cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Abdulwekil’s official

Plan as your work, work as your plan

Show more
Advertising posts
207
Subscribers
-124 hours
-27 days
+130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"ቶንሲል" ቶንሲሎፋርንጃይትስ ወይም የላይኛው መተንፈሻ ክፍል ህመም በዶ/ር ብርሐኑ አለኸኝ (የሕፃናት ሕክምና ሐኪም) 1. ምንነት ቶንሲሎፋርንጃይትስ ወይም (የጉሮሮ ህመም) የሚያመለክተው የላይኛው የመተንፈሻ ክፍል (Pharynx)ን እብጠት ነው፡፡ እሱም መቅላት፣ እብጠት መውጣት፣ ወይም Enanthem (ቁስሎች፣ vesicles) ነዉ:: ቶንሲሎፋርንጃይትስ ወይም (የጉሮሮ ህመም) ከአካባቢያዊ መጋለጥ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል ፤ ለምሳሌ የትምባሆ ጭስ ፣የአየር ብክለት እና አለርጂዎች፣ ከቆሻሻ ንጥረ ነገሮች፣ ሙቅ ምግብ እና ፈሳሾች ጋር ከመገናኘ፡፡ ከተላላፊ ተህዋሢያን ዉስጥ Group A streptococcous መጥፎ የባክቴሪያ ቶንሲሎፋርንጃይትስ ወይም (የጉሮሮ ህመም) መንስኤ ነው ፣ ግን ቫይረሶች በብዛት ተላላፊ ምክንያቶች ናቸው። የላይኛው የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽኖች የሚተላለፉት በአፍ ወይም በመተንፈሻ አካላት ንክኪ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው በመኸር፣ በክረምት እና በጸደይ ወቅት ነው። ብዙውን ጊዜ በትምህርት ቤት ዕድሜ ላይ ባሉ ልጆች ውስጥ ከተበከለ የመተንፈሻ አካላት ፈሳሽ ጋር በመገናኘት የሚተላለፉ ሲሆን በትምህርት ቤቶች እና በህፃናት ማቆያ ማዕከላት ውስጥ የቅርብ ግንኙነት ከ2-4 ቀናት ውስጥ ነው፡፡ 2. አስተላላፊ ተሕዋሲያን ቶንሲሎፋርንጃይትስ ወይም (የጉሮሮ ህመም) በሽታን የሚያስከትሉ ቫይረሶች ውሰጥ ኢንፍሉዌንዛ ፣ ፓራኢንፍሉዌንዛ ፣ አድኖቫይረስ ፣ ኮሮናቫይረስ ፣ ኢንቴሮቫይረስ ፣ ራይኖቫይረስ ፣ ሳይቶሜጋሎቫይረስ ፣ ኤፕስታይን-ባር ቫይረስ ፣እና ሜታፕኒሞቫይረስ ያካትታሉ። ከ ሞኖኒክሎሊስ በስተቀር አብዛኛው የቫይረስ ቶንሲሎፋርንጃይትስ ወይም (የጉሮሮ ህመም) ቀላል ነው። 3. የበሽታው ምልክቶች ከበሽታው ምልክቶች ውሰጥ የstreptococcal እና የቫይረስ ቶንሲሎፋርንጃይትስ ወይም (የጉሮሮ ህመም) ምልክቶች ብዙውን ጊዜ ይደራረባሉ። ነገር ግን በአብዛኛው የባክቴሪያ ቶንሲሎፋርንጃይትስ የሚከተሉት ምልክቶች ይኖራሉ፡፡ ድንገተኛ የጉሮሮ መቁሰል፣ ከ5-15 ዓመት ትኩሳት፣ ራስ ምታት ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ የሆድ ህመም የቶንሲል እብጠት ወይም መግል መሣይ ነጭ ፈሳሽ መቋጠር፡፡ የቫይረስ ቶንሲሎፋርንጃይትስ መልክቶች ደግሞ የአይን መቅላት እና መቆጣት ፣ የአፍንጫ ፈሳሽ፣ ሳል፣ ተቅማጥ፣ የድምጵ መጎርነን እና የ አፍ ቁስለት ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ፡፡ 4. የቶንሲሎፋርንጃይትስ ሕክምና ለአብዛኛዎቹ የቫይረስ ቶንሲሎፋርንጃይትስ ልዩ ሕክምና አይሠጥም ሆኖም፣ ልዩ ያልሆነ ማለትም ምልክታዊ ሕክምና አስፈላጊ አካል ነው። በአፍ የሚወሰድ የህመም ማስታገሻ (Paracetamole ወይም ibuprofen) ትኩሳትን እና የጉሮሮ መቁሰል ህመምን ያስወግዳል፡፡ አብዛኛው ቶንሲሎፋርንጃይትስ ችግር በጥቂት ቀናት ውስጥ በራሡ ይድናል ፤ ነገር ግን ሕክምና ማድረግ በሽታው በ12-24 ሰዓት የመዳን ጊዜን ያፋጥናል፡፡እንዲሁም እንደ Peritonsilar Abcsess ያሉ የባክቴሪያ ቶንሲሎፋርንጃይትስ በሽታዎችን ያስወግዳል። የአንቲባዮቲክ ሕክምና ዋነኛ ጥቅም እና ዓላማ የልብ ቁሥለት ችግር (acute reheumatic fever) መከላከል ነው፡፡ ሕክምናው በሽታው ከጀመረ በ9 ቀናት ውስጥ ሲጀመር በጣም ውጤታማ ነው። የመድሐኒት ሕክምና አጣዳፊ ከላሊት ላይ የሚከሠት ጠባሣ ( poststreptococcal glomerulonephritis) አይከላከልም። የበሽታ ምልክት ከታየ እና የምርመራ ወጤት ላላቸው ሕፃናት የአንቲባዮቲክ ሕክምና መዘግየት የለበትም ፡፡ አንቲባዮቲኮችን መጀመር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ይሕም 1.ከህመሙ የሚከሠቱ ችግሮችን (Complication) ይቀንሳል፡፡ 2.የኢንፌክሽን ጊዜን ይቀንሱ 3. ለሌሎች ማስተላለፍን ይቀንሳል ህክምናዉ ለ 10 ቀናት የተመረጠ አንቲባዮቲክ ሕክምና ነው፡፡ 5. የቶንሲል ቀዶ ጥገና የሚያስፈልግ - በ1 አመት ውስጥ ከሰባት በላይ የቶንሲልፋርጂቲስ ኢንፌክሽኖች - ባለፉት 2 ተከታታይ ዓመታት ውስጥ በእያንዳንዱ ከአምስት በላይ የቶንሲልፋርጂቲስ ኢንፌክሽኖች በመጨረሻም የቶንሲልፋርጂቲስ ኢንፌክሽኖች ከእድሜ ጋር እንደሚቀንስ ይወቁ ዶ/ር ብርሀኑ አለኸኝ : የህጻናት ህክምና ስፔሻሊሥት
Show all...
የሆኑ ቡድኖች አሉ፤ ስማቸውን እየጠራን አስጠንቅቀን ነበር። እስልምናን እናዘምናለን ብለው ያስባሉ። ግና ከምዕራቡና ከአውሮፓው ሰይጣናዊ ዓለም የአካሄድ አናሎጂ እየቀየሱ መልካም እየሠራን ነው ብለው ይሞግታሉ። ያኔ ስንቃወማቸውና የነገ መዘዛቸው ከባድ ስለሆነ ከወዲሁ ያቁም ስንል ብዙው ሰው ስላልተረዳን ሲቃወመን ነበር። አሁን ላይ ግን አካሄዳቸው ይበልጥ ግልፅ እየሆነ ሲመጣ አላህ ያገራላቸው ወንድምና እህቶች፣ ያኔ ሲሟገቱላቸው የነበሩና ተሳታፊዎቻቸው የነበሩትም ጭምር እየኮነኗቸው ነው። አሁንም በጣም አልረፈደምና እነዚህ ሚንበር የምትሏቸው ሰዎች ያለንበትን ወስዋስ ዓለም ታግዘው ኡማውን በፈሳድ ጨርሰው ሳይበክሉት ከወዲሁ ማስቆም ቢቻል መልካም ነው። በየጊዜው ኢስላማዊ ቅብ አለባብሰው የሚያመጧቸው ጉዶች እጅጉን አሳፋሪ ናቸው። ዛሬ ላይ ዝም ካልናቸው ቀጣይ "ኢስላማዊ የቁንጅና ውድድር፣ የሞዴል ውድድር… " ብለው አዲስ ነገር ላለማምጣታቸው ዋስትና የለም። ዛሬ ላሉበት ድፍረት የደረሱት ትናንት ዝም ስለተባሉ ነው። አላህ ይምራቸው፤ ወይም የሚገባቸውን ይስጣቸው። Copied
Show all...
በአደጋ ምክንያት የወለቀ ጥርስ | Avulsed Teeth. ጥርስ የተፈጠረበት ዓላማ በዋናነት ምግብን ለማኘክ ቢሆንም ከዚሁ አገልግሎት ባለፈ ጥርስ መኖሩ በራሱ የመንጋጋ አጥንታችንን ጥንካሬና ቁመት በመጠበቅ የፊት ውበትንም ያጎላል። ለዚሁ ምሳሌ ይሆን ዘንድ በተለያዩ ምክንያቶች ጥርሳቸውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ያጡ ሰዎች የመንጋጋ አጥንታቸው ቀድሞ ከነበረው ቁመት ስለሚቀንስ የፊታቸው የታችኛው 1/3 ክፍሉ በማጠር የሚታይ የውበት መጓደል የመፍጠር አቅም አለው። ወደ ርዕሳችን ስንመለስ ጥርስ በተለያዩ አደጋዎች ይወልቃል የወለቀው ጥርስ የላይኛው መንጋጋ የፊትለፊት ጥርስ ከሆነ ይባስ ብሎ ተፈጥሮ የቸረችንን ሳቅ ለመሳቅም ያሳፍራል፣ በራስ መተማመን ይቀንሳል፣ የወለቀው ጥርስ በጊዜ ካልተተካ የተነቀለው ጥርስ አቃፊ አጥንት ቁስል ሲድን ከጎን ያሉ ጥርሶች ወደ ክፍቱ ቦታ የመንቀሳቀስ ተፈጥሯዊ ሒደት ስላለ በጥርሶች መካከል ክፍተት የመፍጠር አቅምም አለው። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ጥርስ በተለያዩ አደጋዎች ምክንያት ይወልቃል እነዚህም 👇 ✅ ባልታወቀ ምክንያት(17%) ✅ በጦርነት(17%) ✅ አካላዊ ንክኪ ባላቸው የስፖርት ዓይነቶች(15.9%) ✅ በመኪና አደጋ(10.8%) ✅ በሞተር ሳይክል አደጋ(10.4%) ✅ በበረዶ ሸርተቴ ጨዋታ(2.3%) ሲሆን በዚህ አደጋ ከ 7-13% ህፃናቶች(Primary Teeth) ላይ የሚከሰት ሲሆን ከ 1-16% ደግሞ አዋቂዎች(Permanent Teeth) ላይ እንደሚከሰት ጥናቶች ያሳያሉ። ምክንያቱም አደጋ ሲከሰት ብዙን ጊዜ የፊት አደጋ አይጠፋውም ለዚህም ማሳያ በኮርያው ጥርነት ጊዜ ብቻ 3,000 የሚጠጉ የፊትና የአፍ ውስጥ አደጋዎችን እንደተስተናገዱ ታሪክ ያወሳል። የወለቀ ጥርስ መፍትሔው ምንድነው...??? ጥርስ ሲወልቅ ወልቋል ተብሎ አይጣልም ይልቅ መልሶ መትከል ይቻላል። ነገር ግን ህክምናው የመሳካት ሒደቱ ጥርሱ ወልቆ ከአፍ ውጪ የቆየበት ሰዓት ይወስነዋል። ምክንያቱም ጥርሱን ከመንጋጋ አጥንቱ ጋር የሚያያይዙ ጅማቶች እና አብሯቸው ያሉ ሴሎች በቂ የሆነ የደም እና የተለያዩ ንጥረ ነገሮች እገዛ ይፈልጋሉ። ጥርስ ከአፍ ውጪ ወልቆ የቆየበት ሰዓት በጨመረ ቁጥር ጅማቶችና ሴሎች የደም እገዛ ስለሚቋረጥባቸው የመሞት ዕድላቸው እየጨመረ ይመጣል ስለዚህ መልሶ የመትከል ህክምናውም ላይሳካ ይችላል። የጥርስ ጅማት እና ሴሎች እንዳይሞቱ ምን መደረግ አለበት...??? ጥርሱ ወልቆ ከወደቀበት ቦታ ለማንሳት ሲሞክሩ የጥርሱን ስር መንካት ፈፅሞ አይመከር ይልቅ የጥርሱን መስታወት ይዘው ማንሳት ይመከራል። ወደ ጤና ተቋም ይዘውት ሲመጡ በሶፍት እና በተለያየ ነገር ይዞ ማጓጓዝ ሳይሆን ከስር የተቀመጡ አማራጮችን መጠቀም ይመከራል👇 1. ከሁሉም የሚመከረው ወደ ህክምና ተቋም እስኪመጣ ድረስ በተቻለ መጠን አደጋው እንደደረሰ የወለቀውን ጥርስ ወደነበረበት ቦታ መልሶ በመትከል ደግፎ መምጣት 2. ለዚሁ ዓላማ ተብሎ በተዘጋጀ HBSS በተባለ ኬሚካል መጠቀም 3. በፓስቸራይዝድ ወተት (Pasteurized milk) ሌላኛው አማራጭ ሲሆን 4. በፋብሪካ በፈሳሽ መልክ በተዘጋጀ ጨውን (Normal Saline) መጠቀምም አንደኛው አማራጭ ነው 5. ከላይ የተጠቀሱ አማራጮች ካልተሳኩ አፍ ውስጥ በምራቅ ወይም በንፁህ ውኃ ይዞ ወደ ጤና ተቋም መሔድ ወደ ጤና ተቋም እንደደረሱ በተለያዩ የኤክስ ሬይ አይነቶች ተጓዳኝ አደጋዎች አለመኖራቸው ከታወቀ በኋላ የወለቀው ጥርስ የጥርስ ስር ህክምና ታክሞ ጥርሱ የወለቀበት አቃፊ አጥንት እና የወለቀውን ጥርስ በተለያዩ የመድኃኒት ዓይነቶች ከታከመ በኋላ ወደ ቦታው መልሶ ተክሎ ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀ ሽቦ እና ሙሌት ጥርሱ ወደ ቀድሞ ጥንካሬ እስኪመለስ አስሮ ማቆየት። ህክምናው የመሳካት ዕድሉን ከሚወስኑ ብዙ ነጥቦች መካከል ከብዙ በጥቂቱ 👇 1. ከአፍ ውጪ የቅየበት ሰዓት ሲጨምር የመሳካት ዕድሉ ይቀንሳል 2. የጥርሱን ስር ባልተገባ መልኩ መነካካት 3. ስሩ ጨርሶ ያልዘጋ ጥርስ የመዳን ዕድሉ ስሩ ጨርሶ ከዘጋ ጥርስ ሲወዳደር ከፍተኛ ነው ጥርስ በአደጋ ምክንያት እንዳይወልቅ ምን መደረግ አለበት...??? ቦክሰኞች ፍልሚያ ከመጀማራቸው በፊት ብዙን ጊዜ አፋቸው ውስጥ ማውዝ ጋርድ (Mouth guard) የተባለ ነገር ሲከቱ ይስተዋላል ምክንያቱም የተሰነዘረ ቡጢ አንድ ጥርስ ጋር ቢያርፍ ያረፈውን ጉልበት ማውዝ ጋርዱ (Mouth Guard) ወደተቀሩት ጥርሶች የመበተን ወይም የማካፈል ሂደት (Force distribution) ስላለው ጥርስን ከመውለቅ ይታደጋል። ስለዚህ የትኛውም ዓይነት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወይም አደጋ ሊያደርስ ይችላል የተባለ ተሽከርካሪ ሲያሽከረክሩ ማውዝ ጋርድ (Mouth Guard) ቢጠቀሙ ጥርስን ከመውለቅ ይታደጋል። በዶ/ር አብዲልኑር ሺፋ ፡Dental Surgeon.
Show all...
ከሸይጧን ጋር ቃለምልልስ . ሥም ፡ ሸይጧን እንባላለን በዋናው፣ ኢብሊስም ሥማችን ነው፤ ሌሎች አባ ሙራ ይሉናል፤ በተለያየ ቋንቋ የተለያየ ሥም ይሠጡናል፡፡ አድራሻ ፡ ከሰማዩ ዓለም ከተባረርን ቆይተናል፤ ምድር ላይ ከነዝርያችን ተበትነናል፣ ዓለምን ከጫ እስከ ጫፍ ሞልተናል፡፡ ፓሰፖርት ቪዛ አያስፈልገንም፤ አንታይም አንጨበጥም፤ በፈለግነው ቅርፅ እንቀርባለን፤ ደም ዉስጥ ጭምር እንዘዋወራለን፡፡ ዕድሜ ፡ ለምነን በሰፊው ተሠጥቶናል፤ ተማፅነን የጠየቅነውን ተችረናል፤ አላህ ብቻ ይወቀው ቁጥሩን፤ ብቻ እስከ ዓለም ፍፃሜ አለን፡፡ ሥራ ፡ ምን ጥያቄ አለው የታወቀ ነው፤ አናፍርበትም ሥራችን ነው፤ ዓለም በፅድቅ ጎዳና እንዳትጓዝ ማተራመስ፤ በሠላም እኖራለሁ የሚልን ሕዝብ ማመስ፤ ከመንገዳችን የራቀውን አድኖ መመለስ፤ በወንጀል ኃጢኣት ነፍሱን ማደስ፣ ወደተዘጋጀልን የጀሀነም እሣት አብረን መፍሰስ፡፡ የሥራ ልምድና የብቃት ማረጋገጫ ፡- ተጨባጭ ሥራችንን ማየት ይቻላል፤ ጥረታችን በአብዛኛው ተሳክቶልናል፤ የዓለምን ሕዝብ 2/3ኛውን አክፍረናል፤ የሙስሊሞችን አንድነት ላያንሠራራ ንደናል፤ ወጣቶችን እግር በግር ተከታትለን አፍንድተናል፡፡ ደመወዝ : ቁርጣችን ቀድሞውኑ ተነግሮናል፤ ከጠዋቱ በእሣት ተበስረናል፤ ስለበሰበስን ዝናብ አንፈራም፤ ወደ ተውባው በር ፈፅሞ አንመጣም፤ ከጀነት እሣትን መርጠናል፤ በሰዎች ክፋትና ራስ ወዳድነት ተደስተናል፤ ከክፍያ ሁሉ ይህ ብቻ ይበቃናል፤ ምነው በንግግርህ እኛ እኛ ማለት ታበዛለህሳ? ድሮም ይኸው ነበር እኮ ትልቁ ሙሲባችን፤ ከእዝነቱ ለመባረር ምክንያታችን፤ ከንፁህ እሣት ተፈጥረን፤ ከጭቃ ለተፈጠረው ስገድ ተባልን፤ አምርረን ተቃወምን እንቢ አልን፤ በዚያው ተባረን ቀረን። የትምህርት ሁኔታ አልተማረም እንዳትለኝ ተምሬያለሁ፤ አያውቅም እንዳትለኝ አውቃለሁ፤ እያወቅኩ አጠፋለሁ፣ እያየሁም አበላሻለሁ። ዓላማህ ፡ በያዝነው መንገድ እዘልቃለን፤ በሥራችን እንበረታለን፤ ብዙ ተከታዮችን እናፈራለን፤ ወጣቱ እንዳይሾልክብን በሱስ መያዝ፤ ሽማግሌውን በረጅም ምኞት ማደንዘዝ፤ ዘፈን : እሱ እኮ ነው የምድር ላይ ድምፃችን፤ እኛን ወክለሎ መናገሪያችን፤ በዕድሜ ለገፋው ጥሩ ትዝታ፤ ለወጣቱ የልብ ትርታ፤ ሙሰልሰልስ? ታዳጊውን እንቀርፅበታለን፤ ኮረዳዋን እናስለቅስበታለን፤ ጎረምሳውን ሥራ እናስፈታበታለን፤ ግብረገብነትን እናጠፋበታለን፡፡ ስለ ኸልዋ ፡ የተነፋፈቁ ወዳጆችን እናገናኝበታለን፤ በምን ችግር አለው ሥም እናቀራርባለን፤ ሦስተኛ ወገን ሆነን እናደራድራለን፤ ሻይ ቡና እናስብላለን፤ ከኋላ ሆነን እንገፋለን፤ ሲወድቁ ጥለን እንጠፋለን፡፡ ኢኽቲላጥ ፣ ንፁህ እና ጠሃራውን ቀላቅለን፤ አሳስቀን አጨዋውተን አሳስበን፤ አቀራርበን አጠባብሰን፤ ቀዩን መስመር እንንዳለን፤ ከዚያ የለንበትም እንላለን፡፡ ፍቅር ፡ ይህን ጉዳይ እንዴት ላስረዳህ፤ ላታውቅ ነገር ላይገባህ፤ መተዳደሪያችን እሱ ነው፤ በሱ ሥም እንምላለን፤ እናት አባት እናስክዳለን፤ ዲነኛውን እናፈዛለን፤ ኒቃቢስቷን እናደክማለን፤ እናከንፋለን ጨርቅ እናስጥላለን፤ እስከማጋደል ሁሉ እንደርሳለን፤ የሚመችህ የሰው ልጅ ባህሪ: ተናዳጅ ሰው ፈረሣችን ነው እንጋልበዋለን፤ ቀናተኛ ከልብ ያምነናል እንቅልፍ እናሳጠዋለን፤ ተጠራጣሪ ይሠማናል እናቃጥለዋለን፤ ሓሲድ ያዳምጠናል በቁሙ እንገድለዋለን፡፡ የዓላማህ ተባባሪዎች ፡ የቱን ጠርቼ የቱን ልተው፤ የቱን ጠቅሼ የቱን ልለፈው፤ ለጥቅም ያደሩ ሆዳም ዑለሞች፤ በሁለት ፊት የሚኖሩ አስመሳይ ሙናፊቆች፤ በፈጣሪያቸው እምነት ያጡ ከሀዲያን ካፊሮች፡፡ ሰዎችን በምንና እንዴት ታጠምዳለህ? ወጣቱን በፆታዊ ፍቅር ጎልማሳውን በገንዘብ በብር ሽማግሌውን በምኞት በማስከር . ቅጅ
Show all...
እውነተኞቹ ድሆች ~~~~~ ውዱ ገንዘባቸው ልብሳቸው፣ ርካሹ ደግሞ ሥነምግባራቸው የሆኑ ብዙ ሰዎች አሉ። ጥሩ ይለብሳሉ፣ ጥሩ ይሸታሉ ፣ ጥሩ ይመገባሉ። ትልቁ ዓላማቸው ገንዘብ ነው። ሌሎችንም በገንዘብ ይገመግማሉ። ገንዘብ አይተው ሰው ይርቃሉ፣ ይቀርባሉ። በርግጥም እነርሱ አሳዛኝ ድሆች ናቸው። ገንዘብ ብቻ ነው ያላቸው። ልንመቀኛቸው ሳይሆን ልናዝንላቸው ነው የሚገባው። እውነተኞቹ ችግረኞች እነሱ ናቸው። Abx
Show all...
🔅-ቄሱ ዳእዋን ሲያጣጥሙ-🔅 💫-ኢስላም ለ ሁሉም !💫 🚏- መርካቶ አካባቢ ! ✨የጎዳና ዳእዋ✨ 🎙- ኡስታዝ አብዱሶመድ ኡመር https://t.me/rahma_street_daewa_eth
Show all...
👍 1