cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 https://t.me/AiqemAdsMasterBot 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Show more
Advertising posts
32 557Subscribers
+3524 hours
+1887 days
+58930 days
Posts Archive
ከእህቱ ሞት ጋር በተያያዘ በመንፈስ ተወግታ ነው በሚል ወሬ ተነሳስቶ የግድያ ወንጀል የፈፀመዉ ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ በኢሊባቡር ዞን በያዮ ወረዳ አጨቦ ቀበሌ ልዩ ቦታው ብርቂቱ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከእህቱ ሞት ጋር በተያያዘ በመንፈስ ተወግታ ነው በሚል ወሬ ተነሳስቶ አንድ ግለሰብን የገደለ ተከሳሽ በእስራት ተቀጥቷል ። የ29 ዓመት እድሜ ያለው ምትኩ በቀለ የተባለ ግለሰብ ኑሮው ከቤተሰቦቹ ጋር አድርጎ ነበር ። ታላቅ እህቱ በተደጋጋሚ በመታመሟ የተነሳ የአዕምሮ መታወክ ይገጥማታል ። ሆኖም ከገጠማት የአዕምሮ መታወክ በህክምና ስትረዳ ከቆየች በኋላ በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ትለያለች ። ሞቷ በቤተሰቦቿ ላይ ከፍተኛ ሀዘን ያስከተለ ከመኖኑ ባሻገር ከአማሟቷ ጋር በተያያዘ የሚወራው ወሬ መላ ቤተሰቡን ያስከፋ ሲሆን በተለይም ደግሞ ምትኩን አስደንግጧል ። ወሬውም ሟች ህይወቷ ያለፈው በአካባቢው በምትገኝ ጫልቱ ተረፈ በተባለች ግለሰብ መንፈስ ተወግታ ነው ይባላል ። ይህ ወሬ በመጨረሻም የምትኩን ልብ ለበቀል ያነሳሳል ። ጫልቱ በበኩሏ የሚወራው ችላ በማለት የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴዋን ትቀጥላለች ። በዚህም ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም  ዓመታዊውን የመድኃኒዓለም ክብረ በዓል አክብራ ስትመለስ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ምትኩ በቀለ በመንገድ ጠብቆ በገጀራ ጭንቅላቷ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የኢሉባቡር ዞን ፖሊስ ኮሚኒኬሽን ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ገልጿል ። በወቅቱ ተጎጅዋን በመረባረብ ወደ መቱ ካርል ሪፈራል ሆስፒታል ተወስዳ እርዳታ ቢደረግላትም ህይወቷ መትረፍ ሳይችል ይቀራል ። ፖሊስ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ የምርመራ መዝገቡን አጣርቶ ለዓቃቤ ህግ ይልካል ። ዓቃቤ ህግ በደረሰው ማስረጃ ተመስርቶ በኢሊባቡር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ይመሰርታል ። ፍርድ  ቤቱ ዓቃቤ ህግ የመሠረተውን ክስ ሲመለከት ቆይቶ ተከሳሽ ምትኩ በቀለን ጥፋተኛ በማለት በ11 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል ። በአበረ ስሜነህ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
የቻይናው ግዙፍ የስማርትፎን ኩባንያ ዢኦሚ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለገበያ ማቅረብ ሊጀምር ነው የቻይናው የስማርት ስልክ አምራች ዢኦሚ የመጀመሪያውን የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ (ኢቪ) ለገበያ ለማቅረብ የተዘጋጀ ሲሆን ሀሙስ እለት ትእዛዝ መቀበል ጀምሯል። ዋና ስራ አስፈፃሚው ሌይ ጁን በዚህ ሳምንት እንደተናገሩት ስፒድ አልትራ 7 (SU7) ከ500,000 ዩዋን ወይም በ69 ሺ186 የአሜሪካን ዶላር ዋጋ እንደሚሸጥ ተናግረዋል። እርምጃው የቴክኖሎጂ ግዙፉ እንደ ቴስላ እና ቢዋይዲ ካሉ ተቀናቃኞቹ ጋር ያለውን ፉክክር ያጠናክራል። የዢኦሚ ወደ ኤሌክትሪክ መኪና ገበያ መግባቱ በአለም አቀፍ ደረጃ የሽያጭ እድገት በመቀነሱ የዋጋ ጦርነትን አስነስቷል። ኩባንያው የ SU7 የጋራ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከስልኮች፣ ላፕቶፖች እና ሌሎች ምርቶቹ ተጠቃሚ ከሆነ ነባር ደንበኞችን ይስባልኛል ሲል ተስፋ አድርጓል። ዢኦሚ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሶስተኛ ስፍራ ላይ የተቀመጠ የስማርት ስልኮች አቅራቢ ሲሆን 12 በመቶው የገበያ ድርሻ እንዳለው ካውንተር ፖይንት የተባለው የምርምር ድርጅት ገልጿል። ዢኦሚ ካለፈው አመት ጀምሮ ፍተሻ ሲያደርግበት የነበረው SU7 ከፖርሽ ታይካን እና ፓናሜራ የስፖርት መኪና ሞዴሎች ጋር ንፅፅር ተደርጎበታል። በዓመት እስከ 200 ሺ የሚደርሱ ተሽከርካሪዎችን ማምረት በሚችል በቤጂንግ በሚገኝ ፋብሪካ በመንግስት ባለቤትነት በተያዘው የመኪና አምራች ዩኒት ይሠራል። እስከዚህ ድረስ መድረስ በራሱ ትልቅ ስኬት ቢሆንም የመጨረሻው ስኬት ዢኦሚ የሸማቾች ገበያ ላይ ተፈላጊነቱን ማሳየት ነው ሲሉ ኩባንያው አስታውቋል። የኤሌክትሪክ መኪና ለመሥራት የሚፈልጉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎች ለማመልከት የአይፎን አምራች አፕል ባለፈው ወር ተሽከርካሪዎችን የመሥራት ዕቅዱን መሰረዙ ይታወሳል። ዢኦሚ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ በተሽከርካሪ ንግዱ 10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት አደርጋለሁ ብሏል። በቢሊየነሩ ኤሎን ማስክ የሚመራው ቴስላ በቅርብ ወራት ውስጥ በቻይና ያለውን ድርሻ በሀገር ውስጥ ተቀናቃኝ በሆነው ቢዋይዲ ተነጥቋል።የዋጋ ቅናሽ በማድረጉ ቴስላ ፉክክሩን መቋቋም አልቻለም። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
8👍 5
አል አይን አማርኛ በአፍሪካ ስለሚገኙ አየር መንገዶች እና አውሮፕላኖች ቁጥር ያቀረበው አሳሳች መረጃ.... አል አይን አማርኛ በትናንትናው እለት 'በርካታ አውሮፕላኖች ያሏቸውን ሀገራት ዝርዝር' በማለት አንድ መረጃ አጋርቶ ነበር፣ ለዚህም የፕሌን ስፖተርስ ድረ-ገጽ መረጃን መሰረት አድርጓል። በዚህ መረጃ መሰረት ደቡብ አፍሪካ በ195 አውሮፕላኖች አንደኛ፣ ኬንያ በ177 አውሮፕላኖች ሁለተኛ፣ ግብፅ በ166 አውሮፕላኖች ሶስተኛ፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ በ142 አውሮፕላኖች አራተኛ ደረጃን እንደያዙ ዘገባው ይጠቁማል (ስክሪን ቅጂው ተያይዟል)። ይህ የአል አልይን ዘገባ በመግቢያው በአፍሪካ ስለሚገኙ አየር መንገዶች ሀተታ ስላቀረበ ያቀረበው ቁጥርም ስለነዚህ አየር መንገዶች እንደሆነ ያመላክታል። ይሁንና በአቪዬሽን ዘርፍ በሚሰራቸው ዘገባዎች የሚታወቀው ሲምፕል ፍላይንግ (Simple Flying) የዛሬ ሁለት ወር ገደማ ባወጣው ሪፖርት በአፍሪካ ከሚገኙ አየር መንገዶች የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ133 አውሮፕላኖች ቀዳሚው፣ የግብፅ አየር መንገድ በ82 አውሮፕላኖች ሁለተኛ፣ የአልጄርያ አየር መንገድ በ55 አውሮፕላኖች ሶስተኛ፣ የሞሮኮ አየር መንገድ በ51 አውሮፕላኖች አራተኛ እንዲሁም የኬንያ አየር መንገድ በ32 አውሮፕላኖች አምስተኛ እንደሆነ ዘግቧል (https://simpleflying.com/largest-airlines-africa/) ይህን የሚያረጋግጠው ሌላው መረጃ ለምሳሌ የግብፅ አየር መንገድ በራሱ ድረ-ገፅ የአውሮፕላኖቹ ቁጥር 80 ገደማ እንደሆነ አስቀምጧል። በኪሳራ ላይ የሚገኘው የደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ ደግሞ አሁን ላይ ያሉት አውሮፕላኖች 13 ብቻ እንደሆኑ በድረ-ገፁ ላይ ይታያል። የአል አይን ዘገባ በአጠቃላይ በተጠቀሱት ሀገራት ውስጥ ስለሚገኙ አውሮፕላኖች ቢሆን ምናልባት ትክክል ሊሆን እንደሚችል የጠቆሙን አንድ የአቪዬሽን ባለሙያ፣ እንደ ኢትዮጵያ አንድ ግዙፍ አየር መንገድ እና ጥቂት የግል የቻርተር በረራ የሚሰጡ ድርጅቶች ሳይሆኑ በርካታ የግል አየር መንገዶች እና የግል አውሮፕላኖች ያሉባቸው ሀገራት እንዳሉ ጠቁመዋል። ስለዚህ ብዙ አውሮፕላኖች ያሏቸው ሳይሆን ያሉባቸው ሀገራት ተብሎ መቅረብ እንደነበረበት ባለሙያው አስረድተዋል። ይሁንና የዜናው ቅኝት በአየር መንገዶች ዙርያ ስለሆነ መረጃውን አሳሳች ያደርገዋል። Via Ethiopia Check #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 9
ተቀጥሮ በሚሰራበት ቤት ዉስጥ በእንቅልፍ ላይ  የነበረችን የ6 ዓመት ህፃን ለመድፈር ሙከራ ያደረገው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ  በ6 ዓመት ህፃን ላይ የመድፈር ሙከራ አድርጓል የተባለ  ተከሳሽ  በ15  ዓመት ፅኑ እስራት  እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑ   የወረዳዉ ፖሊስ ገልጿል። በሶዶ ወረዳ ጢያ 01 ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ ተመስገን ከበደ በእስራት ሊቀጣ የቻለዉ ጥር 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከለሊቱ 6:00 ሰዓት ላይ ወንጀሉን የፈጸመው። የክልሉ ፖሊስ የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ተቀጥሮ በሚሰራበት  ቤት ዉስጥ በእንቅልፍ ላይ  የነበረችን  የ6 ዓመት ህፃን ለመድፈር በሙከራ ሲያደርግ  የታዳጊዋ እናት ድንገት ደርሳ  እጅ ከፍንጅ መያዙን ገልጿል። የሶዶ ወረዳ ፖሊስ በተከሳሹ ላይ ያጣራዉን የምርመራ መዝገብ  ተቀብሎ ዐቃቤህግ የመሰረተዉ ክስ የተመለከተዉ የወረዳዉ ፍርድቤት ተከሳሹ  ወንጀሉን መፈፀሙን በቀረበለት የሰዉና የሰነድ ማስረጃ  በማረጋገጡ ተከሳሹን ጥፋተኛ ሲል ብይን ሰጥቷል። የሶዶ ወረዳ ፍርድ ቤት መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎች ተከሳሽ በ15 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን  ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ጨምረው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 26🤬 7👎 3
የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት “ዲሞግራፊ ለመቀየር” የሚካሄድ አይደለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተባበሉ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የመንገድ እና አካባቢ ልማት ፕሮጀክት፤ “ዲሞግራፊ ለመቀየር” አሊያም “ኦሮሞዎችን ወደ ከተማ ለመመለስ ነው” የሚሉ ወገኖችን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተቹ። አዲስ አበባ ውስጥ “ከበቂ በላይ” የኦሮሞ እና የሌሎች ብሔር ተወላጆች መኖራቸውን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “የሌለ ሰው ኖሮ፤ ሰው ለማምጣት የምንቸገርበት አይደለም” ሲሉም አስተባብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህን ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራን ከሚያስፈጽሙ አመራሮች እና የስራ ኃላፊዎች ጋር ትላንት ረቡዕ መጋቢት 18፤ 2016 ባደረጉት ውይይት ነው። እርሳቸው የሚመሩት መንግስት ከዚህ ቀደም ባከናወናቸው የግንባታ ስራዎች “ብዙ ስሞታዎች ነበሩ” ያሉት አብይ፤ ለዚህም የምኒልክ ቤተ መንግስት እና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እድሳትን በምሳሌነት አንስተዋል። “ይሄ ግቢ ሲቀየር ሀገራዊ ፖለቲካ ነበር። የእዚህን ግቢ እድሳትን እና ዩኒቲ ፓርክን ለመቃወም ሰዎች በጣም ብዙ ደክመዋል። በኋላ [የአዲስ አበባ ከተማ] ማዘጋጃ ቤት ሲጠናቀቅ፤ ‘ለምን ተሰራ’ ተብሎ ብዙ ተብሏል። አሁንም ብዙ አሉባልታዎች፤ ብዙ ወሬዎች ይሰማሉ። ‘ዲሞግራፊ ለመቀየር ነው’፤ ‘ኦሮሞዎች ለመመለስ ነው’ [የሚሉ] የተለያዩ ስሞች ይሰጣሉ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። Via Ethiopia Insider #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👎 21👍 14 2😁 1
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በተወሰኑ የክልሉ አካባቢዎች ላይ ትንኮሳ መጀመሩን አስታወቀ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ከሰሞኑ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ ምላሽ ሰጥቷል። ሙሉ መግለጫዉ እንደሚከተለው ቀርቧል... የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም የአማራ ክልል ተማሪዎች መማሪያ መጻህፍትን እንደሰበብ ተመርኩዞ ያወጣውን የዛቻ እና የጠብ አጫሪነት መግለጫ ተመልክተናል፡፡ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የአማራ ክልል የትምህርት ሥርዓትን በማጣቀስ የተሳሳተ ካርታ ተሰርቷል ሲል ያወጣው መግለጫ በተሳሳተ ካርታ ወደ አማራ ክልል ተካተዋል ያላቸውን አካባቢ ሕዝቦች ታሪካዊ እውነታን፣ ተጨባጭ ማስረጃዎችን እና ነባራዊ ሐቅን የካደ፣ አሳሳች እና የጠብ አጫሪነት ፍላጎትን የተሸከመ መግለጫ በመሆኑ እና በትናንትናው እለት ማለትም መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ደግሞ ከነበረበት አካባቢ በመንቀሳቀስ የራያ አላማጣ ወረዳ ቀበሌዎችን በመያዝ ነዋሪዎችን በመግደል እና በማሰቃየት ላይ ይገኛል፡፡ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የአማራ ክልል የተማሪዎች የመማሪያ መጻሕፍ ውስጥ የተሳሳተ ካርታ ተሰርቷል ሲል ባወጣው መግለጫ ሊያመላክታቸው የተፈለጉት አካባቢዎች ካለፉት 30 ዓመታት በፊት ጀምሮ የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያሉባቸው ወረዳዎች የማንነት እና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎችን ሲያቀርቡባቸው በነበሩ ቦታዎች ላይ መኾኑ ግልጽ ነው፡፡ አሁን በሥራ ላይ የሚገኘው የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በተስተዋሉት የአስተዳደራዊ መዋቅሮች እና አደረጃጀት ቅመራ ጅማሬ አንስቶ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ አሰቃቂ ጥቃት በመፈጸሙ ምክንያት ጦርነት እስከተቀሰቀሰበት ግዜ ድረስ የወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች በወቅቱ ለነበረው መንግስት የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎችን በማንሳት መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ የነበሩ መሆኑን በበርካታ ታሪካዊ ሁነቶችና ተጨባጭ ማስረጃዎች የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ የነበሩ ሕዝቦች እና አካባቢዎችን ለበርካታ ዘመናት በኃይል ሲገዛ የነበው የቀድሞው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ላነሱት ታሪካዊና ሕጋዊ ጥያቄዎች ሕጋዊ አሰራርን የተከተለ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ የአካባበው ተወላጆችን፣ የሀገር ሽማግሌዎችን፣ የማንነትና የአስተዳደር ጥያቄ አስተባባሪዎችን በማሰር፣ በማሰደድ እና በመግደል የሕዝቡ ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ እስከ ሰሜኑ የህግ ማስከበር ጊዜ ድረስ እንዲገፋ አድርጎታል ማለቱን ዳጉ ጆርናል ከመግለጫው ተመልክቷል፡፡ የማንነት እና የአስተዳደር መብት ዙሪያ ላነሳቸው ጥቄዎች የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ትግል በተፋፋመበትና ከፍተኛ መስዋዕትነት ጭምር እየከፈለ በሚገኝበት ወቅት ህወሓት የሠሜን ዕዝ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን አሰቃቂ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሁሉንም ኢትዮጵያዊያንን በማቀናጀት ለሁለት ዓመታት የቆየ የሕግ ማስከበር እርምጃ ለመውሰድ የተገደደበት ሁኔታ መፈጠሩ ይታወሳል፡፡ የማንነትና የአስተዳደር ጥያቄዎቹ ለዘመናት የታፈኑበት ሕዝብም ከማዕከላዊው መንግስት ጎን ተሰልፎ በህ.ወ.ሓ.ት የክህደት ተግባር በኢትዮጵያ ሕልውና እና ሉአላዊነትት ላይ የተጋረጠውን ግልጽ አደጋ እንዲቀለበስ የበኩሉን አስተዋጽዖ ከማበርከቱ ባሻገር በሂደቱ ህወሓት በኃይል ተገፍፎባቸው የነበረውን የማንነትና ጥያቄና ራስን በራስ የማስተዳደር ነጻነት የተቀዳጁበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በዚህም ምክንያት የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ህዝብ እንደማንኛውም የሀገሪቱ ሕዝብ ሁሉ የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚነት መብቱ ሊቀለበስ የማይችል በመሆኑ በቀድሞው የህ.ወ.ኃ.ት እና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት መካከል የፕሪቶሪያው ስምምነት ከመፈረሙ በፊት ጀምሮ የአማራ ክልል እንደሌሎቹ ዞኖችና የልማት ትሩፋቶች ሁሉ የአካባቢው ሕዝብም በትምህርቱም መስክ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ አካባቢዎቹን በተመለከተ የነበረው፣ ያለው እና የሚኖረው እውነታ ይሄ ሆኖ ሳለ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም ከፕሪቶሪያው ስምምነት ከመፈረሙ በፊት በስራ ላይ የዋሉ የአማራ ክልል ተማሪዎች እንደሌሎቹ አካባቢዎች የነዚህ አካባቢ ህፃናትም የመማራ መብታቸው እንዲከበር የአማራ ክልል መንግስት ግዴታውን መወጣቱን ሰበብ በማድረግ በአማራ ክልል ላይ ጥቃት ከመፈጸም የማይመለስ መሆኑን የሚገልጽ የጠብ አጫሪ መግለጫ ማውጣቱ ካለፉት ድርብርብ ውድቀቶች ትምህርት አለመውሰድን ከማሳየት የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም፡፡ የተፈጠሩ ችግሮችን በህግ አግባብ እንዲፈታ እተደረገ ያለውን ጥረት የአማራ ክልል መንግስት የራሱን ድርሻ እየተወጣ ባለበት ሁኔታ በህዝብ መጎሳቆልና በወጣቶች እልቂት ትምህርት አለመወሰዱና የተለመደ ትንኮሳ በማድረግ ላይ መሆኑ እጅጉን አሳዝኖናል፡፡ ስለሆነም የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ለሀገሪቱ ቋሚ ቀውስ ምንጭ ከሚያደርጉት ተግባራት እንዲታቀብ፣ ሀገራችንንና ሁለቱን ክልሎች ወደ ቀውስ ከሚያስገቡ ተግባራት በመቆጠብ ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣና የህዝብን ፍላጎት ማዕከል ባደረጉ ውይይቶች ላይ እንዲያተኩር እንዲሁም አንድ ሀገር ለመገንባት ለሚፈለገው ዘላቂ ሠላም እና ለሕዝቦች አንድነት መጽናት በሚበጅ ሐሳብና ተግባር ላይ እንዲያተኩር እንመክራለን ሲል መግለጫውን አጠናቅቋል፡፡ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 17😁 6 2🕊 2🔥 1😢 1
የኮንዶሚኒየም ቤት ጠባቂዎች ላልተፈለገ እንግልት እንዳትዳረጉ ተብላችኋል ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ በተለይም በቲክቶክ በተለቀቀ የተሳሳተ መረጃ የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝግባችሁ እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ ብቁ መሆን አለመሆናችሁን ባምቢስ በሚገኘው የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ 5ኛ ፎቅ መታችሁ እንድታዩ በሚል የተለቀቀው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ዳጉ ጆርናል ከአዲስአበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ሰምቷል። በዛሬዉ እለትም ይህን መረጃ የሰሙ በርካታ ሰዎች ወደ ባንቢስ አቅንተዉ ወረፋ መያዛቸዉን ዳጉ ሰምቷል። የአዲስአበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ፤ ተመዝግባችሁ እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ ሰዎች ላተፈለገ እንግልት እንዳትዳረጉ ሲል አሳስቧል፡፡ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ እና ኮርፖሬሽኑ ነዋሪውን በተለይም ተመዝግቦ የሚጠባበቀውን የቤት ባለቤት ለማድረግ የተለያዩ የቤት ልማት አማራጮችን ተግባራዊ በማድረግ ከምንጊዜውም  በተሻለ መልኩ እየሰሩ እንደሚገኝ የገለጸም ሲሆን ተመዝጋቢዎችም ሆነ ሌሎች ነዋሪዎች የተቋሙ ባልሆኑ ማህበራዊ ሚዲያዎችም ሆነ ግለሰቦች በሚያናፍሱት ወሬ እንዳትታለሉ አስገንዝቧል ። #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 12😁 1🙏 1
ሜልኮን የተባለ የግል ድርጅት እያስገነባ ባለዉ ህንፃ ሰራተኞች አርማታ እየሞሉ ተደርምሶ ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰባቸው ትላት በደረሱ ሁለት የእሳት አደጋዎችም የአንድ ትምህርት ቤት ስድስት ክፍሎች እና አንድ ፕላስቲክ ጫማ ፋብሪካ ተቃጥለዋል፡፡ በአዲስ አበባ ትላንት መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 5:55 ሰዓት ቦሌ ክፍለ -ከተማ ወረዳ 3 ቲኬ ህንፃ አካባቢ ሜልኮን የተባለ የግል ድርጅት እያስገነባ ባለዉ ህንፃ ሰራተኞች አርማታ እየሞሉ በነበረበት ሰዓት አንዱ ወለል ተደርምሶ ከተደረመሰዉ ወለል ስር የነበሩ ሁለት ሠራተኞች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን አስታውቋል። የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናሩት ከተደረመሰዉ ወለል ስር የነበሩትን ሁለቱን ሰዎች የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ፈጥነዉ በመድረስ ህይወታቸዉን መታደግ ችለዋል። ጉዳት የደረሰባቸዉን ሰዎች በኮሚሽኑ  አምቡላንስ ወደጤና ተቋም ተወሰደዉ ህክምና እየተደረገላቸዉ ይገኛል። በአዲስ አበባ መሰል የስራ አደጋዎችን ለመከላከል አሰሪዎችና የዘርፉ ባለሞያዎች የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ጠብቀዉ እንዲሰሩ ኮሚሽኑ አሳስባል በሌላ በኩልም ትላንት በአዲስ አበባ ሁለት የእሳት አደጋዎች ደርሰዋል፡፡ የመጀመሪየ አደጋ  ከምሽቱ 1:38 ላይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ጃፓን ኢንባሲ አካባቢ ማርች 8 በሚባል አፀደ ህፃናት ትምህርት ቤት ላይ የተነሳ የእሳት አደጋ ሲሆን በእሳት አደጋው ስድስት ክፍሎች ጉዳት ደርሳል፡፡ እሳቱ ተዛምቶ በትምህርት ቤቱ ላይ ከዚህ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ  መቆጣጠር መቻን አቶ ንጋ ጨምረው ነግረውናል፡፡በአደጋዉ  በአንድ የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል። እንደዚሁም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ -ከተማ ወረዳ አምስት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጀርባ በአንድ ፕላስቲክ ጫማ ማምረቻ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። የእሳት አደጋዉ ተስፋፍቶ በፋብሪካዉ ላይ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 11🥰 2🤔 2
ክሊክ አጥማጆች (clickbaits) ስራቸዉ ምንድን ነዉ ? የፖለቲካ አለመረጋጋት ወይንም ግጭት ሲኖር በየሰዐቱ የሚፈጠሩ ክስተቶችን ለማወቅ ጉጉታቸን ይጨምራል። የማወቅ ጉጉታችንን ለማርካት መረጃ ልናገኝባቸው እንችላለን ያልናቸውን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ወይንም ቻናሎች አልያም ሚዲያዎች ማሰሳችን ይጠበቃል። በአሰሳችን ወቅት ለክሊክ አጥማጆች (clickbaits) የመጋለጥ እድልም ይኖረናል። የክሊክ አጥማጆች ለስሜታችን የቀረበ፣ ጉጉት የሚያጭር፣ “አትለፉኝ አትለፉኝ” የሚል የዜና ርዕስ (headline) እና በደንብ የተቀናበረ ፎቶ በመጠቀም ማስፈንጠሪያዎችን እንድንከተል ወይንም ቪዲዮዎችን እንድንከፍት የሚገፋፉ ገጾችና ቻናሎች ሲሆኑ ወደ ውስጥ ገብተን ይዘታቸውን ስንመለከት ከዜና ርዕሳቸው ጋር የማይገናኝ፣ ምንጭ የሌለው፣ ከዚህም ከዚያም የተቃረመ ሆኖ እናገኘዋለን። ክሊክ አጥማጆች በኢትዮዮጵያ በተለይ በዩትዩብ በርከት ብለው የሚገኙ ሲሆን አብዛኞቹ አላማቸው ብዙ ሰብስክራይበርና ተመልካች በማግኘት ብር ማግኘት ሲሆን ሌሎቹ የፖለቲካ አላማቸውን ለማሳካት ይጠቀሙበታል። ክሊክ አጥማጆች በአብዛኛው ይዘታቸው ምንጭ የማይጠቅስ፣ የተጋነነ፣ ርዕታዊነት የጎደለውና ወገንተኛ ሆኖ ይገገኛል። በዚህም ለሀሠተኛና የተዛቡ መረጃው ስርጭት ከፍተኛ ድርሻ ይወስዳሉ። ስለሆነም በክሊክ አጥማጅ የዩቲዩብ ቻናሎች ወይንም ድረ-ገጾች የሚቀርቡ መረጃዎችን ከማመናችን እና ከማጋራታችን በፊት ቆም ብሎ ማሰብ እና የሚከተሉትን ጥያቄዎች መጠየቅ በሀሰተኛና የተዛባ መረጃ ከመጋለጥ ይታደጋል: * የመረጃ አቅራቢው ሚዲያ ወይንም ግለሰብ ማንነት ይታወቃል? * መረጃ አቅራቢው ለድርጊቱ ወይንም ድርጊቱ ለተፈጸመበት አካባቢ ምን ያህል ቅርብ ነው? * መረጃ አቅራቢው ታማኝ ምንጭ ጠቅሷል? * መረጃውን በአንጻራዊነት ታማኝ የሆኑ የሚዲያ ተቋማት ዘግበውታል? * መረጃ አቅራቢው መረጃውን በፎቶ ወይንም በቪዲዮ አስደግፏል? * ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ትክክለኛ እና እውነተኛ ናቸው? የሚሉ ጉዳዮችን በትኩረት መመልከት ይፈልጋል። Via Ethiopia Check #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 16
በአዲስ አበባ ከተማ የደንበኞችን እንግልት ለመቀነስ  ምስልን እና ንግግርን የሚቆጣጠር ካሜራ በሁሉም ወረዳዎች እና ክፍለ ከተሞች ተግባራዊ ሊሆን ነዉ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር በወረዳዎች እና በክፍለ ከተማ ደረጃ እየተስተዋለ ያለውን የደንበኛ መጉላላት እንዲሁም ስልጣንን በመጠቀም ያልተገባ ተግባር የሚፈጽሙ ሰራተኞችን ለመቆጣጠር በ11 ክፍለ ከተማዎችና 119 ወረዳዎች የካሜራ ቁጥጥር ስራ መጀመሩን የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና  የነዋሪነት  አገልግሎት ኤጀንሲ  አስታዉቋል፡፡ በቀጣይ  ከካሜራ በተጨማሪ  የቃላት ንግግራቸውንም ለመስማት የሚያስችል አሰራር እንደሚገባ ይህም ምንም አይነት ያልተገባ እና ስነምግባር የጎደለው አሰራር እንዳይፈጠር የሚያደርግ መሆኑንም አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪም ለዓቅመ ደካማዎች የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት  መስጠት ሊጀምር መሆኑን ኤጀንሲዉ ገልጿል። ጊዜው ያለፈበት  ወይም የአገልግሎት ጊዜው ሊያበቃ  ቀኑ የተቃረበ  የወረቀት መታወቂያ አቅመ ደካማ የሆኑ ነዋሪዎችን  ቤት ለቤት በመሄድ አሻራ እና የሚያስፈልገውን  መስፈርት በማሟላት  አገልግሎት መስጥት እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ሰርቪስ ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 45👏 2😱 2😁 1
ባይደንን የእስራኤልን ጠላቶችን በዘዴ ይደግፋሉ ሲሉ የእስራኤል ቀኝ ዘመም ኃይሎች ከሰሱ የእስራኤል ብሄራዊ ደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን ጊቪር በጋዛ የሃማስ መሪ ያህያ ሲንዋር እና የዴሞክራቲክ ኮንግረስ አባል ራሺዳ ትላይብን ​​ጨምሮ ፕሬዝዳንት ባይደንን "የእስራኤል ጠላቶች በዘዴ ይደግፋሉ" ሲሉ ክስ ሰንዝረዋል በማለት ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል። "በአሁኑ ጊዜ ባይደን ከቤንጃሚን ኔታንያሁ እና ከቤን-ጊቪር መስመር ይልቅ የራሺዳ ተላይብ እና የሲንዋርን መስመር ይመርጣል" ሲሉ እነዚሁ የእስራኤል የቀኝ ዘመም ኃይሎች ተናግረዋል። "የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የእነሱን መስመር አይከተሉም ይልቁንም የእኛን ይወስዳሉ ብዬ እጠብቅ ነበር ሲሉ ቤን-ጊቪር አንስተዋል። ባይደን እስራኤል በጋዛ ላይ ባደረገችው ጦርነት ላይ ጫና ለመፍጠር በመሞከሩ “በጣም ተሳስቷል” ሲሉ አክለዋል። ባይደን በእስራኤል ላይ ያለማቋረጥ ገደቦችን ለመጣል እና ስለሌላው ወገን መብት በተለይ እኛን ለማጥፋት ለሚፈልጉ አሸባሪዎች ይቆረቆራሉ ብለዋል። በሌላ በኩል የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ለእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር በራፋህ ውስጥ ያሉ የሲቪሎች ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑ እንዳለበት ተናግረዋል። ዮአቭ ጋላንት ማክሰኞ በአካል ለተደረገው ስብሰባ ወደ ፔንታጎን ተጉዘዋል። እስራኤል በደቡባዊ ዳርቻ በምትገኘው የጋዛ ሰርጥ ከተማ የመሬት ጥቃት ለማድረስ ማቀዷ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ፍልስጤማውያን ህይወት ላት ስጋት ደቅኗል። ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘምድ ስጋቶች የምድር ወረራን እስራኤል እንዳትፈፀም ያለው ስጋት ከፍተኛ ሆኗል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 30🤔 6 4
የኬንያ ኤርዌይስ ከ2017 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ትርፍ ማስመዝገቡ ተሰማ ከአፍሪካ ትልቅ አየር መንገዶች መካከል አንዱ የሆነው የኬንያ ኤርዌይስ በ2023 ዓመት ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን ይህም ከ2017 ዓመት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የአየር መንገዱ ሊቀመንበር ማይክል ጆሴፍ የ80 ሚሊዮን ዶላር (£63m) ትርፍ “ትልቅ ምዕራፍ” ሲሉ ጠርተውታል።። የስኬቱ አንዱ ምክንያት በተሳፋሪዎች ቁጥር መጨመር ከ 50% በላይ የገቢ ጭማሪ እንዲኖር አግዟል።በከፊል በመንግስት ባለቤትነት የተያዘው የኬንያ አየር መንገድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ እዳዎች የተነሳ ተጎድቶ የቆየ ሲሆነ በኮቪድ ወረርሽኙ ወቅት ከባድ ኪሳራ ደርሶበታል። እነዚህ አሃዞች አየር መንገዱ በዓመቱ ያስመዘገበውን አስደናቂ አፈጻጸም የሚያጎሉ እና በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ውስጥ ቀጣይ አበረታች ምልክቶችን ይሰጣሉ" ሲሉ ጆሴፍ ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል። በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 10 1
በሞጆ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ የአባትና የሁለት አመት ልጅ ህይወት አለፈ በሞጆ ከተማ አስተዳደር ሉቦ መጋላ በተሰኘዉ አካባቢ በትናንትናው እለት ከቀኑ 6ሰዓት ገደማ በተከሰተ የእሳት አደጋ የአባትና ልጅ ህይወት ማለፉን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። የሞጆ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንፔክተር ነጋሽ ለገሰ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በባጃጅ አሽከርካሪነት ስራ ላይ የተሰማራዉ አባት በቤቱ ዉስጥም ቤንዚን ይሸጥ ነበር ብለዉናል። ከስራ ገብቶ በእረፍት ላይ የነበረዉ አባት አዲሱ ቢራ የ 37 አመት ጎልማሳ ሲሆን ልጅ አብርሃም አዲሱ የ 3አመት ህጻን ነበር። ለአደጋዉ መንስኤ የሆነዉ ሁለት ጄሪካን ቤንዚን በቤት ዉስጥ እንዳለ እናት ምግብ ለማብሰል ለሞከረችበት ወቅት እሳቱ መነሳቱን ነግረውናል። አደጋዉ ካጋጠመ በኋላ የሶስት አመት ልጁን ለማዳን ወደ እሳት ዉስጥ ገብቷል የተባለዉ አባት እርሱም ሆነ ልጁ ከፍተኛ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዉ በአዳማ ሃይለማርያም ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው በትናንትናው እለት ህወታቸዉ እንዳለፈ ማለፉን የሞጆ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንፔክተር ነጋሽ ለገሰ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በአደጋዉ እናት በሰዉነቷ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል የተባለ ሲሆን በህክምና ክትትል ላይ ትገኛለች። በበረከት ሞገስ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
😢 32👍 15 2🥰 1
የኡጋንዳ የመንግስት ሰራተኞች በየሳምንቱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ መመሪያ ተላልፈላቸው የኡጋንዳ መንግስት ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች ጤናማ እና ብቁ እንዲሆኑ በሳምንት ለሁለት ሰዓታት በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲያሳልፉ መመሪያ ሰጥቷል። መመሪያውን የፐብሊክ ሰርቪስ ኃላፊ ሉሲ ናኪዮቤ ለመንግስት ኤጀንሲዎች በፃፉት ደብዳቤ ላይ እንደገለፁት እነዚህ የአካል ብቃት እንስቃሴ ክፍለ-ጊዜዎቹ "የሰራተኞችን ህይወት ለመታደግ እና የበሽታውን ሸክም ለመቀነስ ይረዳሉ" ብለዋል። የኡጋንዳ መንግስት በቀድሞ ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ገፁ እንዳስታወቀው ይህ ተነሳሽነት በሀገሪቱ ውስጥ እየጨመረ የመጣውን ጤናማ ያልሆኑ አኗኗር የሚያስከትለው በሽታን ይገራል ብሏል።ባለፉት 17 ዓመታት ውስጥ በሀገሪቱ ያለው ውፍረት ከ17 በመቶ ወደ 26 በመቶ ከፍ ማለቱን ብሔራዊ የጤና ጥናት ካረጋገጠ ከሁለት ዓመት በኋላ መንግስት ይህንን መመሪያ ለማውራት ተገዷል። የኡጋንዳ መንግስት የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ለማበረታታት ሲሞክር ይህ የመጀመሪያው አይደለም። እ.ኤ.አ. በ 2018 ዩጋንዳ በመላ ሀገሪቱ የሚደረጉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ለሚመለከተው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ብሔራዊ ቀን በመሰየም ዜጎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴን እንዲያደርጉ ስታበረታታ ቆይታለች። ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከል ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ዶክተር ቻርለስ ኦዮ አኪያ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት የጤና ሚኒስቴር ለሰራተኞቻቸው የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ሲያካሂድ እንደነበረ እና በሁሉም ክፍሎች ውስጥ እንዲተገበር እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 24😁 24
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ስድስት ወራት "ሹገር ማሚ" እና "ሹገር ዳዲ" እናገናኛለን የሚሉትን ጨምሮ ከ166 ሺህ በላይ ህገወጥ ማስታወቂያዎች ተነሱ አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ስድስት ወራት 166 ሺህ 875 ህገወጥ ማስታወቂያዎች እንዲነሱ መደረጋቸውን የከተማ ውበት እና የአረንጓዴ ልማት ቢሮ አስታውቋል። በቢሮው የከተማ ውበት ልማት ክትትል ዳይሬክተር ወ/ሮ አልማዝ ከበደ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ፣በአዲስ አበባ  በሁሉም  ክፍለ ከተሞች ሊባል በሚችል ደረጃ በርካታ ህገወጥ ማስታወቂያዎች ይለጠፋሉ።በተለይም ደግሞ የህብረተሰቡ ዋንኛ መዳረሻ በሆኑት እንደ ሜክሲኮ እና መገናኛ ባሉት የአዲስ አበባ ቦታዎች ይህ ሁኔታ በስፋት ጎልቶ ይታያል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ማስታወቂያዎቹ በጊዜው እንዲነሱ ባለመደረጋቸው በቆይታ ብዛት ወይበው መልካቸውን የሚቀይሩበት እና  የአዲስ አበባን ገጽታ የሚያበላሹበት እድላቸው ከፍተኛ በመሆኑ  በግማሽ ዓመቱ 166 ሺህ 875 ህገወጥ ማስታወቂያዎች እንዲነሱ ተደርጓል ሲሉ ዳይሬክተሯ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።እነዚህ ማስታወቂያዎች በየ ስልክ እንጨቱ፣በኤ ፎር ወረቀት መጠን  የተለጠፏ፣በቢልቦርድ እና በሸራ መልክ ጭምር ተሰቅለው የተገኙ ናቸው ተብሏል። ባለፉት ስድስት ወራት  ባልተፈቀዱ ቦታዎች የተለጠፏ እና የተለያዮ መልእክቶችን ያዘሉ ማስታወቂያዎች እንዲነሱ ተደርጓል ያሉት ወሮ አልማዝ "ስራ እናስቀጥራችሗለን"፣ "እከሌ ደላላ" የሚሉት ዋንኛ የንግድ ስራ ማስታወቂያዎች ከእነዚህ መካከል  ይገኙበታል ብለዋል።በተጨማሪም " ትዳር አፋላጊ" የሚሉና ከኢትዮጵያ ባህል ያፈነገጡ ማስታወቂያዎች እንዲነሱ ተደርጓል። ትዳር ወይንም ጋብቻ የተከበረ ነገር ሆኖ ሳለ "ሹገር ዳዲ "እና  "ሹገር ማሚ" እናገናኛለን በሚል ከባህል ያፈነገጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ማስታወቂያዎችን ቢሮው ከደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ጋር በመሆን እንዲነሱ አድርጓል ሲሉ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።በበጀት አመቱ ስድስት ወራት አንድ መቶ 60 ሺህ ህገወጥ ማስታወቂያዎችን ለማንሳት እቅድ ተይዞ የነበረ ሲሆን ከእቅድ በላይ ማሳካት ተችሏል። አዲስ አበባ ከመስከረም ወር ጀምሮ በርከት ያሉ በዓላትን ማስተናገዷ እና ከተማዋን ለመጎብኘት ለመጡ የውጪ  ሀገራት እንግዶች የተደረገው የማስዋብ ስራ  ጥሩ አፈጻፀም እንዲኖር   ጉልህ አስተዋቶኦ አድርጓል በማለት ዳይሬክተሯ አስረድተዋል።የአዲስ አበባ ውበት ተጠብቆ እንዲቆይ ለማድረግ እና ህብረተሰቡ የኔነት ስሜት ተሰምቶት ባልተፈቀዱ ቦታዎች ላይ ማስታወቂያዎችን ከመለጠፍ እንዲቆጠብ የማስተማር ስራዎች እንደሚሰሩ ተገልጿል። በቅድስት ደጀኔ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
😁 49👍 23👏 3 2
👍 4 1
የአለልኝ የሞቱ መንስኤ ከቤተሰብ ጋር በትዳሩ ምክንያት አለመግባባት ነው ተባለ የካናል ፕሉሱ ጋዜጠኛ አብዱ ሞሀመድ "...ለእረፍት  ወደ ቤተሰቦቹ ቤት አርባምንጭ  ባለቤቱን ይዞ እንደሄደና ፡ ቤተሰቦቹ ትዳሩን እንዳልወደዱለትና ጭቅጭቅ እንደነበር፡ ከዛም ሞተሩን አሰነስቶ አዲስ ወደሚያሰራው የግል ቤቱ በመሄድ የኤልትሪክ ምሰሶ ላይ ራሱን አጠፋ "  ብሏል በዘገባው ከመሰረተው ትዳር ጋር በተገናኘ ተደጋጋሚ ጭቅጭቆች እንደነበሩ በዩቲዩብ ቻናሉ አጋርቷል። #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
🤔 26😢 23👍 13💔 4 2
በታይታኒክ ፊልም ሮዝን በህይወት ያቆየው ተንሳፋፊ እንጨት በ718 ሺ 7 መቶ 50 ዶላር ተሸጠ በታይታኒክን ፊልም ላይ ሮዝን በህይወት ያቆየው ተንሳፋፊ እንጨት በጨረታ በ718 ሺ 7 መቶ 50 የአሜሪካን ዶላር ተሽጧል። ፊልሙ ከተለቀቀበት እኤእ ከ1997 ጊዜ አንስቶ ሮዝን በህይወት ያተረፈው ተንሳሳፊ እንጨት ለፍቅረኛሞቹ ሮዝ እና ጃክ በቂ ነበረ ሲሉ ደጋፊዎች በመናገር እርሱም በእዛች እንጨት ላይ ቢንሳፈፍከበረዶ ሞት ያድነው ነበር ይላሉ። ይህው ዝርዝር ጉዳት ከደጋፊዎች ዘንድ ብዙ ክርክር አስከትሏል። ሽያጩ የተካሄደው በሬስቶራንት እና በሪዞርት ሰንሰለት አባል በሆነው ፕላኔት ሆሊውድ ባለቤትነት የተያዙ የቤት ዕቃዎች እና አልባሳት ጨረታ በተካሄደበት ወቅት ነው። ሊዮናርዶ ዲ ካፕሪዮ የተጫወተው ልብ ወለድ ጃክ የያዘው የበር ፍሬም ክፍልለፍቅረኛው ሮዝ ብቻ በቂ ነበር።እናም እርሱ በውሃ ውስጥ ሆኖ ሰውነቱ ወደ ውቅያኖስ ጥልቀት ውስጥ ወድቆ በሚቀዘቅዝ የአትላንቲክ ውቅያኖስ ህይወቱ አልፏል። እ.ኤ.አ. በ 2012 የታይታኒክ ዳይሬክተር ጄምስ ካሜሮን እንደተናገረው ሮዝን “ራስ ወዳድ” እና ጃክን “የማይረባ” የሚሉ በቀን በደርዘን የሚቆጠሩ ኢሜይሎችን ይደርሰኝ ነበር ሲል ዳጉ ጆርናል ዘግቧል። ነገር ግን ጃክ በስክሪፕቱ መሰረት መሞት አለበት በማለት ክርክሩ እንዲቆም አድርጓል። ይህው ሮዝን ያተረፈው ተንሳፋፊ እንጨት ለሁለቱም ይበቃ ነበር በሚለው ክርክር ዙሪያ በተለምዶ በር የሚባለው ከእንጨት የተሰራው ተንሳፋፊ አካል በግምት 2.4 ሜትር ርዝመት እና 1 ሜትር ስፋት አለው።ታይታኒክ እ.ኤ.አ. በ1997 ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተለቀቀ 1.8 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ ገንዘብ መስራት ችሏል። በ2019 ለእይታ ከበቃው አቬንጀርስ፡ ኢንድጌምእና በ2009 ከወጣው አቫተር በመቀጠል ሦስተኛው ከፍተኛ ገቢ ያስገኘ ፊልም ነው። ፊልሙን ለመስራት 200 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ፈጅቷል። 195 ደቂቃዎች የስክሪን ቆይታ በሚወስደው በዚህ ፊልል ላይ በደቂቃ ወደ 1 ሚሊዮን ዶላር ውጪ ጠይቋል። በጊዜው ከነበሩ ፊልሞች አንፃር በጣም ውዱ ፊልም ያደርገዋል።በሌላ በኩል በጨረታው ላይ ከቀረቡት ሌሎች ቁሳቁሶች መካከል ከኢንዲያና ጆንስ የተገኘው ጅራፍ እና የዱም ቤተመቅደስ በ525 ሺ ዶላር ተሽጠዋል።ቶቢ ማጊየር የለበሰው የስፓይደር ማን ልብስ በጨረታው በ125 ሺ የአሜሪካን ዶላር ተሽጧል። እንዲሁም በዘ ሻይኒንግ ጃክ ኒኮልሰን የመታጠቢያ ቤቱን በር ለመፍለጥ የተጠቀመበት መጥረቢያ በተመሳሳይ የተጫራጮችን ትኩረት ስቧል። እሁድ ማምሻውን የተጠናቀቀው ይህ ጨረታ 15.68 ሚሊዮን ዶላር በማሰባሰብ በፊልም ቁሳቁሶች እና አልባሳት ስብስብ በጣም ስኬታማ ከሚባሉት ሽያጭዎች መካከል አንዱ እንዲሆን አድርጎታል ሲሉ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
😁 25👍 16 1🤯 1😱 1
በድሬዳዋ ከተማ የሶስት አመቷን ህጻን አስገድዶ በመድፈር ገድሎ ተሰውሮ የነበረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ ግለሰብ በድሬዳዋ ከተማ መልካ ጀብዱ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል። ተጠርጣሪው ግለሰብ ለአስራ አንድ ወራት ከህግ ተሸሽጎ እንደነበር የገለጸው የድሬደዋ ፖሊስ ህጻን ቢሊሱማ መሃመድ የ3 ዓመት ታዳጊ ክፉን እና ደጉን በቅጡ ለይታ የማታውቅ መሆኑን ገልጿል፡፡ ተጠርጣሪው ግለሰብ  የእንጀራ አባቷ/ ሲሆን ይሄንን የጭካኔ በትር ከመሰንዘሩ በፊት የቢሊሱማ መሃመድ እናት ከባለቤቷ ጋር በትዳር መቀጠል አልቻለችም በመሃከላቸው መግባባት ባለመኖሩ ተለያይተዋል። የቢሊሱማ መሃመድ እናት ወደ ሀሮማያ ከተማ በመምጣት ሌላ ትዳር ትመሰርታለች። ለአጭር ቀናት ቢሆንም ቢሊሱማ መሃመድም በእንጀራ አባቷ ማደግ ግድ የሆነባት ሲሆን ተጠርጣሪው ግለሰብ /እንጀራ አባቷ/ አስከፊውን የወንጀል ደርጊት ፈጽሞ እስከተሰወረበት ቀን ድረስ አብራ በጋራ ትኖር ነበር ፡፡ መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም ቀን ግን ተከሳሽ የሶስት ዓመት ህጻን ቢሉስማ አስገድዶ ከደፈራት በኃላ ህይወቷን በማጥፋት ከአካባው ይሰወራል፡፡ ግለሰብቡ ድርጊቱን በመፈጸም ከአካባቢው ተሰውሮ ድሬዳዋ መልካ ጀብዱ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ለአስራ አንድ ወራት ተሸሽጎ መቆየቱን የመልካ ጀብዱ ፖስ ጣቢያ አዛዥ ም/ኮማንደር ሻምበል ተካኝ ተናግረዋል፡፡ ለአስራ አንድ ወራት ተሸሽጎ የቆየው ተጠርጣሪው ግለሰብ መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት ከተሸሸገበት ወጥቶ ሲንቀሳቀስ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ለሀሮማያ ከተማ ፖሊስ ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ተከሳሹ ግለሰብ/እንጀራ አባቷ/ ፍርድ ቤት ቀርቦ ለምን  ህጻን አስገድዶ በመድፈር ሊገላት እንደቻለ ሲጠየቅ ‹‹ሰይጣን አሳሳተኝ›› በማለት ምላሽ መስጠቱን ፖሊስ አስታውቃል፡፡ የድሬዳዋ ፖሊስ የልጄ ደም ፈሶ እንዳይቀር ስላደረገው ጥረት አመሰግናለሁ ያሉት የቢሊሱማ መሃመድ እናት ወ/ሮ ሮዳ በክሪ ልጄን አጥቼ በሃዘን ተቆራምጄ ባለሁበት ጊዜ የድሬዳዋ ፖሊስ የልጄን ገዳይ ስለያዘልኝ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
💔 33😢 11👍 10🤔 2👏 1
በቬንዝዌላ ወንድ እስረኛ ሴት መስሎ ከማረሚያ ቤት ማምለጡ ተሰማ አንድ አደገኛ የቬንዙዌላ ወንጀለኛ በቅርቡ ራሱን ሴት በማስመሰል እና በጎብኚዎች ሰአታት መጨረሻ ላይ ከማረሚያ ቤት በመውጣት ማምለጥ መቻሉ ተነግሯል። ማኑዌል ሎሬንዞ አቪላ አልቫራዶ የተባለው የ25 ዓመቱ ወጣት በነፍስ ግድያ እና በከባድ ዘረፋ በማረሚያ ቤት ይገኝ የነበረ ሲሆን በቬንዙዌላ ካራቦቦ ግዛት ከሚገኘው ኤል ሊበርታዶር እስር ቤት ማምለጥ መቻሉ ታውቋል። የሀገር ውስጥ ጋዜጣ የሆነው ኤል ካራቦቤኖ እንደዘገበው፣ ክስተቱ ያጋጠመው ከቀኑ ስምንት ሰዓት አካባቢ ታራሚዎችን ለመጎብኘት በተፈቀዱ የመጨረሻ ሰአታት ላይ ነበር። አልቫራዶ ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ቢኖረውም ሰው ሰራሽ ፀጉር ዊግ እና የሴት ልብስ በመልበስ በርካታ የማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎችን ለማታለል ችሏል። እነዚሁ የማታለያ ቁሳቁሶች ምናልባትም በሴት ጓደኛው አማካይነት ወደ ማረሚያ ቤቱ ሳይመጣለት እንዳልቀረ ተሰምቷል።የእስር ቤቱ የደህንነት ካሜራዎች እንዳመላከቱት እስረኛው እንደ ሴት ለብሶ፣ በጉብኝት ሰአታት መጨረሻ ላይ ከነበሩ ሴቶች ጋር በመደባለቅ በከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግለ የማረሚያ ተቋም ሲወጣ የሚያሳየው ቅጽበት ፖሊስ እጁ ላይ እንዳለ ገልጿል። ጠባቂዎቹ እንዴት በቀላሉ ሊታለሉ እንደቻሉ ግልጽ ባይሆንም ከዚሁ ክስተት ጋር በተያያዘ አራት የማረሚያ ቤቱ ሰራተኞች በአሁኑ ጊዜ በምርመራ ላይ ይገኛሉ። አቪላ በቅርቡ በግዛቱ ውስጥ ካለ ሌላ የማረሚያ ቤት ወደ ቶኩዪቶ ማረሚያ ቤት የተዘዋወረ ሲሆን በሴት ጓደኛው ተባባሪነት እና እርዳታ ከማረሚያ ቤቱ ግን ማምለጥ ችሏል። የቬንዙዌላ ፖሊስ ከፍተኛ ጥረት ቢማድረግ ሁለቱም ማኑዌል ሎሬንዞ አቪላ አልቫራዶ እና የሴት ጓደኛው በቁጥጥር ስር ለማዋል እሞከረ ይገኛል ። ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ አንድ ወንድ ታራሚ ከእስር ቤት ለማምለጥ የሴት ቁሳቁስ ሲጠቀም ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ከጥቂት አመታት በፊት ‘ጎርዲቶ ሊንዶ’ የሚል ቅጽል ስም ያለው የፓራጓይ ሰው ጥቁር ዊግ፣ ሜካፕ እና የሴቶች አልባሳትን በመጠቀም ከማረሚያ ቤቱ አምልጧል።ይሁን እንጂ የማረሚያ ቤቱ ባለሥልጣናት በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ሊይዙት ስለቻሉ ነፃነቱ ለአጭር ጊዜ ብቻ የተገደበ ነበር። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 26😁 10🤔 10🤬 1
ውድ አድማጮቼ:- ሰላም ለእናንተ ይሁን! የመላው ዓለም የሬድዮና ቲቪ ጋዜጠኞች ሁሉ የዘወትር ስጋት በሆነው (የህክምና ባለሙያዎች Laryngitis በሚሉት ህመም) ምክንያት ድምጼ በመዘጋቱ ለጊዜው ለሬድዮ ስቱድዮ በማይመች ሁኔታ ላይ መገኘቴን በመግለጽ የቀጥታ ስርጭት ላይ አለመኖሬን አሳውቄ ነበር። ሆኖም ነገሩ በማህበራዊ ሚድያው ላይ እጅጉን ተጋኖ ተመልክቼዋለሁ ሲል ጋዜጠኛዉ መናገሩን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። "ወደ ስራ ላይመለስ ይችላል" የሚሉ ግምቶችንም ሳይቀር አንብቤያለሁኝም ብሏል። ስለጤንነቴ ለተጨነቃችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬን እያቀረብኩኝ - የህክምና ቃሉ ከባድ መስሎ ታይቶ ካልሆነ በስተቀር -  ነገሩ በጉንፋን ቫይረስ ሊመጣ ከሚችል የተለመደ የድምጽ ሳጥን ኢንፌክሽን (የድምጽ መታፈን) የተለየ እንዳልሆነ ለማሳወቅ እወዳለሁ። ለክፉ የማይሰጥ የጥቂት ቀናት ጉዳይ ብቻ ነው። ግፋ ቢል ከማንቸስተር ሲቲና አርሰናል ጨዋታ በፊት (ዓርብ ወይም እሁድ) ወደ ስቱዲዮ እመለሳለሁ። በመልዕክት ማድረሻ መንገዶች ቀና ምኞታችሁን ለገለጻችሁልኝ ሁሉ ለእናንተ ያለኝን ፍቅርና አክብሮት ተቀበሉኝ። አመሰግናለሁ። የሚወዳችሁ አክባሪያችሁ መንሱር አብዱልቀኒ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 91 20
የኢትዮጵያ አወ‍እሮፕላን በሱማሌላንድ አየር እየበረረ በሌላ አቅጣጫ ሲመጣ ከነበረ የኤሚሬትስ አውሮፕላን ጋር ለሁለተኛ ጊዜ ከመጋጨት ለጥቂት ተረፈ በ 37,000 ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረዉ የኤምሬትስ  አየር መንገድ በተመሳሳይ ርቀት ላይ ከነበረው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በድጋሚ ከመጋጨት ለጥቂት መትረፍ ተሰማ። ከሞቃዲሾ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች በተሰጠዉ ትዕዛዝ በተመሳሳይ የጫማ ከፍታ ላይ ሲበሩ የነበሩት ንብረትነታቸው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና የኢትዮጵያ መንግስት የሆኑት አዉሮፕላኖች በድጋሚ ከመጋጨት አደጋ መትረፋቸው የሶማሌላንድ ሲቪል አቪዬሽን እና ኤርፖርቶች ባለስልጣን ማስታወቁን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። ባለፈው የካቲት ወር በተመሳሳይ አጋጣሚ የኢትዮጵያ እና የኳታር አየር መንገዶች ንብረት የሆኑ አውሮፕላኖች ከመጋጨት ለጥቂት መትረፋቸው ይታወሳል። እሁድ መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በ 37,000 ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረዉ የኤምሬትስ አየር መንገድ አዉሮፕላን UAE722 እና በተመሳሳይ በ 37,000 ከፍታ ላይ ከነበረዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ETH690 ለመጋጨት ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀራቸዉ የሶማሊላንድ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪ ባደረጉት ጥረት አብራሪው በፍጥነት ከፍታውን በመቀየር ወደ 39, 000 ጫማ ከፍ እንዲል በማድረግ የተፈራው አደጋ ለጥቂት ሳይደርስ እንዲቀር አድርጓል። በድጋሚ ለተፈጠረዉ ክስተት የሶማሌላንድ የሲቪል አቪዬሽን እና አየር ማረፉያዎች ባለስልጣን  የሞቃዲሾ ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን የወቀሰ ሲሆን። መሰል ቸልተኝነት እና የእውቀት ማነስ ሞቃዲሾ በሚገኙ የሱማልያ የአቪዬሽን ባለሞያዎች በተደጋጋሚ እየተፈጠረ መሆኑን አለም ይወቅ ሲል አክሏል። ሁኔታውም የአየር ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን አፅንኦት በመስጠት ሁኔታውን ኮንኗል። Via ካፒታል #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
🤬 36👍 10🤯 4🕊 4👏 2
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የባሕር ዳር ከተማ ተጫዋች የነበረው አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ አለፈ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የባሕር ዳር ከተማ እተጫዋች የነበረው አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል። ተጫዋቹ በጉዳት ምክንያት ከክለቡ ስብስብ ጋር ያልነበረ ሲሆን በትውልድ ቦታው አርባ ምንጭ ሌሊት በድንገት ማረፉ ተነግሯል። በቅርቡ የተሞሸረው አለልኝ አዘነ ፤ ላለፉት ሁለት አመታት በጣና ሞገዶቹ ቤት ድንቅ ብቃቱን ሲያሳይ ቆይቷል። ከዚህ በተጨማሪም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ተደርጎለት አገልግሎት መስጠቱ ይታወቃል። ስርዓተ ቀብሩ ዛሬ መጋቢት 18/ 2016 በአርባ ምንጭ እንደሚፈፀም ዳጉ ጆርናል ከክለቡ ማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
😢 89👍 17😱 4 3👎 1🔥 1
በመስቀል አደባባይ ነገ ለሚካሄደው የአደባባይ ኢፍጣር የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል በነገው ዕለት በአዲስ አበባ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመስቀል አደባባይ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርኃ ግብር  ጋር ተያይዞ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም መሰረት፡- - ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን - ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ   ኦሎምፒያ - ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ  አሽከርካሪዎች ለከባድ መኪናዎች  አጎና ሲኒማ፤ለሌሎች ተሸከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡ - ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች  በተለምዶ አጠራሩ ክቡ ባንክ አካባቢ - ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሐራምቤ መብራት ላይ - ከ4 ኪሎ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛው ላይ - ከአዋሬ አካባቢ በካሳንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ኢንተርኮንትኔታል አካባቢ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጧር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ ይደረጋሉ። በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅመ ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው ተብሏል። ኅብረተሰቡ ማንኛውም ዓይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በፖሊስ የመረጃ ስልኮች 0111 11 01 11 እና ነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወልና መረጃ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል። #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 51🤬 18👎 16 11😢 4👏 2
በዶዶላ የደብረ  ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ  ክርስቶስ ቤተክርስቲያን 2 አገልጋዩች  ከሙሉ  ቤተሰቦቻቸው  ጋር ለጊዜው ማንንነታቸው  ባልታወቁ  በተባሉ አካላት ተገደሉ:: ግድያው  የተፈፀመው  መጋቢት  16  ቀን  2016  ዓ.ም  ከምሽቱ 3:00  ገደማ  መሆኑንም  ከአካባቢው  ምእመናን   ያገኘነው  መረጃ  ይጠቁማል። በተፈጸመው  ግድያ  የደብረ  ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ  ክርስቶስ ቤተክርስቲያን  አገልጋይ  የሆኑት አንድ መሪጌታና  ዲያቆንን  ጨምሮ  አምስት የቤተሰብ  አባሎቻቸው  በጥይት  ተደብድበው  መገደላቸው  ታውቋል። በምዕራብ   አርሲ  ሀገረ  ስብከት በዶዶላ  ከተማ ጥቅምት  12ቀን  2012 ዓ.ም በርካታ   ኦርቶዶክሳውያን  መገደላቸው  ይታወሳል። Via ማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
😢 67💔 15👍 10🕊 2 1
😁 45👍 8😱 4
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወሰዱትን ገንዘብ አልመለሱም ያላቸውን 565 ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል ከታች ያለውን አታችመንት ይመልከቱ። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!