en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Open in Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 16 044 subscribers, ranking 5 280 in the Religion & Spirituality category and 2 239 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 16 044 subscribers.

According to the latest data from 27 October, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 518 over the last 30 days and by 0 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 24.70%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 10.29% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 963 views. Within the first day, a publication typically gains 1 651 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 29.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 28 October, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

16 044
Subscribers
No data24 hours
+987 days
+51830 days
Posts Archive
#ዐርብ_ቅዳሜና_እሑድ_፤ ++ የጸሎት መርሐ.ግብር፥ በጾሙ ማብቂያ (ከዐርብ - እሑድ፤ ማታ ማታ) ++ የጠቅላላ ጕባኤ ጥሪ፤ (ቅዳሜ በ10 ሰዐት) ++#፻፶፭ኛ ሳምንት የዐርብ ጕባኤ /የሕይወት_ፈተና_ምንጮች_ክፍል_፮፡፡ (ዐርብ_ታኅሣሥ_24፤ #ከ፲፪-፪ ሰዐት) *+* የአራዳና ጉለሌ ክ/ከተማ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት በሰ/ት/ቤታችን አገልግሎትና መምርያ ቦታን በተመለከተ ቅዳሜ #ታኅሣሥ_25 #ከቀኑ_በ10_ሰዐት እንድንወያይ ጥሪ ስላደረገ፤ አባላት በሙሉ በተጠቀሰው ሰዐት በሰ/ት/ቤቱ አዳራሽ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። (የቀ/ደ/ሰ መድኀኔዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት)

ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ ትንቢት የተናገረላት ናት፡- ‹‹እነሆ ድንግል ፀንሳ ወንድ ልጅ ትወልዳለች፣ ስሙንም ዐማኑኤል ትለዋለች፣ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡ /ት.ኢሳ. 7፥14/ **ነቢይ ሕዝቅኤል ‹‹እግዚአብሔርም አለኝ ‹ይህች በር ተዘግታ ትኖራለች፣ አትከፈትም፣ የሚገባበትም የለም የእስራኤል ፈጣሪ እግዚአብሔር እንደተዘጋች ይገባባታልና ተዘግታ ትኑር››› አለ፡፡ **ነቢዩ ዳንኤልም ‹‹ሌሊት በራእይ አየሁ ‹እነሆ ታላቁ እንደ ሰው ልጅ በሰማይ ደመና መጣ፤ ዘመኑን ወደሚያስረጅ ደረሰ፣ ከፊቱም አቀረቡት፣ የዘላለም አገዛዝ፣ ጌትነት፣ መንግሥት ተሰጠው፡፡ ሕዝቡና አሕዛቡ ሁሉ መንደር መንድረው የሚኖሩትና ነገዱም ነገሥታቱም ሁሉ ይገዙለታል፤ አገዛዙም የዘላለም አገዛዝ ነው፤ መንግሥቱም የማያልፍ የማይጠፋ ነው››› አለ፡፡ **ዳግመኛም ኢሳይያስ ‹‹እግዚአብሔር እንደ እኔ የሥጋ መጋረጃ በመጋረድ ተገለጠልኝ›› አለ፡፡ አሁንም ደግሞ ‹‹አዲስ ሰማይ አዲስ ምድር እሠራ ዘንድ አለኝ›› አለ፡፡ ሁለተኛም ‹‹በእሴይ ሥር በትር ትወጣለች፣ ከእርሷም ጽጌ አበባ ይወጣል›› አለ፡፡ ዳግመኛም ‹‹ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና ይኸውም ሥልጣን በጫንቃው የሆነ ክርስቶስ ነው፣ ስሙም ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም አለቃ ይባላል›› አለ፡፡ **ነቢዩ ኤርምያስም ስለ እግዚአብሔር ‹‹በዚያን ወራት ለዳዊት ብርሃንን አወጣለሁ፣ በምድርም የቀና ፍርድን ያደርጋል፣ እግዚአብሔርም ያመኑትን ያድናቸዋል›› አለ፡፡ **ኤልሳም ‹‹እግዚአብሔር ከሰማይ ይወርዳል፣ በእስራኤል ልጆች አደባባይም በመመላለስ ለሕዝቡ ዕውነትን ያስተምራቸዋል፡፡ ከአብርሃም ልጅነት ልዩ ከሆኑ ወገኖች በቀር አሕዛብ ሁሉ ይታዘዙለታል›› አለ፡፡ **ናሆምም ‹‹እግዚአብሔር በእኔ አርአያ ይመጣል፣ ልብሱም እንደልብሴ ነው›› አለ፡፡ **ኢዩኤልም ‹‹የእግዚአብሔር ዙፋን የሆነች ብላቴና ድንግልን አየሁ፣ እርሷም እንደ እሳት ያልባት ነበር፡፡ ስለእርሷ ‹ይህች ማናት/› ብዬ ኪሩብን ጠየቅሁት፡፡ እርሱም ‹ከአዳም ልጆች የተመረጠች የእግዚአብሔር ዙፋን ይህች ድንግል ናት፣ በእርሷም የተጎሳቆሉ አሕዛብ ይድናሉ፤ ለአመነባትም ረድኤትና መጠጊያ ናት› ብሎ ነገረው፡፡›› **ዳዊትም በመዝሙሩ ‹‹እግዚአብሔር አንተ ልጄ ነህ፣ ዛሬም በተዋሕዶ ወለድኩህ አለኝ፡፡ ለምነኝ አሕዛብን ርስት አድርጌ እሰጥሃለሁ፣ ግዛትህም በመላው ዓለም ነው፡፡›› ዳግመኛም አብ አለ ‹‹ቀዳማዊ ወልድ በኃይል ቀን ካንተ ጋራ ሳለሁ ከአጥቢያ ኮከብ በፊት ከሆድ ወለድኩህ፣ እንደ መልከ ጸዴቅ ሥርዓት አንተ የዓለሙ አገልጋይ ካህን ነህ ብሎ እግዚአብሔር ማለ፣ ከማለም አይፀፀትም፡፡›› ዕንባቆምም ‹‹አቤቱ ድምፅህን ሰምቼ ፈራሁ ሥራህንም አይቼ አደነቅሁ፤ በሁለት እንስሳ መካከል አየሁህ›› (ዕን ፫፥፪) **ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ‹‹በበረት ውስጥ የዓለም ገዢ መተኛት እጅግ ድንቅ ነው፤ በበረት ከጽርሐ አርያም ይልቅ ረዘመ፤ ከምድር ዳርቻም ሰፋ፤ ሕዝቅኤል ካየው ሠረገላ ዳንኤልም ካየው ኪሩባዊ ዙፋን በረት በለጠ (ሕዝ 1፡18-23፣ ዳን 7፡9) ብለው ተናገሩላት፡፡ #ኢትዮጵያና ግብፅ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርሰቶስ ልደት በዓልን ታኅሣሥ 29 ቀን (በ4ት ዓመት 1ዴ ታኅሣሥ 28) ያከብራሉ፤ ለምን የሚለውን ከባሕረ ሓሰብ ሊቃውንትና ከመጻሕፍት እንድታነቡ እየጋበዝን ይህን ሁኔታ በጥልቀት ካጠኑት ዐበይት ሊቃውንት መካከል ዋናዎቹ #ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ፤ #ሰዒድ ወልደ በጥሪቅ፤ #መበንጋዊ/ማኅቡብ/፤ #ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ/አልአሚድ/፤ #ወልደ መነኰስ፤ #ሐዋርያት በዲድስቅልያ አንቀጽ 29 ገጽ 37፤ ሊቃውንት ወመምህራን ዘኢትዮጵያ ወግብፅ /ለአብነትም ከኢትዮጵያውን ደብረ ቢዘንና የጕንዳጒንዶ ሊቃውንት፣ አለቃ አሥራስ የኔሰው፣ አለቃ ሰዐት ከብቴ … እንዲሁም ቅዱስ ድሜጥሮስና ዮሐንስ አቤልሄሬም(ዮሐንስ አቡሻኽር) ከግብፅ ሊቃውንት/ ይጠቀሳሉ፡፡ #ታኅሣሥ 29 ልደታቸው ከጌታችን ልደት ጋር የተባበረላቸው ቅዱሳን፤ #አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ፤ #ቅዱስ ላሊበላ፤ #ቅዱስ ነዓኵቶ ለአብ፤ #አቡነ አብሳዲ ዘደብረ መጕና #ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ፤ #ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃ፤ #አቡነ አካለ ክርስቶስ፤ #አቡነ መዝራእተ ክርስቶስ፤ #መስፍኑ ኢያሱ፤ #የገርአልታው አቡነ ዳንኤል፤ #ዳግማዊ ቂርቆስ ዘቡልጋና ሌሎችም ቅዱሳን አሉ፤ ነገር ግን ከቅዱሳን በዓል በላይ የጌታ በዓል መከበር ስለሚገባው የቅዱሳኑ ዋና በዓላቸው በሌላ ቀናት /በዕረፍታቸው…../ ቀን ይታሳባል፡፡ #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#ጌና_እና_ልደት_ ጌና እና ልደት ዋዜማና ክብረ በዓል /የተለያዩ ቀናት/ ቢኾኑም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ጌና ልደትን እየተካ እንጠቀምበታለን፤ ነገር ግን ይህ ሊስተካከል ይገባዋል፡፡ ልዩነት ስላለውም የኢትዮጵያ ብርሃን የተባለው አፈ ጳዝዮን አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ለጌናና ለልደት ለ2ቱም በዓላት ለየብቻቸው በመጽሐፈ ምሥጢር ድርሰት ደርሶላቸዋል፡፡ #ጌና፤ የልደት በዓል ዋዜማ ቀን ሲኾን በዚህ ቀን ‹‹በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ›› የተባለለትን ‹‹የገና ጨዋታ›› እንጫወታለን፤ የምንጫወትበት የኳሱ ስያሜ ‹‹ሩር›› ሲባል ስያሜውን ያገኘው፤ ሰብዓ ሰገል እልፍ እልፍ ሠራዊት አስከትለው የተወለደውን አይሁድ ንጉሥ ፍለጋ ወደ ንጉሡ ሔሮድስ ደርሰው ነበርና፤ ሔሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ፈልጎና በውስጡ ሸሽጎ ለሰብዓ ሰገል ሂዱ ሕፃኑን ፈልጉ ስታገኙትም ንገሩኝ ብሎ ሰድዷቸዋል፤ ነገር ግን በዚያው ሳይነግሩኝ እንዳይሄዱ በማለት እነርሱ ሳያውቁ ‹‹ሩር›› የተባለ ሰላይ በመሃላቸው አስገብቶ ነበርና ሰብዓ ሰገልን ይመራቸው የነበረው ኰከብ ተሠውሮባቸዋል፤ ሰብዓ ሰገል ሠራዊታቸውን ቢያጣሩ ከመሃከላቸው የተቀላቀለ ሩር የተባለ የሔሮድስን ሰላይ አገኙ ይህንንም ሰላይ የሰብዓ ሰገል ሠራዊት አንገቱን በሰይፍ ቀልተውታልና ያን ለማስታወስ ዛሬ በገና ጨዋታ ላይ ሩር የተባለው ኳስ የሔሮድስ ሰላይን ‹‹ሩር›› እንዲያስታውስ አባቶች ሥርዐትን ሠሩ፡፡ #ልደቱ_ለእግዚእነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ #‹‹#ቤዛ_ኩሉ_ዓለም_ዮም_ተወልደ::›› /#ቅዱስ_ያሬድ/ ጌታችን ለሰው ልጆች ብሎ፤ የሰው ልጆች ፍቅር አገብሮት ንጽሕትና ቅድስት ከኾነች ከእመቤታችን ያለ ወንድ ዘር በመጋቢት 29 ተጸንሶ ታኅሣሥ 29 በ1ዓ.ም. (ዓለም ከተፈጠረ፥ ዘመን ከተቈጠረ በ5,500 ዓመት) በበረት ተወልደ፡፡ ሰማይና ምድር የማይወስኑትን በረት ቻለው፤ ወሰነውም በሌሊት መንጋቸውን የሚጠብቁ እረኞች ነበሩ፡፡ መልአኩ መጥቶ እንዲህ አላቸው፡- ‹‹እነሆ! ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና፡፡ ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ›› አላቸው፡፡ ሉቃ2፡10-12፡፡ ከመለአኩም ጋራ ሠራዊተ መላእክት መጥተው ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ለዕጓለ እመሕያው /ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ/›› አሉ፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ እረኞቹ እርስ በርሳቸው ‹‹እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ፣ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ›› ተባባሉና ፈጥነው መጡ፡፡ ማርያምንና ዮሴፍን ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ፡፡ አይተውም ስለዚህ ሕፃን የተነገረላቸውን ነገር ገለጡ፤ የሰሙትን ሁሉ እረኞቹ በነገሯቸው ነገር አደነቁ፤ የብርሃን እናቱ እመ አምላክ ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር፡፡ ሉቃ 2፡13-19፡፡ መላእክትም ሰማይ መንበሩ ምድር የእግሩ መረገጫ የሆኑለት አምላክ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ በጎል ተኝቶ በጨርቅ ተጠቅልሎ አይተውት ደስ ብሏቸው ወደ ሰማይ ቢያርጉ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በዕሪና ከመንበሩ አይተውት ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት›› ብለው አመስግነውት በጣዕም ላይ ጣዕም፤ በጸጋ ላይ ጸጋ ተጨምሮላቸው ደስ ብሏቸዋል፡፡ ልደቱን ይሹታልና፤ መላእክትም ብቻ አይደሉም እንስሳትም አራዊትም ደስ ብሏቸዋል፡፡ #ይህም_ሊታወቅ_አንድ_ባሕታዊ_በቋራ_/_ኋላ_ማኅበረ_ሥላሴ_ገዳም/_ቋርፍ_ሲምስ_ቶራ_ሚዳቋ_ዮም_ተወልደ_ መድኀኔ_ዓለም_ዮም_ተወልደ_ቤዛ_ኵሉ_ዓለም_ዮም_ተወልደ_ከሣቴ_ብርሃን፡፡ እያለች ስትዘል አይቷል። በጌታችን በልደቱ የባሕር ውኃ ወተትና ማር ተራሮች እንጀራ እንጨቶችም የበረከት ፍሬ ሆነዋል፡፡ ልደቱንም በኮከብ ተረድተው ሰብአ ሰገል (የጥበብ ሰዎች) ስማቸውም ማንቱሲማር፣ ሜልኩ በዲዳስፋ የተባሉ የፋርስ ነገሥታት ከገነት የተገኘ ወርቅ፣ ዕጣን ከርቤ አምጥተው ገብረውለታል፡፡ /ዘኅ 20፡17፡፡ ‹‹ሰው ሆይ! ፈጽመህ ደስ ይበልህ፣ እግዚአብሔር ዓለሙን ወዶታልና አንድ ልጁንም የሚያምንበት ሁሉ እስከ ዘለዓለም ፈጽሞ ይድን ዘንድ አሳልፎ ሰጥቷልና ልዑል ክንዱን ሰደደልን፡፡›› ‹‹በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው፤ በቅዱሳን ላይ የሚያድር እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ድንግል ሰው ሆኗልና ኑ ይህን ድንቅ እዩ፤ ስለተገለጠልን ምሥጢር ምስጋና አቅርቡ፤ ሰው የማይሆን ሰው ሆኗልና ቃል ተዋሕዷልና ጥንት የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ፣ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት፡፡ የማይታወቅ ተገለጠ፣ የማይታይ ታየ፣ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ በእርግጥ ሰው ሆነ፡፡›› ‹‹ከቅድስት ሥለሴ አንዱ ወልድ መዋረዳችንን አይቶ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ባሕርዩን ዝቅ አደረገና መጥቶ በድንግል ማኅፀን አደረ፤ ከብቻዋ ከኃጢአት በቀርም እንደ እኛ ሰው ሆነ፡፡ ነቢያት ትንቢት እንደተናገሩለት በቤተልሔም ተወለደ፤ ፈጽሞ አዳነን፣ ወገኖቹም አደረገን፡፡›› ይህችም ዕለት፤

✤✤ #በአዲስ አበባ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ልደት የሚከበርባቸው፤ 1.# ጥንታዊው ዋሻ ሚካኤልና ተክለ ሃይማኖት ገዳም፤ #በአዲስ_አበባ_የመጀመሪያው_ቤ/ክ፡፡ (በ320ዓ.ም. የተመሠረተ፡፡) 2
+2
✤✤ #በአዲስ አበባ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ልደት የሚከበርባቸው፤ 1.# ጥንታዊው ዋሻ ሚካኤልና ተክለ ሃይማኖት ገዳም፤ #በአዲስ_አበባ_የመጀመሪያው_ቤ/ክ፡፡ (በ320ዓ.ም. የተመሠረተ፡፡) 2.#ዳግሚት ደብረ ሊባኖስ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም (በ1898ዓ.ም. የተመሠረተ) 3.#መንበረ ክብር ደብረ ታቦር ቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም 4.#ፊሊዶሮ ደብረ ፀሐይ አቡነ ተክለ ሀይማኖት 5.#ቤቴል ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ፤ በድርብነት ይከብራል፡፡ 6.#ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ቤ.ክ፤ በድርብነት ይከብራል፡፡ 7.#ካራ ምሥራ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤልና 24ቱ ካህናተ ሰማይ 8.#ሲምሲ ተክለ ሃይማኖት 9.#ቦሌ ቡልቡላ ተክለ ሃይማኖት 10.#መልካ ቆራኒ አቡነ ተክለ ሃይማኖት 11.#ምስካበ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት 12.#ቦሌ ለሚ ተክለ ሃይማኖት 13.# ፈለገ ሰላም ቤላ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እና አቡተ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ ሌሎች ካሉ ጨምሩባቸው፤ ፎቷቸውንም ላኩልን፡፡ #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

በእጨጌ የሚመሩት 2ቱ ደብረ ሊባኖሶች፤ 1ኛ) ደብረ ሊባኖስ ገዳም፤ (ሰሜን ሸዋ) 2ኛ) አዘዞ ደብረ ሊባኖስ ገዳም፡፡ (ጎንደር) #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com
+3
በእጨጌ የሚመሩት 2ቱ ደብረ ሊባኖሶች፤ 1ኛ) ደብረ ሊባኖስ ገዳም፤ (ሰሜን ሸዋ) 2ኛ) አዘዞ ደብረ ሊባኖስ ገዳም፡፡ (ጎንደር) #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

የጠቅላላ ጕባኤ ጥሪ፤ ለአባላት በሙሉ፡፡ የአራዳና ጉለሌ ክ/ከተማ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት በሰ/ት/ቤታችን አገልግሎትና መማርያ ቦታን በተመለከተ ቅዳሜ #ታኅሣሥ_25 #ከቀኑ_በ10_ሰዐት እንድንወያይ
የጠቅላላ ጕባኤ ጥሪ፤ ለአባላት በሙሉ፡፡ የአራዳና ጉለሌ ክ/ከተማ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት በሰ/ት/ቤታችን አገልግሎትና መማርያ ቦታን በተመለከተ ቅዳሜ #ታኅሣሥ_25 #ከቀኑ_በ10_ሰዐት እንድንወያይ ጥሪ ስላደረገ፤ አባላት በሙሉ በተጠቀሰው ሰዐት በሰ/ት/ቤቱ አዳራሽ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ (የቀ/ደ/ሰ መድኀኔዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት)

✤✣✤ #በዓለ_ልደቱ_ለሐዲስ_ሐዋርያ_ፀሐይ_ማር_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት #ታኅሣሥ_24_1196ዓም_በሰሜን_ሸዋ_ቡልጋ_ጽላልሽ_እቲሣ_ተወልደው_በአጠገቡ_በምትገኛወ_ደብረ_አጋዕዚት_ክርስትና_ተነሡ፡፡ #አባታቸው ቅዱስ ጸጋ ዘዓብና እናታቸው ቅድስት እግዚእ ኀረያ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲያስተምሯቸው በአካባቢያቸው ደግሞ በዘመኑ የነበሩ ልጆች ይማሩ የነበረውን ፈረስ መጋለብን፣ ቀስት መወርወርን፣ እርሻንና አደንን አስተምረዋቸዋል፡፡ #በ7ት ዓመታቸው ከግብፃዊው ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ ዲቁናን ከተቀበሉ በኋላ እግዚአብሔር በክህነት ሕዝቡን እንዲያገለግሉ መረጣቸው፡፡ ከዮዲት ጉዲት በኋላ ሃገራችን ሰሜኑና ደቡቡ ተቆራርጧል፤ የሐሳብን ልዕልና የሚያመጣው የመንፈስ ልዕልና ተዳክሟል፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያን የሚዋጅ ሐዲስ ሐዋርያ ያስፈልግ ነበርና አምላካችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ጠራ፡፡ #አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቅስናን ከአቡነ ቄርሎስ ተቀብለው በጽላልሽ አካባቢ በክህነት ከአባታቸው ጋር አገልግለዋል፡፡ አባታቸው ሲያርፉ በወንጌሉ ማንም ሊከተለኝ የሚወድድ ቢኖር ያለውን ሁሉ ትቶ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ ያለውን በመከተል ሀብታቸውን ለድኾች መጽውተው በሸዋና በዳሞት በስብከተ ወንጌል አገለገሉ፡፡ ከዚያም፤ #በመጀመርያ ደቡብ ወሎ ቦረና ላይ ገዳማቸውን ደብረ ጎል ገድመው ወደሚገኙት ታላቁና ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን ወደኾኑት ጻድቅ አባት አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ገብተው ዐሥር ሁለት ዓመታት በትምህርትና በሥራ (በአርድእትነት) አሳልፈዋል፡፡ በዚያም ዋሻ ፈልፍለው አስደናቂ ሕንፃ ሠርተው ነበር፡፡ #በ1216 ዓ.ም. አካባቢ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገሳም ገብተዋል፤ በዚሁ ገዳምም ከመመንኰሳቸው በፊት ሰባት ዓመት ከመነኰሱም በኋላ ሦስት ዓመት በድምሩ ለ10 ዓመታት በትምህርት፣ በእደ ጥበብ ሥራ፣ በአገልግሎትና ሥርዐተ ምንኵስናን እያጠኑ ቆይተዋል፡፡ #ከሐይቅ ወጥተው በዘመኑ በሥርዐተ ምንኵስናና በትምህርት ብሎም በጥበበ እድ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ወደ ነበረው ወደ ደብረ ዳሞ በመሄድ በየገዳሙ አበምኔት ከሆኑት ከአቡነ ዮሐኒ ዘንድ መንፈሳዊ ትምህርት፣ ሥርዐተ ምንኵስናና ጥበበ እድ ሲማሩ ለ12 ዓመታት ቆዩ፡፡ ያነጹት ፍልፍል ድንጋይ ዋሻ፣ መጻሕፍት ሲጽፉ ቀለማቸውን ያስቀምጡባቸው የነበሩትን ሽንቁሮች ዛሬም በደብረ ዳሞ ማየት ይቻላል፡፡ #በደብረ ዳሞ የነበራቸውን ቆይታ ጨርሰው በገመድ ሲወርዱ ሰይጣን በቅንዐት መጥቶ ገመዱን በጠሰባቸው እግዚአብሔር አምላክ በዚህ ወቅት የሚበሩበትን እንደ መላእክት ክንፍ ሰጣቸው፡፡ #ለአምስት ዓመታት #አኵስምን_ዋልድባን እንዲሁም ሎሎች የትግራይ ገዳማትን እየተዘዋወሩ ሲመለከቱ ቆዩ #ከሸዋ በወጡ በሃያ ሁለት ዓመት (እድሜያቸው ሃምሳ ሁለት ሲሆን) ለበለጠው ክብር እና ርእይ በግብጽ በኩል ወደ ኢየሩሳሌም ተሻገሩ፡፡ #ከኢየሩሳሌም ሲመለሱ በሐይቅ በኩል አድርገው ደብረ ጎልን ተሳልመው በሚዳ እና በመርሐ ቤቴ በኩል ወደ ሸዋ በመምጣት ከዮዲት ዘመን በኋላ በመንፈሳዊ ሕይወት የተጎዳውን ሸዋን እና ደቡብ ኢትዮጵያን በመዘዋወር ለዐሥር ዓመታት ያህል አስተምረዋል፡፡ #አቡነ ተክለ ሃይማኖት ተግተው በማስተማራቸው የተኛው ሁሉ ነቃ፣ የደከመው በረታ፣ የጠፋውም ተገኘ፡፡ ሐዋርያትን ለማፍራት እንዲችሉ አንድ ገዳም ለመመሥረትና ደቀ መዛሙርትን ለማስተማር አሰቡ፡፡ እናም ወደ ደብረ አስቦ ገዳም ገቡ፡፡ ቦታውን አስተካክለው እና ከደብረ ዳሞ እና ከሐይቅ የተከተሏቸውን ጥቂት ደቀ መዛሙርት ይዘው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ልክ እንደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ሁሉ ሦስቱን ነገሮች ያካተተ አገልግሎት ጀመሩ፡፡ ምንኵስና፣ ትምህርትና ሥራ፡፡ መነኰሳቱ መንፈሳዊ ትምህርት ይማራሉ፤ በሕገ ገዳም ይመራሉ፤ ለራሳቸው እና ለአካባቢው ሕዝብ ርዳታ የሚሆን እርሻ ያርሳሉ፡፡ #ደቀ መዛሙርትን አፍርተው፣ ገዳማቸውን አደራጅተው፣ ስብከተ ወንጌልንም አስፋፍተው ካደላደሉ በኋላ በሕይወታቸው የመጨረሻ ዓመታት ወደ ደብረ አስቦ ዋሻ ገብተው በአንድ እግራቸው በጾም እና በጸሎት ተወሰኑ፡፡ #አገልግሎታቸውን ፈጽመው ነሐሴ 24 ቀን 1297 ዓ.ም. በ99 ዓመታቸው ዐረፉ፡፡ ✤✤ #እቲሣ_ገዳም_ #በቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃና አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የተመሠረተ፤ ሲመሠረትም በታቦተ ኢየሱስና አርባዕቱ እንስሳ ነው፤ #ሊቀ ካህናት አበይድላ ከአኵስም 300 ታቦታትና 300ካህናት ይዞ መጥቶ በጽላልሽ የተቀመጠባት ናት፤ #ፀሐይ አቡነ ተክለሃይማኖት የተወለዱባት (የተወለዱባት ጠፍጣፋ ደንጊያ አሁንም በቦታው አለች)፣ #አባታቸውና ጸጋ ዘአብና እናታቸው እግዚእኀረያ የተወለዱበት፤ ኋላም ክብሩ አጽማቸው ያረፈበት ነው፡፡ #ቅዱስ ያሬድ 3 ዓመት ጸልዮባታል፤ #ቅዱስ ላሊበላ 7 ዓመት ጸልዮባታል፤ #ተሰዓቱ ቅዱሳን 20 ዓመት የጸለዩበት፤ #ሐርቤ በሚባለው ቦታ ላይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ 7 ዓመት ጸልየውበታል፤ #ታቦተ ጽዮን 12 ዓመት (ከ9ሺህ ሕዝብ) ጋር መጥታ ኖራበታለች፤ #በአምሳለ ሲዖል የተሠራ አስደናቂ የጨለማ ዋሻ ያለበት ነው፤ #ብዙ የታሪክ ቅርስ ያለበት ነው፤ #በቅዱስ ሚካኤልና ጸጋ ዘአብ ቤተ ክርቲያን ውስጥ ካየን በኋላ፤ እዚሁ ቦታ በሚገኘው ፈዋሽ ጠበል ተጠምቀንና ጠጥተን ጕዟችንን ወደ #ቦታው_ከአአ_በቅርብ_ርቀት_በደብረ_ብርሃን_መንገድ_አሌልቱ_ከተማ_ላይ_በመታጠፍ_ይገኛል፡፡ #ሥርዐተ_ማኅሌቱን_እንደየደብራችሁ ይትበሃል እንድትጠቀሙበት በማሰብ ሁሉንም (በላይ ቤትና በታች ቤት) (#ዘአባጃሌ_ተክለ_ሃይማኖትና_ዘአደባባይ_ተክለሃይማኖት) አዘጋጅተነዋል፡፡ ጸሎትና በረከታቸው፤ ረድኤትና ምልጃቸው በመላው ሕዝበ ክርስቲያንና በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ሁሉ አድሮ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ /ከቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለምና ደ.ት ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሰሌዳ መጽሔት የተወሰደ/ #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#ታኅሣሥ_23 #ቅድመ_ልደተ_ክርስቶስ_በ1080_ቅዱስ_ዳዊት_አረፈ_፡፡ ፠ እግዚአብሔር እንደ ልቤ ብሎ የጠራው ፤ በዚህም ልበ አምላክ ተብሎ የሚጠራ፤ ፠ 10ር አውታር ባለው በገና የሚያመሰግን፤ መዘምር፤ ፠ ከ15ቱ ነቢያት አንዱ፤ ፠ 40 ዓመታት እሥራኤልን የገዛ፤ አምላኩ ኪዳንን የሰጠው፤ ፠ የዋህ፣ ደግ፣ ትሁትና ርህሩህ (በየዋህነቱ ከሙሴ ጋር፤ በደግነቱ ከአብርሃም ጋር የሚነጻጸር) ፠ ኃይል የሆነ (በኃያልነቱ ከሶምሶን ጋር የሚነጻጸር) ፠ ጀግና (ከጀግንነቱ የተነሣ ዳዊት መጣ ሲባል ደንግጦና ፈርቶ የሚሞት የነበረ) ፠ አስተዋይና ብልህ መሪ (በርካታ አስተዋዮችና ብልህ መሪዎች በሥሩ የነበሩት) ፠ መዝሙሩ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ዕለት ዕለት የሚጸለይ (አንድ ክርስቲያን ግዴታ በየቀኑ ሊጸልየው የሚገባ ጸሎት ተብሎ በፍትሐ ነገሥት የተደነገገ) ፠ ከደረሰው መዝሙር የተውጣጡ ምስባኮች ከዓመት ዓመት በቅዳሴ ጊዜ በዜማ ጭምር የሚባሉለት ፠ የንስሐ አባት (ቶሎ ብሎ ንስሐ በመግባት ከፈጣሪው ጋር የሚታረቅ) * ትውልዱ ከእሥራኤልና እንዲሁም ከሞዓባውያን ወገን ከሆነችው ከደገኛይቱ ሩት ነው * እሥራኤልን በንግሥና መመምራት ከሳዖል ቀጥሎ ሁለተኛ ነው፡፡ (ነገር ግን የሳዖል መንግሥት የይንቆሽ ስለሆነ ዳዊት የመጀመሪያው የእሥራኤል ንጉሥ በመባል ይታወቃል)፤ * ገና በወጣትነት በእረኛ እጅ በፈጣሪው መራጭነት በጠንካራው እምነቱ ወደ ጦር ሜዳ በመጓዝ በግዝፍነቱና በጀግንነቱ ተወዳዳሪ የጠፋለት የዕብራውያንን ልብ እንደሰም ያቀለጠ፥ ንጉሣቸው ሳዖልንም ያሸበረና ያስደነገጠ፤ መምለኬ ጣዖት፥ መዝግበ ኃጢአት ፥ ትዕቢትን የተሞላ ፥ የጣዖት ድልብ ቁመቱ ስድስት ክንድ ከስንዝር የሚሆን ረአይታዊ ጎልያድን በፈጣሪው ኃይል በወንጭፍ ደንጊያ ግንባሩን መቶ ገርስሶ በመጣል ቸብቸቦውን በሰይፍ በመገንጠል እያንዳንዱ ዕብራውያንን ከጎልያድ ሰይፍ ታድጓል፡፡ (መዝ 151) ዳዊት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከጦር ሜዳ ሳይለይ አያሌ ዘመናት አሳልፏል፡፡ * የእስራኤል ሴቶችም ‹‹ሳዖል ሺህ ገደለ፤ ዳዊት ዕልፍ ገደለ /ጎልያድ የእልፍ ያህል ነውና/ እያሉ በመዝፈናቸው በሳዖል ልብ ቅንዐት አደረ፡፡ * በሽፍትነት በረሀ ለበረሀ በመንከራተት ብዙ ዘመን ካሳለፈ በኋላ ሳዖል ሲሞት መሪነቱን ይዟል፤ ነገር ግን እሥራኤልን ለመምራት የተመረጠው ገና ሳዖል በሕይወት እያለ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ በሳሙኤል ቀባዒነት ነው፡፡ * ከጀግንነቱ የተነሣ ዳዊት መጣ ሲባል ደንግጦ እና ፈርቶ የሞተም እንዳለ ታሪክ ይነግረናል፡፤ 1ኛ ሳሙ 25፥1-39፡፡ ነገር ግን ዳዊት እንደ ጀግንነቱ ሁሉ ጨቃኝ አይደለም ርህራሄም የተሞላ መሪ ነበር ከአንዴም ሁለቴ ሳዖልን መግደል ሲችል ራርቶ የመረጠውን እግዚብሔርን ፈርቶ ትቶታል፡፡ * ዳዊት ትልቅ ኃጢአት የሠራው የጦር ጀግናው የኦርዮን ሚስቱን ከመቀማቱም ባሻገር በጦር ሜዳ ለጠላት ጦር አሳልፈው ሰጥተው ወደኋላ እንዲያፈገፍጉ ለእስራኤል በመምከር ኦርዮን ባልተረዳው ነገር ተደብድቦ እንዲሞት አስደርጓል፡፡ በዚህም እግዚአብሔርንም ሆነ የጦር መሪው ኢዮአብን አሳዝኗል፡፡ በዚህም እግዚአብሔር እውነተኛ ፈራጅ በመሆኑ በዳዊት ላይ ከበድ ያለ መከራና ኃዘን አምጥቶበታል፡፡ ለአነብነትም፤ 1ኛ) አምኖን የገዛ እኅቱን ከክብር አሳንሶ አዋረደ ፤ ዳዊት የሰው ሚስት በግፍ ደፍሮ ነበርና፤ 2ኛ) በዚህ ምክንያት አቤሴሎም ወንድሙ አምኖንን ገደለ ፤ ዳዊት ኦርዮንን በግፍ አስገድሎ ነበርና፤ 3ኛ) አቤሴሎም የዳዊትን መንግሥት ገልብጦ የአባቱን እቁባት ሁሉ በአደባባይ አረከሰ፤ ዳዊት የኦርዮንን ሚስት በድብቅ ተገናኝቷታልና እንዲሁም ዳዊት የሳዖልን መንግሥት አስቸግሮ ነበርና፤ 4ኛ) አቤሴሎም በአባቱ የጦር አበጋዞች ተደብድቦ ሞተ፤ በዚህም ዳዊት እጅግ አዝኖ ነበር፡፡ 5ኛ) አዶንያስም በአባቱ ላይ መፈንቅል አድርጎ ለጊዜው ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ነገር ግን ከላይ የተዘረዘሩት 5ት ሐዘኖች ቢገጥሙትም ዳዊት በለመደው የንስሐ ልቅሶ ችግሩን አስተካክሎ ወደ ፈጣሪው ተጠግቷል፡፡ * ኃጢአቱን ይቅር ያለው ፈጣሪው ግን ቤተ መቅደስን እንዳይሠራ በነቢይ አማካይነት ከልክሎታል፤ ዳዊትም ይህን የፈጣሪውን መመሪያ አልተጋፋም ሥራውን አቁሟል፡፡ የእግዚብሔር እንደራሴ ስለነበረ፡፡ •+++• ዳዊት እግዚአብሔር ለሰው ከሚሰጣቸው ልዩ ሐብታትም ባለቤት ነበር፡፡ እነርሱም፤ 1ኛ. ሀብተ ጥበብ ወአዕምሮ 2ኛ. ሀብተ ትንቢት 3ኛ. ሀብተ ኃይል (ገና በእረኝነት ግሩማን አራዊት ድብና አንበሳን ጉሮሯቸውን እያነቀ በመግደል ኋላም ግዙፍ ጎልያድን በአልባሌ መሣሪያ ገርስሶ በመጣል) 4ኛ. ሀብተ ምክር 5ኛ. ሀብተ ልቡና 6ኛ. ሀብተ ፈሪሃ እግዚአብሔር 7ኛ. ሀብተ ፈውስ #መዝሙረ_ዳዊት_፤ ፠151 መዝሙራት ሲኖሩት 88ቱ እርሱ የዘመራቸው ሲሆኑ፤ ቀሪዎቹ ደግሞ ሌሎች የዘመሩትን ሲሆን የሌሎችንም መዝሙራት 10ር አውታር ባለው በበገና ይዘምራቸው ስለነበረ 151ዱም የዳዊት መዝሙራት ተብለዋል፡፡ ፠ መዝሙረ ዳዊት ምሥጢራዊ ነገር ያለበት፥ በምሥጢሩ የጠለቀ፥ በትንቢታዊነቱ የረቀቀ፥ መንፈሳዊ ስብከት ፥ ትንቢታዊ ትምህርትን የተሞላ፥ ቊጥሩ አንድ ውስጡ ብዙ፥ የማይጠቅሰውና የማይናገረው የሌለ ዕፁብ ድንቅ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ ፠ መዝሙረ ዳዊት ባሕር ነው፤ አንድ ሰው ከጥልቅ ባሕር ገብቶ እንደ አቅሙ ትንሽ ዓሣ ይዞ ሊወጣ ይችላል፤ ፠ነቢዩ ዳዊት እግዚብሔር ብዙ ረቀቁ ትንቢቶችን ስለተናገረበት በፈጣሪው ዘንድ #የእግዚአብሔር_ልብ የመባል ልዩ ስያሜ ያገኘ ብቸኛ ሰው እንደነበር ዜና ነገሥት ይናገራል፡፡ /1ኛ ሳሙ 13፥14፣ የሐዋ ሥራ 13፥22/ ፠ ዳዊት በመዝሙሩ አምስቱን አዕማደ ምሥጢር መዝግቦ ያስነብበናል:: ፠ መዝሙረ ዳዊት ከተለያዩ መመዘኛዎች አንጻር በተለያዩ አከፋፈሎች ይከፈላል፡፡ #በቅዳሴ_ጊዜ_የዳዊት_መዝሙር_በዜማ_ይዜማል_ለምን? የዳዊት መዝሙር ለሌሎች የነቢያት መጻሕፍት ተለይቶ ቅድመ ወንጌል በዜማ እንዲሰበክ የተደረገበት ምክንያት፤ በርካታ ነገሮችን በወንጌል የተመዘገቡትን ስለያዘ ነው፡፡ በዚህም መዝሙረ ዳዊት ደረቅ ሐዲስ በመባል ይታወቃል፡፡ ስለ መዝሙረ ዳዊት ታላቁን ሊቅ ቅዱስ ያሬድን (በክስተተ አርያም፣ በመስተጋብዕ፣ …) ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን (በመጽሐፈ ሰዐታቱ፣ በመዝሙረ ድንግል) ይጠይቁ፤ 151ዱን መዝሙር በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ በንባብ ብቻ ሳይሆን በጣዕማዊ ሰማያዊ ዜማ ከእግር እስከ ጫፍ ከጽንፍ አስመልክታ መልዕክቷን ወደ ፈጣሪዋ እንደታቀርብበት ለቤተ ልርስቲያናችን አስረክበዋልና፡፡ ፎቶ ላይ ይምትመለከቱት ቤ/ክ፤ ከ300 ዓመት በላይ የሆነውና #በአድያም #ሰገድ #አፄ #ኢያሱ (1674-1698) የታነጸውን የቅዱስ ዳዊት ቤተ ክርስቲያን ሲሆን፤ ቤተ ክርስቲያኑ የሚገኘው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ዳዊት ቀበሌ ነው፡፡ (ወደ ቦታው ለመሄድ ከፈለጉ ከአዲስአበባ ተነስተው ፡ #በእንጅባራ አልፈው ፡ #ቻግኒና #ግልገል በለስንም ተሻግረው #ማንቡክ ወደምትባል ከዚያም #በላያ የሚባል አካባቢ ላይ ንጉሥ ዳዊት ቀበሌንና የቅዱሱን ደብር ያገኛሉ፡፡) #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#ዜና_ዕረፍት_ የትህትና አባት ፣ የደብረ ዐባይ ቅዳሴ ሊቅ የሆኑት #ብፁዕ_አቡነ_ዳንኤል_የድሬዳዋና_የጅቡቲ_ሀገረ_ስብከት_ሊቀ_ጳጳስ_ዐረፉ፡፡ ትላንት ማምሻውን በመንበረ ፓትርያርክ በሚገኘው መኖሪያ
+1
#ዜና_ዕረፍት_ የትህትና አባት ፣ የደብረ ዐባይ ቅዳሴ ሊቅ የሆኑት #ብፁዕ_አቡነ_ዳንኤል_የድሬዳዋና_የጅቡቲ_ሀገረ_ስብከት_ሊቀ_ጳጳስ_ዐረፉ፡፡ ትላንት ማምሻውን በመንበረ ፓትርያርክ በሚገኘው መኖሪያቸው ያረፉት ብፁዕነታቸው፣ ከልብ ሕመም ጋራ በተያያዘ በሀገር ውስጥ እና በአሜሪካ የሕክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቷል፡፡ ከሳምንት በፊት በአሜሪካ በነበሩበት ወቅት የልብ ቀዶ ሕክምና እንዲደረግላቸው ቢጠየቁም፣ "አልፈልግም፤ አገሬ ገብቼ ልሙት፤" ብለው እንደተመለሱ ታውቋል፡፡ የቀብራቸው ሥነ ሥርዐት ነገ ዐርብ፣ ታኅሣሥ 24 ቀን 2012ዓ.ም. በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን እንደሚከናወን ተጠቁሟል፡፡ (ዘግይቶ በደረሰን መረጃ፤ በቃላቸው መሠረትና በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ግብዐተ መሬቱ የሚከናወነው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ነው፡፡ በቀድሞ ስማቸው አባ ፍቅረ ማርያም ይባሉ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ዳንኤል በምሥራቅ ኢትዮጵያ አህጉረ ስብከት አድባራት(ገለምሶ፣ ጎዴ፣ ድሬዳዋ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል) በአስተዳዳሪነት፣ በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ት/ቤት ዲን ኾነው ሠርተዋል፡፡ በሐምሌ ወር 1997 ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንብሮተ እድ ኤጲስ ቆጶስነት ከተሾሙት 17 አባቶች አንዱ ሲሆኑ፤ ኤጲስ ቆጶስነት ከተሾሙ በኋላ፣ በምሥራቅ አፍሪቃ አህጉረ ስብከት(ኬንያ እና ጅቡቲ)፣ በምዕራብ ሐረርጌ፣ በመጨረሻም የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት እና የጅቡቲ አብያተ ክርስቲያናት ሊቀ ጳጳስ ኾነው በአባትነት አገልግለዋል፤ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያን በበላይ ሓላፊነት መርተዋል፡፡ #የብፁዕነታቸው_በረከት_ይደርብን፤ #ቅድስት_ጸሎታቸው_ትጠብቀን፤ አሜን፡፡

የአርሲ ነገሌ የመስቀል አደባባይና ባሕረ ጥምቀት የቦታው ምልክት መስቀል እንዲነሳ የኦሮሚያ ክልል ወስኗል Share/ሼር በምዕራብ አርሲ ሃገረ ስብከት አርሲ ነገሌ ቅድስት ቤተክርስቲያን ለበርካታ ዓመ
የአርሲ ነገሌ የመስቀል አደባባይና ባሕረ ጥምቀት የቦታው ምልክት መስቀል እንዲነሳ የኦሮሚያ ክልል ወስኗል Share/ሼር በምዕራብ አርሲ ሃገረ ስብከት አርሲ ነገሌ ቅድስት ቤተክርስቲያን ለበርካታ ዓመታት በመስቀል አደባባይና ባሕረ ጥምቀት ትጠቀምበት የነበረበት ይዞታዋ ላይ በርካታ አመታት የቦታው ምልክት የሆነው መስቀል እንዲነሳ የክልሉ መንግስት ወስኗል፡፡ ይህ አሳፋሪ ድርጊት ነው፡፡ መልስ ያጣው የመስቀሉ ጉዳይ ... ባለፈው በጽንፈኞች በኃይልና በጉልበት አንስተውት የነበሩ ቢሆንም ሕዝበ ክርስቲያኑ በላቀ መንፈሳዋ ወኔን ተላብሰው መልሰው መትከላቸው አይዘነጋም፡፡ የአርሲ ነገሌ የአደባባይ መስቀል ለበርካታ ዓመታት መንግሥት አነሳዋለሁ ምዕመናን አይነሳም በሚል ሰጣ ገባ እስከ ፌደራል ድረስ በመሄድ ባለበት ይቆይ አይነካ የተባለበት ደብዳቤ እንደሚገኝ መረጃዎች እየጠቆሙ ለኦርቶዶክስ ካላቸው የከፉ ጥላቻ የተነሣ መስቀል ይነሳ ብለው ወስነዋል፡፡ ታሪክን የመደለዝ ፀረ ኦርቶዶክስ እንቅስቃሴ ስለሆነ እንቃወማለን ፥ እንቃወማለን፡፡ (ከፈለገ ጎርጎርዮስ ገጽ የተወሰደ) #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#ይኩነኒ_በከመ_ትቤለኒ_ (#እንደ_ቃልህ_ይሁንልኝ_)፤ #ታኅሣሥ_22_ብሥራት_ … በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው
+4
#ይኩነኒ_በከመ_ትቤለኒ_ (#እንደ_ቃልህ_ይሁንልኝ_)፤ #ታኅሣሥ_22_ብሥራት_ … በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ፡፡ …… መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት። መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ያጸናሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና። ማርያምም። እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች፡፡ መልአኩም ከእርሷ ሄደ… /የሉቃስ ወንጌል 1፥26-38/ ይህቺም እለት የበዐላት ሁሉ በኵር ናት፤ በእርሷም የዓለም ድኅነት ተጀምሯልና ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስም ከቸር አባቱና ይቅር ባይ ከሆነው ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክብር ምስጋና ለዘላለሙ ይሁን አሜን፡፡ /ስንክሳር ዘታኅሣሥ 22/ በመዲና ከተማችን በአዲስ አበባ ታኅሣሥ_22_ብሥራት_የሚከበርባቸው፤ ፠ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል (ብሥራተ ገብርኤል) ፠ መንበረ ፓትርያርክ ቅዱስ እንጦንስ (ኋላ ቅድስት ማርያም እየተባለ በመጠራት ላይ ያለ) ሲሆን በታላቁ ደብራችን በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ካልዕ መልክአ ቅዱስ ገብርኤልን በማኅሌት በመቆም ይከበራል፡፡ #በፌስቡክ_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ https://t.me/med

SHAREEEEEEE, SHAREEEEEEE፤ እንወያይበት፡፡ ✣✤✣ #ክብር_ለሚገባው_ክብርን_እንስጥ_ለቅዱሳት_ሥዕላት_፡፡ (ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ፤ በማስተዋልም እንጓዝ) በቤተ ክርስቲያናችን ክብር
+3
SHAREEEEEEE, SHAREEEEEEE፤ እንወያይበት፡፡ ✣✤✣ #ክብር_ለሚገባው_ክብርን_እንስጥ_ለቅዱሳት_ሥዕላት_፡፡ (ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ፤ በማስተዋልም እንጓዝ) በቤተ ክርስቲያናችን ክብር ከሚገባቸውና በቅድስና ከሚጠሩት መካከል ቅዱሳት ሥዕላት አንዱና ዋነኛው ናቸው፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ ክብረ በዓላት በይበልጥም በጥምቀት በዓል ላይ፤ በተለይ በባነርና በቲሸርት ላይ የሚታተሙ ቅዱሳት ሥዕላት እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ በባነርና በቲሸርት ላይ የሚታተሙ ቅዱሳት ሥዕላት ለፀሐይ፣ ለአቧራ፣ ለዝናብ፣ … የተጋለጡ፣ የሚሰቀሉበት ቦታም መጥፎ ሽታ ያለበትና ለቅዱሳት ሥዕላት አመቺ ያልሆነ፤ እንዲሁም ከክብረ በዓሉ በኋላም ተጣጥፈው የሚቀመጡ ስለሆነ፤ የታቦታት መተላለፊያ መንገዶችን የምታስውቡ የተለያዩ የወጣት ማኅበራት ወንድሞቻችንና እቶቻችን በባነርና በቲሸርት ላይ በዓሉን የሚገልጹ ትዕይንቶችና ጥቅሶችን እንጂ ቅዱሳት ሥዕላትን እንዳታትሙ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስም እናሳስባለን፡፡ ሌሎቻሁም ይህን መልእክት ላልሰማ አሰሙ!!!፡፡ (የለጠፍናቸው ፎቶች፤ የቀ.ደ.ሰ. መድኀኔ ዓለም ታቦት ከሚጓዝባቸው መንገዶች መካከል በፎቶ ካሜራ ዓይናችን ላይ የገቡልን ናቸው፤ ልብ በሉ በአጠቃላይ ታቦታት በሚያልፉባቸው መንገዶች ሁሉ ላይ የሚሰቀሉትን ቅዱሳት ሥዕላት!!!) #በፌስቡክ_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ https://t.me/medihanaelem

ለእመ አምላክ ፥ ለወላዲተ አምላክ፥ ለቅድስት ድንግል ማርያም ወርኀዊ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን ፥ አደረሳችሁ፡፡ (ፎቶው ላይ የምትመለከቷት፤ ደብረሲና ማርያም 700 ኛ ዓመቷን ኅዳር 21 ቀን
+3
ለእመ አምላክ ፥ ለወላዲተ አምላክ፥ ለቅድስት ድንግል ማርያም ወርኀዊ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን ፥ አደረሳችሁ፡፡ (ፎቶው ላይ የምትመለከቷት፤ ደብረሲና ማርያም 700 ኛ ዓመቷን ኅዳር 21 ቀን 2012 ዓ.ም ያከበረች ናት፤ የተመሠረተችው በ1312 ዓ.ም. በአፄ ዐምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ የምትገኘው ከጎንደር ከተማ በ64 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ጎርጎራ ከተማ ጣና ባሕር ዳር ላይ ነው፡፡ #በፌስቡክ_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ https://t.me/medihanaelem

#ከሰይጣን_ጋር_የተደረገ_ቃለ_ምልልስ (ተዋስኦተ ጳውሊ ምስለ ሰይጣን)፤#ክፍል#፬_ (#ሰይጣን_የቅዱሳን_መላእክትን_ቃል_ምሥጢር_እንደሚሰማና_ #የሰማው_ከመደረጉ_በፊት_ለሰዎች_በመናገር_እንደሚያስት፤ #ሰይጣን_ከተፈጠረ_ጀምሮ_በዘመን_ብዛት_ሰውን_ያሚያስትበት_ብዙ_ጥበብ_እንዳለው፤ #የክርስቶስ_ሰው_መሆን_ከሰይጣን_የተሰወረ_እንደነበር) +አባ ጳውሊ፤ ወደ ሰማይ ወጥታችሁ የመላእክትን ቃል ትሰማላችሁን? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ ፈጽመን አንወጣም አለው፡፡ ++አባ ጳውሊ፤ ስለምንድነው የማትወጡት? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ ከክብራችን ከተዋረድን በኋላ በቧለሟልነት ሥልጣን ወደዚያ እንቀርብ ዘንድ አይፈቀድልንም አለው፡፡ +አባ ጳውሊ፤ ሰዎች እናንተ ወደ ሰማይ እንደምትወጡና ከመላእክት ጋር እንደምትነጋገሩ የሚናገሩት ዋሽተው ነውን? አለው፡፡ ሰይጣን፤ መላእክት ከምስጋና በቀር አይናገሩምና አዎን ዋሽተው ነው አለው፡፡ ++አባ ጳውሊ፤ እንግዲያ ከመደረጉ በፊት አስቀድመህ ለሳኦል ምሥጢር የገለጥክለት በምን አውቀህ ነው? አለው፡፡ /፩ሳሙ.፳፰፥፲፯/ ዲያብሎስ፤ እግዚአብሔር ለሳሙኤል ሲነግረው ሰምቼ ነው አለው፡፡ /፩ሳሙ.፲፮፥፩) እግዚአብሔር ለመላእክቶቹ ምሥጢር ሲነግራቸው እኛም ባለንበት ሆነን እንሰማለን፡፡ ያን ጊዜ ፈጥነን ሄደን ከመደረጉ በፊት ለሰዎች እንነግራቸዋለን፡፡ ሰዎች ሁሉ በየሀገሩ እኛ የነገርናቸውንና በሕልም ያሳየናቸውን ይናገራሉ አለው፡፡ +አባ ጳውሊ፤ ሰዎች ነገርህን እንደምን አምነው ይቀበሉሃል? የመልክህን ክፋት የመዓዛህን ክርፋት አያውቁምን? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ ሰዎች ሁሉ እንደ አንተ ክፉ መሰሉህ? ለአንተ ክፉ መስዬ እታይሃለሁ እንጂ በዚህ ዓለም መዓዛዬን ለማሽተትና መልኬን ለማየት እኔን የሚሹ ብዙ ሰዎች እንዳሉ እነግርሃለሁ፡፡ እነርሱ ወደ እኔ መጥተው እገለጽላቸው ዘንድ ይለምኑኛል እንጂ እኔ ወደ እነርሱ አልሔድም አለው፡፡ ++አባ ጳውሊ፤ ሰዎች ስለምን ይወዱሃል? ይህ የሚሆነው ለምንድን ነው? ዲያብሎስ፤ እኔን ለማየት በሚፈልጉት መልክ ተመስዬ በመገለጽ ስለማስደስታቸው ነው፡፡ +አባ ጳውሊ፤ መልክህን መለወጥ እንደምን ይቻልሃል አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ ይህ የሚያስደንቅ አይደለም ሰይጣን የብርሃን መልአክን ይመስላል ብሎ ጳውሎስ የተናገረውን አልሰማህምን፡፡ /፪ቆሮ.፲፩፥፲፬/ ++አባ ጳውሊ፤ የማታውቀውን ምሥጢር ማስመሰል እንደምን ይቻልሃል አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ #ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በዘመን ብዛት የሰበሰብኩትና የማውቀው ብዙ ጥበብ አለኝ፡፡ #ነገር ግን የክርስቶስ ሰው መሆን ብቻ ተሰወረብኝ እንጂ አለው፡፡ +አባ ጳውሊ፤ የክርስቶስ ሰው መሆን ስለምን ተሰወረብህ? ዲያብሎስ፤ ከእኔ የተሰወረበትን ምክንያት አላውቅም፡፡ ነገር ግን አውቄስ ቢሆን ክፉና በጎ ለይተው ያላወቁ ብዙ ሕፃናትን በሄሮድስ አድሬ ባላስገደልኩም ነበር አለው፡፡ ++አባ ጳውሊ፤ በገዳመ ቆሮንቶስ አንተ ፈትነኸዋልና አላውቅም አትበል አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ በሰውነቱ ስለሚሠራው ሥራ እንደ ነቢይ፥ እንደ ንጉሥ ይመስለኝ ነበርና ባውቅም እጠራጠር ነበር፡፡ ስለዚህ እፈትነው ዘንድ በእርሱ ላይ ተነሳሁ አለው፡፡ +አባ ጳውሊ፤ እርሱ በእውነት አምላክ መሆኑን ያወቅኸው መቼ ነው አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ኃይሌን እስከሚያደክመው ድረስ አላወቅሁም ነበር፡፡ መላእክት ሲያመሰግኑት፥ ሙታን ሲነሡ፥ ምድር ሲነዋወጥ፥ ፀሐይ ሲጨልም አየሁ፤ ያን ጊዜ የዓለም ብርሃን፥ የፍጥረታት ፈጣሪ እርሱ በመስቀል ላይ እንደተሰቀለ አወቅሁ አለው፡፡ #የሰይጣናት_አለቃና_ታዛዥ_እንዳላቸው፤ #ገሃነም_ስለመኖሩና_ዲያብሎስ_ለምን_ንስሐ_እንደማይገባ) #ክፍል_፭.…#ይቀጥላል_ይጠብቁን/ #በፌስቡክ_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ https://t.me/medihanaelem