en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

Open in Telegram

💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።

Show more
8 806
Subscribers
-724 hours
-287 days
-530 days
Posts Archive
አሁን live መርከዝ ተውሒድ የተማሪዎች ፕሮግራም https://t.me/SadatKemalAbuMeryem?livestream

_ اللهمَّ يا مقلب القلوب ثبت قلوبنا على دينك الله المستعان .

የህይወት ትርጉሙ አላህን መፍራት ሲሆን የመኖር ጣዕሙ ግን መልካም ትዳር ነዉ። አላህ ይወፍቀን። منقول

ከሐራም ነገር ከባዱ የመጀመሪያው ነው። ከዚያ ሲደጋገም እየቀለለ ይሄዳል። ከዚያ እንዲሁ ተራ ነገር ይሆናል። ከዚያ ልማድ ይሆናል። ከዚያ ይጣፍጣል። ከዚያ ልብ ይሸፈናል። ከዚያ ልብ ሌላ ሐራም መፈለግ ይጀምራል። አንድ ሷሊሕ ሰው እንዲህ ይላል፦ "ነፍስህ ወደ ወንጀል ከጋበዘችህ በዚች አንቀፅ አጭር ቃለ መጠይቅ አድርግላት :- { قُلۡ أَذَ ٰ⁠لِكَ خَیۡرٌ أَمۡ جَنَّةُ ٱلۡخُلۡدِ ٱلَّتِی وُعِدَ ٱلۡمُتَّقُونَۚ } "(እንዲህ) በላቸው፡ 'ይሄ ነው የሚሻለው ወይስ ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጧት የዘለዓለሟ ጀነት?' " [አልፉርቃን፡ 15] በዚህ ሐራም ነገሮችን መዳፈር በበዛበት ዘመን ይህቺን አንቀጽ ማስተዋል ምንኛ አንገብጋቢ ነው?! ከዐረብኛ የተመለሰ = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

🔖ከእዉቀት በፊት አደብ ይቀድማልና !ይህን ጣፋጭ ምክር አድምጡ። ~

«ሒልየቱ ጧሊቢል ዒልም» ☞︎︎︎ ክፍል - 17 ❝የሱና ብርሃን ትምህርት ቤት ግሩፕ ላይ በየ ሳምንቱ የሚቀርብ ትምህርት።❞ 🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ጆይን፡‐  t.me/fejir_tube

Repost from Sadat_Text_Posts
የመውሊድ ውድድር ፈተና አንድ 1) ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ስንት ጊዜ ነው መውሊድ በኣል ላይ የተሳተፉት? ___________________ 2) የትኛው ከተማ ላይ ነበር መውሊድ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሃባዎች የተከበረው? _____________________________________ 3) ሰሃባዎች የትኛውን አይነት የመውሊድ አወጣጥ ነበር ለታቢኢኖች ያስተማሩት? ________________________________________________________ 4) ምን አይነት ምግብ ነበር በመውሊድ ወቅት ሲመገቡት የነበረው? ________________________________________________________ 5) መውሊድ ላይ በሰሃባዎች ሲዜሙ ከነበሩ ዘፈኖች ውስጥ ዋናዋናዎቹን ጥቀስ ___________________________________ ___________________________________ • አስታውሱ ሁሉም መልሶች ከሚከተሉት መሰረታዊ ምንጮች ነው መሆን ያለባቸው፡ 1. ከቁርኣን፣ 2. ከሀዲስ፣ 3. ከሰሃባዎች ንግግር በደንብ አስባችሁ፣ ጊዜያችሁን ውሰዱና ቁርኣንን ፈትሹ፣ ቡኻሪ ሙስሊም እና ሌሎች የሀዲስ መዛግብትን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ የተተረጎመ https://t.me/SadatTextPosts

በቁርዓን ውስጥ አሏህ የሚያስቀውም የሚያስለቅሰውም እሱ እንደሆነ ይናገራል። ((وَأَنَّهُ هُوَ أَضْحَكَ وَأَبْكَى)) በሌላ ቦታ ላይ በዚህ  ቁርዓን እንደምንደነቅ፣ እንደምንስቅ ግን ደግሞ ስናዳምጠው እንደማናለቅስ ተናግሯል። ((أَفَمِنْ هَذَا الْحَدِيثِ تَعْجَبُونَ وَتَضْحَكُونَ وَلا تَبْكُونَ)) የሚያስቀንም ይሁን የሚያስለቅሰን አሏህ ሆኖ ቁርዓንን ስናዳምጥ ለምን አናለቅስም? በወንጀላችን ምክንያት ልባችን ደረቀ፣ በዚህም ምክንያት ቁርዓንን ስናዳምጥ የማናለቅስ ሆነን አነጋን። #فائدة

ከሞትክ በኋላ ዱንያ ምን እንደምትመስል ማየት ከፈለክ ሌሎች ሰዎች ከሞቱ በኋላ ያለውን ክስትተት ተመልከት!! በጣም የሚዋደዱ ሰዎች በጣም የሚወዱትን ወዳጃቸውን ከሞተ በኋላ በአጭር ጊዜ እንደት እንደሚረሱት ስታይ አንተም ከሞትክ በኋላ በጣም የምትወደው ሰው በፍጥነት እንደሚረሳህ እርግጠኛ ትሆናለህ። ስለዚህ ህይዎትህን መቼም ለማይረሳህ አላህ አድርግ ከአላህ ጋር ያለህን ግንኙነትም አሳምር የማይረሳውና የማይጠፋው እርሱ ብቻ ነውና.....

~«ዘወትር ጠዋትና ማታ "ሱረቱል ፈለቅን እና ሱረቱ ናስን" መቅራት ፣ ከጂንም ሆነ ከሲህር እንዲሁም ከሌሎች የበሽታ አይነቶች ራስን ለመጠበቅ ይህ ትልቅ ሰበብ ነው»። ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁሏህ) t.me/https_Asselfya

ሒልየቱ ጧሊቢል ዒልም ክፍል - 16 የሱና ብርሃን ትምህርት ቤት ግሩፕ ላይ በኢብኑ ሙነወር በየ ሳምንቱ የሚሰጥ ትምህርት። የቴሌግራም ቻናል፡‐ https://t.me/fejir_tube

🎧ከቁርአን ጋር እንኑር ! =

ስደትና ስራ እጥነት ~ስራ እየጠፋ ነው.  ስራ ፈተው የቆዩ ብዙ ወራቶችን ያስቆጠሩ ብዙ  እህቶች እንዳሉ እየሰማን ነው።   ስራ ሊሰራ ተሂዶ ስራ መፍታት ቢከብድም። ሆኖም አላህ ያለው ነው የሚሆነውና. በተስፋ መጠበቁ አማራጭ ነው።  ~ግን.  ለምን ከኩንትራት ቤት. ትወጣላችሁ?የሚለው ጥያቄ ነው። ኩንትራት ቤት ያላችሁ ስራ ከፈቱት ትምህርት ውሰዱ።  ስራ በቀላሉ እየተገኘ አይደለም። ባላችሁበት ፅኑ ።ደሞዝ ቢያንስም. ያለ ስራ ወራትን ከማስቆጠር እዛው ይሻላል። ታገሱ። ሊመቻችሁ አይደለም የሄዳችሁት ። ምቾትን ትታችሁ ምቾት ለማትረፍ ነው። ረፍትን አታችሁ ረፍትን ለማግኘት አይደል እንዴ? ~ሌላው ስራ ፈታችሁ ወራትን እስከ አመት ከመቆየት. መጥታችሁ.  በሌላ መስመር መሄድ.  ይሻላል።  ምናልባት. ዛሬ፣ነገ ይገኛል ሲባል ነው. አመቱ የሚመጣው. ሆኖም ግን.   ያሉትን አማራጮች. መጠቀም ግድ ነው።  በስደት የሚያልፈው ግዜ. ቀላል አይደለም። ስደት  እየጠቀመም.  ይጎዳል ። ብር ሰጥቶ እድሜን ይቆርሳል። እወቁበት ። ~ሌላው.  ስራ የምታማርጡ፣ሲገኝ ዙሪያ አጥር የምታደርጉ እህቶችም እንዳላችሁ ከእህቶች እየሰማን ነው። ማማረጥ መብታችሁ ነው። ስታማርጡ አመት ከሞላችሁ ፣ብዙ ወር ከሆናችሁ.  ኪሳራው የበዛ ነው። አታማርጡ ።ብታማርጡም እየሰራችሁ አማርጡ ። ~ ስደትን አትልመዱት።አይመቻችሁ። የመጨረሻ አማራጫችሁ አታድርጉ ።ገደብ ይኑረው። ሰርታችሁ ለመለወጥ ይሁን። የትዳርም ግዜ እንደሚያልፍ እወቁት። የመውለጃውም ሰአት ያልፋል።ስለዚህ ብዙ አትቆዩበት። የመውለጃና የትዳር ግዜው አልፎ ገንዘብ ቢመጣ ምን ሊሰራ ።ማን ሊበላው። ግማሽ እድሜያችሁን ወይም አብዛሀኛውን አትገብሩበት። ~የመቆያ ግዜያችሁን እራሳችሁ ወስኑ። ቤተሰብ ብዙውን ግዜ እንድትመጡ አይፈልጉም። አንዳንድ ቤተሰቤች ሲቀሩ። የሚያገኟትን ጥቅም እንድትቅር አይፈልጉም። ባሎችም እንደዛው።  አተርፍ ባይ አጉዳይ እንዳ ይሆን ነገሩ በጥንቃቄ ቢሆን። ከማንም በላይ ለራሳችሁ እዘኑ።ለራሳችሁ ዋጋ ስጡ። ብዙ ስራ እንዳለባችሁም ተገንዘቡ።የዛሬን አቃጥላችሁ የነገን አታጨልሙ። እራሳችሁን ምከሩ። ቆይታችሁንና ውጤታችሁን አነፃፅሩ።  አበቃሁ.     ብታደርሱልኝ ደስ ይለኛል         ✍ አቡ ሀፍሷ @AbuHafsaYimam @AbuHafsaYimam

• قال ابنُ الجوزي - رَحِمَهُ الله تَعَالَى- : • - كم لله فِي مجَالِس الذّكر من عين مُحرمَة على النَّارِ! كم قد وضع فِيهَا عَن الظُّهُور من ثقل الأوزار! وتنفجر فِيهَا ينابيع الرَّحْمَة! ويتوفر فِيهَا على الْحَاضِرين من النِّعْمَة! وَيُعْطى كل سَائل مَا سَأَلَهُ! 【 التذكـرة  ( ٢٧ ) 】