en
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Open in Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 373 subscribers, ranking 5 571 in the Religion & Spirituality category and 2 195 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 373 subscribers.

According to the latest data from 05 July, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 30 over the last 30 days and by -4 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 22.23%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 9.08% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 418 views. Within the first day, a publication typically gains 1 397 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 20.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 06 July, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

15 373
Subscribers
-424 hours
-197 days
+3030 days
Posts Archive
#ጥቅምት_3_የቤተ_ክርስቲያን_ማኅቶት ፥ #አፈ_በረከት_ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ፤#_ፅንሰቱ_ነው፡፡ #SHARE ፠ይህ አባት ከ40 በላይ መጻሕፍትን የደረሰና ብዙ መጻሕፍትን እያጻፈ ለመላው ገዳማት ያዳረሰ፤ ጸሓፊ፥ ቅዱስና ጻድቅ፥ ፈላስፋና ደራሲ፥ መናኝና ባሕታዊ፥ ሊቅና ተመራማሪ፥ ገጣሚና በለቅኔ፥ የመጻሕፍት ተርጓሚና የዘመን አቈጣጠር (የአቡሻህር) ሊቅና ተንታኝ፥ አርክቴክትና መሐንዲስ ነው፤ በዚህም ምክንያት በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል፤ ፠ዳግማዊ ቄርሎስ (ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ)፥ ፠ ዐምደ ሃይማኖት ፠ ዳግማይ ቅዱስ ያሬድ፤ ፠ የወርቃማ ዘመን ወርቃማ ደራሲ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን ማኅቶት፥ ፠ አፈ በረከት ፠ የከሃድያን ዘላፊ፥ የቅዱሳን ፀሐይ …….ተብሏል፡፡ እንዲሁም፤ + እንደ ቅዱስ ላሊበላ ቤተ መቅደሱን ራሱ ፈልፍሎ ያነፀ #የሕንፃ_ባለሙያ ነው። + ከጓደኛው ከአባ ጽጌ ድንግል ጋር ሁኖ የወለቃ ወንዝ ድልድይን የሠራ መሐንዲስ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ድልድዩን ሕዝቡ ይጠቀምበታል፡፡ + እንደ ቅዱስ አትናቴዎስ መናፍቃንን የረታ #ብርቱ_የቤተ_ክርስቲያን_ጠበቃ ነው። + እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በርካታ መጻሕፍትን የጻፈ (የደረሰ) #ደራሲ ነው፡፡ + እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን ዙሮ ያስተማረ #ሐዋርያ ነው፡፡ + እንደ ፍጹማን መነኰሳት በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስኖ በተጋድሎ ጸንቶ የኖረ #መናኝ_ጻድቅ ነው፡፡ + እንደ ቅዱስ ያሬድ በሰማያዊ ዜማ አምላኩን ያመሰገነ #የዜማ_ሊቅ #የዜማ_ደራሲ ነው። + እንደ ዕዝራ ሱቱኤል ሰማያዊ መጠጥ ጠጥቶ ምስጢራት የተገለጹለት #ድንቅ_ተመራማሪ #የጥበብ_አባት ነው:: (ለምሳሌ፤ በሰዓታት ድርሰቱ ውስጥ ዑደተ ማይን፣ በሌሎች ድርሰቶቹም ስለ አእባንና እጽዋት ቀድሞ ነግሮናል፣ እንዲሁም የውኃ ማቆር ቴክኖሎጂን በዘመኑ ተግባራዊ አድርጓል። + እንደ ሰማዕታት ከነገሥታቱ ስለ ሃይማኖት ብዙ ጸዋትወ መከራ የተቀበለ #ሰማዕት ነው፡፡ + አቡነ አረጋዊ ደብረ ዳሞን፤ አቡነ ኢየሱስ ሞ ሐይቅ እስጢፋኖስን፤ አቡነ ተከለ ሃይማኖት ደብረ ሊባኖስን፤ አቡነ ሳሙኤል ዋልድባን፤ አቡነ ዐምደ ሥላሴ ማኅበረ ሥላሴ ገዳምን እንደመሠረቱና የተመሠረተውንም እንዳስፋፉ፤ እርሱም ደብረ ባሕርይ ጋሥጫን የመሠረተ ቅዱስ ነው፡፡ + በሰዓታት ድርሰቱ ቤተክርስቲያን አምላኳን ፳፬ ሰዓት ያለማቋረጥ እንድታመሰግን ያስቻለ ምድራዊ #መልአክ ነው፡፡ + "አኀዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ" እስከሚል ድረስ ጸጋ የበዛለት አባት ነውና ስንቱን እንናገረው? አይቻለንምና!!!፡፡ (በፎቶ ላይ የምታዩት ገዳም፤ በዓለም ብቸኛው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ገዳም የኾነው ደብረ ባሕርይ ነው፡፡ የቦታው አቀማመጥ እጅግ በጣም ማራኪና እንደ ደብረ ዳሞ ሲሆን የሚወጣው በመሰላል ነው፡፡)፤ ገዳሙ የሚገኘው በደቡብ ወሎ በቦረና አውራጃ ነው፡፡ (አስተጋባኢ /ይህንን ጽሑፍ ከአባቶች በመጠየቅ ፥ መጻሕፍትን በማንበብ ፥ ከታላቁ ገዳም ደብረ ባሕርይ ጋሥጫ ድረስ ሂዶ ያዘጋጀው የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት ዝግጅት ክፍል ነው/፡፡) አምላከ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሀበነ በረከተ ወረድኤተ፡፡

ወረብ፤_ወበእንተዝ_ማርያም_ወረብ_ዘደብረ_ሰላም_የቤቱ_ቀለም_፣_አጋፋሪ_ይሁኔ_ፈቃዱ.mp32.89 MB

ወረብ፤_ሠርፀ_መንግሥት፣_ከቅኝት_እስከ_ቸብቸቦ፤_ዘደብረ_ሰላም_የቤቱ_ቀለም_፣_መሪጌታ_ሙሉጌታ_ተክለያሬድ.m4a8.91 KB

ወረብ፤_ሚ_ቡርክት፣_ቅኝት_፤_ዘደብረ_ሰላም_የቤቱ_ቀለም_፣_አጋፋሪ_ይሁኔ_ፈቃዱ.mp32.17 MB

#የማኀሌተ_ጽጌ የሦስተኛ ዙር አመት፤ አንደኛ ሳምነት #ወረቦች ወረብ፤ #_ሚ_ቡርክት ቅኝት ፣ ወረብ ዘደብረ_ሰላም ፤ የቤቱ_በቀለም ፣_በአጋፋሪ_ይሁኔ_ፈቃዱ ወረብ፤ #_ወበእንተዝ_ማርያም፣ ወረብ_ ዘደብረ_ሰላም ፤ የቤቱ_ቀለም ፣_በአጋፋሪ_ይሁኔ_ፈቃዱ ወረብ፤ #ሠርፀ_መንግሥት ፤ወረብ ዘደብረ ሰላም ፤ የቤቱ_በቀለም ፤በመሪጌታ ሙሉጌታ ተክለያሬድ

ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት) (፫ኛ ዙር ዓመት፤፩ኛ ሳምንት፥ዘጥቅምት ፩) በዓለ ልደታ ለማርያም ወቅድስት አንስጣስያ ወቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት፡፡ #Share እና #Like ያድርጉ

፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem ፠ በዩቲዩብ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ ፍኖተ ሕይወት የቀጨኔ ደ/ሰ መድኃኔዓለም እና ደ/ት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት

ወረብ፤_ወበእንተዝ_ማርያም_ወረብ_ዘደብረ_ሰላም_የቤቱ_ቀለም_፣_አጋፋሪ_ይሁኔ_ፈቃዱ.mp32.89 MB

ወረብ፤_ሚ_ቡርክት፣_ቅኝት_፤_ዘደብረ_ሰላም_የቤቱ_ቀለም_፣_አጋፋሪ_ይሁኔ_ፈቃዱ.mp32.17 MB

#የማኀሌተ_ጽጌ የሦስተኛ ዙር የመጀመራያ ዓመት #ወረቦች ወረብ፤ #_ሚ_ቡርክት ቅኝት ፣ ወረብ ዘደብረ_ሰላም ፤ የቤቱ_ቀለም ፣_በአጋፋሪ_ይሁኔ_ፈቃዱ ወረብ፤ #_ወበእንተዝ_ማርያም፣ ወረብ_ ዘደብረ_ሰላም ፤ የቤቱ_ቀለም ፣_በአጋፋሪ_ይሁኔ_ፈቃዱ

እንኳን ለ #ቅድስት_አርሴማ ዓመታዊ ክብረ በዓል (በዓለ ዕረፈት) አደረሰን፥ አደረሳችሁ፡፡ share በዚህች በመስከረም 29 ቀን አርሴማ ቅድስት ወሰማዕት እና የእርሷ ማኅበርተኞች ድል አድራጊዎች ፤27 ሰማዕታት በሰማዕትነት ያረፉባት ዕለት ነች፡፡ እግዚአብሔር ከእነዚህ ቅዱሳን ሰማዕታት ረድኤት በረከታቸውን ይክፈለን፡፡ እነዚህም ቅዱሳን፤ 1ኛ. #አርሴማ፤ #ቅድስት_ወሰማዕት_ኃያል_ተጋዳሊት_ 2ኛ. ኢያሚኖስ፤ ጸሎትን የሚያሳርግ ካህን 3ኛ. አፍጢኖስ፤ ከብዙዎች የተመረጠ 4ኛ. በርቲኖስ፤ ጻድቅና ቸር 5ኛ. ጢሞና፤ በመላላክ ሥራ አገልጋይ የኾነ 6ኛ. ጢሞዓና፤ ተአጋሽና ጸዋሚ 7ኛ. ዘኬዎስ፤ ከከበሩ የከበረ 8ኛ. እስጢፋኑ፤ ተጋዳይና የበደሉትን ይቅር ባይ 9ኛ. አርሞና፤ ከጎልማሶች ይልቅ ደም ግባቱና መልኩ ያማረ 10ኛ. ኪርያኮስ፤ ሥጋውን ያላረከሰ ንጹሕ 11ኛ. አንጥያኮስ፤ ቡሩክ የኾነ የአቡሪ ልጅ 12ኛ. ያዕቆብ፤ የእግዚአብሔር ታማኝ የኾነ 13ኛ. ቡራኬሌስ፤ በሰው ዘንድ ተወዳጅ የኾነ 14ኛ. አስቂርያቆስ፤ ክርስቶስን የሚወደው 15ኛ. አስኪርያኖስ፤ ባለሟል የኾነና ግርማው የሚያስፈራ 16ኛ. ሚርያኖስ፤ ፊቱና መልኩ ደስተኛ የኾነ 17ኛ. ትትግርጦስ፤ ወደ ንስሐ የተመለሰ 18ኛ. ያስቲኖስ፤ የሚፈርድና የሚበይን 19ኛ. ጥልያኖስ፤ ያላመኑ ሰዎችን የሚገስጽ 20ኛ. ዑልያኖስ፤ የዚህ ዓለም ጥበብ መምህር የኾነ 21ኛ. ጴርቅላስ፤ በስም አጠራርና በሽምግልና መልካም የኾነ 22ኛ. ኬብያኖስ፤ ተጋዳይ የኾነ 23ኛ. ጴጥሮስ፤ የጠራ የባሕርይ ዕንቊ 24ኛ. ጰኵንዮስ፤ የሮምያ ሹም 25ኛ. ሐናንያ፤ የዋህና ሽንገላ የሌለው 26ኛ. ሐሊባኖስ፤ ጾምና ጸሎትን የሚወድ 27ኛ. ኤስያኖስ፤ በመንፈስ ቅዱስ ጎልማሳ የኾነ 28ኛ. ኤልያብ፤ በረኛና የሰማዕት መጀመሪያ፡፡ ሰላም ለፀዐተ ነፍስኪ በጊዜ ኃለፈ ሰይፍ፤ መንገለ ክሣድኪ ድኑን ለአምሳለ መሥዋዕት ውኩፍ፡፡ እስእለኪ አርሴማ በከናፍር ወአፍ፤ ረድኤትኪ ትሩፍ በላዕሌየ ያንጸፈጽፍ፤ እስመ አርአየኒ ዘንተ ሞትኪ ትሩፍ፡፡ ሰላም ለዘአዕረፉ ምስሌኪ ፳ወ፯ቱ ሰማዕታት፤ ረድኤቶሙ ትረድ ላዕሌየ ዘምስለ ብዙኅ ምሕረት፡፡ ወኀበ ሀለወ ስሞሙ ምስለ ስምኪ ቅድስት፤ ዓዲ ኢይቅረብ አርሴማ ሕማመ ብድብድ ወሞት፤ በኵሉ አዝማን ወበኵሉ ዓመታት፡፡ /የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/ https://t.me/medihanaelem fb / @FinoteHiwotSundaySchool #like #share