Channels intersection
Channel location and language
ናዝራዊ: ማለት የተቀደሰ ወይም ለእግዚአብሔር የተለየ ማለት ነው።  @biblicalmarriage  On YT sub☞  https://bit.ly/2ZCsqFN  Inbox👉  @Nyouth_bot  -- " እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ። -- ኤር 6:16 
Show more
24 047-15
~1 544
~47
6.42%
Telegram general rating
Globally
82 966place
of 4 078 614
113place
of 901
In category
47place
of 1 371

Subscribers gender

Find out how many male and female subscibers you have on the channel.
?%
?%

Audience language

Find out the distribution of channel subscribers by language
Russian?%English?%Arabic?%
Subscribers count
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

User lifetime on the channel

Find out how long subscribers stay on the channel.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
Subscribers gain
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

#የማለዳ_ስንቅ ልባችሁን በፊቱ ኣፍስሱ ብዙ ጊዜ ከኣቅም በላይ የሆነ ኣንድ ፈተና ሲገጥመን ግራ ይገባናል። ባዶነት ይሰማናል፣ የምናደርገው ይጠፋናል፣ እናዝናለንም። እነዚህ ስሜታዊ ምላሾች ተገቢ ናቸው። ሆኖም ግን ምላሾቹ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ወዳልሆኑ ፈጣንና ተግባራዊ ምላሾች እንዳያንደረድሩን መጠንቀቅ ይኖርብናል። የማልደብቃችሁ ነገር ስሜታዊነቴ ብዙ ጊዜ ያልተገባ ሩጫ ውስጥ ዶሎኝ ያውቃልና ነው እንዲህ ልል የቻልኩት። በዚህ ጊዜ መንፈሱን የሚገዛ ሰው፣ ለችግሩ እንደ ቃሉ የሆነ ምላሽ መስጠቱ ከብዙ ኪሣራና ጸጸት ያድነዋል ብዬ ኣምናለሁ። በዚህ ረገድ ዳዊት በመዝሙር 6፥28 "የሕዝብ ማኅበር ሁላችሁ፥ በእርሱ ታመኑ፥ ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ፤ እግዚአብሔር ረዳታችን ነው።" ብሎ መክሯል፡፡ ኣዎ፣ ትክክለኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሽ ቀድመን ልባችንን በእግዚአብሔር ፊት ማፍሰስ ነው። በጸጋው ዙፋን ፊት መቆየት ነው፡፡ በፈለጋችሁት መንገድ ይሁን በልባችሁ ውስጥ ያለውን ፍርሃትና ጭንቀት ኣውጡት–በልቅሶም ሆነ በጩኸት። እውነተኛ ማንነታችሁን ሳትሰስቱ በፊቱ ዘክዝኩት። መንበርከክ ትችላላችሁ፤ በወለል ላይ ተዘርግቶ መቃተት ጥሩ ነው። ስቅስቅ ብላችሁ ያላችሁበትን ሁኔታ በዕንባ መግለጽም መብታችሁ ነው። ጌታ የልብ ኣምላክ ነውና ከልብ መሆኑ ነው ዋናው ጉዳይ! ይኼ ዓይነቱ ምላሽ የወዲያው ጥቅሙ ነፍሳችንን ስለሚያረጋጋና ስለሚያሰክናት ነው። የእግዚአብሔር ጸጋ በውስጣችን በኃይል ስለሚለቀቅ ሳንናወጥም እንቆማለን። ጸሎቱ ዙሪያችንንና በቀጣይ የምናደርጋቸውን ነገሮች በቅጡ እንድናስተውል ያስችለናል፡፡ ቆይቶም ጸሎታችን በጌታ ኣምላክ ፊት ስለሚመለስ ፈተናውን በእርግጠኝነት እንሻገረዋለን። አብርሃም ሊንከን በመከራ ጊዜዎቻቸው የነበራቸው ምላሽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነበር፡፡ ያንን እንዲህ ብለው መስክረዋል፡-“I have been driven many times upon my knees by the overwhelming conviction that I had nowhere else to go. My own wisdom and that of all about me seemed insufficient for that day.” መልካም ጊዜ ተባረኩልኝ! @nazrawi_tube @nazrawi_tube
Show more ...
668
10
በማለዳ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይባረኩ 😊 ከተባረኩበት ያጋሩ!
450
0
` አምላክ በሥጋ ተገለጠ! (በወንድም ሚናስ) ሰሞኑን የክርስቶስን አምላክነት ከማይቀበል አንድ ወዳጄ ጋር በኢንተርኔት በይነመረብ በመታገዝ የቀጥታ ውይይት እያደረግን እያለ ነገረ ሥጋዌ ን ለማስረዳት 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16 ላይ ያለውን ምንባብ አነሳሁ፥ ሆኖም ግን ወዳጄ “በጥቅሱ ውስጥ *እርሱ* በሥጋ ተገለጠ የሚለውን የሥላሴ አማኒያን ሆነ ብለው *አምላክ* በሥጋ ተገለጠ ብለው አጭበርብረዋል” የሚል መከራከሪያ አቀረበልኝ። ለወዳጄ የሰጠሁትን ምላሽ ለብዙዎቻችሁ የሚጠቅም መስሎ ስለ ተሰማኝ በጽሑፍ መልክ አዘጋጅቼዋለሁ። የእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ምስጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ *አምላክ በሥጋ* ተገለጠ፤ በመንፈስ ጸደቀ፤ በመላእክት ታየ፤ በአሕዛብ ዘንድ ተሰበከ፤ በዓለም ባሉት ታመነ፤ በክብር ዐረገ።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16 [ኬ.ጂ.ቪ ትርጕም] “የእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ምስጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ *እርሱ በሥጋ* ተገለጠ፤ በመንፈስ ጸደቀ፤ በመላእክት ታየ፤ በአሕዛብ ዘንድ ተሰበከ፤ በዓለም ባሉት ታመነ፤ በክብር ዐረገ።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16 [አዲሱ መ.ት] “እርሱ ተገለጠ” (ὃς ἐφανερώθη “ሆስ ኤፋኔሮቴ”) የሚለው፥ ኮዴክስ ሳይናቲከስ፤ ኮዴክስ ቫቲካነስ፤ ያሉ ዕደ ክታባት ያካተቱት እንዲሁም አርጌንስ ዘእስክንድርያ፤ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ ...ወዘተ ያሉ የቤተክርስቲያን አባቶች የተጠቀሙት ነው። “አምላክ ተገለጠ” (θεος εφανερωθη) የሚለው ደግሞ፣ ኮዴክስ አሌክሳንድረስ፤ አንዳንድ የሴሪያክ ቅጆች፤ ከቤተክርስቲያን አባቶች ደግሞ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፤ ዮሐንስ አፈወርቅ ጠቅሰውታል። እንግዲህ ከሁለቱ ንባቦች ማለትም፤ “እርሱ”(ὃς) እና “አምላክ”(θεος) ከሚሉት ዕደክታባት ውስጥ “እርሱ” (ὃς) የሚለው የተሻለ ተአማኒነት ሆነ ቀዳሚነት ባላቸው መዛግብቶች፤ እንዲሁም በምንባባዌ ሕያሴ ሊቃውንት ቅቡልነቱ የተረጋገጠ ስለሆነ “አምላክ”(θεος) ከሚሉት መዛግብት ይልቅ “እርሱ”(ὃς) የተሻለ ተአማኒነት አለው። አሁን ወደ ሰዋስዋዊ ትንታኔ ስንመጣ “እርሱ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል ὃς “ሆስ” የሚል ሲሆን አዛማጅ ተውላጠ (Relative pronoun) ነው። ማለትም ቀድሞ ከተጠቀሰው ስም ወይም ተውላጠ ስም ጋር በፆታና በቊጥር ስምም ሆኖ በመግባት አላስፈላጊ ድግግሞሽ እንዳይኖር የሚያደርግ ምእላድ ማለት ነው፤ (Brooks & Winbery, Syntax of New testament Greek ገጽ 169-170)። ታዲያ ሐዋርያው “እርሱ” የሚለን ማንን ነው? የጳውሎስን ሐሳብ ለመረዳት ግዴታ ቊጥር አስራ አምስትን መመልከት ይኖርብናል፦ “ይህንም የምጽፍልህ ብዘገይ እንኳ ሰዎች በእግዚአብሔር ቤት እንዴት መኖር እንዳለባቸው እንድታውቅ ነው፤ ቤቱም የሕያው *እግዚአብሔር* *ቤተ ክርስቲያን* ይኸውም የ*እውነት* ዐምድና መሠረት ነው።” ἐὰν δὲ βραδύνω, ἵνα εἰδῇς πῶς δεῖ ἐν οἴκῳ θεοῦ ἀναστρέφεσθαι, ἥτις ἐστὶν ἐκκλησία θεοῦ ζῶντος, στῦλος καὶ ἑδραίωμα τῆς ἀληθείας. ከላይ ባለው ምንባብ ውስጥ ሶስት ነገሮች በዋነኝነት ተዘርዝረዋል፥ ይኸውም “ቤተክርስቲያን”(ἐκκλησία) ፤ “የእውነት”(τῆς ἀληθείας)፤ “እግዚአብሔር”(θεοῦ)፤ የሚሉ ቃላት ናቸው። ታዲያ ጳውሎስ በቊጥር አስራ ስድስት “እርሱ”(ὃς) ያለው በቊጥር አስራ አምስት ከተጠቀሱት የትኛውን ነው የሚለው በሰዋስው ስነ አፈታት መፍትሄው ይፈይዳል። 1ኛ.“ቤተክርስቲያን”(ἐκκλησία)፦ የሚለውን ሊያመለክት አይችልም ምክንያት ἐκκλησία “ኤክሌሲያ” የሚለው ቃል ሰዋስዋዊ ጾታው አንስታይ(Feminine) ሲሆን “እርሱ”(ὃς “ሆስ”) ከሚለው ጋር አይስማማም ምክንያቱም “እርሱ”(ὃς “ሆስ”) ተባዕታይ (Masculine) ነውና። 2ኛ.“የእውነት”(τῆς ἀληθείας)፦ ይኸውም “እርሱ” ከሚለው ጋር አይስማማም ምክንያቱም ይኼም τῆς ἀληθείας “ቴስ አሌቴያስ” የሚለው በተመሣሣይ አንስታይ ሲሆን ተባዕታይ ከሆነው ተውላጠ ስም “እርሱ” (ὃς “ሆስ”) ከሚለው ጋር ሊዛመድ አይችልም፤ 3ኛ.“እግዚአብሔር”(θεοῦ) የሚለው “እርሱ” ὃς “ሆስ” ከሚለው ጋር በትክክል ይስማማል። ምክንያቱም θεοῦ “ቴኡ” የሚለው ቃል ተባዕታይ፤ ነጠላ፤ ሲሆን በተመሣሣይ “እርሱ” (ὃς “ሆስ”) የሚለው ተውላጠ ስም እንዲሁ ተባዕታይ፤ ነጠላ ነው። ስለዚህ ሐዋርያው ጳውሎስ “እርሱ በሥጋ ተገለጠ” ያለው በቊጥር 15 የተጠቀሰውን “እግዚአብሔር” የተባለውን አካል ነው። ለዚህም ነው የኮዴክስ አሌክሳንድረስ አዘጋጆች ሆነ እንደ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ያሉ የቤተክርስቲያን አባቶች በቀላሉ የጳውሎስን ሐሳብ ሰዎች እንዲረዱት በማሰብ በግሪክ ኮይኔ አስራ አምስተኛው ፊደል O “ኦሚክሮን” መሃል ላይ አግድም ሰረዝ (-) በማድረግ ወደ ስምተኛው ፊደል Θ “ቴህ'ታ” የቀየሩት፥ ይኸውም Θς “ቴስ” የአምላክ ምህፃረ ቃል ይሆንና “አምላክ” የሚል ትርጕም ይኖረዋል። ስለዚህ የፀረ-ሥላሴያውን አቤቱታ የክፍሉን ሰዋስዋዊ አወቃቀር በወጉ ካለመረዳት የሚመጣ ስንኩል ሙግት ነው። @nazrawi_tube @nazrawi_tube
Show more ...
2 127
7
የፍቅር ጓደኝነት(Relationship) ከመፅሐፍ ቅዱስ አንፃር!👩‍❤️‍👩💖💖💝💝 ይመልከቱ 👇👇👇👇👇
675
1
እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! ነቢዩ ኢሳይያስ በትንቢቱ የተናገረው ይፈፀም ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ከቅድስት ድንግል ማሪያም ተወልዶ፤ እንዲሁም "ህዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋል"ማቴ 1:21 የተባለለት አዳኝ ጌታ፤ ስለኛ ቤዛ ሊሆን ከሰማይ የወረደበት ቀን ነው። በዚህ ቀን ባለ ልደቱን የምናስብበትና የምናመሰግንበት ይሁን! መልካም በዓል! ናዝራዊ ትዩብ @nazrawi_tube
2 906
6
በቅድመ ዘላለም በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ፥ ራሱም እግዚአብሔር የነበረው “ቃል” ፣ ሥጋ ሆነ። የሥላሴ አንዱ አካል ፥ መለኮትነቱን ሳይለቅ “ሰውነትን” ጨመረ ። ጸጋንና እውነትን ተመልቶ በሰው ልጆች መካከል “አማኑኤል” ተባለ ። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ። አምላክ በውሱን አካል ተቀንብቦ በፈራሽ ሥጋ ውሎ አደረ ። በብርዳማው ሌሊት የምስራቹን ብስራት የቤተልሔም እረኞች አስቀድመው ሰሙ ። በቅዱሳን መላዕክት የታወጀውን እንግዳ ሰማያዊ ዝማሬ — ‘ለሕዝብ ሁሉ የሚሆን ታላቅ የደስታ ድምጽ’ አደመጡ ። ጥቂት እረኞችን ብቻ ሳይሆን መላውን ፍጥረተ ዓለም የሚያናውጥ የደስታ ዝማሬ ነበር። ለሕጻኑም ዝቅ ብለው ሰገዱለት ፤ አመለኩት ። ሰማይና ምድር - መላዕክትና እረኞችም እኩል ተደነቁ ፤ ሐሴት አደረጉ ። ቁስ-አካላዊውና መንፈሳዊው ዓለም ተናበቡ ። ትልቁን እውነት በአንድነት መሰከሩ ። “በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን ዐየ ፤ በሞት ጥላ ምድር ለኖሩትም ብርሃን ወጣላቸው” ተብሎ ነብዩ ኢሳያስ ስለ ሕጻኑ መወለድ የተነበየው ለዚህ ምልክት ነበር። የተወለደው ሕጻን ሕዝቡን ከኅጢአት ባርነት የሚያድናቸው ብቸኛ ተስፋ ነበር ። ለብዙዎች በደል የሚታረድ ንጹሕ የእግዚአብሔር በግ ፤ የእንግዶች ማረፊያ የታጣለት የዓለሙ ፈጣሪ - በከብቶች ግርግም በጨርቅ ተጠቅልሎ የሚያለቅስ የመለኮት ትሥጉት ፤ ከፈጠራቸው ሰዎች ርዳታ ፈልጎ ጨቅላ ሣንባውን ለማሰራት የሚታገል ደካማ ሕጻን ሆኖ ተገለጠ ። “ሕይወት በእርሱ ነበረች፤ ይህች ሕይወት የሰው ብርሃን ነበረች።” በፊልፕ ያንሲ አገላለጽ “ነገሥታትን እንዳሻው መትከልና መንቀል የሚችለው አምላክ ፥ መናገር ወይም ጠጣር ምግብ መብላት ወይም የፊኛ ከረጢቱን መቈጣጣር የማይችል ሆኖ በአንዲት አይሁዳዊት ወጣት ሴት እቅፍ እንክብካቤ ሲደረግለት” ማየት ምንኛ ይደንቃል? እርሱ በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን ሊለቀው እንደማይገባ አድርጎ ሳይቆጥረው... ድኩሙን ሥጋ ለብሶ የባሪያን መልክ ይዞ ፣ በሰውም አምሳል ተገኝቶ፣ ራስን ባዶ ማድረግ እንዴት ያለ ትሕትና ነው?! ይኼስ ፍቅር በምን ይመሰላል? ምንስ ይገልጸዋል?! መልካም የልደት መታሰቢያ በዓል ይሁንላችሁ! -- Fitsuman Girma @nazrawi_tube
Show more ...
2 140
13
🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄 🎄 🎄 🎄 🎄 🎄 🎄 🎄 🎄 🎄🎄🎄🎄 🎄🎄🎄🎄 🎄 🎄 🎄🎄 🎄 🎄 🎄 🎄 🎄 🎄 🎄 🎄 🎄 🎄🎄🎄 🎄 🎄 🎄🎄🎄🎄🎄 🎄 🎄 🎄 🎄 🎄 🎄 🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄 🎄 🎄 🎄 🎄 🎄🎄🎄 🎄🎄🎄 🎄 🎄 🎄🎄🎄 🌲🌲🌲🌲 🌲🌲🌲🌲 🌲 🌲 🌲 🌲 🌲 🌲🌲🌲🌲 🌲 🌲 🌲 🌲 🌲 🌲 🌲 🌲 እ ን ኳ ን አ ደ ረ ሰ ን። #መልካም_የክርስቶስ_ልደት። 🌈ይሄን ለሚወዱት ሁሉ Forward ያድርጉ ╔══❖•◈•❖══╗ ( @nazrawi_tube ) ( @nazrawi_tube ) ╚══❖•◈•❖══╝ 💒ለበለጠ ቤተሰብ ይሁኑ💒 [ተ🀄️ላ🀄️ሉን]
Show more ...
2 593
44
🎄እንኳን ለጌታችን ለመዳሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ።🎄 አዳዲስ እና ቆየት ያሉ የገና(የጌታችንን ልደት የሚያስታውሱ) ዝማሬዎችን ለማገኘት ይቀላቀሉን 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
1 565
3
ይህ ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው! የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል እርቅ የመፈጸሙ ዋዜማ የተበሠረበት ፣ እግዚአብሔር ሰው በመሆን የምህረቱን ታላቅነት ያወጀበት አስገራሚና አስደናቂ ቀን ነው። አበው፦ "እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል" ይላሉ። "የሰው ልጅ ድኅነት በጽንሰት ተጀመረ፣ በልደት ተበሠረ፣ በስቅለት ተፈጸመ፤ በትንሣኤ ተደመደመ" ሲሉም ስለሁኔታው ይገልጻሉ። የአምላክ ሰው የመሆን ምስጢር በእርግጥም ታላቅ ነውና "ያለጥርጥር ታላቅ ነው" ተብሎ ተጽፏል፡፡ ኢየሱስ “በሥጋ የተገለጠ፣ በመንፈስ የጸደቀ፣ ለመላእክት የታየ፣ በአሕዛብ የተሰበከ፣ በዓለም የታመነ፣ በክብር ያረገ” ጌታ እንደሆነም መንፈስ ቅዱስ ለቅዱሳኑ አብርቶላቸዋል። (1ኛ.ጢሞ 3÷16) ። ክብር ለታላቁ ስሙ ይሁንና እኛም በስሙ የተቀበልነው መንፈስ ይኼንኑ መስክሮልናል ። የጌታ እናት ቅድስት ማርያም ይህ ምህረት የሚመጣበት አዳኝ ከእርሷ እንደሚወለድ ከመልአኩ ገብርኤል በሰማችና ባመነች ጊዜ የተናገረችው ቃልም ልብን በደስታ ያሞቃል። ማርያም፦ "የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና፦ እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው። ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል። በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤ ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤ ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤ የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል። ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል"...... ያለችበትን የወንጌል ክፍል ባነበብኩት ቁጥር አንዳች ለየት ያለ የደስታ ስሜት ይወረኛል። (ሉቃ.1÷48-55) አሁንም የሆነው እንዲሁ ነው። እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ©ሽመልስ ይፍሩ @nazrawi_tube
Show more ...
2 444
13
ውድ የናዝራዊ Tube ቻናል አባላት እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!! መልካም በዓል! ናዝራዊ ትዩብ @nazrawi_tube
1 975
2
Watch "ልዑል ተወለደ | Addis Ababa MKC choir| Amharic Christmas song" on YouTube https://youtu.be/g4v3O99imlU
ልዑል ተወለደ | Addis Ababa MKC choir| Amharic Christmas song
#Thanks for watching for new gosple songs pleas subscribe our channel https://www.youtube.com/channel/UCxFBvvBoNVtSyTEQbp4MScQ/ our channel on telegram https://t.me/nazrawi_tube on fb https://www.fb.com/nazrawitube ista https://www.Instagram.com/qineenazema pleas stay connected #እስከ_ዛሬ_ድረስ_በዩቲዩብ_ቻናላችን_የተለቀቁ:- አዳዲስ መዝሙሮች👇 https://www.youtube.com/playlist?list=PLOPv2HHmFlVf7xiY9by5FsmLkx5XV5NBo ቆየት ያሉ ድንቅ ዝማሬዎች👇 https://www.youtube.com/playlist?list=PLOPv2HHmFlVdeFSRpOtumGaAcMlvxkYJy በኳየራት ብቻ የተዘመሩ ድንቅ ዝማሬዎች👇 https://www.youtube.com/playlist?list=PLOPv2HHmFlVcibFG87amLXiuo0kZiFQYK ድንቅ መልዕክት ያላቸው ስብከቶች👇 https://www.youtube.com/playlist?list=PLOPv2HHmFlVdKLg0SZwWzW9yPnidc1trb
2 046
5
🎄 #የማለዳ_ስንቅ እንደተጠማች ዋላ | Apostle Yohannes Girma Share⤵️ 📢 @nazrawi_tube 📢 @nazrawi_tube Join⬆️

እንደተጠማች_ዋላ_ሐዋርያ_ዮሐንስ_ግርማ_Endetetemach_Wala_Apostle_Yoha_ZWDGt1PvUkg.mp3

29
1
🎄 #የማለዳ_ስንቅ የክርስትና ሕይወት ውስጡ ምን አለው (as a package)? ወደ እርሷ የምንገባባት የእግዚአብሔር መንግሥት ምን ትመስላለች? ይህንን ጥያቄ በግሩም ሁኔታ የሚመልስልን ዘዳግም 11፥10-12 ነው። እንዲህ ይላልና:- ➣ትወርሳት ዘንድ የምትገባባት ምድር፥ በአትክልት ስፍራ እንደሚዘሩ ዘርህን እንደዘራህባት፥ በእግርህም እንዳጠጣሃት፥ እንደ ወጣህባት እንደ ግብፅ ምድር አይደለችም። ➣ነገር ግን ትወርሱአት ዘንድ ተሻግራችሁ የምትገቡባት (by faith) ምድር ኮረብታና ሸለቆ ያለባት አገር ናት፤ በሰማይ ዝናብ ውኃ ትረካለች። ➣አምላክህ እግዚአብሔር የሚጐበኛት አገር ናት፤ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የአምላክህ የእግዚአብሔር ዓይን ሁልጊዜ በእርስዋ ላይ ነው። 1.እንደ ግብፅ ምድር አይደለችም (በመርሕ ማለትም በጽድቅና በቅድስና ነው የሚኖረው)፤ 2.ኮረብታና ሸለቆ የበዛባት ናት (ውጣ ውረድ ይኖራል ቢሆንም የጌታ ረድኤት ከእኛ ጋር ነው)፤ 3.በሰማይ ዝናብ ትረካለች (የጌታ ጸጋና ረድኤት የመንፈስ ቅዱስ ጉብኝት ሳይቋረጥ እለ)፤ 4.የእግዚአብሔር ዓይኖች ሁሌም በእኛ ላይ ናቸው (ባይሰማምን ሆነ ባይመስለንም እንኳ)። ለዚህ ነው ጌታ "አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።" (መዝ.32:8) የሚል ታላቅ ተስፋን የሰጠን! ታዲያ በዚህ መንግሥታዊ ሥርዓት ውስጥ እንደ ጌታ ሐሳብ እንድንኖር በዋናነት ምን እናድርግ? ያንን በተመለከተ ዘዳግም 11፥18 እንዲህ ብሎ ይመክራል:- "እንግዲህ እነዚህን ቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁ አኑሩ፤ እነርሱንም ለምልክት በእጃችሁ ላይ እሰሩአቸው፥ በዓይኖቻችሁም መካከል እንደክታብ ይሁኑ።"! ሌላው ሁሉ ከዚህ ትጋት ይመነጫል! ጌታ ሆይ እንደ ቃልህ እንድንኖር ጸጋህን አብዛልን! --- Dr. Bekele Brihanu @nazrawi_tube @nazrawi_tube
Show more ...
38
0
🎄 በማለዳ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይባረኩ 😊 ከተባረኩበት ያጋሩ!🎄
37
0
🎄 #የማለዳ_ስንቅ የመንፈስ ረሃብ የሚለቅ አምልኮ አድምጡልኝ! @nazrawi_tube @nazrawi_tube

file

778
5
🎄 #የማለዳ_ስንቅ በፊትህ ገበታን አጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ራሴን በዘይት ቀባህ! የእግዚአብሔር ቃል በመዝሙር 23፣ “በፊትህ ገበታን አጋጀህልኝ” ይልና ወዲያው ቀጠል አድርጐ፣ “በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፡፡” (ቁ.5) ብሎ ይናገራል፡፡ የሚገርም ነው፤ ይህ ቃል በአንድ በኩል የሚነግረን የተዘጋጀ ገበታ እንዳለና ሆኖም ግን ግብዣው ላይ እንዳንታደም የሚከለክሉ ጠላቶች እንዳሉ ነው፡፡ ገበታው የሚወክለው በጸሎትና ከቃሉ ጋር በሚኖረን ኅብረት (fellowship) ከጌታ የምናገኘው ሰፊ ባርኮት (ምሕረት፥ ጸጋና ረድኤት) ሲሆን፥ ሌሎችም ብዙ ጥቅምች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ገበታው ላይ የሚቀርበው ምግብ የማያልቅና የማይነጥፍ እንደ ሆነ በተለያየ ስፍራ መስክሯል፡፡ ምግቡ ሕይወት ያስከፈለ ቢሆንም፣ ለእኛ የቀረበው ግን በነጻ ነው፡፡ በራሴ ሕይወት ሳየው፣ ገበታው ላይ መታደሙን ቀላል እንዳልሆነ ደጋግሜ አይቼዋለሁ፤ ምክንያቱም ውጊያ አለውና፡፡ ዳዊት ጠላቶች እንዳሉት ተናግሯል፡፡ ለውጊያ ጣቶቹን ሰልፍ ያስተማረው ጌታ አምላክ፣ በጠላቶቹ ፊት ነው ራሱን በዘይት የቀባው፡፡ በእኛም ሕይወት ጠላቶቻችን ያሉት አጠገባችን ነው፡፡ በጸሎትና ከቃሉ በሚደረግ ኅብረት ነፍሳችን እንዳትከናወንና መንፈሳችን እንዳይበረታ፣ የማያደረጉት ነገር የለም፡፡ የጸሎትን ጥቅም በማሳነስ፣ ፋታ አግኝተን እንዳንጸልይ በማዋከብ፣ መጸለይ ስንጀምር አእምሮአችን ብትንትን ብሎ የረባ ጸሎት ሳንጸልይ እንድንነሣና አንዳንድ የሠራናቸውን በደሎች በማስታወስ በሙሉ እምነት ጸሎታችንን ወደ ጌታ እንዳናቀርብ እያደረጉ ይገዳደሩናል፡፡ ማለትም ውጊያው እንደ ቀላል መታየት የለበትም ማለቴ ነው፡፡ ጠላቶቻችንን የምናሸንፍበት አንዱ ዋና መንገድ ተዘውታሪ በሆነ ዲሲፕሊን ነው፡፡ ለምን ጥቂት ደቂቃዎች አይሆንም፣ በጌታ ፊት የምናሳልፈው ጊዜ መልካም እንደ ሆነ ማሰቡ ተገቢ ነው (ጥቂት ደቂቃ ብቻ ስለ ጸለይን ራሳችንን መኮነን አይገባንም)፡፡ በእርሱ ፊት የምንሆንባቸው ጊዜያት የባከኑ አይደሉምና፡፡ በነገራችን ላይ ጸሎትን አንድ ቋሚ ቦታና ስፍራ ብቻ ካላደረግነው አእምሮአችን የማይረካ ሰዎች፣ ስልቶቻችን እየቀያየርን አዳዲስ መንገዶችን መልመድ ያስፈልገናል፡፡ በተለይ ጊዜ በተጣበበት አሜሪካ የምንኖር ሰዎች፣ ከጌታ ጋር ለመገናኘት ልዩ ልዩ ዘዴዎች ያስፈልጉናል ብዬ አምናለሁ፡፡ እየነዳን፣ ሻወር እየወሰድን፣ ጋደም ብለን ወይም ምናልባት እየተራመድን የሚባክነውን ጊዜ በጸሎት ማሳለፍ እንችላለን፡፡ በግሌ በተለይ መጸለይ የማልችልበት ቦታ ስሆን፣ በወረቀት ላይ በውስጤ ያለውን ጸሎትና ተማጽኖ እጽፈዋለሁ (ፈረንጆቹ Journaling ይሉታል)፡፡ በሥነ ግጥም መልክ ጸሎቴን ወደ ጌታ የማቀርብበት ጊዜ አለ፡፡ በነገራችን ላይ የጸሎት መዝሙሮችን ከፍተን አብረን ብንዘምር (በተለይ መኪና ስንነዳ)፣ ግሩም የሆነ የጸሎት መንፈስ ነው የሚኖረን፡፡ በግሌ አብዛኛውን ጊዜ ምርጫዬ የጸሎት መዝሙር ነው፤ ያድሰኛል፣ ወደ ጸሎትም ያንደረድረኛል፡፡ በዚህና በሌሎች የተለያዩ ዘዴዎች ከእርሱ ጋር የምንገናኝባቸውን ጊዜያት ማስፋት ይቻላል፡፡ እርሱ ሊራቡት፣ ሊጠሙት፣ ሊፈለግና ሊናፈቅ የሚገባው አምላክ ነውና፡፡ እግዚአብሔር ሆይ፣ የጸሎትን መንፈስ አፍስስልን! --- በቀለ ብርሃኑ (ዶ/ር) @nazrawi_tube @nazrawi_tube
Show more ...
760
2
🎄 በማለዳ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይባረኩ 😊 ከተባረኩበት ያጋሩ!🎄
621
1
ከሞላ ጎደል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መላእክት በሚገለጡባቸው ቦታዎች ሁሉ የሚናገሩት የመጀመሪያ ቃል “አትፍራ” (አትፍሪ/አትፍሩ) የሚል ነው፡፡ ይህ መናገራቸው እምብዛም አያስደንቅም፡፡ ልዕለ ተፈጥሮአዊው አካል መሬት ከተሰኘችው ፕላኔት ጋር ሲነካካ ተመልካቾቹ ላይ አስበርጋጊ ፍርሀት ወድቆባቸው ከመሬት መደፋታቸው አይቀርምና፡፡ ወንጌላዊው ሉቃስ ግን እግዚአብሔር በማያስፈራና በማያስደነግጥ ቅርጽ (መልክ) መሬት ላይ መከሰቱን ይነግረናል፡፡ በከብቶች በረት ውስጥ በተወለደውና ከብቶቹ ምግባቸውን በሚበሉበት ስፍራ በተኛው በኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር እኛን ሳያስፈራ የሚገለጥበትን መንገድ አገኘ፡፡ ከአራስ ልጅ በላይ ማንንም የማያስፈራ ምን ነገር አለ? እንደገና ሕፃን መሆንን - መናገር፣ ጡንቻን ማቀናጀት፣ ጠንካራ ምግብ መመገብ፣ ፊኛን መቆጣጠር አለመቻልን - አስቡት እስቲ፡፡ ይህም እግዚአብሔርን ስላለፈበት “ራስን ባዶ የማድረግ” ሂደት ትንሽ ፍንጭ ይሰጣችኋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን ኢየሱስ በምድር ላይ ሰውም፣ አምላክም ነበር፡፡ በአምላክነቱ ተአምር ማድረግ፣ ኀጢአትን ይቅር ማለት፣ ሞትን ማሸነፍ እና ነገን መተንበይ ይችላል፡፡ ኢየሱስ ይህን ሁሉ ሲያደርግ በዙሪያው በነበሩ ሰዎች ላይ ፍርሀትና ድንጋጤ ያድርባቸው ነበር፡፡ እግዚአብሔርን በብሩህ ዳመና እና በእሳት ዓምድ በምናባቸው መሣል በለመዱት አይሁዳውያን ዘንድ ግን ይህ ብዙ ግራ መጋባትና ውዝግብ አስከትሏል፡፡ በቤተ ልሔም የተወለደ ሕፃን፣ የአናጢ ልጅ፣ ከናዝሬት የመጣ ሰው እንዴት ከእግዚአብሔር የተላከ መሲሕ ሊሆን ይችላል? የኢየሱስ ሰው-ነት እንቅፋት ሆነባቸው፡፡ ነገሩ እንቆቅልሽ የሆነባቸው ሰዎች ኢየሱስ ለአገልግሎት በሄደበት ሁሉ ከዙሪያው አይጠፉም ነበር፡፡ ሉቃስ 2 እንደሚያሳየን ግን እግዚአብሔር የኢየሱስን ማንነት ቀደም ብሎ አስታውቋል፡፡ መስክ ላይ የነበሩት እረኞች የመላእከት መዘምራን ያስተላለፉላቸው መልእክት ጥሩ ዜና እንደሆነ ጥርጥር አልነበራቸውም፡፡ አንድ ሽማግሌ ነቢይ እና አንዲት አረጋዊት ነቢይም ማንነቱን ተረድተውታል፡፡ በቤተ መቅደስ የነበሩ ተጠራጣሪ መምህራን እንኳ ተደንቀውበታል፡፡ እግዚአብሔር ለምን ራሱን ባዶ አድርጎ ሰው ሆነ? መጽሐፍ ቅዱስ የተለያዩ ምላሾችን ያቀርብልናል፤ አንዳንዶቹ ነገረ መለኮታዊ ሲሆኑ ሌሎቹ ተግባራዊ ናቸው፡፡ ጌታ ኢየሱስ በወጣትነቱ መቅደስ ውስጥ የአይሁድ ራባዮችን ሲያስተምር ማየቱ አንዳች ፍንጭ ይሰጠናል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ተራ ሰዎች ከሚታይ አምላክ ጋር መነጋገር፣ መወያየት፣ መከራከር ቻሉ፡፡ ኢየሱስ ወላጆቹን፣ አንድን የአይሁድ መምህር፣ አንዲት ድኸ መበለትን - በአጠቃላይ ማንንም ሰው ማናገር ይችላል፤ “አትፍሩ” የሚል ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልገው፡፡ በኢየሱስ፣ እግዚአብሔር ቅርባችን ሆነ፡፡ ፊሊፕ ያንሲ (Meet the Bible)
Show more ...
2 083
8
🎄#የማለዳ_ስንቅ የፍቅር ስጦታ | WKUEvaCSF New song መልካም በዓል!🎄 @nazrawi_tube @nazrawi_tube @nazrawi_tube

የፍቅር ስጦታ WKUEvaCSF.mp3

2 075
10
🎄#የማለዳ_ስንቅ ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ ለመልካም ሆነልኝ! በምንማረውና በንባብ አስተውሎት ከምናገኘው በተጨማሪ የምናልፍባቸው ፈታኝና አስጨናቂ የሕይወት ጎዳናዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ክፍሎች በጥልቀትና ልዩ በሆነ መንገድ እንድናያቸው ያደርጉናል፡፡ ስለሆነም ነው ዳዊት “እኔ ሳልጨነቅ ሳትሁ፤ አሁን ግን ቃልህን ጠበቅሁ።/ ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ።” (መዝ.119፥67፣71) ብሎ የመሰከረው፡፡ በዚህ ረገድ ጀርመናዊው የፕሮቴስታንት እንቅስቃሴ መሪ ማርቲን ሉተር የሚገርም ምስክርነት አለው፡፡ እንዲህ የሚል፡- ➤ “For as long as God’s word becomes know through you, the devil will afflict you, will make real doctor (teacher of doctrine) of you, and will teach you by his temptations to seek and to love God’s word. For I myself….owe my papists (ትላልቆቹ ቄሶች) many thanks for so beating, pressing, and frightening me through the devil’s raging, that they have turned me into a fairly good theologian, driving me to a goal I should never have reached.” ➤God has Hi wise and holy purposes for bringing His loved ones to the brink of despair (see also 2cor.1:8-10). (John Piper, When I Don’t Desire God, 135) ሉተር በጠቀሰው በዚህ በ2ቆሮንቶስ 1፥8-11 በእነጳውሎስ ሕይወት በዚያ እጅግ ከባድ መከራ መኻል የተገለጠው የጸጋ ስጦታ ያስደንቃል (ከመከራው በፊት ለምን አያድናቸውም የሚል አይጠፋም እኮ!)፡- →በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ታውቁ ዘንድ እንወዳለንና፤ ስለ ሕይወታችን እንኳ ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር፤ →አዎን፥ ሙታንን በሚያነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን፥ እኛ ራሳችን የሞትን ፍርድ በውስጣችን ሰምተን ነበር። →እርሱም ይህን ከሚያህል ሞት አዳነን፥ ያድነንማል፤ እናንተም ደግሞ ስለ እኛ እየጸለያችሁ አብራችሁ ስትረዱን፥ በብዙ ሰዎች በኩል ስለ ተሰጠን ስለ ጸጋ ስጦታ ብዙዎች ስለ እኛ ያመሰግኑ ዘንድ፥ ወደ ፊት ደግሞ እንዲያድን በእርሱ ተስፋ አድርገናል። ኦ ጌታ ድንቅ ነው፡፡ አሠራሩ ከአእምሮ በላይ ነው! --- በቀለ ብርሃኑ (ዶ/ር) @nazrawi_tube
Show more ...
1 203
3
🎄 በማለዳ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይባረኩ 😊 ከተባረኩበት ያጋሩ!🎄
975
1
ፍቅር ማለት ሌላውን ከነጉድለቱ መቀበል ነው። 🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑 🌑🌒🌕🌕🌘🌑🌒🌕🌕🌘🌑 🌑🌔🌕🌕🌕🌑🌕🌕🌕🌖🌑 🌑🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌑 🌑🌔🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌖🌑 🌑🌒🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌘🌑 🌑🌑🌒🌕🌕🌕🌕🌕🌘🌑🌑 🌑🌑🌑🌒🌕🌕🌕🌘🌑🌑🌑 🌑🌑🌑🌑🌒🌕🌘🌑🌑🌑🌑 🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑
160
1
ፍቅር ማለት ሌላውን ከነጉድለቱ መቀበል ነው። 🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑 🌑🌒🌕🌕🌘🌑🌒🌕🌕🌘🌑 🌑🌔🌕🌕🌕🌑🌕🌕🌕🌖🌑 🌑🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌑 🌑🌔🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌖🌑 🌑🌒🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌘🌑 🌑🌑🌒🌕🌕🌕🌕🌕🌘🌑🌑 🌑🌑🌑🌒🌕🌕🌕🌘🌑🌑🌑 🌑🌑🌑🌑🌒🌕🌘🌑🌑🌑🌑 🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑
629
4
💐 #የማለዳ_ስንቅ ናፈቀኝ || Yohannes Girma ft. Zetseat Choir እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

ናፈቀኝ_Nafekegn_Live_Version_Yohannes_Girma_ft_Zetseat_C_dRTDcvw6Pog.mp3

2 665
14
💐 #የማለዳ_ስንቅ ትላንት፣ ዛሬ እስከ ለዘላለም ያው ለሆነው ጌታ ኢየሱስ እንዴት መኖር አለብን? ዕብ. ፲፫÷፩-፳፭ ፩. በወንድማማች መዋደድ፡- የወንድማማች መዋደድ መገለጫዎች 1. እንግዳ መቀበል 2. የታሰሩትን መጠየቅ 3. የተጨነቁትን ማሰብ ፪. ትዳርን በማክበር ፡- መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ትዳር 2 ኃይለቃሎች "ክቡር እና ንጹሕ" ናቸው። 1. ክቡር፡- በ1 ወንድና 1ዲት ሴት ስምምነት በእግዚአብሔር መካከለኛነት የሚደረግ ሲሆን 2. ንጹሕ፡- ሴሰኝነትና አመንዝራነት እንዲሁም ሌላ ድብቅ ሕይወት የሌለበት መሆኑን ያመለክታል። ፫. ገንዘብን ባለመውደድ፡- ይህ በሐብትና ንብረት አለመመካትን ያመለክታል። በሐብት የማንመካበት ምክንያት እግዚአብሔር ራሱ "አልለቅህም ከቶም አልተውህም።" ስላለ ነው። የኛ ትምክህት ደግሞ "ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል።" ይሆናል። ፬. ዋኖቻችንን በማሰብ 1. የምዕመናን ኃላፊነት፡- መታዘዝ፣ መገዛትና የእምነት ምሳሌያቸውን መከተል 2. የመሪዎች ኃላፊነት፡- መልካም የእግዚአብሔር ቃል ማስተማርና ስለነፍሳት ሁሉ መትጋት ፭. በልዩ ልዩ እንግዳ ትምህርት አለመወሰድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሌ ያው ስለሆነ የትምህርቶች መለዋወጥ እንደማይቀይሩት ማወቅ ፮. መስዋዕት ማቅረብ፡- የሚናቀርበው መስዋዕት 1. የከንፈራችን ፍሬ- ምስጋናውን፣ ታላቅነቱንና ጌትነቱን መመስከር 2. መልካም ሥራ- ለሌሎች መስጠትና ማካፈል ፯. የፀሎት ሕይወት ፡- 1. ምዕመናን ለመሪዎች መፀለይ አለባቸው 2. መሪዎች ለምዕመናን መፀለይ አለባቸው እነዚህ 7 ነጥቦች ለማይለወጠው ጌታ እንዴት መኖር እንዳለብን የተሰጡን መመሪያዎች ናቸው። --- በአንድ ወቅት ዶ/ር መልሳቸው መስፍን ከስተማሩት ትምህርት የተወሰደ @nazrawi_tube @nazrawi_tube
Show more ...
2 272
14
💐 በማለዳ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይባረኩ 😊 ከተባረኩበት ያጋሩ!
1 773
0
ለተከታታይ 3 ቀናት ተቋርጦ የነበረው #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ነገ ይቀጥላል።😊 እያነበባችሁ ግን አይደለም አንብቡ ድንቅ ድንቅ መልዕክቶች ነው እየለቀቅን ያለነው። ተባረኩ!
1 951
1
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። MERRY CHRISTMAS 🎄🎄🎄🎄 ----- የቻናላችንን ሎጎ እንዲህ ያሳመረልን AD graphics ነው። ማሰራት የትምፈልጉ የቴሌግራም ቻናል ባለቤቶች👇🏾 @ReformedAbeni - 251916698510
2 407
4
የዛሬ ሳምንት (አርብ፣ ታህሳስ 22)፣ በሀልዎት ቤተክርስቲያን፣ ከምሽቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ለአንድ ሰዓት ከሠላሳ ደቂቃ የሚቆይ "እንደገና" የተሰኘ የመዝሙር ድግስ ተሰናድቷል:: እርስዎ (ከወዳጆችዎ ጋር) እንዲገኙ እና ጌታን እንዲያመሰግኑ ከፍቅር እና ፈገግታ ጋር ተጋብዘዋል:: አድራሻ:- ወሎ ሠፈር፣ ጎርጎርዮስ አደባባይ፣ ፊውቸር ታለንት ትምህርት ቤት አጠገብ:: ---- @nazrawi_tube
2 679
4
💐 #የማለዳ_ስንቅ እግዚአብሔር አለቴ | Ayda Abraham New song እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

እግዚአብሔር አለቴ Ayda Abraham.mp3

1 907
7
💐#የማለዳ_ስንቅ #ብዙዎቻችን ዲያብሎስን መቃወም ማለት "የተቃውሞ ጸሎት" ማድረግ ወይም ድምጽን ከፍ አርጎ አንድ ሺህ ጊዜ በኢየሱስ ስም እያሉ #መጮህ ይመስለናል፡፡ እንደዛ ግን አይደለም እንደዛ ስላረግን ዲያቢሎሎስን ተቃዉመናል ዉጤት እናመጣለን ማለት አይደለም ይልቁኑ ጊዜያችንን ዉጤት በማያመጣ ነገር አባክነናል ነዉ የሚባለዉ። "እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን #ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል" (ያዕ 4፡7) እዚህ ጥቅስ ውስጥ "ተቃወሙ" የሚለውን ቃል የግሪኩ መጽሀፍ ቅዱስ "ἀνθίστημι"( አንቲስቴሚ) ብሎታል፥ ትርጉሙም "በተቃርኖ መቆም" ማለት ነው፡፡ ይህም በዲያብሎስ ሃሳብና ሽንገላ ፈጽሞ አለመስማማትን ያመለክታል፡፡ ያዕ 4፡7ን በሌላ አገላለፅ ብናስቀምጥ "ለእግዚአብሔር እሺ በሉ፤ ለዲያብሎስ ሽንገላ ግን እንቢ በሉ" እንደማለት ነው፤ በእግዚአብሔር ቃል መስማማትና በዲያብሎስ የማታለያ ሃሳብ ግን አለመስማማት ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ፦ ጠላት ለክፉ ስራ ሲቀሰቅስህ ፥ "እኔ ለክፉ ስራ ሞቻለሁ፥ በአዲስ ሕይወት እመላለስ ዘንድ ለጽድቅ ሕያው ነኝ" በማለት በተረዳቹት የወንጌል እውነት ጸንታቹ በመቆም የጠላትን ማባበያ ትቃወማላቹ ማለት ነው፡፡ ጠላት ሊኮንንህ ሲመጣ በክርስቶስ ኩነኔ የሌለብህ ጻድቅ መሆንህን ትናገረዋለህ ማለት ነው፡፡ ➥ "የዲያብሎስን ሽንገላ #ትቃወሙ_ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።" (ኤፌ 6፡11) ይሄ ጥቅስ ደግሞ የዲያብሎስን ሽንገላ ለመቃወም #የእግዚአብሔርን_ሙሉ_የጦር_ትጥቅ መልበስ እንዳለብን ይናገራል፡፡ ትጥቅ #የእግዚአብሔር እንጂ እኛው ለእኛ በልካችን የምንሰፋው አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሥራ ለእኛ ያሰናዳውን ትጥቅ ነው የምንታጠቀው፡፡ በኤፌ 6:11 ላይ "ዕቃ ጦር ሁሉ" የሚለው ቃል (phrase) ግሪኩ "ፓኖፕሊያ" በሚል አንድ ቃል ይገልጸዋል፡፡ ፓኖፕሊያ በአንዴ ሁሉን ያሟላ #ሙሉ_ትጥቅ (complete armor) ነው፡፡ በዚህ ሙሉ ትጥቅ ውስጥ የተካተቱ መሣሪያዎች ኤፌ 6፡14-17 ተዘርዝረዋል፡፡ #የእውነት መታጠቂያ ቀበቶ- የጠላትን ውሸት የምንመክተው በእግዚአብሔር ቃል እውነት ነው፡፡ #የጽድቅ ጥሩር- የጽድቅ ጥሩራችን የተረዳነው የጽድቅ እውነት ነው፡፡ ጥሩር ደረት አካባቢ የሚረግ ትጥቅ ነው፡፡ ልብ እንዳይጎዳ ይከላከላል፡፡ መንፈሳዊ ጥሩራችን የውስጥ ሕሊናችንን ከጠላት ክስ የምንከላከልበት የጽድቅ እውነት ነው፡፡ #የሰላም ወንጌል፡ ወንጌላችን የሰላም ወንጌል ነው፡፡ ያለመታወክ ተረጋግተንና ጸንተን መቆም የምንችለው በተረዳነው የሰላም ወንጌል ነው፡፡ #የእምነት ጋሻ- የትኛውንም የጠላት የክፋት ፍላጻ መከላከል የምንችለው ባመንነው እምነት ነው፡፡ #የመዳን ራስ ቁር- ስለመዳናችን የተረዳነው እውነትና በዚህ እውነት መመላለሳችን ለእኛ ጭንቅላታችንን የአስተሳሰብ ክፍላችንን ይከላከልልናል፡፡ እነዚህ ነገሮች ሁሉ በክርስቶስ የእኛ ናቸው፡፡ በየቀኑ እነዚህን ነገሮች መልበስ በነዚህ ነገሮች መሸፈን ነው የሚጠበቅብን፡፡ #ጠቅለል ስናደርግ ዲያብሎስን መቃወም ማለት መጮህ ሳይሆን በተረዱት እውነት ጸንተቶ መቆም ማለት ነው፥ ከእግዚአብሔር ጋር መስማማት ከጠላት ውሸት ጋር አለመስማማት ማለት ነው፡፡ በተቃርኖ በመቆም በብርሀን እንገለጥ ዉጤት ከማያመጣ ከንቱ ጩኸትና ክፉ ልምምድ እራሳችንን በእግዚሀብሄር ቃል እዉነት ነጻ እናዉጣ። “በጥልቅ ለሚያስተውሉ ሁሉም ቀና ናቸው፤ ዕውቀት ላላቸውም ስሕተት የለባቸውም።” — ምሳሌ 8፥9 (አዲሱ መ.ት) ---- @nazrawi_tube @nazrawi_tube "ያጋሩ" - "ይቀላቀሉን"
Show more ...
1 898
18
💐 በማለዳ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊 ከተባረኩበት ያጋሩ!
1 546
0
💐#የማለዳ_ስንቅ እንደ ታላቅነትህ | መጋቢ ታመራት ሀይሌ እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

11 endetalkenethe.mp3

1 807
3
💐 #የማለዳ_ስንቅ በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና! በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ደጋግሜ ከማስባቸውና ከማሰላስላቸው ክፍሎች መካከል “በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና። የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና። ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና። የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና። ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና።” (ማቴ.5፥3-8) የሚለው ምንባብ አንዱ ነው፡፡ በግሌ ራስን ለመፈተሺያ ግሩም የሆነ checklist ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ በመንፈስ ድሀ መሆን ማለት በራሳችን ምንም እንዳልሆንን መረዳት ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የእርሱን ጸጋ ለመፈለግ ትልቅ የሆነ ውስጣዊ የሆነ የልብ ዝግጅት ነው፡፡ ከዚህ መርህ ቀጥሎ ነው “የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው” የሚለው መርህ የሚከለተው፡፡ ለምን? በራሳቸው ባዶ እንደ ሆኑና የጌታ ጸጋ እንደሚያስፈልጋቸው የገባቸው ሰዎች ናቸው በራሳቸው መንፈሳዊ ሁኔታ የሚያዝኑት! በመንፈስ ድሀ መሆን ማለት እውነተኛው ብልጽግና ቁሳዊው ሳይሆን መንፈሳዊ እንደ ሆነ መረዳት ነው፡፡ አዎ፣ እግዚአብሔር ዓይኑን የከፈተለት ሰው በራሱ ምንም አለመሆኑን ያስተውላል፡፡ የእግዚአብሔር ጸጋና ረድኤት እንደሚያስፈልገው ይረዳል፡፡ ያ ነው በመንፈስ ደሀ መሆን ማለት፡፡ በመንፈስ ደሀ የሆነ ሰው ትሑት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰው የሚመካበት ነገር የለውም፡፡ እናም ከእግዚአብሔር ዘንድ ትልቅ ተስፋና ባርኮት አለው፡፡ “እግዚአብሔር ለተሰበረ ቅርብ ነው፤ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል፡፡” (መዝ.34፥18) የሚል፡፡ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ጸጋን ይሰጣል፡፡” (ያዕ.4፥6) የሚል፡፡ “የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም” (መዝ.51፥17) የሚል፡፡ ይህ የልብ ትሕትና ከእግዚአብሔር ጋር connected ለመሆን እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ እግዚአብሔር ቅርብ የሆነው እንዲህ ላሉ ሰዎች ነውና! ይኼ ውስጣዊ መረዳት ነው ሰዎች ጌታን እንዲፈልጉ የሚያደርጋቸው፡፡ ደግሞም ወደ ጸሎት የሚያንደረድራቸው፡፡ “አቃተኝ፣ እርዳኝ፣ አግዘኝ፣ ሳበኝ” ብለው እንዲጮኹና እንዲቃትቱ የሚያደርጋቸው፡፡ የእርሱን ፊት ለመፈለግ ኃይል የሚሆናቸው፡፡ ይህ ጥልቅ የሆነ ውስጣዊ መረዳት በውስጣችን ከተፈጠረ እግዚአብሔር ለግላዊ ሪቫይቫይል እየሳበን ነው ማለት ነው፡፡ በመሆኑም “ሳበን ካንተም በኋላ እንሮጣለን”(መኃ.1፥4) እንለዋለን፡፡ ለመሆኑ በመንፈስ ድሆች የሆኑ ምንድነው በረከታቸው? መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ትሆናለች (ማቴ.5፥3)፡፡ ማለትም እግዚአብሔርን ያውቁታል፤ ፊት ለፊትም ያዩታል፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር አይቶ እንደ ነበረ የሚቀር ማን ነው? መልካም ቀን ተባረኩ! --- በቀለ ብርሃኑ (ዶ/ር) @nazrawi_tube
Show more ...
2 018
8
💐 በማለዳ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊 ከተባረኩበት ያጋሩ!
1 467
0
💐#የማለዳ_ስንቅ ለእኔስ ምንብሆን ቤትህ ይሻለኛል | መጋቢ ታምራት ሀይለ እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

7 meskelhe.mp3

1 684
7
💐 #የማለዳ_ስንቅ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን! የእግዚአብሔር ቃል “አቤቱ፥ በሥራህ ደስ አሰኝተኸኛልና፤ በእጅህም ሥራ ደስ ይለኛልና። አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ትልቅ ነው፥ አሳብህም እጅግ ጥልቅ ነው። ሰነፍ ሰው አያውቅም። ልብ የሌለውም ይህን ያስተውለውም። /A senseless man doesn’t know, fools do not understand (NIV)” (መዝ.92፥6) ብሎ ይናገራል። ለምንድነው ሰነፍ የማያውቀው፣ የማያስተውለውም? የእግዚአብሔር ቃል እንደሚነግረን፣ ልቡናው ስለ ታወረ ነው፤ “ለእነርሱም የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ።” (2ቆሮ.4፥6)፡፡ አሳቡ ስለ ታወረ አያስተውልም! ታዲያ መፍትሔው ምንድነው? ሰነፍ ያስተውል ዘንድ የእግዚአብሔር ብርሃን ልቡ ላይ ይበራለት ዘንድ ያስፈልጋል (መዝ.18፥28)፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ለውጥ ዳግም መወለድ (regeneration) ይለዋል፤ “ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፡፡” (1ጴጥ.1፥3) ብሎ የሚገልጸው ይህንን ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስም ለአይሁድ አለቃ ለኒቆዲሞስ በግልጽ፣ “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም፡፡” (ዮሐ.3፥3) ብሎታል! ይህ ብርሃን በዳግም ውልደት አንዴ ካገኘን በኋላ እየቀጠለና እየደመቀ ይበራልን ዘንድ የጥበብና የመገለጥ መንፈስ ያስፈልገናል፤ የኤፌሶን አማኞች “የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው” (ኤፌ.1፥17-19) የተባሉትም በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ ይህ ማስተዋልና መረዳት እየጨመረ ነው የሚሄደው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ይህን አስመልክቶ እንዲህ ይላልና፡-“ከእናንተ የሆነ የክርስቶስ ባሪያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይጋደላል።” (ቈላ.4፥12)፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ለእነዚሁ ለቈላስይስ አማኞች እንዲህ ብሏቸዋል፡-“ልባቸው እንዲጸናና፥ በፍቅርም ተባብረው በማስተዋል ወደሚገኝበት ወደ መረዳት ባለ ጠግነት ሁሉ እንዲደርሱ የእግዚአብሔርንም ምሥጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ እጋደላለሁ።” (ቈላ.2፥2)፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈሳዊ ማስተዋል (spiritual understanding) እጀግ ግድ ስለሚለው ነው፣ “ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ፤ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ። ከፍ ከፍ አድርጋት፥ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ ብታቅፋትም ታከብርሃለች። ለራስህ የሞገስ አክሊልን ትሰጥሃለች፥ የተዋበ ዘውድንም ታበረክትሃለች።” (ምሳ.4፥7-9) ብሎ የሚመክረው፡፡ ጌታ ሆይ፣ እንድናስተውል እርዳን! --- በቀለ ብርሃኑ (ዶ/ር) @nazrawi_tube
Show more ...
1 637
7
💐 በማለዳ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊 ከተባረኩበት ያጋሩ!
1 387
0
💐 #የማለዳ_ስንቅ የአይኖቻችን ማረፊያ | salem zema እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

FrayTV_Salem_Zema_የአይኖቻችን_ማርፊያ_New_Ethiopian_Amharic_Protestant.m4a

1 569
10
💐 #የማለዳ_ስንቅ ቅድስና የሚያስፈልገን ለምንድነው? (ለምንድነው የምንቀደሰው?) ቅድስና ግባችሁ ለሆነ አንባቢዎቼ ለምን መቀደስ እንደሚያስፈልገን አራት ምከንያቶች እነሆ፡- ✏የእግዚአብሔር ቃል ስለሚያዝዘን ነው፤ “ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤ ከዝሙት እንድትርቁ፥ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ፥ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን ዕቃ በቅድስናና በክብር ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ፤ አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ ወንድሙንም አያታልል። ለርኵሰት ሳይሆን እግዚአብሔር በቅድስና ጠርቶናልና።” (1ተሰ.4፥3-7) ✏ክርስቶስ ወደ እዚህ ምድር ከመጣባቸው ዓላማዎች አንዱና ዋናው ተልዕኮው ቅድስና ስለ ሆነ ነው፤ “ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ።” (ኤፌ.5፥25-27) ✏ቅድስና በክርስቶስ አምነን እንደዳንን ትክክለኛው ማረጋገጫ ስለ ሆነ ነው፤ “ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።…..ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።” (1ጴጥ.1፥19፣ 23) ✏እውነተኛው የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ማረጋገጫው ምልክቱ (sound evidence) እሱ ነው፤ “ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን ደግሞ ያደርጋል፥ ኃጢአትም ዓመፅ ነው። እርሱም ኃጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፥ በእርሱም ኃጢአት የለም። በእርሱ የሚኖር ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፤ ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ አላየውም አላወቀውምም። ልጆች ሆይ፥ ማንም አያስታችሁ፤ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው።” (1ዮሐ.3፥4-7) We must be holy, because our present comfort depends much upon it. J.C.Ryle መልካም ቀን ተባረኩልኝ! --- በቀለ ብርሃኑ (ዶ/ር) @nazrawi_tube
Show more ...
1 939
15
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊 ከተባረኩበት ያጋሩ!
1 365
0
#ሰበር_ዜና በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መንፈሳዊ መፅሐፍ የሚያቀርብ ተወዳጅ የቴሌግራም ቻናል ተከፈተ!አሁኑኑ ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇 @Christian_page @Christian_page @Christian_page @Christian_page @Christian_page @christian_page 👆👆👆👆👆👆 ወንጌልን ለአለም በመፃህፍቶቻችን እናድርስ https://t.me/+n3PAJPjfhV01MjZk
498
1
💐#የማለዳ_ስንቅ ነፍሴ ሆይ | Muluken Melese እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

Muluken Melese #1 (3).mp3

1 727
7
💐 #የማለዳ_ስንቅ ቅመሱ፥ እዩም! እጅግ በጣም ከምወዳቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መካከል "እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው።" (መዝ.34፥8) የሚለው አንዱ ነው፡፡ ክፍሉ እንደሚናገረው፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር፣ ቸርነቱንና ምሕረቱን ቀምሰን ነው ለነፍሳችን መልካም እንደ ሆነ የምናውቀው፡፡ ለዚህም ነው በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ሥፍራዎች “ወደ እኔ ኑ” የሚሉ ግብዣዎችን ደጋግመን የምናነበው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር መንፈሳዊ ኅብረት (fellowship) የምንፈጥረው በግላችን ነው፡፡ እርሱ የልባችን ኣምላክ ነው፤ ስለ ሆነም ከእኛ ጋር መወዳጀት ይፈልጋል፡፡ ታዲያ ይህ ኅብረት በቅምሻ ነው የሚጀምረው፡፡ እያንዳንዳችን በግል ቀምሰንና ኣይተነው ነው ወዳጅነት የምንመሠርተው፤ በዚያም መሠረት ላይ እንደ ትጋታችን መጠን እናድግና ከበረከቱ እንጠግባለን። ከእርሱ ጋር የሚኖረን መስተጋብር የእግዚአብሔርን ጸጋ ይፈልጋል። እርሱ ራሱ ነው ወደዚህ ጸጋ የሚስበን፤ በራሳችን ምንም የለንምና፡፡ ቅዱስ ቃሉ "ጸጋው በእምነት ኣድኗችኋል።" (ኤፌ.2፥8) የሚለውም ለዚህ ነው። ከመጀመሪያው የመንፈስ ቅዱስ ልዕለ ተፈጥሮኣዊ የለውጥ ሥራ (regeneration) በኋላ ወደ ቃሉና ወደ ጸሎት ደጋግመን በመምጣት ፍቅሩን እያጣጥምን ቀምሰንና ኣይተን ነው ወደ እሱ ያለን መሻት፥ እምነት፥ ቅድስናና እግዚአብሔርን የመምሰል ባሕርያት የሚያድጉት! ሁሉ ነገር በመቅመስ ነው የሚጀምረው። ከዚያማ ቅምሻው ጠንከር ወዳለ ናፍቆት፣ ፍለጋ፣ ጥማት፥ ራብ ያድጋል። በመሆኑም በየዕለቱ የሆነ ነገር (እንደ ኣይበታችን መጠን) ካላገኘን ነፍሳችን እረፍት ኣትሰጠንም! ስለሆነም፣ "ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ? ዘወትር። አምላክህ ወዴት ነው? ሲሉኝ እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ። ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች።" (መዝ.42፥1-4) በሚል የነፍስ ቃተታ እርካታ እስክናገኝ ድረስ እንፈልገዋለን፡፡ ይህንን ግሥገሣ የታወቀው የወንጌል ሰው ስሚዝ ዊግልስዎርዝ Holy dissatisfaction ይለዋል፡፡ ልክ በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀ ምግብ ጥሩነቱ በቅምሻ እንደሚታወቅ ሁሉ፣ ጌታችንንም የምናውቀው ልባችንን ከፍተን ፍቅሩንና ቸርነቱን ስንለማመድ ብቻ ነው። God is a relational being; He needs us for relational intimacy! እሱን ለማወቅ ወደ ጸጋ ዙፋኑ መጥቶ ጥፍጥናውን መቅመስ ያስፈልጋል። የነፍስ መድኃኒት መሆኑን ማየትና መረዳት ያስፈልጋል! ያው ከላይ እንዳልኩት፣ በመቀማመስ ነው የሚጀምረው፡፡ አንዴ ከቀመሳችሁት በኋላ ግን የማያባራ የፍለጋ ዑደት (አግኝቶ መፈለግ) ውስጥ ትገባላችሁ! እንዲያ ነበር የሆነው ቅዱስ አውግስጦስ፡፡ እናም እንዲህ የሚል ቅኔን ተቀኘ፡- To fall in love with God is the greatest romance; to seek him the greatest adventure; to find him, the greatest human achievement. ጌታ ሆይ፣ አንተን የምንፈልግበት ቅናት፣ ግለትና የማያባራ መሻት በልባችን አፍስስልን! መልካም ቀን፣ ተባረኩልኝ! --- በቀለ ብርሃኑ (ዶ/ር) @nazrawi_tube
Show more ...
1 743
12
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊 ከተባረኩበት ያጋሩ!
1 341
0
እንዳትታለሉና እንዳታታልሉ ተጠንቀቁ “ሰዎች እኔን ማን ይሉኛል?” በማለት ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን ጠየቀ፤ ከዚያም እነርሱስ ስለ ማንነቱ ምን እንደሚያስቡ ጨምሮ ጠየቃቸው። ሐዋርያው ጴጥሮስ አስደናቂ ምላሽ አቀረበ። ጌታችን፣ “የሰማዩ አባቴ እንጂ ሥጋና ደም አልገለጠልህም” በማለት የምላሹን ትክክለኛነት መሰከረና ስለ ጴጥሮስ ደጋግ ቃሎችን አስከተል። ከዚህ ቀጥሎ ጴጥሮስ የተናገረው ሐሳብ ግን ያስደነግጣል፤ የራሱን ሰዋዊ ግንዛቤ ነበር ያቀረበው (ማቴ. 16÷13-23)። ሞቅታው የፈጠረበት ስሕተት ይሆን? ሰዋዊ ሐሳብ የሰይጣን አጀንዳ ማስተላለፊያ ሊሆን እንደሚችል ከጴጥሮስ ሐሳብ ማስተዋል ይቻላል። ስለዚህም ቅድም አድናቆቱን ያቀረበለት ጌታ በብርቱ ገሰጸው፤ ጴጥሮስ የሰይጣንን ሐሳብ አሾልኮ አስገብቷልና! ለካ ከእግዚአብሔር ዘንድ ትክክለኛ መገለጥንና እውነተኛ ቃልን መቀበል ላለመሳሳት ዋስትና አይሆንም። እናም በሆነ ወቅት አስደናቂ መገለጥን ብናመጣ ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የማይከብርበትን ሐሳብ አናስተላልፍም ማለት አይደለም። ስለዚህ ከሌሎች አገልጋዮች ጋር በሚኖረን ግንኙነት ይህን ጉዳይ ታሳቢ ማድረግ አለብን፤ እኛም እንዳንስት ብንጠነቀቅ እናተርፋለን። ©ምስባከ ጳውሎስ @nazrawi_tube
Show more ...
1 606
3
💐 #የማለዳ_ስንቅ ልሆን አልፈልግም | መጋቢ ታምራት ኃይሌ እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

12 ልሆን አልፈልግም.mp3

1 511
12
💐 #የማለዳ_ስንቅ ዴዚዴራታዊ ቅኝት በዚህ ዓለም ከወንድም ይልቅ የሚጠጋጋ፣ ፈጽሞ ለደቂቃም ቢሆን የማይለይ ወዳጅ ጌታ ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ እናም በዚህች ኣጭር የምድር ቆይታህ እርሱን በሚገባ ለማወቅ ትጋ፤ ተራበው ተጠማው! መልካምነት ያላቸውንና ውስጥህን የሚያበለጽጉ መንፈሳዊ መጻሕፍትን እያሰስህና ኣንባቢያንን እያማከርህ ኣንብብ፡፡ ባገኘኸው ሰዓት ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስህን ብላው፣ ኣሰላስለው፣ ከሰዎች ጋር ኣጥናው ተቀኘውም፡፡ በዕለት ተዕለት የሕይወት ክንውኖችህ ብትጠመድም ልብህ ሁልጊዜ ወዳጅህ ላይ ይሁን! ጌታ ኢየሱስን በስብከት፣ በምክር፣ በባይብል ጥናት፣ በውይይት፣ በጸሎትና ኣምልኮ ፈልገው፡፡ እስክትረካና ብርሃኑ ፈንጥቆ ልብህ ላይ እስኪበራ ድረስ በፍጹም ልብህ እሻው፡፡ ትኩረትህ እሱ ላይ ከሆነ ሌሎች ነገሮች ሁሉ ተገቢ ቦታዎቻቸውን ይይዛሉና! ኣስጨናቂው ዓለም የልብህን ሰላምና እረፍት እንዳይወስድብህ ስትራመድ፣ ስትሠራ፣ ስትነዳም ሆነ በየትም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ጸልይ! ከእጅህ ላይ መንፈሳዊ መጽሐፍ ኣይለይ፡፡ በጸሎት ከተቀጣጠሉ ወገኖች ጋር ኣዘውትር፡፡ ሰዎች ቢጎዱህም ኣትቀየማቸው፤ ይልቁንም ጸልይላቸው፡፡ ሁሌም በጎ ከማድረግ ኣትከልከል! መቼም ቢሆን ክፋትን በልብህ አታስተናግድ፡፡ የሰው ልጆች እርዳታህን ከፈለጉና የምትችል ሆነህ ከተገኘህ እጅህን በለጋስነት ዘርጋ፤ እስከ ጥግ እርዳቸው፡፡ ይህ ላንተ በረከትህ ነውና! ጌታ ኣምላክን ስታሳዝን ቶሎ ብለህ ንስሐ ግባ፡፡ ከምር/ ከልብ በሆነ ጸጸት ሕይወትህን ኣስተካክል፡፡ ጌታም በጸጋው እንዲረዳህ ተማጸነው፡፡ የማይመች ቦታ ከሆንህ ያለኸው ንስሐህን በጽሑፍም መግለጽ እንደምትችል አትርሳ! የሕይወትህ ጊዜ እጅግ ኣጭር ነውና በማይረቡ ነገሮች ኣታባክነው፡፡ አንብብ፣ ጸልይ፣ እርዳታህን የሚሹ ሰዎችን ኣግዝ፤ ጌታ ኢየሱስ የፍቅር አምላክ መሆኑን ለሰዎች ሁሉ ንገር፡፡ ለሰዎች ሁሉ ይህንን የምስራች ወንጌል ቢሰሙህም ባይሰሙህም ስበክ፤ እንዲያ ብትተጋ የተቀጣጠለና ፍሬያማ ሕይወት ይኖርሃል! ጌታ በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ! ተባረክ! --- በቀለ ብርሃኑ (ዶ/ር) @nazrawi_tube
Show more ...
1 864
9
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊 ከተባረኩበት ያጋሩ!
1 506
1
💐 #የማለዳ_ስንቅ ባለዉለታዬ | Suraphel Demissie እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

ባለዉለታዬ Suraphel Demissie.mp3

1 601
5
💐 #የማለዳ_ስንቅ አቤቱ በደቡብ እንዳሉ ፈሳሾች ምርኮአችንን መልስ! (በከባድ ጥያቄ ሆነው በጓዳቸው ለሚቃትቱ ይሁን) በርእሱ የተገለጸው ጸሎት/ ተማጽኖ ዝናብ የሚባል ነገር በሌለበት ጊዜ የተጸለየ ጸሎት መሆኑ አስደናቂ ነው፡፡ ዛሬ አንድ መንፈሳዊ መጽሐፍ እያነበብኩ ነበር ርእሱ የሚገኝበትን ክፍል ያነበብኩት፡፡ ድንገት ጸሐፊው መዝሙር 126 ላይ ጠቅሶ የሚናገርበት ምንባብ ላይ ስደርስ፣ “አቤቱ በደቡብ እንዳሉ ፈሳሾች ምርኮአችንን መልስ” የሚለው ምንባብ ልቤን በኃይል ነካው፡፡ መጽሐፉን ማንበብ ትቼ ክፍሉን ደጋግሜ እያነበብኩ በመልእክቱ በኃይል ተደነቅሁ፡፡ ጸሎቱ የተጸለየው እንኳን ጎርፍ (እንግሊዝኛው “በደቡብ እንዳሉ ፈሳሾች” የሚለውን “የኔጌቭ ጎርፍ” ብሎ ነው የሚገልጸው–i.e. streams of Negev) ካፊያ በማይታሰብበት ሁኔታ ላይ ሆነው የጸለዩት ጸሎት መሆኑ በራሱ አስገራሚ ነው፡፡ በባዶ ነገር ላይ ሆነው እንዲያ ማሰባቸው በራሱ ለአእምሮ ይከብዳል፡፡ እንደማስበው ግን፣ አምላካቸውን ስለሚያውቁት ነው እንደዚያ ደፍረው ተማጽኖ ያቀረቡት፡፡ ደቡቡ የእስራኤል ምድር እጅግ ደረቅ ሲሆን፣ በረጅም ጊዜ አንዴ አዘናግቶ የሚመጣ ከባድ ዝናብ ግን አያጣውም፡፡ ዝናቡ የሚፈጥረውን ከባድ ጎርፍ ነው ምሳሌያዊ በሆነ አገላለጽ ለጸሎት የተጠቀሙበት፡፡ ጸሎቱ በድርቀትና በባዶነት ከተዋጠች ነፍስ የወጣ ጩኸት ስለ ሆነ ነው ልቤን በኃይል የነካው፡፡ እስራኤላውያን በባቢሎን ምርኮኛ ሆነው ሳሉ፣ ካገኛቸው ጉስቁልናና መከራ የተነሣ፣ በብዙ እንባና ምጥ እንዳሳለፉ ምዕራፉ ይናገራል (ሙሉውን አንብቡት)፡፡ የልቅሶና የእንባ ዘርን ዘርተው ነበር፡፡ የአምላካቸውን ትድግና ሽተው ፊቱን ፈልገዋል፡፡ “ሰማዮቹን ቀድደህ ምነው ብትወርድ” (ኢሳ.64፥1) ብለው ጮኸዋል፡፡ ከነበረባቸው ባርነትና እንግልት የተነሣ አምላካቸውን በብዙ ተማጸኑት፡፡ በደቡብ እንዳሉ ፈሳሾች ምርኮአችንን መልስ ብለው አለቀሱ፣ ቃተቱ፣ እሪታቸውን አሰሙ፡፡ እናም ከብዙ ጣርና ምጥ በኋላ የክብር አምላክ በጉስቁልናቸው ላይ በብርታቱ ተገለጠና ታሪካቸውን ቀየረው (ከቁጥር አንድ እስከ ስድስት ያሉት ክፍሎች ያንን ይገልጻሉ)፡፡ • ምርኮአቸውን መለሰላቸው፤ • ከአእምሮ በላይ የሆኑ ነገሮችን አደረገላቸው፤ • ነዶ በነዶ አደረጋቸው፤ • እንደ ጎርፍ በሚያጥለቀልቀውና በሚያስደንቀው በረከቱ ጎበኛቸው (like streams of Negev)፤ • ለመረዳት በሚከብድ ክብር ኃያል መሆኑን አሳያቸው፡፡ በክፍሉ እንደምናየው የሚገርም የጸሎት መልስ ነው ያገኙት፡፡ የመጣው የጸሎት መልስ ማኅበራዊ ተጽእኖም ነበረው፤ ጌታ እግዚአብሔርን የማያምኑ አሕዛብ እየተገረሙ፣ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” (ቁ.2) እያሉ ነበርና፡፡ በልቅሶና በእንባ ዓይኖቻቸው እንዳልሞጨሞጩና አንገታቸውን እንዳልደፉ፣ ትቢያቸውን አራግፈው ብድግ አሉ፡፡ በሐሤትና በደስታ ተንበሸበሹ (ቁ.1-2)፡፡ ይገርማል! ወገኖቼ በትሕትና፣ በተሰበረና በተዋረደ ልብ የእምላካቸውን ፊት ቀንና ሌት ለሚፈልጉ ብሩካን፣ ትልቅ ተስፋን የሰነቀ ክፍል አይመስላችሁም? ይህንን የክብር ጌታ በእንባና በብዙ ጭንቀት እየተማጸናችሁ ያላችሁ እባካችሁ ክፍሉን ቀስ ብላችሁ እያሰላሰላችሁ አንብቡት፡፡ ቢቻል ከውስጣችሁ ጋር እስኪዋሃድ ቆዩበት፡፡ እናም ጌታ ታማኝ ነውና ተስፋ አድርጉት፡፡ በርቱ፣ ልባችሁም ይጽና! መልካም ቀን ተባረኩልኝ! --- በቀለ ብርሃኑ (ዶ/ር) @nazrawi_tube
Show more ...
1 570
6
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊 ከተባረኩበት ያጋሩ!
1 352
0
💐 " በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን።" (1ኛ ቆሮ 15:19) Graphics credit - AD Graphics 📞 - 251916698510 --- @nazrawi_tube
2 202
8
💐 #የማለዳ_ስንቅ ክብሩን ሳየው | mesfin mamo እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

ክብሩን ሳየውፓር መስፍን ማሞ.mp3

1 538
5
💐 #የማለዳ_ስንቅ ዓመቶችህ ከቶ አያልቁም! ዛሬ በማለዳው ስለ እግዚአብሔር ዘላለማዊነት ሳስብ እግረ መንገዴንም “ዘለዓለም” (eternity–infinite or unending time) የሚለውንም ቃል ለመረዳት ሞክሬ ነበር፡፡ አስቤው አስቤው በኃይል ስለ ከበደኝ ተውኩት፡፡ አስቡት እስቲ፣ እግዚአብሔር ያልኖረበት ጊዜና ዘመን የለም፡፡ ሁሌም አለ፡፡ ዩኒቨርስን ሳይፈጥር የኖረበትን ዘመን እንዴት ማሰብ ይቻላል? እጅግ ከባድ ነው፡፡ ራሱ“ከጥንት ጀምሮ እኔ ነኝ/ From eternity to eternity I am God.” (ኢሳ.43፥13) ብሎ ተናግሯል፡፡ እርሱ የሌለበት ጊዜ አልነበረም ማለት ነው፡፡ አይደንቅም?! ቦቲየስ (Boethius) የሚባል ፈላስፋ ስለ እግዚአብሔር ዘላለምነት ሲናገር እንዲህ ብሏል፡- “God’s eternity is the whole, simultaneous and perfect possession of boundless life.” በዚህ ትንሽ አእምሮ ዘለዓለምን መረዳት እጅግ ከባድ ይመስለኛል፡፡ መዝሙረኛው የእግዚአብሔርን ዘላለምነት ተቀኝቶታል እንዲህ በማለት፡-“አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ፥ አንተ ግን ትኖራለህ፤ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፥ ይለወጡማል፤ አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።” ወገኖቼ የሚገርም እኮ ነው! እግዚአብሔር መጀመሪያ የለውም፣ መጨረሻም የለውም፡፡ ከጊዜ ገደብ ውጭ ሆኖ ሁሉን በአንዴ ማየት፣ ማድረግ፣ መመርመርና መቆጣጠር የሚችል ኃያል ጌታና አምላክ ነው፡፡ ሁሌ ያለ ገዥም ነው (He always is!)፡፡ He is a concept our finite minds are barely able to grasp and handle. ዳዊት ይህንን ዘላለማዊ አምላክ ሲገልጸው፣ “አቤቱ፥ አንተ ለትውልድ ሁሉ መጠጊያ ሆንህልን። ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ አንተ ነህ።” (መዝ.90፥1-2) ብሎ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የተጻፉ ሦስት ክፍሎችን እነሆ፡- “አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም።” (ኢሳ.40፥28) “እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።” (1ጢሞ.6፥15-16) “ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥ የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፡፡” (ዘዳ.33፥26-27) መልካም ቀን ተባረኩልኝ! --- በቀለ ብርሃኑ (ዶ/ር) @nazrawi_tube
Show more ...
1 503
6
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊 ከተባረኩበት ያጋሩ!
1 314
0
👉 መዝሙር ፈልጠው አተዋልን? ሙሉ አልበም ፈልገው ተቸግረዋልን? 🤔 MB እየበዛ ተሰላችተዋልን? 🤔 ✔️ እነሆ ይህን ችግር ሁሉ በአንድ ላይ የሚቀርፍ ቻናል፦ 👇👇👇
848
0
#የማለዳ_ስንቅ ተንሰፍስፌ | Singer Yosef Aschalew ድንቅ ዝማሬ እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

KALTUBE ON TELEGRAM.mp3

1 731
18
💐 #የማለዳ_ስንቅ የእግዚአብሔር ዓይኖች በስፍራ ሁሉ ናቸው! የእግዚአብሔር ወሰኑ የት ነው? የትም (infinity)፡፡ እርሱ የሌለበት ሥፍራ የት ነው? በሁሉም ሥፍራ ይገኛል (He is omnipresent)። አይደንቅም?! ንጉሥ ሰሎሞን ስለ እዚህ እውነት ሲናገር፣ “በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም (the highest heavens cannot contain you) ፤ ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ! (1ነገ.8፥27) ብሎ ተናግሯል፡፡ ዳዊትም በሚጥም አገላለጽ ያንኑ እውነት “ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ አለህ። ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች። በውኑ ጨለማ ትሸፍነኛለች ብል፥ ሌሊት በዙሪያዬ ብርሃን ትሆናለች፤ ጨለማ በአንተ ዘንድ አይጨልምምና፥ ሌሊትም እንደ ቀን ታበራለችና፤ እንደ ጨለማዋ እንዲሁ ብርሃንዋ ነው።” (መዝ.139፥7-12) እያለ ተቀኝቶታል፡፡ አዎ፣ እግዚአብሔር በሥፍራ አይወሰንም፡፡ “እዚህ ጋ ነው” ወይም “እዚያ ጋ ነው” አይባልም፡፡ “Our God defies the limitation of space entirely. He is present with His whole being everywhere simultaneously.” ብሏል Matthew Barrett (in his book titled, None Greater). በዚህ ረገድ ቅዱስ ቃሉ እንዲህ ይለናል፡- ➤ “ዓይኖቹ በሰው መንገድ ላይ ናቸው፥ እርምጃውንም ሁሉ ያያል። ኃጢአትን የሚሠሩ ይሰወሩበት ዘንድ ጨለማ ወይም የሞት ጥላ የለም።” (ኢዮ.34፥21-22) ➤ “የእግዚአብሔር ዓይኖች በስፍራ ሁሉ ናቸው፤ ክፉዎችንና ደጎችን ይመለከታሉ።” (ምሳ.15፥3) ➤ “እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለሁም። ሰው በስውር ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል እግዚአብሔር።” (ኤር.23፥23-24) ➤ “እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል።” (ቈላ.1፥15-17) ➤ “በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።” (ኢሳ.43፥2) መልካም ቀን ተባረኩልኝ! --- በቀለ ብርሃኑ (ዶ/ር) @nazrawi_tube
Show more ...
2 029
11
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊 ከተባረኩበት ያጋሩ!
1 423
0
💐 #የማለዳ_ስንቅ ሊመጣ ያለው ጌታ ይመጣል | Wubalem and Mengistu እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

Wubalem_and_Mengistu_New_Protestant_Song_ሊመጣ_ያለው_ጌታ_ይመጣ_dPGAtlO7C60.mp3

1 612
10
💐 #የማለዳ_ስንቅ የእግዚአብሔር ጸጋ! “ጸጋ/ Grace” የሚለውን ቃል በጣም ነው የምወደው፡፡ የዛሬ 20 ዓመት ገደማ ይሆናል፡፡ አንድ ወዳጄ ቤት ስገባ የማየው ልቤን ተርከክ የሚያደርግ በትልቁ የተጻፈ "የእግዚአብሔር ጸጋ" የሚል ጥቅስ በውስጤ ቀርቷል፡፡ ጸጋ ማለት እንዲሁ በነጻ የተሰጠ ስጦታ ነው፡፡ ያንን ስጦታ ለማግኘት ሰውየው ያዋጣው/ የሚያዋጣው ምንም ነገር የለም፡፡ ከእርሱ የሚጠበቀው በትሕትና ልቡን መክፈት ብቻ ነው፡፡ በቃ! ሌላው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው፡፡ ከድረ ገጽ ላይ ያገኘሁት ትርጉም እንዲህ የሚል ነው፡-(in Christian belief) the free and unmerited favor of God, as manifested in the salvation of sinners and the bestowal of blessings. ጸጋ የሚለውን ቃል በግሩም ሁኔታ የሚገልጹ ክፍሎች ሳስብ ወደ አእምሮዬ የመጡ አምስት ክፍሎች አሉ፡፡ እነርሱን ልጋብዛችሁ፡- ➤“ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ። የአስቆሮቱ ያይደለ ይሁዳ ‘ጌታ ሆይ፥ ለዓለም ሳይሆን ራስህን ለእኛ ልትገልጥ ያለህ እንዴት ነው?’ አለው። ኢየሱስም መለሰ አለውም የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን።” (ዮሐ.14፥21-23)፤ ➤“እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።” (ዮሐ3፥20)፤ ➤“የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ።” (መዝ.16፥16)፤ ➤“እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ።” (መዝ.17፥15)፤ ➤“እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።” (ኢሳ.40፥31)፡፡ የእግዚአብሔር ጸጋ ይብዛላችሁ! --- በቀለ ብርሃኑ (ዶ/ር) @nazrawi_tube
Show more ...
1 599
10
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊 ከተባረኩበት ያጋሩ!
1 382
0
💐#የማለዳ_ስንቅ ኹሉን ቻይ | ቴዲ ታደሰ እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

ሁሉን ቻይ ዘማሪ ቴዲ ታደሰ.mp3

1 615
8
💐 #የማለዳ_ስንቅ ያለ እኔ ልታደርጉ አትችሉም! ሰው እጅግ ደካማና ውስን ፍጥረት ነው፡፡ በዚህ ዓለም ማድረግ ከሚችላቸው ይልቅ የማይችላቸው ነገሮ ይበዛሉ፡፡ ለምሳሌ በራሱ ወደ ጌታ ኢየሱስ መምጣት አይችልም፡፡ የእግዚአብሔር ቃል “የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም፡፡” (ዮሐ.6፥44) ይላልና! በዮሐንስ 15 ግልጽ የሆነ “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” (ቁ.5) ምክር እናገኛለን፡፡ ወገኖቼ ይኼ እኮ ትልቅ ዕረፍት የሚሰጥ ቃል ነው፡፡ በመራስ ከመፋገርና ከመድከም ያድናልና፡፡ እኔ የዛሬ 18 ዓመት ገደማ የሕክምና ዲግሪ እጄ ላይ ይዤ መሥራት የማልችልበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር፡፡ መጨረሻ ላይ ጉዳዩ ከላይ እንደ ሆነ ሲገባኝ፣ “ጌታ ሆይ አቅሜን አውቄአለሁ፤ እባክህ እርዳኝ፡፡” ብዬ ተማጸንሁት፡፡ ከዚያም ሁኔታዬን ተአምር በሚመስል መንገድ አስተካክሎ መሥራት እንድችል አድርጎኛል፡፡ ማለትም ዮሐንስ 15፥5ን በተግባር ነው ያስተማረኝ! ለመሆኑ የሰው ልጅ በራሱ ምንም ማድረግ የማይችል ከሆነ ምን ይሻለዋል? የሚበጀው ራሱን በትሕትና ለሠሪው አሳልፎ መስጠት ነዋ! ይኸው “አቅቶኛል፤ ከዚህ በኋላ እንቅፋት አልሆነም፤ በሥጋዬና በነፍሴ አልታገልም፤ አንተ ሥራዬን እንድትሠራው ራሴን አሳልፌ እሰጥሃለሁ” ማለት ነው ያለበት፡፡ ወገኖ እንዲያ በትሕትና ራሳችንን ስናስረክበው፣ “በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ” (ኤፌ.3፥20) መሥራት ያውቅበታል፡፡ ከላይ ያለውን እሳቤ አስመልክቶ ልቤን የሚነኩ ሦስት ክፍሎችን ታጤኗቸው እነሆ፡- ➤“አቤቱ፥ ከንፈሮቼን ክፈት፥ አፌም ምስጋናህን ያወራል።” (መዝ.51፥15)፤ ➤“አፌን ምስጋና ምላ ሁልጊዜ ክብርህንና ግርማህን እዘምር ዘንድ።” (መዝ.71፥8)፤ ➤“ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።” (ፊል.2፥13)፡፡ ሌላውን ተውት ከንፈሮቻችንን ለመክፈት የእርሱ ፈቃድና ኃይል ያስፈልገናል፡፡ ጌታ ሆይ ራሳችንን በአንተ ላይ መጣል እንድንችል ጸጋህ ይብዛልን! --- በቀለ ብርሃኑ (ዶ/ር) @nazrawi_tube
Show more ...
1 634
9
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊 ከተባረኩበት ያጋሩ!
1 379
0
💐#የማለዳ_ስንቅ ሉዓላዊ በረከት ደጀኔ በማልፍበት መንገድ በህይወት ጎዳና በየዕለት ውሎዬ ሳልፍ በጎንበስ ቀና ሊገቡኝ አልቻሉም ለምን ከዛስ እንዴት ለማ መቼ በማ ቀጣዩስ ወዴት በዚ ሁሉ ነፍሴ ስትጨነቅ ያረጋጋል አንድ ነገርን ማወቅ ሉዓላዊ ብቻህን ሉዓላዊ ነህ ሉዓላዊ እግዚአብሄር ሉዓላዊ ነህ ሉዓላዊ ለምን እንዲ አደረክ አንተ አትባልም ሉዓላዊ አንተን ደርሶ ሚጠይቅ የለም ሸማኔው አንተ የህይወቴ ሸማኔ ሸክላ ሰሪው አንተ የሂወቴ ሸክላ ሰሪ /2X ፈረዱ ሊረዱ የወደዱ አሰቡ ምክንያት ሰበሰቡ ዝም አልኩኝ ኦሆኦሆኦሆ እንዳሉኝ ሆንኩኝ ለበጎ ነው ቢሉኝ አሜን ብዬ ጮህኩኝ አጥፍተሃል ቢሉኝ ማረኝ ማረኝ አልኩኝ ጠላት ነው ያሉኝ ለት ቆምኩኝ ለጦርነት የሰው ክፋት ጠቆሙኝ አድነኝ አልኩኝ ጮህኩኝ ሊሰራህ ነው ታገስ እሺ አልኩኝ ጥርሴን ነከስኩኝ እምነቴን አበረታሁ ቆምኩኝ በረታው ፀናው አንዳንዴ ህይወት እንዲህ ነው መልሱ እግዚአብሄር ጋር ነው ቢገባኝም ባይገባኝም በኔ ህይወት ሉዓላዊ ነው /2X ሉዓላዊ (4X) --- እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube
Show more ...

ሉዓላዊ_ዘማሪ_በረከት_ደጀኔ_SOVEREIGN_BEREKET_DEJENE_Lualawi_NEW_PROTESTANT.mp3

1 647
15
💐 #የማለዳ_ስንቅ የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የሰው ኀላፊነት! መዝሙር 57 ዳዊት ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በዋሻ በነበረበት ጊዜ የተቀኘው ቅኔ ነው፡፡ ይህ ምዕራፍ ወደ ጸሎት ከሚያንደረድሩኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት መካከል ዋናው ነው ማለት እችላለሁ (በተለይ በጉዳት ጊዜ)፡፡ ዳዊት በሚያልፍበት መከራ ውስጥ በዋሻ ሆኖ ነው ይህንን ጸሎትና የእምነት አቋም ያንጸባረቀው፡፡ ማለትም እግዚአብሔር ሉዓላዊ አምላክ መሆኑን እና ነፍሱ የወደደችውን ነገር እንደሚያደርግ ያምናል፡፡ በሉዓላዊ ጥበቡ እርሱ የፈቀደው መከራም እንደ ሆነ ያስተውላል፡፡ ሆኖም ግን ኀላፊነቱን አልዘነጋም፡፡ መጸለይ ብቻ ሳይሆን፣ ሳዖል ክፉ እንዳያደርግበት አስተውሎ ነበር ይንቀሳቀስ የነበረው፡፡ እንዲሁ እግዚአብሔር አዋቂ ነው ብሎ አልተዘናጋም፡፡ ከምዕራፉ ልብን የሚነካው ክፍል “ማረኝ፥ አቤቱ፥ ማረኝ፥ ነፍሴ አንተን ታምናለችና፤ ጉዳት እስክታልፍ ድረስ በክንፎችህ ጥላ እታመናለሁ።” (ቁ.1) የሚለው አገላለጽ ነው፡፡ አዎ፣ ወገኖቼ እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ነውና ጉዳት ያልፋል፡፡ እስከ እዚያው ግን የእግዚአብሔር ሕልውና እጅግ ወሳኝ ነው፤ ያለ እግዚአብሔር ጸጋ አይቻልምና፡፡ ጊፍት (Gift Gugu Mona) የምትባል የእግዚአብሔር አገልጋይ እንዲህ ብላለች፡-“The presence of God in our lives provides peace, strength and hope.”! ዳዊት ሉዓላዊ አምላክ መሆኑን በመንፈሱ አስተውሎና በጥልቀት ተረድቶ ነው የመከራውን ጊዜ “ልቤ ጨካኝ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጨካኝ ነው/ my heart is fixed” (ቁ.7) ብሎ የጸናው፡፡ እናም በስተመጨረሻ ሂደቱ በድል ሊጠናቀቅ ችሏል፡፡ “ከሰማይ ልኮ አዳነኝ፥ ለረገጡኝም ውርደትን ሰጣቸው፤ እግዚአብሔር ቸርነቱንና እውነቱን ላከ። ነፍሴን ከአንበሶች መካከል አዳናት።” (ቁ.3-4) ብሏልና! "Trusting God" በሚለው መጽሐፋቸው (ገጹን ረስቼዋለሁ) ጄሪ ብሪጅስ (Jerry Bridges) ይህንን ምዕራፍ አስመልክተው የሚከተለውን ሐሳብ ሰጥተዋል፡-“Prayer is the acknowledgment of God’s sovereignty and of our dependence upon Him to act on our behalf (ለዚህ ነው ዳዊት “ልቤ ጨካኝ ነው” ያለው). Prudence is the acknowledgement of our responsibility to us all legitimate means. We must not separate these two.” ተባረኩልኝ! --- በቀለ ብርሃኑ (ዶ/ር) @nazrawi_tube
Show more ...
1 426
7
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊 ከተባረኩበት ያጋሩ!
1 302
0
💐 #የማለዳ_ስንቅ እየራራህልኝ | Soreti Moges እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

/home/spoti/Eyerarahlegn - Soreti Moges.mp3

1 514
5
💐 #የማለዳ_ስንቅ "በከንቱ ፈልጉኝ" አላለም! እግዚአብሔር ጸሎትን እንደሚመልስ በተግባር በራሴ ሕይወት ደጋግሜ አይቻለሁ፡፡ ላያቸው አልችልም ብዬ ተስፋ እስከ መቁረጥ የደረስኩባቸውና ታልፈው ያየኋቸው ብዙ የጥያቄ መልሶች አሉኝ፡፡ ጌታ አምላክ “ከጨለማ ምድር በምስጢር አልተናገርሁም፤ በከንቱ ፈልጉኝ አላልሁም፡፡ እኔ እግዚአብሔር እውነትን እናገራለሁ፤ ትክክለኛውን ነገር አውጃለሁ፡፡” (ኢሳ.45፥19) ያለው በከንቱ አይደለም፡፡ የተናገረውን የሚያደርግ አምላክ ስለ ሆነ ነው እንዲያ የተናገረው፡፡ ይህንን ታላቅ ተስፋ ይዘን ነው ፊቱን መፈለግ የሚኖርብን፡፡ ዳዊት “ሥጋ ለባሽ ጸሎትን ወደምትመልስ ወደ አንተ ይመጣል፡፡” (መዝ.65፥2) ያለው የጮኸባቸው ጉዳዮች ተመልሰውለት ስለሚያውቅ ነው፡፡ ለመሆኑ እንዲሁ በባዶው ይህንን ምስክርነት ይጽፈው ኖሯል? እግዚአብሔር ከልብ፣ ከውስጥ ከአውነትና ከምር የፈለቀን ጩኸት ያከብራል፣ ይራራልም፡፡ ይህ በብዙዎች የተመሰከረ እውነት ነው። እግዚአብሔር ጸሎትን የማይሰማና የማይመለስ ቢሆን ኖሮ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኛቸው በርካታ ምስክርነቶች ባልተጻፉም ነበር፡፡ ሐና ጸሎቷ በድንቅ ሁኔታ ባይመለስላት ኖሮ፣ “ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፥ ቀንዴ በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህ ደስ ብሎኛል።” (1ሳሙ.2፥1) ብላ ትዘምር ነበር? በፍጹም! እግዚአብሔር ጸሎትን ስለሚሰማ አይደል እንዴ፣ በዚያ ሰገነት ላይ በምጥና ግራ በመጋባት የነበሩትን ደቀ መዛሙርት ሰምቶ በእሳት የመለሰው? እናም “በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥ ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው። እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው። በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።” (የሐዋ.2፥1-2) የሚለው ትንግርታዊ ታሪክ በሰው ሁሉ ፊት የተፈጸመው፡፡ ለመሆኑ “በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ /እጅግ ከባድና ጥልቅ ጸሎት ላይ እንደ ነበረ ነው የማምነው/” (ራእ.1፥10) ያለበቱ የሐዋርያው ዮሐንስ የረጅም ጊዜ ምልጃና ቃተታ ባይሰማና ሞገስ ባያገኝ ኖሮ፣ ያ ባለ 21 ምዕራፍ እጅግ አስደናቂ መጽሐፍ ይወለድ ነበር? ወገኖቼ እግዚአብሔር ጸሎት ይመልሳል፤ እውነተኛ ምልጃን ያከብራል፤ የተሰበረና የተዋረደን ልብ አይንቅም፡፡ ሰምቶም በእሳት ይመልሳል፤ ስለሆነም በጸሎት ጽኑ፤ “በእግዚአብሔር የምታምኑ ሁላችሁ፥ በርቱ ልባችሁም ይጥና።” (መዝ.31፥24)! መልካም ቀን ተባረኩልኝ! --- በቀለ በላቸው @nazrawi_tube
Show more ...
1 511
7
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊 ከተባረኩበት ያጋሩ!
1 334
1
💐 #የማለዳ_ስንቅ አለ በል በኑሮ | Illasha Fekadu From endegena album እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

Alle Noor - Illasha Fekadu.mp3

1 737
5
💐 #የማለዳ_ስንቅ ሆዴ መራራ ሆነ (እውነተኛ ለውጥ)! በዚህ ዘመን በኢትዮጵያ ወንጌላዊያን ቤተ ክርስቲያናት አካባቢ የሚታዩ ችግሮች ብዙ ናቸው፡፡ በተለይ በመማርና በማስተማር ሂደቱ ውስጥ ብዙ ችግሮች ጐልተው ይታያሉ፡፡ ጥቂቶቹን ልጥቀስ፡፡ ለአቅመ ማስተማር ያልደረሱ ወይም የማስተማር አቅም የሌላቸው ሰዎች መድረክ ላይ እንደ ልብ ናቸው፤ የሞራል ብቃት የሌላቸው ሰዎች ያስተምራሉ፤ እርስ በእርስ የሚጣረሱ ትምህርቶች ተዘውትረው ይሰማሉ፤ በመሆኑም ተማሪዎች የቱን እንደሚመርጡ ይቸገራሉ፤ መንፈሳዊ አገልግሎት ላይ በተለይ የማስተማር አገልግሎቱ ላይ ያለ ምንም በቂ ዝግጅት ቶሎ ቂብ የማለት ነገር ይታያል፡፡ ሌላም ሌላም! በግሌ መድረክ ላይ የሚወጡ ሰዎች፣ ሸንጎ ላይ ከመታየታቸው በፊት እጅግ ብዙ መማር አለባቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ በእርግጥ አስተማሪው መንፈስ ቅዱስ ቢሆንም፣ እውቀት ባላቸው ሰዎች እግር ስር ቁጭ ብሎ መማር ጥሩ ነው–ለረጅም ጊዜ፡፡ በተጨማሪም በግል ትጋት ብዙ ነገሮችን መማር ይቻላል፣ የመማር ፍላጎቱ ካለ፡፡ በተለይ የገንዘብ አቅም ያለው ሰው መንፈሳዊ ኮሌጆች ገብቶ ለምን አይማርም (ጤናማ የሆኑት የትኞቹ እንደሆኑ ጠቢባንን አማክሮ)? ለመሆኑ የት ይሄዳል አገልግሎቱ? ለምሳሌ በግሌ የሚያሳዝነኝ ነገር አለ፡፡ ሰዎች አንድ አገር የሚያውቀው ጥፋት ሠርተው በንስሐ ከተመለሱ በኋላ፣ ብዙ ሳይቆዩ ሲያገለግሉ ደግሞ እናያቸዋለን፡፡ ምንድነው ይኼ? ለመሆኑ ምን ሊያስተምሩን ነው? እንዲህ ዓይነት ሰዎች ለተወሰኑ በርከት ያሉ ዓመታት ድምፃቸውን አጥፍተው በጌታ እግር ሆነው ለምን አይማሩም? ለምን ተግተው አይጸልዩም? የት ይሄዳል መድረኩ/ አገልግሎቱ? ምናለ ትሕትና ቢኖር? ጌታ ኢየሱስ ያገለገለው እጅግ ጥቂት ዓመታትን ነው፡፡ ረጅሙን ዓመታት በዝግጅት ነበር ያሳለፈው፡፡ የዝግጅቱ ጊዜ እጅግ ጠንካራ ነበርና፣ አገልግሎቱ እጅግ አስደናቂ ነበር፡፡ ከአፉ ከሚወጣው ከጸጋው ቃል የተነሣ ብዙዎች ተደንቀዋል (ሉቃ.4፥24)፡፡ ፍሬያማ አገልግሎት እንደ ነበረው ማን ያጣዋል? እግዚአብሔር ለረዳው ሰው፣ ድምፁን አጥፍቶ ቃ ብሎ በእግዚአብሔር ነገር እስኪበስልና በጥበብ እስኪሞላ ድረስ በጓዳው ቢቆይ አስተዋይነት ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በአፍ እየጣፈጠ ገብቶ፣ እያደር ሆዳችን መራራ ያደርገዋል (ራእ.10፥10)፤ ማለትም ይለውጠናል፤ ያስጨክነናል፤ እውነትን የምንጋፈጥ ደፋሮች ያደርገናል፡፡ ነገር ግን አፋችን ውስጥ በመጣፈጥና ሆዳችንን መራራ በማድረግ መሀል incubation period እንዳለ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ ደጋግሞ በማንበብ፣ በማጥናትና በማሰላሰል ነው፣ “የቤት ቅናት በልታኛለች” (መዝ.69፥9) ወደሚል authentic ለውጥ የምንሸጋገረው፡፡ እንዲያ የተለወጠና የተማረ ሰው ሲያስተምር ብዙ ፍሬን ያፈራል፡፡ የብዙዎችን ልብ ወደ እግዚአብሔር ሐሳብ ይመልሳል፡፡ ታዲያ እንዲህ ዓይነት ለውጥ በሕይወታችን እንዲታይ ከፈለግን፣ “ከእኔም ተማሩ” የሚለውን አምላካዊ ትዕዛዝ እናክብራ! መልካም ቀን ተባረኩልኝ! --- በቀለ በላቸው @nazrawi_tube
Show more ...
1 609
6
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊
1 347
0
💐 #የማለዳ_ስንቅ ርዕስ እራስህን ጠብቅ በንፅህና | መጋቢ ታምራት ሀይሌ Old song እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

4 rasehen tebik.mp3

1 674
11
💐 #የማለዳ_ስንቅ እግዚአብሔርን በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት! የእግዚአብሔር ቃል “ኤፍሬም ከአሕዛብ ጋር ተደባለቀ፣ ኤፍሬም እንዳልተገላበጠ ቂጣ ነው፡፡ እንግዶች ጉልበቱን በሉት፣ እርሱም አላወቀም፤ ሽበትም ወጣበት፣ እርሱም አላወቀም፡፡ የእስራኤልም ትዕቢት በፊቱ መሰከረ ወደ አምላካቸው አልተመለሱም፣ በዚህም ሁሉ አልፈለጉትም፡፡” (ሆሴ.7፥8-10) ብሎ ይናገራል፡፡ ኤፍሬም የሚለው ቃል ፍሬያማነትን የሚያሳይ ቃል ሲሆን በዚህ ክፍል የሆነው ግን ተቃራኒው ነው፡፡ ክፍሉ የሚያሳየው ትልቅ ደረጃ ላይ የደረሰ ውድቀትን ነው፡፡ ኤፍሬም እንግዶች ጉልበቱን ሲበሉት አላወቀም፡፡ ሽበትም ሲወጣበት አላወቀም፡፡ እናም ውድቀቱን ስላልተገነዘበ ወደ አምላኩ ለመመለስም አልሞከረም፡፡ "አድነኝ" ብሎ አልጮኸም፡፡ ለምን? መንፈስ ቅዱስ ከእሱ ጋር ስላልነበረ ነዋ! በሳምሶንም ሕይወት የሆነው ተመሳሳይ ነው፡፡ ጸጋው ከላዩ ላይ ከተገፈፈ በኋላ፣ “እወጣለሁ እንደ ወትሮውም ጊዜ አደርጋለሁ፡፡” ብሎ አስቦ ነበር፤ “ነገር ግን እግዚአብሔር ከእርሱ እንደተለየው አላወቀም፡፡” (ሆሴ.16፥20-21)! ከዚያ በኋላ የደረሰበትን እናውቃለን፡፡ ጠላት ዲያቢሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ በዙሪያችን ይዞራል (1ጴጥ.5፥8)፡፡ የሚውጠውን ካገኘ ያለ ምሕረት ተበቃይ ነውና በሳምሶን ሕይወት የደረሰው ጉዳት እጅግ ከባድ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ያጣው ለእግዚአብሔር ስሱ (sensitive) የሆነውን መንፈሳዊቱን ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ጠላት የማየት ችሎታውን ሙሉ በሙሉ ነጠቀው፡፡ የብዙ መንፈሳዊ ሥራዎች ባለቤት የሆኑት ቶዘር (A.W.Tozer) እንዲህ ብለዋል፡- “I remind you that there are churches so completely out of the hands of God that if the Holy Spirit withdrew from them, they wouldn't find it out for many months”! ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለን ኅብረት እንደ ትጋታችን እየጠለቀ የሚሄድ ሲሆን፣ ዳተኞችና የማንታዘዝ ስንሆን በሂደት በምንሠራቸው መልካም ያይደሉ ነገሮች በመመረር ይተወናል፡፡ የሚያሳዝን ነገር ግን አለው፡፡ እዚያ ደረጃ ላይ ደርሶ ሲተወን አብዛኛዎቻችን አለማወቃችን ነው፡፡ ለዚህም ነው የእግዚአብሔር ቃል፡- "እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፣ ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤ ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፣ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ፡፡” (ኢሳ.55፥6-7) ብሎ የሚመክረው፡፡ እግዚአብሔር ሆይ ስትናገረን በቶሎ እንድንመለስ ጸጋህን አብዛልን! --- በቀለ በላቸው @nazrawi_tube
Show more ...
1 535
7
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊
1 284
0
💐 #የማለዳ_ስንቅ የአለም ምናምንቴ አይስበኝም ከቶ አያምረኝም የሚያብረቀርቀው አይገዛኝም ከቶ አያታለኝም በሚያልፈው በሚጠፋው አልማልልም ከቶ አልጎመጅም ሀሳቤ ተወርሷል ባንተ በኢየሱስ ነፍሴን የሚያረካት ፍቅርህ ነው በፊትህ መፍሰስ እወድሃለሁ ከውስጤ ከአንጀቴ አንተ ብቻኮ ነህ የሞላኸው ቤቴን ብዬ ብዬ አልጠግብ ስላንተ ባወራ የህይወት ውሀ ነህ የህይወት እንጀራ እራብሀለው እራብሀለው ጌታ መዳኒቴ አንተን እሻለው እጠማሀለው እጠማሀለው ኢየሱስ መዳኒቴ አንተን እሻለሁ የፀዳልህ ብርሀን ሚናፈቀው ክብር የልቤ ተማፅኖ እንዳየው ያን ፊትህን ምጠይቅህ አለኝ ከእጅህ(እንድቀበል ?) ግን እንዲያው ዝም ብዬ ከእግርህ ስር ቁጭ ልበል ገና በማለዳ ወዳንተ ሮጣለው የመንፈስህ እሳት ህይወቴን ያግለው ልማርህ እሻለው እንዳውቅህ እጥብቄ ከህልውናህ ጋር ልቅር ተጣብቄ ፈልግሀለው ፈልግሀለው እስካገኝህ ድረስ እጣደፋለሁ እጠማሀለው እጠማሀለው ጌታ መዳኒቴ አንተን እሻለሁ ክብሬ ነህ አዶናይ ቀኔን ምታፈካ የምትሰጠው ደስታ በምንም አይተካ አምሮና (ተኩኖ?) ህይወቴን ያጣመ ዛሬም ልቤ አንተን አንተን ብቻ አለመ ገና በማለዳ ወዳንተ ሮጣለው የመንፈስህ እሳት ህይወቴን ያንድደው ልማርህ እሻለው እንዳውቅህ እጥብቄ ከህልውናህ ጋር ልቅር ተጣብቄ እወድሃለሁ ከውስጤ ከአንጀቴ አንተ ብቻኮ ነህ የሞላኸው ቤቴን ብዬ ብዬ አልጠግብ ስላንተ ባወራ የህይወት ውሀ ነህ የህይወት እንጀራ እራብሀለው እራብሀለው ጌታ መዳኒቴ አንተን እሻለው እጠማሀለው እጠማሀለው ኢየሱስ መዳኒቴ አንተን እሻለሁ --- @nazrawi_tube @nazrawi_tube
Show more ...

MESKEREM GETU 2021 - እራብሀለው 😭.mp3

1 524
13
💐 #የማለዳ_ስንቅ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ! የእግዚአብሔር ቃል “በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፣ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድ ሁሉ እርሱን እወቅ፣ እርሱ ጎዳናህን ያቀናልሃል፡፡” (ምሳ.3፥5-6) ብሎ ነው የሚመክረው፡፡ The Word encourages total dependence on Him for He is faithful. ሐጌና ዘካሪያስ በመዝሙራቸው እግዚአብሔር የፈረስ ኃይል እንደማይወድድ፣ በሰው ጭን እንደማይደሰት ተናግረዋል፡፡ ይልቁንም እግዚአብሔር በምሕረቱ በሚታመኑ እንደሚደሰት ነው በዝማሬያቸው ያስተማሩት (መዝ.147፥10-11)፡፡ ነቢዩ ኤርምያስም “በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው። በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ይሆናል፥ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፤ ሰውም በሌለበት፥ ጨው ባለበት ምድር በምድረ በዳ በደርቅ ስፍራ ይቀመጣል። በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው።” (ኤር.17፥5-7) ብሎ ተናግሯል፡፡ እግዚአብሔር በዚሁ ነቢይ አንደበት “ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው። ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና።” (ኤር.9፥23-24) ብሏል፡፡ ከላይ ያለው እንዳለ ሆኖ፣ ጌታ አምላክ በራሳቸው ኃይልና በፍጥረት ጥበብና ዕውቀት የሚመኩትን በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ሥፍራዎች ገሥጿል፡፡ “ስለ እርዳታ ወደ ግብጽ ለሚወርዱ፣ በፈረሶችም ለሚደገፉ፣ ስለ ብዛታቸውም በሰረገሎች እጅግ ብርቱዎችም ስለ ሆኑ በፈረሰኞች ለሚታመኑ፣ ወደ እስራኤልም ቅዱስ ለማይመለከቱ ወዮላቸው፡፡” (ኢሳ.31፥1) ብሎ ያስጠነቅቃል፡፡ በዚህ ዘመን አገላለጽ፣ በባንክ ደብተራቸው ለሚመኩ፣ በሀብታም ዘመዶቻቸው ለሚጓደዱ፣ በባለሥልጣናት ለሚታመኑ፣ ባላቸው ዕውቀትና ጥበብ ለሚኮሩ ወዮላቸው ማለቱ ነው፡፡ ለምን ወዮላቸው? በፈታኝ ሰዓታት እነዚህ መደገፊያዎች ወንዝ አያሻግሩምና ነው፡፡ ዲግሪ እያለኝ መሥራት አቅቶኝ ያውቃልና የምናገረው ዝም ብሎ የዳበሳ ወሬ አይደለም፡፡ የእሱን ረድኤት ስጠይቅ ግን ታሪክ ነበር የተቀየረው፡፡ በእርግጥ እርሱ አስተማማኝ መሸሸጊያ መሆኑን ያስመሰከረ፣ ጽኑ ረዳት የሆነና በሕይወታችን ዳስሰን ያረጋገጥነው ታማኝ አምላክ ነው፡፡ ስሙ ለዘላለም የተባረከ ይሁን! “Riches take wings, comforts vanish, hope withers away,but love stays with us. Love is God.” ― Lew Wallace ተባረኩ! --- በቀለ በላቸው @nazrawi_tube
Show more ...
1 303
3
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊
1 224
0
💐 #የማለዳ_ስንቅ አንተ ምስጋናዬ ነህ Live worship እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tub

አንተ_ምስጋናዬ_ነህ_አማኑኤል_ጥላሁን.mp3

1 472
7
💐 #የማለዳ_ስንቅ ትሑታን የራሳቸውን መንገድ አይመርጡም (ክሌቱ)! ባለፈው ሳምንት "ትሑታን የራሳቸውን መንገድ አይመርጡም" በሚል ርእስ አንድ ሐሳብ አጋርቻችሁ ነበር። የተነሣሁበት ክፍል የሚከተለው ነው:- “እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው? በሚመርጠው መንገድ ያስተምረዋል (አካሄድ) ------›ነፍሱም በመልካም ታድራለች (ባርኮት)፡፡” (መዝ.25፥12-13፤ አጽንኦት የእኔ)! ለመሆኑ ይህንን መርሕ በቅጡ መረዳትና ማስተዋል ፋይዳው ምንድነው? ብዙ ጥቅሞች አሉት ብዬ አምናለሁ። በተለይ አንዳንድ አሳዛኝ ነገሮች በሕይወታችን ሲገጥሙን "ለምን እኔን?" ከሚል ብዙ ጊዜ መልስ ከማይኖረው ጥያቄ እንወጣለን። እግዚአብሔር በወደደው መንገድ ቢወስደንም (እስቸጋሪና አስጨናቂ እየሆነም) ያረፈ ሕይወት ይኖረናል። በሚደርሱብን መከራዎችም ተስፋ አንቆርጥም። ደግሞም አጉረምራሚ አንሆንም። ያ ብቻ አይደለም—"የጻድቃን መንገድ ቅን ናት፤ አንተ ቅን የሆንህ የጻድቃንን መንገድ ታቃናለህ።" (ኢሳ.26፥7) ይላል አይደል? ባይመችም እግዚአብሔር በሚሻው መንገድ እንዲመራን ራሳችንን በፈቃደኝነት እንሰጠዋለን። ጊዜ ስታገኙ ይህንን ከላይ ያለውን እሳቤ ይዛችሁ የሚከተሉትን ክፍሎች እዩአቸው:- ☛"ገሮችን (the meek) በፍርድ ይመራል፥ ለገሮችም መንገድን ያስተምራቸዋል።" (መዝ.25፥9)፤ ☛"አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።" (መዝ.32፥8)፤ ☛"በቸርነትህ የተቤዠሃቸውን ሕዝብህን መራህ፤ በኃይልህ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ አገባሃቸው።" (15፥13)፤ ☛"በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።" (ምሳ.3፥5-6)፤ ☛"እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም።" (ዮሐ.8፥12)። The antidote to frustration is a calm faith, not in your own cleverness, or in hard toil, but in God's guidance. -Norman Vincent Pearle ጌታ ሆይ እባክህ ከአንተ ጋር እንድንስማማ እርዳን! --- በቀለ በላቸው @nazrawi_tube
Show more ...
1 376
1
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊
1 183
0
💐 #የማለዳ_ስንቅ ይፃፍልኝ | ህሊና ዳዊት addis mezmur እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tub

ይፃፍልኝ ህሊና ዳዊት.mp3

1 310
10
💐 #የማለዳ_ስንቅ በእውቀት ፍጹም የሆነ ከአንተ ጋር አለ (ኢዮብ 36፥4) የእግዚአብሔር ቃል ብዙ ባሕርያት አሉት፡፡ ከእነዚያ መኻል እኔን በግሌ የሚያስደነቀኝ ነገር፣ ለረጅም ጊዜ እያነበብነው ስናልፈው የኖርነው አንድ ክፍል አንድ ቀን ግን ድንገት ልብን ሰቅዞ የሚይዝ መልእክት ሆኖ ከተፍ ማለቱ ነው፡፡ በዚህ ሳምንት ያስደነቀኝ ምሳሌ 15፥11 ላይ የሚገኝ መልእክት ነው፡፡ እንዲህ ይነበባል፡-“ሲኦልና ጥፋት (Sheol & Abbadon ጥልቅ ናቸው) በእግዚአብሔር ፊት የታወቁ ናቸው፤ ይልቁንም የሰዎች ልብ የታወቀ ነው።”! በሌላ ስፍራ ቅዱስ ቃሉ “የሰው የውስጥ ሐሳቡና ልቡ የጠለቀ ነው።” (መዝ.64፥6) ይላል፡፡ ቢሆንም የሰው ልብ በእግዚአብሔር ፊት የታወቀ ነው! ወገኖቼ የሲኦልን ጥልቀት አስባችሁታል፡፡ ከዚያ ሁሉ ይልቅ የሰው ልብ ይጠልቃል፣ ቢሆንም በእግዚአብሔር ፊት የተገለጠ እና የተራቆተ ነው (ዕብ.4፥13)፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በኤርምያስ መጽሐፍ “የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል?” ብሎ ይጠይቃል፡፡ አዎ፣ እጅግ ጥልቅና አሳች ነውና ማንም አያውቀውም ከፍጥረት ገዢው እግዚአብሔር በቀር፤ ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ ይሰጥ ዘንድ ልብን የሚመረምረው ኵላሊትንም የሚፈትነው እርሱ ግን ያውቀዋል (17፥10)፡፡ ማንኛውም ጥልቅ የሆነ ነገር ሁሉ የተገለጠ ነው፡፡ ይልቁንም የሰው ልጆች ልብ በሚገባ የታወቀ ነው፡፡ ስለሆነም ነው ዳዊት “በውኑ ጨለማ ትሸፍነኛለች ብል፥ ሌሊት በዙሪያዬ ብርሃን ትሆናለች፤ ጨለማ በአንተ ዘንድ አይጨልምምና (እንኳን የሰው ልብ ይቅርና)፥ ሌሊትም እንደ ቀን ታበራለችና፤ እንደ ጨለማዋ እንዲሁ ብርሃንዋ ነው።” (መዝ.139፥11-12) ብሎ የተቀኘው፡፡ God is an important person because he knows all things — all motives, all causes, all designs, all effects, all structures, all secrets, all possibilities. ይህንን እውነታ መረዳት ከእርሱ ጋር ባለን መስተጋብርም ሆነ ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት የምር የምሩን እንድንኖር ይረዳናል፤ ታዛቢ እንዳለ conscious እንሆናለንና፡፡ ከሸንጋይነት፣ ከግብዝነት፣ ከአስመሳይነትና ከሌሎችም ድራማዊ ምልልሶች ራሳችንን እንድንጠብቅ ጥሩ insight ነው የሚሆነን፡፡ በትሕትናና በእውነተኛ ንስሐ በፊቱ እንድንመላለስ ያደርገናል፡፡ እግዚአብሔር ሆይ፣ በፊትህ በንጽሕና እንድንመላለስ እርዳን! --- በቀለ በላቸው @nazrawi_tube
Show more ...
1 786
7
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊
1 296
0
💐 #የማለዳ_ስንቅ እፈልግሃለው | ዳዊት ጌታቸው ከአዲሱ አልበም የተወሰደ ሙሉ አልበሙን ለማግኘት👇 @amnihalehubot እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

798295622.mp3

2 055
21
💐 #የማለዳ_ስንቅ እግዚአብሔርን ፈልጉ ሕያዋንም ሁኑ! ርእሱ ላይ ያለችው ድንቅዬ መልእክት በዚህ ሳምንት መዝሙር 69ን ሳነብብ በልቤ ላይ በደማቁ የተጻፈች ናት (ቁ.32)። ዛሬ ደግሜ ስላነበብኳት ነው ላጋራችሁ የወደድሁት! ለመሆኑ "ሕያዋን ሁኑ" ማለት ምን ማለት ነው? የKJVው ትርጉም "Seek God and your heart will be revived.” ነው የሚለው። “Revived” መሆን ማለት መነቃቃት፥ መለወጥ፥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ፥ መታዘዝ፥ በመንፈስ መመላስ ማለት ነው። እኔ ይኼንን ቃል ሳሰላልና ሌሎች ተመሳሳይ ክፍሎችን ሳጠና ለክርስትና ሕይወታችን ማበብ/ ማደግ/ መለምለም የእግዚአብሔርን ፊት ሳያሰልሱ መፈለጉ ወሳኝ እንደ ሆነ ነው የገባኝ። በመሆኑም ነው ብዬ አምናለሁ መዝሙረኛው "እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም፥ ከመከራዬም ሁሉ አዳነኝ። ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል፥ ፊታችሁም አያፍርም።" (መዝ.34፥ 4-5) ብሎ የመከረው። ለመሆኑ እንዴት ባለ መንፈስ ነው ፊቱን የምንሻው? ይኸው መዝሙር 34 መልሱን ይሰጠናል:-"እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፥ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል።" (ቁ.18) ብሎ— We need humility and brokenness! በዚህ ዐውድ ልናጠናቸውና ልናሰላስላቸው የሚገቡ አራት ክፍሎችን እነሆ:- ✈"በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።" (1ዜና.16፥ 10-11)፤ ✈"እኔ የሚወድዱኝን እወድዳለሁ፥ ተግተው የሚሹኝም ያገኙኛል።" (ምሳ.8፥17)፤ ✈"አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና፥ የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘላለም ይጥልሃል።"(1ዜና.28፥9)፤ ✈"እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ። እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ፤ ከእናንተም ዘንድ እገኛለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ምርኮአችሁንም እመልሳለሁ።" (ኤር.29፥12-14)። መልካም ጊዜ ተባረኩ! --- በቀለ በላቸው @nazrawi_tube
Show more ...
1 843
9
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊
1 459
1
💐 #የማለዳ_ስንቅ አምንሃለው | ዳዊት ጌታቸው ከአዲሱ አልበም የተወሰደ ሙሉ አልበሙን ለማግኘት👇 @amnihalehubot እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

1555507372.mp3

1 731
27
💐 #የማለዳ_ስንቅ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን! እግዚአብሔር “በጨለማ የተሰወረውን…ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ” (1ቆሮ.4፥5) ነው፡፡ ሰው ፊትን ያያል፣ እርሱ ግን የሰውን የውስጡን ስሜትና ሐሳብ ያውቃል፡፡ እናም ከእግዚአብሔር ራስን መሰወር አይቻልም፡፡ ስለዚያም ነው ያንን እውነታ በጥልቀት የተረዳው ዳዊት “የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።” (መዝ.19፥14) ብሎ አምላኩን የተማጸነው፡፡ ስለሆነም ነው የሚወደውን ልጁን ሰሎሞንን “አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና፥ የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘላለም ይጥልሃል።” (1ዜና.28፥9) ብሎ የመከረው፡፡ ይህንን በተመለከተ የብዙ መንፈሳዊ ሥራዎች ባለቤት የሆኑት Jerry Bridges እንዲህ መክረዋል፡-“God searches the heart and understands every motive. To be acceptable to Him, our motives must spring from a love for Him and a desire to glorify Him.”! እግዚአብሔር የልብ አምላክ ነውና ሁሉን ያያል፣ ሁሉን አብጠርጥሮ ያውቃል፤ “እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።” (ዕብ.4፥13)፡፡ በዚህ ረገድ አራት ግሩም ክፍሎችን ልጋብዛችሁ፡- ➤ “እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን ‘ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል’ አለው።” (1ሳሙ.16፥7)፤ ➤ “እንዲህም አላቸው:-ራሳችሁን በሰው ፊት የምታጸድቁ እናንተ ናችሁ፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ፊት ርኵሰት ነውና።” (ሉቃ.16፥15)፤ ➤ “እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ ኵላሊትንም እፈትናለሁ።” (ኤር.17፥10)፤ ➤ “የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለች፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል።” (ምሳ.21፥2)፡፡ አባት ሆይ፣ ከታይታ ሕይወት አውጥተህ የልብ ሰው አድርገን! --- በቀለ በላቸው @nazrawi_tube
Show more ...
2 181
17
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊
1 410
0
💐 #የማለዳ_ስንቅ ቢገልኝም እንኳን | ደረጀ ከበደ (ዶ/ር) እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

Bigelegnem Esun Tebikalehu.mp3

1 638
11
💐 #የማለዳ_ስንቅ ትሑታን የራሳቸውን መንገድ አይመርጡም! ብዙ ጊዜ ጌታ አምላክ እኛ በምንፈልገው መንገድ ላይ መጥቶ ሐሳባችንንና መሻታችንን እንዲያጸድቀው (to endorse it) ነው ፍላጎታችን፡፡ የራሴን ሕይወት የኋሊት ስመለከተው፣ ሳጤነውና የጸሎት ደብተሬን ስቃኘው ፈተናዬ እሱ እንደ ሆነ ተገንዝቤአለሁ፡፡ እርሱ የሚመክረኝና የሚያሳየኝ መንገድ ለሥጋዬና ለስሜቴ ስለማይመች በብዙ ትግል ነው የምስማማው፡፡ ባንዳንድ ጉዳዮች ሳልስማማ ረጅም ጊዜ የምቆይባቸው ጊዜያት መኖሩንም አልደብቃችሁም፡፡ የብዙዎቻችሁም ዋና ፈተናና ትግል ይኸው ይመስለኛል፡፡ ምነው እግዚአብሔር አምላክ እንደ ይሳኮር ትሑትና ታዛዥ ቢያደረገን? ቃሉ ስለ እሱ ሲመሰክር፣ “ይሳኮር አጥንተ ብርቱ አህያ ነው፤ በበጎች ጉረኖም መካከል ያርፋል፡፡ ዕረፍት መልካም መሆንዋን አየ፣ ምድሪቱም የለማች መሆንዋን፣ ትከሻውን ለመሸከም ዝቅ አደረገ፣ በሥራም ገበሬ ሆነ፡፡” (ዘፍ.49፥14-15) ይላል፡፡ ወገኖቼ ሰው እንደ እንጨት ተገትሮ እንዴት ቀንበር መሸከም ይቻለዋል? ክርስትና ሸካራ ግን የመንፈስ ነጻነት የሚያጎናጽፍ መንገድ ነው፡፡ የራሳችንን ፈቃድ ትተን የእርሱን ሐሳብ ለመኖር የምንስማማበት የትሑታን መንገድ ነው፡፡ ኢየሱስ “በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፣ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ፡፡” (ሉቃ.9፥23) ብሎ በግልጥ ተናግሮ የለ? እንዲያ ዓይነት አካሄድ ነው የተመረጠልን፡፡ ለመሆኑ ይመቻል? ውጣ ውረድ የበዛበት ነውና አይመችም፤ ፈተና ይበዛዋል፡፡ ሕመም አለው ወይ? በእርግጥ፡፡ ነገር ግን ሰላምና እረፍት ያለበት ነው። ሆኖም ግን ዕለት ዕለት እየሞትን የምናገኘው መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ለዚህ ነው ንጉሥ ዳዊት “ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችህ ወደድሁ” (መዝ.17፥4) ያለው፡፡ ቢያመኝም እንኳ ካንተ ጋር እስማማለሁ ማለቱ ነው፡፡ “እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው? በሚመርጠው መንገድ ያስተምረዋል (አካሄድ) ------›ነፍሱም በመልካም ታድራለች (ባርኮት)፡፡” (መዝ.25፥12-13፤ አጽንኦት የእኔ) ጌታ ኢየሱስ በመረጠው መንገድ እያስተማረ ይመራን ዘንድ፣ የተስማማ/ የተመቸ ልብ ይስጠን! መልካም ጊዜ ተባረኩልኝ! --- በቀለ በላቸው @nazrawi_tube
Show more ...
1 649
14
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊
1 391
1
💐#የማለዳ_ስንቅ ሰው ያረገኝ: ዘማሪ አገኘው ይደግ Live worship እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

ሰው ያደረገኝ agegnew yideg.mp3

1 618
1
💐 #የማለዳ_ስንቅ ጸጋ ምንድነው? ጸጋን ሳስብ ቶሎ ወደ አእምሮዬ የሚመጣው የዮናታን ልጅ ሜምፊቦስቴ ነው (2ሳሙ.9):: የሰው እጅ/ መዋጮ የሌለበት መሆኑን ያስታውሰኛልና! ጄሪ ብሪጅስ እንዲህ ይላሉ ጸጋን ሲገልጹት:-"God’s free and unmerited favor shown to guilty sinners who deserve only judgment. It is the love of God shown to the unlovely."! ጸጋ ማለት ገንዘብ የሌላቸው እንዲሁ በነጻ የሚገዙት ስጦታ ነው በክርስቶስ ተከፍሎአልና (ኢሳ.55፥1)! C.Samuel Storms ደግሞ እንዲህ ይላሉ:-"Grace ceases to be Grace if God is compelled to bestow it in the presence of human merit….Grace ceases to be Grace if God is compelled to withdraw it in the presence of human demerit. …” “Legalism says God will love us if we change. The gospel says God will change us because He loves us.” ― Tullian ጸጋን ለመቀበል የሚያስፈልገው ትሕትና ነው:- Nothing in my hand I bring, Simply to Thy cross I cling! —Augustus Toplady (Bridges, Jerry, Transforming Grace, 23) ☛”በተነ፥ ለምስኪኖች ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ያበዛላችሁ ይችላል።” (2ቆሮ.9፥8-9)፤ ☛”እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።” (ዮሐ.1፥16)፤ ☛”ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ። እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል።”(ያዕ.4፥6)። ጌታ ሆይ ጸጋህን አብዛልን! --- በቀለ በላቸው @nazrawi_tube
Show more ...
1 658
9
💐 በማለደ በረከት ይዘን መጥተናል #የማለዳ_ስንቅ ፕሮግራማችን ተጀመረ😁 ዘወትር 12:00am ይከታተሉንና በዝማሬና በቃል ይበረኩ 😊
1 458
0
💐#የማለዳ_ስንቅ ብዙ ሃያላን ነበሩ በአምላኬ ላይ የተኩራሩ ቅዱሱ ላይ የተገዳደሩ ያ ዝናቸው አምድ ለብሶ ታሪካቸው ተቀልብሶ አለ ጌታ በላያቸው ነግሶ አዝ፦ ክቡር ክቡር ሃያል ክቡር ለዘለዓለም የምትኖር አምላካችን እግዚአብሔር (፪x) ዘማሪ አዲሱ ወርቁ እባክዎትን ያጋሩ @nazrawi_tube @nazrawi_tube

01 Addisu Worku - 01 Kebur Kebur.mp3

1 829
11
Last updated: 13.01.22
Privacy Policy