cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Rebi Media Network-(RMN)

Rebi Channel . . . join join join Create causative Generation

Show more
Advertising posts
379
Subscribers
-124 hours
No data7 days
-630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ወንድ እነዚህ ምልክቶች ራሱን ላይ ካለ በፍጥነት  ራስህን አውጣ! 1ኛ በየቀኑ ራስን ለማርካት መሞከር 2ኛ ሰዎች ሲኑቁን በዝምታ ማለፍ 3ኛ ለነገሮች በቀላሉ ስሜታዊ መሆን ማለቃቀስ 4ኛ መፅሀፍ ላለማንበብ የተለያዩ ምክንያቶች መደርደር 5ኛ ሁልጊዜም ሶሻል ሚዲያ ላይ መደመጥ ከእውነተኛ ግንኙነት መራቅ 6ኛ የወሲባዊ ቪዲዮ መመልከት 7ኛ ታላላቆችን አለማክበር... በቃ ሁሉም አንተ ለመጉዳት የመጣ ሲመስል 8ኛ ሁልጊዜም ሴቶችን ስትከተል 👇 ከእነዚህ ስሜቶች አንዱ ወይም ሁለቱ ብቻ ካሉብህ ብዙም አያሳስብ ታልፈዋለህ ግን ከአራት በላይ ካለብህ በፍጥነት ራስህን መክረ ተመልስ!
Show all...
አንዳንዴ . . . ያለ ነው! አንዳንድ ጊዜ ማመንታት ያለ ነው - በፍጹም ግን ወደ ኋላ አንመለስም! አንዳንድ ጊዜ መፍራት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንንበረከክም! አንዳንድ ጊዜ ተስፋ መቁረጥ ያለ ነው - በፍጹም ግን አናቆምም! አንዳንድ ጊዜ መሸነፍ ያለ ነው - በፍጹም ግን ሕይወት ከሚያቀብለን የየእለት ጦርነት አንሸሽም! አንዳንድ ጊዜ መድከም ያለ ነው - በፍጹም ግን ዝለን አንወድቅም! አንዳንድ ጊዜ ግራ መጋባት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንቅበዘበዘም! አንዳንድ ጊዜ በሰው መገፋት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከዚያ ሰው ውጪ መኖር አየቅተንም! አንዳንድ ጊዜ ድብርት ያለ ነው - በፍጹም ግን ደንዝዘን አንቀርም! አንዳንድ ጊዜ ለጥያቄ መልስ ያለማግኘት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከመጠየቅ አናርፍም! አንዳንድ ጊዜ ክፋት ያሸነፈ መምሰሉ ያለ ነው - በፍጹም ግን መልካምነትን አንጥልም! @T2T4T5
Show all...
ለተዓምር ተፈጥረሀል! ድንጋይ የተጫናቸው ትሎች እንኳን ያለ ምክንያት አልተፈጠሩም፤ ያለ ትሎች የአፈር ምህንድስና አይካሄድም ስለዚህ ዛፎች ይደርቃሉ፤ እንስሳት ያልቃሉ። ትሎች ለአላማ ከተፈጠሩ አንተማ ምን አይነት ተዓምር ልትሰራ እንደተፈጠረከ አስበው?! ወዳጄ አንተ የምታስፈልገው ሰው አለ፤ አንተ ብቻ የምትፈታው ችግር አለ፤ ያለ ምክንያት ወደዚህ አልመጣህም! 🙏 👇👇👇👇 @T2T4T5
Show all...
እንደንቦቹ! 👇 "ንቦች ከቆሻሻ ይልቅ ማር ይሻላል ብለው ለዝንቦች በማብራራት ጊዜያቸውን አያጠፉም" (ካልታወቀ ምንጭ) 🚶 እንደ ንቦቹ ዝም ብላችሁ ዓላማችሁ ላይ አተኩሩ!
Show all...
እንደንቦቹ! 👇 "ንቦች ከቆሻሻ ይልቅ ማር ይሻላል ብለው ለዝንቦች በማብራራት ጊዜያቸውን አያጠፉም" (ካልታወቀ ምንጭ) 🚶 እንደ ንቦቹ ዝም ብላችሁ ዓላማችሁ ላይ አተኩሩ!
Show all...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

👇 አንዳንዱ ነገር ልክ እንደ ምግብ በእሳት ውስጥ ካላለፈና ካልበሰለ አይፈለግም፣ አይሸጥምም፡፡ 👇 አንዳንዱ ነገር ልክ እንደ አይስክሬም በበረዶና በቀዘቀዘ ሁኔታ ውስጥ ካላለፈ አይፈለግም፣ አይሸጥምም፡፡ 👇 አንዳንዱ ነገር ልክ እንደቆዳ ካልለፋና ካልለሰለሰ አይፈለግም፣ አይሸጥምም . . . አንዳንዱ ነገር ልክ እንደ ጥሬ መሬት ላይ ተጥሎ ካልተረገጠ፣ ካልተቀበረና ካልተረሳ ጊዜ ጠብቆ አድጎና አፍርቶ አይፈለግም፣ አይሸጥምም . . .፡፡ 👇 የምታልፉበት ሁኔታ ዋጋና ትርጉም አለው!
Show all...
ሁሉንም ሰው ለማስደሰት ትታገላላችሁ? (Are you a people pleaser?) ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚታገል ሰው . . . •  የራሱን ሕይወት ሳይኖር የሚያልፍ ሰው ነው •  ሰዎች ለተሰማቸው ስሜት ሃላፊነቱን የሚወስድ ሰው ነው •  ጊዜውን፣ ገንዘቡን፣ የስሜት አቅሙንና ሌሎች ወሳኝ ነገሮች የሚከስር ሰው ነው •  የግል የቀይ መስመር የሌለው ሰው ነው . . . . . .
Show all...
ሁሉን ሰው ለማስደሰት አትታገሉ || Dr. Eyob Mamo || በዶ/ር ኢዮብ ማሞ || "ሁሉንም ሰው ለማስደሰት ከፈለጋችሁ ..."

ሁሉንም ሰው ለማስደሰት ትታገላለህ? ራስህን መዝነው 1. ሌሎች ሰዎች ስለተሰማቸው ስሜት አንተ ሃላፊነት ይሰማሃል? 2. አንድ ሰው በአንተ ላይ እንደተበሳጨ ወይም እንዳዘነ ስታውቅ ከልክ ባለፈ ሁኔታ በስሜትህ ላይ ጫና ያስከትልብሃል? 3. ሰዎች እንደፈለጉ ወዲህና ወዲያ የሚያደርጉህ አይነት ሰው እንደሆንክ ይሰማሃል? 4. በአንድ ጉዳይ ላይ ከሌሎች ሰዎች ተቃራኒ ሃሳብ እያለህ እንኳን ተቀባይነት አጣለሁ በሚል ሰበብ ያንን ሃሳብህን ከመናገር ይልቅ መተባበር ይቀልሃል? 5. ብዙ ጊዜ ግልጽ የሆነ ጥፋት እንዳልሰራህ እያወከው እንኳን ይቅርታ የመጠየቅ ዝንባሌ አለህ? 6. አለመግባባት እንዳይፈጠር ለማድረግ ከአቅምህ በላይ ስትታገል ራስህን ታገኘዋለህ? 7. ሰዎች ስሜትህን ሲጎዱት ስለሁኔታው ለሰዎቹ በግልጽ ማውራት ይከብድሃል? 8. ሰዎች አንድን ነገር እንድታደርግላቸው ሲጠይቁህ ማድረግ ባትፈልግም እንኳን ካለብህ የመገደድ ስሜት የተነሳ እሺ የማለት ዝንባሌ አለህ? 9. ሌሎች ሰዎች የሚፈልጉትን ነገር ስታይ ከዚያ በመነሳት እነሱን ለማስደሰት ስትል ሁኔታህን፣ ተግባርህንና ባህሪህን ትለዋውጣለህ? 10. ሰዎች በአንተ ላይ ያላቸው አመለካከት ጥሩ እንዲሆን ብዙ ስትሯሯጥ ራስህን ታገኘዋለህ? ከላይ ለተጠየቁት አስር ጥያቄዎች ከግማሽ በላይ ለሆኑት “አዎ” የሚል መልስ ከሰጠህ በዚህ ምእራፍ ለተጠቀሱት ነጥቦች አስፈላጊ ትኩረት በመስጠት ለውጥን ለማስተናገድ ጥረት አድርግ፡፡ መንስኤው አለመግባባትን ፍርሃት የአስተዳደግ ሁኔታ ቅድመ-ልምምድ መዘዙ የዋጋ ተመንን ማውረድ በሰዎች መጎዳት የውስጥ መራቆት መፍትሄው ራስህን አደላድል ሰዎችንለይተህ እወቅ ገደብህን አስምር #selfimprovement #selfawareness #happiness

መልቀቅ ሲሻል! 👇 “የኑሮ ጥበብ ያለው አንዳንድ ነገሮችን በመያዝና በመልቀቅ መካከል ሚዛናዊ አድርጎ በመኖር ውስጥ ነው” - Havelock Ellis 👆 ከጥበብ ገጽታዎ አንዱ የግል ሰላምህንና ጤንነትህን፣ የቤተሰብ ደህንነትን፣ ማሕበራዊም ሆነ ሃገራዊ አንድነትንና አጠቃላይ ሊዛቡ የማይገባቸውን መሰረታዊ የሕይወት ሂደቶችን ለመጠበቅ ሲባል መልቀቅ ያለብህን አመለካከት፣ መብት፣ ልማድ፣ የሕይወት ዘይቤና የመሳሰሉትን ሁኔታዎች መለየትን ያጠቃልላል፡፡ 👇 አንዳንድ መልቀቅ ያለብህ ነገሮች እንዲያውም ዋጋ ከፍለህና የሚያስፈልገውን መስዋእትነት አድርገህ መልቀቁ የሚያዋጣህ ጊዜ ሊኖር ይችላል፡፡ በአሁን ወቅት ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍልህም ልትለቃቸው የሚገቡህ ልማዶችና የሕይወት ዘይቤዎች መኖራቸውን አልጠራጠርም፡፡ 🙋 ቆም በል፣ አስብ፣ አዋቂዎችን ስማ፣ መሪዎችን አድምጥ፣ በዙሪያህ እየሆነ ያለውን አጢን . . . ምናልባት አንዳንድ ለብዙ ጊዜ ስለለመድካቸው መተው ያቃቱህ ነገሮች ለአንተና ለወዳጆችህ ጥፋት እንዳይሆን ተጠንቀቅ፡፡ መልቀቅ ያለብህን ልማድና ዘይቤ አሁኑኑ ልቀቅ፡፡ 👇 https://t.me/Dreyob
Show all...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

#ሕይወት_እንደ_ማዕበል_ሲሆን! አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንደ ማዕበል ነው፡፡ በሰላም ይሄዱ የነበሩ ነገሮች ልክ የተመካከሩ ይመስል በአንድ ላይ ይናጋሉ፡፡ የሁኔታዎች አልሳካ ማለት፣ ድንገተኛ ወጪዎች፣ የገንዘብ እጥረት፣ የጉዳዮች መጥመም፣ የሰዎች ክህደት፣ ስጋትን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች መከሰት፣ የጤንነት መቃወስን የሚጠቁሙ ምልክቶች . . . ልክ እንደ ማዕበል በአንድ ላይ ይመጣሉ፡፡ ይህ የተለመደ የሕይወት አካል የሆነ ክስተት በእኛም ላይ ሲደርስ መረጋጋት ወሳኝ ነው፡፡ ማዕበል ይመጣል፣ ልክ እንደመጣ ደግሞ ይሄዳል፡፡ ነፋስ ከየት እንደመጣ ሳናውቀው ወደ እኛ ይነፍሳል፣ ወደየት እንደሚሄድ ሳናውቀው ደግሞ ወደሌላ ቦታ ይነፍሳል፡፡ አይዟችሁ! ጽኑ! አትናወጡ! ተንጋግቶ የመጣው ተንጋግቶ ይሄዳል! መልካም  ቀን!   ዶ/ር ኢዮብ ማሞ 📕📕📕 (በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።) ቴሌግራም- https://t.me/teklu_tilahun ፌስቡክ ገጽ 1- https://bit.ly/3sNq5Kd ፌስቡክ ገጽ 2- https://bit.ly/3sJcsMa
Show all...
👍 2