en
Feedback
ስለ ቢዝነስ ማስታወሻ

ስለ ቢዝነስ ማስታወሻ

Open in Telegram

ስለ ቢዝነስ ማስታወሻ በነፃ ስለ business ግንዛቤ ለማግኘት ትክክለኛ ቦታ 👉https://t.me/businessIdea_7 የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ፡፡ የቢዝነስ መረጃዎች እና አነቃቂ ሃሳቦችን በቀላሉ ታገኛላችሁ፡፡ https://t.me/+KoGdFzHO8eA3YWE0

Show more
341
Subscribers
No data24 hours
+37 days
+1630 days
Posts Archive
ዩኒቨርስቲ መግባት አስፈላጊነት እየቀነሰ ነው ። ሥራ ለመቀጠር እና ውጤታማ ለመሆን የተሻለ ሆኖም ለመገኘት ድሮ ድሮ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ዲፕሎማ ዲግሪ ማስተርስ እና ፒኤችዲ መያዝ ግድ ነበር ። አሁንስ ? አሁንማ ይህ አስፈላጊነት እየቀነሰ መጥቷል ይላል አንድ በአሜሪካ የተደረገ ጥናት ። በ2022 ዓም ዩኒቨርስቲ ለመግባት የአመልካቾች ቁጥር በ 13 በመቶ ያህል መቀነሱን በመግለፅ ። ለመቀነሱ በዋናነት የተገለፀው ቀጣሪዎች ክህሎት ወይንም (skill ) ያለውን ተመራጭ በማድረጋቸው ነው ። ይህንንም በራሳቸው የማስልጠኛ ተቋም መስጠት ጀምረዋል ። የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የሚያቀርባቸው prompters ደግሞ ይህንን ክህሎት በማቅረብ የሰዎችን ዩኒቨርስቲ መግባትን አስፈላጊነት በማስቅረቱ ረገድ ሚናው የጎላ ሆኗል ። እንደ ChatGPT ዓይነቱ የ AI ኩባንያ ሰባት ዲጂት ያህል ቁጥር ደመወዝ የሚከፍላቸው ሰራተኞቹ ክህሎታቸውን እያየ እንጂ የዩኒቨርስቲ ወረቀታቸውን አይደለም ። ፌስ ቡክም ቢሆን ቅጥር ለመፈፀም የትምህርት ወረቀትን ማየት ትቶታል ይላል ጥናቱ ። በእኛ አገር ያሉ ወጣቶች ገና በመጀመሪያ አመት እና ሁለተኛ አመት ተማሪ ሆነው በክህሎታቸው እንደ ጎግል ባለ ኩባንያ የሚቀጠሩ እየበዙ ነው ። በአሜሪካ ብቻ 85 ሚሊየን ቴክኒካል እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች በሚቀጥለው አስር አመታት ያስፈልጋሉ የሚለው ይህ ሪፖርት እነዚህ ክህሎት እንጂ የዩኒቨርሲቲ ወረቀት የማይጠየቅባቸው ናቸው ይላል ። አሁን ላይ ለ AI ኢንደስትሪው አስፈላጊ የሆነ prompt engineering የሚባል ዘርፍ ታዋቂ እየሆነ መጥቷል ። የCNN ጋዜጠኛ ፋሪድ ዘካርያ ወደ ፊት ዓለም ላይ እጅግ ተፈላጊው ችሎታ ቋንቋ ነው ይህም AI እጅግ አስፈላጊ ነው ሲል ተናግሮ ነበር ። የ AI ክህሎት Data -Driven ለሆነው ዓለም እልል በቅምጤ ሆኖለታል ። ለማንኛውም prompt engineering ላይ የራስን ክህሎት ለማዳበር የሚፈልግ ሰው Linguistic Proficiency. ... Problem Solving and Critical Thinking. ... AI and NLP Knowledge. ... Creative and Adaptable Writing. ... Ethical Awareness. ... Iterative Testing and Learning የመሳሰሉት ክህሎቶች ባለቤት ይሁኑ ።

ገቢዎትን በ 3,514 % ማሳደግ እንዴት.... ? *** Timing ! ቻርልስ ሚዝራሂ የአርሴናል ግብ ጠባቂ አንድ ጊዜ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን እየተመለከትን ሳለ ኳሷን ሊይዛት ሲወረወር አየነው ። ነገር ግን ካለፈች ሽርፍራፊ ሰኮንዶች በኋላ ነበር ይህን ያደረገው ። ጥረቱ ከንቱ ድካም ሆነና ግብ ተቆጠረ ። " ቀሽም !!! " አለ አንድ ጨዋታውን ሲከታተል የነበረ የአርሴናል ደጋፊ " ታይሚንግ አለመጠበቁ እኮ ነው ችግሩ " ሲል አከለበት ። ለምን ታይሚንግ መጠበቅ አልቻለም ? ለሚለው ጥያቄ መልስ መስጠትን አላስፈለገውም ወይንም አላስበበትም ። ግብ ጠባቂው ታይሚንግ መጠበቅ ያልቻለበት ምክንያት በመጀመሪያ ኳሷ በየት እንደምትመጣ ትክክለኛውን ሰዓት አለማወቁ ወይንም አለመገመቱ ነበር ። ቢያውቅ ወይንም በትክክል ቢገምት ኖሮ አስቀድሞ ሚዛኑን በመጠበቅ ኳሷ በምትመጣበት አቅጣጫ የግቡን መስመር ከማለፏ በፊት ታይሚንጉን ጠብቆ ተወርውሮ ማዳን ይችል ነበር ። እዚህ ጋ ሁለት ነጥቦችን እናስተውል ። አንደኛው ኳሷ የምትመጣበትን አቅጣጫ መገመት እና ማወቅ የሚለው ነው ። ይህ ደግሞ የሚመነጨው በፍጥነት ወይንም timely ከምንጠቀመው መረጃ ወይንም ዴታ አናላሲስ ብቃት ላይ የተመሰረተ ነው ። በዚህም መሰረት Data ወይንም መረጃን መጠቀም እጅግ አስፈላጊ ነገር መሆኑን ነው ። ሁለተኛ ደረጃ ሚዛንን ወይንም Balance ን መጠበቅ የሚለውን ነው ። ይህም ዝግጁነት ብለን የምንወስደው ነጥብ ነው ። ስናጠቃልለው የእነዚህ የሁለቱ ዴታ እና ታይሚንግ የጠበቀ ዝግጁነት መሟላት የራስ ገቢንም ለማሳደግ ቁልፍ ተግባር መሆናቸውን ነው ። በገበያ ውስጥም እነዚህ ነገሮች ወሳኝ ስለመሆናቸው በፋይናንሻል ማርኬት ውስጥ ላለፉት አርባ አመታት ስኬታማነቱን ያረጋገጠው profit accelerator system የሚል ስልጠና የሚሰጠው ቻርልስ ሚዝራሂ ከቀመረው ስሌት በመነሳት ነው ይህንን ላካፍላችሁ የወደድኩት ። በፋይናንሻል ገበያ ላይ 3,514 በመቶ እንዴት ትርፍህ ሊያድግ ቻለ ? ሲል ጆን ዴሊ የተባለ ጋዜጤኛ ለ ቻርልስ ባቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ " ቀላል ነው ታይሚንግ ነው " ነበር ያለው ወይንም Market Timer መሆን በሚል ነው የገለፀው ! " የMarket Timer ምስጢርስ ምን ይሆን ? " ጠየቀ ጋዜጠኛው " አንዳች psychic power ወይንም ሌላ ነገር የለውም ? የሚለውንም አስከተለለት ። የ ማርኬት ታይመር ምስጢሩ ዴታ ነው በቃ ! It's Data ! እና ምን ለማለት ነው ? Data ሃብት ነው ማዕድን የሆነ ለዚህም ነው Data mining የሚባለው ! ለዛም ነው machine learning, Artificial Intelligence .... ወሳኝ ነገር የሆኑት ። ገቢያችንን ለማሳደግ የማርኬት ዴታ እና ዴታ አናላሲስ ሃብታችንን መጠቀም ግድ ነው ። Data and Timing ( Market timer) Market timer ካልሆንን ገበያው ደግሞ ቆሞ አይጠብቅም ። ...........ይቅርታሽ ደረሰኝ ምነው ከረፈደ ? እንዳለው ዘፋኙ ገበያውም ለእኛ እንዲህ አይነት ዘፈን መዝፈኑ አይቀሬ ነው ። ድሃና ገበያ አይገናኙምን ትተን በዴታ የሚመራ ማርኬት ታይመር ሁኑ ነው የቻርልስ ምክር !

ስማስቲ ጐረቤትህ የሚሰራውን ስራ እንዳለ መኮረጅ አዋጭ ቢዝነስ ላይሆን ይችላል አይደል? ኧረ ብሮ በምርምር ስራ ራሱኮ "plagiarism" የሚባል ነገር አለ የምርምር ስራህን ውድቅ የሚያስደርግ :: ========================= እዉነት እዉነት ጐረቤትህ የሚሰራውን ስራ እንዳለ ለመኮረጅማ እንዳትምክር። ቪዲዮ ቤት ሲከፍቱ አንተም ከጐናቸው ቪዲዮ ቤት ፣ ዲሸ ቤት ሲከፍቱ ዲሸ ቤት ፣ ቡና ቤት ሲከፍቱ ቡና ቤት ፣ ሽሮ ቤት ሲከፍቱ ሽሮ ቤት ብዙ ጊዜ አይሰራም። ሰው ምን ይፈልጋል? እኔስ ይህን ክፍተት / ፍላጐት እንዴት ልሙላው ብሎ ማሰብ ማሰላሰል የተገባ ነው:: ሁሉም ፍላጐቶች በተመሳሳይ መንገድ አይሟሉም። አንድ መፍትሄ ለሁሉም ችግሮች አይሰራም :: ለዚያም ነው "One size doesn't fit all" የምንለው። ከዚህ አለፍ ስንል ደግሞ ሰዎች ያንተን ቢዝነስ ሊኮርጁ እንደሚችሉ አውቀህ በቀጣይ ከነሱ የምትሻልበትን እስትራቴጅ መንደፍም ይኖርብሃል:: ይህን ደግሞ ቴክኒካሊ "Core Competency" ብለን እንጠራዋለን። ሲቀጥል ደግሞ ጥሩ የገንዘብ አያያዝ ልምምድ ልናዳብር ይገባል። ይህ ደግሞ ቢዝነሳችንን ለመጀመር የመነሻ ገንዘብ እንዲኖረን ያደርጋል። ጠንካራ የሂሳብ አያያዝ ስር0ት የሌለው የንግድ ስራም ወጭና ገቢውን በትክክል ሊያውቅ አይችልም :: እንዲህ አይነቱ ቢዝነስ ደግሞ አይኑን ጨፍኖ በርካታ ገድጓድ ባለበት ቦታ ከሚጓዝ ሰዉ የተለየ አይደለም ::

ከገና ጾም በፊት 14 እና 15 ብር የነበረው አንድ የዶሮ እንቁላል፣ በዚህ የገና በዓል በ10 ብር እየተሸጠ ነው። ቅናሹ ጥሩ ነው። ዋጋዎች በብዙ መልኩ ቅናሽ ማሳየት የጀመሩ ይመስላል። ስሚንቶ ቀንሷል፣ ብረትም፣ ሌላም ሌላም! ድሮም ስንል እንደነበረው ዋጋ የጨመረው ገበያው ላይ ብር በዝቶ እንጂ በደላላ እና ስግብግብ ነጋዴ ምክንያት አልነበረም። አሁን ብር ውድ ሆኗል። ገና ይቀንሳል! ታድያ ቀስ! የብሩን ቅናሽ ቀስ እያልን። እንቁላል ከቀነሰ፣ መኖ ሊቀንስ ግድ ነው። መኖ እንዲቀንስ እነ በቆሎም መቀነስ አለባቸው። በቆሎ ሲቀንስ፣ ስንዴም ይከተላል። ስንዴ ከቀነሰ ጤፍም ይቀንሳል። ለምን? ተተካኪ ምርቶች (substitute products) ናቸዋ! ይህንን ጠብቅ።

ማናጀር ነህ ወይ ? ካልሆንክም ብታነበው ዛሬ የምነግርህ ነገር ሳይጠቅምህ አይቀርም ። አንድ ማናጀር የመሰረተውን ወይንም የሚመራውን ቢዝነስ ወይንም ተቋም ወይንም ራሱን እና ቤተ ሰቡን ሲመራ ምን ምን ማወቅ እንዳለበት የሚለውን ብናወራው ምን ይልሃል ? ወጣት ከሆንክም ለ ወደፊትህ የእነዚህ ክህሎት እና እውቀት መኖር ያስፈልግሃል ። እነ Emebet Teshome Seble Asefa Yetnayet Tesfaye በሴት አንቀፅ ለምን አልፃፍክም እንደማይሉኝ ተስፋ ላድርግና ልቀጥል አይደል? ሁለቱንም ፆታ የሚመለከት ስለሆነ ለአፃፃፍ ስለሚመች ብዬ ነው በወንድ አንቀፅ በማድረግ ፈቃድን የጠየኩት እሺ ። ለማኛውም እነዚህ እውቀቶች ጠቃሚ መሆናቸው የገባኝ በጣም ዘግይቼ መሆኑን ስነግርህ በመቆጨት ነው ። በሃያዎቹ እድሜዬ ኖረውኝ ቢኖር ኖሮ ፐ ! ያስብላል መቼም ወይንም የፈፀምኳቸውን ስህተቶቼን ባልሰራኋቸውም እላለሁ ። አንተ ግን እነዚህን ክህሎትና እውቀቶችን የገቡበት ገብተህ አሳደህ ብትታጠቃቸው ታተርፋለህ ለማለት ነው ። ይቅርታ አስረዘምኩብህ እንዴ ? በነፃ የተሰጠ ነገር አይፈለግም ብለህ እንደ ርዳታ ስንዴ እንዳታቀለው አደራ ። ለማንኛውም በእነዚህ ርዕሶች ላይ መሰረታዊ እውቀት ይኑርህ ነው የምልህ ። ጥቂቶችን ለዛሬ ልንገርህ ። 1 ኛ አካውንቲንግ ፎር ማኔጄርስ Accountings for managers በዚህ ርዕስ ስር ፈይናንሻል ስቴትመንት ማንበብ መሰረታዊ አካውንቲንግ ቃላቶችን ፍቺ ምነንት አስፈላጊነት ሪከርድ አደራረግ ገቢና ወጭን ዋጋ አወጣጥን ( Cost Accounting ) ማወቅ ትርፍና ኪሳራን ማስላት የፈይናንስ ማኔጅመንት የመሳሰሉትን ማወቅ ትችላለህና please Don't Underestimate ። 2 ኛ ማኔጄሪያል ኮሚኒኬሽን ተግባቦትን በተመለከተ በህይወትህ ውስጥ ማወቅ የምትችለው ይህን ማኔጄሪያል ኮሚኒኬሽን መሰረታዊ እውቀት ሲኖርህ ነው ። ስለ Blind, Hidden, open እና Closed communicator የመሳሰሉትን ምንነትና ባህርይ ታውቃለህ። ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች በዕየለቱ ያጋጥሙሃላ ። ያለበለዚያ እንዴት አድርገህ ትግባባለህ? 3ኛ ቢዝነስ ሎው (Business law ) ይህ እንደ ላይኛዎቹ ሁሉ አንድ ኮርስ ያህል ነው ። መሰረታዊ ህግ ምንድን ነው ? ውል እንዴት ይፈፀማል ? የማይፀና ውል እንዴት ያለ ነው ። የመሳሰሉትን ማወቅ ትችለበታለህ ። ከውል ውጭ ስለሚመጣ ኃላፊነት ጭምር የምትረዳበት ስለሆነ እውቀው ።አጫጭር ናቸውና ውሰድ ። 4ኛ ማኔጄሪያል ስታቲክስ ዳታ እንዴት እንደሚያዝ እንዴት እንደምትጠቀመው ምን ማለት እንደሆነ የመሳሰሉትን ታውቅበታለህ ። ቀላል እንዳይመስልህ ታድያ ። 5 ኛ የ ታክስ ህግ ። ታክስ ምንም ብትሆን ይመለከትሃል ። መብት እና ግዴታህን ለመወጣት ስለ ታክስ ማወቅ አልፍልግም ብትል ዋጋ የለውም ። አለማወቅ አያድንህም ። በመቶ ሺህ ብር ካፒታል ስራ ጀምረው በስድስት ወር ውስጥ አራት መቶ ሺህ ብር የተጠየቁ ቢዝነስ መስራቾች አጋጥመውኝ ያውቃል ። ለዛውም ምንም ሳይሰሩ ነው ይህን የምልህ ። እና ማወቅ አይጠቅምም ትላለህ ? ይህን ሳታውቅ እንዴት ቢዝነስ መክፈት ታስባለህ ? አነበብካቸው ታድያ ? የሚጠቅሙ ሆነውስ አገኘሃቸው ? እስቲ አንተ ደግሞ አንድ ሁለት ነገር ጨምርልን !! ➦የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ፡፡ የቢዝነስ መረጃዎች እና አነቃቂ ሃሳቦችን በቀላሉ ታገኛላችሁ፡፡ https://t.me/+KoGdFzHO8eA3YWE0

ሰባ ጥያቄዎች ባሉት ፈተና ላይ ተቀምጠሃል እንበል ። የ ፈተናው ዓይነት ደግሞ ምርጫ ነው ።የተሰጠህ ሰባ ደቂቃ ብቻ እንደሆነ አስብ ። (የሰው እድሜ ሰባ ነው ተብሎ የለ?) ከተመሳሳይ ጥያቂዎች አንዱን ለምሳሌ እንዲህ ይላል 1ኛ ከሚከተሉት ውስጥ ስለ አየር ትክክለኛው አባባል የትኛው ነው ? በምርጫው ዝርዝር ውስጥ ስድስት ሺህ አማራጭ መልሶችን ቢያስቀምጥልህ ምን ታደርጋለህ ? Moral of the story is ህይወት ብዙ ምርጫ ስላቀረበችልህ ሁሉም ትክክል ነው ማለት አይደለም ። Focused የምትሆንበትን ነገር እወቅ limit ይኑርህ identify your talent and strength, then do it in that area! የቀረበልህ ሁሉ ላንተ እንደሚስማማ ለማወቅ ያንን ሁሉ ማወቅ አይጠበቅብህም ። ለምን መሰለህ 37% ማቲማቲካል ሞዴል የሚባል ነገር አለ ። የበለጠ ለማወቅ ጎግልን ጠይቀው ። እንደገና የበለጠ እንዲብራራልህ ደግሞ Dawit Benti ጠይቀው ይነግርሃል ። ወዳጄ ትዳርህንም ለመወሰን ይጠቅምሃል ይላል ይህ ማቲማቲካል Trick . (The '37 Percent Rule': The Mathematical Trick for Making Much Better Decisions Whether you're choosing a spouse or a storefront, this math-based trick can help you pick well.)

ቢዝነስ መጀመር አስበሃል? በምን መስክ? የቢዝነስ ዘርፍህን እንዴት ትመርጣለህ? ገበያ ያለውን፣ የምትወደውን፣ የምትችለውን የቢዝነስ ዘርፍ ምረጥ። ያ ብቻ ግን ለስኬት በቂ አይደለም። ስኬታማ ቢዝነስ ለመፍጠር ፩) ቢዝነስ ስትፈጥር ከደንበኛ ምርጫ ጀምር! ማገልገል የምትሻው ማንን ነው? ~ ህጻናትን፣ ወጣቶችን፣ እናቶችን፣ ጎልማሶችን፣ ወላጆችን፣ አረጋውያንን ~ ድሆችን፣ ሀብታሞችን ~ ከተሜዎችን ወይንስ ገጠሬዎችን ~ ሴቶችን ወይንስ ወንዶችን ~ ተማሪዎችን ወይንስ መምህራንን የመረጥካቸው ጥሩ ይከፍሉሃል? ይሄ ቢዝነስ ነው መዝናኛ አይደለምና መክፈል መቻላቸውን አረጋግጥ። የምታገለግለውን ለይተህ ምረጥ! ፪) የደንበኛህን ችግር ምረጥ። ደንበኛህ ብዙ ችግር ይኖረዋል። ሁሉን ችግር አንተ ልትፈታ አትችልም። አንተ ልትፈታ የምትችለውን ችግር ምረጥ። ፫) ደንበኛህ አሁን ችግሩን እንዴት እየፈታ ወይም እንዴት እየተቋቋመ እንዳለ አጥና። ፬) ለደንበኛህ አሁን ካለው የተሻለ መፍትሔ ልታቀርብ የምትችልበትን መንገድ ፈልግ። ፭) ያንተ መፍትሔ ከሌሎች በምን ይመረጣል? ተመራጭ መፍትሔ እስክታገኝ መፍትሔ ፍለጋ ላይ አተኩር። ፮) የመፍትሔህን ተቀባይነት በትንሹ ሞክር። ተቀባይ ካላገኘህ ወደ ተራ ቁጥር ፭ ተመለስ። ተቀባይ ካኘኘህ ግን እሰየው! ወደ ተራ ቁጥር ፯ ተሻገር። ፯) ምርትህንና አገልግሎትህን አስተዋውቅና ወደ ገበያ ግባ! ሁሌም አፈጸጸምህን እየለካህና ምርትና አገልግሎትህን እያሻሻልክ ቀጥል። በርታ! ➦የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ፡፡ የቢዝነስ መረጃዎች እና አነቃቂ ሃሳቦችን በቀላሉ ታገኛላችሁ፡፡ https://t.me/+KoGdFzHO8eA3YWE0

ወደ ራስ ቢዝነስ ለመግባት በዋነኝነት ሶስት አቃቢዎች አሉ 1. የግል አመለካከት ብዙው ወደ ስራ ለመግባት ይፈልግና በገንዘብ/ በካፒታል ያመካኛል። እውነታውን በደንብ መፈተሽ አለበት። ስራ ለመስራት የሚያቅበንን እውነተኛ ምክንያት መለየት/ማስለየት/ የመጀመርያ እርከን ነው። ፍርሀት፣ ይሉኝታ፣ እውቀት ማነስ፣ ካፒታል እጥረት፣ ልምድ ማጣት፣ ፅናት . . . የመሳሰሉትን በደንብ ፈትሾ ማረቅ ይፈልጋል። 2 ከባቢያዊ ምክንያት፦ በብዛት ማህበረሰባችን የሚሰራን አያበረታታም። የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠረ ሰሪን ማኩሰም ስራዬ ብሎ ተያይዞታል። በርትተው የሚሰሩ ይሾፍባቸዋል። ስራን ሳይመርጡ ስራ ገበታ ላይ የሚገኙ ስላቅ ይዘንብባቸዋል። ከዚህ በዘለለ ለኪሳራ በጣም የተጋነነ ግምት ስለሚኖር ሰሪን ከማበረታታና ተደጋጋሚ የሞራል፣ የሀሳብና የገንዘብ እገታ ከማድረግ ይልቅ ማስበርገግ ይቀናናል። መታረም ይፈልጋል‼ 3 መንግስት ፦ መንግስት ሰሪዎችን የሚይዝበት አግባብ አስበርጋጊ እንጂ አበረታች አይደለም። በቅርቡ ገቢዎች ከሚሰራ አንድ ግለሰብ ጋር ይህን ሀሳብ አንስቼ ሳወጋ "ለምን ይሆን መንግስት ነጋዴውን በሙሉ በሌባና አጭበርባሪ መነሻ ፍረጃ የሚጀምረው" አልኩት "አንድ ሰው ዛሬ ሱቅ/ቢሮ ከከፈተ ወዲያው መጥተው የሚያናግሩበት አግባብ እጅግ ፀያፍ ነው። ጠዋት ሱቁን የከፈተ ነጋዴ መንግስት ምንም አይነት ማበረታቻ ሳያደርግለት ፈቃድ ካላወጣ ወድያው ያሽግበታል። ግልምጫው፣ መመናጨቁና አንዳንዴም አካላዊ ጉንተላው ቀላል አይሰብርም። ይህ ግለሰብ ምን አልባት ስለ ህጋዊ አሰራሮች እውቀቱ ላይኖረው ይችላል። ማስረዳት፣ ማስተማር፣ ማበረታት አልፎም እገዛዎችን ማድረግ ሲገባ ሰርቼ ራሴን ልቻል፣ ሀገሬን ልጥቀም ያለን ግለሰብ በዚህ አግባብ ማከም ምን ይሉታል?!🤔 በሚል ከተጨማሪ ማብራሪያ ጋር ጠየኩት እሱም ጉዳዩ እንደሚገርመው ነገረኝ። አሰራሮች በብዛት ፍትሀዊነት እንደሚጎላቸው በዝርዝር አስረዳኝ። ከፍተኛ አቅም ያላቸው ላይ ጫናዎች እንደሚቀሉ በተቃራኒው በታችኛው ነጋዴ ማህበረሰብ ላይ ጫናዎችና ክትትሎች እንደሚያይሉ አወጋኝ። በምሳሌ እያስረዳ ሁኔታው ገፊ መሆኑን በዝርዝር አስቀመጠልኝ። አዎ፣ ሀገር እንድትቀየር ንግዱን ማህበረሰብ ጨፍልቀው የያዙ መመሪያዎች መከለስ ይኖርባቸዋል። ጀማሪዎችን ማበረታታት አስፈላጊ ነው። ልስራ የሚልን፣ አዎ ስራልን የሚል ግለሰብ፣ ማህበረሰብና አስተዳደር መገንባት አለበት! እስከዛው ግን መሰናክሎችን በመጋፈጥ ወደ ስራ መሰማራት ግድ ይላል! ➦የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ፡፡ የቢዝነስ መረጃዎች እና አነቃቂ ሃሳቦችን በቀላሉ ታገኛላችሁ፡፡ https://t.me/+KoGdFzHO8eA3YWE0

በዚህ ዘመን የእውቀት ችግር የትም የለም። ችግሩ ያለው እውቀትን ገጣጥሞ እና አሰካክቶ መጠቀም ላይ ነው። ችግሩ የOptimization ነው። የምትነግረውን ነገር የሚረዳ እና "አውቃለሁ" የሚል ብዙ ነው። "ያዝ እንግዲህ! ውረድ እንውረድ!" ስትል ነው ችግሩ። እንዲያ ሆኖ ነው ያ ሁላ ኳስ የሚችል ተጫዋች ባለበት ሜሲ እና ሮናልዶ ባላንዶርን እየተመላለሱ ማንሳታቸው። አየህ ልምድና ክህሎት የማይተካ ሚና አላቸው። Our businesses need capable managers. Our institutions need capable leaders. ተቋሞቻችን የሚችሉ መሪዎችና ገሪዎች ይፈልጋሉ። We need great decision makers that optimize resources. ሀብት የማያባክኑ ውሳኔ ሰጪዎች ያስፈልጉናል። ይህ ግን ቀላል አይደለም። እነዚህን ሰዎች ማግኘት ከባድ ነው። አግኝቶ መጠቀም መቻል ደግሞ እጅግ ከባድ ነው። ብዙ እውቀት ይዘህ፣ የቱን የት ጋ እንደምትጠቀም ግራ ከገባህ ካርታ ተጫወት። የውሳኔ ችግር ካለብህ ሴካ ኮንከር ተለማምደህ ብትመጣ ይሻላል። ካርታዎች ተሰካክተው ደርሰውት፣ ጆከር ይዞ "አንድ ቀረኝ" እያለ ሌላው ከኋላ ተነስቶ በዝብርቅርቅ ካርታ ያሸንፋል። ለምን? ነገሩ የእድል አይደለም! የልምድና የውሳኔ ነው። ካርታ ጥሩ ነበር - ቁማሩ ባይኖር። #ሴካ_ኮንከር

ብስለትህ ሲለካ! በሕይወትህ የመብሰልህና ያለመብሰልህ ጉዳይ ከሚለካባቸው መለኪያዎች ዋና ዋና የሆኑትን ሁለቱን ልንገርህ፡፡ በሕይወትህ እይታ እውነታን ከገዛው፤ ስሜታዊነት ደግሞ ምክንያታዊነትን ከገዛው ገና ይቀርሃል፡፡  በህይወትህ ሁለቱ ገዢዎች አሉ፤ እነሱም እይታና ስሜታዊነት ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ገዢዎች የራሳቸው ጥቅም ቢኖራቸውም እንኳን ሊገዟቸው የማይፈቀድላቸው ሁለት ነገሮች አሉ፡፡ እይታና እውነታ እይታ እውነታን ሊገዛው በፍጹም አይገባውም!!! እይታ በእውነታ ላይ እንዲገዛ የፈቀድክለት ቀን ህይወትህ ቀውስ ውስጥ መግባት ይጀምራል፡፡ በራስህ ላይ፣ በሰዎች ላይና በሁኔታዎች ላይ ያለህን እይታ በተረጋጋ መልኩ ከእውነታው ጋር ማስታረቅ ካልቻልክና ሁልጊዜ በእይታህ ብቻ የምትንቀሳቀስ ከሆነ ሁኔታው በውሳኔዎችህ ላይ ጣልቃ በመግባት ከእይታህ ብቻ በመነሳት ከእውነታ የራቁ ውሳኔዎች ውስጥ መግባትህ አይቀርም፡፡ ለምሳሌ እውነታው መማር የመቻልህ ጉዳይ ሆኖ ሳለ በራስህ ላይ ያለህ እይታ ግን እንደማትችል ከሆነ የሚገዛህ እይታህ መሆኑን አትዘንጋ፡፡ ስለዚህም አልችልም በሚል የራስ በራስ እይታ ሳትማር አመታትን ትፈጃለህ፡፡ ይህንን አትዘንጋ፣ አንተ በስለህ ነገሩን ካልገለበጥከው በስተቀር እይታ ሁልጊዜ እውታን እንደገዛው ይኖራል፡፡ በሕይወትህ እውነታ በእይታ ሲሸነፍ አንተም አብረህ ተሸናፊ ነህ፡፡ ስሜታዊነትና ምክንያታዊነት ስሜታዊነት ምክንያታዊነትን በፍጹም ሊገዛው አይገባውም!!! ስሜታዊነት በምክንያታዊነት ላይ እንዲገዛ የፈቀድክለት ቀን ህይወትህ ቀውስ ውስጥ መግባት ይጀምራል፡፡ ከራስህ ጋር ባለህ የውሳኔ ሂደት፣ ከሰዎች ጋር ባለህ ግንኙነትና ለሁኔታዎች በምትሰጠው ምላሽ ያለህን ስሜታዊነት በተረጋጋ መልኩ ከምክንያታዊነት ጋር ማስታረቅ ካልቻልክና ሁልጊዜ በስሜታዊነት የምትንቀሳቀስ ከሆነ ሁኔታው በውሳኔዎችህ ላይ ጣልቃ በመግባት ከምክንያታዊነት የራቁ ስሜታዊ ውሳኔዎች ውስጥ መግባትህ አይቀርም፡፡ ለምሳሌ በስራህ አካባቢ አንድ በጣም የማይመችህ ሰው ካለና በየእለቱ ስሜትህን የሚቀሰቅስ ነገር የሚያደርግ ከሆነ ስሜታዊ ከሆንክ ወደ እሱ ኢላማ በመግባት ግብ ግብ ውስጥ ትገባለህ፣ ምክንያታዊ ከሆንክ ግን ሁኔታውን በሚገባ በማጤንና ምን ብታደርግ ከሁኔታውና ከሰውየው አመለካከት በላይ እንደምትሆን በማሰብ የሚያዛልቅ ምላሽን ትሰጣለህ፡፡ ይህንን አትዘንጋ፣ አንተ በስለህ ነገሩን ካልገለበጥከው በስተቀር ስሜታዊነት ሁልጊዜ ምክንያታዊነትን እንደገዛው ይኖራል፡፡ በሕይወትህ ምክንያታዊነት በስሜታዊነት ሲሸነፍ አንተም አብረህ ተሸናፊ ነህ Dr አዮብ ማሞ

5. የባሎን ኢሪጌሽን(Balloon Irrigation) በተለይ ባሌ÷ጎጃም÷አርሢ÷ጎንደር÷አዋሣ ዙሪያ÷አፋር ÷ሡማሌ...ወዘተ አካባቢ ጠቃሚ ነው:: ባሎን÷ሂሊየምን ማሥመጣትም ጥሩው ቢዝነሥ ይሆናል:: እንዲህ ነው..... በግብርና ሥራ ላይ ውሃ የማይተካ ሚና አለው::በሥዕሉ ላይ ባመለከትኩት መሠረት ተነጂ ሠፊ የኢሪጌሽን ሢሥተም በትራክተር የሚነዳ ሢሆን ዋጋው ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ይፈጃል አፎርዴብል አይደለም ::የጥገና ወጪውም ከፍተኛ በመሆኑ የሃገራችን ሠፋፊ እርሻዎች they dont buy it. በውሃ እጥረት በአመት ሁለቴና ሦሥቴ ማምረት አይችሉም:: ለዚህ ችግር ቀላል መፍትሄ በቪዲዮው ላይ አሥቀመጥኩላችሁ ባሎን ኢሪጌሽን ይባላል:: ለራሥ ፋርም ወይንም ለሌላ ፋርም አገልግሎት በመሥጠት ቢዝነሡን መሥራትም ይቻላል ባሎን ኢሪጌሽን (balloon irrigation)የውሃ ታንከርና ፓንፑን በባጃጅ በመጫን ÷በአጠጪ በኖዝል የተሠራውን የፕላሥቲክ ቱቦ በባሎን ላይ በማንጠልጠል ሁለት ሠዎች በቀላሉ ይዘውት የሚዘዋወሩት ቀላል መሣሪያ ነው ስፋቱ 300 ሜትር የሆነ ማሣ በቁጠባ ማጠጣት ይቻላል :: ባጃጅ በቀን ከአንድ ሺህ ብር በላይ ላይሠራ ይችላል በዚህ ሢሥተም ግን በሠዓት አንድ ሺህ ብር በላይ ሊሠራ ይችላል:: ባሁኑ ዋጋ ከነባጃጁ ሂሊየም ባሎንን ጨምሮ 1.3 ሚሊዮን ያወጣል በቀን ከ 30,000 ሺህ ብር በላይ ይገኝበታል :: እርሻ መሠረታዊ የቢዝነሥ ሃሣብ ነው በዕውቀትና ትጋት ከተመራ:: https://www.facebook.com/vijai.naiker?mibextid=ZbWKwL

Network is Power! ኔትወርክ ኃይልና! በደህና ቀን ያልገነባኸው ኔትወርክ ለፈለግኸው ጊዜ አይደርስልህም። አንዳንድ ሰው አስቀድሞ ያልገነባውን ኔትወርክ የቸገረው ቀን ሊዘረጋ ይሞክራል። ያ ግን ትርፉ ድካም ነው። ባልተዘረጋ ኔትወርክ ወይም በተበጣጠሰ ኔትወርክ የሚደረግ ጥሪ አይሰማም፣ ቢሰማም ይቆራረጣል፣ ወይም የሚፈልገውን ምላሽ በአጥጋቢ አያገኝም። ኔትወርክ እንደ ንብርብር አለት ነው። በሂደት ተደምሮ ተደማምሮ፣ በጊዜ ሂደት ሲደድር metamorphosed ሆኖ አንድ ቀን ነዳጅ ያወጣል፣ አንድ ቀን እምነበረድ ይሆናል፣ አልማዝ ይሆናል። አለዚያ እንደ ተራ ከሰል ወይም ኖራ ነው። ኔትወርክህን ገንባ፣ አጠንክር። እንዴት? ለኔትወርክ ግንባታ ጣሪያ ላይ ወጥተህ አንቴና ትከል አልልህም። ይሄኛው ኔትወርክ ሌላ ነው። Jerry Weibtraub እንደሚለው Be where the action is ድርጊት ያለበት ቦታ ተገኝ፣ ሁነኛ ኩነት ያለበት ቦታ ተገኝ። ቀብር ይሁን ምርቃት፣ ውይይት ይሁን ውድድር ያለበት ቦታ ተሳተፍ። ደስ ያለህን አድንቅ፣ ለምትፈልገው ሰው ደውልና appreciate አድርግ። እየደገምህ፣ እያሰለስህ እንዴት ናችሁ? በል። ታድያ አንተም ጥሩ ሰው ሁን። ለጓደኝነት፣ ለወዳጅነት የምትፈለግ ሁን። መልካምና ዋጋ/እሴት ያላቸውን ሃሳቦች አፍልቅ ወይም አጋራ። ዘመኑ የNetizen ዘመን ነው። አሁን ያሉ ብዙ የልብ ጓደኞቼ፣ ለቁም-ነገር የምጠራቸው ከተፎ ወዳጆቼ የተገኙት ከዚህ መድረክ ነው። መረቡ ውስጥ ከሌለህ ወይም መረቡ ውስጥ ገብተህ ካንቀላፋህ ግን ያንተ ኔትወርክ ችግር አለበት። ኔትወርክህን አንቀሳቅስ! ደውል፣ ተደዋወል! ተጠራርተህ ሻይ ጠጣ! ምሳ ብላ! እራት ተገባበዝ! ተወያይ! ተግባባ! 👏👏👏 Don't undermine the power of the internet.

#አንድ_ቢዝነስ_011 የግብርና መረጃ የመሸጥ  ቢዝነሥ። አዋጪ ነው ተከታተሉት.... ሀ: መግቢያ። በዘመናዊ ግብርና ውሥጥ በመረጃ የተደገፈ ግብርና ውጤቱ አመርቂ ፣ምርታማነትን ከ 50% በላይ ከመጨመሩም በተጨማሪ ጉልበት፣ግዜን እና ሃብትን ቆጣቢ ነው።ለምሣሌ:- 👉መረጃ የመሥጠት አገልግሎት(information service)፣ 👉የገበያ ትሥሥር የመፍጠር አገልግሎት(online market place)፣ 👉የማህበረሠብ ትሥሥርና ውይይት አገልግሎት(community interaction) ፣ 👉የፋይናንሥ አገልግሎትን (financial services)፣ 👉የቴክኖሎጂ ትሥሥር አገልግሎት (technical services) ወዘተን... አንድ ላይ በመጠርነፍ ፤ ኢንተራክቲቭ የሦፍት ዌር ፕላት ፎርም በማዘጋጀት የሚሠራ አዋጪና አመታዊው ገቢ በቢሊዮኖች የሚያሥገኝ ነው። (ለአሥረጅ:- ኢትዮጵያ በፖሥት ሃርቨርሥት ብክነት በአመት 26 ቢሊዮን ብር አካባቢ ታጣለች) እንዴት እንሥራው? 1ኛው፣ ቀላል የባሎን ሣተላይት ማምጠቅ 300k ብር አካባቢ ይወሥዳል። ጥሩ ሌንሥና ሤንሠሮች የተገጠሙለት አይፎን፣የሦላር ሤል ያለው ፣ እንደሣተላይት በገመድ በታሠረ የሂሊየም ባሎን ወደሠማይ ማምጠቅ።የተወሠነ አካባቢ የ24 ሠዓት የምሥልና ፣የሌሎች መረጃን አይነቶችን ይሠበሥብና ወደ ምድር ያሥተላልፋል። 2ኛው፣ በእርሻ አካባቢ የሚተከሉ የአፈር ሁኔታን መረጃ ሠብሣቢ ዋየርለሥ ሤንሰሮች መትከል። ለ100 ሺ ሄክታር 300k ብር አካባቢ ወጪ ። ለምሣሌ :-የአፈር ኒዩትረንት(ንጥረ ነገርን)፣እርጥበትን፣ሙቀትን፣አይነትን ፣ብርሃንን ወዘተ ን የሚለካ እና መረጃ የሚያሥተላልፍ ሤንሰሮች መትከል። 3ኛው፣ የምድር ላይ ሠርቨር ኮምፒዩተር እና ሦፍት ዌር። 250k ብር አካባቢ በሚሆን ወጪ። ሦፍት ዌሩ(መተግበሪያው) 👉እያሥከፈለ የሚትሮሎጂ መረጃ የሚሠጥ ፣ 👉የትራክተር ተከራይና አከራይ ማገናኘት እንዲሁም ምን ያህል እንዳረሠ የሚያሣይ ፣ 👉አቅራቢያ የሚገኝ የቴክክኒክ ድጋፍን ማገናኘት፣ 👉የሠብል ወይም የመሬት ሊዝ ውልን ማዋዋል፣ 👉የገንዘብ አበዳሪና ተበዳሪን አገናኝቶ ማዋዋል፣ 👉ሣይመረት ጀምሮ እሥከመጨረሻው የንግድ ትሥሥርን ማሣለጥ(ገበሬ በቅድሚያ ክፍያ እንዲያመርት ማሥቻል ብዙ ወጣቶች ወደእርሻ እንዲገቡ ያደርጋቸዋል)፣ 👉ህጋዊ አካሄድ መረጃና ድጋፍ መሥጠት ፣ 👉የቴክኖሎጂና አዲሥ አሥተሣሠቦችን የሚያወያይ፣ 👉ለግብርና ተዋናዮች መድረክ የሚሠጥ፣የመድሃኒት አቅርቦትና አጠቃቀምን የሚያሣለጥ ፥ 👉ለመንግሥት መረጃ የሚሸጥ (ለምሣሌ የተተከሉ ዛፎችን ሁኔታ መዘገብ) ወዘተ። ለ:መውጫ፣ ሦፍትዌር ለመሥራት ኤአይ ተጠቀሙ.... ቻት ጂፒቲ፣ጉግል ባርድ፣ኖቫ ወዘተን። 30 ሆናችሁ ብትደራጁ እያንዳንዳችሁ ከማይክሮ ፋይናንሥ 100k ብር ብትበደሩ፤ ሦሥት ሚሊዮን ብር ከእውቀት፣ክህሎትና ጉልበታችሁ ጋር በቂ ነው። በአመት 200,000 ገበሬ ተጠቃሚ ቢኖራችሁና በአመት የአገልግሎት ዋጋ 2500 ብር ብታሥከፍሉ፤ በአመት ግማሽ ቢሊዮን ብር ትሠበሥባላችሁ። ወደፊት ዋናውን ሣተላይት በማምጠቅ ሃገራችንን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂው መሥክ ትለውጣላችሁ::ለግብርና ምርት እድገታችንም መሠረት ትጥላላችሁ።

Traction | የገበያ ፍተሻ Traction = Trial Action. የአንድ ቢዝነስ ሥራ ጅማሬ ላይ መታለፍ የሌለበት ጉዳይ የገበያ ፍተሻ ወይም traction ነው። ሥራ ልጀምር? ስትለው "አሪፍ ነው፣ ይሠራ" የሚልህ ሁሉ ድጋፉ የእውነት መሆኑ የሚፈተሸው "ግዛኝ" ስትለው ነው። አባቶቻችን ብልሆች ናቸው "በቅሎ ግዙ ግዙ አንድ አሞሌ ላያግዙ" ያሉት ያለምክንያት አይደለም። እናም ደጋፊህ የድራፍት አረፋ ይሁን ቢራ ለመለየት፣ የሙከራ ምርት ይዘህ "ና ግዛኝ" በለው። ያኔ የምር ደጋፊህን ትለያለህ። ትራክሽን በቢዝነስ ጅማሬ ወሳኝ ሚና አለው። ➦የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ፡፡ የቢዝነስ መረጃዎች እና አነቃቂ ሃሳቦችን በቀላሉ ታገኛላችሁ፡፡ https://t.me/+KoGdFzHO8eA3YWE0

አካል፣ ነፍስና መንፈስ ሰው የዚህ ሁሉ ቅንብር ነው ይባላል - የአካል፣ የነፍስና የመንፈስ። ተንቀሳቃሽ ሮቦትም አካል አለው፤ ነፍሱ ከኤሌክትሪክ ኃይል የሚገኝ ኤነርጂ ነው፤ የሮቦቱ መንፈስ ላዩ ላይ የተጫነው ሶፍትዌር ፕሮግራም ነው። ተንቀሳቃሽ ሮቦቱ ከሰው በምን ይለያል? እንደሰው ያያል፣ ይሰማል፣ ሰምቶም ይታዘዛል፣ ይንቀሳቀሳል፣ ኃይሉ ሲቀንስ ኢነርጂ ይፈልጋል፣ ኢነርጂው እንዲሞላ ጊዜ ይወስዳል። አንተስ ከሮቦቱ በምን ትለያለህ? በተጻፈልህ ፕሮግራም፣ በተጫነልህ ሶፍትዌር መሠረት አይደል የምትንቀሳቀሰው? ባትሪህ በየቀኑ ስትተኛ አይደል የሚሞላው? መንፈስህስ በትምህርትና መረጃ አይደል የሚታደሰው? መታደስ(update) ለሶፍትዌር እጅግ ጠቃሚ እንደሆነው ሁሉ ለሰው ልጅም update አስፈላጊ ነው። Update ለመደረግ ግን አዲሱን ፕሮግራም ለመቀበል የሚያስችል የትውስታ ማዕከል (memory space) እና ፈቃድ (permission) ይፈልጋል። ያለፈቃድ ማንም update አያደርግህም። Update/ተሃድሶ ለምን ያስፈልጋል? ከሁኔታዎች፣ ከዘመንና ከቴክኖሎጂ ጋር ለመስማማት ተሃድሶ አስፈላጊ ነው። የማይታደስ (update የማይደረግ) ኮምፕዩተርን አስበው እስኪ? ያቺን ሚጢጢ ሞባይል አስባት እስኪ? Update አልደረግ ብትልስ? አዲስ application አልቀበል ብትልስ? ቦታ የለኝም ብትልህስ? አሮጌውን ሰርዘህ ሌላ app ትጭን የለ? ሰፊ ቦታ ካለ ግን አዲስ app መጫን ይሁን፣ ያለውን ማደስ(update) ማድረግ ይሁን ቀላል ነው። እንዲያ ሲሆን፣ በቂ ቦታ ያለ ሲሆን፣ ለupdate ወሳኙ ጉዳይ መጀመሪያ የተጫነው የኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ባህሪይ ነው። አንተ ከምታስበው በላይ የትውስታ ዓቅም አለህ። አዲስ ነገር እንዳትቀበል ጠፍንጎ የያዘህ መጀመሪያ የተጫነብህ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ነው። የአንዳንድ ሰው ኦፕሬቲንግ ሲስተም እንደ አንድሮይድ ከሁሉ በቀላሉ ተስማሚ ነው። የአንዳንዱ ደግሞ እንደ አይፎን ios ከራሱ መስመር ውጪ ከሌላ የማይግባባ ነው። ያንተ ኦፕሬቲንግ ሲስተም እንዴት ያለ ነው? ያንን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ማን ጫነብህ? ያው ታውቃለህ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በቀላሉ አይቀየርም አይደል? ትውልድ ላይ ስለምትጭነው መሠረታዊ አስተሳሰብ ተጠንቀቅ። የአዲሳባ፣ የድሬዳዋና የደሴ ኦፕሬቲንግ ሲስተም እንደ አንድሮይድ ይመስለኛል። የአንተ/አንቺ ኦፕሬቲንግ ሲስተም (OS) እንዴት ያለ ነው?

ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው! ዘመኑ የአዳዲስ መንገዶች፣ የአዳዲስ ዕድሎች፣ የአዳዲስ እሳቤዎች ዘመን ነው። በድሮ መንገድ፣ በድሮ እሳቤ፣ በድሮ አሠራርና አኗኗር አትታሠር። ነጻ የሚያወጣህ አስተሳሰብህ፣ እምነትህ፣ ቴክኖሎጂና ሥራህ ነው። በየ 3 ዓመቱ ከፍተኛ ለውጥ አለ! ማየት ለቻለ ሁሌም አዲስ መንገድ አለ። አዲስ መንገድ ይታይሃል? ብሩህ ሰንበት!

2016 ዓ.ም. የቢዝነሥ ሃሣብ #007 ኬኔቶ ሠርቶ አሽጎ መሸጥ። ኮካኮላ፣ፔፕሢ፣ጁሥ፣ማልት ወዘተ ፋብሪካዎች ተደራሽነታቸውን ያሠፉት በ 'bottel it' ማርኬቲንግ እሥትራቴጂ ነው። ኬኔቶ ከአልኮል
+2
2016 ዓ.ም. የቢዝነሥ ሃሣብ #007 ኬኔቶ ሠርቶ አሽጎ መሸጥ። ኮካኮላ፣ፔፕሢ፣ጁሥ፣ማልት ወዘተ ፋብሪካዎች ተደራሽነታቸውን ያሠፉት በ 'bottel it' ማርኬቲንግ እሥትራቴጂ ነው። ኬኔቶ ከአልኮል ነጻና በተለየ መልኩ በብዛት ማህበረሠባችን እየተጠቀመውና እየተለማመደው ያለ የመጠጥ አይነት ነው።በምግብ የጎለበተ ማድረጉን እንዳትረሡ።በተረፈ የምግብ፣የጤና ወዘተ ባለሙያ ምክርን /እገዛን ተጠቀሙ። በዘመናዊ መልክ ገብሡን አበጥረን ፣ቆልተን፣ፈጭተን፣ቀቅለን፣የተለያዩ ግብአቶችን በመጨመር (እንደየ ቅመማው ይለያያል) ወዘተ... በማጣራት በ ካርቦን ዳይኦክሣይድ ጋዝ በጠርሙሥ ወይም በ PET bottel በማሸግ ወደገበያ ማሥገባት ነው።ድግሦች፣ሆቴሎች፣ሡቆች፣ ወዘተ ገበያችሁ ይሆናሉ። በማሽን የታገዘ ምርት ቢኖራችሁ ደግሞ የማምረት አቅማችሁ ይጨምራል። ለምሣሌ.... ማበጠሪያ፣ ማጠቢያ፣መቁያ፣መፍጫ፣መቀቀያ፣ ሪአክተር(optional)፣መቀላቀያ፣ሤትለር፣መቀመሚያ፣ማጣሪያ እና ማሸጊያ ማሽን በጥቂቱ ያሥፈልጋችኋል። የካርቦን ዳይኦክሣይድ ግብአት በቀላሉ ሥለምታገኙ ጋዙን መሥሪያ ለጊዜው አያሥፈልጋችሁም።ኦግዝለሪ ኢኪውፕመንት ቦይለር፣ኮምፕረሠር፣ጀነሬተር እና የውሣ ማጣሪያ መረሣት የለበትም።ሢአይፒ ሢሥተማችሁን ተመልከቱት። ለምሣሌ በቀን 5,000 ሊትር የተጣራ ኬኔቶ ለማምረት 100kw 3phase የኤሌክትሪክ ሃይል፣15m by 10m በ5m ከፍታ የማሽን ቦታ ይፈልጋል። አሥፈላጊውን ህጋዊ ፍቃዶች እንዳትረሡ። በመደራጀት መሥራት ብትችሉም አሪፍ ነው።ቦታ ያለው፣እውቀት ያለው ፣ገንዘብ ያለው፣ጉልበት ያለው ተደራጅቶ መሥራትም ይቻላል። በርቱ!

2016 ዓ.ም. ቢዝነሥ ሃሣብ። #008 ትራፍል(truffle) እና የትራፍል ዘይት ለገበያ ማቅረብ። ትራፍል ማለት ምን ማለት ነው?? አዋጪ ነው ተከታተሉት...... ትራፍል የፈንገሥ አይነት ሢሆን በ
+3
2016 ዓ.ም. ቢዝነሥ ሃሣብ። #008 ትራፍል(truffle) እና የትራፍል ዘይት ለገበያ ማቅረብ። ትራፍል ማለት ምን ማለት ነው?? አዋጪ ነው ተከታተሉት...... ትራፍል የፈንገሥ አይነት ሢሆን በዛፍ ሥር በማይታይ መልኩ የሚበቅል ነው። ለምግብነት፣ለመድሃኒትነት ይጠቅማል። ብዙ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን በመያዙ ድንቅ ምግብና ገራሚ መድሃኒት ነው።ሣይንሣዊ ጥናቶች እና ባህላዊ ህክምና አዋቂዎች እንደሚያመለክቱት የካንሠር ሤሎችን ለመግደል የሚያግዝ ባህርይ አለው።የእርጅናን የመከላከል ጠቀሜታ አለው።ሤክሹዋል ኢንፖተንሢን ይቀንሣል።ውፍረትን ይከላከላል ወዘተ.....ይላሉ። በሃገራችን በጫካ ውሥጥ ባሉ በተመረጡ ዛፎች ሥር ይበቅላል።ሃርቨሥት ለማድረግ ሽታውን በለመዱ ውሾች መጠቀም ይቻላል።ጅማ፣ጉሙዝ፣ጭልሞ፣አርባምንጭ፣ወላይታ ሦዶ፣ከላላ፣ሃረር፣ ደቡብ ምእራብ፣ጉራጌ ሠንሠለታማ ተራሮች ወዘተ ቦታዎች ተሥማሚ ናቸው። አንድ ኪሎ ነጭ ትራፍል እሥከ 1500 USD ድረሥ ሊሸጥ ይችላል። ሌሎች ዝርያዎች በኪሎ እሥከ 200 USD ሊሸጡ ይችላሉ። ዘይቱም ውድ ነው እሥከ 400USD ሊሸጥ ይችላል። ዛፍ ይመርጣል።ጥናቶችን ተመልከቱ። ጫካዎቻችሁን እንጨት ከመልቀም ባለፈ ለዚህ አይነቱ ተግባር ልትጠቀሙባቸው ትችላላችሁ። ትራፍል ገዝታችሁ ውሻን በማለማመድና በማሠልጠን ብቻ የሚሠራ ሥራ ነው። ንግዱ አሪፍ ነው ትልልቅ ሆቴሎች ከውጪ እያሥመጡ ነው። ከበረታህ ደሞ እንደ አበባና ቡና ኤክሥፖርት ታደርገዋለህ ።ማምረትም ሞክሩ። በርቱ!

#አንድ_ቢዝነስ_008 አንድ ወንዴሜ🤔 ምን ልጀምር ይላል...?? ➦ከዳቦ ቤት, ➦ከቡቲክ እና ➦ከምግብ ቤት የቱ ላይ ልጀምር 1ሚ ካፒታል አለኝ የቱ ያዋጣኛል ሌላም ሃሳብ ካላችሁ ንገሩኝ ይለናል አማክሩት መልስ 1, በተቻለክ አቅም 3faze ያለው ቤት ከ60-70 ካሬ ጥሩ ቦታ ተከራይ እናም ኮንዲሚኒየም ዶቦ ቤት 20% ከፍለክ ከአዲሰ ካቢታል ግዛ 400--500ሺ ይጠበቅብካል መዎጮ 20% ወደ 30ካሬ አካባቢ ለfast food ምግብ ቤት የሚሆን ቦታ አዘጋጅ እዛው ከተከራየከው ቦታ ላይ Burger &pizza  አዘጋጅ ከቻልክም ቀለል ያሉ የሀበሻ ምግብ ጨምርበት ወንበር ከ 5 or 6 ጠረቢዛ በቂ ነው ከተቻለ በረንዳ ያለው /L ላይ ያለ ቦታ ካገኝክ  ጥሩ የኔ ሃሳብ ይህን ይመሰላል እናንተ ጨምሩበተሰ ።