en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Open in Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 16 042 subscribers, ranking 5 277 in the Religion & Spirituality category and 2 237 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 16 042 subscribers.

According to the latest data from 25 October, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 503 over the last 30 days and by 9 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 24.94%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 9.77% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 4 001 views. Within the first day, a publication typically gains 1 567 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 29.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 26 October, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

16 042
Subscribers
+924 hours
+987 days
+50330 days
Posts Archive
#የቅዱስ_ያሬድ_ድርሰቶች፤#የዜማው_ይዘት_የዜማው_ጠባያት_ከሌሎች_ዓለማዊ_ዜማዎች_የሚለይበት_ጠባይና_የዜማው_ጥቅም #ሀ_የቅዱስ_ያሬድ_የዜማው_ይዘት ፠ቅዱስ ያሬድ ዜማውን ያዘጋጀው ከብሉያት፣ ከሐዲሳት፣ ከሊቃውንት መጻሕፍት እየመረጠ ለምስጋናና ለጸሎት እንዲኾኑ አድርጎ ነው፡፡ ፠ዜማው ምስጢሩ የማይጠገብ፥ቃሉ የሚያረካ፥ አነጋገሩ የተሳካ፥ ጣዕመ ቃሉና ኀይለ ቃሉ ደስ የሚያሰኝ፥ ልብን የሚነካ ነው፡፡ ፠በይዘቱም የሥነ ፍጥረት ውበትን በማድነቅና የሥነ ፍጥረት አስገኝ የኾነውን እግዚአብሔርን በማመስገን ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ፠በአጠቃላይ የቅዱስ ያሬድ ድርሰት ጌታ ለሰው ልጆች ሲል በዚህ ዓለም የፈጸመውን የማዳን ሥራ ሁሉ ገልጦ የሚያስረዳ ነው፤ የቅድስት ድንግል ማርያምን፣ የቅዱሳን መላእክትን፣ የነቢያትን፣ የሐዋርያትን፣ የጻድቃንና የሰማዕታትን ክብርና ቅድስና በማውሳት በስማቸው መማፀንና መጸለይ የሚያስገኘውን ጥቅም የሚያስረዳ ታላቅ ዜማዊ ሀብት ነው፡፡ ፠ከእርሱ በፊት የነበሩና በእርሱ ዘመን የተጻፉ የቅዱሳን ገድላትና ድርሳናትን እንዲሁም የበዓላትን ጥንታዊ አመሠራረት ውስጠ ምሥጢር በማስረዳት በዜማ ድርሰቱ አካቷል፡፡ ፠ምስጋናውንም ለአራቱ ክፍላተ ዘመን ለክረምት፣ ለመፀው (ለጥቢ)፣ ለሐጋይ (ለበጋ)፣ ለጸደይ (ለበልግ) እንዲኾን አዘጋጅቶታል፡፡ #ለ_የዜማው_ጠባያት ፨የቅዱስ ያሬድ ዜማ ሰማያዊ በመኾኑ ኅሊናን የመመሠጥ፣ ሥጋዊ ደስታንና ኀጢአትን ከማሰብ የመጠበቅ፣ ሰማያዊውን ድንቅ የምስጋና ምስጢር የማሳወቅ ኀይል አለው፡፡ ፨ከእግዚአብሔር የተገኘ ስጦታም በመኾኑ ብልየት (እርጅና)፣ ውላጤ (መለወጥ) የማይታይበት ዘወትር ሕያው የኾነ ብቸኛ ዜማ ነው፡፡ ፨የመንፈስ ቅዱስ ስጦታም በመኾኑ ዘወትር አዲስና የማያልቅ ጥልቅ ምንጭ ያለው ሕይወትን የሚያለመልም ነው፡፡ ፨ዜማውም ሰማያዊና መንፈሳዊ፣ ከእግዚአብሔር የተገኘ ለመኾኑ ማስረጃ የሚኾነን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ውጪ ያሉ ሰዎች ዜማውን ለተለያየ ዐላማ ይመኙታል፤ ነገር ግን ለመያዝም ኾነ ለመወሰን አይችሉም፡፡ ምክንያቱም በምድራዊ ጥበብና ፍልስፍና የሚያዝ የሚወሰን ሳይኾን ታላቅ መሥዋዕትነትን የሚጠይቅ፣ ሌት ተቀን ልቡናን ለሥላሴ ሰጥተው ከእግዚአብሔር የሚያገኙት በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የሚያጸኑት፣ የሚማሩትና የሚያዜሙት እንጂ በገንዘብ የማይገዛ ታላቅ ጸጋ መኾኑ ነው፡፡ #ሐ.#የቅዱስ_ያሬድ_ዜማ_ከሌሎች _ዓለማዊ_ዜማዎች_የሚለይበት_ጠባይ፤  ዜማው አሳብን የሚገዛ፣ ከሥጋ ይልቅ በመንፈስ መመላለስን የሚያስተምር በመኾኑ፤  በአቀራረቡም የተወሰነ የዜማ ስልትና ቀመር ያለው በመኾኑ፤  ዜማው በአዝማናት ተለይቶ በወቅት ተከፋፍሎ የሚዜም መኾኑ፤  ማንኛውም ሰው ከተወሰነ የዜማ ስልትና ቀመር ውጪ በራሱ ፍላጎት የድምፅ ቅላጼውን ለማሳመር ስለፈለገ የሚያሻሽለው ወይም የሚለውጠው አለመኾኑ፤  ዜማው በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌና ምሥጢር የተሞላ መኾኑና  የዜማው ምልክቶችና ዐይነቶች ጥልቅ ምሳሌና ምስጢር ያላቸው መኾናቸው ነው፡፡ #መ_የቅዱስ_ያሬድ_ዜማ_ጥቅም ሀ. የቤተ ክርስቲያንን አንድነት በመጠበቅ፤ በየትኛውም አካባቢ የምትኖር የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አንድ ዓይነት መዝሙር፣ አንድ ዓይነት ቅዳሴ፣ አንድ ዓይነት ማኅሌት፣ አንድ ዐይነት ሥርዐት በአንድ ዓይነት ጊዜ በአንድ ቀን ማቅረብና መፈጸም እንድትችል አስችሏታል፡፡ ለ. በነገረ መለኮት ትምህርት፤ ሊቁ የትርጓሜ መምህር ስለሆነ ከብዙ መጻሕፍት ስለሚጠቅስና የሃይማኖት ትምህርቱትንም በዜማ አቀነባብሮ መድረሱ በጣም ተወዳጅ ትምህርት እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ሐ. በሥርዓተ ጸሎት፤ ከዓመት እስከ ዓመት ለሚከናወኑ (የዘመናትና የሳምንታትን ጨምሮ) ማንኛውም ሥርዐተ ጸሎት ዋና መሪው የቅዱስ ያሬድ ድርሰት ነው፡፡ ማኅሌቱ፣ ቅዳሴው፣ ፍትሐቱ፣ ጥምቀተ ክርስትናው ሁሉ በዜማው መሪነት የሚከናወኑ አገልግሎቶች ናቸው፡፡ መ. ለቱሪዝም ሀብት (መስህብነት)፤ ክርስቲያናችን በየወሩና በየዓመቱ ከምታከብራቸው በዓላት ላይ ከሚቀርቡት ዝግጅቶች አብዛኛውን ክፍል የሚይዘው በቅዱስ ያሬድ ዜማ የሚቀርበው የዝማሬና የቅዳሴ አገልግሎት ነው፡፡ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem ፠ በዩቲዩብ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ Https://m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

#የቅዱስ_ያሬድ_አስደናቂ_ነገሮች ፠#ከጌዴዎን ዘንድ ትምህርቱን አቋርጦ ሄደ ስንል፤ በአንድ ሾላ ዛፍ ላይ በትል አማካይነት ትዕግስትንና ማስተዋልን ቀስሞ፤ ወደ አጎቱ ተመልሶ ተምሮና ትምህርትን አምላክ ገልጾለት መምህረ መምህራን ሁኖ እንገኘዋለን፤ /እግዚአብሔር አምላክ ለቅዱስ ያሬድ ያንን ኹሉ ጥበብ ቶሎ ያልገለጸለት በቀላሉ ቢያገኘው ኋላ እንዳይታበይ ብሎ ነው፤ የሐዊራ ብስድር እስክንድራን ታሪክ ልብ ይሏል) ፠#መምህር ነው ስንል፤ መናኝ ባሕታዊ ኾኖ እናገኘዋለን፤ /በደብረ ሐዊ ለ22ዓመታት መመኑን ልብ ይሏል/ ፠#መናኝ ነው ስንል የተለያዩ የሃገራችንን ክፍሎች ገዳማትና አድባራት ሲጎበኝ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ሲጓዝ እንገኘዋለን፤ /ጣና ቂርቆስ፤ ዙር አባ አቡነ አረጋዊ፣ …. ሌላውንም ልብ ይሏል) ፠#ወደ ገዳማትና አድባራት ይጓዛል ስንል፤ ወደ ደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ በደመና ተጭኖ ሂዶ ምሽቱን ወደ በዓቱ ሲመለስ እንገኘዋለን፡፡ ፠#በሃገራችን በዋና ከተማ አኵሱም ተወልዶ ያደገ ነው ስንል፤ ሰው ሊኖርበት በማይችለው፥ በረድ በሚፈላበት፥ የነፋስ እሩምታ በሚያይልበት፥ ቅዝቃዜው አጥንት በሚሰነጥቅበት፥ ውርጩ እጅጉን በሚቀዘቅዝበት፥ ደመና በሚፈስስበት በራስ ደጀን ተራራ አጠገብ በደብረ ሐዊ መንኖ እናገኘዋለን፡፡ ፠#ከሰዎች ጋር አብሮ ኑሯል ስንል፤ ከሰው የማይቀርቡና በዐለማችን ላይ ብርቅዬ ኾነው በሃገራችን የሚገኙ ከሃገራችን ኢትዮጵያም በሰሜን ተራሮች በአብዛኛው ከሚገኙት ዋልያ ጋር አብሮ ሲኖር፤ ዋልያዎችንም እንደ መጓጓዣና እንደ መጫኛ ሲያገለግሉት እንገኛለን፡፡ ፠#በሙራደ ቃል የመላእክት ዜማ ተገልጾለት ተማረ ስንል፤ የግእዝ ቋንቋ ምሁርና ጠበብት ሁኖ እናገኘዋለን፡፡ (ለተሰዓቱ ቅዱሳን መምህር መሆኑን ልብ ይሏል) ፠#የዜማ ጀማሪ አባት ነው ስንል ባለቅኔ ኾኖ እንገኘዋለን (ሕንፄሃ ወሡራሬሃ …. የሚለው ቅኔውን ልብ ይሏል)፤ ፠#ባለቅኔ ነው ስንል መተርጕም ኾኖ እንገኘዋለን፤ (ድጓው የብሉይና የሐዲስ ትርጓሜ መሆኑን ልብ ይሏል) ፠#መተርጕም ነው ስንል ባለታሪክ፥ የታሪክ ምሁር ኹኖ እናገኘዋለን፤ ፠#የታሪክ ምሁር ነው ስንል፤ የመርሐ አዝማን ሊቅ ኹኖ እናገኘዋለን፤ (ዓመቱን በሚገርም ሁኔታ ከወቅታቱ ጋራ አገናዝቦ መሠየሙን ልብ ይሏል) ፠#የመርሐ አዝማን ሊቅ ነው ስንል ቅዱስ ኾኖ እንገኘዋለን፤ የቅዱሳንም ጓደኛ ኹኖ እንገኘዋለን፡፡ /የአቡነ አረጋዊ፣ የአጼ ገብረ መስቀልን ታሪክ ልብ ይሏል፡፡/ ፠#ነቢይ ነው ሰንል ሐዋርያ ሁኖ እናገኘዋለን፡፡ (ስለ ዳግም ምጽአት፣ ስለ መንግሥተ ሰማያትና …. ሌሎችንም ልብ ይሏል) ፠#ሐዋርያ ነው ስንል ሰማዕት ኹኖ እናገኘዋለን፡፡ (እግሩን በጦር መወጋቱን ልብ ይሏል)፤ ሌላም ሌላም …. ፠#በአጠቃላይ ምድራዊ ነው ስንል ሰማያዊ፤ ሰማያዊ ነው ስንል ምድራዊ (ብእሲ ሰማያዊ ወመልአክ ምድራዊ) ሁኖ እናገኘዋለን፡፡ #ዜማውን በግዕዝ ዕዝል አራራይ የዜማ ስልት የደረሰ፤ #በዓለም ደረጃ የዜማ ምልክቶች ባልታወቁበት ጊዜ ዜማዎቹን በምልክት የቀመረ፤ #የዜማ ሥርዓትን በመንደፍ የዓመቱን ቀለም ያዘጋጀ፤ #ዜማውን በ4ት ዘመናት ከፋፍሎ፤ ዘመናቱን በንዑሳን ዘመናት ከፋፍሎ ለወራቱና ለሰሙኑ ለእለቱ የሚገባውን ቀምሮ የደረሰ፤ #እንኳን በእርሱ ዘመን ዛሬ እንኳን ብዙ ነገሮች ተሰባስበዋል በተባለበት ዘመን ሊሠራ አይደለም ሊታሠብ በማይችሉ መልኩ መጽሕፍትን እንደ ንብ እየቀሰመ፤ እንደ ወይን እየጨመቀ፤ እንደ አረቂ እያጣራ፤ እየተረጐመ ላሰበው ድርሠት ያዋለ፤ … ስለ ቅዱሱ ምኑን ተናግረን እንጨርሰዋለን፡፡ … ##.. ይኼማ ኢትዮጵያዊ ሊኾን አይችልም ብለው ብዙ የውጭ ሃገራት ወደ ራሳቸው ለመውሰድ የሚዳዳቸው፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

#ማሕሌቱን_ለማሕሌት_አባት_እናቅርብለት:: #ሥርዐተ_ማኅሌት_ዘግንቦት_፲፩ #፫) የቅዱስ_ያሬድ_ሌሎች_መጠሪያ_ስሞች ፠ ጥዑመ ልሳን፤ ፠ የሱራፌል አምሳያ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን እንዚራ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን ብርሃን፤ ፠ መዓርዒረ ዜማ፤ ፠ ካህን (ካህነ ስብሐት) ፠ ማኅሌታይ፤ ፠ መዘምር ዘበድርሳን፤ ፠ ሊቅ (ርእሰ ሊቃውንት) ፠ ዓርከ ሊቃውንት፤ ፠ ደራሲ፤ ፠ የመጽሐፍ መምህር፤ (ብሉያትንና ሐዲሳትን የሊቃውንትንም መጻሕፍት አስማምቶ የተረጐመ) ፠ ባለቅኔ (የቅኔ ጀማሪ)፤ ፠ የቤተክርስቲያን ጌጧና መሠረቷ ሕይወቷና እስትንፋሷ ፠ ልዑለ ስብከት፤ ፠ ሰማዕት፤ ፠ ባሕታዊ፤ ፠ መናኝ ፠ የዜማ አባት፤ ፠ የኢትዮጵያ ብርሃን፡፡ ፠ አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም) የኾነ:: ፠ እግሮቹ በመልካም መንገድ የሚጓዙና ወደ መልካም መንገድ የሚያስጕዙ ፠ ልቡናው የቅድስና ማኅደር የኾነ:: ፠ ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ የኾነ:: ፠ አእምሮው የመጠቀ፤ ፠ ድርሰቱ የተራቀቀ፤ ፠ እስከ አርያም ተነጥቆ ዕፁብ ድንቅ ምሥጢራትን የተመገበ ማን እንደርሱ:: …... /ማኅሌቱን በአ.አ ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤ/ክ የምትቆሙ በደብረ ይባቤ የሚለውንና በሰማየዊ ቀለም የተቀባውን እየመረጣችሁ መጠቀም ስትችሉ፤ በሌሎች አድባራት ግን ሰማያዊ ቀለም የሌለበትን (በቢጫና እንዲሁ ያለቀለም የተቀመጠውን) እየመረጣችሁ መጠቀም ትችላላችሁ፡፡/ ፨*፨(ሥርዐተ ማኅሌቱን ስናዘጋጅ የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያንን ይትበሃል በመንገር ለተባበራችሁን ለሊቀ ጠበብት አባ ኤርምያስና አርድዕቶቻቸው በተለይም ለዲ.ን አውራሪስ አምላከ ቅዱስ ያሬድ መድኀኔ ዓለም ይስጥልን፡፡) #የቅዱስ_ያሬድ_ልደትና_የስሙ_ትርጓሜ ꔰ ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ ሚያዚያ 5 ቀን በ505 ዓ.ም. ከአባቱ ይስሐቅ(አብድዩ) ከእናቱ ክርስቲና (ታውክልያ) በአኵሱም ከተማ ተወለደ፡፡ (አንዳንዶች ልደቱን 493 ዓ.ም. ነው ይላሉ፤ እንዲሁም አባቱ ኖኅ ነው ይሉና መሪጌታ ይስሐቅ የቀለም አባቱ /መምህሩ/ ነው ይላሉ፡፡) ꔰ የስሙም ትርጓሜም ያሬድ ማለት እንዚራ፣ በገና፣ መሰንቆ ማለት ነው ፡፡ እነዚህ መሣሪያዎች በስልት በስልት ሲመቱ ለሚሰማቸው ደስ እንዲያሰኙ የያሬድም ዜማ በንጉሠ ነገሥቱ ክርስቶስ አደባባይ በቤተ ክርስቲያን ሲሰማ መላእክትን፥ ሰውንና እንስሳትን ደስ ያሰኛልና፡፡ አንድም ያሬድ ርደት፣ ወሪድ፤ መውረድ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ሰማያዊውን ልዩ ጣዕመ ዜማ ወደ ኢትዮጵያ አውርዷልና፡፡ * አንድም ያሬድ ማለት ንብ ማለት ነው፤ ንብ የማይቀስመው አበባ እንደሌለ ሁሉ ቅዱስ ያሬድም ከመጻሕፍት የማይጠቅሰው የማይቀሰመው የለም፤ ** አንድም ያሬድ ማለት ረአዬ ምሥጢር፥ ነጻሬ ኅቡአት ማለት ነው፤ የመላእክት ምሥጢራት የነበሩትን ጸዋትወ ዜማ አምልቶ አስፍቶ ተናግሯልና፣ ነጻሬ ኅቡአት አለ፥ ኅቡእ (ስውር) የሆነ የጻድቃን፣ የሰማዕታት የነቢያት የሐዋርያትን ገድል አምልቶ አስፍቶም ይናገራልና፡፡ *** አፄ ካሌብ ቤተ እስራኤል፣ ገብረክርስቶስና ገብረ መስቀል የሚባሉ ልጆች ነበሩት፤ ቅዱስ ያሬድ የተነሳው ከእነዚህ ውስጥ በአፄ ገብረመስቀል ዘመን ነው፡፡ #የቅዱስ_ያሬድ_ድርሰቶች፤ #፩ኛ) #ምዕራፍ (ውዳሴ ማርያም በዜማን፣ መስተጋብዕ፣ አርባዕት፣ አርያም፣ ሠለስት፣ ክስተተ አርያምን) ያጠቃልላል፡፡ ፠ #የውዳሴ_ማርያም_ዜማ ቅዱስ ኤፍሬም ሦርያዊ የደረሰውን ለቅዱስ ያሬድ እየነገረው ልብን የሚመስጥ ዜማ ደርሶለታል፡፡ ፠ #መስተጋብዕ፤ ስብስብ ማለት ሲኾን፡፡ ከዳዊት መዝሙር (ከ180ው የመስተጋብእ ድርሰት 1ድ ድርሰት በስተቀር) ለጸሎትና ለዝማሬ ተስማሚ የኾነው እየተውጣጣ ለመዝሙር ተስማሚ የኾነው የተቀመረ ነው፡፡ መስተጋብዕ ሲጀምር ‹‹ወለቡ ጽራኅየ (ጩኸቴን ልብ አድርግ›› ብሎ ነው፡፡ በዐቢይ ጾም ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ጠዋት ይዘመራል፤ የቀድሞ መምህራን በፍልሠታም ይዘምሩት ነበር፤ ዜማው በዋነኛነት በግዕዝና በዕዝል ሲኾን በአራራይ ከሐሙስ ‹‹አንተሰ እግዚኦ ለዓለም›› የሚለውና ከቅማዴ ‹‹መንግሠትከሰ መንግሥት›› የሚለው ይገኙበታል፡፡ በየእለቱ እንዲደርስ (ከእሑድ በስተቀር) አድርጎ የደረሰው ነው፤ ፠ #አርባዕት፤ አራት አራተኛ ማለት ሲን በዳዊት መዝሙር በአራተኛው መሥመር ውስጥ እየገባ የሚዘመር ነው፤ ‹‹ቃልየ አጽምእ እግዚኦ ወለቡ ጽራኅየ፤ ወአጽምአኒ ቃለ ስእለትየ፤ ንጉሥየኒ ወአምላኪየኒ፡፡ ከፈጸመ በኋላ አርባዕት ይገባል፡፡ አርባዕት ሲጀመር ‹‹ቃልየ፤ ከመ ያፈቅርለ ጐሥዓ፤ ዐቢይ፤ ተሣሃለኒ›› ብሎ ነው (በዳዊት መዝሙር ጀምሮ ቀጥሎ በቅዱስ ያሬድ ድርሠት በኾነው በአርባዕት ያጠናቅቃል፡፡አብዛኛው በግጥም መልክ የተቀመረ ሲኾን አልፎ አልፎም በስድ ንባብ መልክ ይገኛል፡፡ ግእዝ ዕዝልና አራራይ ዜማ አለው፡፡ ፠ #አርያም፤ አርያም ልዑል፥ ከፍተኛ ማለት ሲኾን፤ ቅዱስ ያሬድ ከአርያም ሰምቶ ‹‹ቀዳሚ ዜማ፤ አንድም ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ›› ስላመጣው ነው፡፡ ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ብሎ የግጥም መል ባለው አእያም በተባለው ይጀምራል፡፡ በግጥም መልክና በስድ ንባብ ሲገኝ የግጠም አገጣጠሙ ከፍ ያለ የግጥም አገጣጠምን የተከተለነው፡፡ የሚባልበት ጊዜ በጾም ጊዜ በጾመ ድጓው እየገባ፣ በተለይ ደግሞ በክብረ በዓል ክሥተተ አርያም ሲደርስ ይዘመራል፡፡ ሠለስት፤ ስምዐኒ ብሎ የሚጀምር ባለ ብዙ ሃሌታ ያለው፤ በዳዊት መዝሙር በሦስተኛው መሥመር እየገባ የሚዘመር፤ አንድም 3 መዝሙሮች ብቻ የሚዘመሩለት ብዙውን ጊዜ በግጥም የሚቀርብ ሲኾን፤ ይኽ ዜማ የሚደርሰው በክብረ በዓላት ዋይዜማ፤ በስብሐተ ነግህ፣ በአርያም፣ በጾመ ድጓ ውሎ፣ በአርያም፣ በሰንበት፣ በፍትሐት ጊዜ ነው፡፡ ክስተተ አርያም፤ የሰማይ መከፈት ማለት ሲኾን በታላላቅ በዓል ቀን እንዲሁም ታላላቅ? ሰዎች ሲሞቱ የሚዘመር ነው፤ ክስተትን ቅዱስ ያሬድ ያዘጋጀው ከዳዊት መዝሙራት፥ ከጸሎተ ነቢያትና ከራሱም ጭምር ኀይለ ቃል ያላቸውን ባለሁለት መስመሮች ሐረግ በመውሰድ ሲኾን ዜማው እጅጉን ነፍስና ሥጋን፥ ልብንና ኅሊናን የሚመስጥ ነው፡፡ ፪ኛ) #ጾመ_ድጓ፤ በዐቢይ ጾም የሚባል ነው፡፡ ፫ኛ) #ድጓ፤ በ4ት ክፍላተ ዘመናት የተቀመረና ጾመ ድጓን በውስጡ የሚያካትት ነው፡፡ ፬ኛ) #ዝማሬ፤ ቅዱስ ቊርባን ድርገት ሲወርድ ለቅዱስ ቊርባን ክብር የሚዘመር ነው፡፡ ፭ኛ) #መዋሥዕት፤ ሰው ሥጋው ከነፍ ስትለይ ፍትሐት የሚደረግበት ጸሎት ነው፡፡ ፮ኛ) #የ፲፬ቱ ቅዳሴያት ዜማ፤ 14ቱን ቅዳሴያት 14ት አባቶች የደረሷቸው ቢሆንም ዜማ የደረሰላቸው ግን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ ፯ኛ) #አንቀጸ ብርሃንን፤ ድርሰቱ ነው፡፡ /ይቀጥላል……/ በተጨማሪም ደግሞ፤ የቅዱስ ያሬድ የዜማ ዐይነቶች ግእዝ፣ ዕዝልና ዓራራይ በመባል ይታወቃል፡፡እነዚህ የዜማ ዐይነቶች የአንዱ ድምፅ ከሌላኛው ድምፅ ያልተደባለቀ፣ ወጥ የሆነ ድምፅ አላቸው፡፡ በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌና ትርጉም ያላቸው በሆኑ የዜማ ምልክቶች (ድፋት፤ ሂደት፤ ቅናት፤ ይዘት፤ ቁርጥ፤ ጭረት፤ ርክርክና ደረት) ደርሷል፡፡ የቅኔ ጀማሪም ነው፡፡ ‹‹ሕንፄሃ …›› የሚለውን ቤት መምቻ ያለውን ቅኔ ልብ ይሏል፤ አንድ ባለቅኔ ግን ይህን ሳይረዳ ‹‹ተትሕተ ያሬድ …›› የሚል ቅኔን ተቀኝቷል፡፡

እንኳን ለቅዱስ ያሬድ በዓለ ስዋሬ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን፡፡ #18ቱ_የቅዱስ_ያሬድ_ገዳማትና_አድባራት፡፡ እሑድ ግንቦት 11 ከዋይዜማው ጀምሮ ቀጠሯችሁን የት ለማድረግ አስባችኋል???፤ በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ታደርጉ ዘንድ 15ቱን የቅዱስ ያሬድ ገዳማትና አድባራት እናስተዋውቃችሁ፡፡ ፠ (#ቅዱስ_ያሬድን_ያልዘከረ_ኢትዮጵያዊ_ምኑን_ኢትዮጵያዊ_ኾነ!?) ፠ (#ቅዱስ_ያሬድን_ያልዘከረ_ካህን_ምኑን_ካህን_ኾነ!?) ፠ (#ቅዱስ_ያሬድን_ያልዘከረ_ሰንበት_ተማሪ_ምኑን_ሰንበት_ተማሪ_ኾነ!?) ፩ኛ). #ደብረ_ሐዊ_ቅዱስ_ያሬድ_ገዳም፤ (ሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት በበየዳ ወረዳ ቤተ ክህነት ከራስ ደጀን ተራራ አጠገብ የሚገኝ)፡፡ እመቤታችን በስደቷ ወቅት ያረፈችበት፤ ጃንደረባው ባኮስ የተሠወረበት፤ ቅዱስ ያሬድ ለ22 ዓመታት የመነነበት፥ ያስተማረበትና የተሠወረበት፤ በሀገራችን ትልቁ የሱባዔ መግቢያ ቅዱስ መካን፤ በዓለም ላይ በሃገራችን ብቻ፤ ከሀገራችንም በአብዛኛው በሰሜን ተራሮች ላይ ብርቅዬ ኾነው የሚገኙት ዋልያና ጭላዳ በአብዛኛው የሚገኙበት ቦታም ነው፡፡ በዚህ ቦታ ቅዱስ ያሬድ ያስተማረበትና የተማሪዎቹ ወንበር ጕባኤ ቦታና የደንጊያ ወንበር፤ ጽዮንን ከሩቅ እያየ ያለቀሰበት ቦታ ላይ የፈለቀ ጠበልና በዘንጉ ያፈለቀው ፈዋሽ ጠበል፤ የተሠወረበት የዋሻ ቤተ ክርስቲያን፣ እንዲሁም አበውና እማት የሚኖሩበት ገዳም ይገኛል፡፡) ፪ኛ). #በየዳ_ደብረ_ገነት_ቅዱስ_ያሬድ_ቤተ_ከርስቲያን፤ በደብረ ሐዊ ተራራ በስተጀርባ የሚገኝ ሲኾን፤ ቅዱስ ያሬድ በደብረ ሐዊ በምናኔ እንደመኖሩ መጠን በተራራው ጀርባ በገጠሩ መንደር የሚገኙ ምዕመናን እኛም ቅዱስ ያሬድን ልንዘክረው ይገባል፤ የቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ደብረ ሐዊ ላይ ብቻ ሳይኾን በኹሉም ቦታ መኖር ይገበዋል በሚል መንፈሳዊ ቅንዓት ተነሣሥተው የሠሩት ነው፡፡) ፫ኛ). #ጣና_ቂርቆስና_ቅዱስ_ያሬድ_ገዳም፤ (ከፎገራ ከመንገዱ የ3 ሰዓት መንገድ እንደተጓዙ፤ በመርከብ ደግሞ ከባሕር ዳር፣ ከጎርጎራ፣ ከደልጊ፣ ከቁንዝላ ተሣፍረው ከጣና ክርስቶስ ሠምራ አጠገብ የሚያገኙት ታላቅ ገዳም ነው፤ መስዋዕተ ኦሪት ይሰዋበት የነበረ፤ ታቦተ ጽዮን ለበርካታ ዓመታት ያረፈችበት፤ ቅዱስ ያሬድ ምልክት ያለውን ድጓ የጻፈበት ቦታ ነው) ፬ኛ). #ወገራ_ደልደሊት_ቅዱስ_ያሬድ_ቤተ_ክርስቲያን፤ (በሰሜን ጎንደር ወገራ አውራጃ አምባ ጊዮርጊስ ወረዳ የሚገኝ ሲኾን፤ በቅዱስ ያሬድ ዜማ ከብቶች ኹሉ ተመስጠው ሳያርሱ በመቆማቸው ምክንያት ቅዱስ ያሬድ የተገረፈበት ቦታ ነው) ፭ኛ). #አኵሱም_ደብረ_ዝማሬ_ቅዱስ_ያሬድ_ቤተ_ክርስቲያን፤ (ከአኵሱም ዩኒቨርሲቲ አጠገብ የሚገኝ ሲኾን፤ የአኵሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንዴት ቅዱስ ያሬድ ተወልዶ ባደገባት፥ ተምሮ ባስተማረባት፤ ሰማያዊ ምሥጢራትና በተገለጡለት፤ የተሰዓቱ ቅዱሳንን የበርካታ ቅዱሳን መናኸሪያ በኾነችው፤ የገዳማትና የአድባራት ራስ፤ የምዕመናን ሁሉ አምባ መጠጊያ በኾነችው ከተማ እንዴት መታሰቢያ ቤተ ከርስቲያን ሳይሠራለት እስካሁን ቀረ ብለው በመንፈሳዊ መነሣሣት በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሠሩት ቤተ ክርስቲያን ነው) ፮ኛ). #አኵሱም_ማይኪራህ_ደብረ_መድኀኒት_ወፈለገ_ጥበብ_ቅዱስ_ያሬድ_ቤተ_ክርስቲያን፤ (ከአኵሱም ከተማ በ4 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በቅዱስ ያሬድ የትውልድ ቦታ አጠገብ በዋናው መንገድ ዳር የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ነው፤ ቅዱስ ያሬድ ከትሏ መውደቅና መነሳት በመመልከት ማስተዋልን የተማረባት ቦታ ስትኾን ሾላዋ እስካሁንም ድረስ እየተካች ትገኛለች፤ ከሾላው ሠር የሚፈልቅ ፈዋሽ ጠበልም አለ፡፡ ይህ ቤተ ክርስቲያን የተሠራው የአኵሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የደብረ ዝማሬን ቤተ ክርስቲያን ሲሰሩ የሃገሬው ሰው ተመልክቶ እንዴት የትውልድ ቦታው ላይ እኛ ቤተ ክርስቲያን ሳንሠራ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቀድመውን ሠሩ በሚል መንፈሳዊ ቅንዓት ተነሣሥጠው በተፋጠነ ሁኔታ ያነጹት ነው፡፡) ፯ኛ). #አዲስ_አበባ_ደብረ_ይባቤ_ቅዱስ_ያሬድ_ቤተ_ክርስቲያን (አዲስ አበባ ጎተራ ማሰለጫ መንገድ አጠገብ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ሲኾን፤ የቅዱስ ያሬድ ፍቅር በልባቸው ባደረባቸው እናት ወ/ሮ ደስታ ሞላ በ1948 የተሠራ ሲሆን ኋላ ላይ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት የፓትርያርክነት ዘመን በምዕመናን አሁን ያለው ሕንፃ ቤ/ክ ተሠርቷል፤ የቅዱስ ያሬድ ትምህርቶች እየተሰጡበት የሚገኝና ወደፊትም በኮሌጅ ደረጃ አስፋፍቶ በርካታ ደቀመዛሙርትን ለማስተማር እቅዱ አለ፤ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ፈዋሽ ጠበልም ይገኛል፡፡) ፰ኛ). #ጎንደር_ደብረ_ሣህል_ቅዱስ_ሩፋኤል_ወአቡነ_ሐራ_ድንግል_ቤተ_ክርስቲያን፤ (ይህ ቤተ ክርስቲያን በጎንደር ከተማ የሚገኝ ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ ሲኾን፤ በዚህ ቦታ ታቦተ ቅዱስ ያሬድ በድርብነት ይከበራል) ፱ኛ). #ጎንደር_ጎሐ_ተራራ_ቅዱስ_ያሬድ_ቤተ_ክርስቲያን ፲ኛ). #ደብረ_ብርሃን_አንሳስ_ማርያም_ቤተ_ክርስቲያን (በደብረ ብርሃን ከተማ የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን ስትኾን ፈዋሽ ጠበል ያለባትና፤ የአቋቋሙ ሊቅ፣ የቅዳሴና የሌሎች ዜማ ትምህርቶች መምህር የኾኑት የመምህር ለምኔ ማስተማሪያ ደብር ነች፤ በዚህ ቦታ ታቦተ ቅዱስ ያሬድ ያሬድ በድርብነት ይከበራል) ፲፩ኛ). #ጀርመን_ክሮምበርግ_ቅዱስ_ዑራኤልና_ቅዱስ_ያሬድ_ቤተ_ክርስቲያን (በጀርመን ሃገር በክሮምበርግ ከተማ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያናችን ነው፡፡) ፲፪ኛ). #ዋሽንግተን_ዲሲ_ኆኅተ_ምሥራቅ_ኪዳነ_ምሕረት_ቤተ_ክርስቲያን፤ (በአሜሪካ ሃገር ዋሽንግተን ዲሲ የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን ስትኾን፤ በዚህ ቦታ ታቦተ ያሬድ በድርብነት ይከበራል) ፲፫ኛ). #ርዕሰ_አድባራት_ዱባይ_ሻርጃ_አጅማን_ሰአሊተ_ምሕረት_ቅድስት_ማርያም_ቤ/ክ (በዱባይ ሃገር ሻርጃ አጅማን የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን ናት፤ በዚህ ቦታ ታቦተ ቅዱስ ያሬድ በድርብነት ይከበራል) ፲፬ኛ). #ባሕር_ዳር_ፈለገ_ጥበብ_ቅዱስ_ማርቆስና_ቅዱስ_ያሬድ ቤ/ክ፤ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ይባብ ካምፓስ አጠገብ የሚገኝ፡፡ ፲፭ኛ). #ደቡብ_አፍሪካ_የቅድስት_ሥላሴና_የቅዱስ_ያሬድ_ገዳም፤ በደቡብ አፍሪካ የሚገኝ፡፡ ፲፮ኛ). #ድሬደዋ_ደብረ_ሰላም_መድኀኔ_ዓለም፤ (በዚህ ደብር ታቦተ ቅዱስ ያሬድ ያሬድ በድርብነት ይከበራል) ፲፯ኛ). ደረስጌ ወረዳ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ፲፰ኛ). #ዳንግል_ደብረ_ሣህል_ቅዱስ_ሚካኤል_ቤ/ክ፤ በጎጃም ክፍለ ሃገር በአዊ ሃገረ ስብከት የሚገኝ ሲሆን በዚህ ደብር ታቦተ ቅዱስ ያሬድ ከ8/10/2008 ዓ.ም. ጀምሮ በድርብነት ይከበራል)፡፡ ከላይ በተጠቀሱት በአቅራቢያችን ባሉ ገዳማትና አድባራት እንድንገናኝ መድኀኔ ዓለም ይፍቀድልን፡፡ /አስተጋባኢ፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት፡፡/ ሌሎች ያላካተትናቸው ካሉና በፎቶ ያልዘገብናቸውን ጨምሩበት፡፡

‹‹እንበይነ አውሎጊስ ለዳንኤል አመ አርአዮ ስቅለተ፤ ከመ እገሪሁ ሰዓምኪ ወሰአልኪዮ ምሕረተ፡፡ ለተአምረ ሣህል ወልድኪ በእንተ ፍቅረ ሰብእ ዘሞተ፤ እንዘ ታዘክሪዮ ድንግል ይምሐረኒ ሊተ፤ ከናፍሪሁ ጽጌ አንኂ ስዕመተ፡፡›› ፠ #አባ_ዳንኤል_፤ እንጀራን ዓሣንም ቢሆን ማርንም ዘይትንም ቢሆን ከብቻው ቅጠል በቀር ሳይቀምስ ፵ ዓመት ተኩል በአስቄጥስ ገዳም ኖረ፡፡ ዜናውም በአስቄጥስ ገዳምና በዓለም ሁሉ ተሰማ፥ የነገሥታት ልጆችም ወደ እርሱ እየመጡ እየተባረኩ ይሄዱም ነበር፤ ግማሾቹም በዚያው ይመነኵሱ ነበር፡፡ ከብዙ ዘመንም በኋላ መነኰሳትን የሚፈትን የመመካት ጾር (‹‹በገዳም ውስጥ እንደእኔ ትርሕምትን ገንዘብ ያደረገ ይኖር ይሆን?›› የሚል) መጣበት፡፡ ይህ ፈተና አንድ ጊዜ ታላቁን ቅዱስ አባ መቃርስን በፈተነው ጊዜ ሰውን የሚወድ ቸሩ አምላካችን አባ መቃርስን ወደ ከተማ እንዲኼድና የወንድማማች ሚስቶችን ኹነው ልጆቻቸውን እያሳደጉ በከተማ ከሚኖሩት ኹለት ገድለኛ እናቶች እንዲማርና ጾሩ እንዲጠፋለት አድርጓል። አሁንም ይህ ታላቅ ቅዱስ አባ ዳንኤል የመጣበትን ጾር ቢመለከት መልአከ እግዚአብሔር ተገለጠና ወንድሜ፣ ቸሩ አምላካችን ክርስቶስ እንዲህ ያለውን የመመካት ከትሕትናና ከፍቅር በቀር አይወድምና ተው አለው። ፠ አባ ዳንኤልም ጌታዬ ይህን እንድተውና ጦሩም እንዲጠፋልኝ ከኔ የሚበልጥ ጻድቅ አሳየኝ አለው፡፡ መልአኩም በሮሜና በቊስጥንጥንያ የነገሠ ንጉሥ ኹኖ ሳለ ነገር ግን በገድሉ ጽኑዕ ታጋይ ተጋዳይ መነኰስ የሆነውን #የጻድቁን_አኖሬዎስን_ ነገር ነገረው። አባ ዳንኤልም ይህን ሲሰማ በምድር ላይ ተደፋና በራሱ ላይ አመድ ነስንሶ አለቀሰ፤ በኋላም ይህን ገድለኛ ንጉሥ ሊያየው ወደደና ጸለየ፡፡ ‹‹ንጉሥ አኖሬዎስም የመነኰሳትን ሥራዎች ሁሉ ስለሚሠራ ከልብሰ መንግሥቱ ሥር በሥጋው ላይ ማቅ ይለብስ ነበር›› ተብሎ የተመሠከረለት ነው፡፡ ፠ ብርህት ደመናም አባ ዳንኤልን መጣችለትና ተጭኖ ወደ ሮሜው ንጉሥ ዘንድ ኼደ፡፡ እንደደረሰም አገልጋዩን ጠርቶ እባክህ ወንድሜ ንጉሡን ማግኘት እሻለሁና የሚያገናኘኝን መኰንን አገናኘኝ አለው፡፡ እርሱም እኔ ባስገባህስ አትገባምን? አለው፤ እግዚአብሔር ይባርክህ ልጄ አስገባኝ አለው፤ አባቴ ሆይ ግን ምድራዊ የሆነ ሟች ፈራሽ ንጉሥን ስለምን ማየትን ወደድህ አለው፣ እርሱም ቸሩ ጌታዬ ስላዘዘኝ እንጂ ነው አለው፤ በኋላም ቆየኝ ለጌታዬ የሚሻውን ገዝቼ ልምጣ ብሎ ወጣና ጥቂት ጨው አምባሻና እና መጻጻ ገዝቶ መጣ፡፡ ይህንም ይዞ አምባሻ ጨው መጻጻና የጎመን ቅጠልም ገዝቶ ወደ ጌታው ወደ ንጉሡ እና ወደ ንጉሡ መምህር አባ አውሎጊስ ዘንድ ገባ፣ አባ ዳንኤልንም በውጭ ተወው፡፡ ንጉሡም ረዳቱን አንተ አላዋቂ ነህን? ስለምን አባ ዳንኤልን በአፍአ ተውኸው አለውና ከመምህሩ ከአውሎጊስ ጋራ ወጣ፡፡ ለአባ ዳንኤልም ሰገዱለት፡፡ ሰላምታም ተሰጣጥተው ወደ ቤተ መንግሥት አስገቡትና በአንድነት ተቀመጡ፡፡ ፠ ዘጠኝ ሰዓትም በሆነ ጊዜ ለማዕድ ሲሰየሙ አባ ዳንኤል እንዳይታመም ፈርቶ ጌቶቼ እንጀራን ባለመብላቴ በእኔ ላይ አታጒረምርሙ፣ እንዳልታመም ፈርቼ ነው አላቸው። ጸሎትንም ጸለዩ፣ ከዚህም በኋላ ንጉሥ አኖሬዎስ አባ ዳንኤልን ስለአመጣጡ መረመረው፣ አባ ዳንኤልም የሚቻልህስ ከሆነ ከንጉሡ ዘንድ አስገባኝ፣ በጌታ ክርስቶስ ትእዛዝ መጥቻለሁና አለው፣ ነገ አስገባሃለሁ አለው፡፡ በማግስቱም አኖሬዎስ ዐይን የሚበዘብዝ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፣ አባ ዳንኤልንም ንጉሡን በዙፋኑ ላይ ሆኖ ባየው ጊዜ ከግርማው የተነሣ አይቶት በታላቅ ፍርሃት ውስጥ ሆኖ ከእግሩም በታች ሰገደለትና አስገቡት ባየውም ጊዜ ፈርቶ ተንቀጠቀጠ፣ ረዳቱም መፍራቱን አይቶ ወደ ማደሪያው መለሰው፡፡ ንጉሡም ችሎቱን ሲጨርስ ልብሰ መንግሥቱን ጨርሶ ልብሰ ምንኲስናውን ለብሶ ወደ አባ ዳንኤል መጣ፣ እርሱም ወንድሜ ሆይ በልቤ ያለውን ነግሬው ወደ ቦታዬ እመለስ ዘንድ ወደ ንጉሡ ለምን አላስገባኸኝም አለው፡፡ አኖሬዎስም አባቴ ሆይ አልገባህምን? ለዚህች ምድር ንጉሥ ብለው የሰየሙኝ እኔ ነኝ አለው፤ አባ ዳንኤልን በሰማ ጊዜ ከእግሩ በታች ሰገደለትና አኗኗሩን ሁሉ ይነግረው ዘንድ በጌታችን ስም አማጸነው፤ አኖሬዎስም በእጅ ሥራው ሰሌን በመታታት ሸጦ ፈጽሞ ከሚያገኘው በቀር ሳይበላ ሳይለብስ ፵ ዓመታት እንደሆነው፣ የሚተርፈውንም ለድኆች እንደሚሸጥ፣ ምግቡም እንጀራና ጨው ቅጠል መጻጻም እንደሆነ፣ የማንንም ገንዘብ ለመቀማት እንዳልደፈረ፣ ድንግልናውንም መጠበቁን ነገረው። ** አባ ዳንኤልም ከእግሩ በታች ሰገደለትና አባቴ በአንተ ላይ ስለተመካሁ ይቅር በለኝ አለው። ከዚህም በኋላ አባ ዳንኤል ፈጽሞ እያዘነ ወደ ቦታው ተመለሰ። ከኹለት ወራትም በኋላ ጻድቁ ንጉሥ አኖሬዎስ ከመምህሩ ተማክሮ መንግሥቱን ጥሎ ወደ አባ ዳንኤል ኼደ። መልአከ እግዚአብሔርም ተሸክሞ አደረሰው። እነርሱም በአንድነት ሲጋደሉ በፍቅር ኑረዋል፡፡ ፠ ደናግል ወደሚኖሩበት ገዳም አንድ የወንበዴዎች አለቃ ሰይጣን አነሳስቶት ወደ ገዳሙ በአባ ዳንኤል ተመስሎ ቆቡን ደፍቶ በሩን አንኳኳ፤ ደናግላኑም ሊዘርፋቸው መምጣቱን ምንም ባለማወቅ ይልቁንም አባ ዳንኤል መጣ ብለው በሩን ከፈቱለትና አስገቡት፤ እግሩንም አጥበው ለበረከት ብለው የእግሮቹን ዕጣቢ በፊታቸው ላይ ረጩት፤ ከመካከላቸውም አንዷ ዐይነ ሥውር ነበረችና ዐይኗ ወዲያው በራላት፤ በዚህም ደናግሉ እጅግ ተደስተው ‹‹አባ ዳንኤል አንተ ንዑድ፥ ክቡድ ነህ›› ብለው ሰገዱለት፡፡ ይህን ጊዜ የሽፍቶቹ አለቃ በጣም ደንግጦ በመጸጸት ወደ አባ ዳንኤል ዘንድ ሄዶ ያደረገውን ሁሉ በመናገር ንስሓ ገባ፡፡ መንኵሶም በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመረ፡፡ ተአምራት እስከማድረግ ደርሶ በሰላም ዐረፈ፡፡ እንዲሁም መምህሩ አውሎጊስና ረዳቱ ቅዱሱ አባ ዳንኤልም ተጋድሏቸውን ፈጽመው በዚህችው ቅድስት እለት በአንድነት አረፉ፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን፡፡ /የቀ.ደ.ሰ. መድኀኔ ዓለምና ደ.ት.ቅ. ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት/

#ለ2ት #ዓለም_ሰዎች (በገዳም ለሚኖሩም በዓለምም ለሚኖሩ) #ትምህርት_የሚሆኑ_አባቶች፡፡ #አባ_ዳንኤል_ገዳማዊ_ንጉሡ_ጻድቁ_አኖሬዎስና_አውሎጊስ ታሪካቸው እጅጉን ከመሚሰጠውና ከጀመሩት ሳይጨርሱት ከማያቋርጡት በስንክሳር ላይ ከተጻፉት መካከል አንዱ ዛሬ ግንቦት 8 በዓለ ዕረፍቱ የሚታሰበው፤ የከበረና የተቀደሰ፥ የገዳማውያን መብራት #አባ_ዳንኤል_ገዳማዊ_ነው፡፡ ‹‹አባ ዳንኤል ዘደብረ ሲሐት›› (ገዳመ ሲሐትን ለብዙ ዘመን ተጋድሎባታል፤ ብዙ ቅዱሳን ደቀመዛሙርትን ወልዶባታልና) ‹‹አባ ዳንኤል ዘገዳመ አስቄጥስ›› (በአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ሆኖ ተሹሞ እልፍ አእላፍ መነኰሳትን በጽድቅ መንገድ መርቷልና) #አባ_ዳንኤል፤ ፠ በትውልድ ግብጻዊ ሲሆን ወደ ገዳም የገባው ገና በወጣትነቱ ሲሆን ዘመኑም በዘመነ ጻድቃን (በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን) ነው፡፡ ፠ ቀን ቀን መነኰሳቱን ሲናዝዝ ፥ ድውያንን ሲፈውስ ፥ ሥርዐተ ገዳምን ሲቈጣጠር ይውላል፡፡ ከብዙ የቅድስና ዓመታት በኋላም ከትጋቱ የተነሳ ለምግብና ለእንቅልፍ ጊዜ አልነበረውም፤ ስለዚህ ሲመሽ ደግሞ ጭው ወዳለውና ስውራን ወደ ሚገኙበት በርሃ ይወርዳል፡፡ ሙሉውን ሌሊትም የተሰወሩ አባቶችን ሲፈልግ ያድር ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት የብዙ ስውራንን ገድል የጻፈ ሲሆን፤ ባረፉ ጊዜም ገንዞ በመቅበር በረከታቸውን ተሳትፏል፡፡ ፠ እርሱ ገንዞ ቀብሮ፤ ዜናቸውን ከጻፈላቸው ሥውራን ቅዱሳንም እንደ አብነት እሥራኤላዊቷን ቅድስት ዓመተ ክርስቶስን (መላ ሰውነቷን ጠጉሯ የሸፈናትና ለ38 ዓመት ራቁቷን በሥውር የኖረች) እንዲሁም ስሟን እንጣልዮስ አስብላ የነበረች ቅድስት በጥሪቃ ንግሥትን (መንግሥቷን ትታ በሥውር የኖረች፤ ወንድ መስላ ኖራ ስታርፍ ሴት መሆኗ የታወቀውን) መጥቀስ እንችላለን፡፡ ፠ ራሳቸውን የተናቀ አድርገውና ሰውረው የሚኖሩትን የሚያከብር ነበር፤ ለምሳሌ በሴቶች ገዳም እብድ ናት ተብላ በበር የተጣለችውን ቅድስት አናሲማን ፤ በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ዻዻሳቱ ሳይቀር ‹‹እብድ ነው›› ብለው የናቁትን ከዝሙት ጦር በመሸሽ ራሱን እብድ ያደረገውን ቅዱስ ምሕርካን እብድ ሳይሆኑ ራሳቸውን የሠወሩ ቅዱሳን መሆናቸውን ገልጧል፡፡ ፠ በሐዋርያዊነቱም በጊዜው ጦማረ ልዮን የሚባል የኑፋቄ ደብዳቤ ይላክ ነበርና ለዚህ ኬልቄዶናዊ ኑፋቄ በትጋት ምላሽ ይሰጥ ነበር፡፡ አንድ ቀንም በንጉሥ ትዕዛዝ ኑፋቄው በእርሱ ገዳም ሊነበብ ሲል ቅዱሱ ከወታደሩ ቀምቶ ስለ ቀደደው ለሞት እስኪደርስ ደብድበውታል፡፡ ፠*፠ አውሎጊስ የሚባለል የወፍጮ ድንጋይ እየወቀረ (እየጠረበ) በመሸጥ ለድኆችና ጦም አዳሪዎች የሚመጸውት ጻድቅ ሰው ነበር፡፡ አባ ዳንኤልም የአውሎጊስን መልካም ሥራ ተመልክቶ እጅግ ደስ ብሎት ለአውሎጊስ የሀብቱን መጠን እንዲጨምርለትና ይበልጥ እንዲመጸውት በማሰብ ወደ እግዚአብሔር በጸሎት አሳሰበ፡፡ ለአውሎጊስም ዋስ ሆነውና ሀብቱ ተጨመረለት፥ ብዙ ወርቅንም አገኘ፡፡ አንድ ቀን የሚወቅረውን ድንጋይ ሲፈነቅል በሸክላ ዕቃ የተደፈነ ሙሉ ወርቅ አገኘ፡፡ ወደ ቊስጥንጥንያም ከተማ ሄዶ ለንጉሡ አስረከበና የንጉሡ የሠራዊት አለቃ ሆኖ ተሾመ፡፡ ከተሾመም በኋላ የቀድሞውን የጽድቅ ሥራውን ተወ፡፡ አባ ዳንኤልም ስለ እርሱ ሰምቶ ሊያየው ቢሄድ በፈረስ ላይ ተቀምጦ በሠራዊት ታጅቦ በትዕቢት ተመልቶ አገኘው፡፡ ክፉ የትዕቢት መንፈስ አድሮበት ነበርና፡፡ አባ ዳንኤልም አውሎጊስ ሀብት እንዲያገኝ በመለመኑ አዘነ፡፡ በሌሊትም የአውሎጊስ ነፍስ በእርሱ ምክንያት እንደጠፋች ራሱ አባ ዳንኤልም ሲሰቀልና እመቤታችን ስለ እርሱ ስትማልድ ራእይ አየ፡፡ ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ የአውሎጊስ ሀብት እንዲጠፋና ወደ ቀደመ ግብሩ እንዲመለስ በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዘ፡፡ መልአክም ተገልጦለት በእግዚአብሐር የፍርድ ሂደት ውስጥ ጣልቃ በመግባቱ ከገሠጸው በኋላ አውሎጊስም ምሕረት እንደሚያገኝ ነገረው፡፡ አውሎጊስን የሾመው ንጉሥም ሞተና ሌላ ንጉሥ ነገሠ፡፡ አውሎጊስንም ንብረቱን ሁሉ ቀምቶ ነፍሱንም ለመግደል አሳደደው፡፡ አውሎጊስም ነፍሱን ለማዳን ሽሽቶ ወደ ሀገሩ በመግባት የቀድሞ ሥራውን መሥራት ጀመረ፡፡ ነዳያንንም እንደ ዱሮ መመገብ ጀመረ፡፡ ፠ ይህንን ታሪክ በተመለከተ ሊቁና የወርቃማው ዘመን ወርቃማው ደራሲ ከሚባሉት አንዱ የሆነው አባ ጽጌ ድንግል ማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ እንዲህ ሲል እመቤታችንና ከልጇ አውሎጊስን የተዋሰውን አባ ዳንኤልን እንዳስማረችው አመስጥሮ አስቀምጦልናል፡፡

‹‹ ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይህ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት በጥር ፲፯/፳፻፲፪ ዓ.ም በቀ
+1
‹‹ ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይህ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት በጥር ፲፯/፳፻፲፪ ዓ.ም በቀ/ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለም ቤ/ክ በሥርዐተ ተክሊል ጋብቻሽን የፈጸምሽው የሰ/ት/ቤታችን አባል እኅታችን፤ #አለምነሽ_ዳምጣቸው_ከምስጋናው_በላይ ጋር የፈጸማችሁትን ጋብቻ፤ የይስሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ፥ ያጣምራችሁ፥ ያዋሕዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኋላ ይከተላችሁ፡፡ ✤ ‹‹ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንዲሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እንደዚሁ ጌታ ቤተ ክርስቲያንን እንደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡›› ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለፖሊካርፐስ በላከው መልእክቱ ✤ ከተጋባችሁ በኋላ ባልና ሚስት አንድ አካል ናችሁ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>> ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ዘርአያዕቆብ፡፡ /ከቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#ከሰይጣን_ጋር_የተደረገ_ቃለ_ምልልስ (ተዋስኦተ ጳውሊ ምስለ ሰይጣን)፤#ክፍል#፮_ (#የሰይጣን_ኀይል_በምን_እንደሚደክም፤ #ሰው_በሰራው_ኀጢአት_ተጠያቂው_ራሱ_እንጂ_ሰይጣን_እንዳልሆነ፤ #ሰይጣን_ሰዎችን_ፈጣሪያቸውን_እንዴት_ባለ_መንገድ_እንደሚያስክዳቸው፤ #አንድን_ኀጢአት_ያለፈን_ሰው_በሌላ_ኀጢአት_እንደሚፈትኑት፤ አባ ጳውሊ፤ ኃይላችሁ በምን ይደክማል? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ #ከፍቅር፥ ከትዕግሥት፥ ከጾም፥ ከጸሎት፥ ከመታዘዝ፥ ከትጋሃ ሌሊትና ከመሳሰሉት ትሩፋቶች ሁሉ ጋር ኃይላችን የሚደክመው #በትሕትና ነው አለው፡፡ እኛ በፍጥረታት ሁሉ ላይ ጭንቅ የሆነ መከራ ከማምጣት ቸል አንልም አንቦዝንም፡፡ በሚቻለን ሁሉ እንፈትናቸዋለን አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ አንተ እንደምትለኝ ከሆነስ ሰዎች ምንም ኃጢአት የለባቸውም፡፡ ኃጢአትስ የሚሆንባችሁ የክፋትንና የርኵሰትን ሥራ በምታሠሯቸው በአንተና በወገኖችህ ላይ ነው አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ እኔ የንግድ ቤቱ ነኝ፡፡ በእኔ ዘንድም ብዙ የሚሸጡ የኃጢአት ዕቃዎች አሉኝ፡፡ የንግድ ቤቱንም በር እከፍታለሁ፡፡ ሁሉም እንደየፍላጎቱ የሚሻውን ይገዛል፡፡ ስለዚህ #ሰው ሁሉ በራሱ ፍላጎት የሚበድል ከሆነ እርሱ በሠራው ኃጢአት እኔ ስለ እርሱ አልጠየቅም፤ ኃጢአትም የለብኝም አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ አንተ የተረገምህ! የንግድ ቤትህ እንዳይከፈት እግዚአብሔር ይቅር አይበልህ፡፡ ፈጽመህም መሸጥ እንዳትችል የንግድ ቤትህ ይዘጋ፤ ይፍረስ አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ አንተ ክፉ ሽማግሌ ያለ በደሌ ስንት ጊዜ ትረግመኛለህ፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ከአንተ ጋር በመሆኔ ሃይሌን አደከምከኝ፤ ሰውነቴንም አሠቃየሃት፡፡ ስለዚህ እሄድ ዘንድ ተወኝ አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ ሰዎች ፈጣሪያቸውን እንዲክዱ የምታደርገው በምን መንገድ እንደሆነ እስኪ ዳግመኛ ንገረኝ አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ በዚህ ዓለም የማደርገውን ሁሉ ነገርሁህ፡፡ #መጀመሪያ ልጆች የወላጆቻቸውንና የአሳዳጊዎቻቸውን ምክር እንዳይሰሙ፣ ለቃላቸውም እንዳይታዘዙና ከእናንተ ይልቅ በእውቀት እኛ እንበልጣለን፣ እኛ እናውቃለን እንዲሉ እናደርጋቸዋለን፡፡ ##ዳግመኛም ወላጆቻቸውንና በዕድሜ የሚበልጧቸውን እንዲሳደቡ እናደርጋቸዋለን፡፡ /፪ጢሞ.፫:፪/፡፡ በዚህ ምክንያት የቤተሰብ ፍቅር እናሳጣቸዋለን፡፡ በሄዱበት ሁሉ እየተረገሙ ይኖራሉ፡፡ ###ከዚህ በኋላ በዝሙት፥ በክህደት፥ የምንዝር ጌጥን በመውደድ፥ በስካር፥ በስርቆት፥ ነፍስን በመግደል እንዲወድቁ እናደርጋቸዋለን፡፡ በመጨረሻም ተስፋ ቆርጠውና አእምሮ አጥተው ቊጥር የሌለው ኃጢአትን እንዲሠሩ እናደርጋቸዋለን አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ በዕድሜ ያረጀ ዘመኑም የተቃረበና ሥጋውም የደከመ ሽማግሌ ኃይሉ ይደክማልና በምን ትፈትኑታላችሁ? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ እኛ በሽማግሌዎች ብዙ ምክንያት እናገኛለን፡፡ ስንፍና እናመጣባቸዋለን፤ ጾምንና ጸሎትን እንከለክላቸዋለን፡፡ ዘመናቸውን እስኪረግሙና ራሳቸውን እስኪያጠፉ ድረስ የሚያደርስ ጭንቀትና ጥርጣሬን እናመጣባቸዋለን፡፡ ክፉ ሐሳብንና ገንዘብ መውደድንም እናመጣባቸዋለን፡፡ ተስፋ መቁረጥን ሰላም ማጣትን በውስጣቸው እናደርጋለን፡፡ ከልባቸው የኅሊና ጸሎትን፥ ከአንደበታቸው ምስጋናን እናጠፋባቸዋለን፡፡ ለልጆቻቸው፥ ለዘመዶቻቸው፥ ለሚረዷቸው፥ ለሚቀርቧቸው ሁሉ ሁከተኞች እንዲሆኑ እናደርጋቸዋለን አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ ዳግመኛ እንዲህ ብሎ ጠየቀው፤ አንተ የተረገምክ ከእናንተ እያንዳንዳችሁ ሰው ሁሉ በፍትወት ተማርኮ ኃጢአትን እንዲሠራ ለማድረግ ሁላችሁም የተሰለፋችሁ አይደለምን? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ አዎ ሁላችንም #ሰውን በኃጢአት ምኞት ተማርኮ እንዲወድቅ ለማድረግ የተሰለፍን ነን፡፡ ብዙዎችንም እናስታቸዋለን፤ በኃጢአት ላይ ኃጢአት እንዲሠሩ እናደርጋቸዋለን፡፡ ዳግመኛም #ከአጠመድነው ወጥመዳችን አምልጦ የወጣውን ሰው በሌላ በታላቅ የኃጢአት ወጥመድ እንዲወድቅ አጥብቀን እንዋጋዋለን አለው፡፡ #ለሰው በሚፈልገው ተመስለው በምትሐት እንደሚገለጹ፤ የሰይጣናት አሳሳች መሆናቸው ለጥቂት ደጋጎች እንጂ (በመጨረሻ በሥራቸው) እንጂ ለሁሉ እንደማይታወቁ፤ በገዳም የሚኖሩትን በምን እንደሚዋጋቸውና እንደሚያሸነፉት፤ ከሰው ልጆች የሚፈራቸውና የማይፈራቸውን .… ክፍል ፯.… ይቀጥላል ነገ ይጠብቁን/ #በፌስቡክ_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ https://t.me/medihanaelem

፠ #የ2012 ዓ.ም. #የርክበ_ካህናት_የቅዱስ_ሲኖዶስ_ጕባኤ_ውሳኔ፤ ፩ኛ) በቫይረሱ የተጠቁትን ምሕረት እንዲሰጥልን፥ እስካሁን ያልተያዙትን እንዲጠብቅልን ተማኅጽኖውን ለእግዚአብሔር አቅርቧል ያቀርባ
+3
፠ #የ2012 ዓ.ም. #የርክበ_ካህናት_የቅዱስ_ሲኖዶስ_ጕባኤ_ውሳኔ፤ ፩ኛ) በቫይረሱ የተጠቁትን ምሕረት እንዲሰጥልን፥ እስካሁን ያልተያዙትን እንዲጠብቅልን ተማኅጽኖውን ለእግዚአብሔር አቅርቧል ያቀርባልም፤ ፪ኛ) ካህናትና ምዕመናን እንደ አንድ ልብ መካሪ፥ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ በመሆን በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በቤታቸው የሚያደርጉትን ጸሎት አጠናክረው እንዲቀጥሉ፤ ፫) ምዕመናን ከቤተ ክርስቲያን ተለይተው መኖር ስለማይችሉ በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች አስተናጋጅነት ጥንቃቄ በተመላ መልኩ (የሃይማኖት አባቶችና የጤና ባለሙያዎች በሚሰጡት ምክርና መንግሥትም በሚሰጠው መመሪያ መሠረት) መንፈሳዊ ተግባራትን በቤተ ክርስቲያን እንዲያከናውኑ፤ ፬) ያለው ለሌለው በማካፈል መንፈሳዊ ትሩፋት እንድንሠራ፤ ፭) በአሁን ጊዜ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ከሁሉም በፊትና በላይ ለሃገራዊ ሰላምና ሕዝባዊ አንድነት በጋራ እንዲቆሙ፤ ፮) ለሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ሕዝባዊ አንድነትና ተሳትፎ እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን፡፡ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem ፠ በዩቲዩብ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ Https://m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

ሰበር ዜና፤ #የተዘጉ_የቤተ_ክርስቲያን_በሮች_እንዲከፈቱ_ቅዱስ_ሲኖዶስ_ወሰነ፡፡ ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 5 የርክበ ካህናት ስብሰባውን እያደረገ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ የተዘጉ የቤተ ክርስቲያን በሮች ተከ
+2
ሰበር ዜና፤ #የተዘጉ_የቤተ_ክርስቲያን_በሮች_እንዲከፈቱ_ቅዱስ_ሲኖዶስ_ወሰነ፡፡ ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 5 የርክበ ካህናት ስብሰባውን እያደረገ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ የተዘጉ የቤተ ክርስቲያን በሮች ተከፍተው መንፈሳዊ አገልግሎቱ በፀረ ኮቪድ-19 የጥንቃቄ ተግባራት እየተመራ እንዲፈጸም አዘዘ፡ • ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከመንግሥት ጋራ በመነጋገር ትእዛዙን እንዲያስፈጽም መመሪያ ሰጠ፤ • አገልግሎቱን በጥንቃቄ ተግባራቱ መሠረት ለማስፈጸም አጥቢያዎች ሓላፊነቱን ይወስዳሉ፤ • የሰንበት ት/ቤቶችን በማስተባበር፣ መንፈሳዊ አገልግሎቱ በአግባቡ እንዲከናወን ያደርጋሉ፤ • ጥምቀቱ፣ ቊርባኑ፣ ተክሊሉ፣ ፍትሐቱ ርቀትን ጠብቆ በተገቢ የልኡካን ቁጥር ይፈጸማል፤ • ቅዱስ ሲኖዶሱ፥ የቤተ ክርስቲያን በር በግድ እየተዘጋ በፖሊስ የሚደረገውን ጥበቃ ተችቷል፤ ቋሚ ሲኖዶሱ፥ “በስሜ የተደረገ እንጂ የእኔ ውሳኔ አይደለም፤” ብሏል፤ • የጠቅላይ ቤተ ክህነት ፀረ ኮቪድ-19 የተስፋ ልኡክ ዐቢይ ግብረ ኀይል፣ ሪፖርቱን ለምልዓተ ጉባኤው አቅርቧል፤ • አስቸኳይ ዐዋጁን በማስፈጸም ሰበብ፣ ፖሊስ፣ በአገልጋይ ልኡካንና ምእመናን ላይ ጥቃቶችንና ማጥላላቶችን መፈጸሙ ቅዱስ ሲኖዶሱን አሳዝኗል፤ • ማንም እገዛ ሳይጠይቃቸው በበሯ ቆመው እየተሳደቡና እየደበደቡ ከፍተኛ የኀይል ርምጃ መውሰዳቸው ሳያንስ፣ ሥርዐተ አምልኮዋን የሚያጥላሉ የሌላ እምነት ተከታይ ፖሊሶችም እንዳሉበት በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡ ፠ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኃዋ (ቤተ ክርስቲያኖች ይከፈቱ) /ሃይማኖተ አበው/ ፠ ኢይትዓጸዉ አናቅጽኪ፡፡ (ደጆችሽ አይዘጉ) /ት.ኢሳ. 60/ /ምንጭ፤ ሐራ ዘተዋሕዶ/ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ት

#ርክብ_ካህናት (#ዕለተ_ጥብርያዶስ፤ #ዳግሚት_ዕለተ_አግብኦተ_ግብር፤ የሃገራችን የቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ ቀን)፤ #ረቡዕ_ግንቦት_5 ርክበ ካህናት የሁለት ቃላት ጥምረት ሲኾን እነዚህም፤ **1ኛ. ረክብ የሚለው ቃል ተራከበ ተገናኘ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጕሙም ማግኛ፣ መገኛ፣ መገናኛ ማለት ነው፡፡ /ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገጽ ፰፴፩/፡፡ **2ኛ. ክህነት የሚለው ቃል ከዲቁና ጀምሮ እስከ ከጵጵስና ድረስ ያሉትን መዓርጋት (በጥቅሉ ዲያቆናትን፣ ቀሳውስትንም ኾነ ጳጳሳትን) የሚያጠቃልል ስያሜ ነው፤ ካህን (ነጠላ ቍጥር) ሲኾን ካህናት ደግሞ (ብዙ ቍጥር) ነው፤ ብዙ ጊዜ ግን ይህን ባለማወቅ ካህናት የሚለውን ለቀሳውስት ብቻ መጠሪያ ሲኾን እናያለን፤ አለማወቅ ነው! (ለምሳሌ በቅዳሴ መጨረሻ ላይ ዲያቆኑ በእደ …… ካህን ይባርከነ ቢል ለኹሉም ያስኬዳል፥ ሰዋስዉም ያዛል፥ ሥርዐቱም ይኸው ነው፤ ነገር ግን ዛሬ ዛሬ በእደ … ካህን ይባርከነ በማለት ፈንታ በእደ ብፁዕ ፓትርያርክ፣ በእደ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ፣ በእደ ቆሞስ …. ሲባል ይታያል፤ መስተካከል ያለበት ጉዳይ ነው፡፡) ርክበ ካህናት ማለትም የአባቶች ካህናት (ማለትም በጵጵስና ማዕረግ ያሉ /ኤጲስ ቆጶሳት፣ ጳጳሳት፣ ሊቃነ ጳጳሳትና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስን ያጠቃለለ (የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት) ጕባኤ፤ የካህናት መገኛ፥ መገናኛ ጉባኤ (መሰባሰቢያ፣ መወያያ) ማለት ነው፡፡ በዓሉ በየዓመቱ የትንሣኤ በዓል በዋለ በ፳፭ኛው ቀን ሁልጊዜ በዕለተ ረቡዕ ይውላል፤ ወሩና የሚውልበት ቀን ግን በኢየዓርግና በኢይወርድ (በባሕረ ሓሳብ የበዓላትንና የአጽዋማትን) ቀመር ተከትሎ የሚወጣ ስለኾነ ከፍና ዝቅ ይላል፡፡ የአጽዋማትና የበዓላት ቀመር በቅዱስ ድሜጥሮስ አማካኝነት ከመዘጋጀቱ በፊት (ዐቢይ ጾም ሰኞ፣ ስቅለት ዓርብ፣ ትንሣኤ እሑድ፣ ርክበ ካህናት ረቡዕ፣ ዕርገት ሐሙስ፣ ጰራቅሊጦስ እሑድ እንዲሆን ከመደረጉ በፊት) ርክበ ካህናት በየዓመቱ ግንቦት ፳፩ ቀን ይውል ነበር /መጽሐፈ ግጻዌ ግንቦት ፳፩/፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጐ ከተነሳ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ በየጸጋቸው መጠን እየተገለጠ ያጽናናቸው፥ ያጸናቸው፥ ያስተምራቸው፥ ይባርካቸውም ነበር፤ ጌታችን እስከ ዕርገቱ ባሉ ፵ ቀናትም መጽሐፈ ኪዳንን፣ ትምህርተ ኅቡዓትን፣ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን አስተምሯቸዋል፤ በልቡናቸውም አሳድርድሮባቸዋል፡፡ ፠ በመጽሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ ወንጌል፤ ከዕርገቱ አስቀድሞ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ፫ ጊዜ በጕባኤ መገለጡ ተዘግቦ ይገኛል፡፡ እነዚህም፤ 1ኛ. የትንሣኤ (ዮሐ. 20፥19) 2ኛ. የአግብኦተ ግብር (ዳግም ትንሣኤ) /ዮሐ. 20፥:26/ 3ኛ. የጥብርያዶስ፤ (ዮሐ. 21፥1) ለድንግል ማርያም ግን በኹሉም እለታት መገለጡን አበው ያስተምራሉ፡፡ በጥብርያዶስ ባሕርም ከዐሥራ አንዱ ቅዱሳን ሐዋርያት ጋር ምሳ በልቷል፡፡ የርክበ ካህናት በዓል መነሻም ጌታችን ለሦስተኛ ጊዜ ከተገለጠበት ከጥብርያዶስ ባሕር ካለው ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በዚህች ዕለት በቅዱስ ዼጥሮስ መሪነት ሐዋርያቱ ወደ ጥብርያዶስ ባሕር ሔዱ፡፡ አሶችን ሊያጠምዱም በብዙ ደከሙ፤ ነገር ግን ጌታችን በረድኤት አብሯቸው አልነበረምና አንዳች አሣ በመረባቸው ሊገባ አልቻለም፡፡ ማጥመድ (አስተምሮ ከክህደት ወደ ሃይማኖት፤ ከኀጢአት ወደ ጽድቅ መመለስ) የሚቻለው በረድኤተ እግዚአብሔር እንጂ በእውቀት ብዛት ወይም በአንደበተ ርቱዕነት ብቻ አይደለምና፡፡ ሲነጋ ግን መድኀኒታችን ወደ ቅዱሳን ደቀ መዛሙርቱ መጣ፤ በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻም ቆሞ ታያቸው፤ ከሚወደው ደቀ መዝሙሩ ከቅዱስ_ዮሐንስ በቀር ጌታችን መሆኑን ያወቀው ግን አልነበረም፡፡ ቸሩ አባት ‹‹ልጆቼ! አንዳች የሚበላ ነገር አላችሁ?›› ሲል ጠየቀ፤ ‹‹ጌታ ሆይ! የለም›› አሉት፡፡ ‹‹የለንም›› ብሎ የሌለንን ነገር በጌታ ፊት ማመኑ እጅግ መልካም ነው፤ ምክንያቱም ያጣነውን ነገር ሊሰጠን፥ የጎደለንን ሊሞላልን፥ የጠፋብንን ሊጠቁመን ቸርነቱ ብዙ ነውና፡፡ ያን ጊዜ ሐዋርያቱን መረባቸው በመርከብ ቀኝ እንዲጥሉ አዘዛቸው፡፡ እነርሱም በደስታ ጣሉ፤ በአግራሞት እስኪሞሉ ድረስ መረባቸውን መሳብ አቅቷቸው ሊቀደድ እስኪደርስ ድረስ 153 ዓሦች ተያዙላቸው፡፡ ያን ጊዜም የሚወደው ደቀ መዝሙሩ ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችን መኾኑን ለቅዱስ ዼጥሮስ ‹‹ጌታ እኮ ነው›› አለው፤ ሽማግሌው ቅዱስ ግን ራቁቱን ነበርና ወደ ባሕሩ ተወረወረ፡፡ ከአፍታ በኋላም ጌታችን ከሐዋርያቱ ጋር በድጋሚ (ለ፪ኛ ጊዜ) ለምሳ ተቀመጠ፤ ባርኮ ሰጥቶ ልባቸውን ሊያጸና አብሯቸው በላ፡፡ በዚያች ሰዓት ቅዱስ ዼጥሮስን ፫ ጊዜ ‹‹ትወደኛለህን?›› ሲል ጠየቀው፤ ቅዱሱ አረጋዊም እየደጋገመ ‹‹ለሊከ ተአምር ከመ አነ አፈቅረከ (እንድወድህ አንተ ታውቃለህ)›› ሲል መለሰ፡፡ ጌታም በበጐች ሐዋርያት (ካህናት)፤ በጠቦቶች አርድእት (ዲያቆናት)፤ በአባግዕት ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት (ምዕመናን ወምዕመናት) ላይ ሁሉ እረኛ እንዲሆን ሾመው፡፡ ይህ ምሥጢር ለጊዜው ጌታችን ሐዋርያትን፣ ሰብዐ አርድእትንና ሠላሳ ስድስቱን ቅዱሳት አንስት በአጠቃላይ መቶ ሃያውን ቤተሰብእ እንዲጠብቅና እንዲከባከብ ቅዱስ ጴጥሮስን ማስጠንቀቁን፤ ፍጻሜው ግን የቤተ ክርስቲያን አባቶች (ጳጳሳት) መምህራንንና መላው ሕዝበ ክርስቲያንን እንዲጠብቁና እንዲያስተዳድሩ በእግዚአብሔር መሾማቸውን የሚያስረዳ ትርጕም አለው /ዮሐ.፳፩፥፩-፲፯ (አንድምታ ትርጓሜ)/፡፡ ቀጥሎም የቅዱስ ጴጥሮስን የሰማዕትነቱን ምሥጢር ገልጦለት ‹‹ተከተለኝ›› (ለጊዜው በእግር፤ በኋላ ግን በግብር ምሰለኝ) ብሎታል፡፡ ወልደ ነጐድጓድ ወፍቊረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስም ሞትን እንደማይቀምስ እንዲሁ ተናግሮለታል:: ፠ ጌታ ለሐዋርያት በአንድነት የተገለጠባትን ይህች ቀን እነዚህ ሁሉ ተግባራት የተከናወኑባት ናትና (የትንሣኤ በዓል ፳፭ኛ ቀን) መሠረት በማድረግ፤ የኋላ ሊቃውንት በየዓመቱ የትንሣኤ በዓል በዋለ በ፳፭ኛው ቀን ዐራቱ ሊቃነ ጳጳሳት የሚሰበሰቡበት የካህናት መገናኛ ቀን ርክበ ካህናት ይሁን ብለው ወስነዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ርክበ ካህናት በዓለ ትንሣኤ በዋለ በ፳፭ኛው ቀን፣ በበዓለ ሃምሳ እኩሌታ በዕለተ ረቡዕ ይዘከራል፤ በያዝነው ዓመት በ፳፻፲፪ ዓ.ም የትንሣኤ በዓል ከተከበረበት ዕለት (ሚያዝያ ፲፩ ቀን) ጀምሮ ብንቈጥር ፳፭ኛው ቀን ግንቦት ፭ ቀን ይኾናል፡፡ በመኾኑም የዘንድሮው ርክበ ካህናት ግንቦት ፭ ቀን በዕለተ ረቡዕ ይውላል ማለት ነው፡፡ ይህ በዓል ከቅዱሳን ሐዋርያት ጀምሮ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተዳድሩ የቆዩ አባቶቻችን ጌታንና ደቀ መዛሙርቱን አብነት በማድረግ በጋራ በመሰባሰብ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን የተቀላጠፈ አገልግሎት እንደዚሁም ለምእመናን አንድነትና መንፈሳዊ ዕድገት የሚበጁ መንፈሳውያን መመሪያዎችን የሚያስተላልፉበት እለት ነው፡፡ *** ይህንን የጌታችን ትእዛዝና የሐዋርያትን ሥልጣነ ክህነት መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜ ጉባኤ ያደርጋል፤ ፠ ፩ኛ. የመጀመሪያው ጉባኤ ጥቅምት ፲፪ ቀን (የቅዱስ ማቴዎስ በዓለ ዕረፍት) ሲሆን፣ ፠ ፪ኛ. የትንሣኤ በዓል በዋለ በ፳፭ኛው ቀን የሚደረገው ይህ ርክበ ካህናት ነው፡፡ ከላይ በተጠቀሱት ዕለታት በዋዜማው ሁሉም ጳጳሳት ከየሃገረ ስብከታቸው በመንበረ ፓትርርኩ በምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው የመሐረነ አብ ጸሎት ይደርሳል በነጋታው ጕባኤው ይካሄዳል፡፡ የቀ.ደሰ.መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት

የመርካቶ ደብረ ኃይለ ቅዱስ ራጕኤል አንቀጸ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት አድራሻ ከዚህ የሚከተለው ስለሆነ እንድትጠቀሙበት እነሆ ብለናል፡፡ የፌስ ቡክ ገጽ፤ https://www.facebook.com/
የመርካቶ ደብረ ኃይለ ቅዱስ ራጕኤል አንቀጸ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት አድራሻ ከዚህ የሚከተለው ስለሆነ እንድትጠቀሙበት እነሆ ብለናል፡፡ የፌስ ቡክ ገጽ፤ https://www.facebook.com/sundayschoolofSR/ የቴሌግራም ገጽ፤ https://t.me/Anqetseberhansundayschool የዩቲዩብ ገጽ፤ አንቀጸ ብርሃን ሚዲያ Anqetse berhan media (https://www.youtube.com/channel/UCj5T3d_1kE4BFizwS12ompQ

ሰይጣን በአባ ጳውሊ ተገዝቶ ሳለ ያወጣው ምሥጢር #ከሰይጣን_ጋር_የተደረገ_ቃለ_ምልልስ (#ተዋስኦተ_ጳውሊ_ምስለ_ሰይጣን)፤ #ክፍል#፭_ ++አባ ጳውሊ፤ የወገኖችህ ቊጥራቸውና ስማቸው እንዲሁም በዚህ ዓለም የምትታዩት ብዛታችሁ ምን ያህል እንደሆነ እውነቱን ትነግረኝ ዘንድ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ባየኸው በፈጣሪ ስም አምልሐለው አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ ነገዳችን ብቻ ነው እንጂ ቊጥራችን አይታወቅም አለው፡፡ +አባ ጳውሊ፤ በአኗኗራችሁ ከእናንተ የበላይ አለቃ አለን አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ አዎን አለ ፤ ታላቁ አለቃ እኔ ነኝ አለው፡፡ ++አባ ጳውሊ፤ ከእናንተ ወገን በክፋትና በማሳት ከወገን ወገን፥ ከሰይጣን ሰይጣን የሚበላለጥ አለን? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ አዎን አለ አለው፡፡ +አባ ጳውሊ፤ ከሰው ወገን ዘመድ ወዳጅ አለህን? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ አዎን አለኝ አለው፡፡ ++አባ ጳውሊ፤ አንተ የረከስክ ነህና ወዳጅህ ማነው? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ #የእግዚአብሔርን ሕግ ትቶ ኃጢአትን የሚሠራ ነው አለው፡፡ +አባ ጳውሊ፤ ስለምጠይቅህ ነገር ምንም እንዳትሸሽገኝ በመስቀል ላይ በተሰቀለው በጌታ ስም አምዬሃለው አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ አንተ ክፉ ሽማግሌ ከአንተ የተነሳ ወዮልኝ ፤ ከሥራዬ ምንም የምደብቅህ የለኝምና በዚህ ቅዱስ ስም አታቃጥለኝ ዝም በል አለው፡፡ ++አባ ጳውሊ፤ አንተ ከክብርህ የተዋረድክና የተረገምህ! #ክፉ ሥራህን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው እስኪ ንገረኝ አለው፡፡ ሰይጣን፤ አንተ ሽማግሌ ብዙዎች እኔ እንደማስታቸውና እንደማልጠቅማቸው አያውቁምና ሥራዬን አትነግርብኝምን? አለው፡፡ +አባ ጳውሊ፤ የምጠይቅህን ክፉ ሥራህን ንገረኝ እንጂ እኔ እንዳልናገር የማዘዝ ሥልጣን የለህም አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ ከቸርነቱ ያርቃቸው ዘንድ አምላካቸውን ሐሰተኛ አድርገው እስኪያዩትና ፣ እስኪነቅፉት እስኪሰድቡትም ድረስ ሐሰትን እናስተምራቸዋለን፡፡ ዳግመኛም የማስተዋል አእምሮን በመንሳት የነቀፋና የስድብ መንፈስ ከልባቸውና ከአፋቸው እንዳይጠፋ እናደርጋለን አለው፡፡ ++አባ ጳውሊ፤ አንተ የተረገምክ እንዲህ በማድረግህ #ምን ትጠቀማለህ? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ እናንተን ከዘለዓለም ሕይወት ማጥፋትና በገሃነም እሳት ማቃጠል ነው እንጂ የምጠቀመው ጥቅም የለኝም አለው፡፡ +አባ ጳውሊ፤ በውኑ ገሃነም የሚባል ቦታ አለን? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ አዎ ገሃነመ እሳት አለ፡፡ በዚያ መጽናናት የሌለው ልቅሶ፥ ጥርስ ማፋጨት እንዲሁም የማያንቀላፋ ትል፥ ታላቅ ስቃይና የማይቋረጥ ልቅሶ ድቅድቅ ጨለማ አለ፡፡ ኑሯችን በዚያ ነው አለው፡፡ ++አባ ጳውሊ፤ አንተ ከክብርህ የተዋረድክ፤ በገሃነመ እሳት እንደምትቀጣ የምታውቅ ከሆነ ለምን ንስሐ አትገባም!? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ #ንስሐ እንዳልገባ #የሚጸጸት ልብ የለኝም አለው፡፡ +አባ ጳውሊ፤ እግዚአብሔር መሐሪና ይቅር ባይ ነውና ከለመንከው ይሰጥሃል!! አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ ለዚህ ሥራ ዕድል የለንም አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ ከእናንተ በዚህ በክፉ ሥራችሁ የበላይ አለቃ አለን? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ አዎን አለ፤ በጨለማ ሠራዊት ላይ ታላቁ አለቃ እኔ ነኝ፡፡ እኔ ሰይጣናትን ሁሉ ሰውን ለማሳት በየቦታው እልካቸዋለሁ፡፡ ከአጋንንት ጭፍራና ከወገኖቼ መካከል ከእኔ የሚከፋ የለም፡፡ ከእኛ መካከል ሰዎች ዝሙትንና ስርቆትን፥ ቂምና ስካርን ይህን የመሰለ ኃጢአት እንዲሠሩ የሚያደርጉ እጅግ የከፉ ጨካኝ አጋንንት አሉ አለው፡፡ #የሰይጣን ኀይል በምን እንደሚደክም፤ ሰው በሰራው ኀጢአት ተጠያቂው ራሱ እንደሆነ፤ ሰይጣን ሰዎችን ፈጣሪያቸውን እንዴት ባለ መንገድ እንደሚያስክዳቸው፤ አንድን ኀጢአት ያለፈን ሰው በሌላ ኀጢአት እንደሚፈትኑት፤ ለሰው በሚፈልገው ተመስለው በምትሐት እንደሚገለጹ … ክፍል ፮.… ይቀጥላል ነገ ይጠብቁን/ #በፌስቡክ_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ https://t.me/medihanaelem

‹‹ ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይህ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት በሚያዝያ ፲፰/፳፻፲፪ ዓ.ም
+1
‹‹ ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይህ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት በሚያዝያ ፲፰/፳፻፲፪ ዓ.ም በደ/ኃይል ቅዱስ ራጕኤል ወኤልያስ ቤ/ክ ጋብቻችህን የፈጸማችሁት የሰ/ት/ቤታችን አባላት፤ #ሳሙኤል_እሸቴ_ከሃገሬ_ብሩ ጋር የፈጸማችሁትን ጋብቻ፤ የይስሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ፥ ያጣምራችሁ፥ ያዋሕዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኋላ ይከተላችሁ፡፡ ✤ ‹‹ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንዲሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እንደዚሁ ጌታ ቤተ ክርስቲያንን እንደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡›› ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለፖሊካርፐስ በላከው መልእክቱ ✤ ከተጋባችሁ በኋላ ባልና ሚስት አንድ አካል ናችሁ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>> ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ዘርአያዕቆብ፡፡ /ከቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/