en
Feedback
የጥበብ ማዕድ

የጥበብ ማዕድ

Open in Telegram

ዝም ብለህ ተቀላቀል!

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel የጥበብ ማዕድ

Channel የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 16 107 subscribers, ranking 5 309 in the Religion & Spirituality category and 2 094 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 16 107 subscribers.

According to the latest data from 01 July, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 660 over the last 30 days and by 29 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 2.96%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 2.05% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 477 views. Within the first day, a publication typically gains 331 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 10.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
ዝም ብለህ ተቀላቀል!

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 02 July, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

16 107
Subscribers
+2924 hours
+2067 days
+66030 days
Posts Archive
#ዓሳ_ጎርጓሪ_ዘንዶ_ያወጣል ከታች በፎቶ የሚታዩት ፈረንሳዊቷ ወ/ሮ Jeanne Calment ይባላሉ። በ1875  ነው  የተወለዱት፤ ይህ ማለት የፓሪሱ ኤፊል ታወር ተሰርቶ ሲመረቅ እሳቸው  የ14 ዓመት ታዳጊ ነበሩ ። ይህ ብቻ አይደለም ..እኚህ ሴት ሰአሊውን ቬንሰንት ቫን ጎኽ ን  ሁሉ በአካል ያውቁት ነበር  ። ....... እና እኚህ አርጅተው ብዙ ጎብኝና ጠያቂ ያጡት አዛውንት በ90 ዓመታቸው ላይ ቤታቸውን ለመሸጥ ፈልገው ገዥ ሲያጠያይቁ ከአንድ ጠበቃ ጋር ተገናኙ ። ይህ ጠበቃ André-François Raffray  ይባላል።  የሴትየዋን በእድሜ መግፋት ካየ በኋላ ይህን ቤት መግዛት እንደሚፈልግ ቀርቦ አናግሯቸው  ዝርዝር ጉዳዩን ማስረዳት ጀመረ ። .... "በ90 አመት እድሜዎ ፣በስተርጅና ሌላ ቤት ፍለጋ መንከራተት የለብዎትም። በህይወት እስካሉ ድረስ እዚሁ በቤትዎ ሊቆዩ ይችላሉ ። እና እኔም የቤቱን ዋጋ በአንድ ጊዜ ሳይሆን በየወሩ 2,500 ዶላር እሰጥዎታለሁ ። ከእርስዎ የሚጠበቀው ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ይህን ቤት ለኔ ያወርሱኛል"  አላቸው ። የ90 አመቷ አዛውንት Jeanne Calment በሀሳቡ ተስማምተው ፤ ሰውየው ከቤቱ ዋጋ ላይ  በወር 2500 ዶላር ሊሰጣቸው  በምትኩ ደግሞ  ቤቱን ሊያወርሱት ተስማምተው ፈረሙ ። .... አቅመ ደካማዋ አዛውንት Jeanne በእድሜም ሆነ በህመም ምክንያት ይህን ውል በፈፀሙ በወርም ሆነ በስድስት ወር ቢሞቱ ጠበቃው መሀል ፓሪስ የሚገኘውን ይህን  የሴትየዋን ቤት ይወርሳል ። .... አንድ ወር ሞላ።  ጠበቃው  ወርሀዊ ክፍያውን 2,500 ይዞ መጣ።  ሴትየዋ ልክ ባለፈው ወር እንዳያቸው ናቸው። ንቁ እና  ጤናማ ። ..... እንዲህ እንዲህ እያለ ለስድስት ወራት እየተመላለሰ ብሩን ሰጣቸው ። ወ/ሮ Jeanne Calment በስተርጅና በጣለላቸው  ሰው በሚሰጣቸው ገንዘብ የሚወዱትን ወይን እና ምግብ እያገኙ በራሳቸው ቤት ሆነው   እርጅናን እያጣጣሙ ነው ። .... በዚህ ሁኔታ አመት አለፈ፣ ሁለት አመት... ሰውየው በየወሩ እየመጣ ክፍያውን መስጠቱን አላቆመም ። .... የሴትየዋን መድከምና በእድሜ መግፋት ግምት ውስጥ በማስገባት በቅርብ ሞተው ቤቱን አገኛለሁ ብሎ ያሰበው ጠበቃ  እንዳሳቡ ሳይሆን በየወሩ እየከፈለ አምስት አመት ሆነ ። .... ስድስት አመት፣ ሰባት ..አስር አመት አለፈ። አዛውንቷ ሴት አሁንም በህይወት  አሉ ። ...... እንዲህ እንዲህ እያለ ሀያ አመት ሞላ ። ...... ሰውየው ውል በገባው መሰረት በየወሩ እየመጣ እየሰጠ 20 አልፎ ፣25 ዓመት ሆነ።  በዚህ ወቅት ግን ሰውየው ለአመታት የከፈለው ገንዘብ  ከቤቱ  ዋጋ በልጦ ነበር ። ....... የ47 አመት ጎልማሳ  እያለ ላገኛቸው የ90 አመት አዛውንት የቤቱን ዋጋ በአንድ ጊዜ ከመክፈል ይልቅ ያንን መሳይ ተንኮል ያለበት ውል ሲፈርም አዛውንቷ ደክመዋልና በቅርብ ይሞታሉ በማለት ነበር ። André-François Raffray  ያሰበው ሳይሆን ቀርቶ አዛውንቷ የ 116 ኛ ዓመት የልደት በአላቸውን አከበሩ ። ... በዛው አመትም እራሱ ባመጣው ህግ ተገዶ የማያውቃቸውን አዛውንት ሲጦር የኖረው ይህ ሰው በ73 አመት እድሜው  ከሴትየዋ ቀድሞ በሞት ተለየ ። .......... በተረጋገጠ የልደት ሰርተፍኬት የአለማችን የረጅም እድሜ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ Jeanne Calment ከዚህ ሁሉ በኋላ  ለተጨማሪ ስድስት አመታት በህይወት ኖረው በ122 አመታቸው በ1991 ነበር ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ።

ተቃርኖ እውነትን ያጠፋብሃል! እውነት ደግሞ የሚኖር ነው።

ፍቅር የአለም ንጉስ ነው ። ክብር ደግሞ የአለም እኩሌታ ይመስላል፦ ምክንያቱም ሰዎች በሁለት መንገድ ሰውን ልናከብር እንችላለን። አንዱ በሀይል ፤ አንዱ በፍቅር ። ሀይል ግን ጊዜያዊ ነው ፤ ፍቅር ደግሞ ዘላለማዊ ።ለዚያም ነው ፍቅር የአለም ንጉስ ነው የምልህ። ክብር የሌለዉ ፍቅር ጨዉ እንደሌለዉ ምግብ ነዉ አይጣፍጥም መከባበርም ከሌለ ፍቅር ትርጉም ያጣል

ትልቁ መንገድ መሳት የማይወዱህን መውደድ ነው! ልፋትህ ሁሌ መሻትህን አያስገኝልህም ሚገባህን ሊሰጥህ ይችላል እንጂ! ስለዚ አትቁም ተንቀሳቀስ!!!

አንዳንድ ሰላም ማጣቶች ሰላምን ለማግኘት በተሞከሩ ሙከራዎች የሚከሰቱ ናቸው።

አንዳንዴ መናቅ እንደ ማክበር ነው ያኛው ወገን ሊረዳ ከቻለ!

፡ ሰው መሻቱ ሲጠፋበት እንዳልነበር ለመኖር ሲል ትጉህ መልኩን ያጠለሸ በሚያልፍ ቀን አያልፍ ቃል ገፊ መሆን ክብር መስሎት አንደበቱን ያበላሸ ከአዛዥ እስከ አጎብዳጅ ከጠፊው እስከ አለሁ ባይ ካለው እስከ ለማኙ ከከሀዲው እስከ ሀቀኛ ወትሮ ምህረትን ጠባቂ ከጌታው ፈውስን አማኙ የሚያፀና የእግዜር ፍቅር ከእውነት ደጃፍ እያለ ፍርድ ከሀዘን ኋላ የሚክስ ቀን በአምሳሉ ሰው ሆነን ሳለ "እኛ ማለት" ጠፍቶን ዋጋው ክፉ ሀሳብ ነው ያናናቀን ✍Mekdi @amen1995

እድል ምቾት ከሆነህ የእርካታን ዋጋ አታውቀውም!

"ኩርቢት"

"እንጋባ" ሲል ጠየቃት አሳምነው ። አልተቀበለችውም አስማሩ "ወንድምና እህትነቱ ይበልጣል" አለችው። ተስማሙ ቤት እየመጣ ይጠይቃታል። ቡና ታፈላለች ይጠጣሉ፣ ካላት ታቀርባለች ይበላሉ። አወግተው ይለያያሉ። የትዳር ነገር ዳግም አልተነሳም። አሳምነው አንድ ቀን በጠራራ ፀሀይ መጣ። እንደመጣ የደረበውን ሹራብ አውልቆ አስቀመጠ። ስለ ሙቀቱ ብዙ አውርተው ተለያዩ። አስምሩ አሰምነው ረስቶት የሄደውን ሹራብ ልብሷን ስታጥብ አጠበችለት። ዳግም ሲመጣ ደርቦ ደራርቦ ነበርና የሚያወልቀው እንጂ የሚደርበው ልብስ አላስፈለገውም ጃኬቱን አውልቆ ሄደ። አስምሩ እሱንም አጥባ አኖረችው ሱሪውን ደርቦ መጣ "ወበቀኝ!" አወለቀው። አስማሩ አጥባ አኖረችው ካፕርቱን ጥሎ ሄደ ፣አጥባ አኖረችው አንድ ቀን በጠራራ ፀሀይ ብርድ ልብሱን ለብሶ መጣ ፣አስማሩ "ምነው?" አለችው በጠራራ ፀሀይ ብርድ ሆዴ ገባ አላት ። "ምች ይሆናል" አለችው ። የምች መድኀኒት ብታሽለት ተሻለው ። ሲሻለው ብርድ ልብሱ አላስፈለገውም ጥሎት ሄደ። አስማሩ አጥባ አኖረችው። ትንሽ ቆይቶ ፍራሹን ተሸክሞ መጣ ። "ምነው?" አለችው ። "ላሳድሰው መሄዴ ነው ። አይቼሽ ልለፍ ብዬ ነው"አላት አመነችው ጨዋታው ደራ ፣ ፍራሹን ረስቶት ሄዶ ኖሮ እኩለ ሌሊት ቢመጣ አስማሩ ቦታ ስላጣች ፍራሹን ፍራሿ ላይ ደርባው ደረሰ..ያኔ "ተነሼ ከማለት "ጠጋ በይ" ማለት ቀልሎ ተገኘ። ጠጋ አለች 😊 ደራሲ:- ዓለማየሁ ገላጋይ

ቡጢህ በከባዱ እንዲሰማው እጅህን ለረጅም ጊዜያት በዝምታህ አጠንክረው!!!

ፈረሱን በቀላሉ ለመግራት ባሐሪውንና የትላንቱን ኑሮ መመለከት በጣም ወሳኝ ነው።

ሰላም መሆን ከፈለክ በየጊዜው ለራስህ ምህረትን አድርግ ያ ማለት ግን ስህተትህን ደጋግም አይደለም።

ራሳችንን ለሐላፊነት አብዝተን ከሰጠን ጭንቀትና ለነገሮች ተገጪነታችን ይጨምራል! በእርግጥ ጥንካሬን ቢሰጥህም ማንም ግን ያለህበትን ሁኔታ አይረዳልህም!

፡           ቀለም ስንጨልፍ አይደለም ለመድረክ በሰው ለመባረክ ለሙገሳ አጀባ ለአንባቢ ጭብጨባ ለንግድና ለትርፍ ፈራንክ ለመልቀም እንደዚህ አይደለም ... ልባዊ ነው ግጥም ዜማው የቅዱሳን ጥዑም የነፍስያ ተቀብሮም ወርቅ ነው ተነጥሮም ወርቅ ነው ሳይጀርስ ተገበያ                    "የፀሓይ እግሮች"

፡           ቀለም ስንጨልፍ አይደለም ለመድረክ በሰው ለመባረክ ለሙገሳ አጀባ ለአንባቢ ጭብጨባ ለንግድና ለትርፍ ፈራንክ ለመልቀም እንደዚህ አይደለም ... ልባዊ ነው ግጥም ዜማው የቅዱሳን ጥዑም የነፍስያ ተቀብሮም ወርቅ ነው ተነጥሮም ወርቅ ነው ሳይጀርስ ተገበያ                    "የፀሀይ እግሮች"

በታሪክ አጭር ዕድሜ ያለው ትዳር የቆየው ለ3 ደቂቃ ብቻ ነው። በ2019 ኩዌታዊ የሆኑት ጥንዶች የጋብቻ ውላቸውን ፈርመው ዘወር እንዳሉ ሙሽሪት ቀሚሷ ያደናቅፋታል እና ሙሽራው አዞሽ ከማለት ይልቅ ደ
በታሪክ አጭር ዕድሜ ያለው ትዳር የቆየው ለ3 ደቂቃ ብቻ ነው። በ2019 ኩዌታዊ የሆኑት ጥንዶች የጋብቻ ውላቸውን ፈርመው ዘወር እንዳሉ ሙሽሪት ቀሚሷ ያደናቅፋታል እና ሙሽራው አዞሽ ከማለት ይልቅ ደደብ ይላታል። እሷም ወድያው ዞራ ፍች ጠየቀች። እናንተ በሴቷ ቦታ ብትሆኑ ኖሮ ምን ትወስኑ ነበር?

የህንድ ወንዶች ሴት ይደፍራሉ። ከብት ያከብራሉ። ህንድ ውስጥ ላም የሚፈራ ወንድ ሴት እየደፈረ እያስቸገረ ነው። በሂንዱ እምነት ላም ከሴት ልጅ በላይ ትከበራለች። ይሄን የተረዱ የህንድ ሴቶች በወንድ
የህንድ ወንዶች ሴት ይደፍራሉ። ከብት ያከብራሉ። ህንድ ውስጥ ላም የሚፈራ ወንድ ሴት እየደፈረ እያስቸገረ ነው። በሂንዱ እምነት ላም ከሴት ልጅ በላይ ትከበራለች። ይሄን የተረዱ የህንድ ሴቶች በወንድ ላለመደፈር አንድ ዘዴ ዘየዱ። ቀንድ ተክሎ መሄድ። የዚህ ጊዜ ወንዱ ከመድፈር ይልቅ ለሴት መስገድ ጀመረ

ደቡብ አፍሪካ ላይ NYAOPE ተብሎ የሚጠሩ ወጣቶች የሰውን አፅም ለማጨስ ከመቃብር ውስጥ እያወጡ ነው። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ያለው ጥንቆላ አለም ላይ የለም ጥንቁልናቸው አደገኛ ከመሆኑ የተነሳ ህገ
ደቡብ አፍሪካ ላይ NYAOPE ተብሎ የሚጠሩ ወጣቶች የሰውን አፅም ለማጨስ ከመቃብር ውስጥ እያወጡ ነው። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ያለው ጥንቆላ አለም ላይ የለም ጥንቁልናቸው አደገኛ ከመሆኑ የተነሳ ህገ መንግስታቸው ላይ ሁሉ ሰፍሯል አንድ ሰው በጥንቁልና ሌላን ሰው ለመጉዳት ቢሞክር በወንጀል ህግ ይቀጣል

🙀ይህ ህንፃ መገኛውን በሆንግ ኮንግ ያደረገ ሲሆን የህዝቦች መኖሪያ ቤት ነው።
🙀ይህ ህንፃ መገኛውን በሆንግ ኮንግ ያደረገ ሲሆን የህዝቦች መኖሪያ ቤት ነው።