ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Открыть в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 15 948 подписчиков, занимая 5 316 место в категории Религия и духовность и 2 234 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 15 948 подписчиков.

Согласно последним данным от 21 октября, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 408, а за последние 24 часа — 1, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 25.79%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 10.92% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 4 113 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 1 742 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 29.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 22 октября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Религия и духовность.

15 948
Подписчики
+124 часа
+1627 дней
+40830 дней
Архив постов
የ2013 ዓ.ም የታኀሣሥ ወር ቅዱስ ገብርኤል በዓል ማስታወሻዎች ፤ከፍቶ ማሕደራችን፡የ2013 ዓ.ም የታኀሣሥ ወር ቅዱስ ገብርኤል በዓል ማስታወሻዎች ፤ከፍቶ ማሕደራችን፡
የ2013 ዓ.ም የታኀሣሥ ወር ቅዱስ ገብርኤል በዓል ማስታወሻዎች ፤ከፍቶ ማሕደራችን፡የ2013 ዓ.ም የታኀሣሥ ወር ቅዱስ ገብርኤል በዓል ማስታወሻዎች ፤ከፍቶ ማሕደራችን፡

የ2013 ዓ.ም የታኀሣሥ ወር ቅዱስ ገብርኤል በዓል ማስታወሻዎች ፤ከፍቶ ማሕደራችን፡
+1
የ2013 ዓ.ም የታኀሣሥ ወር ቅዱስ ገብርኤል በዓል ማስታወሻዎች ፤ከፍቶ ማሕደራችን፡

የ2013 ዓ.ም የታኀሣሥ ወር ቅዱስ ገብርኤል በዓል ማስታወሻዎች ፤ከፍቶ ማሕደራችን፡፡
+2
የ2013 ዓ.ም የታኀሣሥ ወር ቅዱስ ገብርኤል በዓል ማስታወሻዎች ፤ከፍቶ ማሕደራችን፡፡

እንኳን አደረሳቹህ ✤✣✤ #በዓለ_ልደቱ_ለሐዲስ_ሐዋርያ_ፀሐይ_ማር_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት #ታኅሣሥ_24_1196ዓም_በሰሜን_ሸዋ_ቡልጋ_ጽላልሽ_እቲሣ_ተወልደው_በአጠገቡ_በምትገኛወ_ደብረ_አጋዕዚት_ክርስትና_ተነሡ፡፡ #አባታቸው ቅዱስ ጸጋ ዘዓብና እናታቸው ቅድስት እግዚእ ኀረያ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲያስተምሯቸው በአካባቢያቸው ደግሞ በዘመኑ የነበሩ ልጆች ይማሩ የነበረውን ፈረስ መጋለብን፣ ቀስት መወርወርን፣ እርሻንና አደንን አስተምረዋቸዋል፡፡ #በ7ት ዓመታቸው ከግብፃዊው ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ ዲቁናን ከተቀበሉ በኋላ እግዚአብሔር በክህነት ሕዝቡን እንዲያገለግሉ መረጣቸው፡፡ ከዮዲት ጉዲት በኋላ ሃገራችን ሰሜኑና ደቡቡ ተቆራርጧል፤ የሐሳብን ልዕልና የሚያመጣው የመንፈስ ልዕልና ተዳክሟል፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያን የሚዋጅ ሐዲስ ሐዋርያ ያስፈልግ ነበርና አምላካችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ጠራ፡፡ #አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቅስናን ከአቡነ ቄርሎስ ተቀብለው በጽላልሽ አካባቢ በክህነት ከአባታቸው ጋር አገልግለዋል፡፡ አባታቸው ሲያርፉ በወንጌሉ ማንም ሊከተለኝ የሚወድድ ቢኖር ያለውን ሁሉ ትቶ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ ያለውን በመከተል ሀብታቸውን ለድኾች መጽውተው በሸዋና በዳሞት በስብከተ ወንጌል አገለገሉ፡፡ ከዚያም፤ #በመጀመርያ ደቡብ ወሎ ቦረና ላይ ገዳማቸውን ደብረ ጎል ገድመው ወደሚገኙት ታላቁና ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን ወደኾኑት ጻድቅ አባት አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ገብተው ዐሥር ሁለት ዓመታት በትምህርትና በሥራ (በአርድእትነት) አሳልፈዋል፡፡ በዚያም ዋሻ ፈልፍለው አስደናቂ ሕንፃ ሠርተው ነበር፡፡ #በ1216 ዓ.ም. አካባቢ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገሳም ገብተዋል፤ በዚሁ ገዳምም ከመመንኰሳቸው በፊት ሰባት ዓመት ከመነኰሱም በኋላ ሦስት ዓመት በድምሩ ለ10 ዓመታት በትምህርት፣ በእደ ጥበብ ሥራ፣ በአገልግሎትና ሥርዐተ ምንኵስናን እያጠኑ ቆይተዋል፡፡ #ከሐይቅ ወጥተው በዘመኑ በሥርዐተ ምንኵስናና በትምህርት ብሎም በጥበበ እድ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ወደ ነበረው ወደ ደብረ ዳሞ በመሄድ በየገዳሙ አበምኔት ከሆኑት ከአቡነ ዮሐኒ ዘንድ መንፈሳዊ ትምህርት፣ ሥርዐተ ምንኵስናና ጥበበ እድ ሲማሩ ለ12 ዓመታት ቆዩ፡፡ ያነጹት ፍልፍል ድንጋይ ዋሻ፣ መጻሕፍት ሲጽፉ ቀለማቸውን ያስቀምጡባቸው የነበሩትን ሽንቁሮች ዛሬም በደብረ ዳሞ ማየት ይቻላል፡፡ #በደብረ ዳሞ የነበራቸውን ቆይታ ጨርሰው በገመድ ሲወርዱ ሰይጣን በቅንዐት መጥቶ ገመዱን በጠሰባቸው እግዚአብሔር አምላክ በዚህ ወቅት የሚበሩበትን እንደ መላእክት ክንፍ ሰጣቸው፡፡ #ለአምስት ዓመታት #አኵስምን_ዋልድባን እንዲሁም ሎሎች የትግራይ ገዳማትን እየተዘዋወሩ ሲመለከቱ ቆዩ #ከሸዋ በወጡ በሃያ ሁለት ዓመት (እድሜያቸው ሃምሳ ሁለት ሲሆን) ለበለጠው ክብር እና ርእይ በግብጽ በኩል ወደ ኢየሩሳሌም ተሻገሩ፡፡ #ከኢየሩሳሌም ሲመለሱ በሐይቅ በኩል አድርገው ደብረ ጎልን ተሳልመው በሚዳ እና በመርሐ ቤቴ በኩል ወደ ሸዋ በመምጣት ከዮዲት ዘመን በኋላ በመንፈሳዊ ሕይወት የተጎዳውን ሸዋን እና ደቡብ ኢትዮጵያን በመዘዋወር ለዐሥር ዓመታት ያህል አስተምረዋል፡፡ #አቡነ ተክለ ሃይማኖት ተግተው በማስተማራቸው የተኛው ሁሉ ነቃ፣ የደከመው በረታ፣ የጠፋውም ተገኘ፡፡ ሐዋርያትን ለማፍራት እንዲችሉ አንድ ገዳም ለመመሥረትና ደቀ መዛሙርትን ለማስተማር አሰቡ፡፡ እናም ወደ ደብረ አስቦ ገዳም ገቡ፡፡ ቦታውን አስተካክለው እና ከደብረ ዳሞ እና ከሐይቅ የተከተሏቸውን ጥቂት ደቀ መዛሙርት ይዘው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ልክ እንደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ሁሉ ሦስቱን ነገሮች ያካተተ አገልግሎት ጀመሩ፡፡ ምንኵስና፣ ትምህርትና ሥራ፡፡ መነኰሳቱ መንፈሳዊ ትምህርት ይማራሉ፤ በሕገ ገዳም ይመራሉ፤ ለራሳቸው እና ለአካባቢው ሕዝብ ርዳታ የሚሆን እርሻ ያርሳሉ፡፡ #ደቀ መዛሙርትን አፍርተው፣ ገዳማቸውን አደራጅተው፣ ስብከተ ወንጌልንም አስፋፍተው ካደላደሉ በኋላ በሕይወታቸው የመጨረሻ ዓመታት ወደ ደብረ አስቦ ዋሻ ገብተው በአንድ እግራቸው በጾም እና በጸሎት ተወሰኑ፡፡ #አገልግሎታቸውን ፈጽመው ነሐሴ 24 ቀን 1297 ዓ.ም. በ99 ዓመታቸው ዐረፉ፡፡ ✤✤ #እቲሣ_ገዳም_ #በቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃና አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የተመሠረተ፤ ሲመሠረትም በታቦተ ኢየሱስና አርባዕቱ እንስሳ ነው፤ #ሊቀ ካህናት አበይድላ ከአኵስም 300 ታቦታትና 300ካህናት ይዞ መጥቶ በጽላልሽ የተቀመጠባት ናት፤ #ፀሐይ አቡነ ተክለሃይማኖት የተወለዱባት (የተወለዱባት ጠፍጣፋ ደንጊያ አሁንም በቦታው አለች)፣ #አባታቸውና ጸጋ ዘአብና እናታቸው እግዚእኀረያ የተወለዱበት፤ ኋላም ክብሩ አጽማቸው ያረፈበት ነው፡፡ #ቅዱስ ያሬድ 3 ዓመት ጸልዮባታል፤ #ቅዱስ ላሊበላ 7 ዓመት ጸልዮባታል፤ #ተሰዓቱ ቅዱሳን 20 ዓመት የጸለዩበት፤ #ሐርቤ በሚባለው ቦታ ላይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ 7 ዓመት ጸልየውበታል፤ #ታቦተ ጽዮን 12 ዓመት (ከ9ሺህ ሕዝብ) ጋር መጥታ ኖራበታለች፤ #በአምሳለ ሲዖል የተሠራ አስደናቂ የጨለማ ዋሻ ያለበት ነው፤ #ብዙ የታሪክ ቅርስ ያለበት ነው፤ #በቅዱስ ሚካኤልና ጸጋ ዘአብ ቤተ ክርቲያን ውስጥ ካየን በኋላ፤ እዚሁ ቦታ በሚገኘው ፈዋሽ ጠበል ተጠምቀንና ጠጥተን ጕዟችንን ወደ #ቦታው_ከአአ_በቅርብ_ርቀት_በደብረ_ብርሃን_መንገድ_አሌልቱ_ከተማ_ላይ_በመታጠፍ_ይገኛል፡፡ #ሥርዐተ_ማኅሌቱን_እንደየደብራችሁ ይትበሃል እንድትጠቀሙበት በማሰብ ሁሉንም (በላይ ቤትና በታች ቤት) (#ዘአባጃሌ_ተክለ_ሃይማኖትና_ዘአደባባይ_ተክለሃይማኖት) አዘጋጅተነዋል፡፡ ጸሎትና በረከታቸው፤ ረድኤትና ምልጃቸው በመላው ሕዝበ ክርስቲያንና በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ሁሉ አድሮ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ /የቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለምና ደ.ት ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሰሌዳ መጽሔት / Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

ዝማሜ ፤ «ገብርኤል መልአክ» ፤ በሰንበት ት/ቤት መዘምራን «ታኀሣሥ 19 ፤ 2013 ዓ.ም የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓል» በyouTube ገጻችን ይመልከቱ፤ https://youtu.be/q-sIXLDktHM

ዝማሜ ፤ «ገብርኤል መልአክ» ፤ በሰንበት ት/ቤት መዘምራን «ታኀሣሥ 19 ፤ 2013 ዓ.ም የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓል» በyouTube ገጻችን ይመልከቱ፤ https://youtu.be/_amtQEm79Pk

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓል ወረብ ፤( የታኀሣሥ 19 | 2013 ዓ.ም) እምዕቶነ እሳት ፤ በደብረሰላም ሊቃውንት ፤ በYouTube ገጻችን ይመልከቱ(1080p) https://youtu.be/p3H4kxjbnM8

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓል ወረብ ፤( የታኀሣሥ 19 | 2013 ዓ.ም) እምዕቶነ እሳት ፤ በደብረሰላም ሊቃውንት ፤ በYouTube ገጻችን ይመልከቱ (1080p) https://youtu.be/p3H4kxjbnM8

፨ #ይኩነኒ_በከመ_ትቤለኒ_ (#እንደ_ቃልህ_ይሁንልኝ_)፤ #ታኅሣሥ_22_ብሥራተ_ገብርኤል … #በስድስተኛውም_ወር_መልአኩ_ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል #ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ፡፡ …… መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት። መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ያጸናሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና። ማርያምም እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች፡፡ መልአኩም ከእርሷ ሄደ… /የሉቃስ ወንጌል 1፥26-38/ #ይህቺም_ዕለት_የበዓላት_ሁሉ_በኵር_ናት፤ በእርሷም የዓለም ድኅነት ተጀምሯልና ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስም ከቸር አባቱና ይቅር ባይ ከሆነው ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክብር ምስጋና ለዘላለሙ ይሁን አሜን፡፡ /ስንክሳር ዘታኅሣሥ 22/ ——- #በመዲና ከተማችን በአዲስ አበባ ታኅሣሥ_22_ብሥራት_የሚከበርባቸው፤ ፠ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል (ብሥራተ ገብርኤል) ፠ መንበረ ፓትርያርክ ቅዱስ እንጦንስ (ኋላ ቅድስት ማርያም እየተባለ በመጠራት ላይ ያለ) ሲሆን በታላቁ ደብራችን በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ካልዕ መልክአ ቅዱስ ገብርኤልን በማኅሌት በመቆም ይከበራል፡፡ —————— የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

#ይኩነኒ_በከመ_ትቤለኒ_ (#እንደ_ቃልህ_ይሁንልኝ_)፤ #ታኅሣሥ_22_ብሥራት_ … በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው
#ይኩነኒ_በከመ_ትቤለኒ_ (#እንደ_ቃልህ_ይሁንልኝ_)፤ #ታኅሣሥ_22_ብሥራት_ … በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ፡፡ …… መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት። መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ያጸናሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና። ማርያምም። እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች፡፡ መልአኩም ከእርሷ ሄደ… /የሉቃስ ወንጌል 1፥26-38/ ይህቺም እለት የበዐላት ሁሉ በኵር ናት፤ በእርሷም የዓለም ድኅነት ተጀምሯልና ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስም ከቸር አባቱና ይቅር ባይ ከሆነው ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክብር ምስጋና ለዘላለሙ ይሁን አሜን፡፡ /ስንክሳር ዘታኅሣሥ 22/ በመዲና ከተማችን በአዲስ አበባ ታኅሣሥ_22_ብሥራት_የሚከበርባቸው፤ ፠ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል (ብሥራተ ገብርኤል) ፠ መንበረ ፓትርያርክ ቅዱስ እንጦንስ (ኋላ ቅድስት ማርያም እየተባለ በመጠራት ላይ ያለ) ሲሆን በታላቁ ደብራችን በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ካልዕ መልክአ ቅዱስ ገብርኤልን በማኅሌት በመቆም ይከበራል፡፡

የ2012 ዓ.ም እና የቀደሙ ዓመታት የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ድባብ በደብራችን ፤ ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን::