cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኢትዮጵያ

ስለ ሀገራችን ታሪክ ፣ ባህል ፣ ጥንታዊ ቅርሶች ፣ ገዳማት ፣ መጎብኘት ስላለባቸው ስፍራዎች መረጃ ለማግኘት ካስፈለገ ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ ። ኢሉሚናቲን እናወግዛለን። የዚህ ቻናል አላማ ትውልዱ ሐይማኖቱንና ታሪኩን ያውቅ ዘንድ እና ሙሉ ትውልድ ይሆን ዘንድ ማገዝ ነው ። አንድነታችን ለህልዉናችን @HISCULHEROFETHIOPIA

Show more
Advertising posts
392
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-1430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ⚡️📌⚡️ አክፍሎት (ማክፈል) በሰሙነ ሕማማት ዕለተ አርብ ከስግደት በሗላ ምዕመናን በየቤታቸው ጥቂት ነገር ቀምሰው እስከ እሁድ /የትንሳኤ ሰዓት/ ይሰነብታሉ፡፡ ይህ አክፍሎት ይባላል ከአርብ እስከ ቅዳሜ ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ ማክፈል የብዙዎች ነው። አንዳንዶች ግን ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ፡፡ ይህም እመቤታችን፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ የጌታን ትንሳኤ ሳናይ እህል ውሃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤ መቆየታቸውን ተከትሎ የመጣ ትውፊት ነው ይህንን ትውፊት አስመልክቶ ሄሬ ኔዎስ፣ አውሳብዮስ የተባሉ ጸሐፍት፣ ሐዋሪያት በሰሙነ ሕማማት ከደረቅ ዳቦ እና ከትንሽ ውሃ በቀር እንደማይመገቡ እና ከሐሙስ ጀምረው እንደሚያከፍሉ ጽፈዋል ይህም ብቻ ሳይሆን ሐዋሪያት ሌሎቹንም እንድያከፍሉ እንዲያሳስቡና ከሐሙስ ጀምሮ ያልተቻላቸው ቢያንስ ከአርብ ጀምሮ እንዲያከፍሉ ማዘዛቸውን ጽፈዋል፡፡ የኛ ቤተክርስቲያን ትምህርትም ይሄው ነው፡፡ 👉 ምንጭ፦ ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት
Show all...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 📌 ቀዳም_ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ) የዐቢይ ጾም የመጨረሻዋ ቅዳሜ ብዙ ስያሜዎች አሏት፦ 👉 ቀዳም_ሥዑር፡- በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡ 👉 ለምለም_ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡ (የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡) 👉 ቅዱስ_ቅዳሜ፡- ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ (ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት ሚያዝያ 2004 ዓም)
Show all...
❮❮ ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ገነዝዎ ለኢየሱስ - ዮሴፍ ኒቆዲሞስም ጌታችን መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን ገነዙት ❯❯ 📜 ወንጌለ ማቴዎስ 27 📜 ⁵⁷ በመሸም ጊዜ ዮሴፍ የተባለው ባለ ጠጋ ሰው ከአርማትያስ መጣ፥ እርሱም ደግሞ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበረ፤ ⁵⁸ ይኸውም ወደ ጲላጦስ ቀርቦ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው። ⁵⁹ ጲላጦስም እንዲሰጡት አዘዘ። ዮሴፍም ሥጋውን ይዞ በንጹሕ በፍታ ከፈነው፥ ⁶⁰ ከዓለት በወቀረው በአዲሱ መቃብርም አኖረው፥ በመቃብሩም ደጃፍ ታላቅ ድንጋይ አንከባሎ ሄደ። ⁶¹ መግደላዊት ማርያምም ሁለተኛይቱም ማርያም በመቃብሩ አንጻር ተቀምጠው በዚያ ነበሩ። ⁶² በማግሥቱም ከመዘጋጀት በኋላ በሚሆነው ቀን፥ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ወደ ጲላጦስ ተሰበሰቡና፦ ⁶³ ጌታ ሆይ፥ ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ፦ ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ እንዳለ ትዝ አለን። ⁶⁴ እንግዲህ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው በሌሊት እንዳይሰርቁት ለሕዝቡም፦ ከሙታን ተነሣ እንዳይሉ፥ የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለችና መቃብሩ እስከ ሦስተኛ ቀን ድረስ እንዲጠበቅ እዘዝ አሉት። ⁶⁵ ጲላጦስም፦ ጠባቆች አሉአችሁ፤ ሄዳችሁ እንዳወቃችሁ አስጠብቁ አላቸው። ⁶⁶ እነርሱም ሄደው ከጠባቆች ጋር ድንጋዩን አትመው መቃብሩን አስጠበቁ።
Show all...
1
"ሮማውያን የሚሰቅሉትን ሰው ምን ያህል ዕርቃኑን እንደሚያዋርዱት አይሁድ በተግባር አይተው ስለሚያውቁ ጌታችን በዚህ በአሰቃቂ አሟሟት እንዲሞትና ‹እውነት እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ቢሆን ኖሮ ይህ ሁሉ መከራ ደርሶበት ይሰቀል ነበር?› እያሉ እንደ ማስረጃ በማቅረብ ‹ክርስቶስ አይደለም!› ለማለትና ክርስቲያኖችንም ለበዓል በመጣው ሕዝብ ፊት በጌታ መሰቀል ለማሸማቀቅ ነበር፡፡ እነርሱ ለማሸማቀቅ ብለው እንዲሰቀል ቢያደርጉም እኛ ግን በመሰቀሉ አፍረን አናውቅም፡፡ ‹‹የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን›› ፤ መመካት ቢያስፈልግም ‹‹ከጌታዬ ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ›› እያልን እንድናፍር ባዘጋጁት የጌታችን መሰቀል እንመካበታለን፡፡ (ገላ. ፲፮፥፲፬ ፩ቆሮ.፩፥፳፫)"
Show all...
#ሥርዓተ_ጸሎት_ወስግደት_ዘዓርብ_ስቅለት 👉🏽ዐርብ #ጠዋት በ፲፪ ሰዓት አቡን ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ነአምን ሕማሞ ለዘኢየሐምም፤ ርግዘተ ገቦሁ ነአምን፤ ወቅንዋተ እደዊሁ ነአምን፤ ዬ ዬ ዬ፤ ነአምን ሞቶ ወትንሣኤሁ። በመቀጠል "#ለከ_ሃይል" ይባላል። ከኦሪት ምንባብ እስከ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል። ምስባክ መዝ: ፳፮ ፣ ፲፪ እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ፤ ወዘኢየአምር ነበቡ ላዕሌየ፤ እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ። ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በዜማ በኅብረት ይበሉ:- 👉🏽ማቴ: ፳፯ : ፩ - ፲፬ ከተነበበ በኋላ ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት ይስቅልዎ ለኢየሱስ ዲበ ዕፀ መስቀል። 👉🏽ማር: ፲፭ : ፩ - ፭ ከተነበበ በኋላ ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽእዎ አፍአ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ። 👉🏽ሉቃ: ፳፪ : ፷፮ - ፸፩ ከተነበበ በኋላ ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽዕዎ ለኢየሱስ ወመጠውዎ ለጲላጦስ። 👉🏽ዮሐ: ፲፰ : ፳፰ - ፵ ከተነበበ በኋላ ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽዕዎ ለኢየሱስ ወነበረ ዐውደ ሶቤሃ። ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"#ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚያም በመቀጠል #የሰዓቱን "#መልክዐ_ሕማማት" ያድርሱ። 👉🏽ዐርብ #ጠዋት በ፫ ሰዓት አቡን ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) አርዑተ መስቀል ፆረ (፪)፤ ይስቅልዎ ሖረ፤ ዬ ዬ ዬ፤ ከመ ኪያነ ይቤዙ እግዚእ ኮነ ገብረ። በመቀጠል "#ለከ_ሃይል" ይባላል። ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል። ዲያቆኑ መዝሙር ፴፬ትን ፫ ቦታ ከፍሎ በውርድ ንባብ ይበል። በቀመጠል ካህኑ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል እየተሰገደ:- ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ፤ ጽብኦሙ እግዚኦ ለእለ ይጸብኡኒ፤ ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ። ይ.ዲ ምስባክ:- መዝ: ፳፩ : ፲፮ ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን፤ ወአኃዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን፤ ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን። 👉🏽ማቴ: ፳፯ : ፲፭ - ፲፯ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ፫ቱ ሰዓት አኃዝዎ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ። 👉🏽ማር: ፲፭ : ፮ - ፲፭ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ፫ቱ ሰዓት አሕየወ ሎሙ በርባንሃ ወወሀበ ሎሙ ኢየሱስሃ ይስቅሉ። 👉🏽ሉቃ: ፳፫ : ፲፫ - ፳፭ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ፫ቱ ሰዓት ወሰድዎ ለኢየሱስ ውስተ ዓውደ ምኲናን። 👉🏽ዮሐ: ፲፱ : ፩ - ፲፪ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ፫ቱ ሰዓት ቀሠፎ ጲላጦስ ለኢየሱስ ወመጠዎሙ ይስቅልዎ። ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"#ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚያም በመቀጠል #የሰዓቱን_መልክዓ_ሕማማት ያድርሱ። #ዐርብ_በስድስት_ሰዓት አቡን ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ተሰቅለ (፫)፤ ወሐመ ቤዛ ኲሉ ኮነ፤ ዬ ዬ ዬ፤ በመስቀሉ ቤዘወነ እሞት ባልሐነ። በመቀጠል "#ለከ_ሃይል" ይባላል። ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል። ዲያቆኑ ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ከገላትያ በውርድ ንባብ ይበል። ከዚያም ካህኑ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል በዜማ እየተሰገደ:- ለመስቀልከ ንሰግድ ኦ ሊቅነ፤ ወለትንሣኤከ ቅድስት ንሴብሕ ኲልነ፤ ይእዜኒ ወዘልፈኒ። ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፳፩ : ፲፮ ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ ወኆለቊ ኲሎ አዕፅምትየ ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በኅብረት ይበሉ:- 👉🏽ማቴ: ፳፯ : ፳፯ - ፵፭ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ፮ቱ ሰዓት አልበስዎ አልባሲሁ ለኢየሱስ ወወሰድዎ። 👉🏽ማር: ፲፭ : ፲፮ - ፴፫ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ፮ቱ ሰዓት ዐበጥዎ ለስምኦን ከመ ይፁር መስቀሉ። 👉🏽ሉቃ: ፳፫ : ፳፯ - ፵፬ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ፮ቱ ሰዓት ሰቀልዎ ለኢየሱስ በቀራንዮ መካን። 👉🏽ዮሐ: ፲፱ : ፲፫ - ፳፯ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ፮ቱ ሰዓት ቀትር ሶቤሃ ሊቃነ ካህናት ሰቀልዎ ለኢየሱስ ማዕከለ ፪ኤ ፈያት። ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"#ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚያም በመቀጠል የሰዓቱን መልክአ ሕማማት ያድርሱ። #ዐርብ_በዘጠኝ_ሰዓት አቡን ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ሶበ ሰቀልዎ(፫) ለእግዚእነ፤ ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ፤ ዬ ዬ ዬ፤ አድለቅለቀት ምድር ወተከሥቱ መቃብራት። በመቀጠል "#ለከ_ሃይል" ይባላል። ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ምንባብ ይነበባል። ከዚያም በኃላ ካህኑ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል በዜማ እየተሰገደ:- ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ፤ ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ፤ ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ። ዲያቆኑ ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ከ ግብረ ሕማማት በውርድ ንባብ ይበል። በመቀጠልም ሶስት ካህናትና አንድ ዲያቆን ጥቁር ልብሰ ተክህኖ ለብሰው በስዕለ ስቅለት ፊት ይቀመጡ፤ ከአንዲት መብራት በቀር ሌላውን ያጥፉና አንድ ግምጃ በራሳቸውና ገፃቸው ላይ ያድርጉ (ምዕመናን ደግሞ በነጠላቸው ይሸፈኑ)። አንገታቸውን ዝቅ አድርገው በዕዝል ዜማ በታላቅ ድምጽ በሀዘንና በፍርሃት በለቅሶና በዕንባ ጭምር ካህኑና ሕዝቡ በመቀባበል "አምንስቲቲ"ንና "ተዘከረነ እግዚኦ"ን እያንዳንዱን ሦስት ሦስት ጊዜ ይዝለቁ። እንደገናም "አምንስቲቲ"ንና "ተዘከረነ እግዚኦ"ን እያንዳንዱን አንድ አንድ ጊዜ በመቀባበል በሁለት ዙር (አጠቃላይ ቁጥሩ ፲፪ እስኪሞላ ድረስ) ይበሉ። ዲያቆኑም በየክፍሉ በሐዘን ዜማ (በውርድ ንባብ) እያስገባ ያንብብ። ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል:- አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ አምንስቲቲ ሙዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል:- ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ፤ ተዘከረነ እግዚኦ ኦ ሊቅነ፤ ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ። ይ.ሕ በከመ ተዘከርኮ ለፈያታዊ ዘየማን እንዘ ሀሎከ ዲበ ዕፀ መስቀል ቅዱስ። ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፷፰ : ፳፮ ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ፤ ወአስተዩኒ ብሒዐ ለጽምዕየ፤ ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ። ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በኅብረት ይበሉ:- 👉🏽ማቴ: ፳፯ : ፵፮ - ፶ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ጸርሐ ኢየሱስ በቃሉ ወይቤ ኤሎሄ ኤሎሄ። 👉🏽ማር: ፲፭ :፴፬ - ፴፯ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ገዓረ ኢየሱስ በቃሉ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ። 👉🏽ሉቃ: ፳፫ : ፵፭ - ፵፯ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ከልሐ ኢየሱስ በቃሉ ወአማኅጸነ ነፍሶ ሶቤሃ። 👉🏽ዮሐ: ፲፱ : ፳፰ - ፴ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት አጽነነ ርእሶ ኢየሱስ ወይቤ ተፈጸመ ኲሉ። ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"#ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚያም በመቀጠል #የሰዓቱን_መልክዐ_ሕማማት ያድርሱ። #ዐርብ_በአስራ_አንድ_ሰዓት አቡን ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ንዜኑ (፫) ዘአምላክነ ኂሩተ ትሕትና ወየውሃተ ዘእንበለ ዐቅም፤ ዬ ዬ ዬ፤ እንዘ ይጼዕልዎ ኢጸዐሎሙ፤ እንዘ ያሐምምዎ ኢተቀየሙ። በዚህ ሰዓት "ለከ ሃይል፣ ኪርያላይሶንና መልክዐ ሕማማት" #የለም። ............. ምንጭ ፦ የአ/አ/ዩ/ሳ/ቴ/ፋ/ ግቢ ጉባኤ
Show all...
መጋቢት 27 የአምላካችን የክርስቶስ ነገረ ስቅለት   ✥•••••••••••●◉ ✞ ◉●•••••••••••✥ ❖ የነገሥታት ንጉሥ የሕይወት ራስ ኢየሱስ ክርስቶስን የአይሁድ ጭፍሮች የእሾኽ አክሊል ጐንጒነው በራሱ ላይ ደፍተውለታል፤ የእሾኽ አክሊል በመቀዳጀቱ ኦሪት ዘፍጥረት ላይ አዳምን አስቀድሞ ✍“ምድር እሾኽንና አሜከላን ታበቅልብኻለች” ብሎት ነበርና ያነን መርገም ደምስሶለት ለአዳም ክሷል፡፡ 📖ዘፍ 3፥18 ❖ ዳግመኛም አዳምና ሔዋን ምክረ ከይሲን ሰምተው የድል ነሺዎች አክሊል ተለይቷቸው ነበርና ያነን ሰማያዊ አክሊል እንደመለሰልን ለማጠየቅ፡፡ ❖ ይኽ ለካሳ አምላካችን ስለፈጸመው የድኅነት ምስጢር ቅዱሳት ደናግል በጥልቀት እንዲኽ አብራርተዋል ✍“አስተቀጸልዎ ከመዝ ለርእሰ ሕይወት አክሊለ ሦክ …” 👉የሕይወት መገኛ ርሱን የእሾኽ አክሊልን አቀዳጁት፤ መላእክትን የብርሃን ራስ ቁር የሚያቀዳጃቸው የነገሥታት ገዢ የሚኾን ርሱን የሾኽ አክሊል አቀዳጁት፤ በሾኽ አክሊልም ከራሱ ክፍል ያቆሰሉት ሺሕ ናቸው፤ ከራሱም ቊስሎች ደም እንደ ውሃ በዝቶ ፈሰሰ፤ ፊቱም ደምን ለበሰ ሰውነቱም በደም ተጠመቀ፤ የጽዮን ልጆች እናቱ ያቀዳጀችውን አክሊል ተቀዳጅቶ አዩት፤ ተድላ ደስታ የሚያደርግበትና የሙሽርነቱ ቀን ነውና። 📖መኃ 3፥11 ❖ … ነገርና ግን የሾኽ አክሊልን በመቀዳጀቱ በምድራችን ላይ የበቀሉትን አሜከላና እሾኽ ርግማንን አጠፋልን። 📖ዘፍ 3፥18 ❖ ራሱንም በዘንግ በመመታቱ የታላቁን እባብ ሰባቱን ራሶቹን ዐሥሩን ቀንዶቹን አጠፋልን። 📖ራእ 13፥1 ❖ ሊቁ ቅዱስ ኤራቅሊስም ስለፈጸመው ካሳ እንዲኽ አስተምሯል ✍“እንዘ ይትቄጸል አክሊለ ሦክ አብጠለ ኲነኔሁ ለቀኖተ ሞት ወእንዘ ቅንው ዲበ ዕፀ መስቀል ኢተዐርቀ እምነ መንበሩ…” 👉የእሾኽ አክሊል ደፍቶ የሞትን ሥልጣን ፍርድ አጠፋ፤ በመስቀል ላይ ተቸንክሮ ሳለ ከዙፋኑ አልተለየም፤ ከባሕርይ አባቱ ከአብ፤ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ አልተለየም፤ በምድር አይሁድ እንደ በደለኛ ሲዘብቱበት፤ መላእክት በሰማይ የከበረ ጌትነቱን ይናገሩ ነበር። 📚ቅዱስ ኤራቅሊስ ❖ እጆቹና እግሮቹ ስለመቸንከሩ አስቀድሞ በነቢዩ ዳዊት ዐድሮ በመዝሙር ላይ ✍“ብዙ ውሾች ከብበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዙኝ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ፤ ዐጥንቶቼ ኹሉ ተቈጠሩ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም” በማለት ውሻ ከአፉ ያወጣውን መልሶ ለምግብነት እንዲፈልገው፤ አይሁድም ኦሪትን እለፊ ካላት በኋላ ሲሠሯት በመገኘታቸው በውሻ መስሎ ትንቢት ያናገረባቸው ሲኾን፤ ይኽም ሊፈጸም ንጹሓት እጆቹና እግሮቹ በምስማር ከዕፀ መስቀሉ ጋር አያይዘው ቸንክረውታል፡፡  📖መዝ 21፥16 ❖ የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ሔዋን በእግሮቿ ወደ ዕፀ በለስን በማምራቷ በድላ ነበርና ለርሷ ካሳ ሊኾን ንጹሓን እግሮቹ ሲቸነከሩ፤ በእጆቿም በለስን በመቊረጧ ንጹሐ ባሕርይ አምላክ እጆቹ በችንካር ተቸንክረዋል፡፡ ❖ በመቸንከሩም ለ5ሺሕ 500 ዘመን በሰው ልጆች ላይ የሠለጠነ የሞት ችንካር ጠፍቶልናል፤ ምስጋና ይግባውና ኢየሱስ ክርስቶስ በመቸንከሩ ስለፈጸመው ካሳ ደናግል ሲተነትኑ ✍“ወበቅንዋቲሁ ሠበረ ለነ ቀኖተ ሞት …” 👉በመቸንከሩም የሞት ችንካርን አጠፋልን፤ ሔዋን በእግሮቿ ወደ ዕፀ በለስ ስለ ተመላለሰች እጆቹንና እግሮቹን በመቸንከር ከፍሏልና፤ በእጆቿም የበለስን ፍሬ ስለቈረጠች ፈንታ በእውነት የእግዚአብሔር ቃል በሥጋው ከመስቀል ዕንጨት ጋራ ተቸነከረ በማለት አስተምረዋል፡፡ ❖ መተርጒማን ሊቃውንት እንዳመሰጠሩት ጌታ በዕንጨት መስቀል ላይ መሰቀሉ ስለምን ነው ቢሉ፤ እሾኽ በሾኽ ይነቀሳል ነገር በነገር ይወቀሳል እንዲሉ በዕፀ በለስ ምክንያት የገባውን ኀጢአት በዕፅ ለማውጣት በዕፀ መስቀል ላይ ተሰቅሏል፡፡ ❖ ጌታችን ከምድር ከፍ ከፍ ብሎ ስለምን ተሰቀለ ቢሉ  ✍“እምከመ ተለዐልኩ እምድር እስሕብ ኲሎ ኀቤየ” 👉ከምድር ከፍ ከፍ ባልኊ ጊዜ ኹሉን እስባለኊ ብሎ ነበርና ይኽነን ሊፈጽም ነው። 📖ዮሐ 12፥32 ❖ ዳግመኛም ከምድር ከፍ ከሰማይ ዝቅ ብሎ መሰቀሉ “ኅሩይ ማእከለ እግዚአብሔር ወሰብእ” እንዲል አምላክ ወሰብእ ኾኖ እንዳስታረቀን ለማጠየቅ፡፡ ❖ በመጨረሻም ምድርን በኪደተ እግሩ እየተመላለሰ እንደ ቀደሳት፤ ዐየራትን ደግሞ ሥብ እያጤሱ አስተራኲሰውት ነበርና አየራትን ለመቀደስ ነው፡፡ ❖ ንጹሐ ባሕርይ ጌታችንን አይሁድ መስቀሉን አሸክመው ቀራንዮ ወደሚባል ቦታ ከወሰዱት በኋላ ኹለት ወንበዴዎችን በቀኝና በግራ አድርገው ጌታችንን በመኻከል ሰቅለውታል። 📖ማቴ 27፥38፤ 📖ማር 15፥27፤ 📖ሉቃ 22፥23፤ 📖ዮሐ 19፥18 ❖ ክፉዎች አይሁድ ይኽነን ያደረጉበት ምክንያት በክፋት ነው፤ ይኸውም በቀኝ የሚመጡ ሰዎች በቀኝ የተሰቀለውን ወንበዴ አይተው “ይኽ ምንድ ነው” ብለው ሲጠይቁ “ወንበዴ ነው” ይሏቸዋል፤ ከዚያም ጌታን “ይኽስ ምንድ ነው” ብለው ሲጠይቁ “ይኽስ ከርሱ ልዩ ነውን አንድ ነው እንጂ” ብለው ሰዎችን ለማሳሳት፤ በግራ የሚመጡ ሰዎች በግራ የተሰቀለውን ወንበዴ አይተው “ይኽ ምንድ ነው” ብለው ሲጠይቁ “ወንበዴ ነው” ይሏቸዋል፤ ከዚያም ጌታን “ይኽስ ምንድ ነው” ብለው ሲጠይቁ “ይኽስ ከርሱ ልዩ ነውን አንድ ነው እንጂ” ብለው ሰዎችን ለማሳሳት ያደረጉት ነው፤ ዳግመኛም አነገሥንኽ ብለውታልና ቀኛዝማች ግራዝማች ሾምንልኽ ለማለት ለመዘበት። ✍“ከዐመፀኞችም ጋር ተቈጥሯልና” የሚለው ትንቢቱን ሊፈጽም ሲኾን ምሥጢሩ ግን እኛን ከጻድቃን ጋራ አንድ ያደርገን ዘንድ ርሱ ከበደለኞች ጋር ተቈጥሯል፤ ሌላውም በዕለተ ምጽአት እኛን ኃጥኣንን በግራ ጻድቃንን በቀኝ ታቆማለኽ ሲያሰኛቸው ነበር። 📖ኢሳ 53፥12 📖ማቴ 25፥33፤ 📖ራእ 1፥7 ❖ በኹለት ወንበዴዎች መኻከል ከሰቀሉት በኋላ ጲላጦስም “የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ” የሚል ጽሕፈት በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው። 📖ዮሐ 19፥18-22 ❖ የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን “ርሱ የአይሁድ ንጉሥ ነኝ እንዳለ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለኽ አትጻፍ” ሲሉት፤ ጲላጦስም “የጻፍኹትን ጽፌአለኊ” ብሎ መልሶላቸዋል፤ ይኽነንም በሕማማት ድርሳኑ ላይ ሲተረጒሙት ✍“ወዝ መጽሐፈ ጌጋይ ዘጸሐፎ ጲላጦስ ወአንበሮ መልዕልተ ርእሱ ይደምስስ ለነ በኲሉ ጊዜ መጽሐፈ ዕዳነ ዘጸሐፉ አጋንንት” አዘጋጅ ዲ/ን ቡሩክ ይርጋ ዘዉብ
Show all...
🎚🎚🎚 እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን 🎚🎚🎚 🎚🎚🎚ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰኝ ያድርሳችሁ አሜን 🎚🎚🎚 ኆኅተ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት
Show all...
📜 - ጊዜ ስድስቱ ሰዓት አልበስዎ አልባሲሁ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ ። 📜 - ጊዜ ስድስቱ ሰዓት ዐበጥዎ ለስምዖን ከመ ይፁር መስቀሎ ። 📜 - ጊዜ ስድስቱ ሰዓት ሰቀልዎ ለኢየሱስ ማዕከለ ክልኤ ፈያት ። 📜 - ጊዜ ስድስቱ ሰዓት ቀትር ሶቤሃ ሰቀልዎ ለኢየሱስ በቀራንዮ መካን ።
Show all...
✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞   በነግሕ ጊዜ የሚነበብ ተዓምረ ማርያም # አምስቱ_የእመቤታችን ኃዘናት፦ 1• ከአምስቱ አንዱ አይሁድ እንዲገድሉህ በቤተ መቅደስ ስምዖን ትንቢት በተናገረ ጊዜ ነው፡ ሉቃ 2:34-35 2• ሁለተኛውም ሦስት ቀን በቤተመቅደስ ፈልጌህ ባጣሁህ ጊዜ ነው፡ ሉቃ 2:41-48 3 • ሦስተኛውም እግርህንና እጅህን አሥረው በጲላጦስ አደባባይ የገረፉህን ግርፋት ባሰብኩ ጊዜ ነው፡ ዮሐ 19:1 4 • አራተኛውም በዕለተ ዓርብ ራቁትህን ቸንክረው በሁለት ወንበዴዎች መካከል እንደሰቀሉህ ባሰብኩ ጊዜ ነው አለችው፡ ዮሐ 19:17-22 5• አምስተኛውም ወደ ሐዲስ መቃብር ውስጥ እንዳወረዱህ ባሰብኩ ጊዜ ነው፡ ዮሐ 19:38-42               ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
Show all...