en
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Open in Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 399 subscribers, ranking 5 564 in the Religion & Spirituality category and 2 183 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 399 subscribers.

According to the latest data from 30 June, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 21 over the last 30 days and by 1 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 21.61%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 10.23% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 327 views. Within the first day, a publication typically gains 1 576 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 17.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 01 July, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

15 399
Subscribers
+124 hours
+307 days
+2130 days
Posts Archive
ኅዳር 24 እንኳን ለ የ24ቱ_ካህናተ_ሰማይ(ሱራፌል)_በዓል እና በቆብ አያትና የልጅ ልጅ የኾኑት #አቡነ_ተክለሃይማኖትና_አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_ከካህናተ ሰማይ ጋር #የሥላሴን መንበር ላጠኑበት ዕለት በሰላም አደረሳቹህ ፡፡ #Share ያድርጉ ካህናት ሰማይ ከሠራዊተ #ሩፋኤል (ሊቃናት) ሃያአራት ሊቃናት መርጦ በመንበረ ስብሐት በመጋረጃዋ ውስጥ ዙርያዋን ክንፍ ለክንፍ ገጥሞ አቁሟቸዋል፡፡ ሕዝ 1 ፥11-12 ※ስማቸውን #ካህናተ_ሰማይ አላቸው የእሳትና የወርቅ ጽና አስያዛቸው ፤ የብርሃን አክሊል ጳዝዮን ከሚባል የብርሃን ዘውድ ደፋላቸው የብርሃን ዘንግ ማኀተሙ መስቀል የሆነ አስያዛቸው ፤ የብርሃን ላንቃ ኀብሩ መብረቅ የመሰለ አለበሳቸው ፡፡ ‹‹በዙፋኑ ዙርያ ሀያአራት ዙፋኖች ነበሩ፤ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሀያ አራት ሽማግሌዋች ተቀምጠው ነበር›› ዮሐ ራዕ 4፥-5 ካሕናተ ሰማይ ( ሱራፌል ) የሐዲስ ኪዳን ካህናት ምሳሌዎች ናቸው ፡፡ እነዚያ በሰማይ ሲያገለግሉ የሐዲስ ኪዳን ካሕናት ደግሞ በምድር ያገለግላሉ ፡፡ ሰማውያኑ አክሊል ተቀዳጅተው ፣ መብረቅ ለብሰው ሲያገለግሉ ምድራውያኑ ደግሞ ለአክብሮተ ወንጌል ልብሰ ተክህኗቸውን ለብሰው ማዕጠንተ ወርቃቸውን ይዘው ጸሎታችንን ለማሳረግ ሲወጡ ሲወርዱ ይኖራል ፡፡ እነዚህ መላእክት ለምሕረት ወደዚህ አለም እንደሚመጡ ከልዑለ ቃል ኢሳይያስ እንረዳለን ይህም እግዚአብሔር ኢሳይያስን ይቅር ብሎ ሃብተ ትንቢትን ሲሰጠው የላከለት ከሱራፌል አንዱን ነው ፡፡ ኢሳ 6 ፥ 5 ※እነዚህም በአንድ ላይ በአጠኑ ጊዜ ከማዕጠንታቸው የሚወጣው ጢስ መልኩ #መብረቅ ፤ ድምጹ ነጎድጓድ ፣ መዓዛው መልካም የሆነ ነው ፡፡ ‹‹ ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሠዊያው አጠገብ ቆመ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሠዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምርው ብዙ ዕጣን ተሰጠው ፤ የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ወጣ››ዮሐ ራዕ 8 ፥3-5 ※የሚያጥኑት ምንድን ነው ቢሉ የጻድቃን ጸሎት ፤ የሰማዕታት ገድል ፣ የደጋግ ሰዎች ምግባር ነው ፡፡ በእናንተ እየጣጠነ ወደ እኔ ያርግ ( ይድርስ ) ብሏቸዋልና ፡፡ ያለ እነርሱም አቅራቢነት ጽድቅና ምጽዋት ወደ እግዚአብሔር አይቀርብም፡፡ የሥላሴን መንበር ካጠኑ ቅዱሳን ውስጥም ፤ ለምሳሌም ፤ በቆብ አያትና የልጅ ልጅ የኾኑት #አቡነ_ተክለሃይማኖትና_አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር አጥነዋል ፨ አቡነ ዮሴፍ ዘጂፋት፣ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ እንዲሁ አጥነዋል ፡፡ #Share ያድርጉ ፨ካህናተ ሰማይ የዐውዶ ሡራሄ፤ ሎቱ ለባህቲቱ ይደሉ ስባሔ፨ /ሰዐታት/ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

በሰንበት ት/ት ቤቱ እና በደብሩ መካከል በባለፉት ጊዜያት ተፈጥሮ በነበረው አለመግባባት ወደ ስምምነት እንድንመጣ ጉዳዩ ሲጀመር በሽምግልና ፣ ኋላም ደግሞ በሚዲያም ጭምር ውጤት እንዲመጣ ትልቁን አስተዋጽኦ ካደረጉት ወንድሞቻችን መካከል መሪጌታ ጋዜጠኛ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ዋናው እና ተጠቃሹ ናቸው፡፡ በመጣውም ውጤት የደብሩ አስተዳደር ከፍቶት የነበረውን ማንኛውም አይነት ክስ እንዲያቋርጡ ተስማምተን የነበረ ቢሆንም ‹‹ ስሜን አጥፍቷል ›› በሚል ምክንያት የተከፈተው የመሪጌታ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ክስ አልተዘጋም፡፡ በዚህም ምክንያት ምንም እንኳን ጉዳዩ በሀገሪቱ የሚዲያ ህግ ባያሳስርም ወንድማችን ታስሮ በ10,000.ብር ዋስ እንዲፈታ ተደርጓል፡፡ ቢሆንም ግን ሁላችንም ሀገራችን ኢትዮጵያን እንዴት አድርገን ለልጆቻችን ማስተላለፍ አለብን የሚል ሃገራዊ አጀንዳ እያሰብን እየጸለይን ባለንበት በዚህ ወቅት ፣ በፍቅር ማገልገል እንጂ መካሰስ በማይጠቅምበት በዚህ ጊዜ እንዲህ ባሉ አጀንዳዎች መጠመድ አላስፈላጊ በመሆኑ ይህ የክስ አጀንዳ ዳግም እንዳይነሳ ክሱን የከፈታችሁት የደብራችን አስተዳደር በአውደ ምህረት በተናገራችሁት መሰረት በአስቸኳይ እንድታቋርጡ እና በሁሉም አካላት ርብርብ የመጣውን ትልቁን ስራችንን እንድንጀመር እናሳስባለን፡፡ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

#በጽዮን_ስም_የተመሠረቱና_ዐቢይ_ዓመታዊ_ክብረ_በዓላቸው_ኅዳር_21_የኾኑ፤ ✣ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አኵሱም ደብረ ጽዮን ማርያም (ከክርስቶስ ልደት 980 ዓመታት በፊት በቀዳማዊ አፄ ምኒልክ ዘመን ታቦቷ የመጣው) ✣ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አዲስ ዓለም ደብረ ጽዮን ማርያም (በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ተመሠረተች) ✣ዝዋይ ደብረ ጽዮን ማርያም (ደቡብ ሸዋ) ✣ሳዶቅ አምባ ማርያም (በ1670 ዓ.ም. በአባ ሳዶቅ የተመሠረተች ፥ ሰሜን ተራሮች) ✣እንፍራንዝ ደብረ ጽዮን ማርያም (ጥንታዊዋ ደብር) ✣ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ደረስጌ ደብረ ጽዮን ማርያም (በወርቅና በዕንቊ ተደርጋ በራስ ውቤ የታነጸች፤ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ የነገሠባት፤ ስሜን፣ ራስ ደጀን አጠገብ) ✣ ደብረ ጽዮን ማርያም (ነቀምት) ✣ ደብረ ጽዮን ሰላም አድርጊው ቅድስት ማርያም (ባሕርዳር) ✣ አርባ ምንጭ ደብረ ጽዮን ማርያም ✣ ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ማርያም (እንግሊዝ ፥ ለንደን) /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

ኅዳር 21 ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን ወይም ታቦተ ሕጉ ) ጽዮንን ክበቧት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ ግንቦቿንም ቅጠሩ፥ አዳራሿን ተመልከቱ፥ በብርታቷ የልባችሁን ተስፋ አኑሩ፡፡ /መዝ. 47፥12/ share እና like ያድርጉ #ኅዳር_21_የታቦተ_ጽዮን_(#ጽላተ_ኪዳን_ወይም_ታቦተ_ሕጉ_) #ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_የምናከብርበት_ምክንያት_፤ ፩ኛ. በሊቀ ካህናት ኤሊ ዘመን በሕዝበ አስራኤል(በአፍኒን ፊንሐስ) ኀጢአት ምክንያት፤ ታቦተ ጽዮን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካ፤ ዳጐን የተባለ የአሕዛብ ጣዖትን ቀጥቅጣ አድቅቃ ወደ እስራኤል የተመለሰችበት በመኾኑ፡፡ (1ሳሙ. ከ1-6) ፪ኛ. ታቦተ ጽዮን መፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን ወዳሠራው ቤተ መቅደስ (በዓለም ላይ እስካሁን ያልታየ ድግስ ደግሶ) የገባችበት እለት በመኾኑ፡፡ / (1ኛ ነገ. 8፥2፣ 2ኛ ዜና. 5፥1፣ ስንክሳር ዘሐምሌ 23) ፫ኛ. በቀዳማዊ አፄ ምኒልክ (ዕብነ ሐኪም) አማካኝነት ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር በ318ቱ ሌዋውያን ካህናት ፥ በሊቀ ካህናቱ አዛርያስ እየተመራች ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ የገባችበት በመኾኑ፡፡ /ክብረ ነገሥት፣ መጽሐፈ ምሥጢር፣ መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ አንድምታ መቅድም፣ …/ ፬ኛ. ነቢያት ስለ እመቤታችን በተለያየ ኅብረ መልክእና አምሳል (ዕዝራ በቅድስት ሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተ መቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ፣ ……) ያዩበት በመኾኑ፡፡ /ሕዝ. 44፥1፣ መጽ. ዕዝራ/ ፭ኛ. በንጉሥ አፄ ባዜን (በ4 ዓ.ም. አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ዋልድባን፣ ደብረ ዐባይን፣…… ሌሎችንም የኢትዮጵያ መካናት በስደት ከልጇ ጋር ባርካ አኵስም ጽዮን ላይ መጥታ የገባችበትና የባረከችበት፤ በወቅቱም አኵስምና አካባቢዋ በብርሃን ጎርፍ የተጥለቀለቁበት በመኾኑ፤ /ታሪከ ዋልድባ፣ ታሪከ አኵስም፣ ድርሳነ ዑራኤል፣ ....) ፮ኛ. በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱሳን ጻድቃን ነገሥታት አብርሐ ወአጽብሐ አማካኝነት መሥዋዕተ ኦሪት ሲሰዋባት የቆየችው አኵሱም ጽዮን፤ ጽዮን ማርያም ተብላ ባለ 12 መቅደሶች ባሏት በወርቅና በዕንቊ ያሸበረቀች ቤ.ክ ሠርተው ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበትና ክርስትና ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ የታወጀበት፡፡ ፯ኛ. በየጊዜው (በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ) ወደ ዝዋይ፣ ወደ ጣና ቂርቆስ፣ …… ተሰድዳ ቆይታ፤ ተመልሳ (ከዮዲት በኋላ በአንበሳ ውድምና፤ ከግራኝ በኋላ በአፄ ፋሲል የታነጹት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን) ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበት በመኾኑ፡፡ ፰ኛ. ወደ አኵሱም ደብረ ጽዮን ማርያም በቦታው ርቀት ለመሳለም ላልቻሉ ክርስቲያኖች ዳግሚት ደብረ ጽዮን በዳግማዊ አፄ ምኒልክ አዲስ አለም ላይ የተሠራችበት በመኾኑ፡፡ ፱ኛ. ሴቶችም ወንዶችም የሚያስቀድሱበትና ያለ ዐምድ ዕፁብ ድንቅ በኾነና በሃግያ ሶፍያ ቤ.ክ. አምሳል የተሠራው የጽዮን ቤተ ክርስቲያን (ኅዳር 21 ጾም በመኾኑ ቅዳሴ ቤቷ የተከበረው ግን ጥር 30 ቀን 1957 ዓ.ም ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ዐፄ ኀይለ ሥላሴ፣ እቴጌ መነን፣ የታላቋ ብሪታንያ ንግሥት ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥና ልዑል ፊልፕ በተገኙበት ቢሆንም) ቅዳሴ ቤት የተከበረበት በመሆኑ፡፡ ———— #ታቦተ_ጽዮንና #ጽዮን_ድንግል_ማርያም_፤ ፠ ታቦተ ጽዮንን፤ ሌዋውያን ከበዋት ውዳሴ፥ ዝማሬ ያቀርቡላት እንደነበረው፤ ✤ ዛሬም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካህናትና ምእመናን ከሩቅ እና ከቅርብ ተሰብስበው በማኅሌት፥ በዝማሬ፥ በቅዳሴና በውዳሴ ያከብሯታል፡፡ ፠ ታቦተ ጽዮን በደብተራ ኦሪት በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የኖረች ፥ የዮርዳኖስን ባሕር የከፈለች /ኢያሱ 3÷14-17/ ፥ ቅጽረ ኢያሪኮን ያፈረሰች /ኢያሱ 6÷1-21/ ፥ ዳጎን የተባለ የፍልስጤማውያንን ጣዖት የቈራረጠች /1ኛ ሳሙ. 5÷1-5/ ፥ በድፍረት ሊነካ የሞከረውን ኦዛን የቀሰፈች /1ኛ ሳሙ. 6÷6/ ፥ በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀምጣ ቤቱን በበረከት የመላች /2ሳሙ 6÷12/ ፥ ዳዊት የዘመረላት /2ሳሙ 6÷14/ ፥ ጠቢቡ ሰሎሞን በቤተ መቅደስ በክብር ያኖራት /1ኛ ነገ፣ 8÷1/ ፥ የእግዚአብሔር የክብር መገለጫ ናት፡፡ ✤ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያምም ንጽሐ ጠባይዕ ሳያድፍባትና የቅድስና ባሕርይ ሳይጎድፍባት፤ (በማየት፣ በመስማት፣ በመዳሰሰ፣ በማሽተት አንዳችም እድፍ ጉድፍ ሳያገኛት) በንጽሕናና (በኀልዮ፣ በነቢብ፣ በገቢር) በቅድስና ጸንታ በኀጢአት ሳትለወጥ ኖራለች፡፡ /ውዳሴ ማርያም፣ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም፤ አንቀጸ ብርሃን፣ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ/ እንዲሁም ‹‹ምክንያታዊ ነውር ኃጢአት የሌለብሽ የኀጢአት ሸታ ያልደረሰብሽ ንጽሕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና ክብርት በልዕልና አንቺ ነሽ» ብሏታል ጠቢቡ ሰሎሞን /መሓ. 4÷7/ ፠ ታቦተ ጽዮን በከበረ ወርቅ እንደተሸለመች ✤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ እና በንጽሐ ልቡና የተሸለመች ያጌጠች ናት፡፡ ፠ ታቦተ ጽዮን የቃለ እግዚአብሔር ማደሪያ እንደሆነች፤ ✤ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያምም ለአካላዊ ቃል ለእግዚአብሔር ወልድ ማደሪያ ኾናለች፡፡ «ድንግል ማርያም ሆይ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አምላክ ለእርሱ ማደሪያ ሆንሽ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀንሸ ቻልሽው ተሸከምሽው ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ለመወሰን የታመንሽ አንቺ ነሽ» /ውዳሴ ማርያም፣ ቅዱስ ኤፍሬም/ ——- **** በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቃል ኪዳኑ ታቦት መካከል ጥልቅ የሆነ ምሥጢራዊ ትምህርት አለ፡፡ /ዘፀ. 25÷9-20/፡፡ ይህንንም በተመለከተ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል ምሥጢሩን ከምሥጢር አመሳጥሮ፤ እንደ ሸማ አንከባሎ፥ እንደ ወርቅ ከብልሎ እንዲህ አስቀምጥታል፤ «ታቦተ አምላከ እስራኤል ጽዮን ዘነገደት ምድረ ኢሎፍሊ፤ ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኃን ማህጎሊ፡፡ አመ ነገደት ቊስቋመ በኀይለ ወልዳ ከሃሊ፤ ወድቁ አማልክተ ግብፅ መናብርተ ሰይጣን ሐባሊ፤ ወተኀጉሉ ኲሎሙ ዘቦሙ አስጋሊ፡፡ ወደ ኢሎፍሊ ምድር ተማርካ የሔደች የእስራኤል አምላክ የቃል ኪዳኑ ታቦተ ጽዮን የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው፡፡ ድንግል ማርያምም ሁሉን ማድረግ ከሚችለው ከልጇ ጋር ግብፅ ወደሚባል ሀገር በሔደች ጊዜ የሐሰተኛ ሰይጣን ዙፋኖች የሆኑ የግብፅ ጣዖታት ፈረሱ ጠንቋይ አስጠንቋይ ያላቸው ሁሉ ዐፈሩ» /ኢሳ 19÷1፣ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል/ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/