራቢ ነበረች በዝሙት ጣልኳት ሥዕሏን ስስል ይጥለኝ ነበር 14 ዓመት ጠብቃ ልጅ አገኘች || የልደታ ማሪያም ተዓምር | ቁርባንዋን አፈረስኩባት! 💥🚩
https://youtu.be/hUhXFLPSGl8
🌹የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር። (ት.ኢሳ 1፥9) 🌹🌹🌹
🌹እንኳን ለእመቤታችን ለቅደስት ድንግል ማሪያም የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ጸሎታችሁን ትስማችሁ። ረድኤት በረከቷ፣ አማላጅነቷ ከሁላችን ጋር ይሁን። #ሸር #ሸር
🌹🌹🌹🌹
ለመቁረብ ብቁ አይደለሁም ለምትሉ! 5ቱ የእመቤታችን ሀዘናት 3ቱ የመከራ ምንጮች እውነተኛ ጸጸትና ኃይሉ የቅዱስ ቁርባን በረከቶች 🚩💥🙏😭
https://youtu.be/y1z0nZzS84M
◈ ኮከብ ብሩህ ቅዱስ ማርቆስ ዘሠረቀ አምእስክንድርያ፤ ቤተ ክርስቲያን ዘንሰምያ ኮኖሙ አበ ለሰብዓ ግብጽ ወኢትዮጵያ በከመ ጳውሎስ ሐዋርያ። (በእስክንድርያ ቤ/ክ የተገኘው ብሩህ ኮከብ ቅዱስ ማርቆስ ለኢትዮጵያና እናት ለግብጽ ሰዎች እንደ ጳውሎስ ሐዋርያ አባት ሆናቸው።) 🚩💥
የወንጌላዊው እንዲሁም የሰማዕቱ ✨✨ የቅዱስ ማርቆስ ✨✨ ረድኤት በረከቱ ከሀላችን ጋር ይሁን። 🙏🙏
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
