Quran
Open in Telegram
አላህን በማስደሰት ላይ ራስህን ጥመደው! ካልሆነ ሸይጣን አላህን እንድታስከፋ ያጠምድሀል! ✒العلم قبل القول والعمل >ድንቅ ድንቅ አባባሎችን ማራኪ ንግግሮችን ቆንጆ ቆንጆ ምክሮችን...በየቀኑ ያገኛሉ >ከወደዳችሁት ኑ አብረን እንስራ!!!! If You have any comment @abunes @abu_useymin @hik_j @quranabandba
Show more930
Subscribers
No data24 hours
-57 days
-1530 days
Posts Archive
930
Repost from Uswa kids terbiya center
🔊🔊🔊ኑር ፌስቲቫል
የነገን ትውልድ ዛሬ እናንፅ!
Nurturing the future generation now!
ለበለጠ መረጃ
📞 0906182071
📞 0906178071
@Uswa_kids_terbiya
930
የታሉ ነቢ!!!🥺
አስማ (ረ.ዐ) በኡሁድ ዘመቻ ወቅት ወንድሟ፣ ባሏ፣ አባቷ እና ልጇ በሸሂድነት እንደወደቁ ሲነገራት «ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ደህና ናቸውን?» ስትል ጠየቀች። «አልሐምዱ ሊላህ እርሳቸው ደህና ናቸው» ሲሏት፡
«እርሶ ደህና ከሆኑ ከእርሶ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም መከራና ጭንቅ ለእኔ ቀላል ነው!» («ኩሉ ሙሲበቲን ባዕደከ ጃለል»)
ብላ ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) በሰላም ስታያቸው ልቧ የታገሰና ለአላህ መልእክተኛ የነበራትን ጥልቅ ፍቅር ያሳየች ታላቅ ሴት ናት
አላህዬ እንደው በህልማችን ያሳየን ያረብ
ነገም ከሀውዳቸው አጠጥቶ ጎረቤታቸው ያርገን🤲
#صلوا_على_النبي ﷺ
اللهم صل وسلم وبارك على نبينا محمد ﷺ
@quranabandba
930
Repost from "እንዴት ልዋብ?"
የፀደዩ ንፋስ ሲያውድ፣ የደስታ አፀዶች ሲፈኩ፣ የረቢዑ ፀሃይ ሲፈነጥቅ .... ነፍሶች በደስታ ይዋባሉ
ለተከታታይ አመታት በሙስሊም ውመን ኔትዎርክ አዘጋጅነት ውብ መድረኮችን ሲያካፍላችሁ የቆየው ተወዳጁ የ "እንዴት ልዋብ?" መሰናዶ 13ኛ መድረኩን የሴትን ልጅ ሰብዓዊ ማንነት ያከበረ ለደህንነቷ ከለላ፣ ለህይወቷ ዋስትና የሆነውን የነብያችን ሰዐወ አስተምህሮ እንዲሁም ውብ ስብዕና ዳግም በውብ መሰናዶዎች ሊያስታውሰን ቀጠሮ ይዟል። ኑ ውቡን የኢስላም የነጻነት መንገድ አብረን እንጓዝ
የነጻነት መንገድ
ነሀሴ 24 በአምባሣደር ቲያትር
መግቢያ በነፃ
በዕለቱ ውድ ኡስታዛዎቻችን የመድረካችን ድምቀቶች ሲሆኑ ከተለያዩ አዝናኝ እና አስተማሪ መሰናዶዎች ጋር እንጠብቃችኃለን።
ለበለጠ መረጃ በ 0930402754 ይደውሉ
"እንዴት ልዋብ?"13
930
✨አል-ባሪእ (الْبَارِئُ)
ፍጹም አስገኚውና ፈጣሪው
አል-ባሪእ ማለት ምንም ነገር በሌለበት...
ያለምንም ምሳሌና ቅጂ ፍጥረታትን ከባዶ ወደ ህልውና ያመጣ...
እንዲሁም እያንዳንዱን ፍጡር ያለ ስህተትና ያለ ግድፈት በተሟላ ሁኔታ የፈጠረ ማለት ነው...
ስለዚህ ህይወትህን በዓላማ ምራ...
በጥበቡ ከምንም ያስገኘህ አላህዬ በከንቱ እንድትኖር አልተወህም...
የፈጠረህን አላህ(ሱ,ወ) ማወቅና ማምለክ...
እንዲሁም ለሰዎች ጠቃሚ መሆን...
የህይወትህ ዋና ዓላማ ይሁን...
هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ۚ يُسَبِّحُ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
እርሱ አላህ ፈጣሪው (ከኢምንት) አስገኚው፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አልሉት፡፡ በሰማያትና በምድርም ያለው ሁሉ ለእርሱ ያሞግሳል፡፡ እርሱም አሸናፊ ጥበበኛ ነው።
【ሱረቱ ሀሽር 24】
#የአላህ ስምች
@quranabandba
930
هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ۚ يُسَبِّحُ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
እርሱ አላህ ፈጣሪው (ከኢምንት) አስገኚው፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አልሉት፡፡ በሰማያትና በምድርም ያለው ሁሉ ለእርሱ ያሞግሳል፡፡ እርሱም አሸናፊ ጥበበኛ ነው።
【ሱረቱ ሀሽር 24】
#የአላህ ስሞች
@quranabandba
930
+1
✨አል-ባሪዕ" (الْبَارِئ)
እንከን-አልባ አድርጎ ፈጣሪ...
🩸 በደማችን ውስጥ ያለ አስገራሚ "ሚዛን" (The Perfect Brake System)...
ስለት ሲቆርጠን ወይም በትንሹ ስንቧጨር ደም መፍሰስ ይጀምራል...
ነገር ግን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ደሙ መፍሰሱን አቁሞ ይረጋጋል አደል...
ይህ ቀላል የሚመስለን ሂደት በሰውነታችን ውስጥ የሚከናወን እጅግ ውስብስብና አስደናቂ ተአምር ነው...
ሁለቱን ሂደቶች በአጭሩ እንይማ...
ጡብና ሲሚንቶ (ግንባታው)፦ ስንቆረጥ በደማችን ውስጥ ያሉ ጥቃቅን ህዋሳት (Platelets) ልክ እንደ ጡብ በተቆረጠው ቦታ ላይ ይከማቻሉ...
ሌሎች ፕሮቲኖች ደግሞ እንደ ሲሚንቶ በመሆን ቀዳዳውን ይደፍኑታል...
ሁለተኛው ሂደት ደሞ...
አስደናቂው "ፍሬን" (The Miracle)፦ እጅግ የሚገርመው ነገር ቀዳዳው ተደፍኖ ሲያበቃ ሰውነታችን ወዲያውኑ "የማቆሚያ ፍሬን" ይረጫል...
ይህ ፍሬን የደሙ መርጋት እዚያው የተቆረጠው ቦታ ላይ ብቻ እንዲቆም ያደርገዋል...
እስቲ እናስተውልማ
ይህ "የማቆሚያ ፍሬን" ባይኖር ኖሮ፣ ደሙ መርጋቱን በመቀጠል መላው የሰውነታችን የደም ቧንቧ ይዘጋና ህይወታችን ወዲያውኑ ያልፍ ነበር...
በሌላ በኩል ደግሞ የመርጋት አቅሙ በጥቂቱ እንኳ ቢቀንስ ኖሮ፣ በትንሽ ስለት ደማችን አልቆ እንሞት ነበር...
ይህንን ፍጹም የሆነ ሚዛንና የደህንነት ስርዓት በደማችን ውስጥ የዘረጋው ማነው?
እርሱ እያንዳንዱን ነገር ያለ ምንም እንከንና ግድፈት፣ ተስማሚ አድርጎ የፈጠረው "አል-ባሪዕ" (الْبَارِئ) ነው!!!☺️
930
✨አል-ኻሊቅ (الخالق) —
ነገሮችን ሁሉ ካልነበሩበት ወደ መኖር ያስገኘ...
ፍፁም እና ውብ አድርጎ የፈጠረ ጌታ ..
አንተን ከምንም አስገኝቶ ውብ ቅርጽ ሰጥቶ...
በዚህች ምድር ላይ እንድትኖር የፈጠረህ ጌታ...
በህይወትህ ውስጥ የሚገጥሙህን ...
ከባድና የተዘበራረቁ ሁኔታዎችን ሁሉ መልሶ ውብ...
የማድረግና የማስተካከል ሙሉ ችሎታ የለውምን!?...
በሰማያት ላይ ሰፊው አጽናፈ አለም ከዋክብትና...
ጋላክሲዎች ያለ አንዳች ምሰሶ ተደግፈው በስርዓት እንዲሽከረከሩ ያደረገው እርሱ ነው...
በሰው ልጅ ላይ ከጥቃቅን የዲኤንኤ (DNA) ኮዶች ጀምሮ እያንዳንዱ የሰውነት ክፍልና ስነ-ህይወታዊ ስርዓት (Biological system) በሚያስደንቅ ሁኔታ አመጣጥኖ የፈጠረ ነው ሱብሀነል ኻሊቅ...
ብቻ ብዙ ብዙ ነውና በ«አል-ኻሊቅ» ላይ ያለህን እምነትን አድስ...
መልካም ቀን ...ፊአማኒላህ☺️
هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ۚ يُسَبِّحُ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
እርሱ አላህ ፈጣሪው (ከኢምንት) አስገኚው፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አልሉት፡፡ በሰማያትና በምድርም ያለው ሁሉ ለእርሱ ያሞግሳል፡፡ እርሱም አሸናፊ ጥበበኛ ነው።
【ሱረቱ ሀሽር 24】
#የአላህ ስሞች
@quranabandba
930
Repost from Uswa kids terbiya center
አሰላሙ አለይኩም የኡስዋ ቤተሰቦች
uswa kids terbiya center
የ 2018 የክረምት መርሀ ግብር ምዝገባ መጀመራችንን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው!!!
የነገን ትውልድ አሁን እንገንባ!
Nurturing the future generation now!
ለመመዝገብ
📞 0906182071
📞 0906178071
@Uswa_kids_terbiya
930
ሙሀረም ዘጠኝ ነገ ማለትም እሮብ ፣ አሹራ ሀሙስ ሲሆን ጁምዐ ደግሞ አስራ አንደኛው ቀን ሆኖ ይውላል ሌሎችንም በማስታወስ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን።
930
#አሹራ የድል መዘክር ትምህርት 2
ሰበብ ማድረስ ካንተ፣ ውጤቱ ከአላህ
ባህሩን ለመሰንጠቅ የሙሳ በትር ...
ምንም ዓይነት ቁሳዊ ኃይል አልነበራትም...
ነገር ግን አላህ ያዘዛቸውን ሰበብ...
(በትር የመምታት ተግባር) እንዲያደርሱ ፈለገ...
አንተም በተመሳሳይ ሁኔታ ...
መማርህን፣ መሥራትህንና መጣርህን ...
ሰበብ ማድረስህን አታቋርጥ...
ውጤቱን በእምነት ከአላህ☺️...
@quranabandba
930
#አሹራ የድል መዘክር ትምህርት 1
ተስፋ መቁረጥ ለሙስሊም ወጣት አይገባውም!!!...
ሁኔታዎች ምንም ያህል ቢጨልሙና በሰውኛ ስሌት "መውጫ የለውም" ቢባል እንኳ...
አላህዬ ካልታሰበበት ቦታ መንገድ ይከፍታል...
በሕይወትህ ውስጥ "የተዘጋ በር" ሲገጥምህ...
ባህሩን የሰነጠቀው ጌታ ዛሬም እንዳለ አስታውስ...
እመነኝ ሁሉም ነገር ይስተካከላል...
አንተ ብቻ በእምነት ትንሽ ሰበብ አድርስ...
መልካም ቀን ፊ አማኒላህ☺️
@quranabandba
930
አል-ሙተከቢር (المتكبر)
በታላቅነት...በክብር.. በኃይል እና በፍጹምነት ከሁሉም በላይ የሆነ ጌታ ማለት ነው...
ይህ ባህሪ ለአላህ ብቻ የሚገባ ነው...
ይሄን ጌታ በማወቅ ውስጥ ነው...
የልብ ትዕቢት ስክን ሚለው...
የአላህን ታላቅነት ባወቅን መጠን ልባችን በትህትና ይሞላል...
ትህትና ደሞ ደረጃን ከፍ ታደርጋለች...
#የአላህ ስሞች
@quranabandba
930
በተሰበሩ ክንፎች ወደ አላህ የሄዱት ሁሉ...
እየበረሩ ተመልሰዋል ...
ጉዞ ወደ አላህ እናድርግ...
በአዲስ አመት ወደ አዲስ ህይወት☺️...
ሂጅራ 1448...
@quranabandba
930
4ተኛ የህይወት ትምህርት☺️...
በሶስት ወር ቆይታዬ ብዙ ነገሮችን አይቻለው ...
ሀዘን ..ደስታ..ምስጋና ..ትዝብት ...
ብቻ ብዙ ብዙ ከሁሉም ግን የአጀበኝ...
አንድ ነገር መሰጠቱ ብቻ በቂ እንዳልሆነ ምናይበት ክስተቶች ነበሩ ...
የሁላችንም ተመሳሳይ ምኞት የሆነው ልጅ ...
ለሚስኪን እናቱ የእንቅልፍ እጦት ሲሆን ...
አባት ጀግንነቱን ሀይል ያሳጣው የልጁ ለቅሶ ...
ከዛ ደሞ በአንድ ልጇ ምክኒያት ሌሎቹን እስክትረሳ ምትጨነቀው እናት...
ሁሉም በልጅ ህመም ምክንያት መሆኑ ትልቅ ትምህርት ይሰጠናል...
ልባችን ሚንገበገብለትን ነገር ስንጠይቅ ...
ከነ ሙሉ ኒዕማው እንዲሆን እና ከመፈተኛነት በሱ ለመጠበቅ ዱዐ ያስፈልጋል...
ልጅ ስንል ከነ ሙሉ አፊያው እና ሷሊህነት ጋር...
ትዳር ስንል ከነ ሙሉ ፍቅር እና እዝነት ጋር...
ቤተሰብ ስንል ከነ መተሳሰቡ እና ደስታው ጋር...
እውቀት ስንል ከነ ማስተዋሉ እና ጥበቡ ጋር...
ሀብት ስንል መሰደቁ እና ሀጅ ማድረጉን ጨምሮ...
እድሜ ስንጠይቅ ከመልካም ስራው ጨምሮ ...
ብቻ ምኞታችን ሁሉን ያማከለ ይሁን...
ሰጪው እኮ አላህዬ ነው ...
ስለዚህ ሀያ ወደ ሀምድ እና ዱዐው...
አላህዬ ኒዕማውን ያሟላላቹ ...🤲
@quranabandba
930
❤️🩹 አል-ጀባር (ٱلْجَبَّارُ)
ሁሉን በኃይሉ የሚያሸንፍ... የተሰበረ ልብን የሚያስተካክል...የተጨነቀን የሚያጽናና ማለት ነው...
🔹 ልባችን ሲሰበር የሚጠግነው አላህ ነው...
🔹 ችግራችን ቢበዛ መፍትሄው ከአል-ጀባር ዘንድ ነው.
🔹 ሰዎች ሲተዉን ማይለቀን እሱ ነው...
ከአል ጀባር ጋር...
اللهم يا جبار اجبر كسر قلوبنا، وأصلح أحوالنا، واغفر ذنوبنا.
አላህዬ አንተ አል-ጀባር ነህ..የልባችንን ስብራት አስተካክልልን...ሁኔታችንን አሳምርልን..ኃጢአታችንንም ይቅር በለን... አሚን🤲
#የአላህ ስሞች
@quranabandba
930
إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡
【ሱረቱ አህዛብ 56】
@quranabandba
