💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Open in Telegram
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Show more8 859
Subscribers
+1124 hours
+287 days
-1730 days
Posts Archive
ዉድ እህቶቸ! የኔ አበቦች ምንም ቃላት የለኝም አላህ ያስደስታችሁ ያክብራችሁ ጀዛኩሙሏሁ ኸይራ! አላህ ይጠብቃችሁ ። ያገባችሁት ዉለዱልኝ ክበዱልኝ ያላገባችሁ#አላህየ መልካም የሆነዉን ትዳር ይወፍቃችሁ። የምድራችሁ የምኩላችሁ ያደርገኝ።🌸🌹🌸🌹🌸🌹
አልሀምዱሊላሂ ይመስገን ጌታችን
ዛሬ ለዚህ በቃሽ መካሪ እህታችን
እንኳን ደስ አለሽ ይባረክ ትዳርሽ
በሰኪና ኑሪ በረከት ያቋድስሽ
የነብዩ መንገድ ሱና ነው ጋብቻ
ቢጤውን ላገኘ ሁኖት አቻ ላቻ
የነዓኢሻ መንገድ ደግሞም የነዘይነብ
ሷሊህ ልጅ ይስጣችሁ ለድኑ የሚከንብ
እመሩ ድመቁ ጎጇችሁ ይፋፋ
ሸይጧን ይነጫነጭ ከልቡ ይከፋ
በሰኪና ኑሩ ቤቱ ይሙላ ደስታ
ሰላም ይስፈንበት ይራቅ ከሁካታ
ባልሽን ያድርገው ሷሊህ መልከ ቀና
ከፍ በይ በስኬት እድልሽ ይቃና
ፍቅር እስከ ጀነት ይለምልም አብቦ
ሀላል ያብቃቃችሁ አሚን በሉኝ አቦ
ቤቱን የሚያደምቅ የግገኑ ድምቀት
ጀግና ልጅ ውለዱ ይራቃችሁ ጭንቀት
መብሩክ እንበላቸው ለዛሬ ሙሽሮች
ዱአ እናድርግላችሁ ሁኑ መርፌ ክሮች
በደስታ በሀሴት ኑሩ በሰኪና
ሷሊሆች ውለዱ አናብስት ጀግና !
بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في خير
«ጦይቢዬ የኔዉድ እህት የኔመልካም ደስታሽ ደስታዬ ነው ትዳርሽ ያማረ የሰመረ አላህ ያድርገዉ!! »
✍ከእህትሽ ኡሙ ሓቲም
🔖ውዷ እህቴ ጦይቤ በመጀመሪያ አላህን አመስግኚ ለዚህ ውብ ለሆነ ትዳር ለወፈቀሽ ፣ ሲቀጥል ትንሽ ማስታወስ የፈለኩት ትዳር ከምንም በላይ ትእግስት መቻቻልን እና መተሳሰብን ያስፈልጋል !ትዳር ትምህርት ቤት ነው ብዙ ነገርን ያስተምራል !
• ከምንም በላይ ደግሞ በትዳር ውስጥ ስነ ምግባር ለባለቤትሽ ለቤተሰቦቹም መልካም መሆን፣ የሚጠላውን መተው ተይ ይህን አልወድም ካለሽ ያን ነገር መተው የሚወደውንና የሚጠላውን ማወቅ አለብሽ !
• አብዘሀኛውን ጊዜ ትዳር ላይ ፀብ የሚፈጠረው ባሏ የሚወደውን የሚጠላውን የሚያስደስተውን ጠንቅቀን ባለማወቃችን ነው ! የሚጠላውን ደግሞ መራቅ ይህን ካደረግሽ ትዳርሽ ሰላም ይሆናል በአላህ ፍቃድ ኢንሸአላህ !
• የሰው ወሬ ደግሞ አደራ በተአምር እንዳሰሚ አንች ብቻ ባልሽን እመኝው ሰው እንኳን መቶ ወሬ ቢነግርሽ አይ የኔ ባል እንድህ አያደርግም ይህን በምትይ ሰአት እሱም ላንች ያለውን ክብርና ውዴታ ይጨምራል! ንፅህናሽንም በተለይ እሱ ሊመጣ ሲል በጅሽ የያዝሺውም ካለ መተው ለሱ ተዋቢለት !
• አላህ እኛም በምንናገረው የተግባር ሰው ያድርገን ትዳር ማለት ህዝብን እንደመምራት ማለት ነው ! ሶብርን ይጠይቃል ማድረግ የፈለግሺውን ነገር እሱን መጠየቅ ለሱ ክብር ይሰመዋል !
«አላህ ላገቡትም መልካም ትዳር ያድርገው ላላገቡትም መልካምና ያማረ የሆነውን ትዳር ይወፍቃችሁ !»
በድጋሜ መብሩክ
✍ከእህትሽ አመቱሏህ ሁሰይን
بَارَكَ الله لَكُما، وَبَارَكَ عَلَيْكُما، وَجَمَعَ بَيْنَكُمَا فِي خَيْرٍ
መብሩክ እህት አለም በጣም ደስ ብሎኛል
ለዚህ ቀን መብቃትሽን ለማየት አድሎኛል
ደርባባዋ እህቴ ጦይቤየ የኔውድ
ደስታሽን ያብዛልኝ በዱኒያም በአኼራ
አላህ ያስምርልሽ ትዳርሽም ይብራ !
እድለኛ እኮነው አችን አላህ ሰጠው
ከቶ ምን ብሎነው እድህ ዱአ ያረገው
የእናቱ ዱዓ ነው አንችንስ የሰጠው
እርግት ያልሽዋን ልጅ በሀላል አፈሰው
መሀመድ ታድሏል አላህ ነው ያደለው !
ገራገሯን ቆንጆ አላህም ሲያድለው
ከሁሉም መርጦ ለመሀመድ ነው
እንግድህ እንድህ ነው አላህ ሲያጣምርሽ
አጥሩን ሁሉ ገልጦ በሀላል ሊያዋድድሽ
ትዳራችሁ ይስመር ተደሰቱ ሁሌም
ሷሊህ ልጆች ሰጥቶ ያሳያችሁ አለም
የዱኒያ ፀጋዎች ልጆች ናቸውና
አላህ ያስደሳችሁ ኻሊቁ ረበና
ጦይቢየ የኔውድ ትግስትሽ አፈራ
መሀመድን ሰጠሽ መጣልሽ እያበራ
በሀላል አስዋበሽ አየሽ ይቺን ጮራ
የትዳሩን አለም አሳየሽ ሀያሉ
መታገስ ዋጋ አለው ይከፍላል ጀሊሉ !
አልሀምዱሊላሂ ተጣመር በቃ
የብቸኝነት አለም በዚህ ላይ አበቃ
ባይ ባይ ብቸኝት ብላ ተጉዛለች
የሱናዋ ቆንጆ መሰሏን ይዛለች
ረቢ ያድርገው ሰምሮ የተዋበ
በሱና በተውሂድ ደምቆ ያበበ
✍ከእህትሽ ዙበራ አሊ ኡሙ ሩመይሳ
Repost from ≺≺ኢብኑ ተይምያ የሱናው አንበሳ≻≻የእውቀት ማእድ
بَارَكَ الله لَكُما، وَبَارَكَ عَلَيْكُما، وَجَمَعَ بَيْنَكُمَا فِي خَيْرٍ
የሱና እሕታችን ጦይቢ ልታገባ
ለዚህ ላደረሳት ምስጋና ይገባ
የሱና እህታችን በጣሙን ታምራለች
በፆም በዱአዋ እዚህ ቀን ደርሳለች
ደስታን ይወፍቅሽ በትዳር ሒወትሽ
ተቅይ አቢድ ሷሊህ ሀፊዝ ልጅ ወፍቆሽ
ደስ የሚል ሀያትን አላህዬ ይስጥሽ
መልካም ሀላል እሪዝቅ ጀሊሉ ይወፍቅሽ
መብሩክ ብለናል እንኳን ደስ ያለሽ
አላህ በፍቃዱ ለዚህ አበቃሽ
ትዳር መስርተሻል ኢማንሺም ሞላ
ምን ያስደስትሻል ታድያ ከዚህ ሌላ
የደስታ የአለም ይሁን ጋብቻችሁ
ሁሌም ተዋደዱ አላህ ይዉደዳችሁ
መቻቻል ነዉና የትዳር ሚስጥሩ
በአንድነት ፀንታችሁ በፍቅራችሁ አብሩ!
«የኢብኑ ተይሚያ ጀመአ እህቶችሽ ደስታሺ ደስታችን ነዉ መልካም የትዳር ዘመን እንመኝልሻለን «እንወድሻለን»🌸🌺
•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
t.me/Ibnu_Teymya_Ye_Ewket_Maed
تألِيف👈 سَناء بِنت عَبد الواحد
👉በችግር ጊዜ መታገስ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿ما يُصِيبُ المُسْلِمَ، مِن نَصَبٍ ولا وصَبٍ، ولا هَمٍّ ولا حُزْنٍ ولا أذًى ولا غَمٍّ، حتّى الشَّوْكَةِ يُشاكُها، إلّا كَفَّرَ اللَّهُ بها مِن خَطاياهُ.﴾
“አንድ ሙስሊም አንድም ችግር፣ በሽታ፣ ስጋት፣ ሀዘን፣ አዋኪ ነገርም ሆነ ጭንቀት አይገጥመውም እሾህ እንኳ ቢወጋው አላህ ኃጢአቱን በዛ የተነሳ ያብስለታል (ይምረዋል)።”
📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 5641
t.me/ibnumohammedyimer
🔖 የአሹራ ፆምን በተመለከተ..!
አቡ ቀታዳ አል አንሷርይ አላህ መልካም ስራው ይውደድለትና እንዲህ አለ፦
የአላህ መልእክተኛ ﷺ ስለ አሹራ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህም አሉ፦ 【ያለፈውን አንድ አመት ወንጀል ያብሳል】ብለዋል።
📚 (ሙስሊም ዘግቦታል።)
~የሚፆመዉ 10ኛዉ ቀን ሲሆን ነገር ግን አህለል ኪታቦችን ለመሀለፍ 9ኛዉ(ዘጠነኛዉን) ቀን መፆም የፈለገ በላጩ ይህ ነዉ።
~የአሹራ ቀን ፆም የሚጀመረው ነገ እሮብ እና ሐሙስ ይሆናል ማለት ነዉ። ዘጠንኛዉን ቀን መፆም ያልቻለ 10ኛዉ እና 11ኛዉ ቀን መፆም ይችላል።
مَنْ دَلَّ عَلَى خَيْرٍ فَلَهُ مِثْلُ أَجْرِ فَاعِلِهِ }.
(ሌሎችን) ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የተገበረውን ሰው አምሳያ ምንዳ ይኖረዋል።
