uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 790 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 384-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 253-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 790 obunachiga ega bo‘ldi.

14 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 236 ga, so‘nggi 24 soatda esa 0 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 9.49% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 9.51% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 1 498 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 501 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 13 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 15 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 790
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+1837 kun
+23630 kun
Postlar arxiv
‹‹ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡ ›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት ጥር 1 ፤ 7 እና 21 ሥርዓተ ፤ ፤ 2014 ዓ.ም በቀ.ደ.ሰላም መድኃኔዓለም ወደብረ ትጉኀን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ ጋብቻቹሁን የፈጸማችሁት የሰ.ት.ቤት ወንድምና እኅቶቻችን ፤ #አበራ ማሙዬ ከ ሰርካለም ደረጄ፤ #ሰሎሞን አጥሌ ከ እሥራኤል አስማማው ፣ #ቡሩክ አባቢ ከ እታበዛው ጉልች፤ የፈጸማቹሁትን ጋብቻ መድኀኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ የይሰሐቅንና የርብቃን ጋብቻ ያድርግላችሁ ፡፡ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ ÷ ያጣምራችሁ ÷ ያዋህዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኃላ ይከተላቹ፡፡ †<<ከተጋባቸሁ በኋላ ባልና ሚስት አንድ አካል ናችሁ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>> ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ቅዱስ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ፡፡ ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም እና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት

#ሰማዕቱ_ቅዱስ_መርቆሬዎስ_በሥዕሉ_ላይ_አድሮ_ቅዱሳን_የሆኑ_ባስልዮስንና_ጎርጎርዮስን_በመርዳት_ከሃዲውን_ንጉሥ_ዑልያኖስን_የገደለበት_ዕለት_ነው፡፡ #ራሱን_የሸጠው_ቅዱስ_ጴጥሮስ_ዕረፍቱ_ነው፡፡ #ከበሬ_ጋር_ተጠምደው_በማረስ_ሰማዕትነትን_የተቀበሉት_አቡነ_ሕፃን_ሞዐ_ልደታቸው_ነው፡፡ **ዳግመኛም በዚህ ዕለት፤ #ስብስትያኖስ_ሰባስትያኖስ_ሰማዕት_ጥር_25 ፠ በሕመም፥ በጭንቅ፥ በመከራ፥ በስቃይ፥ #በደዌ_ዳኛ፥ #በአልጋ_ቁራኛ_ላይ_ያላችሁ_ሁሉ በእምነት የሰማዕቱ የቅዱስ ስብስትያኖስን ስሙን ጥሩት፥ ገድሉን አድምጡ ተሻሹ፥ እምነቱን ተቀቡ፥ ቤተ ክርስቲያኑን ተሳለሙ #ፈዋሽ_ሰማዕት_ነው፡፡ #ፈትለ_ሥላሴ በመባል በሚጠራው ቤ.ክ. (ከአዲስ አበባ በሞጣ/በደብረ ድማኅ/ በኩል ወደ ባሕር ዳር ሲሄዱ አዴት ከተማ ከመድረስዎ በፊት ዠማ ወንዝ ለመድረስ ሲቃረቡ ያገኙታል)፡፡ ጥር 25 ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ይከበራል፡፡ እንዲሁም በጥንታውያን ታላላቅ ገዳማትና አድባራት የብራና ገድሉ ስላለ አስነብቡ፥ ተሻሹ፤ ፍጹም ፈውስን ታገኛላችሁ፡፡ ፠ ሰባ(ስብ)ስትያኖስ ሰማዕት፤ በስዕሉ ላይ እንደምንመለከተው በጽኑ ሕማምና ስቃይ ሰማዕትነትን የተቀበለ ነው፡፡ በተለይም በሕመም፤ በጭንቅ መከራ፤ በስቃይ ውስጥ ኾኖ ያለ ሰው አምላከ ሰብስትያኖስ ብሎ ለጠራኝ እደርስለታለሁ ብሎ በማይታበል ቃሉ እግዚአብሔር አምላካችን ቃል ኪዳን የሰጠው ሰማዕት ሲኾን ለጠሩትም ፈጥኖ የሚደርስ ሰማዕት ነው፡፡ ፠ የስብስትያኖስ አባቱ የሮሙ ንጉሥ ሲሆን ሃይማኖቱ የቀናና እግዚአብሔርንም የሚወድ ስለነበር ልጁን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማረ ፈሪሃ እግዚአብሔርን እያስተማረ አሳደገው፡፡ አባቱም ከሞተ በኋላ ከሃዲያኑ ዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ ነገሡ፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስንም አገረ ገዥ አድርገው ሾሙትና እንደ አባቱ እጅግ አድርገው አከበሩት፡፡ ፠ ቅዱስ ስብስትያኖስ በጥበብና በማስተዋል የሚጓዝ ነው፡፡ በተጋድሎ ሕይወቱ የተመሰገነ ሆነ፡፡ እግዚአብሔርም በእጆቹ የተለያዩ ተአምራትን ገለጠ፡፡ ድውያንን ይፈውሳል፤ በጸሎቱም የዕውራንን ዐይኖች ያበራል፡፡ በእንዲህም ዓይነት በተጋደሎ ሲኖር ዲዮቅልጥያኖስ እግዚአብሔርን ክዶ በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖችን እያሳረደ አብያተ ክርስቲያናትንም ማቃጠል ጀመረ፡፡ ይኸውም ከሃዲ አገረ ገዥ አድርጎ ሾሞትና በእጅጉ አክብሮት የነበረውን ቅዱስ ስብስትያኖስን አሁን ለጣዖት እንዲሰግድ ግድ አለው፡፡ ፠ ቅዱስ ስብስትያኖስ ግን የከሃዲውን ንጉሥ ትእዛዝ ቸል በማለት በፊቱ ቆሞ የጌታችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፤ ጣዖታቶቹንም ረገመበት፡፡ ንጉሡም በዚህ ጊዜ በታላቅ ቁጣ ሆኖ ቅዱስ ስብስትያኖስን ብዙ አሠቃየው፡፡ ከግንድ ጋር አሥሮ በብዙ ፍላጻዎች(ቀስቶች) ሰውነቱን አስነደፈው፤ በዚህም ጊዜ እንደሞተ አስበው ትተውት ሄዱ፡፡ ምእመናንም ሥጋውን ለመውሰድ በሌሊት ቢመጡ በሕይወት አገኙትና ወስደው በደሴት መካከል አስቀመጡት፡፡ ፠ ዲዮቅልጥያኖስም የቅዱስ ስብስትያኖስን በሕይወት መኖር ሲሰማ ድጋሚ አስመጣውና በብረት ዘንጎች ሲያስደበድበው ዋለ፡፡ ለብዙ ቀናትም እንዲሁ በብረት ዘንግ ሲያስደበድበው ቆየ፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስም በጥር 25 ቀን ነፍሱ ከሥጋው ተለየችና የሰማዕትነት ፍጻሜው ሆነ፡፡ ጌታችንም መታሰቢያውን ለሚያደርግና ስሙን ለሚጠራ የቸነፈር ሕመም፥ የሕመም ስቃይና መከራ እንዳይቀርበው ቃልኪዳን ሰጥቶታል፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስም ካረፈ በኋላ ውሉዱስና ለምትባል ለአንዲት ቅድስት ሴት ተገለጠላትና ቅዱስ ሥጋው ያለበትን ነገራት፡፡ እርሷም ወደ ከበሩ ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ መቃብር ወስዳ ቀበረችው፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Telegram... https://t.me/medihanaelem www.finotehiwotsundayschool.com .Facebook... https://youtu.be/3o4wj7Qqcaw... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w http://tiktok.com/@finotehiwot #ቅዱሳን #Saints #ክብረ_በዓላት #Feasts

#ዜና_እረፍት የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነችው እህታችን ርግበ ገ/ጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፋለች ። ሥርዓተ ቀብርዋም በዛሬው እለት ጥር 21 ከቀኑ 6 ሰዓት እስከ 7 ሰዓት የሚፈፀም ሲሆን
+1
#ዜና_እረፍት የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነችው እህታችን ርግበ ገ/ጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፋለች ። ሥርዓተ ቀብርዋም በዛሬው እለት ጥር 21 ከቀኑ 6 ሰዓት እስከ 7 ሰዓት የሚፈፀም ሲሆን በእህታችን ሥርዓተ ቀብር ላይ አጠቃላይ የሰንበት ት/ቤቱ አባላት በሰዓቱ በመገኘት እህታችንን እንድንሰናበታት ይሁን። የእህታችንን ርግበ ዳዊት ነፍስ ይማርልን።

ገብርኤል ሆይ ! ለሚጠሩት ፈጽሞ ለሚራራ ርኅሩኅ እሣታዊ ነበልባል አንጀትህ ሰላም እላለሁ ፡፡ ገብርኤል ሆይ ! አንተ በሁሉ ዘንድ አሸናፊ ነህ፡፡ አንተ በእግዚአብሔር ዘንድ መሥዋዕትን የሚያሰረጉ የ
ገብርኤል ሆይ ! ለሚጠሩት ፈጽሞ ለሚራራ ርኅሩኅ እሣታዊ ነበልባል አንጀትህ ሰላም እላለሁ ፡፡ ገብርኤል ሆይ ! አንተ በሁሉ ዘንድ አሸናፊ ነህ፡፡ አንተ በእግዚአብሔር ዘንድ መሥዋዕትን የሚያሰረጉ የካህናት ሰማይ ሱራፌል ጓደኛ ነህ፡ ምናልባት ሚካኤል ቢተካከልህ እንጂ እንዳንተ ማን አለ፡፡ #orthodox_quotes

እንኳን አደረሳቹሁ #ጥር21_አስተርእዮ_ማርያም_ ( #በዓለ_ዕረፍታ_ለማርያም_(ለሶልያና ) #እመቤታችን_በ64_ዓመቷ_ጥር_21_በ49ዓም_ያረፈችበት_ዕለት_መታሰቢያ_ክብረ_በዓል_ነው፡፡ #ተናገራ_ዕዝራ_ተናገራ_ዳዊት_ዘመራ፤ #ዕዝራ_በመሰንቆ_ዳዊት_በበገና_እያጫወቷት፤ #ሳታውቀው_አለፈች_ያንን_መራራ_ሞት፡፡ ፠ ጌታችን ለእናታችን ለቅድስት ማርያም ብዙ ቃልኪዳንን ከገባላት በኋላ፤ ቅድስት ነፍሷን ከክብርት ሥጋዋ ለይቶ በቃለ አቅርንት፥ በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት ደመና ጠቅሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ በአጎበር አድርገው እናትና አባቷ ወደተቀበሩበት ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲወስዷት አይሁድ አይተው፤ ልጇ ተነሳ፥ አረገ እያሉ ሲያውኩን ኖሩ አሁን ደግሞ እሷ ተነሳች፥ አረገች እያለ ሉያውኩን አይደለምን? ንዑ ናዓውያ ሥጋሃ ለማርያም /ኑ ሥጋዋን እናቃጥልባቸው/ ብለው ተነሱ፤ ለዚሁም ከመካከላቸውም ታውፊኒያ የተባለውን የጎበዝ አለቃ መረጡ፤ እርሱም የአልጋዋን ሸንኮር ሊያቃጥል ሲይዝ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማፀናት እራሷን ዘምበል አድርጋ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደነበረው አድርግለት ብላ አዘዘችው፤ እርሱም እጁን አድኖለታል፡፡ ከዚህ በኋላ ጌታችን ከመካከላቸው ነጥቆ ከገነት ከዕፀ ሕይወት ስር አኑሯታል፡፡ ….. ሐዋርያት የቀበሯት ግን ከ6 ወር በኋላ በነሐሴ 14 ነው ----›እርሱን እዚህ ያንብቡ ----›https://t.me/medihanaelem/6840፤ ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር እንዲሉ፡፡››ረፍታ ለሶልያና(ለማርያም) ወረደ ወልድ ዲበ እምዲበ ልዕልና ወረደ፡፡ #ሶልያና_የእመቤታችን_የማርያም_ሌላ_ስሟ_ነው፡፡ *የእመቤታችንን ዕረፍት ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ‹‹ሞትሰ ለመዊት ይደሉ፥ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኵሉ፡፡ /ሞት ለሚሞት ሰው ሁለ የተገባ ነው፥ የማርያም ሞት ግን ሁለን ያስደንቃል፡፡›› በማለት አደንቆ ጽፏል፡፡ *እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠቀሙበት ዘንድ የላይ ቤት (የግምጃ ቤት ማርያም) አብነትና የታች ቤት(የበዓታ) አብነትን ሁለቱንም አዘጋጅተንላችኋል፡፡ መልካም ክብረ በዓል፡፡ **ክብረ በዓሉ በሃገራችንና በዓለማችን ክፍሎች ባሉ የእመቤታችን አብያተ ክርስቲያናት የሚከብሩ ቢሆንም ግን፤ በልዩ ሁኔታ እንደ ጎንደር አዘዞ ሎዛ ማርያም ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ግን እንደ ጥምቀት በዓል፤ ከዋይዜማው ጀምሮ ወደ ጥምቀተ ተወርዶ በማደር ክብረ በዓሉ በልዩ ሁኔታ መከበሩን ልብ ይሏል:: /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ቅዱሳን #Saints #ክብረ_በዓላት #Feasts #Our_mother_Virgin_mary #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም https://youtu.be/3o4wj7Qqcaw...

፫. መሎጥ አምባ ጊዮርጊስ (አንድ መግቢያ እና መውጫ ያለው፤ ዐፄ ይኵኖ አምላክ ከመንገሡ በፊት በአያቱ መሐሪዉ አምላክ በግዞት የታሰረበት፤) አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ዋድላ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ዋድላ፡፡ ፬. ደብረ ድማኅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም፤ አድራሻ፤ ምሥራቅ ጎጃም ሃገረ ስብከት፥ ደብረ ድማኅ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር መንገድ (በሞጣ መስመር) → ደብረ ድማኅ፡፡ ፭. ሞጣ ጊዮርጊስ፤ አድራሻ፤ ምሥራቅ ጎጃም ሃገረ ስብከት፥ ሞጣ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር መንገድ (በሞጣ መስመር) → ሞጣ፡፡ ፮. መሐል ዘጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ አድራሻ፤ ምዕራብ ጎጃም (ባህር ዳር) ሃገረ ስብከት፥ ባሕር ዳር ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር፡፡ ፯. ባሕር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ አድራሻ፤ ምዕራብ ጎጃም (ባሕር ዳር) ሃገረ ስብከት፥ ባሕር ዳር ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር፡፡ ፰. ዋሻ ነጎድጓድ ጊዮርጊስ ገዳም፤ (በ16ኛው ክ/ዘመን በዐፄ ልብነ ድንግል ዘመን የተመሠረተ፤ ፈዋሽ ጠበል ያለበት) አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ መንዝ ላሎ ምድር፤ (ከአ.አ. 293 ኪ.ሜ.) ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መንዝ ላሎ → ወገሬ ከተማ → ዝንዝ (ጦጥ) (ዘብር)፡፡ ፱. ጎንደር እልፍኝ ጊዮርጊስ፤ (ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ) አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር፤ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት፡፡ ፲. ጎንደር ቀዳሜ አድባራት አበራ ጊዮርጊስ፤ (ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ) (በጎንደር ከተማ ታቦቱ ወደ ጥምቀተ ባሕር ወርዶ የሚከበርበት) አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር፥ ኮሌጅ፡፡ ፲፩. ደሴ ጊዮርጊስ፤ አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ደሴ ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ፡፡ ፲፪. ወራኢሉ ጊዮርጊስ፤ አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ወራኢሉ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ወራኢሉ፡፡ ፲፫. ግሸን ጊዮርጊስ፤ አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ አምባሰል ወረዳ፥ ግሸን፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ግሸን፡፡ ፲፬. ጋሞ ጎፋ ካምባ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ጋሞ ጎፋ ሃገረ ስብከት፥ ካምቦ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ጋሞ ጎፋ (አርባ ምንጭ) → ካምቦ፡፡ ፲፭. ቆላድባ ኳሬና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ደምቢያ ወረዳ (ማሩ ቀመስ)፥ ቆላ ድባ ከተማ ፤ (ከጎንደር ከተማ 35 ኪ.ሜ.) ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር አዘዞ አውቶቡስ ተራ → ቆላድባ፡፡ ፲፮. ደብረ ታቦር ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ደቡብ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ደብረ ታቦር ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ታቦር፡፡ ወይም፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር → ወረታ → ደብረ ታቦር፡፡ ፲፯. አገው ምድር ሳሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ አዊ ዞን ሃገረ ስብከት፥ አገው ምድር (አዊ) (ምዕራብ ጎጃም) ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → አዊ (በቡሬ፥ ባሕር ዳር መስመር)፡፡ ፲፰. ድሬደዋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ድሬደዋ ሃገረ ስብከት፥ ድሬደዋ ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ድሬደዋ፡፡ ፲፱. ደብረ ሲና ጉርጅ ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ሲያ ደብር፥ ዋዩ ወረዳ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አስኮ አውቶቡስ ተራ → ሆለታ/ኢንጪኒ/፡፡ ፳. ኢንጭኒ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ምዕራብ ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ኢንጪኒ፤ (ከአ.አ. በሆለታ 65 ኪ.ሜ.) ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን → ደነባ → ሲያ ደብር → በእግር፡፡ ፳፩. ኢንጭኒ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ምዕራብ ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ኢንጪኒ፤ (ከአ.አ. በሆለታ 65 ኪ.ሜ.) ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን → ደነባ → ሲያ ደብር → በእግር፡፡ ፳፪. ቆሪቻ ኮቲቻ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ምዕራብ ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ጮቢ ወረዳ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አስኮ አውቶቡስ ተራ → በአምቦ መስመር (ጊንጪ) → ጮቢ → ቆሪቻ ኮቲቻ፡፡ ፳፫. ጊዶሌ የጋርዱላው (የዐድዋው) ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ ፳፬. ያበደማን ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ ፳፭. ደንደገብ ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ ፳፮. አትርፎ ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ የአድራሻ ምንጭ /ገዳማትና አድባራት ገጽ/ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ቅዱሳን #Saints #ክብረ_በዓላት #Feasts https://youtu.be/3o4wj7Qqcaw...