cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

✝️ የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ኆኅተ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት ✝️

➺ " ዛቲ ይእቲ በትረ ዮሴፍ አረጋዊ " ይኽ በደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የኆኅተ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት የቴሌግራም አውታር ነው፡፡ youtube ➺ https://www.youtube.com/channel/UCZRaICOgLd5zp0_zc9a6BkQ መልእክት ካሎት ➺ @Biruk2010

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
1 037
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✍️"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል" 📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቀናችንን በጸሎት እንጀምር 📌 ስንክሳር ዘወርኀ ታኅሣሥ ፲፭ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ዐሥራ አምስት በዚች ቀን ያለ ደም መፍሰስ ሰማዕት የሆነ የአርማንያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ጎርጎርዮስ አረፈ። ❖ ይህንንም ቅዱስ የንጉሡን ትእዛዝ ስለመተላለፉና ለአማልክት አልሠዋም ስላለ የአርማንያ ንጉሥ ድርጣድስ አሠቃይቶ ጥልቅ ወደ ሆነ ደረቅ ጒድጓድ ውስጥ ጨመረውና በዚያ ዐሥራ አምስት ዓመት ኖረ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበር አንዲቷን አሮጊትም ሁል ጊዜ ምግቡን እንድታመጣለት አደረጋት ሕያው እንደሆነም የሚያውቅ የለም። ❖ ንጉሥ ድርጣድስም ቅድስት አርሴማን ሊአገባት ሽቶ ነበርና በእርሷ ምክንያት ደናግሎችን ገደላቸው፤ የእሊህ ደናግልም ሥጋቸው በተራራ ላይ እንደ ወደቀ ነበር ንጉሡም ስለ ገደላቸው ደናግል ይልቁንም ውበቷንና ደም ግባቷን እያሰበ ስለ ቅድስት አርሴማ አብዝቶ የሚያዝንና የሚጸጸት ሆነ። ❖ ከዚህም በኋላ ወገኖቹ ለመኑት እንዲህም አሉት አውሬ ታድን ዘንድ በፈረስ ተቀመጥና ወደ ዱር እንውጣ የልብህም ኀዘን ይወገድልሃል፤ በዚያንም ጊዜ አውሬ ለማደን በፈረሱ ተቀምጦ ወደ ዱር ወጣ፤ ወዲያውኑ ሰይጣን አደረበትና ሥጋውን የሚነክስ ሆነ ወገኖቹንም ነከሳቸው እግዚአብሔርም መልኩን ለውጦ እንደ እሪያ አደረገው ያገኘውን ሁሉ የሚነክስ ሆነ፤ እንዲሁም ከቤተ መንግሥት ሰዎች በብዙዎቹ ላይ ሰይጣን አደረባቸው ታላቅ ድንጋጤም ሆነ ይህም ሁሉ የሆነ ስለ ቅዱሳት ድናግልና ስለቅድስት አርሴማ ነው። ❖ የንጉሡ እኅት ግን ጎርጎርዮስን ከጒድጓድ ካላወጣችሁት ድኅነት የላችሁም የሚላትን ሰው በራእይ አየች ይህንንም ለወገኖቿ ነገረች እርሱ አስቀድሞ በጎድጓድ ውስጥ የሞተ ስለ መሰላቸው ደነገጡ። ❖ በዚያንምም ጊዜ ወደ ጒድጓድ ሔዱ በሕይወት እንዳለም ያውቁ ዘንድ ወደ ጒድጓዱ ውስጥ ገመዶችን አወረዱና ገመዶቹን እንዲይዝ ወደርሱ ጮኹ እርሱም ገመዶችን ያዘ ስበው አወጡት አጥበውም ንጹሕ ልብስን አለበሱት በበቅሎም አስቀምጠው ወደ ቤተ መንግሥት አደረሱት። ❖ በዚያንም ጊዜ በሰማዕትነት ስለሞቱ ደናግል ሥጋ ጠየቀ እነርሱም የደናግሉ ሥጋቸው ወዳለበት መርተው አደረሱት የዱር አራዊትና አዕዋፍ ሳይበሏቸው በደኅና አገኛቸው ያማሩ ቦታዎችን አዘጋጅተው በውስጣቸው ያኖሩዋቸው ዘንድ አዘዘ እንዳዘዛቸውም አደረጉ። ❖ ከዚህም በኋላ ንጉሡን ያድነው ዘንድ ሕዝቡ ለመኑት ንጉሡም ወዳለበት ዱር አደረሱት እርሱም ከክፉ ሥራህ ትመለሳለህን ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታምናለህን አለው፤ እሪያ የሆነውም ንጉሥ አዎን እንደሚል ራሱን ዘንበል አድርጎ አመለከተ በዚያንም ጊዜ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ጸለየ ከንጉሡም ላይ በእሪያ አምሳል ሰይጣንን አስወጣው። ❖ የንጉሡም አእምሮውና መልኩ እንደ ቀድሞው ተመለሰለት ነገር ግን ዳግመኛ እንዳይታበይ ከእግሩ ላይ የእሪያ ጥፍር አስቀረ ለፈጣሪውም ተገዢ ይሆን ዘንድ ዳግመኛም የቤተ መንግሥት ሰዎችን ሁሉንም አዳናቸው ከላያቸውም አጋንንትን አስወጥቶ ሰደዳቸው። ❖ ከዚህም በኋላ የአርማንያን ሰዎች ሁሉንም ሰበሰባቸውና ሥርዓትን ሠራላቸው ስምንት ቀንም እንዲጾሙ አዘዛቸው እንዳዘዛቸውም አደረጉ የእግዚአብሔርንም ሕግ እያስተማራቸው ኖሩ። ❖ ዳግመኛም ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆኑን አስተማራቸው ታላቆችም ታናሾችም ትምህርቱን ተቀበሉት ለአርማንያም ሰዎች ሃይማኖትን የመቀበላቸው ምክንያት ይህ ነው። ❖ ከዚህም በኋላ የክርስትና ጥምቀትን ያጠምቃቸው ዘንድ ቅዱስ ጎርጎርዮስን ለመኑት እርሱም እኔ ካህን ስለአልሆንኩ አይገባኝም ነገር ግን የሚያጠምቃችሁን ካህን ይልክላችሁ ዘንድ ወደ ሮሜ ሊቀ ጳጳሳት መልእክተኞችን ላኩ አላቸው። ❖ በዚያንም ጊዜ ከርሱ ጋር ወደ ንጉሥ አኖሬዎስና ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ መልክተኞችን ልከው የአርማንያ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር እንደተመለሱ አስረዱአቸው ንጉሡም ሊቀ ጳጳሳቱም ሰምተው ደስ አላቸው ከዚህም በኋላ ሊቀ ጳጳሳቱ የአርማንያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ይሆን ዘንድ ቅዱስ ጎርጎርዮስን ሾመው ወደ አርማንያን ንጉሥ ወደ ድርጣድስም በክብር ላከው። ❖ ቅዱስ ጎርጎርዮስም ተሹሞ ወደ አርማንያ አገር በደረሰ ጊዜ በመምጣቱ ደስ ተሰኙበት እርሱም የአርማንያን ሰዎች ሁሉንም አጠመቃቸው በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም ስም ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሠራላቸው በሃይማኖትም ከአጸናቸውና መልካም ጎዞውንም ከፈጸመ በኋላ በሰላም በፍቅር አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምሥጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን። 📌 ታኅሣሥ 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሊቅ (ዘአርማንያ) 2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ረባን 3.ቅዱስ ሉቃስ ዘዓምድ 4.አባ ይምላህ 📌 ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት) 2.ቅድስት እንባ መሪና 3.ቅድስት ክርስጢና 4.ቅዱስ ሚናስ ሰማዕት 5.ቅዱስ ቂርቆስ ሰማዕት 4.ብጽዕት ኢየሉጣ ሰማዕት
Show all...
❖ ከዚህም በኋላ ሥራዋን ከእኔ ሳትሠውር እንድትነግረኝ በክርስቶስ ስም አምላት ዘንድ ወደርሷ ሔድሁ። ግን አላገኘኋትም ከአምስት ወርም በኋላ ከንጉሥ አባቷ ዘንድ የተላኩ ብዙ ሰዎች እርሷን እየፈለጉ መጡ። እነርሱም ቤተሰቦቿ ከተኙ በኋላ በሌሊት እንደወጣች እነርሱም እርሷን ሲፈልጉ ዐሥራ ሁለት ዓመት እንደሆናቸው ሥራዋን ነገሩን። ከዚህም በኋላ መጻተኞች ሰዎች በዚች ቀን እንዳረፈች ነገሩን። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።                 📌 በዚችም ዕለት መድኃኒታችን በዓለም ውስጥ ብርሃንን ገለጠ። እርሱ የታሠሩትን ይፈታ ዘንድ በበደል ምክንያት የመጣውን ጨለማ ያርቅ ዘንድ ወደ ዓለም የመጣ ብርሃን እንደመሆኑ ለእርሱም ክብር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።                📌 ታኅሣሥ 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ዕለተ ብርሃን 2.ቅዱስ መርምሕናምና እህቱ ሣራ 4."170,000" ሰማዕታት (የቅዱሱ ሠራዊት) 5.ቅድስት ነሣሒት ቡርክት 6.ቅዱስ ስምዖን ሰማዕት 7.ቅዱስ አሞንዮስ ሰማዕት 8.አባ ገብረ ክርቶስ ሊቀ ዻዻሳት 📌 ወርኀዊ በዓላት 1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል) 2.አባ ስምዖን ገዳማዊ 4.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት) 5.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ 6.ቅዱስ ሙሴ መርዓዊ
Show all...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"          📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 📌 ስንክሳር ዘወርኀ ታኅሣሥ ፲፬ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ዐሥራ አራት በዚች ቀን ከፍ ከፍ ካለች ከመኑፍ ከተማ ቅዱስ ሰምዖን በሰማዕትነት አረፈ። እርሱም በእስላሞች ዘመን ከመሳፍንቶቻቸው ከአንዱ ጋር ተከራከረና ቅዱስ ስምዖን ረትቶ አሳፈረው ያም እስላም ወደ መሳፍንቱ አለቃ ሒዶ ይህ ስምዖን የእስላሞችን ሃይማኖት ያቃልላል ብሎ ወነጀለው ስለዚህም ይዘው በጽኑዕ ሥቃይ አሠቃዩት ከዚያም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 📌 በዚችም ቀን ቅዱሳን አባ ብሑርና አረጋዊ ሚናስ በሰማዕትነት አረፉ። በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 📌 በዚችም ቀን የቅዱሳን መርምህናምና እኅቱ ሣራ አርባ አገልጋዮቹም በሰማዕትነት አረፉ። የዚህም ቅዱስ አባቱ የአቶር ንጉሥ የተቀረጹ ስማቸው ቤል፣ አጵሎን የሚባሉ ጣዖቶችን የሚያመልክ ነው እናቱ ግን ክርስቲያን ናት። 📌 በዚችም ዕለት ዳግመኛ ከቅዱስ መርምህናም አባት ከአቶር ንጉሥ ከሰናክሬም ሠራዊት የአሥራ ሰባት እልፍ ሰማዕታት መታሰቢያቸው ሆነ፤ ይህም እንዲህ ነው የአቶር ንጉሥ ሰናክሬም ከሞተ በኋላ መንግሥቱን መጠበቅና ማዘዝ የማይችል ታናሽ ብላቴና ልጁ በእርሱ ፈንታ ነገሠ ግን እናቱ ስለርሱ ሹሞችን ታዝዛቸዋለች እነርሱም ይታዘዙላት ነበር። ❖ ከለዳዊ ንጉሥም ይህን በሰማ ጊዜ የአቶርን መንግሥት ለመውሰድ ስለዚህ ሠራዊቱን ሰብስቦ ለመዋጋት መጣ የሰናክሬምም አሽከሮችና መቃብሩን ጠባቂዎች የሆኑ የቅዱስ መርምህናም አሽከሮችም ሊከላከሉ ወጡ የከለዳውያን ንጉሥም አሸንፎ ከተማዪቱን ከፍቶ ገባ ብላቴናውንም ንጉሥ ይዞ ከእናቱ ጋር ገደለው ከዚህም በኋላ የአቶር አገር ሰዎች ተገዙለት በላያቸውም ነግሦ መንግሥትን ያዘ። ❖ ከጥቂት ቀኖችም በኋላ የአቶርን አገር ሰዎች ሰብስቦ ስለ ሃይማኖት ጠየቃቸው እነርሱም ክርስቲያን ነን አሉት፤ እርሱም ለጣዖት እንዲሰግዱ አዘዛቸው ከእነርሱም ውስጥ ሃይማኖታቸውን ለውጠው ለጣዖት የሰገዱ አሉ። ❖ የቅዱስ መርምህናምና የአባቱ አገልጋዮች መጥተው እንዲህ አሉት እኛ የክርስቶስ አገልጋዮች የሆን በግልጥ ክርስቲያኖች ነን ጌታችን ያስተማረንን ሃይማኖታችንን አንክድም በእኛ ላይ የፈለግኸውን አድርግ አሉት በዚያንም ጊዜ ተቆጣ ይገድሏቸውም ዘንድ አዘዘ ቁጥራቸውም አንድ መቶ ሰባ ሺህ ሆነ እነርሱም የቅዱስ መርምህናም ማኀበር ተብለው ተጠሩ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 📌 በዚችም ቀን ቅዱስ አባት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጰሳት አባ ገብረ ክርስቶስ አረፈ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስድሳ ስድስተኛ ነው። 📌 በዚችም ቀን የሀገረ እስና ኤጲስቆጶስ አባ አሞንዮስ በምስክርነት አረፈ፤ አርያኖስም ወደ እስና ከተማ በደረሰ ጊዜ ብዙ ሰዎችን ከአባ አሞንዮስ ዘንድ ተሰብስበው የሃይማኖትን ትምህርት ሲማሩ አገኛቸውና ሁሉንም ይዞ ገደላቸው አባ አሞንዮስን ግን አሥሮ ወሰደው ለጣዖትም እንዲሰግድ ብዙ አግባባው። ❖ አባ አሞንዮስም ለፈጣሪህ እግዚአብሔር ትሰግድ ዘንድ እርሱንም ብቻውን ታመልክ ዘንድ ተጽፎአልና ከንቱ የሆነ የእንቆቅልሽ ጨዋታችሁን ብላሽ የሆነ ነገራችሁንም መስማት አልወድም የረከሱ አማልክቶቻችሁንም ማየት አልሻም ፈራሽ በሆነ የጣዖት ቤታችሁም መመላለስን የከረፋ የሸተተ ማዕጠንታችሁንና መሠዊያችሁን አልይዝም አለው። ❖ መኰንኑ አርያኖስም የዚህ አባት ልብ ፈጽሞ እንደማይበገር በአየ ጊዜ በሕይወት ሳለ በእሳት እንዲአቃጥሉት አዘዘ አባ አሞንዮስም እስከሚጸልይ ጥቂት ይጠብቁት ዘንድ ወታደሮቹን ለመናቸውና እጆቹና አግሮቹም እንደታሠሩ ቆመ የወንጌልንም ጸሎት ጸለየና ሀገሩን ሕዝቡን በክርስቶስም የሚታመኑትን ሁሉ ባረከ ዳግመኛም ስለ መኰንኑ አርያኖስ ጸለየ በሰማዕትነትም እንደሚሞት ስለርሱ ትንቢት ተናገረ ደግሞ ነፍሱን አሰናበተ። ❖ ጸሎቱንም ሲፈጽም ወደ እሳት ወረወሩትና ያማረ ተጋድሎውን ፈጸመ ከዚህም በኋላ እሳቱ በጠፋ ጊዜ ከእሳት ቃጠሎ የነካው ሳይኖር ንጹሕ ሁኖ ሥጋውን አገኙት በአማሩ ልብሶችም ገንዘው በእንጽና ከተማ በስተምዕራብ የንጉሥ በጥሊሞስ ልጅ ንግሥት አክላወባጥራ በአሠራችው ግምብ ውስጥ ቀበሩት ከሥጋውም ታላላቅ አስደናቂዎች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአበሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።    📌 በዚችም ቀን የውሲም ኤጲስቆጶስ አባ ያዕቆብ ስለርሷ እንደተናገረ የሮም ንጉሥ ልጅ ስሟ ነሳሒት የተባለ አረፈች፤ እንዲህም አለ በአንዲት ዕለት አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያለሁ የገዳሙን ደጅ ሰው ሲያንኳኳ ሰማሁ ተነሥቼም ወደ በሩ ሔድኩ ያረጀ ዓጽፍ የለበሰ ፊቱንም የተሸፋፈነ ሰው አየሁ ከወዴት መጣህ ወዴትስ ትሔዳለህ አልሁት። ❖ ከአባ መቃርዮስ ገዳም መጣሁ በዚች ሌሊት ከዚህ ገዳም አድሬ ቊርባንን መቀበል እሻለሁ አለኝ ያን ጊዜ ቀዳሚት ሰንበት ነበረች እኔም ፊትህን ካላሳየኸኝ አልከፍትልህም አልሁት እርሱም ፊቴን ማየት አትሻ ፊቴ በኃጢአቴ የጨለመ ነውና ፊቴንም ለሚያይ የከፋች ሥራዬ ትታየዋለች አለኝ ። ❖ በከለከልኩትም ጊዜ ወደ ዱር ሊመለስ ወደደ እኔም ተርቦ ወይም ተጠምቶ እንደሆነ ብዬ በልቤ አሰብኩ ስለዚህም ከፈትኩለትና ወደ ማደሪያዬ አስገባሁት መብልንም አመጣሁለት እርሱም ከነገ ከቊርባን በኋላ በቀር እኔ አልበላም በማለት እምቢ አለኝ። ❖ ከዚህም በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገባና በጨለማ ቦታ ቆመ ከዚያ ያሉ መነኰሳትም እስከ አደነቁ ድረስ የዳዊትን መዝሙር ሲያነብ ድምፁን እንደ መላእክት ድምፅ ሁኖ ሰማሁት በነጋም ጊዜ በእግሮቹ ላይ ተቀመጠ ምንም ምን ማንበብ አልሻም፤ እኛ ግን ይጸልይልን ዘንድ ልንለምነው ቀረብን እርሱም አባቶቼ ሆይ በበደሌ ብዛት ፊቴን ያጨለምኩ ስሆን ስለ እናንተ እንዴት እጸልያለሁ አለን። ቁርባንንም በምናሳርግ ጊዜ በእግሩ ቆሞ የጳውሎስን መልእክት የሐዋርያትንም መልእክትና የሐዋርያትን ሥራ ማንበብ ጀመረ በአራተኛም ጊዜ በመሠዊያው ፊት ቁሞ የዮሐንስን ወንጌል ማንበብ ጀመረ በፊቱም ላይ የተከናነበውን ልብስ አስወገደ ከፊቱም ብርሃን ገናናነት የተነሣ ሊያዩት አልተቻላቸውም። ❖ እኛ ቊርባንን ከተቀበልን በኋላ ቆረበ ከነገሥታት ልጆች ወገንም እንደሆነ ተጠራጠርን መብልንም በአቀረብንለት ጊዜ ከእኛ አልተቀበለም ነገር ግን ሰይጣን በእነርሱ ከሚያስትባቸው ሴቶችን ከማየት እንርቅ ዘንድ መከረን። ❖ ሮማዊ የሆነ አንድ ደግ ጻድቅ አረጋዊ መነኵሴ ነበር እርሱም አባቴ ያዕቆብ ሆይ ይቺ ከነገሥታት ልጆች ውስጥ የሆነች ሴት ናት ስለዚህም እንዳትታወቅ ፊቷን ከሰው ትሠውራለች አለኝ።
Show all...
አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ ሃገራችን ኢትዮዽያ ብሉይ ከሐዲስ ያልጐደለባት በክርስቶስና በድንግል እናቱ ኪደተ እግር የተቀደሰች የቅዱሳን መጠጊያ እና ብዙ ቅዱሳንን ከእቅፏ ያፈራች ስለ ሆነች የተባረከች ሃገር ትባላለች፤ ሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ቅዱሳንን አፍርተዋል:: ❖ በምሥራቅም፣ በምዕራብም፣ በሰሜንምና በደቡብም ያሉ አካባቢዎች ሁሉ የቅዱሳን ቤቶች ናቸው፤ ቅዱሳንን በብዛት ካፈሩ አካባቢዎች አንዱ ደግሞ ምድረ ጐጃም ነው፤ በጐጃም አካባቢ ከተነሱ ቅዱሳን ደግሞ አንዱና ስመ ጥሩ ጻድቅ አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ናቸው፤ አቡነ ዘርዓ ቡሩክ በብዙ ጐዳና የተለዩ አባት ናቸው፤ ለመጥቀስ ያህል እንኩዋ 1⃣ በታሪክ ዓለምን ከበው የያዙ 2ቱ ግሩማን አራዊት (ብሔሞትና ሌዋታንን) ጥርስ ቆጥረው ብዙ ምሥጢራትንም ተመልክተው ተመልሰዋል፤ (በነገራችሁ ላይ ይህ ጉዳይ ዛሬም ድረስ ሳይንሱ በብዙ ድካም ያልደረሰበት ነው) 2⃣ ጻድቁ በልደታቸው ጊዜ ዓይነ ስውራንን አብርተዋል፤ ለራሳቸው ግን ይህን የግፍ ዓለም ላለማየት ጸልየው ዓይናቸው እንዲጠፋ አድርገዋል:: ❖ ጻድቁ የተወለዱት በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እዚያው ጐጃም ውስጥ ሲሆን አባታቸው ደመ ክርስቶስ እናታቸው ደግሞ ማርያም ሞገሳ ይባላሉ፤ ወላጆች በልጅ እጦት ተማረው ይህን የተቀደሰ ፍሬ አገኙ፤ "ጸጋ ኢየሱስ" ብለውታል፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ተሰጥቷቸዋልና:: ❖ ቀጥሎ የወለዱትንም "ተስፋ ኢየሱስ" ብለውታል፤ ይህም የጻድቁ ታናሽ ወንድም ነው፤ በሒደት ግን የጸጋ ኢየሱስ ስም በፈቃደ እግዚአብሔር ወደ ዘርዓ ቡሩክነት ተቀይሯል:: ❖ ጻድቁን ስመ ጥር ካደረጉዋቸው ሥራዎቻቸው መካከል በአፄ ሱስንዮስ ዘመን የሠሩት ቅድሚያውን ይወስዳል፤ ነገሩ እንዲህ ነው፤ በ1598 ዓ.ም በኢትዮዽያ ላይ የነገሡት አፄ ሱስንዮስ ዼጥሮስ (ፔድሮ) ፓኤዝ ከሚባል ፈረንጅ መናፍቅ ጋር በፈጠሩት ወዳጅነት ሃይማኖታቸውን ለወጡ:: ❖ ካቶሊክ (ሮማዊም) ሆኑ፤ በሁዋላም አልፎንሱ ሜንዴዝ የሚሉት እሾህ መጥቶ ሁሉም የኢትዮዽያ ሕዝብ መናፍቅ እንዲሆን ከንጉሡ ጋር መከረ፤ ለጊዜው በቤተ መንግስቱ አካባቢ የነበሩ መሣፍንት ተቀላቀሉ፤ እየቆየ ግን ዜናው በመላ ሃገሪቱ ተሰማ፤ በተለይ በ1611 በተዋሕዶ አማኞችና በመናፍቁ ንጉሥ መካከል ነገሩ ተካሮ ዻዻሱ አቡነ ስምዖን ጠዳ ላይ መገደላቸው ተሰማ:: ❖ በዚህ ጊዜ ገበሬው ከእርሻው ሴቷ ከማዕድ ቤት ካህኑ ከመቅደሱ ነጋዴው ከገበያው እየወጡ ስለ ቀናችው ሃይማኖት ደማቸውን አፈሰሱ፤ በበዓት የተወሰኑ በሺህ የሚቆጠሩ ቅዱሳንም ወጥተው ተሰየፉ:: ❖ በዚህ ጊዜም የግሺው አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ዳዊታቸውን አንግበው ለሰማዕትነት ሔዱ፤ ዓባይ ወንዝ ላይ ሲደርሱ ዳዊታቸውን ወደ ወንዙ ውስጥ ጣሉት፤ ተሻግረውም ከንጉሡ አደባባይ ደንቀዝ ደረሱ፤ በጊዜውም ልክ እንደነ ፍቅርተ ክርስቶስና ወለተ ዼጥሮስ እርሳቸውም መከራ ደረሰባቸው:: ❖ ንጉሡም ሳይገደሉ እንዲታሠሩ አደረገ፤ በጨለማ እስር ቤትም 5 ዓመታትን ሲያሳልፉ ትኩስ ምግብን ያመጡላቸው ነበር፤ እርሳቸው ግን ምግባቸው ሰማያዊ ነበርና አልነኩትም፤ ከ5 ዓመት በሁዋላም ያ ሁሉ ምግብ በተአምራት በትኩስነቱ እየጨሰ ተገኝቷል፤ ዘርዓ ቡሩክም ከእሥር ተፈትተዋል:: ❖ እግዚአብሔርም በከሐዲው ንጉሥ ላይ ፈርዶ ፋሲል ነግሷል፤ ሃይማኖት ተመልሷል፤ ጻድቁም በዓባይ ወንዝ ላይ የጣሉት ዳዊታቸውን ሳይርስ አግኝተውታል፤ ጐጃም ሲደርሱም ሰይጣን እርሳቸውን መስሎ ሲያስት ስላገኙት ወደ ጥልቁ አስጥመውታል፤ በተረፈ ዘመናቸው አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ብዙ ተጋድለው ጥር 13 ቀን ዐርፈዋል፤ ድንቅ ሠሪ አባት ናቸውና ዛሬም በግሺ ብዙ ተአምራት ይደረጋሉ። ረድኤታቸው በረከታቸው ይደርብን፤ በጸሎታቸው ይማረን፤ ሀገራችን ሰላም ፍቅር ያድርግልን 
Show all...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ                አሜን 📌 ስንክሳር ዘወርኀ ታኅሣሥ ፲፫ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን አባ በጽንፍርዮስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም የከበረ መነኰስ በምስር አገር በወንዝ ዳር በአለች በሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መንኵሶ ታላቅ ተጋድሎን ሲጋደል ኖረ ስለቀናች ሃይማኖትም ከእስላሞች መሳፍንት ጋር ተከራከረ የጌታችን ክርስቶስንም መለኮቱን ገለጠላቸው አምላክነቱንም አስረዳቸው ስለዚህም እስላሞች በአፈሩ ጊዜ ተቆጡ ጽኑዕ ሥቃይንም አሠቃዩት ራሱንም በሰይፍ ቆረጡ የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 📌 በዚችም ቀን ከላይኛው ግብጽ ቅዱስ አባት አብራኮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ዕድሜው ሃያ ዓመት ሲሆን መንኵሶ መልካም የሆነ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ። ሰይጣንም ከእርሱ ጋር በመጣላት በተሸነፈና በደከመ ጊዜ በእርሱም ላይ ምንም ምን ማድረግ ባልተቻለው ጊዜ ፊት ለፊት ተገልጦ መጥቶ እነሆ ከዚህ ዕድሜህ ሌላ ኀምሳ ዓመት ቀረህ አለው። በዚህም ወደ ስንፍና ሊጥለው ወዶ ነው ሽማግሌውም እንዲህ ብሎ መለሰለት አሳዘንከኝ እኔ ሌላ መቶ ዓመት እኖር ዘንድ ስለ አሰብኩ ቸል ብያለሁ አንተ እንዳልከውም ከሆነ ከቀድሞው እጅግ አብዝቼ እጋደል ዘንድ ይገባኛል። ከዚህም በኋላ ተጋድሎውንና በገድል መጸመዱን አበዛ ሰባ ዓመታትም ከተጋደለ በኋላ በዚያች ዓመት አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።          📌 በዚችም ቀን በደብረ ቀልሞን የሚኖር የገዳማዊ የአባ ሚካኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር አሜን። 📌 በዚችም ቀን ቆቅ ሲመገብ የነበረ የአባ መቃርስ መታሰቢያው ነው፤ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ሕያው እግዚአብሔርን መከተል ፈለገ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት መጻሕፍትንም ተማረ የዚህንም ዓለም ኃላፊነቱን ለጻድቃንም በጎ ዋጋ ለኃጥአን ቅጣት እንዳለም አስተዋለ ስለዚህም ዓለምን ትቶ በአንድ ገዳም ውስጥ መነኰሰ ከዚያም ወጥቶ የዐሥር ቀን ጐዳና ተጓዘና በውስጡ ኵዕንትና ቆቆች ውኃም ካለበት ተራራ ደረሰ። ❖ አስቦም እንዲህ አለ ኵዕንትን ወደመልቀም ብሰማራ የስግደቴና የጸሎቴ ሥራ ይቋረጣል ሰብሰቦ የሚያስገባልኝ ረዳት የለኝ ብቸኛ ነኝና ሥጋ አትብላ ያለውስ የባልንጀራችንን ሥጋ በሐሜት የምንበላውን አይደለምን ሌላ ምግብ እንደሌለኝ ፈጣሪዬ ያውቃል ብሎ ከዚያችም ዕለት ወዲህ ቆቆችን የሚያጠምድ ሆኖ በየቀኑ አንድ አንድ የሚያዙለት ሆኑ፡፡ ❖ እርሳቸውንም እየተመገበ ከዚያ ውኃም እየጠጣ በማመስገን ኖረ በቀንና በሌሊትም በጸሎትና በስግደት በመትጋት ወደ እግዚአብሔርም እየለመነ ብዙ ዘመናት ኖረ የሰውንም ድምጽ አይሰማም የሰውንም ፊት አያይም ሐሜትንም ሆነ ስድብን በማንም ላይ አብሮ አይነጋገርም ከሰው ጋር ካልሆነ በቀር ሰይጣን አይመጣም ይባላልና። ❖ ከዚህም በኋላ ከቁስጥንጥኒያ ከተማ አንድ መነኲሴ ዋሻ እየፈለገ አባ መቃርስ ካለበት ደርሶ ቆቅን ሲያጠምድ አየው ያንጊዜ አልታገሠም ግን ወንድሙን በሐሜት እስከሚገድለው ቸኮለ ወደ ቁስጥንጥንያ ከተማ ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ ተመልሶ እንዲህ ብሎ ነገረው እኔ ዋሻ እየፈለግሁ ወደ በረሀ ሔድሁ በዚያም ሥጋ ሊበላ ቆቅን ሲያጠምድ መነኲሴውን አየሁት የሚሰራውን ሲያዩ በአሕዛብ ዘንድ ሊያስነቅፈን ነው አለው፡፡ ❖ ሊቀጳጳሳቱም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ነገሩ እውነት እንደሆን ያውቅ ይረዳ ዘንድ ከዚያ ከነገረው መነኲሴ ጋር ሌላ መነኲሴ ላከ እነርሱም በጕዞ ላይ በጐዳና ሳሉ ገና ሳይደውሱ አባ መቃርስ እንደልማዱ ወደ ወጥመዱ ሔደ በአንዲት ወጥመድ የተያዙ ሦስት ቆቆችን አገኘ እንዲህም ብሎ አሰበ ጌታዬ እሊህን የሰጠኝ እኔን ሊፈትነኝ ነውን ወይስ ከዚች ዕለት በፊት ሆዴ ያልጠገበች ኑራለችን ወይም ለሌላ ነው እንዳልል በዚህ በረሀ ውስጥ ከሰው ወገን ያየሁት የለም፡፡ ❖ እንዲህም እያሰበ ሳለ ከሊቀ ጳጳሳቱ የተላኩት እሊያ መነኰሳት ደረሱ በአያቸውም ጊዜ ደስ አለው ችግረኛነቴን አውቀህ ለአገልጋዮችህ ቅዱሳን ምግባቸውን የሰጠኸኝ አቤቱ አመሰግንሃለሁ ብሎ ሰገደ። እነርሱ ግን ማዕድ ሠርቶ አዘጋጅቶ እስከአቀረበላቸው ድረስ ይጠቃቀሱበት ነበር ከዚህም በኋላ አቅርቦላቸው ንሱ አባቶቼ ባርኩና ተመገቡ አላቸው እርሱም የራሱን ድርሻ ይዞ እስከሚጨርስ ያለ መነጋገር በጸጥታ ተመገበ። ❖ ከዚህም በኋላ ዓይኖቹን ቀና ቢያደርግ እንዳልበሉ አየ አባቶቼ እንዴት አልበላችሁም አላቸው እኛ መንኰሳት ስለሆን ሥጋ አንበላም ትኅርምትም አለን አሉት እርሱም ተዋቸው አላስገደዳቸውም እነዚያን ያበሰላቸውን ቆቆች አንሥቶ ሦስት ጊዜ እፍ አለባቸው ያን ጊዜም ድነው በረሩ ወደ ቦታቸውም ሔዱ እነዚያ መነኰሳትም ይህን ተአምር አይተው ደነገጡ የእግዚአብሔር ቅዱስ ሆይ በደላችንን ይቅር በለን ብለው ሰገዱለት እርሱም የሁላችንንም በደል እግዚአብሔር ይቅር ይበለን አላቸው። ❖ ከዚህም በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ያዩትን ይህን ድንቅ ተአምር ለሊቀ ጳጳሳቱ ነገሩት እርሱም ሰምቶ አደነቀ ወደ ንጉሥም እንዲህ ብሎ ላከ በዘመናችን ጻድቅ ሰው መነኰስ ተገኝቷልና አንተም ና ሒደን በረከቱን እንድንቀበል አለው። ❖ ወዲያውኑ ንጉሡ ከሠራዊቱ ጋር ተነሣ ሊቀ ጳጳሳቱም ከካህናቱ ጋር አባ መቃርስ ወዳለበት እነዚያ መነኰሳት እየመሩአቸው ሔዱ ወደርሱም ሲቀርቡ ወደ ብሔረ ሕያዋን ያደርሰው ዘንድ መልእክ አንሥቶ በክንፎቹ ተሸከመው ሲያርግም በአዩት ጊዜ የእግዚአብሔር ቅዱስ ሆይ ባርከን የምንድንበትን አንዲት ቃል ንገረን ብለው ጮኹ፣ እርሱም ከሐሜትና ከነገር ሥራ አንደበታችሁ ይከልከል። ❖ ካህን ብዙ ባይማር ትዕቢትና መታጀር ባልመጣበት ነበር መነኵሴም ትኅርምት ባያበዛ ባልተመካም ነበር እርስበርሳችሁ ተፋቀሩ እግዚአብሔርም አድሮባችሁ ይኑር አላቸው ይህንንም ብሎ ዐረገ ከዐይናቸውም ተሠወረ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ? ታኅሣሥ 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ጻድቅ 2.ቅዱስ መቃርስ ገዳማዊ 3.አባ አብራኮስ ገዳማዊ 4.ብጽዕት ሐና (የእመቤታችን እናት) 5.አባ በጽንፍርዮስ ሰማዕት 6.አባ ሚካኤል ዘቀልሞን 📌 ወርኀዊ በዓላት 1.እግዚአብሔር አብ 2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት 3.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ 4.አእላፍ (99ኙ) ነገደ መላእክት 5.ቅዱስ አስከናፍር ሮማዊ 6."13ቱ" ግኁሳን አበው
Show all...
📌 ከ 1696 ዓመት በላይ ያስቆጠረውን ፡ 📌ልክ እንደ ላሊበላ ከአንድ ወጥ ዐለት ከላይ ወደ ታች የተፈለፈለውን ዋሻ ተክለ ሃይማኖትን እንሳለማለን 📌 ውስን ቦታዎች ብቻ ነው የቀረው እንዳያመልጦት 📌 እዚሁ ቅርብ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኝ 📌 ግን የማናውቀው ዓላማውን በመረዳት በረከት የምናገኝበት መንፈሳዊ የሰንበት ትምህርት ቤታችን የ2016ዓ.ም የመጀመሪያ ጉዟችን
Show all...
❖ ከዚህም በኋላ ብዙ ደቀ መዛሙርት ወደርሱ ተሰበሰቡ በተጋድሎም ተጠመዱ ከእርሳቸውም የመጀመሪያው አባ ዘሩፋኤል ነው፤ በአንዲትም ዕለት በገዳመ ለጋስ ከሚኖር ከአባ ገብረ መስቀል ጋር ተገናኘ ከዚህም በፊት አልተያዩም ነበር የእግዚአብሔርንም ገናናነት ሲጨዋወቱ ዋሉ በራት ጊዜም ጸሎትን ሲያደርጉ የተዘጋጀ ማዕድ ወርዶላቸው ተመግበው እግዚአብሔርን አመሰገኑ። ❖ ከዚህም በኋላ በአንዲት ዕለት ከአንድ ገዳማዊ ጋር ተገናኘ እግዚአብሔርም ያደረገላቸውን ምሥጢር በሚነጋገሩ ጊዜ አባታችን ሳሙኤል እንዲህ አለ እነሆ እኔ በአርያም ቁሜ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የአምላክን መንበር ሳጥን ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆነኝ፤ ለመቀደስም በሚገባ ጊዜ ኅብስትና ወይንን የተመላ ጽዋ ይውርድለታል። ❖ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ውዳሴዋን ሲያነብ ክንድ ያህል ከምድር ወደ ላይ ከፍ ከፍ ይላል እምቤታችን ማርያምም ወደርሱ መጥታ የሚያበራ ዕንቁንና ንጹሕ ዕጣንን ሰጠችው። # ፍልሰቱም ሲቀርብ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በክንፎቹ ተሸክሞ አወጣው የሰማያዊት ኢየሩሳሌምን ተድላዋን ሁሉ አሳየው ወደ ልዑል እግዚአብሔርም ዙፋን ፊት አቅርቦት ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውንም ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ተቀበለ ወደ በዓቱም ሲመለስ ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው ከዚህም በኋላ በሰላም በፍቅር አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ቅዱስ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።            📌 በዚችም ዕለት ደግሞ የአባ ነድራ ከደብረ እስዋን የታማኙም የቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያ ነው በረከታቸውም ትድረሰን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን አሜን። 📌 በዚችም ቀን የቅዱሳን ኤጲስቆጶሳት የቀሳውስትና የዲያቆናት የአንድነት ስብሰባ በሮሜ ከተማ ሆነ፤ ይህም የሆነው ከሀዲው ዳኬዎስ በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት በሮሜው ሊቀ ጳጳሳት በቆርኔሌዎስ የሹመት ዘመን በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በዲዮናስዮስ ዘመን በላንድዮስም በአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ሁኖ ሳለ ግርማኖስም የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ሁኖ ሳለ ነው ይህም የሆነበት ምክንያት በስደት ጊዜ የካደ ቢኖር ወይም በዝሙት የወደቀ ወይም በየአይነቱ በሆነ ኃጢአት ቢሰናከል በንሰሓ ሊቀበሉት አይገባም በማለቱ ስለ ቀሲስ ብናጥስ ነው። 📌 በዚችም ዕለት በከሀዲው ዲዮቅልጢያኖስ ዘመን ቅዱሳን አንቂጦስና ፎጢኖስ በሰማዕትነት አረፉ። ይህም ሰማዕት አንቂጦስ ንጉሡ ምእመናንን ያሥራቸው ዘንድ አሠርቶ በፊቱ ያኖራቸውን የሥቃይ መሣሪያዎች በአየ ጊዜ በቆራጥነት ከሕዝብ መካከል ተነሥቶ ንጉሡን ተከራከረው ንጉሡም አሥረው ወደ ጨዋታ ማያ ቦታ አውጥተው ክፉውን አንበሳ እንዲለቁበት አዘዘ፤ አንበሳውም ወደርሱ በደረሰ ጊዜ ቀኝ እጁን ዘርግቶ ፊቱንና ጒንጩን አሻሽቶ ተወው ንጉሡም አይቶ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። ❖ ወታደሩም ሰይፉን በመዘዘ ጊዜ ተንቀጠቀጠ መንቀሳቀስም ተሳነው ሁለተኛም ሰውነቱ ፈጥና እንድትቆራረጥ ከበታቹ የእሳት ፍም ወደተነሠነሠበትና ቆራርጦ የሚለያይ መሣሪያ ወዳለው መንኰራኵር ውስጥ እንዲጨምሩት አዘዘ እግዚአብሔርም ከዚህ አድኖት ያለ ጉዳት በጤና አስነሣው። ❖ ዳግመኛም በውስጧ እርሳስ ወደአፈሉባት ጋን ውስጥ እንዲጨምሩት አዘዘ ሕዝቡም እያዩ የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ ከጋኑ ውስጥ ነጥቆ በዲዮቅልጥያኖስ ፊት አቆመው ፎጢኖስም ይህን ድንቅ ተአምር በአየ ጊዜ ልብሱን ጥሎ ተነሥቶ ወንድሙን አንቂጦስን ሳመው፤ ከዳተኛውንም ንጉሥ አንተ ጐስቋላ ወንድሜን እንዴት ታሸንፈዋለህ ብሎ ረገመው ዲዮቅልጥያኖስም ሰምቶ በአንገታቸው ዛንጅር በእግሮቻቸው እግርብረት አግብተው ወደ ወህኒ ቤት እንዲጨምሩአቸው አዘዘ። ❖ ከዚህም በኋላ ሥጋቸው ሁሉ ይበታተን ዘንድ ጥፍር በአለው ብረት እንዲሰነጣጥቋቸው አዘዘ ዳግመኛም ወደ ጨዋታ መስክ ወስደው በድንጋይ ይወግሩአቸው ዘንድ አዘዘ፤ ምንም ምን የነካቸው የለም ደግመኛም በብዛት ገርፈው በቊስላቸው ውስጥ ጨው ጨመሩ ሦስት ቀንም ወደ አንደዱበት የውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ጨመሩአቸው እርሱም እንደ ቀዘቀዘ ጠል ሆነላቸው የውሽባ ቤቱንም በከፈቱት ጊዜ የእግዚአብሔርን ገናናነት ሲነጋገሩ አገኙአቸው። ❖ ከዳተኛው ንጉሥም በአየ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ነበልባሉም ከፍ ከፍ እስከሚል በማንደጃው ውስጥ እሳትን አንድደው ቅዱሳኑን ወደዚያ ይጥሏቸው ዘንድ አዘዘ በውስጡም ቁመው ረጅም ጸሎትን አደረጉ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ፊታቸውን አማተቡ ነፍሳቸውንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ። ❖ ሥጋቸውም ከቀኑ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊቱ ስድስት ሰዓት ድረስ በእሳቱ ፍም ላይ ነበር የነካው ነገር የለም የራሳቸው ጠጒር እንኳ አልተቃጠለም ምእመናንም ሥጋቸውን በሌሊት ወሰዱ ለክብራቸውም እንደሚገባ ገንዘው በመልካም ቦታ ቀበሩአቸው። ከእሳቸውም አስደናቂዎች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 📌 ታኅሣሥ 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ 2.ቅዱሳን አንቂጦስ ወፎጢኖስ (ሰማዕታት) 3.አባ ነድራ 4.ቅዱስ ዮሐንስ ተአማኒ 5.ጉቡዓን ኤዺስ ቆዾሳት 1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት 2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ) 4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት) 5.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ 6.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ 7.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቅ
Show all...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"                   ቀናችንን በጸሎት እንጀምር 📌 ስንክሳር ዘወርኀ ታኅሣሥ ፲፪ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው። በዚች ቀን በዚህ ወር እግዚአብሔር ወደባቢሎን አገር ላከው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሦስቱን ልጆች አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን ከእሳት ማንደጃ ውስጥ በጣላቸው ጊዜ አራተኛ ገጽ ሁኖ ታየ። ❖ የእሳቱም ነበልባል አርባ ዘጠኝ ክንድ ያህል ወደላይ ከፍ ከፍ አለ የጨመሩአቸውን ሰዎችና እሳት የሚያንዱትን አቃጠላቸው ይህም የከበረ መልአክ ሚካኤል የእሳቱን ነበልባል በበትሩ መትቶ ከሠለስቱ ደቂቅ ላይ አጥፍቶ አዳናቸው ምንም አልነካቸውም እንደ ቀዘቀዘ እንደ ጧት ጤዛ አድርጎታልና። ❖ በዚያንም ጊዜ የአባቶቻችን ፈጣሪ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን እያሉ ስድስት ቃላትን ተናገሩ በዚህም ከስድስት መቶ ዓመት በኋላ ክርስቶስ እንደሚወለድ ትንቢት ተናገሩ። ❖ ከዚህም በኋላ የጌታ እግዚአብሔር ሥራዎቹ ሁሉ ያመሰግኑታል እርሱ ለዘላለሙ ምስጉን ልዑልም ነው እያሉ ሠላሳ ሦስት ጊዜ አመሰገኑት በዚህም በምድር ላይ ሠላሳ ሦስት ዓመት ክርስቶስ እንደሚኖር አመለከቱ፤ ስለዚህም አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያን መምህራን የመላእክት አለቃ የሆነ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ እንድናደርግ ሠሩ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 📌 ❖ በዚችም ዕለት ዳግመኛ የከበረ አባት የዋልድባው አባ ሳሙኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ለዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም እስጢፋኖስ የእናቱ ስም አመተ ማርያም ነው፤ እነርሱም በዘመድ የከበሩ ደጎች ናቸው በአክሱም ምድርም ወለዱት በአደገ ጊዜም የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት አስተማሩት አባቱና እናቱም በሞቱ ጊዜ ወደ ደብረ በንኰል ገዳም ወደ አባ አድኃኒ ሒዶ የምንኲስና ልብስን ለብሶ በጾምና በጸሎት እየተጋደለ ኖረ፤ ፈጽሞ ከሻገተ ጎመን በቀር አይበላም የሚጠጣውም ውኃ ነው እህል በመፍጨትና ውኃ በመቅዳት ሥራ መነኰሳቱን ይረዳቸው ነበር። ❖ ዘመዶቹም ወደርሱ እየመጡ በአስቸገሩት ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ሔደ እግሮቹም እስቲያብጡ ድረስ በጾም በስግደት በመቆም ተጋደለ ከዚያም ወደሌላ በረሀ ሒዶ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ምንም ምን ሳይቀምስ ኖረ አንበሶችና ነብሮች የሚያስፈሩም አራዊት ሁሉ ወደርሱ በመምጣት ይሰግዱለታል የእግሮቹን ትቢያ ይልሱ ነበር። ❖ በአንዲት ዕለትም በጐዳና ሲጓዝ ታላቅ ወንዝን ውኃው መልቶ አገኘ መጽሐፍና እሳትም ከእርሱ ጋር ነበረ ጸሎትንም አድርጎ ወደ ውኃው ገባ ውኃውም ዋጠውና ወደታች አወረደው በእግዚአብሔርም ኃይል ወደማዶ በጣለው ጊዜ መጽሐፉ ሳይደመሰስ እሳቱም ሳይጠፋ አገኘው። ❖ ሰይጣንም በሚያስፈሩ አራዊት እየተመሰለ ይፈታተነው ነበር እርሱ ግን ፈጣሪውን በመታመን ልቡ የታሠረና የጸና ስለሆነ አይፈራም፤ እርሱም ሲጸልይ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደርሱ መጣ በምራቁም መላ ሕዋሳቱን ቀብቶ ኃይልን አሳደረበት ከዚያችም ዕለት ጀምሮ እግሮቹን የሚያሥር ሆነ፤ ማቅንም ለብሶ በየሌሊቱ ሁሉ ከውኃ ውስጥ በመግባት የዳዊትን መዝሙር አምስት ጊዜ ያደርሳል ቊጥር በሌለውም ግርፋት ጀርባውን ይገርፍ ነበር፤ አንበሶችም በበዓቱ አጠገብ ይሰማራሉ አርሱም አካላቸውን ይሰፍራል ይለካል ቊስላቸውንም በጥቶ እሾህና አሜከላ ያወጣላቸዋል። ❖ ከዚህም በኋላ ብዙ ደቀ መዛሙርት ወደርሱ ተሰበሰቡ በተጋድሎም ተጠመዱ ከእርሳቸውም የመጀመሪያው አባ ዘሩፋኤል ነው፤ በአንዲትም ዕለት በገዳመ ለጋስ ከሚኖር ከአባ ገብረ መስቀል ጋር ተገናኘ ከዚህም በፊት አልተያዩም ነበር የእግዚአብሔርንም ገናናነት ሲጨዋወቱ ዋሉ በራት ጊዜም ጸሎትን ሲያደርጉ የተዘጋጀ ማዕድ ወርዶላቸው ተመግበው እግዚአብሔርን አመሰገኑ። ❖ ከዚህም በኋላ በአንዲት ዕለት ከአንድ ገዳማዊ ጋር ተገናኘ እግዚአብሔርም ያደረገላቸውን ምሥጢር በሚነጋገሩ ጊዜ አባታችን ሳሙኤል እንዲህ አለ እነሆ እኔ በአርያም ቁሜ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የአምላክን መንበር ሳጥን ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆነኝ፤ ለመቀደስም በሚገባ ጊዜ ኅብስትና ወይንን የተመላ ጽዋ ይውርድለታል። ❖ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ውዳሴዋን ሲያነብ ክንድ ያህል ከምድር ወደ ላይ ከፍ ከፍ ይላል እምቤታችን ማርያምም ወደርሱ መጥታ የሚያበራ ዕንቁንና ንጹሕ ዕጣንን ሰጠችው። # ፍልሰቱም ሲቀርብ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በክንፎቹ ተሸክሞ አወጣው የሰማያዊት ኢየሩሳሌምን ተድላዋን ሁሉ አሳየው ወደ ልዑል እግዚአብሔርም ዙፋን ፊት አቅርቦት ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውንም ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ተቀበለ ወደ በዓቱም ሲመለስ ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው ከዚህም በኋላ በሰላም በፍቅር አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ቅዱስ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 📌 በዚችም ዕለት ዳግመኛ የከበረ አባት የዋልድባው አባ ሳሙኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ለዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም እስጢፋኖስ የእናቱ ስም አመተ ማርያም ነው፤ እነርሱም በዘመድ የከበሩ ደጎች ናቸው በአክሱም ምድርም ወለዱት በአደገ ጊዜም የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት አስተማሩት አባቱና እናቱም በሞቱ ጊዜ ወደ ደብረ በንኰል ገዳም ወደ አባ አድኃኒ ሒዶ የምንኲስና ልብስን ለብሶ በጾምና በጸሎት እየተጋደለ ኖረ፤ ፈጽሞ ከሻገተ ጎመን በቀር አይበላም የሚጠጣውም ውኃ ነው እህል በመፍጨትና ውኃ በመቅዳት ሥራ መነኰሳቱን ይረዳቸው ነበር። ❖ ዘመዶቹም ወደርሱ እየመጡ በአስቸገሩት ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ሔደ እግሮቹም እስቲያብጡ ድረስ በጾም በስግደት በመቆም ተጋደለ ከዚያም ወደሌላ በረሀ ሒዶ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ምንም ምን ሳይቀምስ ኖረ አንበሶችና ነብሮች የሚያስፈሩም አራዊት ሁሉ ወደርሱ በመምጣት ይሰግዱለታል የእግሮቹን ትቢያ ይልሱ ነበር። ❖ በአንዲት ዕለትም በጐዳና ሲጓዝ ታላቅ ወንዝን ውኃው መልቶ አገኘ መጽሐፍና እሳትም ከእርሱ ጋር ነበረ ጸሎትንም አድርጎ ወደ ውኃው ገባ ውኃውም ዋጠውና ወደታች አወረደው በእግዚአብሔርም ኃይል ወደማዶ በጣለው ጊዜ መጽሐፉ ሳይደመሰስ እሳቱም ሳይጠፋ አገኘው። ❖ ሰይጣንም በሚያስፈሩ አራዊት እየተመሰለ ይፈታተነው ነበር እርሱ ግን ፈጣሪውን በመታመን ልቡ የታሠረና የጸና ስለሆነ አይፈራም፤ እርሱም ሲጸልይ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደርሱ መጣ በምራቁም መላ ሕዋሳቱን ቀብቶ ኃይልን አሳደረበት ከዚያችም ዕለት ጀምሮ እግሮቹን የሚያሥር ሆነ፤ ማቅንም ለብሶ በየሌሊቱ ሁሉ ከውኃ ውስጥ በመግባት የዳዊትን መዝሙር አምስት ጊዜ ያደርሳል ቊጥር በሌለውም ግርፋት ጀርባውን ይገርፍ ነበር፤ አንበሶችም በበዓቱ አጠገብ ይሰማራሉ አርሱም አካላቸውን ይሰፍራል ይለካል ቊስላቸውንም በጥቶ እሾህና አሜከላ ያወጣላቸዋል።
Show all...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✍️"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል" 📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቀናችንን በጸሎት እንጀምር 📌 ስንክሳር ዘወርኀ ታኅሣሥ ፲፩ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ዐሥራ አንድ በዚች ቀን የግብጽ ደቡብ ከሆነ ከመጺል አውራጃ ከሬስ ከተማ ሰዎች ወገን የሆነ ቅዱስ አባት አባ በኪሞስ አረፈ። እርሱም የአባቱን በጎች የሚጠብቅ ነበር ዕድሜውም ዐሥራ ሁለት ዓመት ሲሆነው ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ በጐልማሳ አምሳል ተገለጠለትና በአንድነት ሒደን እንመነኵስ ዘንድ ትሻለህ አለው እርሱም አዎን አለ ሁለቱም ተስማምተው ወደ አስቄጥስ ገዳም በአንድነት ተጓዙ ሦስት አረጋውያን መነኰሳትንም አገኙ አባ በኪሞስም ከእነርሱ ጋር ሃያ አራት ዓመታትን ኖረ። ❖ ከዚህም በኋላ አባ በኪሞስ ከዚያ ተነሥቶ የሦስት ቀን ጐዳና ያህል ተጓዘና ሩቅ ወደ ሆነ በረሀ ውስጥ ገባ ሰይጣናትም በእሪያዎችና በዘንዶዎች አምሳል ሁነው መጡበት ሊነክሱትም አፋቸውን ከፍተው ከበቡት እርሱ ግን የአጋንንትን ሐሳብ አወቀ በእግዚአብሔርም ኃይል እፍ አለባቸው በዚያንም ጊዜ ተበተኑ። ❖ እርሱም ወንዝ አገኘ ሰባት ሰባት ቀን እየጾመ በዚያ ሦስት ዓመት ኖረ በሱባዔውም መጨረሻ በመሀል እጁ ተምር መልቶ ያንን ይመገባል ውኃም በጥቂቱ ይጠጣል ሁለት ሽህ አራት መቶ ጊዜ በሌሊት እንዲሁም በቀን ሁለት ሽህ አራት መቶ ጊዜ አቡነ ዘበሰማያትን ይጸልያል። ❖ ከዚህም በኋላ አርባ አርባ ቀን እየጾመ ሃያ አራት ዓመታት ያህል ኖረ አርባውም ቀን ሲፈጸም አንድ ጊዜ ይበላል ከዚህም በኋላ አንድ ጊዜ ቆዳው ከዐጥንቶቹ ጋር እስቲጣበቅ ሰማንያ ቀን ጾመ በዚያንም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ይበላና ይጠጣ ዘንድ እንጀራና ውኃን አመጣለት ያም ውኃና እንጀራ ሳያልቅ እስከ አረፈ ድረስ ብዙ ዓመታትን ኖረ። ፈጣሪ እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ ተገልጦ ወደ አገሩ እንዲመለስ አዘዘው በዚያንም ጊዜ ተነሥቶ ሔደ ወደ አገሩም ደርሶ በዚያ ታናሽ ማደሪያ ጎጆ ሠርቶ በውስጡ ብቻውን የሚኖር ሆነ ወደርሱም ለሚመጣ ሁሉ መጠጊያና ወደብ በጎ አለኝታም ሆነ ሰዎችም ሁሉ በትምህርቱ እየተጽናኑ ኖሩ ንጹሕ በሆነ አምልኮቱ በትሩፋቱና በተጋድሎው መንፈሳዊ ቅናትን ይቀኑበት ነበር። ❖ በአንዲት ዕለትም ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተሸክሞ ወደ ኤፍራጥስ ምድር አደረሰው የዚያ አገር ሰዎች በመተላለፍ ከእውነተኛ ሃይማኖት ወጥተው ነበርና ሁሉንም ወደ ቀናች ሃይማኖትና ወደ በጎ ምግባር መለሳቸው ከዚያም ወደ ቦታው ተመለሰ። ❖ አንድ ጊዜም ሽጦ ምግቡን ያገኝ ዘንድ አገልግሎችን ተሸክሞ ወደ ከተማ ሲሔድ በጎዳና ላይ ደክሞት አገልግሎቹን አስቀምጦ ጥቂት ያርፍ ዘንድ ተቀመጠ በዚያንም ጊዜ ከአገልግሎቹ ጋር የእግዚአብሔር ኃይል ተሸክሞ ወደሚሻው ቦታ አደረሰው። ❖ በዚያንም ወቅት አባ ሲኖዳ ከፍተኛ የዕንቈ ባሕርይ ምሰሶ በራእይ አየና ይህ ታላቅ ምሰሶ ምንድን ነው ብሎ ደነገጠ የእግዚአብሔርም መልአክ ተገልጦ ይህ አባ በኪሞስ ነው አለው። ❖ አባ ሲኖዳም ወዲያውኑ ተነሥቶ ወደ አባ በኪሞስ አገር እስቲደርስ በእግሩ ተጓዘ ከዚያችም ቀን በፊት ከቶ አላየውም ነበር በተገናኙም ጊዜ እርስበርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ። ❖ አባ በኪሞስም ወጥ ሊአበስል ወደደ አባ ሲኖዳንም ይቺን እንስራ ያዛትና ሔደህ ውኃ ቀድተህ መልተህ አምጣልኝ አለው በዚያንም ጊዜ አባ ሲኖዳ ተነሣና ያቺን እንስራ ተሸከማት ውኃውንም ቀድቶ መልቶ አመጣለት ወጡንም ፈልቶና በስሎ አገኘው በዚያንም ጊዜ አባ በኪሞስ መሆኑን አወቀ ከእርሱም ጋር ሰላምታን ደገመ እጅ በመነሣሣትም ሰላምታ ተለዋወጡ፤ ከዚህም በኋላ አባ ሲኖዳ ስለርሱ ያየውን ራእይ ነገረው በእርሱም ዘንድ ጥቂት ቀኖች ኖረ። ❖ ዳግመኛም በአንዲት ቀን በአንድነት ሲጓዝ የሞተ ሰው ራስ አገኙ አባ ሲኖዳም በበትሩ ነቅነቅ አደረገውና ምውት ሆይ ያየኸውን ትነግረንና ታስረዳን ዘንድ ተነሣ አለው በዚያን ጊዜ ነፍሱ ወደ ዐፅሙ ተመልሳ ሥጋ ለብሶ ተነሣና ሰገደላቸው በሲኦል የሚሠራውንም ሁሉ በየወገናቸውም በውስጧ የሚሠቃዩትን እርሱም አረማዊ እንደሆነ ነገራቸው። ❖ እንዲህም አለ ክብር ይግባውና በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ያመኑ ትእዛዙን ግን ያልጠበቁ በአሕዛብ ሥራና በአረማውያን ርኵስት የኖሩ ከእኛ በታች የሚኖሩ ክርስቲያኖች አሉ አለ ቅዱሳንም ተመልሰህ ተኛ አሉት ወዲያውኑ እንደ ቀድሞው ሆነ። ❖ ከዚህም በኋላ አባ ሲኖዳ ቅዱስ በኪሞስን ተሰናብቶ ወደ ቦታው ተመለሰ። ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ ቅዱስ አባ በኪሞስ አገልጋዩን ጠርቶ በኖረበት ቦታ ሥጋውን እንዲቀብር አዘዘው። ❖ ከዚህም በኋላ በሆድ ዝማ ሕመም ጥቂት ታመመ፤ ቅዱሳንን በአንድነት ወደርሱ ሲመጡ አያቸው በዚያንም ጊዜ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ፤ መላእክትም ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት እስከአደረሷት እያመሰገኑና እየዘመሩ አሳረጓት፤ መላ ዕድሜውም ሰባ ዓመት ሆነ ዐሥራ ሁለት ዓመት በዓለም ውስጥ ሃምሳ ስምንት ዓመት በምንኵስና ሥራ ኖረ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 📌 በዚችም ቀን የኤጲስቆጶሱ በርተሎሜዎስና የሰማዕቱ በጥላን መታሰቢያቸው ነው በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 📌 ታሕሳስ 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ታላቁ አባ በኪሞስ 2.ቅዱስ በርተሎሜዎስ 3.ቅዱስ ቴዎድሮስ 4.ቅዱስ በጥላን 📌 ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ያሬድ ካህን 2.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት 3.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት 4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ 5.ቅድስት ሐና ቡርክት
Show all...
📌 ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ 2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ 3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ 4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ) 5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት 6.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ 7.ቅዱስ እፀ መስቀል
Show all...