Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 16 129 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 230,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 226 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 16 129 名订阅者。
根据 31 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 520,过去 24 小时变化为 7,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 22.41%。内容发布后 24 小时内通常能获得 10.30% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 597 次浏览,首日通常累积 1 653 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 28。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 01 十一月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
16 129
订阅者
+724 小时
+197 天
+52030 天
帖子存档
‹‹ ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይህ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት
በወርኃ ጥር ፲፰ና ፲፱/፳፻፲፩ ዓ.ም. ጋብቻችሁን ለፈጸማችሁ የሰ/ት/ቤታችን አባላት፤
#ባዩልኝ_ጌታዬነው_ከሕይወት_አየነው ጋር
#ማኅሌት_የኋላው_ከፍጹም ጋር የፈጸማችሁትን ጋብቻ፤
የይስሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ፥ ያጣምራችሁ፥ ያዋሕዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኋላ ይከተላችሁ፡፡
✤ ‹‹ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንዲሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እንደዚሁ ጌታ ቤተ ክርስቲያንን እንደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡›› ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለፖሊካርፐስ በላከው መልእክቱ
✤ ከተጋባችሁ በኋላ ባልና ሚስት አንድ አካል ናችሁ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>> ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ዘርአያዕቆብ፡፡
/ከቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/
ዛሬ ጥር 22 ቀን፤
#ርዕሰ_መነኰሳት_ቅዱስ_አባ_እንጦንስ_ልደቱና_ዕረፍቱ ነው፡፡
በፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው አብያተ ክርስቲያናት፤
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት ብቸኞቹ 2ት የቅዱስ እንጦንስ ገዳማት፡፡
1ኛ) #ጎንደር_ደብረ_እንጦንስ፤ በጻድቁ አፄ ዮሐንስ /ከ1659-1674/ የተመሠረተ፥ ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱና ዋነኛው፡፡ ጎንደርከ300 ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ መዲና ከተማ ሆና በቆየችባቸው ዘመናት የአቡን (የጳጳስ) ቤት (መንበረ ጵጵስና) ሆኖ ያገለገለ፡፡
2ኛ) #እንጦንስ_ኢየሱስ፤ በጣና ላይ ከሚገኙ የደሴት ገዳማት አንዱ፡፡
እንዲሁም
3ኛ) #ግብጽ_እንጦንስ_ገዳም ናቸው
ዛሬ ጥር 22 ቀን፤
#የብርሃን_መልአክ_ከሣቴ_ምሥጢር_የሆነው_ቅዱስ_ዑር/ራ/ኤል_በዓለ_ሢመቱ ነው፤
በፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው አብያተ ክርስቲያናት፤
1ኛ) በአዲስ አበባ የሚገኘውና ጥንታዊው ደብር #ደብረ_ጽጌ_ቅዱስ_ዑርኤል
2ኛ) #ግሸን_ቅዱስ_ዑርኤል
3ኛ) #ጎንደር_ደብረ_ኀይል_ቅዱስ_ዑርኤል_ወበዓታ፤ /ዛሬ ታቦተ ሕጉ ወደ ጠበል በመውረድ ይከብራል/
እንዲሁም የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል መራሔ ብርሃናት ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ናቸው፡፡
#ጥር21_አስተርእዮ_ማርያም_በዓለ_ዕረፍታ_ለማርያም_ለሶልያና #እመቤታችን_በ64_ዓመቷ_ጥር_21_በ49ዓም_ያረፈችበት_ዕለት_መታሰቢያ_ክብረ_በዓል_ነው፡፡
#ተናገራ_ዕዝራ_ተናገራ_ዳዊት_ዘመራ፤
#ዕዝራ_በመሰንቆ_ዳዊት_በበገና_እያጫወቷት፤
#ሳታውቀው_አለፈች_ያንን_መራራ_ሞት፡፡
ጌታችን ለናታችን ለቅድስት ማርያም ብዙ ቃልኪዳንን ከገባላት በኋላ፤ ቅድስት ነፍሷን ከክብርት ሥጋዋ ለይቶ በቃለ አቅርንት፥ በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት ደመና ጠቅሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ በአጎበር አድርገው እናትና አባቷ ወደተቀበሩበት ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲወስዷት አይሁድ አይተው፤ ልጇ ተነሳ፥ አረገ እያሉ ሲያውኩን ኖሩ አሁን ደግሞ እሷ ተነሳች፥ አረገች እያለ ሉያውኩን አይደለምን? ንዑ ናዓውያ ሥጋሃ ለማርያም /ኑ ሥጋዋን እናቃጥልባቸው/ ብለው ተነሱ፤ ለዚሁም ከመካከላቸውም ታውፊኒያ የተባለውን የጎበዝ አለቃ መረጡ፤ እርሱም የአልጋዋን ሸንኮር ሊያቃጥል ሲይዝ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማፀናት እራሷን ዘምበል አድርጋ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደነበረው አድርግለት ብላ አዘዘችው፤ እርሱም እጁን አድኖለታል፡፡ ከዚህ በኋላ ጌታችን ከመካከላቸው ነጥቆ ከገነት ከዕፀ ሕይወት ስር አኑሯታል፡፡ ….. ሐዋርያት የቀበሯት ግን ከ6 ወር በኋላ በነሐሴ 14 ነው /ሌላውን ታሪክ በፍልሰታ ጾም ላይ ያንብቡ፤ ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር እንዲሉ፡፡››/
ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና(ለማርያም)
ወረደ ወልድ ዲበ እምዲበ ልዕልና ወረደ፡፡
**#ሶልያና_የእመቤታችን_የማርያም_ሌላ_ስሟ_ነው፡፡
*የእመቤታችንን ዕረፍት ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ‹‹ሞትሰ ለመዊት ይደሉ፥ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኵሉ፡፡ /ሞት ለሚሞት ሰው ሁለ የተገባ ነው፥ የማርያም ሞት ግን ሁለን ያስደንቃል፡፡›› በማለት አደንቆ ጽፏል፡፡
***እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠቀሙበት ዘንድ የላይ ቤት (የግምጃ ቤት ማርያም) አብነትና የታች ቤት(የበዓታ) አብንትን ሁለቱንም አዘጋጅተንላችኋል፡፡ መልካም ክብረ በዓል፡፡
**ክብረ በዓሉ በሃገራችንና በዓለማችን ክፍሎች ባሉ የእመቤታችን አብያተ ክርስቲያናት የሚከብሩ ቢሆንም ግን፤ በልዩ ሁኔታ እንደ ጎንደር አዘዞ ሎዛ ማርያም ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ግን እንደ ጥምቀት በዓል፤ ከዋይዜማው ጀምሮ ወደ ጥምቀተ ተወርዶ በማደር ክብረ በዓሉ በልዩ ሁኔታ መከበሩን ልብ ይሏል፡፡ (የሎዛ ማርያምና የጥር 21 በዓል አከባበሯን ፎቶ ያላችሁ ላኩልን፡፡)
ጥር 18 ዝርወተ አጽሙ ለቅዱስ ጊዮርጊስ በተለያዩ የሃገራችንና የዓለማችን ክፍሎች ተከብሮ ውሏል፤ በተለይ ግን በጎንደር ከተማ የሚገኘው ርዕሰ አድባራት አበራ ጊዮርጊስ እንደ ጥምቀት በዓል ወደ ባሕረ ጥምቀት በዋይዜማው ወጥቶ አድሮ ነው የሚመለሰው፤ እኛ ለዛሬ በደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኘው የደብረ ጽባሕ ቅዱስ ጊዮርጊስ የገበያ ቦታውን ባርኮ ሲመለስ የሚያሳየውን በፎቶ አቅርበንላችኋል /በፎቶ ላይየምታይዋቸው ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ታላቁ አባት ናቸው/ ፡፡ የጎንደር አበራ ጊዮርጊስ ፎቶ ያላችሁ ላኩልን፡፡ /በነገራችን ላይ በጎንደር በጥር ወር የሚከበሩ በዓላት ወደ ጥምቀተ ባሕር በመውጣት የሚከበሩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ጥር 18 አበራ ጊዮርጊስ፤ ጥር 21 ሎዛ ማርያም፣ ጥር 22 ቅዱስ ዑራኤል (በዓታ ያለው)፤ ጥር 25 ቅዱስ መርቆሬዎስ በተለይ በገጠሩ አካባቢ፡፡
እርሱ እንደ ንብ አውራ ፈረሱ እንደ አሞራ፤
ጊዮርጊስ፥ ጊዮርጊስ፥ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያን አደራ፡፡
ሰአል ለነ ጊዮርጊስ፤
ሰማዕተ ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡
ዘሐረፀከ ዱድያኖስ፤
ወወገረከ ደብረ ይድራስ፤
ዘዘረወከ በነፋስ፡፡
5.18 ሥርዐተ ማኅሌት ዘጥር ፲፰ በዓለ ስባረ ዓፅሙ ለቅዱስ ጊዮርጊስ፡፡
አዲስ ቤተ ክርስቲያን ሲሰራ (ቅዳሴ ቤት ሲከበር) ወይም
ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ሲመረቅ የሚባለውን #ሥርዐተ_ማኅሌት እነሆ አቅርበንላችኋል፡፡
(ቤተ ክርስቲያኑ የቅዱስ ገብርኤል ከሆነ የሚቆመው ማኅሌት ከሌሎቹ ሁሉ ስለሚለይ የማኅሌቱን ጽሑፍ ያለ ሐረግ አዘጋጅተነዋል፡፡)
#የሚመረቁ_አብያተ_ክርስቲያናትን_እንጠቁማችሁ #እናንተም_ጨምሩባቸው፤
#አዲስ_አበባ_ደብረ_በረከት_ቅዱስ_ገብርኤል፤ ካራቆሬ፤ አየር ጤና አጠገብ፤ ጅማ በር (ጥር 18 ስባረ ዓጽሙ ለጊዮርጊስ፤ ጥር 19 ቅዳሴ ቤቱ ለቅዱስ ገብርኤል)
#መጠቆሚያ_ማርያም፤ ጊንጪ፤ በ1942ዓ.ም. የተመሠረተች፤ /ጥር 21 ይመረቃል/፤ #ሰንበት_ትምህርት_ቤታችን_ወደዚህች_ቤተ_ክርስቲያን_ለመሄድ_የምትፈልጉ_በምረቃዋ_ዋይዜማ_ጥር_20_ጀምሮ_ጉዞ_አዘጋጅቷል_/
#ሻምቡ_ከምቦልቻ_ማርያም፤ ሆሮ ጉድሩ፥ ወለጋ፤ /ጥር 21 ይመረቃል/
#ሻምቡ_ቃዎ_ጊዮርጊስ፤ ሆሮ ጉድሩ፥ ወለጋ፤ /ሚያዝያ 21 ይመረቃል/
#ተጎራ_ማርያም፥ መርሐ ቤቴ፥ ሰሜን ሸዋ /ጥር 21 ይመረቃል/
/የቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ. ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት/
በባሌ ሀገረ ስብከት ሮቤ ከተማ የሚገኘው የመ/መ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ረቡዕ ጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ላይ ለጊዜው ባልታወቀ መንስኤ መቃጠሉን መ/ር ያሬድ ገ/ማርያም የወረዳው ቤተ ክህነት ጸሐፊ ገለጹ፡፡ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ቃለ ምዕዳን በሰጡበት ወቅት "ልጆቼ ሁሉም ፈቃደ እገግዚአብሔር ነው፤ ቃጠሎው ከምን እንደሆነ እግዚአብሔር ይመርምር" ብለዋል፡፡ ችግሩን ለመፍታት ክርስቲያንና ቀናነት ያላቸው ሙስሊም በአንድነት ተባብረዋል፡፡
#ጸልዩ_በእንተ_ሰላመ_ቤተ_ክርስቲያን_አሐቲ_ቅድስት_ጕባኤ_እንተ_ሐዋርያት_ርትዕት_በኀበ_እግዚአብሔር፡፡ (ሐዋርያት በሰበሰቧት በእግዚአብሔር ዘንድ ሰለቀናች፤ ክብርት ስለምትኾን አንዲት ቤተ ክርስቲያን ጸልዩ፡፡)
#ጸልዩ_በእንተ_ሰላም_ፍጽምት_ወፍቅር_ተአምኁ_በበይናቲክሙ_በአምኃ_ቅድሳት፡፡ (ፍጽምት ስለምትኾን ሰላምና ፍቅር ጸልዩ፤ እርስ በእርሳችሁ በተለየች ሰላምታ እጅ ተነሳሱ፡፡)
#አድኅነኒ_ወባልሐኒ_እምእዴሆሙ_ለደቂቀ_ነኪር_እለ_ከንቶ_ነበበ_አፉሆሙ_ወየማኖሙኒ_የማነ_ዐመፃ፡፡ (አድነኝ አፋቸውም ምናምን ከሚናገር ቀኛቸውም የሐሰት ቀኝ ከኾነ፤ ከባዕድ ልጆች እጅ አስጥለኝ፡፡) /#መዝ.፻፵፫፥፯/
✤#በሐኪ_በሐኪ_ቤተ_ክርስቲያን_እምነ፤
#ግበሪ_ጸሎተነ_በእንቲአነ፤
#እምኀይለ_ጸላዒ_ወፀር_ዕቀቢ_ኪያነ፤
#ትንባሌኪ_የሃሉ_ምስሌነ፡፡
✤‹‹#እግዚኦ በመዓትከ ኢትቅሰፈነ፥ ወበመቅሰፍትከ ኢትገስጸነ፡፡›› መዝ.ዳዊት
እንኳን ደስ አለን፤ በመዲናችን በአ.አ. የቤተ ክርስቲያን ቤተ መዘክሮቻችንን ቊጥር ወደ 9 ከፍ የሚያደርገውን ቤተ መዘክር (Museum) በጥንታዊቷ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ጥር 4/2011ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተመርቆ ለእይታ ክፍት ሆነ፡፡ በእለቱም ጥሪ የተደረገላቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት ተገኝተዋል፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኙ 9ኙ ቤተ መዘክሮቻችን የሚከተሉት ሲኾኑ እየሄዳችሁ ታዩ ዘንድ እንጋብዛለን፡፡
#የጠቅላይ ቤተ ክህነት መንበረ ፓትርያርክ ቤተ መዘክር(Museum) ፤
#እንጦጦ ደብረ ኀይል ቅዱስ ራጕኤል ወኤልያስ ቤተ መዘክር(Museum) ፤
#እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ማርያም ቤተ መዘክር(Museum) ፤
#ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ቤተ መዘክር(Museum) ፤
#መናገሻ ገተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ መዘክር(Museum) ፤
#ጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል የአቡነ ቴዎፍሎስ መታሰበያ ቤተ መዘክር(Museum) ፤
#መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ መዘክር(Museum) ፤
#ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤተ መዘክር(Museum) ፤
#እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳማ ቤተ መዘክር(Museum) ፡፡
(ሰፋ ያለ ታሪካቸውን ግን አዲስ በጀመርነው ‹‹ገዳማትና አድባራት›› መርሐ ግብር ላይ ከቤተ ክርስቲያናቸው ታሪክ ጋራ አብረን እናቀርባለን፡፡)
#እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳም፡፡
ይህች ገዳም ታሪኳ ከታላቁ ገዳማችን ዋልድባ (ገዳመ ዋሊ) ለ2ኛ ጊዜ መሥፋፋት (መመሥረት ጋር) የተያያዘ ታሪክ ያላት ናት፡፡ ይኸውም የሸዋ አባቶች ወደ ዋልድባ #በ485_ዓ_ም_በንጉሥ_አልአሜዳ_ዘመነ_መንግሥት_ባቀኑ_ጊዜ_ለ3_ወራት_የተሰባሰቡባት_ቦታ_ናት፡፡ እነዚህም አበው ከመኖሪያ ቀዬቸው (ቡልጋ/ምንጃር/……) ሁለት ታቦታትን (ታቦተ ኪዳነ ምሕረት ዘምሕረት አምባና፤ ታቦተ መድኀኔ ዓለም ዘአብዬ ገዳምን) ይዘው ነበር፤ ይዘዋት በመጡት ታቦተ ኪዳነ ምሕረትም ገዳመ ሐመረ ኖኅን መሥረተዋል፡፡ የመድኀኔዓለም ታቦትን ደግሞ በታላቁ ገዳም በዋልድባ አኑረዋል፡፡
ይህች #ሐመረ_ኖኅ_፤
*በ500 ዓ.ም. በአባ ሊባኖስ የአንድነት ገዳም ሆና ተስፋፍታ ተቋቋመች፡፡
*በ9ኛ መቶ ክ/ዘመን ዮዲት ጉዲት የአክሱም ጽዮንን ቤተ መቅደስ ለማቃጠል ስትነሳ ንጉሡ አንበሣ ውድም ታቦተ ጽዮንን በምሥጢር በማስያዝ ወደ ሸዋ መጥተው በእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት ገዳም ታቦተ ጽዮንን አሳድረው ወደ ዝዋይ ደሴት ሲሄዱ ለገዳሟ ንዋየ ቅድሰት ስጦታ አበርክተዋል፤ ጠበሏን ተጠምቀው ቦታዋን መርቀው ሄደዋል፡፡
*በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከንጉሥ ላሊበላ ጋር ወደ ዝቋላ አምባ ሲመጡ በዚህች ገዳም በእንግድነት አድረው በጠበሏ ተጠምቀው ቦታውን ባርከዋል፡፡
*አፄ ዘርዓ ያዕቆብም ወደዚህች ገዳም መጥተው አቀማመጧንና የጠበሏን ፈዋሽነት ተመልክተዋል፤ ‹‹ዳሯ እሳት መሐሏ ገነት ይሁን›› ብለው ብዙ ስጦታ አበርክተዋል፡፡
*አፄ ልብነ ድንግልም ወደ ገዳሟ መጥተው ተማህጽኖ አድርገው በጠበሏ ተጠምቀው ታቦተ ልደታንና ብዙ ንዋየ ቅድሳት ሰጥተው ሄደዋል፡፡
*በንግሥት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት ይህች ገዳም ሐመረ ኖኅ ኪዳነምህረት ገዳም ተብላ ተሰይማለች፤ አሁን ያለው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንም ታንጿል፡፡
***ይህች ቦታ ከታላቁ ገዳም ከዋልድባ ጋር አሁንም ግንኙነቷ እንደጠነከረ ነው፤ በዋልድባ ያሉ አባቶች ለተለያየ ጉዳይ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ በዋነኛነት የሚያርፉባት ጥንተ ርስታቸውም ናት፡፡
ይህች ቦታ በርካት ቅዱሳን በኪደተ እግር የረገጧት በመኾኗ የብዙ መነኰሳት መጠጊያ ናት፡፡ ጠበሏም የአጋንንት ድል መንሻ፥ የሕሙማን መፈወሻ፥ የአእምሮ ማደሻ ናት፡፡ የእመቤታችንን ቃል ኪዳን ለማግኘትም በአዲስ አበባ ከሚገኙ ቦታዎች ብዙ ጊዜ ለሱባኤ ከሚመረጡ ቦታዎችም አንዷ ናት፡፡
**ወደዚህች ገዳም በየወሩ ለኪዳነ ምሕረት የሚጎርፈው ምዕመን ኈልቈ መሳፍርት ያልተገኘለትና በሃገራችን በየወሩ ምዕመናን በመሳለም ትልቁን ቊጥር ይዟል፡፡ የዓመታዊ ክብረ በዓሉንማ ምንን እንነግራችኋለን፡፡
(ከሽሮ ሜዳ ታክሲ ቦታው ድረስ ያደርስዎታል፡፡)
