cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Show more
Advertising posts
34 394Subscribers
+524 hours
+1087 days
+1 83730 days
Posts Archive
በእድሜ ትንሹ የሴኔጋል ተመራጭ ፕሬዝዳንት ፋዬ በትህትና ሁሉንም አስተዳድራለሁ ሲሉ ቃል ገቡ የሴኔጋል ተመራጩ ፕሬዝዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ ከእሁድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በኋላ ባደረጉት የመጀመሪያ ንግግር በትህትና እና በግልፅነት ለማስተዳደር ቃል ገብተዋል። የፋዬ ዋና ተቀናቃኝ የሴኔጋል ገዢው መንግስት ጥምረት ፓርቲ ተወካይ የነበሩት አማዱ ባ አስቀድማው ሽንፈታቸውን በማመን የ44 አመቱ በሀገሪቱ ታሪክ በእድሜ ትንሹ ፕሬዝዳንት ለመባል የሚያስችል መድረክ አመቻችተዋል። ፋዬ እንዳሉት "እኔን በመምረጥ የሴኔጋል ህዝብ ካለፈው ስርዓት ለመላቀቅ መርጧል" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። "በትህትና እና በግልጽነት ለማስተዳደር ቃል እገባለሁ" በፕሬዚዳንትነቴ ትኩረት ከምሰጣቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል አንዱ ለሶስት ዓመታት የዘለቀውን አለመረጋጋት እና በሀገሪቱ የፖለቲካ ቀውስ ተከትሎ የተፈጠረውን ውጥረት “በብሄራዊ እርቅ” መፍታት ነው ሲሉ ፋዬ አክለዋል። ሙስናን በየደረጃው ለመታገል፣ ተቋማትን ለመገንባት እና የኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ ቃል ገብተዋል። ፋዬ ተሰናባቹን ፕሬዝዳንት ማኪ ሳልን የተሳካ የህዝብ አስተያየት እንዲሰጥ ላደረጉት እገዛ አመስግነዋል። የሕገ መንግሥታዊ ጉባኤው የመጨረሻ የምርጫውን ውጤት በይፋ አልገለፁም።ነገር ግን በመላ አገሪቱ በምርጫው ውጤት የተደሰቱ ዜጎች ከፍተኛ ድምፅ በማሰማት ደስታቸውን እያገለፁ ይገኛሉ።በምርጫው ጊዜያዊ ውጤቶቹ መሰረት ፋዬ 53.7 በመቶ የመራጮችን ድምፅ ሲያገኙ እና ተቀናቃኛቸው ባ 36.2 በመቶ ድምፅ አግኝተዋል።ይህው ድል የተገኘው ፋዬ ከእስር ከተለቀቁ ከሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው። አሸናፊው የግራ ክንፍ ፖፑሊስት ፓርቲ የፕሬዚዳንት ማኪ ሳል መንግስትን በሙስና በመወንጀል እና ሥር የሰደደ ድህነትን ሊፈታ ባለመቻሉ የተቃውሞ ሰልፎችን ሲያዘጋጅ ቆይቷል። ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ሳል ውሳኔ በመጀመሪያ በየካቲት ወር የታቀዱትን ምርጫዎች ለማራዘም መወሰኑ የመጨረሻውን የፖለቲካ ቀውስ አስነስቷል።የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ባለፈው ወር ሊካሄዱ የነበረውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማራዘም ባደረጉት ሙከራ ምንም አይነት ፀፀት እንደማይሰማቸው የገለፁ ሲሆን በመላው በሀገሪቱ የሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ተቃውሞ ማስነሳቱ ይታወሳል። ሳል ምርጫው እንዲዘገይ የተወሰነው በአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን፣ በፓርላማ አባላት በተነሱ የምርጫ ስጋቶች ነው ብለዋል። "ይቅርታ የምጠይቀው የለኝም፣ ምንም ስህተት አልሰራሁም። እንደ ሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ማድረግ ያለብኝን ወስኛለሁ ሲሉ ተደምጠዋል። የተወሰዱት እርምጃዎች በሙሉ በህግ እና በመመሪያው ማዕቀፍ ውስጥ ናቸው ሲሉ ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ሳል ተናግረዋል። በመላ አገሪቱ ወደ ሁከት ፣ግጭቶች እና የፖለቲካ ውጥረት ምክንያት የሆነው ምርጫውን ለማዘግየት ቢታቀድም በስተመጨረሻ በሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምርጫን የማዘግየት ሂደት ተሽሯል። ምርጫው እስከ ታህሳስ ወር ድረስ እንዲካሄድ የተደረገው እንቅስቃሴ ከከሸፈ በኋላ ምርጫው እሁድ እለት ተካሂዷል። ተቺዎች ፕሬዚዳንቱን የስልጣን ቆይታቸውን ለማራዘም ሞክረዋል ሲሉ ከሰዋል። ነገር ግን ፕሬዝዳንት ሳል የእሁድ ምርጫ ከተከሄደ በኃላ ከአንድ ቀን በላይ ስልጣን ላይ እንደማይቆይ አጥብቀው ሲናገሩ ነበር። በበረከት ሞገስ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 24 2👎 1
ከአርኖልድ ሽዋርዜንገር የበለጠ የሰውነት አቋም ያላት ግለሰብ በበርካቶች ዘንድ መነጋገሪያ ሆናለች ጃኪ ኮር በመባል የምትታወቀው በአካል ብቃቷ በርካቶች የሚገረሙባት የ34 አመቷ ኔዘርላንዳዊት የአካል ብቃት አድናቂ ሲሆን አርኖልድ ሽዋርዜንገር ካለው የእጅ ባይሴፕ 22 ኢንች ጋር ሲወዳወር የእርሷ በሁለት ብልጫ በማሳየት 24 ኢንች አላት ተብሏል። ኮርን ሁል ጊዜ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ የምትገኝ ሰው ናት። ነገር ግን በ2020 በኮቪድ-19 እገዳዎች ምክንያት ከኪክ ቦክስ እረፍት እንድትወስድ ከተገደደች በኋላ በትልቁ ለውጥ ወዳመጣችበት ውሳኔ ተሸጋግራለች። ይህም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ክብደቷ ከእጥፍ በላይ ጨምሯል፣ በተለምዶ ከርቪ የሚባለውን የሰውነት አቋሟን በመቀየር ግዙፍ ጡንቻዎችን መገንባት ስራዋ ሆነ። ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንካራ እንደሆንኩኝ ይሰማኛል፣ በማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ላይ 'ወፍራም' ወይም 'በጣም ወንድ' መሳይ ብትባልም፣ በአዎንታዊው ላይ ብቻ አተኩራለች እና ሌሎች ሰዎችም እንዲሁ እንዲያደርጉ ታበረታታለች።አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ያለን ስም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አስተያየት ሲሰጡኝ አስተያየቱብ አጠፋለሁ ከዚያም ሰውዬውን አግደዋለሁ፣ በአሉታዊ አስተሳሰቦች ላይ ምንም ቦታ የለኝም ትላለች። "በእውነት በጉዞህ ላይ ሰዎች አጸያፊ ነገሮችን የሚነግሩህ ከሆነ አሉታዊ ሃሳቦችን ወይም አስተያየቶችን ችላ በል" ስትል ታክላለች።ኮርን ኪክቦክስን በምሰራበትት ጊዜ ሁል ጊዜ ጠንካራ ስሜት ይሰማኛል፣ ነገር ግን በተከታታይ የአመጋገብ ተሰላችቼ ነበር። አሁን ሰውነቴን መገንባት ስጀምር የበለጠ ጥንካሬ ይሰማኛል።  ሁልጊዜ ክብደት መቀነስ አይኖርብኝም ጤናማ አመጋገብ ላይ ብቻ ትኩረት አደርጋለው ትላለች። ብዙ ካሎሪዎችን ለመጠቀም እየሞከረች እና ክብደትን በማንሳት ጡንቻዎችን ለመገንባት እንደምትሰራ ትናገራለች።ሆላንዳዊቷ ግለሰብ የእለት የስልጠና ዝግጅቷን በ100 ፑሽአፕ እና 250 ሲት አፕ በመስራት ትጀምራለች። በመቀጠልም ለሁለት ሰአት የጥንካሬ ስፖርት የምትሰራ ሲሆን ይህም አብዛኛውን ጊዜ ከ150 ኪሎ ግራም እስከ 200 ኪ.ግ ክብደት ታነሳለች። ተጨማሪ ክብደቷት በመጎተት እና በእግር ፕሬስ ላይ እስከ 450 ኪሎ ግራም በመግፋት አስደናቂ የሰውነት አካል ገንብታለች። አንዳንድ ወንዶች በአካል ለማግኘት እና እንደርሷ ሰውነታቸውን ለመገንባት አልፎም ተርፎ ለጋብቻ የሚፈልጓት ሰዎች ጥያቄ እያቀረቡ መሆናቸውን ተናግራለች። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
😁 16👍 9🔥 2
🤔 9👍 2 1🙏 1
በድሬዳዋ ከተማ ሀዘን ላይ ከነበሩ ወላጆቿ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት የዘረፈችው ግለሰብ  በቁጥጥር  ስር ዋለች የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም  ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አራት ልዪ ስሙ መብራት ሃይል  አብዩ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሀዘን ላይ  ከተቀመጡ ወላጆቿ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት  ዘርፋ ለማምለጥ  የሞከረችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውላለች። ወላጆቿ የስርቆት ወንጀል እንደተፈጸመባቸው ለፖሊስ አመልከተው የነበረ መሆኑን የአካባቢው  ፖሊስ ጣቢያ ወንጀል ምርመራ አስተባባሪ  ተወካይ ዋና ሳጅን ስንዱ ካሳሁን  በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ተከሳሿ ግለሰብ በአንድ ትምህርት ቤት አብሯት የሚማሩ ጓደኞቿን ከቤተሰቦቿ ንብረቱን እንዲዘርፉ በመንገር  እና ንብረቱን ሸጠው ከተማ ቀይረው የራሳቸውን ህይወት እንደሚመሩ አሳምናቸው  የነበረ መሆኑ ተጠቁሟል። ቤተሰቦቿ ሀዘን ላይ ባሉበት ሰዓት ከጓደኛዋ ጋር ተባብራ በሳጥን ተቀምጦ  የነበረ ወድ የሆነ ጌጣጌጥ እና ንብረት ሰርቀው በደላላ አማካኝነት ወርቁን በማሽን አስፈትሸው አብሯት የሰረቀችውን ጨምሮ ሁለት ጎደኞቿን ወደ ሀረር ከተማ  የላከቻቸው መሆኑ ተረጋግጧል ። ወላጆቿ ጉዳዩን ለፖሊስ ማመልከታቸውን ያወቀችው ልጅ ድርጊቱን መፈጸሟን ፖሊስ ጥርጣሬው ውስጥ  እንዳስገባት ስታውቅ  ድርጊቷን አምና ቃሏን  እንዲሁም ጎደኞቿ ያሉበት ቦታ ልታመለክት ችላለች ። የድሬዳዋ ፖሊስ ከሀረሪ ፖሊስ ጋር በመነጋገር ባደረገው ጠንካራ ክትትል  በሀረር ከተማ ሆቴል ውስጥ ተከራይተው  በቁጥጥር  ስር ሊውሉ መቻላቸውንና  መዝገቡም እየተጣራ እንደሚገኝ  ዋና ሳጅን ስንዱ ካሳሁን ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ። በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 25🤔 7😢 4
የኢህአፓ ሊቀመንበር ዝናቡ አበራ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ(ኢህአፓ) ሊቀመንበር ዝናቡ አበራ ዛሬ መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም ማለዳ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፓርቲው ለአሻም አረጋግጦላታል፡፡ ሊቀመንበሩ በአዲስ አበባ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙ ሲሆን በምን ጉዳይ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ግን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ለማወቅ አልተቻለም፡፡ [Asham] #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
😁 14👍 11🤬 5 1
ለባንክ ጥበቃ የተረከበውን መሳሪያ ይዞ የተሰወረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጰያ ካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ኡፋ ከተማ ታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት የተሰጠዉን ኃላፊነት ወደጎን በመተዉ በጥበቃ ሰራተኝነት ከሚሰራበት ቦታ መሳሪያ ይዞ የተሰወረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የዞን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ በደብቡ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት እና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በዳሸን ባንክ የጥበቃ ሰራተኛ ሆኖ በሚሰራበት ቦታ ለጥበቃ ስራ አገልግሎት ተሰጥቶት የነበረዉን አንድ ክላሽ ከመሰል 30 ጥይትና ከአንድ ካርታ ጋር ተረክቦ የነበረው ይዞ መሰወሩ ተገልፆል፡፡ የካፋ ዞን ዐቃቤ ህግ መምሪያ የሙስና ነክ ወንጀሎች ተከሳሽ አንዱአለም ብረሃኑ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በፈፀመዉ በስራ ተግባር የሚፈፀም የመዉሰድና የመሰወር ወንጀል ክስ መሰርቶበታል።የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የክስ መዝገቡን ሲመለከት ቆይቶ ተከሳሹ በፈፀመው የሙስና ወንጀል በሰዉ እና በኤግዚቢት ማስረጃ በመረጋገጡ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል ። በዚሁ መሰረት የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰሞኑን ባስቻለዉ የችሎት ተከሳሽ አንዱአለም ብረሃኑ በ1 ዓመት እስራትና በአንድ ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወስኖበታል ሲሉ ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡ በሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 14😁 14 3
በአሜሪካ ቁልፍ የሚባለው የባልቲሞር ድልድይ መፈራረሱ ተሰማ የሜሪላንድ ትራንስፖርት ባለስልጣን (ኤምቲኤ) ክስተቱን አስመልክቶ ዛሬ ማለዳ ብሎ በ ኤክስ ገፁ ላይ በምስል አጋርቷል። "አይ-695 የሚባለው ቁልፍ ድልድይ ክፉኛ መውደሙን በመግለፅ አሽከርካሪዎች በፓታፕስኮ ወንዝ ላይ ያለውን መንገድ ከመጠቀም እንዲቆጣቡ። በሁለቱም አቅጣጫ ያሉት መንገዶች ተዘግተው የትራፊክ እንቅስቃሴው ተስተጓጉሎ ውሏል።በዩናይትድ ስቴትስ ባልቲሞር ከተማ የሚገኘው ይህው የፍራንሲስ ስኮት ቁልፍ ድልድይ በመርከብ ከተመታ በኋላ ፈርሷል ሲል ባለስልጣኑ አክሏል። አደጋው ከጠዋቱ 1፡30 ላይ ሲደርስ መርከቧ ድልድዩን ከመምታች በኃላ በእሳት ተቃጥላ የሰጠመች ሲሆን በርካታ ተሽከርካሪዎች ውሃ ውስጥ መውድቃቻውን የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ባለሥልጣናቱ ክስተቱን "የጅምላ ጉዳት" ብለውታል የባልቲሞር ከንቲባ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በቦታው እንዳሉ እና የነፍስ አድን ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሰጭዎች ቢያንስ ሰባት ሰዎች በውሃ ውስጥ አሉ ተብለው መገመታቸውን እና እየተፈለጉ ነበር ሲል የባልቲሞር የእሳት አደጋ መከላከያ ዲፓርትመንት የግንኙነት ዳይሬክተር ኬቨን ካርትራይት ለአሶሼትድ ፕሬስ ተናግረዋል። አደጋው ሲደርስ የትራክተር ጎታችን ጨምሮ በርካታ ተሽከርካሪዎች በድልድዩ ላይ ነበሩ። ካርትራይት "አሁን ትኩረታችን እነዚህን ሰዎች ለማዳን እና መልሶ ለማግኘት መሞከር ነው" ብለዋል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 27😢 4 2
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንክ ስርዓት ላይ በተፈጠረው ችግር ገንዘብ የወሰዱ 9 ሺ 2 መቶ 81 ግለሰቦች በፈቃደኝነት መልሰዋል ተባለ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባጋጠመው ችግር ምክንያት ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በሂደቱ ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቦችን ሂሳብ ልየታ ተከናውኗል የተባለ ሲሆን በዚህም 15 ሺህ 8 ያህል ሂሳብ ቁጥሮች መገኘታቸውን ባንኩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል ። በዚህም ጠቅላላ በተፈጠረው ችግር ያላግባብ የተወሰደ ገንዘብ መጠን በ25 ሺህ 716 ደንበኞች 801 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን የባንኩ ፕሬዝዳንት አ/ቶ አቤ ሳኖ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል ። ሆኖም በመጀመሪያው ቀን በተደረገ ጥረት ከ10 ሺህ 727 በአካውንታቸው ውስጥ በቂ ገንዘብ ከነበራቸው ደንበኞች 44 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል ተብሏል ። ጥረቱ ቀጥሎ በቀጣይ ቀናት ከ15 ሺህ 8 በአካውንታቸው ውስጥ ያለው ገንዘብ በቂ ባይሆንም የነበረን ገንዘብ በማካካስ 205 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሏል ተብሏል ። በተለይም  ባንኩ ባቀረበው ጥሪ መሠረት 9 ሺ 2 መቶ 81 ያህል ግለሰቦች በፈቃደኝነት የወሰዱትን 223 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር መሉ በሙሉ መመለሳቸው ተገልጿል ። እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ተሳትፎ የነበራቸው 5 ሺ 1 መቶ 60 ያህል ግለሰቦች ከወሰዱት ገንዘብ በፈቃደኝነት ሙሉ በሙሉ ባይሆንም በከፊል 149 ሚሊዮን ብር መልሰዋል ተብሏል ። በአጠቃላይ በተደረገው ጥረት እስከ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ባለ ሪፖርት መሠረት ከ622 ነጥብ 9 ወይንም 78 በመቶ ያክሉን ገንዘብ ወደ ባንኩ ተመላሽ መደረጉ ተገልጿል ። ነገር ግን ቀሪ 567 ግለሰቦች ያላግባብ ከወሰዱት 9 ሚሊዮን 838 ሺህ 329 ብር ውስጥ እስከ አሁን ድረስ ምንም አይነት ክፍያ ወደ ባንኩ ቀርበው እንዳልፈፀሙ አ/ቶ አቤ ተናግረዋል ። ስለሆነም ባንኩ ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ በፈቃደኝነት ምላሽ ያልሰጡ ግለሰቦችን በተመለከተ በጉዳዩ የተሳተፉ ግለሰቦችን ማንነት የሚገልፅ ማስታወቂያዎችን ፎቶግራፍን ጨምሮ በተመረጡ መገናኛ ብዙሃን ይፉ ይደረጋሉ ተብሏል። ይኸውም እስከ ሚቀጥለው ቅዳሜ ድረስ ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ ደግሞ በህግ አግባብ ለመጠየቅ እንደሚሰራ ተገልጿል ። በአበረ ስሜነህ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 20😁 13 4🔥 2
👍 1
ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ የአፍሪካ በእድሜ ትንሹ ፕሬዝዳንት በመባል በሴኔጋል ምርጫ አሸነፉ ከአንድ አመት በፊት ስለ አዲሱ ፕሬዝዳንት ማንነት  የሰሙ በጣም ጥቂቶች ናቸው፣ አሁን ፋዬ ፕሬዝዳንት ለመሆን ተዘጋጅተዋል። የባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ ያልተለመደ ድል በሴኔጋል ፖለቲካ ውስጥ አግራሞትን ፈጥሯል። ከአጋራቸው ኦስማን ሶንኮ ጋር በእስር ላይ ለወራት ለማሳላፍ ተገደው የነበረ ሲሆን ከእሁዱ ከፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አንድ ሳምንት በፊት ከእስር ተለቀዋል። "ሚስተር ክሊን"፣ በሚል በቅፅል ስማቸው የሚታወቁትና ሰኞ እለት 44ኛ ዓመት ልደታቸውን የሚያከብሩት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ በርካታ ማሻሻያዎችን ከሴኔጋል ሰማይ ስር እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል። በርካታ ተቀናቃኞች ሽንፈታቸውን አምነው መቀበላቸውም ተሰምቷል።ከሦስት ዓመታት አለመረጋጋት እና በስልጣን ላይ በነበሩት ማኪ ሳል ላይ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ሚሊዮኖች እሑድ በተደረገው ሰላማዊ ምርጫ ተሳትፈዋል። ለፕሬዝዳንትነት 19 እጩዎች በምርጫው ቀርበው ነበር።የገዢው ፓርቲ ተወካይ አማዱ ባ ወይም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመባል ይገደዳሉ።ደጋፊዎቻቸው ርችቶችን ሲተኩሱ፣ የሴኔጋልን ባንዲራ ሲያውለበልቡ እና ቩቩዜላዎችን ሲነፉ ተስተውለዋል። የግራ ክንፍ ፖፑሊስት የፕሬዚዳንት ማኪ ሳል መንግስት በሙስና በመወንጀል እና ሥር የሰደደ ድህነትን ሊፈታ ባለመቻሉ የተቃውሞ ሰልፎችን ሲያዘጋጅ ቆይቷል። ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ሳል ውሳኔ በመጀመሪያ በየካቲት ወር የታቀዱትን ምርጫዎች ለማራዘም መወሰኑ የመጨረሻውን የፖለቲካ ቀውስ አስነስቷል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 35 5😁 1🕊 1
የፀጥታው ምክር ቤት የጋዛን የተኩስ አቁም የሚጠይቅ ውሳኔ ለመጀመሪያ ጊዜ አሳለፈ 👉 እስራኤል የውሳኔ ሀሳቡን ተቃውማለች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በጋዛ ላይ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረስ ጠይቋል። ዩናይትድ ስቴትስ እርምጃውን ከቀደመው አቋሟ በተለየ መልኩ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቷን አልተጠቀመችም። በሁለቱም ወገኖች በኩል ያኩ ታጋቾች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ምክር ቤቱ ጠይቋል። ጦርነቱ በጥቅምት ወር ከጀመረ ወዲህ ከበርካታ የከሸፈ ሙከራዎች በኋላ ምክር ቤቱ የተኩስ አቁም ጥሪ ሲያቀርብ የመጀመሪያው ነው። የዩናይትድ ስቴትስ እርምጃ በዋሽንግተን እና በተባባሪዋ እስራኤል መካከል ያለው ልዩነት እስራኤል በጋዛ ላይ የምትወስደውን ያልተመጣጠነ ጥቃት ላይ ያላቸውን ልዩነት ያሳያል።የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት ከወትሮው በተለየ ጠንካራ ተግሣጽ ዩናይትድ ስቴትስ ቀደም ሲል የነበራትን የተኩስ አቁም የመሻር መብቷን ከታጋቾቻችን ጋር በቀጥታ የሚያገናኘውን አቋሟን “ትታለች” ብሏል። "በሚያሳዝን ሁኔታ ዩናይትድ ስቴትስ አዲሱን የውሳኔ ሃሳብ አልቃወመችም" ሲል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት ገልጿል። ይህም ሃማስ የወሰዳቸውን ምርኮኞች ሳይፈታ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ በእስራኤል ላይ አለም አቀፍ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ተስፋ በማድረግ ታጋቾችን ለማስፈታት የሚደረገውን ጥረት ጎድቶታል ሲል መግለጫው አክሏል። በተጨማሪም ኔታንያሁ በዚህ ሳምንት በዋሽንግተን የእስራኤል ልዑካን እና የአሜሪካ ባለስልጣናት ሊያደርጉት የነበረውን ስብሰባ ለመሰረዝ ወስነዋል። የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር የእስራኤል ታጋቾች አሁንም እዚያው ታስረው እያሉ በጋዛ ያለውን ጦርነት ቴላቪቭ አታቆምም ብለዋል። የፀጥታው ምክር ቤት ሰኞ ዕለት ባደረገው ድምፅ ዩናይትድ ስቴትስ ድምፀ ተአቅቦ ስታደርግ፣ የተቀሩት 14 አባላት ደግሞ ድጋፍ ሰጥተዋል።የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ እንዳሉት ዩኤስ ውሳኔው እንዲፀድቅ መወሰኗ "የፖሊሲያችን ለውጥ" አለ ማለት አይደለም ብለዋል። ዩናይትድ ስቴትስ የተኩስ አቁም ስምምነትን ትደግፋለች ነገር ግን የውሳኔ ሃሳቡን አልደገፈችም ምክንያቱም የቀረበው ጽሑፉ ሃማስን የማያወግዝ ነው ብለዋል ። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 36 2
በጋምቤላ ሴት መስሎ ሲሰራ በፖሊስ ተይዞ የነበረዉ ግለሰብ ከስድስት ወራት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በሸካ ዞን በቤት ሰራተኝነት ሲሰራ በቁጥጥር ስር ዋለ  በደቡብ  ምእራብ ኢትዮጵያ ሸካ ዞን በአንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ ሴት በመምሰል ህብረተሰቡን ሲያታልል የነበረው ቢኒያም ከበደ የተባለ ግለሰብ  በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል። የደብቡ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ግለሰቡ ቃልኪዳን ወርቁ በሚል ሀሰተኛ ማንነት በቤት ሰራተኝነት ተቀጥሮ በመስራት ላይ እንዳለ ጥርጣሬ የነበራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች  በመጠቆማቸው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጸዋል። ህብረተሰቡ ከእንደዚህ ዓይነት ግለሰቦች ራሳቸውን እንዲጠብቁና በተለይም ሆቴሎች እና የምግብ ቤት ባለቤቶች ሰራተኛ ሲቀጥሩ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ተብሏል። ግለሰቡ ከዛሬ 6 ወር በፊት በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ሴት መስሎ በአስተናጋጅነት ተቀጥሮ የቀን ስራ እየሰራ እንዳለ በሰራተኞቹ ጥቆማ መያዙን ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን መዘገቡ አይዘነጋም። ወጣቱ በጋምቤላም ሆነ በሸኮ ዞን በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት በተመሳሳይ ሀሰተኛ ስምን በመጠቀም እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። በሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
😁 92👍 21😢 8🤔 5👎 4🤯 2💔 2 1
በአዊ ዞን ባለፉት ስድስት ወራት  ምንም አይነት የውጪ ሀገር ጎብኝ ወደ አካባቢው አለመሄዱ ተነገረ 👉ከሀገር ውስጥ ጎብኝዎች  ብቻ 1ሚሊዮን ብር  ገቢ ማግኘቱም ተጠቁሟል በ2016  ዓ.ም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ  በአዊ ዞን ባሉ የባህል እና የቱሪዝም ስፍራዎች   ላይ ምንም አይነት የውጪ ሀገር ጎብኝዎች አለመጎብኘታቸው   ተገለጸ፡፡ በዞኑ የተለያዩ ለቱሪዝም መስህብ የሆኑ ስፍራዎች መኖራቸው  ተገልጿል ፡፡ ከእንዚህም መካካል በአካባቢው ያለው የዶንዶር  ፣ ኪስኪ፣ ፏንቅ የተባሉ  ፏፏቴዎች እንዲሁም   ዘንገና ፣ ጥርብ ሃይቅ እና በርካታ  ገዳማትም በቱሪስት ከሚጎበኙ ቦታዎች ቀዳሚዎቹ እንደሆኑ በአዊ ዞን ባህል እና  ቱሪዝም የባህል እሴቶች ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ወለሌ ጌቴ  በተለይም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን  ተናግረዋል። በ2016 በጀት ዓመት  ባለፉት ስድስት ወራት የሀገር ውስጥ ጎብኝዎች 10ሺህ 7መቶ የነበሩ ሲሆን የውጪ ጎብኝ ደግሞ ምንም አለመመዝገቡንም ተጠቁሟል ፡፡ በዚኅም ከሀገር ውስጥ ጎብኝዎች ብቻ  1ሚሊዮን 176ሺህ 746 ብር  ገቢ ተገኝቷል ፡፡  በተመሳሳይ ያለፈው  በተመሳሳይ  በጀት ዓመት ላይ  29ሚሊዮን ብር በላይ ማግኘት  ተችሎ የነበረ መሆኑን ተገልጿል፡፡ በዚህም የ2016 በጀት ዓመት ከቱሪዝም የገተገኘው ገቢ ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር  በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የሚያመላክት እንደሆነ  እና ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑንም   ሃላፊው ነግረውናል፡፡ በተጨማሪም  በተያዘው ዓመት  የቱሪዝም ገቢ ለመቀነሱ እንደምክንያት  ከሚጠቀሱት መካካል የትራንሰፖርት አገልግሎት እና በአካባቢው ከዚህ በፊት ይካሄዱ የነበሩ  የኮንፍረንስ እና ፕሮግራሞች  አለመደረጋቸው በገቢ ላይ የራሱ የሆነ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳለውም  አቶ  ወለሌ ጌቴ   ጨመረውም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡ በኤደን ሽመለስ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 17😢 5 1
ሩስያ በዩክሬን ላይ በፈፀመቺው ጥቃት ከ 1 ሚልየን በላይ ሰዎችን ጨለማ ውስጥ ጥሏል ተባለ ሩሲያ የዩክሬን የኤሌትሪክ ሃይል ተቋማትን በሚሳኤልና ሰው አልባ አውሮፕላኖች መታለች። በሩስያ በኩል የተሰጠው ወታደራዊ መግለጫ ኢላማዎቹን እንዴት እንደመታ ባይገልጽም በክልሉ የተሰየመ የሩስያ ባለስልጣን እንደገለፀው ከሆነ በከፍተኛ ሁኔታ ከዩክሬን የአየር ላይ ጥቃት እንደተሰነዘረና እና የአየር መከላከያዎች በክሬሚያ ሴቫስቶፖል ወደብ ላይ ከ 10 በላይ ሚሳይሎች ኢላማቸው ሳይመቱ እንዲወድቁ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። በሩሲያ የተሾመው የሴቫስቶፖል ገዥ ሚካሂል ራዝቮዛይቭ በቴሌግራም ባጋራው ፅሑፍ "በቅርብ ጊዜ ውስጥ በጣም ግዙፍ ጥቃት ነበር" ያለ ሲሆን የ65 አመት አዛውንት መሞታቸውን ፣ ሌሎች አራት ሰዎች መቁሰላቸውን እንዲሁም የመንገደኞች ጀልባዎችና አውቶብሶችን ጨምሮ የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች በከፊል ጉዳት እንደደረሰባቸው እንዲሁም አምስት ጀልባዎችም በጥቃቱ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልፀዋል። ጉዳት ከደረሰባቸው ተሽከርካሪዎች መካከል ሶስት የመንገደኞች አውቶቡሶች ፣ 13 የትምህርት ቤት አውቶብሶች እና አንድ ትሮሊ አውቶብስ መሆናቸውንም አክለዋል። በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የተሰራጨው ምስል በከተማው ውስጥ ከፍተኛ ፍንዳታ እሳትና ጥቁር ጭስ ታይቷል። የሳተላይት ምስሎች እንደሚያሳዩት ሩሲያ ብዙ መርከቦችን ወደ ምስራቅ አቅጣጫ ወደ ኖቮሮሲይስክ ወደብ በማዛወር ላይ እያለች ነው አብዛኞቹ ጥቃቶች የተፈፀሙት። ሩሲያ ከቅርብ ቀናት ወዲህ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን የአየር ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ በማባባስ በድንበር ክልሎቿ ላይ ለደረሰባት ጥቃት የበቀል እርምጃ ነው ብላለች። ሞስኮ ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በዩክሬን የኢነርጂ ዘርፍ ላይ ትልቁን የአየር ላይ ጥቃት የጀመረች ሲሆን ሞስኮ የዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭን ኢላማ ማድረግም ጀምራለች። እሁድ እለት ኪየቭ እና የሊቪቭ ምዕራባዊ ክልል "ግዙፍ" የሩስያ የአየር ጥቃት ደርሶባቸዋል የተባለ ሲሆን ምንም እንኳን በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ባይደርስም ሩሲያ በአንድ ሌሊት 29 ክራይዝ ሚሳኤሎችን እና 28 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መተኮሷን የዩክሬን ባለስልጣናት ተናግረዋል። ኪየቭ ተጨማሪ የምዕራባውያን ዕርዳታ አቅርቦት መዘግየት ስላጋጠማት የሩሲያ ኃይሎች በሰው ኃይል እና በጥይት ያላቸውን የበላይነት ለመጠቀምም እየሞከሩ ነው። ቅዳሜ እለት ሞስኮ በምስራቃዊ ዩክሬን በባክሙት ምዕራባዊ ዳርቻ ላይ ያለች መንደር መያዙን ተነግሯል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የፖላንድ ጦር በምእራብ ዩክሬን ላይ ከተተኮሰው የሩስያ ሚሳኤል አንዱ ወደ አየር ክልሉ መግባቱን ተናግሯል። “በምሽት ከተተኮሱት የክሩዝ ሚሳኤሎች በአንዱ የአየር ክልላችን ጥሷል…”ሲል ሰራዊቱ በኤክስ ላይ የገለፀ ሲሆን ፖላንድ በዚህ ጉዳይ ከሞስኮ ማብራርያ እንደምትፈልግም ተገልጿል። በሚሊዮን ሙሴ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 20 3😢 1
የሰራሁበትን ገንዘብ  ተከለከሉኝ በማለት  የመግደል ሙከራ የፈጸመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ግራዋ ከተማ ውስጥ የሰራሁበትን  የጉልበቴን  ገንዘብ ተከለከልኩ በማለት  ቂም በመያዝ የመግደል ሙከራ የፈጸመው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የወረዳው ፖሊስ አስታወቀ። የግራዋ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ወጋሪ ጀቤሳ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን እንደገለጹት ተከሳሽ አራርሶ ከድር በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ግራዋ ከተማ መናሀሪያ የተባለው አካባቢ መጋቢት  23 2015 ከምሽቱ 12 ሰአት የሰራሁበት ገንዘብ ከለከለኝ በማለት ጸብ በማንሳት በያዘው ቢላ ተበዳይ ፍራኦል ጅብሪልን በመውጋት ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል። ተበዳይ በአካባቢው ህብረተሰብ እና ፖሊስ እገዛ ሆስፒታል ገብቶ በተደረገለት የቀዶ ጥገና ህክምና ከሞት መትረፉ ተገልጿል። በዚህም መሰረትም ፖሊስ ተከሳሽን በቁጥጥር ስር በማዋል ከአቃቤ ህግ ጋር በመሆን የምርመራ መዝገቡ በሰው እና በህክምና ማስረጃ አጠናክሮ ለፍ/ቤት ያቀርበዋል። የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ ቤት ተከሳሽ አራርሶ ከድር በፈጸመው የአካል ማጉደል እና የመግደል ሙከራ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ7 አመት እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የግራዋ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ወጋሪ ጀቤሳ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 5🔥 3🤔 3👏 1
ዚምባብዌ ፤ ባለፉት 18 ወራት የተካሄዱ ጋብቻዎች ህጋዊ አይደሉም አለች በዚምባብዌ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ አዲስ ተጋቢዎች የጋብቻ የምስክር ወረቀታቸው ተቀባይነት እንደሌለው ተነግሯቸዋል ተብሏል። ባለፉት 18 ወራት ውስጥ የተሰጡ የምስክር ወረቀቶች ባዶና ህጋዊነት እንደሌሌቸው የተነገረ ሲሆን ይህም በዚህ ጊዜ ውስጥ ያገቡትን ጥንዶች ሊጎዳ ይችላል ተብሏል። የዚምባብዌ የህግ ማህበረሰብ በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ የህግ ባለሙያዎች የማንቂያ ማስታወቂያ ባወጣ ጊዜ ነበር ጉዳዩ ግልጽ የሆነው። በመስከረም 2022 ተግባራዊ የሆነው አዲሱ ድርጊት በባህላዊ ትዳር ውስጥ ለትዳር አጋሮች ከፍተኛ መብቶችን መስጠትን ጨምሮ ሰፊ ለውጦችን አምጥቷል ተብሏል። ይህም የታዳጊ ልጆች ጋብቻንም ወንጀል አድርጓል። የህግ ባለሞያዎች ህብረትም ተጎጂዎቹ ወይንም ወረቀታቹ ህጋዊ አይደለም የተባሉት ባለትዳሮች ጊዜው ሳይረፍድ የምስክር ወረቀታቸውን ወደ ሬጅስትራር እንዲወስዱና ሰነዱን አስተካክለው ማህተም እንዲያስደርጉ መክረዋል። በዚህ ምክንያት ሊፈጠሩ ከሚችሉ ችግሮች መካከል የህግ ባለሙያዎቹ ሲጠቅሱ ልክ ያልሆነ የምስክር ወረቀት ካለህ መፋታት አትችልም ሲሉም ጠበቆቹ አስጠንቅቀዋል። ከቢቢሲ ጋር የተነጋገሩ በርካታ አዲስ ተጋቢዎች የምስክር ወረቀታቸው ትክክል እንዳልሆነ ከዚህ ቀደም እንደማያውቁ የተናገሩ ሲሆን ማግባታቸው ለቆጫቸውና ከትዳራቸው መውጫ መንገድ ለሚሹ ሰዎች ጥሩ አጋጣሚ ነው ሲሉም በርካቶች እያፌዙባቸዉ መሆኑን ገልፀዋል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
😁 17👍 8 2🤔 2🤯 1
የተማረኩት የሶማሊያ የባህር ላይ ዘራፊዎች በመርከብ ጠለፋ ወንጀል ተከሰው ለፍርድ ለመቅረብ ህንድ ገቡ 35ቱ የባህር ላይ ወራፊዎች በታህሳስ ወር ኤም ቪ ሩየን (MV Ruen ) የተባለውን የጭነት መርከብ በመጥለፍ ነው የተከሰሱት። ህንድ 35 የተያዙ የሶማሊያ የባህር ላይ ዘራፊዎችን ለፍርድ ለማቅረብ ወደ ሙምባይ ያመጣች ሲሆን ይህ የሆነውም የባህር ሃይሏ የተጠለፈቺዉን የእቃ አጓጓዥ መርከብ መልሶ በቁጥጥር ስር ካዋለ እና በርካታ ታጋቾችን ካስለቀቀ ከቀናት በኋላ ነው። በሰሜናዊ አረቢያ ባህር ከሶኮትራ በስተምስራቅ ታህሳስ ወር ላይ የማልታ ባንዲራ ያለባት ኤምቪ ሩየን የተባለች መርከብ የተጠለፈች ሲሆን ከ 2017 በኃላ የሶማሊያ የባህር ላይ ወምበዴዎች በተሰካ ሁኔታ የጭነት መርከብ የጠለፉበት አጋጣሚ ሆኖም ተመግቧል። የህንድ የባህር ሃይል ኮማንዶዎች መርከቧን መልሰው የተቆጣጠሩት መጋቢት 17 ቀን ሲሆን ከሶማሊያ የባህር ዳርቻ በ480 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነበር። በወቅቱ መርከቧ 17 ሰራተኞችንም እንደያዘች ነበረች። እ.ኤ.አ. በ 2011 የሶማሊያ የባህር ላይ ወንበዴዎች ጥቃት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ወቅት የህንድ ባህር ሃይል በህንድ ንብረቶች ላይ በውንብድና የተሳተፉትን ይከስ እና ያስር ነበር። በህንድ የፀረ-ባህር ወንበዴ ሕጎች መሠረት ደግሞ ጠላፊዎቹ በነፍስ ግድያ ወይም የግድያ ሙከራ ከተከሰሱ በሞት ፍርድ  እንዲሁም በሌብነት ወይም ዝርፍያ ከተከሰሱ ደግሞ የዕድሜ ልክ እስራት ይጠብቃቸዋል ተብሏል። ይህ ጠለፋ ከ2017 በኋላ ማንኛውም የጭነት መርከብ በተሳካ ሁኔታ በሶማሊያ የባህር ወንበዴዎች ሲታገት የመጀመርያው ነውም የተባለ ሲሆን የህንድ ባህር ሀይል ቅዳሜ እለት 40 ደቂቃ በፈጀ ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን መርከባን ነፃ በማውጣት መርከባን በመጥለፍ ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ 35 የባህር ላይ ወምበዴዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ችሏል። በሚሊዮን ሙሴ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 21👎 2👏 1
ኢትዮጵያ ባለፏት ስድስት ወራት ከእንጆሪ ሽያጭ ከ3 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች ኢትዮጵያ ባለፏት ስድስት ወራት ለውጪ ገበያ ካቀረበችው የእንጆሪ ምርት ሽያጭ 3 ሚሊዮን 1 መቶ 91 ነጥብ 84 የአሜሪካን ዶላር ገቢ አግኝታለች ሲል የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል። በሚኒስቴሩ የግብርና ኢንቨስትመንት እና ምርት ግብይት መሪ ስራ አስፈጳሚ አቶ ደረጄ አበበ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የእንጆሪ ምርት በበርካታ የአለም ሀገራት ተፈላጊነቱ እየጨመረ መጥቷል። በበጀት አመቱ ስድስት ወራት  ለውጪ ገበያ ከቀረቡት የተለያዮ የፍራፍሬ አይነቶች መካከል  ትልቁን ገቢ በማስገኘት በኩል የእንጆሪ ምርት  ቀዳሚው ነው ሲሉ  ተናግረዋል።ባለፏት ስድስት ወራት ከፍራፍሬ  የውጪ ንግድ  7 ነጥብ 44  ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር  መገኘቱን መሪ ስራ አስፈጻሚው ገልፀው  የእንጆሪ ምርት ትልቁን ድርሻ ይይዛል ብለዋል። በዚህም በበጀት አመቱ ግማሽ አመት ወደ ውጪ ሀገራት ከተላኩት የፍራፍሬ ምርቶች ውስጥ ከእንጆሪ ምርት ብቻ  ከ3 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት ተችሏል ያሉት አቶ ደረጄ በዋናነት ምርቱ ወደ ተለያዮ የአውሮፓ፣  ፣ኤዥያ እና አፍሪካ ሀገራት መላኩን ተናግረዋል። የገበያ መዳረሻ ከሆኑት ሀገራት መካከልም ጀርመን፣ጋና፣ጋቦን ፣ሴራሊዮን፣ኢኳቶሪያል ጊኒ፣እንዲሁም ኔዘርላንድ ተጠቃሾች ናቸው ተብሏል።የሆለታ እንጆሪ ከሌሎች ሀገራት በጣእሙ ተወዳጅ በመሆኑ በተለይም  በአውሮፓና አሜሪካ ላይ ምርቱ ያለው ተፈላጊነት ከፍተኛ እንደሆነ ተጠቅሷል። ይህን ፍላጎት ተከትሎ ባለሀብቶች ሆለታ ላይ የእንጆሪ ምርትን እያመረቱ እንደሚገኙ የተናገሩት መሪ ስራ አስፈጳሚው  ይህም ምርቱን በብዛት አምርቶ ለገበያ ለማቅረብ አስተዋጵኦ አድርጓል ነው ያሉት ። ምርቱን በቀጥታ አምርተው ለገበያ የሚያቀርቡ በርካታ አምራችና ላኪዎች  በዘርፉ መሰማራታቸውን ገልፀዋል።ይሁን እንጂ ባለሀብቶቹ ምርቱን ከዚህ በበለጠ በተሻለ ለማምረትና ለውጪ ገበያ ለማቅረብ ፍላጎት ቢኖራቸውም  የማስፋፊያ ጥያቄ እንደሚያነሱ ተገልጻል። በዘርፏ የተሰማሩ አምራችና ላኪዎች ምርቱን በብዛት አቅርበው ለገበያ የሚያቀርቡበትን መንገዶች የማመቻቸት እና  ከማስፋፊያ ስራ ጋር ተያይዞ ለሚያነሱአቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት  ጥረት እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ ገልጻዋል። በቅድስት ደጀኔ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 20👎 11🔥 3 2😱 1
በጋዛ የሚፈጸመውን ጥቃት በመቃወም የረሃብ አድማ በማድረግ ላይ የነበረች ካናዳዊት ተማሪ ራሷን ሳተች ተማሪዋ የምትማርበት ማክጊል ዩኒቨርሲቲ ለእስራኤል የጦር መሳሪያ በሚያቀርቡ ኩባንያዎችን በመቃወም ለ34 ቀናት የረሃብ አድማ ካደረገች በኋላ ነው ራሷን የሳተችው፡፡ በሞንትሪያል በሚገኘው የማክጊል ዩኒቨርሲቲ የምትማረው ራኒያ አሚን ራሷን ከሳተች በኋላ አሁን በሆስፒታል ውስጥ  ክትትል ላይ እንደሆነች ሚድል ኢስት አይ ዘግቧል። አሚን፣ ማክጊል ዩኒቨርሲቲ ለእስራኤል የጦር መሳሪያ ከሚያቀርቡ ኩባንያዎች ራሱን እንዲያርቅ ግፊት ለማድረግ የረሃብ አድማ ከጀመሩ የተማሪዎች ቡድን አንዷ ናት። በረሃብ አድማው 17 የሚደርሱ ተማሪዎች እየተሳተፉ ነው። እርሷ ከሌሎቹ በተለየ የረሀብ አድማውን ጠንከር አድርጋ ስትገፋበት ቆይታለች፡፡የማክጊል ዩኒቨርስቲ ድረ-ገጽ እንደሚያሳየው ተቋሙ ሎክሂድ ማርቲን በተባለ የኤሮስፔስ እና የጦር መሳሪያ አምራች ላይ የአክስዮን ድርሻ አለው፡፡ ይህ ኩባንያ ለእስራኤል ተዋጊ ጄቶችን በማቅረብ ይታወቃል፡፡ ሌላኛው ዩኒቨርስቲው ገንዘቡን ያፈሰሰበት ድርክት ሳፋራን የተባለ የፈረንሳይ የጦር መሳሪያ አምራች ነው። ይህም ኩባንያ ለቴልአቪቭ መሳሪያ ከሚያቀርቡት መሀል ይገኝበታል፡፡ተማሪዎቹ እንደሚሉት ማክጊል ዩኒቨርሲቲ 20 ሚሊዮን ዶላር በጦር መሳሪያ አምራቾች እና ሌሎች ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ባላቸው ኩባንያዎች ላይ ፈሰስ አድርጓል። እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ መጠነ-ሰፊ የሆነ ጥቃትን ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ከ32,000 በላይ የጋዛ ነዋሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ በዓለም ዙሪያ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ተቃውሞዎች እየተካሄዱ ናቸው፡፡ አሚን "የማክጊል ዩኒቨርሲቲ ምንም አይነት አማራጭ አላስቀረንም፡፡ ምክንያቱም ሰላማዊ ተቃውሞዎችን፣  ችላ ተብሏል" ስትል ወድቃ ሆስፒታል ከመግባቷ በፊት ለዘ-ጋርዲያን ተናግራለች። “ማክጊል በመጨረሻ ይህንን ከባድ እርምጃ እንድንወስድ አድርጎናል፡፡ የመማሪያ ገንዘባችንን በዚህ መንገድ ኢንቨስት ለማድረግ መጠቀማቸው በፍጹም ተቀባይነት የለውም” ስትልም አክላለች። ባለፈው ህዳር የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች በጋራ ተፈራርመው ድርጊቱ እንዲቆም ቢጠይቁም፣ ማክጊል ግን ከኩባንያዎቹ ገንዘቡን ለማውጣት ፈቃደኛ አልሆነም። በሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 35😢 24 10💔 4👎 1
በቤንች ሸኮ ዞን በዝሆነ በሽታ ለተጠቁ ከ200 በላይ ሰዎች ህክምና መሰጠቱ ተገለፀ በቤንች ሸኮ ዞን በሼይቤንች ወረዳ በሁሉም ጤና ጣቢያዎች በዝሆነ በሽታ ለተጠቁት የህብረተሰብ ክፍሎች የህክምና አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል ። የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት በጽህፈት ቤቱ ስር በሚገኙ ስድስት ጤና ጣቢያዎች በዝሆነ በሽታ ለተጠቁ ሰዎች የህክምና አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ በወረዳው ጤና ጽህፈት ቤት የእናቶችና ህፃናት ቡድን መሪ አ/ቶ ሰለሞን ሀይለማሪያም ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ። ለተጠቃሚዎች የህክምና አገልግሎቱን ለመስጠት ከወረዳው የተውጣጡ የህክምና ባለሙያዎች ስልጠና መውሰዳቸው አንስተዋል ።  በዚህም መሠረት ህክምናው በተጠናከረ ሁኔታ ተሰጥቶ ከ200 በላይ ሰዎች አገልግሎት ማግኘታቸውን ገልፀዋል ። በቀጣይም የሚሰጠው ህክምና የሚቀጥል መሆኑና አገልሎቱ ለተሰጣቸው የሚደረገው ክትትል ቀጣይነትም ያለው ነው ብለዋል ። የተደረጉ ድጋፎች እንዳሉ የተገለፀ ሲሆን የዝሆነ በሽታ በስፋት በመኖሩ እንዲሁም በሽታው እግር ላይ የሚከሰት በመሆኑ በዚሁ በሽታ ለተጠቁ ሰዎች የሚሆን የጫማ ግባት ችግር እንዳለ ተጠቁሟል ። አያይዘውም በሽታው በቂ ትኩረት እንዳልተሰጠው ያነሱት አ/ቶ ሰለሞን በተለይም ተጠቂዎች ከፈጣሪ እንደሆነም የማሰብ ሁኔታም እንዳለ ተናግረዋል ። በአበረ ስሜነህ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 23😢 7
በፒያሳ እና አካባቢው በመንገድ ግንባታ ምክኒያት አማራጭ መንገዶችን ተጠቀሙ ተባለ በመንገድ ግንባታ ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጮችን  እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ከመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከ4 ኪሎ እስከ ፒያሳ ባለው መስመር የራስ መኮንን ድልድይ እየተሰራ በመሆኑ  የመንገድ ግንባታው እስከሚጠናቀቅ  የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር በተለይም በስራ መግቢያ እና መውጪያ ሰዓት አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጪ  መንገዶችን በመጠቀም ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ በዚህም መሰረት፡- • ከ4 ኪሎ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ • ከደጎል አደባባይ ትራፊክ መብራት ወደ 4 ኪሎ • ከቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ • ከደጃች ውቤ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ • ከአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ • ከባሻወልዴ ችሎት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ እና ከቀበና ወደ ፒያሳ የሚመጡ አሽከርካሪዎች መንገዱ ግንባታ ላይ መሆኑን ተገንዝበው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቋል፡፡ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 14👎 4 1
የሞስኮውን ጥቃት ተከትሎ የሩሲያ ፍርድ ቤት አራት ሰዎችን በሽብርተኝነት ከሰሰ ሩሲያ በሞስኮ የኮንሰርት አዳራሽ ላይ በተሰነዘረው ጥቃት ከ130 በላይ ሰዎችን እንዲገደሉ አድርገዋል የተባሉ አራት ሰዎች ላይ ነው ክስ የተመሰረተው። የእስላማዊ መንግስት ቡድን ወይም አይ ኤስ አርብ እለት የፈፀመውን ጥቃት ሙሉ ሀላፊነት የወሰደና ጥቃቱን የተመለከት ቪዲዮም በማህበራዊ መገናናኛ ዘዴዎች ለጥፏል። ምንም እንኳ በዚህ ጥቃት ላይ ዩክሬን መሳተፉ ክሚያሳዩ አሳማኝ ማስረጃዎች ባይገኙም የሩሲያ ባለስልጣናት ግን የዩክሬን ተሳትፎ ሊኖረው ይችላል እሚል ጥርጣሬ አሳድረዋል። አራቱ በሽብር የተከሰሱት ግለሰቦች ዳሌርዞን ሚርዞዬቭ፣ ሳይዳክራሚ ሙሮዳሊ፣ ሻምሲዲን ፋሪዱኒ እና መሀመድሶቢር ፋይዞቭ በመባል እሚታወቁ ሲሆን በተጋራው ቪዲዮው ለመመልከት እንደተቻለ ከሆነ ደግሞ ሦስቱ ተከሳሾች ጭንብል በለበሱ ፖሊሶች ታጅበው በሩሲያ ዋና ከተማ ወደሚገኘው የባስማንይ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲገቡ ታይተዋል። አራተኛው ተከሳሽ በቁጥጥር ስር ሲውል በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት በዊልቸር ነው ወደ ፍርደ አደራሹ የገባው። የፍርድ ሂደቱን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ በቴሌግራም ላይ ባወጣው መግለጫ ሚርዞዬቭ የታጂኪስታን ዜጋ እንደሆነና "ጥፋቱንም ሙሉ በሙሉ አምኗል" ብሏል።  ራቻባሊዞዳ እንዲሁ በተመሳሳይ“ጥፋተኛነቱን አምኗል” ብሏል። አራቱም ተከሳሾች የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ እስኪሰጣቸው ድረስ ቢያንስ እስከ ሜይ 22 ድረስ በእስር እንደሚቆዩ ፍርድ ቤቱ አክሎ ገልጿል። ሰዎቹ የተያዙት አርብ ምሽት አራት ታጣቂዎች በክራስኖጎርስክ ሰሜናዊ ሞስኮ አውራጃ በሚገኘው ክሮከስ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ ከገቡ እና በሮክ ኮንሰርት ላይ በተገኙ 6,000 የሚገመቱ ሰዎች ላይ መተኮስ ከጀመሩ ከሰዓታት በኋላ ነው። የሩሲያ ባለስልጣናት እንዳሉት 137 ሰዎች ሲገደሉ ከ100 በላይ ደግሞ ቆስለዋል። አይ ኤስ ጥቃቱን በሰአታት ውስጥ ሀላፊነት ወስዶ፣ በኮራሳን ውስጥ እስላማዊ መንግስት ተብሎ በሚጠራው ቅርንጫፍ ወይም በIS-K የተፈጸመ መሆኑን የገለፀ ሲሆን ቆየት ብሎም አጥቂዎቹ በኮንሰርት አዳራሽ ውስጥ በተሰበሰበው ህዝብ ላይ ሲተኩሱ የሚያሳይ ምስል አውጥቷል። ነገር ግን አንድም የሩስያ ባለስልጣን ጥቃቱ በአይኤስ ነው የተፈፀመው ብሎ አምኖ ያልተቀበለ ሲሆን፣ ይልቁንም አጥቂዎቹ በዩክሬን እሚረዱ መሆናቸውን እና ወደ ዩክሬን ድንበር ለማቋረጥ ሲዘጋጁ በብራያንስክ ክልል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቁመዋል። #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 28🤔 2
👍 3
በሐመር ወረዳ በአንድ ወር ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ አጋጥሟል ተባለ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በሐመር ወረዳ በዲመካ ከተማ ከትናንት በስቲያ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ከ 59 ደቂቃ ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ተሰምቷል ። ይህ ክስተት በአንድ ወር ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ ያጋጠመ መሆኑን የሐመር ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አ/ቶ አወቀ ንጋቱ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ። በተለይም የአሁኑ ክስተት ባለፈው ከተከሰተው ጋር ሲነፃፀር የንዝረት ደረጃው ከፍ ያለ ሲሆን የተወሰኑ ደቂቃዎች ልዩነት ቢኖረውም በተመሳሳይ ሰዓት የተከሰተ መሆኑን አንስተዋል ። በዚህ ክስት የተመዘገበውን የልኬት መጠን ማረጋገጥ የሚያስችል መሳሪያም ሆነ ባለሙያ በአካባቢው ባለመኖሩ የተነሳ ምን ያክል እንደተመዘገበ አይታወቅም ብለዋል ። በተጨማሪም በአሁኑም ሆኖ ባለፈው ጊዜ ባጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ በሰውና በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ተናግረዋል ። ነገር ግን ለአራተኛ ጊዜ ያጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ  ከፍተኛ ስለመሆኑ ከንዝረቱ መረዳት ይቻላል ሲሉ አክለዋል ። አ/ቶ አወቀ ክስተቱን ሲያስረዱም የቁሳቁስ መንቀሳቀስ ጭምር ማጋጠሙን በመግለፅ የቆይታ ጊዜው ግን ለሰከንዶች እንደሆነ ተናግረዋል ። በአበረ ስሜነህ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 10😱 5 4
የ 11፣ 12 እና የ 16 ዓመት ታዳጊዎች ባንክ መዝረፋቸው ተነገረ የ 11፣ 12 እና የ16 አመት እድሜ ያላቸው እና "ትንንሾቹ  ራስካሎች" በሚል በኤፍ ቢ አይ የቡድን ስያሜ የተሰጣቸዉ ሶስት ልጆች በሂዩስተን ባንክ ዘርፈዋል በሚል ልእስር ተዳርገዋል። አብዛኛዎቹ ልጆች የፀደይ እረፍታቸውን የቪዲዮ ጌሞችን በመጫወት፣ ቴሌቪዥን በመመልከት ወይም ከጓደኞቻቸው ጋር በመገናኘት ያሳልፋሉ ፣ ነገር ግን ሶስቱ  የሂዩስተን ታዳጊ ወጣቶች የእረፍት ጊዜያቸውን በዙርያቸው ያለውን አንድ ባንክ በመዝረፍ ለማሳለፍ ወስነዋል ተብሏል። ፖሊስ እንዳስታወቀው ሦስቱ ህጻናት ወንዶች መጋቢት 14 ቀን በሰሜን ሂዩስተን ግሪንስፖይንት አካባቢ ወደሚገኝ ዌልስ ፋርጎ ባንክ ገብተው ለባንኩ ሰራተኛ የማስፈራሪያ የያዘ ወረቀት በመስጠት  መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብ በመቀበል የተሳካ ዘረፋ ፈፅመው ለማምለጥ  ችለዋል መባሉን ዳጉ ጆርናል ከዘገባዎች ተመልክቷል። ፖሊሶች መጥተው የድህንነት ካሜራዎቹ የያዙትን ምስል በሚፈትሹበት ሰዓት ደግሞ የባንክ ዘራፊዎቹ በማይታመን ሁኔታ ታዳጊዎች ሆነው በማየታቸው መደንገጣቸውን ገልፀዋል። ህጻናቱ  ፍርድ ቤት የቀረቡት ሲሆን ዳኛው ማይክ ሽናይደር " የዘራፊዎቹ እድሜ በጣም ዝቅተኛ  ነው ይህ ደግሞ ለባንኮ ዘረፋ እጅግ ያልተለመደና በህይወት ዘመኔ ከተመለከትኳቸው በዕድሜ ትንሾቹ የዘረፋ ወንጀል ፈፃሚዎችም ናቸው " ይላሉ። ቀጠል አድርገውም ታዳጊዎቹ በራሳቸው ይህንን ፈፅመዋል ብዬ ለማመን  እቸገራለው ምናልባትም ያሰማራቸው አንድ አዋቂ ሰው ሊኖር ይችላልም ባይ ናቸው። ታድያ ፖሊስ በዚህ ዝረፍያ ውስጥ ሌላ ሰው መሳተፉን እሚያሳይ መረጃ እስካሁን ይፋ አላደረገም። ሶስቱን ታዳጊዎች ግን በዘረፋ ወንጀል ተከሰወ በቁጥጥር ስር ውለዋል። የተከሳሾቹ ተከላካይ  ጠበቃ እንደተናገሩት ከሆነ ደግሞ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ 18 ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ የሙከራ ጊዜ ወይም 19 ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ ለአካለ መጠን ላልደረሱ ሰዎች በተዘጋጁ ማረሚያ ቤቶች ሊቆዩ ይችላሉ ብለዋል። እንደ ሃሪስ ካውንቲ የሸሪፍ ፅህፈት ቤት መረጃ ደግሞ ምንም እንኳን እድሜያቸው 11፣ 12 እና 16 የሆኑት ሦስቱ የታዳጊ ባንክ ዘራፊዎች መሳርያ ይዘው በግልፅ ያልታዩ ቢሆንም ፖሊስ ግን የታጠቁ እንደነበሩ ነው አስታዉቋል። ኤፍቢአይ ከባንኩን ካሜራዎች ባገኘዌ ምስዕል ታዳጊዎቹ የሰሩትና  አስገራሚ ነገር ከተመለከተ በኃላ ባወጣው የአፋልጉኝ ማስታወቅያም ብታምኑም ባታምኑም እነዚህ ሶስት ታዳጊዎች ባንክ ቤት ዘርፈዋል ብሏል፡፡ ኤፍቢአይ  አክሎም ምታውቋቸው ካለቹ አፋልጉኝ በማለት ያስነገረ ሲሆን የሶስቱ ታዳጊዎች ፎቶ ከተለቀቀ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የሁለቱ ታናናሽ ልጆች ወላጆች ወደ ፊት ቀርበው ልጆቻቸውን አስረክበዋል ተብሏል። ሶስተኛው የ16 ዓመቱ ታዳጊ ደግሞ በፖሊስ እየተፈለገ ሳለ ሌላ ግጭት ላይ ተሳትፎ በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉ ታዉቋል። በሚሊዮን ሙሴ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
😁 52👍 33👏 3🤯 2😱 1
👍 6
በጅግጅጋ ከተማ ታይዋን የገበያ ማዕከል በእሳት አደጋ ንብብታቸዉን ላጡ ግለሰቦች መልሶ ማቋቋሚያ የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ለሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ታይዋን የገበያ ማዕከል ተጎጂዎች ለመልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል። ድጋፉን የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ እና የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ለሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ አስረክበዋል። የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ከተማ ታይዋን የገበያ ማዕከል ተጎጂዎች መልሶ ለማቋቋም የሚደረገዉን ጥረት ለማገዝ እያንዳንዳቸዉ የ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ተጠቅሷል። በገቢዎች ሚኒስቴር እና በጉምሩክ ኮሚሽን አዘጋጅነት በሶማሌ ክልል የአፍጥር ፕሮግራም መካሄዱንም የሶማሊያ ክልል መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 19😁 2