cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Alpha Keranyo Sec. & Prep. School Community

+251113498906

Show more
Advertising posts
1 154
Subscribers
+124 hours
+197 days
+6430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አልፋ ቀራንዮ አፀደ ህፃናት፣ የመጀመሪያ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት      የተማሪዎች ወላጆች እና ተማሪዎች በሙሉ የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የነባር እና አዲስ ተማሪዎችን ምዝገባ ከሐምሌ 01/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደ ጀመርን ይታወቃል። በመሆኑም ምዝገባው የሚቆየው እስከ ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም  ብቻ ስለሆነ ልጆቻችሁን ያላስመዘገባችሁ ወላጆች የምዝገባው ጊዜ ሳያልፍባችሁ እንድታስመዘግቡ ስንል በአክብሮት እንገልፃለን።                                                          ት/ቤቱ
Show all...
አልፋ ቀራንዮ አፀደ ህፃናት፣ የመጀመሪያ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት                 ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት   የተማሪዎች ወላጆች እና ተማሪዎች በሙሉ                         ማስታወቂያ እንደሚታወቀው የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተጠናቆ ተማሪዎችም የማጠቃለያ ፈተና ወስደው ውጤታቸውንም ተመልክተው ለሚቀጥለው የትምህርት ዘመን እየተዘጋጁ እንደሆነ ይታወቃል። በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችም  የበለጠ ጠንክረው እንዲሠሩ በሌሎች ተማሪዎች ላይም  መነሳሳትን እንዲፈጥር ትምህርት ቤታችንም ለተማሪዎቹ ለሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ከነፃ የትምህርት ዕድል ከመስጠት  አንስቶ እንደ የደረጃቸው የተለያዩ  የማበረታቻ ሽልማቶችን ያበረከተ ሲሆን ከፍተኛ ውጤት ያመጡ የተወሰኑትን ተማሪዎችንም በምስል (በፎቶ) እንደሚከተለው አያይዘን አቅርበናል።                                                                ት/ቤቱ
Show all...
አልፋ ቀራንዮ አፀደ ህፃናት፣ የመጀመሪያ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት                 ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት   የተማሪዎች ወላጆች እና ተማሪዎች በሙሉ                         ማስታወቂያ እንደሚታወቀው የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተጠናቆ ተማሪዎችም የማጠቃለያ ፈተና ወስደው ውጤታቸውንም ተመልክተው ለሚቀጥለው የትምህርት ዘመን እየተዘጋጁ እንደሆነ ይታወቃል። በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችም  የበለጠ ጠንክረው እንዲሠሩ በሌሎች ተማሪዎች ላይም  መነሳሳትን እንዲፈጥር ትምህርት ቤታችንም ለተማሪዎቹ ለሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ከነፃ የትምህርት ዕድል ከመስጠት  አንስቶ እንደ የደረጃቸው የተለያዩ  የማበረታቻ ሽልማቶችን ያበረከተ ሲሆን ከፍተኛ ውጤት ያመጡ የተወሰኑትን ተማሪዎችንም በምስል (በፎቶ) እንደሚከተለው አያይዘን አቅርበናል።                                                                ት/ቤቱ
Show all...
አልፋ ቀራንዮ አፀደ ህፃናት፣ የመጀመሪያ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት                 ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) የተማሪዎች ወላጆች  በሙሉ                                ማስታወቂያ የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ሀገር አቀፍ ፈተና ዛሬ የሚጠናቀቅ ሲሆን ተማሪዎችም በዛሬው ዕለት ወደ ቤት የሚመለሱ ይሆናል። በመሆኑም ወላጆች ከምሽቱ 12:30 ጀምሮ በትምህርት ቤታችን ግቢ በመገኘት ልጆቻችንን መውሰድ እንደምትችሉ በአክብሮት እንገልፃለን።                                                                ት/ቤቱ
Show all...
አልፋ ቀራንዮ አፀደ ህፃናት፣ የመጀመሪያ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት                 ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) የተማሪዎች ወላጆች በሙሉ                                ማስታወቂያ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ሀገር አቀፍ ፈተና ከማክሰኞ ሐምሌ 09/2016 ዓ.ም እስከ ሐሙስ 11/2016  ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል። በመሆኑም የትምህርት ቤታችን የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት   ተፈታኞች እሁድ  ማለትም  07/11/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ሠዓት ወደ  ተመደባቹበት  የፈተና ጣቢያ    ማለትም  ወደ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ  ዋና ግቢ ጉዞ የሚደረግ በመሆኑ ተማሪዎች  በተጠቀሰው ሠዓት እንድትገኙ እናሳስባለን። ማሳሰቢያየትምህርት ቤቱን የደንብ ልብስ (Uniform) መልበስ   ይኖርባችኋል። ፨ አድሚሽን ካርድ እና የትምህርት ቤቱን መታወቂያ መያዝ ይኖርባችኋል። ፨ በዕለቱ በማርፈድ ወይም በመቅረት ለሚፈጠረው ክፍተት  ትምህርት ቤቱ ኃላፊነት አይወስድም።                                                                ት/ቤቱ
Show all...
አልፋ ቀራንዮ አፀደ ህፃናት፣ የመጀመሪያ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት                 ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) የተማሪዎች ወላጆች እና ተማሪዎች በሙሉ ማስታወቂያ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ሀገር አቀፍ ፈተና ከማክሰኞ ሐምሌ 09/2016 ዓ.ም እስከ ሐሙስ 11/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል። በመሆኑም የትምህርት ቤታችን የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት   ተፈታኞች እሁድ  ማለትም 07/11/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ሠዓት ወደ ተመደባቹበት  የፈተና ጣቢያ    ማለትም  ወደ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ  ዋና ግቢ ጉዞ የሚደረግ በመሆኑ ተማሪዎች በተጠቀሰው ሠዓት እንድትገኙ እናሳስባለን። ማሳሰቢያ በዕለቱ በማርፈድ ወይም በመቅረት ለሚፈጠረው ክፍተት ትምህርት ቤቱ ኃላፊነት አይወስድም። ት/ቤቱ
Show all...
አልፋ ቀራንዮ አፀደ ህፃናት፣ የመጀመሪያ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት  ለመጀመሪያ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪ ወላጆች እና ተማሪዎች በሙሉ የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ትምህርት ተጠናቆ የማጠቃለያ ፈተና መሠጠቱ ይታወቃል።  በመሆኑም የተማሪዎች የውጤት መግለጫ ሪፖርት ካርድ የሚሠጠው ነገ እሁድ ማለትም በቀን 30/10/2016 ዓ.ም ስለሆነ የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች እንዲሁም ህጋዊ አሳዳጊዎች በዕለቱ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በትምህርት ቤቱ አዳራሽ በመገኘት የልጆቻችሁን የትምህርት ውጤት መግለጫ ሪፖርት ካርድ እንድትወስዱ በአክብሮት እንጋብዛለን።                                                                ት/ቤቱ
Show all...
አልፋ ቀራንዮ አፀደ ህፃናት፣ የመጀመሪያ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት                     ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የተማሪዎች ወላጆች እና ተማሪዎች በሙሉ ነገ አርብ እና ከነገ ወዲያ ቅዳሜ ማለትም በቀን 28/10/2016 ዓ.ም እና በ29/10/2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የሞዴል ፈተና በኦን ላይን የሚሠጥ በመሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በዕለቱ በመገኘት ፈተናውን እንድትወስዱ እንገልፃለን። የሞዴል ፈተናው ፕሮግራም እንደሚከተለው ይሆናል፡፡ ፨ ማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) ጠዋት      2፡30  - 5፡30 ፨ አርብ         እንግሊዘኛ          ፨ ቅዳሜ       ሒሳብ ፨ የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science)  ከሰዓት     7፡00 እስከ 10፡00  ይሆናል። ፨ አርብ         እንግሊዘኛ ፨ ቅዳሜ       ሒሳብ ማሳሰቢያ በዕለቱ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስትመጡ: - ፨ የትምህርት ቤቱን ሙሉ የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) ብቻ አድርጋችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን። ፨ የትምህርት ቤቱን መታወቂያ እንዲሁም አድሚሽን ካርድ መያዝ እንደሚኖርባችሁ እናሳስባለን። ፨ የትምህርት ቤቱን የደንብ ልብስ  (ዩኒፎርም) ሳይለብስ እንዲሁም የትምህርት ቤቱን መታወቂያ እና አድሚሽን ካርድ ያልያዘ ተማሪ ወደ ትምህርት ቤቱ ግቢ እንደማይገባ እንገልፃለን።                                                                ት/ቤቱ
Show all...
አልፋ ቀራንዮ አፀደ ህፃናት፣ የመጀመሪያ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት                     ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የተማሪዎች ወላጆች እና ተማሪዎች በሙሉ ነገ ማለትም በቀን 25/10/2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የሞዴል ፈተና በኦን ላይን የሚሠጥ በመሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በዕለቱ በመገኘት ፈተናውን እንድትወስዱ እንገልፃለን። የሞዴል ፈተናው ፕሮግራም እንደሚከተለው ይሆናል፡፡ ፨ ማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) ጠዋት 2፡30  - 5፡30 ፨ የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science)  ከሰዓት 7፡00 እስከ 10፡00 ይሆናል። ማሳሰቢያ በዕለቱ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስትመጡ: - ፨ የትምህርት ቤቱን ሙሉ የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) ብቻ አድርጋችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን። ፨ የትምህርት ቤቱን መታወቂያም እንዲሁም አድሚሽን ካርድ መያዝ እንደሚኖርባችሁ እናሳስባለን። ፨ የትምህርት ቤቱን የደንብ ልብስ  (ዩኒፎርም) ሳይለብስ እንዲሁም የትምህርት ቤቱን መታወቂያ እና አድሚሽን ካርድ ያልያዘ ተማሪ ወደ ትምህርት ቤቱ ግቢ እንደማይገባ እንገልፃለን።                                                                ት/ቤቱ
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.