cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Rebi Media Network-(RMN)

Rebi Channel . . . join join join Create causative Generation

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
375
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
-630 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

እውነት ብለሃል አብዛኞቻችን መለወጥ፣ ማደግ፣ሀብታም መሆን እንፈልጋለን ነገር ግን ዋጋ ለመክፈል አንፈልግም። ለዚህም ነው በምድራችን ስኬታማና ባለፀጋ ሰዎች በቁጥር ትንሽ የሆኑት። የምንፈልገው ስኬት ከእኛ የሚፈልገው መስዋዕትነት እንዳለ ስላልተገነዘብን ይሁን መቀበል ስላልፈለግን ብቻ አላውቅም ግን ዝም ብሎ በሆነ ተዓምር፣ወይ በዕድል የሆነ ነገር እንዲፈጠር እንፈልጋለን፡እንመኛለን። አንተ እንዳልካው "ስኬታማ መሆን ከፈለግክ ይህንና ያንን አድርግ" የሚል ሀሳብ የያዘ ጽሑፍ ብዙ ተመልካች የለውም። ቪዲዮ ተሰርቶ ብለቀቅም ስኬት በዕድል ወይም በውርስ ካልሆነ ዓላማና ግብ ስላለህ፣ጠንክረህ ስለሰራህ፣ተስፋ ባለመቁረጥ አይመጣም ብሎ ስላሳመነ ሞትቬሺን ምናምን ብሎ ያላግጣል። እውነታው ግን የስኬት ህግ ለሁሉም ስለሚሰራ ማንም ምንም ቢል ህጉን መለወጥ አይችልም። 🎯 @T2T4T5
إظهار الكل...
👍 1
የባሕርይ ችግር ሕመሞች - (Personality disorders) አንድ ሰው በቅርቡም ሆነ ለረዥም ጊዜያት የሚያሳያቸው ባሕርያት (ከጉርምሥና ወይም ወጣትነት ጀምሮ ያለው አጠቃላይ ጠባዩ) ከአካባቢው ጋር ፍፁም የማያስማሙት ሲሆኑ የባህርይ ችግር ሕመም (ፐርሰናሊቲ ዲስኦርደር) አለበት ይባላል፡፡ የአንድ ሰው ተፈጥሮአዊ ባሕርይ (ፐርሰናሊቲ ትሬይት) ግለሰቡ አካባቢውን ወይም ራሱን በተመለከተ የሚሰማው ስሜት፣ አተርጓጎም እና አስተሳሰብ ሲሆን ዘርፈ ብዙ በሆነ ማኅበራዊ እና ግለሰባዊ ሁኔታ ይገለጻል፡፡ ይህ ተፈጥሮአዊ ባሕርይ ሊቀየር የማይችል፤ ከአካባቢው የማይገጥም፤ የማይጠፋ እና በማኅበራዊ ሕይወት እና በሥራው ላይ ከባድ መሰናክል ሲፈጥርበት የባሕርይ ችግር ሕመም ተከሥቷል ይባላል፡፡ ግለሰቦቹ ስለአካባቢያቸውም ሆነ ስለራሳቸው ያላቸው አመለካከት ሥር የሰደደና ሊስማማ የማይችል አካሄድ ያለው ሲሆን ይህ ባሕርይ ወይም አፈጣጠር በአንድ ወቅት ብቻ የሚከሠት ሕመም ሳይሆን የረዥም ጊዜ ጠባይ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ጊዜያዊ የድብርት ሕመም ሲገጥመው የባሕርይ ችግር አለበት ለማለት አይቻልም፡፡ ሕመሙ ያለባቸው ሰዎች የባሕርይ ችግር እንዳለባቸው አያውቁም፣ ወደ ሕክምና የሚሄዱትም በትዳራቸው ወይም በሥራቸው ላይ ችግር ስለተከሠተ፣ በሱስ ምክንያት እና አብዛኛውን ጊዜ በድብርት ሕመም የተነሣ ነው፡፡ 👉👉ዓይነቶቹ:- ዐሥር ዓይነት የባሕርይ ችግር ሕመሞች ያሉ ሲሆን በሦስት ምድቦች ውስጥ ተከፋፍለዋል፡፡ ከሦስቱ ምድብ የማይገጥም የባሕርይ ሕመም ከሆነ ደግሞ ‹‹ሊመደብ ያልቻለ›› ይባላል፡፡ 👉ምድብ (ክላስተር) A - (አፈንጋጭ የሚባሉ ሕመሞች) ° ° ፓራኖይድ (ተጠራጣሪ) ° ስኪዞይድ (ራሱን ከማኅበራዊ ሕይወት የሚያገል) ° ስኪዞቲፓል (ማኅበራዊ ሕይወት በጣም የሚረብሸውና ከእውነታው የተነጠለ አእምሮ ያለው) 👉ምድብ B - (ድፍረት የሚታይባቸው ሕመሞች) ° አንቲሶሻል (ማኅበራዊ ዕሴቶችን የሚያስጠላ ሕመም) ° ቦርደርላይን (ስሜቱን፣ ባሕርዩን፣ ወዳጅነቱን የሚቀያይር) ° ሂስትሪዮኒክ (ልታይ ልታይ የሚል፣ ስሜታዊ እና ስሜቱ በቀላሉ የሚነካ ባሕርይ) ° ናርሲሲስቲክ (በጣም ተፈላጊ ነኝ የሚያስብል፣ ትኩረት እና አድናቆት የሚፈልግ፣ ወዳጅነቱን የሚያበላሽ እና የሰው ስሜት የማይገባው) 👉ምድብ C - (ጭንቀት ያለባቸው ሕመሞች) ° አቮይዳንት (ማኅበራዊ ሕይወት በጣም የሚያስጨንቀውና ራሱን የሚያገል፣ ማኅበራዊ ብቃት የለኝም እና ትንሽ ነኝ ብሎ የሚያስብ፤ ነቀፌታ ሲደርስበት ስሜቱ በጣም የሚነካ፣ ወዳጅነትን ለመመሥረት ግን ጠንካራ ፍላጐት ያለው) ° ዲፔንደንት (ሌሎች ካልመከሩትና ካላረጋጉት በስተቀር ቀላል ውሳኔ እንኳን ማድረግ የማይችል) ° አብስሲቭ ኮምፓልሲቭ (የሚረብሹ ሐሳቦች እያወኳቸው ተደጋጋሚ ያልተለመዱ ድርጊቶችን የሚያደርጉ) 👉👉መንሥኤዎች፦ ° ሥነ ልቦናዊ ሁኔታዎች፡- ግለስቡ በልጅነቱ ከሰዎች ጋር በተለይም ከወላጆቹ ወይም ከተንከባካቢዎቹ ጋር የነበረው ግንኙነት በባሕርዩ ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡ ራሳቸው የባሕርይ ችግር ሕመም ያለባቸው ወላጆች ልጆቻቸውን ለሕመሙ ያጋልጧቸዋል፡፡ °የዝርያ ሁኔታዎች፦ በቤተሰብ ውስጥ በአንዱ ላይ የባሕርይ ችግር ከተከሠተ፣ በተለይም በሌላውም አካል ላይ ይህ የባሕርይ ሕመም ወይም በክላስተሩ ውስጥ ያለ ሌላ ሕመም ሊከሠትበት ይችላል፡፡ ሌላ የአእምሮ ሕመም በቤተሰቡ ውስጥ ተከሥቶ ከነበረ፣ በአንዱ አባል ላይ የባሕርይ ችግር የመከሠት ዕድል አለ፡፡ ° ማኅበራዊ እና የባህል ሁኔታዎች፦ በአፈነገጡ ማኅበራዊ ወይም ባህላዊ ሁኔታዎች ውስጥ ያደገ ወይም የኖረ ሰው ለባሕርይ ችግር ሕመሞች ይበልጥ ይጋለጣል፡፡ ልዩ ኢኮኖሚያዊ ክሥተቶችም እንዲሁ፡፡ 👉👉የበሽታው ሥርጭት፦ ከአጠቃላይ ሕዝቡ ውስጥ ከ10 እስከ 20 በመቶ የሚሆነው አንድ ወይም ከዚያ የበለጠ ችግር ሕመም አለበት፡፡ በሳይካትሪ ሆስፒታሎች ውስጥ ቁጥሩ ከዚህ በጣም ይጨምራል፡፡ ለምሳሌ የድብርት ሕመም በተደራቢነት ሲኖር ሕሙማኑ በአብዛኛው ዕድሜያቸው ይቀንሳል፣ ያልተረጋጋ ትዳር ይኖራቸዋል፣ በሽታውን የቀሰቀሰባቸው ጫና መኖሩን ይናገራሉ፤ ቀለል ያለ ራስን የመግደል ሙከራም ያደርጋሉ፡፡ አንዳንዶቹ የባሕርይ ሕመሞች (ለምሳሌ፦ አንቲሶሻል፣ ስዚዞይድ፣ አብሰሲቭ ኮምፓልሲቭ) ይበልጥ በወንዶች ላይ ይታያሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ (ለምሳሌ አቮይዳንት እና ዲፔንደንት) ይበልጥ በሴቶች ላይ ይታያሉ፡፡ 👉👉ሕክምና፦ የባሕርይ ችግር ሕመም በተደራቢነት ካለ መድኃኒቶች ብዙም ውጤታማ አይሆኑም፡፡ ሥነ ልቦናዊ ሕክምናዎች ችግሮችን የመፍታት ቴክኒኮች፣ ብስጭትን የመቆጣጠር ቴክኒኮች፣ ለራሱ የመቆም ብቃት ማዳበሪያ ቴክኒኮች እና ማኅበራዊ ክህሎትን ማዳበሪያ ቴክኒኮች ናቸው፡፡ ቤንዞዳያዜፓይን መድኃኒቶች ሱሰኝነት ስለሚያመጡ አይታዘዙም፡፡ 🙏 ምንጭ፦ "የአእምሮ ሕመሞች እና ሕክምናቸው" ከተሰኘው የዶክተር አብርሃም ክብረት መጽሐፍ የተወሰደ
إظهار الكل...
#ተመሳሳይ_ምርት_አትሁን_ለየት_ብለህ_ውጣ! ስኬታማ ለመሆንና በበቂ መጠን ለመሸጥ፣ የአንተን ምርት ወይም አገልግሎት ከሌሎች የላቀ ወይም በሆነ መንገድ ልዩ መሆን አለበት። ነባር ምርቶችን መምሰል፣ የቀደመውን ማባዛት ብቻ ነው የሚሆነው። ያንተ ምርት ከተወዳዳሪ ምርቶች ወይም ተወዳዳሪ ሊሆኑ ከሚችሉ ምርቶች የሚለይበት ልዩ ጥንካሬዎች ወይም ባህሪያት ሊኖሩት ይገባል።
إظهار الكل...
إظهار الكل...

ወንድ እነዚህ ምልክቶች ራሱን ላይ ካለ በፍጥነት  ራስህን አውጣ! 1ኛ በየቀኑ ራስን ለማርካት መሞከር 2ኛ ሰዎች ሲኑቁን በዝምታ ማለፍ 3ኛ ለነገሮች በቀላሉ ስሜታዊ መሆን ማለቃቀስ 4ኛ መፅሀፍ ላለማንበብ የተለያዩ ምክንያቶች መደርደር 5ኛ ሁልጊዜም ሶሻል ሚዲያ ላይ መደመጥ ከእውነተኛ ግንኙነት መራቅ 6ኛ የወሲባዊ ቪዲዮ መመልከት 7ኛ ታላላቆችን አለማክበር... በቃ ሁሉም አንተ ለመጉዳት የመጣ ሲመስል 8ኛ ሁልጊዜም ሴቶችን ስትከተል 👇 ከእነዚህ ስሜቶች አንዱ ወይም ሁለቱ ብቻ ካሉብህ ብዙም አያሳስብ ታልፈዋለህ ግን ከአራት በላይ ካለብህ በፍጥነት ራስህን መክረ ተመልስ!
إظهار الكل...
አንዳንዴ . . . ያለ ነው! አንዳንድ ጊዜ ማመንታት ያለ ነው - በፍጹም ግን ወደ ኋላ አንመለስም! አንዳንድ ጊዜ መፍራት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንንበረከክም! አንዳንድ ጊዜ ተስፋ መቁረጥ ያለ ነው - በፍጹም ግን አናቆምም! አንዳንድ ጊዜ መሸነፍ ያለ ነው - በፍጹም ግን ሕይወት ከሚያቀብለን የየእለት ጦርነት አንሸሽም! አንዳንድ ጊዜ መድከም ያለ ነው - በፍጹም ግን ዝለን አንወድቅም! አንዳንድ ጊዜ ግራ መጋባት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንቅበዘበዘም! አንዳንድ ጊዜ በሰው መገፋት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከዚያ ሰው ውጪ መኖር አየቅተንም! አንዳንድ ጊዜ ድብርት ያለ ነው - በፍጹም ግን ደንዝዘን አንቀርም! አንዳንድ ጊዜ ለጥያቄ መልስ ያለማግኘት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከመጠየቅ አናርፍም! አንዳንድ ጊዜ ክፋት ያሸነፈ መምሰሉ ያለ ነው - በፍጹም ግን መልካምነትን አንጥልም! @T2T4T5
إظهار الكل...
ለተዓምር ተፈጥረሀል! ድንጋይ የተጫናቸው ትሎች እንኳን ያለ ምክንያት አልተፈጠሩም፤ ያለ ትሎች የአፈር ምህንድስና አይካሄድም ስለዚህ ዛፎች ይደርቃሉ፤ እንስሳት ያልቃሉ። ትሎች ለአላማ ከተፈጠሩ አንተማ ምን አይነት ተዓምር ልትሰራ እንደተፈጠረከ አስበው?! ወዳጄ አንተ የምታስፈልገው ሰው አለ፤ አንተ ብቻ የምትፈታው ችግር አለ፤ ያለ ምክንያት ወደዚህ አልመጣህም! 🙏 👇👇👇👇 @T2T4T5
إظهار الكل...
እንደንቦቹ! 👇 "ንቦች ከቆሻሻ ይልቅ ማር ይሻላል ብለው ለዝንቦች በማብራራት ጊዜያቸውን አያጠፉም" (ካልታወቀ ምንጭ) 🚶 እንደ ንቦቹ ዝም ብላችሁ ዓላማችሁ ላይ አተኩሩ!
إظهار الكل...
እንደንቦቹ! 👇 "ንቦች ከቆሻሻ ይልቅ ማር ይሻላል ብለው ለዝንቦች በማብራራት ጊዜያቸውን አያጠፉም" (ካልታወቀ ምንጭ) 🚶 እንደ ንቦቹ ዝም ብላችሁ ዓላማችሁ ላይ አተኩሩ!
إظهار الكل...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

👇 አንዳንዱ ነገር ልክ እንደ ምግብ በእሳት ውስጥ ካላለፈና ካልበሰለ አይፈለግም፣ አይሸጥምም፡፡ 👇 አንዳንዱ ነገር ልክ እንደ አይስክሬም በበረዶና በቀዘቀዘ ሁኔታ ውስጥ ካላለፈ አይፈለግም፣ አይሸጥምም፡፡ 👇 አንዳንዱ ነገር ልክ እንደቆዳ ካልለፋና ካልለሰለሰ አይፈለግም፣ አይሸጥምም . . . አንዳንዱ ነገር ልክ እንደ ጥሬ መሬት ላይ ተጥሎ ካልተረገጠ፣ ካልተቀበረና ካልተረሳ ጊዜ ጠብቆ አድጎና አፍርቶ አይፈለግም፣ አይሸጥምም . . .፡፡ 👇 የምታልፉበት ሁኔታ ዋጋና ትርጉም አለው!
إظهار الكل...