en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Open in Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 932 subscribers, ranking 5 345 in the Religion & Spirituality category and 2 243 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 932 subscribers.

According to the latest data from 17 October, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 251 over the last 30 days and by 10 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 10.75%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 10.25% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 1 699 views. Within the first day, a publication typically gains 1 620 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 16.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 18 October, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

15 932
Subscribers
+1024 hours
+297 days
+25130 days
Posts Archive
ይህንን ማስፈንጠርያ ይጠቀሙ https://www.youtube.com/channel/UC9HCZKEuvymsChwLuR2lTsw ዛሬ ከ2:00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የሚኖረንን ቆይታ ከታች ያለውን
ይህንን ማስፈንጠርያ ይጠቀሙ https://www.youtube.com/channel/UC9HCZKEuvymsChwLuR2lTsw ዛሬ ከ2:00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የሚኖረንን ቆይታ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይከታተሉ። እንዳያመልጦት! #ስለ ታሰሩ አባላት፣ ለምን ታሰሩ? #ወቅታዊ ጉዳዮች

#ሐምሌ_7_ቀን_ቅድስት_ሥላሴ_ለአብርሃም_የተገለጹበት_ነው፡፡ ቅድስት ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣና ትርጕሙም ልዩ ማለት ሲኾን የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ልዩ ስለኾነ (የሥላሴን አንድነትና ሦስትነትን የሚመስል ስለሌለ፤ ቢመስልም ፍጹም ሦስትነት የሌለውና ምሳሌ ዘየኀጽጽ ስለሆነ)፤ ሥላሴን ቅድስት በሚል ቅጽል እንጠራለን፡፡ በዚህች #ሐምሌ_7_ቀን_ቅድስት_ሥላሴ_ለአብርሃም_የተገለጹበት_ነው፡፡ ይኸውም ስለ ፫ት ምክንያቶች ነው፤ #፩ኛ) ለመልካም ነገር /በአብርሃም አንግዳ መቀበል ፀር የኾነ ሰይጣንን ለማሳፈር/ (ሰይጣን በምቀኝነት አብርሃም እንግዳ እንዳይቀበል የውሸቱን ወደ አብርሃም ቤት በሚወስድ መንገድ ላይ ግንባሩን ገምሶ፥ ደሙን አፍስሶ ሰዎች አብርሃም እንዲህ መጥፎ ነውን እንዲሉና እንግዶች ወደ ቤቱ ሂደው እንዳይስተናገዱ አድርጓል፤ አብርሃምም ለ3 ቀናት እንግዳ እየጠበቀ ጾሙን ውሎ ነበር፡፡ ይህን የሰይጣን ክፋት የአብርሃምን እምነትና እንግዳ መቀበል የተመለከቱ ፥ ምግብን የማይመገቡ ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተው እሳት ቅቤን እንደሚበላ ተስተናግደዋልና ነው፡፡ መስተናገዳቸውንም መምህረ ጋሥጫ የኾነው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በመልክአ ሕማማት ድርሰቱ እንዲህ በግጥም አስቀምጦታል፤ ለንግሥክሙ ሰገደ አብርሃም በርእሱ፡፡ ቤተ ገብርክሙ እንዘ ይብል ገሐሡ፤ አጋዕዝትየ ዘትሤለሱ ግናይ ለክሙ፡፡ እዚህ ላይ ልናስተውለው የሚገባው አምላካችንም ኾነ ቅዱሳን መላእክት ለአብርሃምና ለሌሎችም ቅዱሳን በተለያየ አምሳል መገለጻቸውን ልብ ይሏል፡፡ ለአብነትም፤ ፠ #ለአብርሃም በአምሳለ አረጋዊ፤ ፠ #ለሕዝቅኤል በዘባነ ኪሩብ፤ ፠ #ለዳንኤል በአረጋዊ፣ ፠ #ለዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ በተለያየ አምሳል፤ ፠ #ለደብረ መጕናው (ሞጊና) ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን #አቡነ አብሳዲ ደግሞ ራሱ መድኀኔዓለም ተገልጾላቸውና ተቀብለውት እንደ አብርሃም እግሩን ያጠቡት መኾኑን ልብ ይሏል፡፡ #፪ኛ) ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ፥ እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛልሃለሁ ያሉት ሥላሴ ቃሉ የማይታበይ መኾኑን ለማሳየት (ሰማይና ምድር ያልፋል ፥ ቃሌ ግን አያልፍም ብሎ በኋለኛው ዘመን ጌታችንም እንዳረጋገጠው)፤ ለአብርሃምና ለሣራ ልጅ ሊሰጧቸው፡፡ አባታችን አብርሃም 99 ዓመት ፥ እናታችን ሣራ 89 ዓመት መልቷቸውና የመውለጃ ጊዜያቸው ባለፈበት ሰዐት እንደሚወልዱ ለማብሰር፡፡ #፫ኛ) ምግብ ተመግበን ካበቃን በኋላ አምላካችንን ማመሰገን እንደሚገባን ለማስተማር፡፡ (የታረደው ወይፈንም በተዓምራት ተነሥቶ ስብሐት ብሎ አመሰግኗል፤ ይህንንም መምህረ ጋሥጫ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በመልክአ ሕማማት ድርሰቱ በግጥም እንዲህ አስቀምጦታል፤ ድኅረ በላዕክሙ ላሕመ እንበይነ ፍቅረ ሰብእ ፍጹም ፤ ዘበኀይልሙ ሐይወ ላሕም፤ ሥላሴ ክቡራነ ስም፡፡ ግናይ ለክሙ፡፡ SHARE ꔰ ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ꔰ Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem www.Finotehiwotsundayschool.com

.......#የደብራችን አስተዳደር የከሰሰው አባላችን የዋስ መብት ተከለከለ:: .......#ዛሬ የታሰሩት አባላት አዳራቸው እስር ቤት ነው:: #ለቤተክርስሰቲያን እና ለእውነት የቆመው ወንድማችን በቀለ አሰፋ ዛሬ ጠዋት ጉለሌ ፍርድ ቤት ቀርቦ በ1000 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቅ ቢወሰንለትም መርማሪው ይግባኝ ስለጠየቀ ጉዳዩ ወደ ልደታ ፍርድ ቤት እንዲዘዋወር ሆኗል፡፡ #ለእውነት መቆም እና ለቤተክርስቲያን መቆርቆር ዋስ የሚያስከለክል ወንጀል ነውን? ቃለ እግዚአብሔር ማስተማር ልደታ ፍርድ ቤት ድርስ ያስከስሳልን ? ጉዳዩ ውስጥ ውስጡን ጠንከር ያለ ይመስላል፡፡ #የቀሩት 10 ወንድም ና እህቶቻችን ዛሬ አዳራቸው ፤ ቅዱስ ጴጥሮስንና ጳውሎስን እየዘከሩ እስር ቤት ይሆናል ፡፡ ነገ ጠዋት ወደ ፍርድ ቤት ይሄዳሉ ፡፡ አሁንም ሐገረ ስብከቱ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ሆኗል :: ደም እስኪፈስ እየጠበቁ ይመስላል፡፡ #አስተዳደሩ ወንጌል #ለማስተጓጎል ፣ #ትውልድ ማፍራያ ተቋም ላማጥፋት ፣ #እውነት ለምን ተወራ ፣ #መማርያ ቦታ ለምን ተጠየቀ ብለው እያደሩጎት ያለው ተግባር እጅግ ስር የሰደደ ነው ይህም አገልጋዩች ቂሊንቶ እንዲወርዱ ነው ፡፡የደብራችን አስተዳዳሪ መልአከ ስዩም ወልደ ገብርኤል በዚህ የሚያቆሙ አይመስሉም እጃቸው ረጅም ነው፡፡በአውደ ምሕርት ላይም ለምዕመናን ውሸት መናገረቸው እናዳይዘነጋ፡፡ #ከዚህ በተረፈ ሽብሻቦ በካቴና እንደሚቀጥል ፣ #መልዕክታት ለቀጨኔ ሕዝብ ከእስር ቤት እንደሚላኩ ከዚህም በላይ በዝተን እውነትን መስበካችንን እንደምንቀጥል 11 አገልጋይ ያሳሰሩ ቢሆንም 111 አገልጋይ እንደበዙልን እና ፍትሕ ደግሞ ከእውነት ጋር ስለሆነች እኛ ጋር መምጣቷ የማይቀር መሆኑን እናምናለን፡: ለማንኛውም ቀጣይ ስም ዝርዝሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ ሁላችንም እንዘጋጅ ፡፡ የቀጨኔ ምዕመናን ቀጣይ የማን #ልጅ ፣ የማን #ወንድም እንደሚታሰር አይታወቅም የእርሶ ቢሆንስ? የማን #ጓደኛ ፣ የማን #ዘመድ እንደሚታሰር አይተወቅም የእርሶ ቢሆንስ ? ከእነዚህ ምክኒያቶች ሁሉ ለሚበልጠው ምክንያት ‹‹ስለ እውነት እና ስለ ደብራችሁ›› ስትሉ ዛሬውኑ ለምን በሉ! #ታውቋቸው ዘንድ ቀጣይ የሚሆኑትን እንዘረዝራልን ገብርኤል ፍርዱን ይሰጣል

.......#የደብራችን አስተዳደር የከሰሰው አባላችን የዋስ መብት ተከለከለ:: .......#ዛሬ የታሰሩት አባላት አዳራቸው እስር ቤት ነው:: #ለቤተክርስሰቲያን እና ለእውነት የቆመው ወንድማችን በቀለ አሰፋ ዛሬ ጠዋት ጉለሌ ፍርድ ቤት ቀርቦ በ1000 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቅ ቢወሰንለትም መርማሪው ይግባኝ ስለጠየቀ ጉዳዩ ወደ ልደታ ፍርድ ቤት እንዲዘዋወር ሆኗል፡፡ #ለእውነት መቆም እና ለቤተክርስቲያን ...... ፌስቡክ ገጻችን ላይ መሉውን በማንበብ ሃሳባቹህን በኮሜንት ስጡ + share + like https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool

.......#የደብራችን አስተዳደር የከሰሰው አባላችን የዋስ መብት ተከለከለ:: .......#ዛሬ የታሰሩት አባላት አዳራቸው እስር ቤት ነው:: #ለቤተክርስሰቲያን እና ለእውነት የቆመው ወንድማችን በቀለ አሰፋ ዛሬ ጠዋት ጉለሌ ፍርድ ቤት ቀርቦ በ1000 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቅ ቢወሰንለትም መርማሪው ይግባኝ ስለጠየቀ ጉዳዩ ወደ ልደታ ፍርድ ቤት እንዲዘዋወር ሆኗል፡፡ #ለእውነት መቆም እና ለቤተክርስቲያን ...... ፌስቡክ ገጻችን ላይ መሉውን በማንበብ ሃሳባቹህን በኮሜንት ስጡ + share + like https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool

#በድጋሚ አሳዛኝ ዜና #የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር ቅዳሜ ዕለት ለሕጻናት ቃለ እግዚአብሔር አስተምሮ ሲወጣ ያሳሰርው አባላችንን በቀለ አሰፋ ፤ ከሁለት ቀን የእስር ቤት ቆይታ በኃለ ወደ ፍርድ ቤት ሄዷል ፡፡ #አስተዳደሩ የከሰሳቸው እና በዕለተ ሰንበት ከቤተክርስቲያ ግቢ ውስጥ በሲቪል ፖሊሶች ሊታሰሩ ሰፈለጉ የነበሩት 11 አባላት ዛሬ ጠዋት ቃል ሰጥተው ታሰረዋል፡፡ #ስም ዝርዝራችው.. በቀለ አሰፋ ( በአሁኑ ሰዓት ፍርድ ቤት ያለ ) ዲ/ን ታምራት መሉነህ ዲ/ን ፍቅረ ሥላሴ አዳነ ዲ/ን ዮሐንስ መስፍን መ/ር ኪሩቤል ጀቤሣ ዲ/ን ተሻለ አለሙ ይሰሐቅ ወርቅዬ ሰላም ታመነ ፀጋዬ ቶላ እሙዬ ሽታዩ መስታወት ይጥና አሳልፈው ጎረምስ #እነዚህ የሰ.ት.ቤት አገልጋዮች ወንጌል ማስፋፋያ ቦታ ፣ ትውልድ ማፍርያ ቦታ ይሰጠን ብለው እውነት ይዘው ስለጠየቁ ለክስ እና ለእስር ተዳርገዋል፡፡ የደብሩ አስተዳደር አካል ከሃገረ ስብከቱ የመጣለትን ውሳኔ የማይቀበል እና የማይተገብር መሆኑ እና በአውደ ምሕረትም ላይ ለምዕመናኑ ክሴን አንስቻለሁ በሰላም እንፈታዋለን ብሎ ቢናገርም ፤ ንግግር እና ተግባር አንድ ሳይሆን ቀርቶ በየዕለቱ እውነትን የያዙ የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮች እየተከሰሱ እና እየታሰሩ ነው ያለው ፡፡ #የአዲስ አበባ ሐገረ ስብከትም እንደወትሮ አይቶ እንዳላይ ዝም ብሏል ፡፡ ለቅድስት ቤተክርስቲያናችን ፍትሕ የሚሰጥ አካል እሱ ሆኖ ሳለ ደም ካልፈሰሰ አንነቃም ያሉ ይመስላል፡፡ እውነትን የያዙ አጋልጋዮች እያተሳሩ ሳለ መፍትሔ ባለመስጠት አሁንም ዝም ብሎ ተቀምጧል፡፡ #የቀጨኔ ምዕመናን እስከመቼ ዝምታ ፣ እስከመቼ በአውደ ምሕርት ሌላ መልዕክት ተነግሮዋቹ ሌላ ተግባር የምታዩት ፣ እሰከ መቼ ነው ደብራቹህ ላይ ሰላም የምታጡት ፡፡ የቀጨኔ ምዕመናን ለቤተክርስቲያናቹ ሰላም ዛሬ ነገ ሳትሉ አሁኑኑ ልቶቆሙ ይገባል ፡፡ #በእስር ቤት ያሉት ወንድምና እና እህቶቻች ምን እንደተባሉ እና ፍርድ ቤት የቀረበው ወንድማችን ምን ላይ እንደደረሰ ከሰዓታት ቆይታ ቦኃላ እናሳውቃለን! አስተዳደሩም በቅርቡ ይፋ የምናደርጋቸውን ስሞች በተጨማሪ ለመክሰስ እንዳቀዱ ደርሰንበታል ፡፡ #ቅዱስ_ገብርኤል ፍርዱን ይሰጣል! መድኀኔዓለም ከፊታችን ይምራን ቅዱስ ገብርኤል ከኃላ ይከተለን ፡፡ ተጨማሪውን በፌስቡክ ገጻችን ተመልከቱ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool

ዛሬም ከቅዳሴ በኋላ የሰንበት ት/ት ቤታችን አባላት እየታደኑ ነው፡፡ ***************************************** የቅዳሴው ስርዓት በሰላም ግቡ ተብሎ ምዕመኑ ከተሸኘ በኋላ የሰንበት ት/ት ቤታችንም አባላት ወደ ቤት ሊሄዱ ሲሉ የሲቪል ልብስ የለበሱ የፖሊስ አካላት መኪና ይዘው በመምጣት አባሎቻችንን ሊወስዱ ሲሉ በጊዜው የነበረው ምእመን ልጆቻችን እንዳይያዙ በማለት አስጥሏቸዋል፡፡ በአሁን ሰዓት ሁሉም የሰ/ት/ቤቱ አባላት ከግቢ ሳይወጡ በአንድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከታሰርን ሁላችንም እንታሰር እያሉ ናቸው፡፡ የራሳችንን ችግር በቤታችን እንፈታዋለን ብንልም የሚሆን አልሆነም፡፡ ስለሆነም ሰ/ት/ቤቱ በዚህ ሁኔታ እየታደነ እና አገልግሎቱ እየተስተጎለ መቀጠል ስለሌለበት የአ.አ ሰንበት ት/ት ቤቶች እና የአጥቢያው ማኅበራት እንዲሁም የአጥቢያችን ምእመናን በዚሁ ጉዳይ የስብሰባ ጥሪ በቅርቡ የምንጠራችሁ ይሆናል፡፡ የአ.አ ሐገረ ስብከትም ላይ ያላችሁ አመራሮች ለህሊናችሁ ስትሉ እየሆነብን ያለውን ተመልክታችሁ እልባት ስጡ::

#አሳዛኝ ዜና #ዛሬም የደብራችን አስተዳደር የሰ/ት/ቤት አባሎቻችንን እያሳሰረ ይገኛል፡፡ በዛሬው እለት ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ሁኔታ አባሎቻችንን መታወቂያ በመጠየቅ እየታሰሩብን ይገኛሉ ፡፡ የደብራችን ማኅበረ ካህናት እኛን የሰ/ት/ቤት ልጆቻችሁ ለበርካታ ዓመታት በፍቅር እና በአንድነት ኮሽታ ሳይሰማብን ስናገለግል ኖረን ዛሬ በእስር ቤት ስንታሰር እያያችሁ እንዳላያችሁ ፣ እየሰማችሁ እንዳልሰማችሁ የምትሆኑት እስከ መቼ ድረስ ነው ፡፡ ልጆቻችን ከመታሰራቸው በላይ የእናንተ ዝምታ ልባችንን ያደማል፡፡ የአ.አ ሀገረ ስብከከትም ጉዳዩን በተደጋጋሚ ብናሳውቅም ‹‹ሰው ካልሞተ በቀር አንነቃም›› ያሉ ይመስላል ፡፡ ምን እስኪመጣ ነው እየተጠበቀ ያለው? #ደብረ ሰላም መቼ ይሆን ወደ ሰላሟ የምትመለሰው የሰ/ት/ቤታችን አባላትስ ለምን በየጊዜው ይታሰሩብናል፡፡ ትውልድ ማፍሪያ የሚሆን ተለዋጭ ቦታ ሳይሰጥ አዳራሻችን አይፍረስብን ስላሉ?? ሀገረ ስብከት ተመላልሰው ለ 5 ጊዜያት ውሳኔ ስላስወሰኑ?? ተማሪዎች አይበተኑ ስላሉ?? ዛሬ ላይ ህጻናትን ለማስተማር የሚወጡ መምህራን ቤተሰቦቻቸውን ‹‹ከታሰርኩ አታስቡ›› እያሉ ነው እየወጡ ያሉት መቼ ይሆን የደብረ ሰላም ስቃይዋ የሚያበቃው #የታሰሩት አባላት ፤ ለቀን ህጻናትና ወጣት ክፍል ተማሪዎች ትምህርት አስተምረው ሲውጡ ነው ፡፡ ይህ ወንጌልን ለማመስ እና ለማጥፋት ሆን ተብሎ የተሴረ ተግባር እንደሆነ እንረዳለን ፡፡ሰንበት ትምህርት ቤቱ ባገኛት ቦታ ዋና ዓላማው የሆነውን ቃለ እግዚአብሔርን ማስተማር እንዲያቆም ማድረግ ከሁሉ ነገር የከፋ ነው ፡፡ ሰ/ት.ቤቱም ትልቅ ትኩረት እንሚስጠው ልናሳውቅ እንወዳለን፡፡ #ሰንበት ት/ት ቤታችን ዛሬም እንደትላንቱ አገልግሎቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፣ ህጻናትም አይበተኑም ፣ አባቶቻችን ‹‹ ክርስቲያን እንደ ሚስማር ሲመታ ይጠነክራል›› እንዳሉ እኛም ጠንክረን አገልግሎታችንን ለአጥቢያችን ፣ ከአጥቢያችን አልፈን ለከተማችን ፣ ከከተማችን አልፈን ለሀገራችን ፣ ከሀገራችን አልፈን ለአለማችን እናዳርሳለን መጽሐፉም የሚለው ይህንኑ ነውና፡፡ በአገልግሎታችን ሁሉ #መድኀኔዓለም ይቅደምልን!!! የታሰሩትን ያስፈታልን ።