cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

LOGOS CHRISTIANS' CHANNEL

ሎጎስ ክርስቲያን ቻናል የተሐድሶ ድምፅ LOGOS CHRISTIANS' CHANNEL THE VOICE OF REVIVAL መጸሐፍቅዱሳዊ ፣ጥቅሶች ፣መልዕክቶች ፣መዝሙሮች ፣ጥያቄዎች እና ሌሎችንም ክርስቲያናዊ መርሐ ግብሮች ከፈለጉ ✝👇👇👇👇👇✝ @ logoschristianschannel @ logoschristianschannel @ logoschristianschannel

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
443Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
Repost from Zaphnath-paaneah
🔘ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም!! 📌ኤፌሶን 2 ⁸ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ⁹ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ✍ከደህንንነት ጋር በተያያዘ መፅሃፍ ቅዱሳችን ግልፅና ቀጥተኛ አቋም ይለው ሲሆን ብዙ ሰዎች እንዲሁም አንዳንድ የኃይማኖት ተቋማት ግን ሲያወሳሰቡት ይስተዋላል....ይህም የመጀመሪያዎቹ ካለማወቅ የተነሣ ሲሆን(መፅሃፍ ቅዱስ ትተው ሌሎች በሰው የተደረሱ መፅሃፍትን በማንበብ) ሁለተኞቹ ግን እውነቱን በደንብ እያወቁ ነገር ግን እውነቱን መስበክ ቢጀምሩ የግል ጥቅማችን ሊነካ ይችላል ብለው በፍርሃትና በይሉኝታ ገመድ ተተብትበው የተቀመጡት ናቸው.....የአምላክ ቃል እንደሚያስረዳን ከሆነ ግን ወንጌላችን ሙሉ በሙሉ የሚነግረን የእግዚአብሔር ልጅ ስለሆነው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነና እርሱም ደግሞ እንደተሰቀለ፣ በሶስተኛውም ቀን በክብር እንደተነሣ፣ ወደ ሰማይም እንዳረገ እና በአብ ቀኝም ተቀምጦ ስለ እኛ ዘወትር እየማለደልን ስላለው ፍፁም ሰው፣ ፍፁም አምላክ ስለሆነው ጌታ ነው:- 📌ሮሜ 1 ¹-² ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ። ³-⁴ ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ✍ይህ ጉዳይ ያለማናችንም አስተዋፅዖ በራሱ በእግዚአብሔር የተሰራልንን የቤዛነት ሥራ በመሆኑ በፍፁም ልባችን አምነን በመቀበልና በአፋችን ለሰዎች በመመስከር መፅደቅም ሆነ መዳን እንችላለን.....ምክንያቱም እርሱ የሠራልን ሥራ እኛን ለማፅደቅም ሆነ ለማዳን በቂ ብቻ ሳይሆን ከበቂ በላይ ነውና #ሃሌሉያ እግዚአብሔር ይመስገን#...በኤፌሶን ምዕራፍ ሁለት ላይ እግዚአብሔር በኃጢያት ምክንያት ጠፍቶ የነበረውን ሰው ለማዳን በነበረው ዕቅድ የማንንም አስተዋፅዖ ለምን እንዳልፈለገ ይነግረናል:- 📌ኤፌሶን 2 ⁴ ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ⁵ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ ⁶-⁷ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ✍ከላይ በጥቅሱ ላይ እንደምንመለከተው እግዚአብሔር መዳናችንን ሙሉ በሙሉ ራሱ የጨረሰው አንደኛ የፀጋው ባለጠግነት ይመሰገን ዘንድ ነው ሲቀጥል ደግሞ እኛ የሰው ልጆ በሥራ የመፅደቅ ብቃት ስለሌለን ነው....በስራ እንፀድቃለን ብላችሁ የምታስቡ ሰዎች ከፀጋው ወድቃችኃል:- 📌“በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል።”ገላትያ 5፥4 📌ኤፌሶን 2 ⁸ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ⁹ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ✍ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጪ የሆነ ወንጌል ወንጌል ሳይሆን ወንጀል በመሆኑ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስጠይቅም ጉዳይ ነው....የኢየሱስ ወንጌል ሰዎችን የሚያድነውና ነፃ የሚያወጣው እንደወረደ ሲሰበክ ብቻ እንጂ ከተለያዩ የሰው ፍልስፍናዎች ጋር ሲደባለቅ አይደለም...ለዚህም ይመስላል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከክርስቶስ ወንጌል ጋር የማይስማማ ማንም ቢኖር የተረገመ ይሁን ብሎ በድፍረት የተናገረው:- 📌ገላትያ 1 ⁶ በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤ ⁷ እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ። ⁸ ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን። ⁹ አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን። ✍እግዚአብሔር የልቦና አይኖቻችንን ይክፈትልን(..ነገ ብቀጥለው ሳይሻል አይቀርም..እወዳችኃለሁ) @ZaphnathPaaneah1 @Yoni4Christ #Share #Join
Show all...
“ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።” — ሉቃስ 24፥5
Show all...
በእርሱ ቁስል እኔ ተፈወስኩ!!! የዛሬ 1989 አመታት በፊት በመስቀል ተሰቅሎ ብሉይን ዘግቶ አዲስን ሲከፍት ፤እኔ ዳንኩ። ያኔ ነው የዳንኩት ፤እርሱ ሲቆስል እኔ ግን ስፈወስ ፣ ያኔ ነው የዳንኩት፤ ❣በከበረው ደሙ አለሙን ሲቀድስ፣ እጆቹና እግሮች በሚስማር ተይዘው☦፣ ልብ ምቱ ደም ዝውውሩ ተዛብተው፣ ለኔ ብሎ ተሰቅሎ መተንፈስ ሲያቅተው፤ እኔ ግን በሰላሙ እወጣለሁ ፣እገባለሁ ፣ እተነፍሳለሁ ልብ ምቴም ጤነኛ ነው። አይኑን አስረው ሲመቱት፣ ግንባሩን በእሾህ ሲያስጨንቁት፣ መስቀል አሸክመው ሲገፉ ሲገፈትሩት ፣ ልብሱን ሲገፉት ፣እርቃኑን ሲያሳዩት፣ያለልክ ገርፈው ቆዳውን ሲያበላሹት ፤ እኔ ግን የፅድቅን አክሊል ደፍቼ ፣ብርሃንን ለብሼ 🧖፣ እንኳን ልመታ ይቅርና ፣ እንኳን ልገፋ ወዜ እያማረ መጣ ድሮ ከነበረው። ውሃ ቢለምን ሆምጣጤ ሲሰጡት ፣የደም ላብ እስኪያልበው ሲጨነቅ፤ እኔ ከሕይወት ውሃ ምንጭ 💧እየጠጣሁ ያለጭንቀት በደስታ ኖራለሁ።🤗 በእርሱ ቁስል እኔ ተፈወስኩ!!! ይህ ብቻ አይደለም እርሱ ተፈፀመ ሲል ፤ እኔ አዲስን ሕይወት ጀመርኩ፣ እርሱ ከአባቱ ሲለይ ፤ እኔ አባት አገኘሁ። ይህ ነው"በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን!" ማለት። “እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።” — ኢሳይያስ 53፥5 መልካም በዓል !!! @logoschristianschannel @logoschristianschannel @logoschristianschannel
Show all...
ቦታው የኔ ነው የሞተበት❤ #ፋሲካችን_ክርስቶስ_ታርዶልናል🤍 @christian_mezmur
Show all...
ቦታው የኔ ነው የሞተበት❤ #ፋሲካችን_ክርስቶስ_ታርዶልናል🤍 @christian_mezmur
Show all...
“ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።” — ሉቃስ 24፥5
Show all...
“ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።” — ኢሳይያስ 1፥18
Show all...
እዩልኝ | Singer Jerry | የዘማሪት ጄሪ አዲስ ድንቅ አምልኮ/ True Light Tv/ Meklit mamo Worship/ Nov 19, 2021
Show all...
#ድንቅ_እና_አስተማሪ_መልዕክት ⛵️ ⛵️የመርከቡ ተሳፋሪ ⛴ ⛴ ከዘመናት በፊት አንድ ሰው የሚኖርበትን አገር ለመቀየር ያለውን ሁሉ ሸጦ ወደ ሌላኛው አገር ሲገባ የሚያስፈልገውን ነገር ብቻ አሽጎ ጉዞውን በመርከብ ጀመረ፤ ጉዞው ሁለት ወር ይፈጅ ነበር፡፡ ታዲያ ይህ ሰው በመርከብ ቆይታው ሁልጊዜ በመመገቢያ ሰዓት ሰዎች ወደ መርከቡ ሬስቶራንት በመሄድ እንደልባቸው ይበላሉ፣ ይጠጣሉ ይዝናናሉ እርሱ ግን በራሱ ክፍል ውስጥ ተቀምጦ ለመንገዱ የገዛውን ደረቅ ኮቾሮ ብስኩት ይበላ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ መርከቧ ጉዞዋን አጠናቃ ወደ ታሰበው አገር ለመድረስ ሁለት ቀን ይቀራታል፤ በዚህ ጊዜ ይህ ሰው በክፍሉ ውስጥ ተቀምጦ ያንን ደረቅ ብስኩት እየበላ እያለ የመርከቡ አስተናጋጅ ድንገት ወደ ክፍሉ ገባ። ባየውም ጊዜ “ሌላ ምግብ አላስፈለገህም ማለት ነው ለምንድነው ይሄን የደረቀ ብስኩት የምትበላው?” በማለት ጠየቀው ሰውዬውም “ሁልጊዜ ሰዎቹ ሲበሉና ሲጠጡ፣ ሲዝናኑም እዚህ ክፍሌ ውስጥ ሆኜ አያለው ነገር ግን እንደ እነርሱ የምዝናናበት በቂ ገንዘብ ስለሌለኝ ላለፉት ሁለት ወራት ስበላ የነበረውን ደረቅ ብስኩት ነው” በማለት ይመልስለታል፤ ያን ጊዜ አስተናጋጁ በማዘንና በመደነቅ “ትኬት ስትቆርጥ የከፈልከው ገንዘብ እኮ ሁሉንም የሚያጠቃልል ነው፤ እንደነሱ መብላት መዝናናት ትችል ነበር ይህን ባለማወቅህ በጣም አዝናለሁ” አለው፡፡ ሰውዬው ባሳለፋቸው የመከራ ቀናት በጣም ተጸጸተ የቀሩትን ቀናት ሲያስብ እንደሰው መሆን የሚችልባቸው ሁለት ቀን ብቻ ነበረች፤ ባለማወቁ በራሱ ተበሳጨ፣ አዘነ፡፡ 📌 አያችሁ አለማወቅ ከስንት ነገር እንደሚያጎድል? ክርስቲያን በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘውን ጽድቅ ካለማወቁ የተነሣ ሕይወቱን ዛሬም የሥራና የሕግ በማድረግ ይታገላል፡፡ ጽድቅ በእግዚአብሔር ፊት እንድንቆም የሚያስችለን፣ ሙሉ መብት ያስገኘልን ቅዱስ የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስለ እኛ ሲል ኃጢአተኛ ሳይሆን ኃጢአት ሆኖ ጽድቅ ያደረገን እርሱ ነው፡- “እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።” — 2ኛ ቆሮ 5፥21 🧷 ይህን እወቁ! ክርስቲያን ከኃጢአት ጋር መጫወት የሌለበት እግዚአብሔር ስለሚቀጣው፣ ተቆጪ አምላክ ስለሆነ ሳይሆን ማንነቱን ስለማይመጥንና ኃጢአት ተራ ነገር ስለሆነ ነው፡፡ እስኪ ልጠይቃችሁ ነጭ በነጭ ለብሳችሁ የሞላ ታክሲ ውስጥ ተጋፍታችሁ የምትገቡ ስንቶቻችሁ ናችሁ? በእርግጠኝነት ልብሳችሁ ስለሚቆሽሽ ያልሞላና ግፊያ የሌለበትን ትመርጣላችሁ፡፡ አያችሁ ልክ እንደዚሁ የጽድቅ ልብሳችን የሆነውን ኢየሱስን ይዘን ተራ የሆነ ኃጢአት ሰፈር ልንውል የማንችለው ኢየሱስ ስለእኛ ኃጢአት መሆኑ ሲገባን ብቻ ነው፡፡ ያከበረውን ሕይወቴን በክብር እጠብቀዋለሁ! ተራ ተርታ አልገኝም! @logoschristianschannel @logoschristianschannel
Show all...
አያለሁ!!! ሳሙኤል ተ/ሚካኤል @logoschristianschannel @logoschristianschannel
Show all...
#ሰዎች ለምን ረሱኝ አትበል የማይረሳ አለ! በሰማይ ለአንተም ቀን ይመጣል! እንደ #ዮሴፍ መታሰብ ይሆናል! ህልምህ/ሽ ህልም ሆኖ አይቀርም! ወዳጅም ጠላትም ባለበት መፈጸሙ አይቀርም። #እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና በመንገድ ባለ መከራ አትናወጥ! ጥቂት ነው የቀረ ሹመት አለ! ክብር አለ! በኢየሱስ ስም🔥🔥🔥እንኳን ሸጡህ/ሽ! እንኳንም ገፉሁ/ሽ! እንኳን ጠሉህ/ሽ! እንኳንምን እረሱህ/ሽ! ቀን አለ! ለችግራቸው መፍትሔ ከአንተ ሚቀዳበት: ማረን ብለው ሚወድቁበት: በገዛ ክፋታቸው ሚታመሙበት ቀን አለ! ተወው አትከፋ መንገዱ ነው ወዳጄ! ዳገት መዳረሻውማ ፍጻሜው የተዋበ ነው እግዚአብሔር ሰርቶ ጨርሶታል!❤🙏 @logoschristianschannel @logoschristianschannel
Show all...
#አየርላንድን_የለወጠው_ሐዋርያ የሴንት ፓትሪክ የህይወት ታሪክ ክፍል-15 በፍቅር እና በሰላም የተቀበሉት ለመምሰል በመርዝ የተሞላ ጽዋ ሰጡት። ፓትሪክም በጽዋው በክርስቶስ ስም በማለት መርዙ ከጽዋው ውስጥ እንዲለይ ፀለየ። ወዲያውም መርዙ ለብቻው ሲንሳፈፍ ወደ መሬት አፍስሶ ንፁሁን ወይን ጠጣው። ንጉሡ እና ጠንቋዩ ከእርሱም ጋር የታደሙት ባለስልጣኖችና ተጋባዥ እንግዶች ያደረገውን ባዩ ጊዜ ተደነቁ። የዚህን ጊዜ የንጉሡ ጠንቋይ ለፓትሪክ "አንተ እንዲህ የማድረግ ችሎታ ካለህ ለምን በአምላኮቻችን ስም ተአምራት አናደርግም የሚያሸንፍ እርሱ አምላክ ይሁን" ብሎ ሃሳብ አቀረበለት። ፓትሪክም ሁኔታውን ተጠቅሞ የወንጌልን ታላቅነት ለመስበክ ሰለፈለገ በውድድሩ ይስማማል። ጠንቋዩም ፦"እኔ አሁን ይህንን ቀን በዚህ አካባቢ ጨለማ እንዲሸፍነው አደርጋለሁ አለና የተወሰኑ ድግምቶችን ተናግሮ አከባቢውን በጨለማ እንዲለወጥ አደረገው።" ፓትሪክም ፦"ይህንን ጨለማ አሁን እንዲጠፋ አድርግ አለው።" ጠንቋዩም ፦"ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ነገ እስኪነጋ ድረስ እንደዚህ ማድረግ አልችልም"ብሎ መለሰለት። ፓትርክም፦"እኔ ግን ይህንን ማድረግ እችላለሁ "በማለት የያዘውን በትር ዘርግቶ ጨለማው እንዲወገድ ብርሃን መልሶ እንዲሆን ተናገረ። መልሶም ፀሀያማ ቀን ሆነ። ህዝቡም ለሁለቱም በአድናቆት አጨበጨቡ። በመጨረሻም ከሁለቱ አንዱ አሸናፊ የሚሆንበት ውድድር ተደረገ። ለሁለታችንም ... ክፍል 16ን በቀጣይ ሳምንት ይጠብቁን።
Show all...
ሰላም ለናንተ ይሁን እስኪ አንድ ነገር ላስታውሳችሁ 👉በዛሬው ቀን ብዚ ሰዎች ተወልደዋል ደግሞ ብዙ ሰዋች ሞቷል ። 👉 በህይወት እየኖሩ ያሉትም ፣ ⚡️አንዳንዶቹ ሰዋችን ገድለዋል ⚡️አንዳንዶችም ሰዋችን አድነዋል 💫 አንዳንዶቹ ቀኑን ሙሉ ያለ ምንም ትርፍ ቀናቸው ባክኗል 💫አንዳንዶቹ ስለ ወንጌል ብሎ ዋጋ ከፍሏል ጌታንም አክብሯል ❓❓❓❓❓❓❓❓ እናነተሰ ውሎ አዳራችሁ ምን ይመስላል ⁉️⁉️ ጌታን እያከበራችሁ ነው ወይስ በእናንተ እያዘነ ነው ❔❔❔ ቃሉስ ምን ይላል ⚠️ “ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና፤ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር፤” — ምሳሌ 23፥17 💛በጌታ ፍቅር እለምንሃለሁ ሼር አድርግ 💛 @logoschristianschannel @logoschristianschannel
Show all...
በጨመረልኝ ቀን ዘማሪ ሳሚ 😐ሁሉን ወስደው ባዶ ቢያስቀሩኝ😐 🥱ሀ... ብጀምር ምንም ባይኖረኝ0⃣ 🤷ጉዳዬ አይደለም የእኔስ ጭንቀቴ🤔 🤗ጉልበታሙ ስምህ እስካለ በአፌ😀 😇ኢየሱስ ማለቴን እጀምረዋለው🙏 💫የነገሬ ስኬት እዛ ውስጥ ነው ያለው🤏 😐ከባዶ ነገር ላይ ከፍ ያረገኛል ☄ ✨ማንም ያላየውን ክብር ያሳየኛል😲 @logoschristianschannel @logoschristianschannel
Show all...
መጸሐፍቅዱሳዊ ጥቅሶች መልዕክቶች እና ጥያቄዎች ከፈለጉ ✝👇👇👇👇👇✝ @logoschristianschannel ይቀላቀሉ !!!
Show all...
👉"የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም በኢየሱስ እና በሐዋርያቱ"👈 የመጽሐፍ ቅዱስ የአተረጓጎም ዘዴ በየዘመኑ የተለያየ መንገድ እንደነበረ ስለ አተረጓጎም ዘዴ ታሪክን ስናጠና እናገኛለን። የብሉይ ኪዳንን መጻሕፍት ኢየሱስና ሐዋሪያቱ በዋነኝነት የተጠቀሙ ሲሆን፤ ለመልዕክቶቻቸው ማጠናከሪያ ይሆን ዘንድ በተለያየ የአተረጓጎም ዘዴ ቃሉን ተጠቅመዋል። እነርሱ የተረጎሙበትን የአተረጓጎም ዘዴ እና የብሉይ ኪዳን ቃል አጠቃቀም ስናነብ እንዲሁ አንብበን ፊት ለፊት የምናገኘው የተጠቀሙት አንዳንድ ጥቅስ ትርጉም የሚያወራውን ስናይ እና እነሱ ስለሚሉት ነገር ነውን???ብለን ስንጠይቅ ሀሳቡ ስለሌላ እንደሚያወራ እንመለከታለን።ነገር ግን ከእነርሱ ሀሳብ ሊገናኝ በሚችልበት መልኩ ቃሉን በድፍረት ይጠቀሙታል።ተሳስተው ነው ልንል አንችልም ግን ቃሉ እነሱ ተርጉመው ስለተናገሩትም ሀሳብ ያወራል ማለት ነው።ስለዚህ "ትርጉም አንድ ነው አተገባበሩ ልዩ ልዩ ነው" እንደሚለው "ትርጉም በተለያየ መልኩ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው አተገባበሩም ልዩ ልዩ ነው" ወደሚለው የአተረጓጎም ሀሳብ ልናመራ ይገባል ማለት ነው።
Show all...
. ተራራው አዜብ ሐይሉ | New Clip@yedestaye_elilta ◁ ▷ @yedestaye_elilta ◁ ▷Join Us◁
Show all...
. ዘማሪ ዳዊት ጌታቸው °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° አምንሀለሁ: ሁለተኛ አልበም ▽Join it▽ @Yemezimur_Maikel @Yemezimur_Maikel
Show all...
ቻናሉን ወደውታል ?
Show all...
👍 5
#አየርላንድን_የለወጠው_ሐዋርያ የሴንት ፓትሪክ የህይወት ታሪክ ክፍል-14 መዝሙሩና የእምነት አዋጁ እንዲህ ይል ነበር:- "ክርስቶስ ከእኔ ጋር ነው፣ ክርስቶስ ከፊቴ ነው፣ ክርስቶስ ከኋላዬ ነው፣ ክርስቶስ በእኔ ውስጥ ነው፣ ክርስቶስ በቀኝና በግራዬ ነው ተኝቼም ክርስቶስ ከእኔ ጋር ነው ተቀምጬም ክርስቶስ ከእኔ ጋር ነው። በጎዳናዬ ላይም ከእኔ ጋር ነው። ክርስቶስ ስለእኔ በሚያስቡ ልቦች ሁሉ ላይ ነው። ክርስቶስ ከእኔ ጋር በሚነጋገሩት ሁሉ ላይ ነው። ክርስቶስ በሚያዩኝና በሚሰሙኝ ሁሉ ፊት ነው። የእግዚአብሔር ኃይል በእኔ ላይ ነው፣ የእግዚአብሔር ጥበብ ይመራኛል። የእግዚአብሔር አይን ከፊቴ ነው፣ የእግዚአብሔር ጃሮዎች ይሰሙኛል። የእግዚአብሔር ቃል የእኔ ነው ፣ የእግዚአብሔር እጁ ይመራኛል። የእግዚአብሔር መንገድ ከፊቴ ተዘርግቷል። የእግዚአብሔር ጋሻ ይጋርደኛል። የእግዚአብሔር ሰራዊት ከክፉዎች ያድኑኛል"የሚል ነበር የእምነት አዋጁ። ይህንን እየዘመረና እያወጀ ሲሄድ በምን ውስጥ ያሸመቁት ወታደሮች ጋር ሲደርስ ከየት መጣ የማይባል ደመና መጥቶ ፓትሪክንና ሰዎቹን ጠቅልሎ ከወታደሮቹ ሰውሮ አሳለፋቸው። ወታደሮቹ ዓይናቸውን ሲከፈት ያዩት ቀድሞም በሜዳው ላይ የነበሩትን አጋዘኖች እንጂ ሌላ ነገር አልነበረም። ንጉሱ በመንገድ ያስቀመጣቸው ወታደሮቹ በማንኛውም ጊዜ ገድለውት የሞቱን ዜና ይዘውለት እንደሚመጡ ይጠብቅ ነበር። ነገር ግን ፓትሪክ ምንም ሳይሆን በመሃከላቸው ተገኘ። በዚህም ንጉሡ እና ታዳሚዎቹ ተደናገጡ።ይኸኛው እቅድ እንዳልሰራ ባዩ ጊዜ "እቅድ ሁለት" ያሉትን በመርዝ የመግደል እቅድ ለንጉሡ ጥንቆላ "ሉካት" የተባለው ጠንቋይ እንዲሰራው ተደረገ። በፍቅር እና በሰላም የተቀበሉት ለመምሰል በመርዝ የተሞላ ጽዋ ሰጡት። ፓትሪክም በጽዋው በክርስቶስ ስም በማለት መርዙ ከጽዋው ውስጥ እንዲለይ ... ክፍል 15ን በቀጣይ ሳምንት ይጠብቁን። ----14----
Show all...
ልጅ መሆን በክርስቶስ በማመናችን የእግዚአብሔር ልጆች ሆንን። ይህ በክርስቶስ ያግኘነው ደህንነት አንዱ ገጽታ ነው። አስቀድመን የስይጣን ባሪያዎች ነበረን አርሱ የስዎች ሁሉ ፈጣሪ ቢሆንም የሁሉም አባት አይደለም። እርሱ በኢየሱስ ለሚያምኑት ብቻ አባት ነው። የክርስቶስ ጽድቅ በእምነት ስንቀበል ብቻ የእርሱ ቤተሰብ አድርጎ ይቀበለናል። ማንኛውም በማደጎ ያለ ልጅ በአሳዳጊነት የወስደውን ሰው ሀብት መውረስ ይችላል በሥጋ ክእሳዳጊው የተወለደ ባይሆንም እንኳ በሕግ ልጅ ትደረጎ ስለሚቆጠር የልጅነት ሙሉ መብት ይቀበላል። ቀድሞ በፍጥረታችን ሃጢአትኞች የነበረን እኛም በክርስቶስ ኢየሱስ በመንፈስ የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ልጆች ሆነናል። በስማይ ሙሉ ውርስ እንቀበላለን። ከመዳናችን አንድ ታላቅ በረከት የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን ነው።ይህም የእግዚአብሔር ባሕርይ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ወደ እኛ ተዋሀደ ማለት ነው። ልጅ የሥጋ አባቱን እንደሚቀርብ እንዲሁ እኛም ክእግዚአብሔረ ጋር የቀረበ ግንኙነት ማድረግ እንችላለን እንዲሁም እንደ እግዚአብሔር ልጆች መኖር አለብን። የእግዚአብሔር ልጅ መሆን ታላቅ በረከትና ደስታ ነው። @logoschristianschannel 🔥🔥@lewotatoch🔥🔥 🔥🔥@lewotatoch🔥🔥
Show all...
ራእይ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴-⁵ ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥ ⁶ መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን። ⁷ እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።
Show all...
#አየርላንድን_የለወጠው_ሐዋርያ የሴንት ፓትሪክ የህይወት ታሪክ ክፍል-13 ንጉሡ ግን ሽንፈቱን ሲያይ ለፓትሪክ "ነገ ወደ ቤተ መንግስቴ መጥተህ ህግ መጣስህን ህዝብ ፊት ተናዘዝ።"ብሎ አዞት ሄደ። ፓትሪክም አጋጣሚውን ተጠቅሞ ወንጌል ለመስበክ ሰለፈለገ በደስታ እንደሚመጣ ገለጠለት። ፓትሪክም በቀጣዩ ቀን ከእርሱ ጋር የሚያገለግሉ 8 አገልጋዮችና አንድ ደቀመዝሙር ሆነው ወደ ንጉሡ ቤተመንግሥት ተጓዙ። ንጉሡ ግን በፓትሪክ መሸነፉ እልህ ስላገባው በመንገድ ላይ ሳለ እንዲገሉት ወታደሮችን ላከ ። ወታደሮችም ጫካ ውስጥ አሸምቀው እየጠበቁት ሳለ ፓትሪክና በወቅቱ በነበረው በክርስትናው ዓለም የሚታወቅበት መዝሙርና የእምነት አዋጅ እያወጀ ይሄድ ነበር። መዝሙሩና የእምነት አዋጁ እንዲህ ይል ነበር:- "ክርስቶስ ከእኔ ጋር ነው፣ ክርስቶስ ከፊቴ ነው፣ ክርስቶስ ከኋላዬ ነው፣ ክርስቶስ በእኔ ውስጥ ነው፣ ክርስቶስ በቀኝና በግራዬ ነው... ክፍል 14ን በቀጣይ ሳምንት ይጠብቁን። ----13----
Show all...
Show all...
#የሕይወት ትርጉም ኢየሱስ ➥ ወንድሜ በሕይወትህ አንድ ቀን እደርስበታለው ብለህ ያሰብከው ህልምህ የደረስክበት ቀን ሕይወትህ ከዚያን ቀን በኋላ ትርጉም እንደሚሮረው የምታስብ ከሆነ እንግዲያውስ ልንገርህ አንተ ከሁሉም ሰው ይልቅ ሞኝ ነህ። መኖርህ ትርጉም ሊያገኝ የሚገባው ዛሬ ነው። አንተ እንድትኖር የተፈለገው ዛሬን ነው ። እርካታና ደስታ ከብዙ ጥረትና ስራ በኋላ የምትደርስባቸው እንደሆኑ አስበህ ሩቅ አታድርጋቸው። ወንድሜ ከሰሎሞን ተማር እንጂ ሕይወትህ ትርጉም የሚያገኘው በሰበሰብከው ገንዘብ፣ዕውቀት፣የሰዎች ፍቅር፣የእናንትህና የአባትህ አድናቆት አይደለም።ንጉስና ጠቢብ የነበረው ሰሎሞን አንተ በሕይወት ዘመንህ የምትመኛቸው ነገሮች በሙሉ እንዲያውም ከዚያ በላይ ነበረው ነገር ግን ለሰለሞን ሁሉ ከንቱ ነበረ። እነዚህ አሁን አንተ እየሰበሰብካቸው ያለሀቸው ነገሮች ያንተን ሕይወት ትርጉም ሊሰጧት በፍፁም አይችሉም። ሕይወትህን ትርጉም የሚሰጣት ነገር አጠገብህ ነው ያለው። ኢየሱስ ይባላል! ወንድሜ አይንህን ክፈት ደስታ አጠገብህ ነው ያለው። እርካታ አጠገብህ ነው ያለው። ምናልባት ይሄን የምታነቡ ፕሮቴስታንት ልጆች ለቀባሪው አረዳው በሚል አስተሳሰብ እያነበባቹት ሊሆን ይችላል ሚገርመው ግን መልዕክቱ ለናንተም ጭምር ነው። የተቀበልከው ሐይማኖት አይደለም ሕይወት ነው። የዘለዓለም ደስታና ዕርካታ ያለበት ሕይወት። የሚያሳዝነው ግን አንተም ጌታን እንደማያውቅ ሰው ሕይወትህን በምትሰበስባቸው ነገሮች ትርጉም ልትሰጣት መሞከርህ ነው። “የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና።” — ሮሜ 14፥17 ➛ ብራዘር የመዳን ቀን ዛሬ ነው የሚለው ቃል ለጴንጤም የተፃፈ ነው። የደስታ ቀን ዛሬ ነው! የመርካት ቀን ዛሬ ነው! የተቀበልከው ፅድቅ የዛሬ ነው። በእግዚአብሔር አለም ነገ የሚባል ነገር የለም። ሁሉም ነገር አሁን ነው። አሁንና አሁን ነው። ጌታ አሁን ከወደደህ በላይ ነገ አይወድህም። ጌታ እንድትደሰት የሚፈልገው አሁን ነው። “ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤” — 1ኛ ዮሐንስ 1፥2 ፀጋና ሰላም ይብዛላቹ። @logoschristianschannel @logoschristianschannel @logoschristianschannel @logoschristianschannel 🔥@lewotatoch🔥🔥 🔥@lewotatoch🔥🔥
Show all...
#የሕይወት ትርጉም ኢየሱስ ➥ ወንድሜ በሕይወትህ አንድ ቀን እደርስበታለው ብለህ ያሰብከው ህልምህ የደረስክበት ቀን ሕይወትህ ከዚያን ቀን በኋላ ትርጉም እንደሚሮረው የምታስብ ከሆነ እንግዲያውስ ልንገርህ አንተ ከሁሉም ሰው ይልቅ ሞኝ ነህ። መኖርህ ትርጉም ሊያገኝ የሚገባው ዛሬ ነው። አንተ እንድትኖር የተፈለገው ዛሬን ነው ። እርካታና ደስታ ከብዙ ጥረትና ስራ በኋላ የምትደርስባቸው እንደሆኑ አስበህ ሩቅ አታድርጋቸው። ወንድሜ ከሰሎሞን ተማር እንጂ ሕይወትህ ትርጉም የሚያገኘው በሰበሰብከው ገንዘብ፣ዕውቀት፣የሰዎች ፍቅር፣የእናንትህና የአባትህ አድናቆት አይደለም።ንጉስና ጠቢብ የነበረው ሰሎሞን አንተ በሕይወት ዘመንህ የምትመኛቸው ነገሮች በሙሉ እንዲያውም ከዚያ በላይ ነበረው ነገር ግን ለሰለሞን ሁሉ ከንቱ ነበረ። እነዚህ አሁን አንተ እየሰበሰብካቸው ያለሀቸው ነገሮች ያንተን ሕይወት ትርጉም ሊሰጧት በፍፁም አይችሉም። ሕይወትህን ትርጉም የሚሰጣት ነገር አጠገብህ ነው ያለው። ኢየሱስ ይባላል! ወንድሜ አይንህን ክፈት ደስታ አጠገብህ ነው ያለው። እርካታ አጠገብህ ነው ያለው። ምናልባት ይሄን የምታነቡ ፕሮቴስታንት ልጆች ለቀባሪው አረዳው በሚል አስተሳሰብ እያነበባቹት ሊሆን ይችላል ሚገርመው ግን መልዕክቱ ለናንተም ጭምር ነው። የተቀበልከው ሐይማኖት አይደለም ሕይወት ነው። የዘለዓለም ደስታና ዕርካታ ያለበት ሕይወት። የሚያሳዝነው ግን አንተም ጌታን እንደማያውቅ ሰው ሕይወትህን በምትሰበስባቸው ነገሮች ትርጉም ልትሰጣት መሞከርህ ነው። “የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና።” — ሮሜ 14፥17 ➛ ብራዘር የመዳን ቀን ዛሬ ነው የሚለው ቃል ለጴንጤም የተፃፈ ነው። የደስታ ቀን ዛሬ ነው! የመርካት ቀን ዛሬ ነው! የተቀበልከው ፅድቅ የዛሬ ነው። በእግዚአብሔር አለም ነገ የሚባል ነገር የለም። ሁሉም ነገር አሁን ነው። አሁንና አሁን ነው። ጌታ አሁን ከወደደህ በላይ ነገ አይወድህም። ጌታ እንድትደሰት የሚፈልገው አሁን ነው። “ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤” — 1ኛ ዮሐንስ 1፥2 ፀጋና ሰላም ይብዛላቹ። @logoschristianschannel @logoschristianschannel @logoschristianschannel @logoschristianschannel 🔥@lewotatoch🔥🔥 🔥@lewotatoch🔥🔥
Show all...
#አየርላንድን_የለወጠው_ሐዋርያ የሴንት ፓትሪክ የህይወት ታሪክ ክፍል-12 ሰረገላና ፈረሶች ላይ ተጭነው ወታደሮቹ ተከትሉት። ከንጉሡ ጋር አብራው ንግስቲቱ እና ሁለት የሚተማመንባቸው ጠንቋዮች አብረውት ነበሩ። ፓትሪክ የፋሲካን በዓል እያከበረ የነበረበት ቦታ ላይ ደረሰ። ፓትሪክ ሸለቆውን በሚያበራው የእሳት ብርሃን ንጉሱንና ወታደሮቹን አየ። የንጉሱም ወታደሮች አዛዥ ፓትሪክን ሊገለው ሲንቀሳቀስ ፓትሪክ "ኦ ሁሉን የምትችል ጌታ ይህ እግዚአብሔርን የማያውቅ አንተንና ስምህን በሰደበው ሰው ላይ እጅ ትምጣበት ብሎ" ጸለየ። በቅፅበትም ከሰማይ የማይታይ ስውር እጅ መጣና ፓትሪክን እንዲገለው የታዘዘው የወታደሮች አዛዥ ካለበት ቦታ ወደ ላይ አንስቶ ድንጋይ ላይ ፈጠፈጠው። ንጉሡም ይህንን ሲያይ በንዴት"ፓትሪክ ላይ ውደቁበት!" ብሎ ትእዛዝ ሰጠ። በዚህ ጊዜ ፓትሪክ ከቦታው ላይ ሳይንቀሳቀስ የያዘውን በትር ወደ ንጉሱና ወደ ወታደሮቹ ላይ ዘርግቶ "እግዚአብሔር ይነሳ ጠላቶቹም ይበተኑ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ"(መዝ 68:1) የሚለውን የመዝሙረ ዳዊት ቃል ጠቅሶ ቃሉን ማወጅ ጀመረ። በጊዜው ቀኑ ሊነጋ በግርማ የተሞላችው ፀሐይ ልትወጣ ብርሃኗን እያሳየች የነበረበት ጊዜ ቢሆንም ከየት መጣ በማይባል ድቅድቅ ጨለማ በድንገት ከሰማይ ወጣና በንጉሡ እና በሰራዊቱ ላይ ከደነባቸው። ጨለማው ጨለማ ብቻ አልነበረም። በውስጡ የሚያስፈራ ግርማ ነበረው፤ ከግርማውም የተነሳ ፈረሶቹና ሰረገላዎች የተሸከሙትን ሰው ይዘው በየአቅጣጫው በፍርሃት ወደ ሃይቁ ወረዱ። በጨለማው ውስጥ የቀሩትም ወታደሮች እርስ በእርሳቸው ተዋጉ። ጨለማው ሲገፈፍ የንጉሡ ወታደሮች ሲሞቱ ንጉሡ ፣ሚስቱና የተወሰኑ ሰዎች ብቻ በሕይወት ቀሩ። ንግስቲቱ ይህንን ያደረገባቸው ምን አይነት ንጉሥ እንደሆነ ለማየት ወደ ፓትሪክ ተጠጋች። የእግዚአብሔር እጅ ያለበት ፓትሪክ እንጂ ሌላ ማንም እንዳልሆነ ስታይ ወድቃ ሰገደች ። ንጉሡ ግን ሽንፈቱን ሲያይ ለፓትሪክ "ነገ ወደ ቤተ መንግስቴ መጥተህ ህግ መጣስህን ህዝብ ፊት ተናዘዝ።"ብሎ አዞት ሄደ። ፓትሪክም አጋጣሚውን ተጠቅሞ ወንጌል ለመስበክ ሰለፈለገ በደስታ እንደሚመጣ ገለጠለት። ክፍል 13ን በቀጣይ ሳምንት ይጠብቁን
Show all...
#አየርላንድን_የለወጠው_ሐዋርያ የሴንት ፓትሪክ የህይወት ታሪክ ክፍል-11 የንጉሡ በቁጣ ነደደ "ማነው የንጉሡን ትዕዛዝ ተላልፎ ያንን እሳት ያነደደው" ብሎ ሰዎችን ጠየቀ ። ከሰዎቹም አንዱ ስለእሳቱ ታላቅነት እስኪነጋ ድረስ ሊጠፋ የማይችል አይነት ሆኖ እንዳየው ምናልባትም ከንጉሡ የሚበልጥ ሌላ ሃይል ያለው ሰው ሊያደርገው እንደሚችል ነገረው። ንጉሡም "ማን እንዳደረገው እራሴ ሄጄ አረጋግጣለሁ። ዙፋኔን የተፈታተነውን ይህንን ሰው እራሴ ሄጄ አገለዋለሁ ተነሱ"ብሎ ጦሩን አስከትሎ ከቤተመንግሥቱ ተነሳ። ሰረገላና ፈረሶች ላይ ተጭነው ወታደሮቹ ተከትሉት። ከንጉሡ ጋር አብራው ንግስቲቱ እና ሁለት የሚተማመንባቸው ጠንቋዮች አብረውት ነበሩ። ፓትሪክ የፋሲካን በዓል እያከበረ የነበረበት ቦታ ላይ ደረሰ። ፓትሪክ ሸለቆውን በሚያበራው... ክፍል 11ን በቀጣይ ሳምንት ይጠብቁን። ----11----
Show all...
አየርላንድን የለወጠው ሐዋርያ ክፍል-4 መልአኩም በተደጋጋሚ ከመገለጡ የተነሳ በስጋ የሚያውቀውን ሰው ያክል ነበር ያውቀው የነበረው። "ታድያ አንድ ቀን ፓትሪክ የመልአኩ ስም ማን እንደሆነ ለማወቅ ፈለገና ጠየቀው የሰማይ መልእክተኛውም መልአክ ''መዳን ያገኙትን ለማገልገል የተላኩ መንፈስ ነኝ። ስሜም ቪክቶር ተብሎ ነው የሚጠራው ፣ሰማያዊ መንፈስ የሆነ መልእክተኛ ሰዎች በሚጠሩበት ስም መጠራት አስፈላጊ ባይሆንም ይህንን ስም አለቆችና ስልጣናትን ድል ከነሳው ከክርስቶስ የተሰጠኝ ነው። አገልግሎቴ በተለይ አንተንና አገልግሎትህን በመረዳት ላይ የሚያተኩር ነው።''በማለት የአገልግሎቱንም ተልእኮ ወደ ፍፃሜ እንዲያመጣ በአብሮነት የሚሰራ ረዳቱ እንደሆነ መልአኩ ነገረው።ከዚያም ፓትሪክ ወደ እንግሊዝ የሚመልሰውን መርከብ ወደሚያገኝበት ወደ አይሪሽ ባህር ዳር የሚወስደውን የ200 ማይሎች ጉዞ እንዴት መጓዝ እንዳለበት መመሪያ ሰጠው። ፓትሪክም በመልአኩ መመሪያ... ክፍል አምስትን በቀጣይ ሳምንት ይጠብቁን ። ----4---- #አየርላንድን_የለወጠው_ሐዋርያ ክፍል-5 ፓትሪክም በመልአኩ መመሪያ መሰረት በተሳካ ሁኔታ ያለፍቃዱ ከተያዘበት ባርነት አምልጦ ወደ እንግሊዝ ተመለሰ። ከጌታውም ተደብቆ መርከብ የሚያገኝበት ቦታ ላይ እስከሚደርስ ድረስ 200 ማይሎችን እርቆ በእግሮቹ ተጓዘ። የተባለውን መርከብ አግኝቶ ከሶስት ቀን አስቸጋሪ የባህር ጉዞ በኋላ እንግሊዝ ደረሰ። ፓትሪክ በእንግሊዝ ከቤተሰቦቹ ጋር ለብዙ አመታት ከተደሰተ በኋላ ጠባቂ መልአኩ በህልሙ በድጋሚ ተገልጦለት ቀጥሎ እግዚአብሔር በሕይወቱ ሊያደርግ ስላለው አላማ ነገረው። መልአኩ መልእክቱንም ድራማ በሚመስል ህልም በማሳየት ነበር የነገረው። መልአኩ የሚያንፀባርቅ ልብስ ለብሶ በተገለጠለት ምሽት በእጁ ብዙ ደብዳቤዎችን ይዞ ነበር። ከደብዳቤዎቹም አንዱን ለይቶ ሰጠው። ፓትሪክ ይህንን ራዕይ እንዴት እንደተቀበለው ሲናገር "መልአኩም በእጁም ብዙ ደብዳቤዎች ይዞ ነበር ከደብዳቤዎቹም አንዱን ሰጠኝ። የሰጠኝንም ደብዳቤ ተቀብዬ ርዕሱ ስመለከተው... ክፍል-6 ን በቀጣይ ሳምንት ይጠብቁን። ----5---- #አየርላንድን_የለወጠው_ሐዋርያ ክፍል-6 ፓትሪክ ይህንን ራዕይ እንዴት እንደተቀበለው ሲናገር "መልአኩም በእጁም ብዙ ደብዳቤዎች ይዞ ነበር ከደብዳቤዎቹም አንዱን ሰጠኝ። የሰጠኝንም ደብዳቤ ተቀብዬ ርዕሱ ስመለከተው "የአየርላንድ ድምፅ" ይላል። ገና ርዕሱን ማንበብ ስጀምር በመንፈስ ተወስጄ ወዲያውም በአየርላንድ ሃገር ወደሚገኘው 'ውድፎከልት' ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የሚገኙ ህዝቦች ድምፅ በአንድ ላይ ሲናገሩ ሰማሁ። እነሱም በአንድ ድምፅ "ወጣቱ አገልጋይ፣ ወደ እኛ መጥተህ በእኛ መካከል እንድትመላለስ እንለምንሃለን።" ሲሉኝ ሰማሁ። ይህንንም ድምፅ ስሰማ ልቤ በኃይል ስለተናወጠብኝ ደብዳቤውን ቀጥዬ ማንበብ አልቻልኩም። በዚህም መልክ ነበር እግዚአብሔር ወደ አየርላንድ ተመልሶ ወንጌልን ለህዝቡ እንዲሰብክ ለዚህ አገልግሎት እንደጠራው የነገረ። ፓትሪክም ይህንንም የወንጌል ጥሪ ካየ በኋላ አህዛብ ለሆኑት የአየርላንድ ህዝቦች ነፃ አውጪውን ወንጌል ለመስበክ በባርነት ተገዝቶበት ወደ ነበረው ሃገር ለመመለስ ወሰነ። ለአገልግሎት የሚያበቃውን ትምህርት በቅድምያ ወደ ፈረንሳይ ሄዶ መማር ጀመረ። ትምህርቱንም ተምሮ ሲጨርስ ወደ አየርላንድ ጉዞውን ጀመረ። -ምዕራፍ 2- ◁ተዓምራዊ ጉዞ ወደ አየርላንድ▷ ◈◁---------------------------------------▷◈ ፓትሪክ ይህንን ራዕይ ካየ በኋላ ወደ አየርላንድ ክርስቲያን ሚሽነሪ ሆኖ ለወንጌል ተልዕኮ ተጓዘ። ፓትሪክ ከፈረንሳይ ተነስቶ ወደ አየርላንድ ሲመጣ ሳለ በመንገድ ላይ አዲስ የተሰራ ቤት የሚመስል ቤት አገኘና ወደ እዚያ ቤት ጎራ አለ። በቤቱ ውስጥ አዲስ ተጋቢ የሚመስሉ ወጣት ባል እና ሚስቶች ነበሩ። ቤቱ ውስጥም እጅግ ያረጀች የወጣት ተጋቢዎቹ አያት የምትመስል ሴት አብራቸው ነበረች። ወጣት ተጋቢ የሚመስሉት ባለትዳሮች አሮጊቷን ሴት ሲያስተዋውቁት "ይህቺ የልጅ ልጅ፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ፣ በብዙ አመታት ውስጥ የነበሩ የልጆቻችን ልጅ ናት።"አሉት። ፓትሪክም "እንዴት ሊሆን ይችላል?፣ እናንተ ገና ወጣቶች ሆናችሁ ሳለ የልጅ ልጃችሁ እንዴት ልትሆን ቻለች?" ብሎ ጠየቃቸው። ባልየውም ሲያስረዳው እንዲህ አለ "ኢየሱስ በአንድ ወቅት በሰው ተመስሎ ወደ እኛ ቤት እንግድነት መጥቶ ነበር። እንደ እንግዳ ተቀብለን ምግብ አዘጋጅተን አስተናገድነው። እርሱም እኛንና ቤታችንን ባረከ። የማናረጅ ሆነን ረጅም አመታት እንድንኖር ባረከን። ለዚህ ነው እንዲህ ሆነን የምንታየው" አለው። "ነገርግን ይህንን ባርኮት ወደ.... ክፍል-8ን በቀጣይ ሳምንት ይጠብቁን። ----7---- #አየርላንድን_የለወጠው_ሐዋርያ የሴንት ፓትሪክ የህይወት ታሪክ ክፍል-8 "ነገርግን ይህንን ባርኮት ወደ ልጆቻችን ማስተላለፍ ባለመቻላችን ምክንያት ነው ልጆቻችን እያረጁ የሚሞቱት። ይህችም የልጃችን ልጅ አርጅታ የምታያት ለዚህ ነው። ኢየሱስ አንተ ለወንጌል ስራ በዚህ አከባቢ እንድታልፍ እንዲሁም ይህንንም የሃይል በትር እንድንሰጥህ ነግሮናል" አሉትና በትር ሰጡት። ፓትሪክም በትሩን ተቀብሎ ወደ አየርላንድ አብረውት ከሚሰሩ የወንጌል አርበኞች ጋር በመርከብ ተጓዘ። ፓትሪክና ጓደኞቹ በአየርላንድ የባህር ዳርቻ ሲደርሱ አካባቢው ላይ የአሳማ መንጋ ተሰማርተው ነበር። ከመርከቡ ሲወርዱ እረኛው አርማዎችን ሊወስዱ የመጡ የባህር ወንበዴዎች ሰለመሰሉት እየሮጠ ሄዶ የአሳማዎቹን ባለቤት አደገኛ ውሻውን በላያቸው ላይ እንዲለቅባቸው ነገረው። ባለቤቱም ነገሩን ሳያረጋግጥ የአውሬነት ባህሪ ያለውን ውሻ በላያቸው ላይ ለቀቀባቸው። ፓትሪክ ፈርቶ ከመሸሽ ይልቅ ወደ ውሻው እየቀረበ ከመዝሙረ ዳዊት "የምትገዛልህን ነፍስ ለአራዊት አትስጣት..."(መዝ 74: 19) የሚለውን ቃል ጠቅሶ በውሻው ላይ ተናገረ። አውሬ ሆኖ የመጣው ውሻ ባህሪውን ቀይሮ እግራቸው ስር እንደቤተሰብ በፍቅር ተቀስቅሶ ተቀመጠ። ባለቤቱም ይህንን ሲያይ ይደነቅና ቀርቦ ያናግራቸዋል። ሰላማዊ ሰዎች እንደሆኑ... ክፍል-9ን በቀጣይ ሳምንት ይጠብቁን። ----8---- #አየርላንድን_የለወጠው_ሐዋርያ የሴንት ፓትሪክ የህይወት ታሪክ ክፍል-9 ባለቤቱም ይህንን ሲያይ ይደነቅና ቀርቦ ያናግራቸዋል። ሰላማዊ ሰዎች እንደሆኑ ዘራፊዎች እንዳልሆኑ ሲረዳ ሰላምታ ሰጥቶ በቤቱ ተቀበላቸው። ፓትሪክም የመጣበትን አላማ ከነገረው በኋላ ወንጌል ሰብኮ ንስሐ አስገብቶ አጠመቀው። ሰውየውም ለእህል ጎተራ የለየውን ቤት ለፓትሪክና ለጓደኞቹ ሰጣቸው። ፓትሪክም እዚያ ቦታ ላይ የመጀመሪያውን አገልግሎት ጀመረ። -ምዕራፍ 3- ◁ፓትሪክ እንደነቢዩ ኤልያስ▷ ◈◁---------------------------------------▷◈ በዚያን ዘመን ሊግሄር የተባለው ንጉስ የአየርላንድ ንጉስ ነበር። የሚኖረውም ታራ በሚባል ኮረብታ ላይ ነው። ከዚህ ኮረብታ 10 ኪሎ ሜትር እርቆ ባለው "ስላን" ተብሎ በሚጠራ ኮረብታ ላይ ፓትሪክና ተከታዮቹ የጌታ ኢየሱስን የፋሲካ በዓል ለማክበር ተሰብስበው ነበር። የአየርላንድ ንጉስ ደግሞ በዚሁ ተመሳሳይ ቀን ...
Show all...
#አየርላንድን_የለወጠው_ሐዋርያ የሴንት ፓትሪክ የህይወት ታሪክ -ምዕራፍ 3- ◁ፓትሪክ እንደነቢዩ ኤልያስ▷ ◈◁---------------------------------------▷◈ ክፍል-10 በዚያን ዘመን ሊግሄር የተባለው ንጉስ የአየርላንድ ንጉስ ነበር። የሚኖረውም ታራ በሚባል ኮረብታ ላይ ነው። ከዚህ ኮረብታ 10 ኪሎ ሜትር እርቆ ባለው "ስላን" ተብሎ በሚጠራ ኮረብታ ላይ ፓትሪክና ተከታዮቹ የጌታ ኢየሱስን የፋሲካ በዓል ለማክበር ተሰብስበው ነበር። የአየርላንድ ንጉስ ደግሞ በዚሁ ተመሳሳይ ቀን ባህላዊ እምነቱን የሚያከብርበት ምሽት ነበር። በዓሉ የሚከበረው ህዝቡ በምድሪቱ ዙሪያ ባሉ ኮረብቶችና ተራሮች ላይ እንዲሁም በየመንደራቸው እሳት በማንደድ በእሳቱ ዙርያ ሆነው በመጨፈር ነበር። ንጉሡ ዋናው በዓል የሚሆንበት ቀን እስኪነጋ ድረስ በዙርያው ያሉ ህዝቦች ሁሉ በአንድነት ችቦ በማንደድ እንዲያከብሩት ትእዛዝ ሰጥቶ ነበር። ፓትሪክና ተከታዮቹ ደግሞ የክርስቶስ ኢየሱስን የፋሲካ በዓል በምሽት ለማክበር በተራራው አናት ላይ እሳት አንድደው ይዘምሩ ነበር። እሳቱ ንጉሡ ካለበት ተራራ ላይ ሲታይ ታላቅ እሳት ሆኖ ይታይ ነበር። የእሳቱ ትልቅነትና ስፋት ከስሩ ያለውን ሐይቅ በውበት አድምቆት ነበር። ንጉሱ ያንን እሳት ያለእርሱ ትዕዛዝ ቀድሞ ያነደደ ከባህሉ ተከታዮች መካከል አንድ ሰው መስሎት በቁጣ ነደደ። እሳቱን ከተቀጠረለት ሰዓት ቀድሞ ያነደደ ማናቸውም ሰው ቢገኝ በሞት እንዲቀጣ ትዕዛዝ ወጥቶ ነበር። በዚህ ምክንያት የሚነድበት ሰዓት እስኪደርስ ድረስ ማንም ሰው እሳት አላነደደም ነበር። ፓትሪክ ግን የፋሲካው በዓል እሳት አንድዶ ከአማኞች ጋር ጌታውን ያከብር ነበር። ከእሳቱም ታላቅነት የተነሳ የሚያስፈራ ግርማ በእሳቱ ውስጥ ይታይ ነበር። የንጉሡ ቁጣ ነደደ... ክፍል 11ን በቀጣይ ሳምንት ይጠብቁን። ----10----
Show all...