HUHCSF ✞
Open in Telegram
Haramaya University, Harar Health Campus Christian Students Fellowship Worship Center: @ Me'erab Harar MKC Meet Leaders: @DestaMekonnen
Show more542
Subscribers
No data24 hours
+27 days
+730 days
Posts Archive
543
❤️ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች!
በዚህ ቅዳሜ የተከታታይ ትምህርታችንን ሦስተኛ ክፍል “የመንግሥቱን ተስፋ መኖር” በሚል ርዕስ ከተጋባዥ እንግዳችን ጋር አብረን እንማራለን። 📖✨
ጓደኞቻችሁንም ጋብዙ፤ መጽሐፍ ቅዱሳችሁንና ማስታወሻችሁን ይዛችሁ በሰዓቱ 12:00 እንገናኝ! ❤️
🔥 መቅረትም ሆነ ማርፈድ አይታሰብም!
👑 የመንግሥቱ ተስፋ ማየት | መኖር | መመስከር ✨
543
(13) እናንተ፣ “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህች ወይም ወደዚያች ከተማ እንሄዳለን፤ በእርሷም አንድ ዓመት እንቈያለን፤ እንነግዳለን፤ እናተርፋለንም” የምትሉ እንግዲህ ስሙ። (14) ነገ የሚሆነውን እንኳ አታውቁም። ሕይወታችሁ ምንድን ናት? ለጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት ናችሁ። (15) ይልቁንም፣ “የጌታ ፈቃድ ቢሆን እንኖራለን፤ ይህን ወይም ያንን እናደርጋለን” ማለት ይገባችኋል።
(
የያዕቆብ መልእክት 4:13-15)
ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦችና የተወደዳችሁ የፌሎሺፓችን አባላት፣በጉጉት የምንጠብቀው የ 2019 ዓ.ም የፌሎሺፕ መክፈቻ ፕሮግራም በመጪው ቅዳሜ፣ መስከረም 30 በመደበኛው ሰዓት ይካሄዳል። በዚህ ቀን እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት፣ የጀመርነውን አዲሱን ዓመት ለእርሱ አደራ የምንሰጥበት እና በጸሎት ወደ እርሱ ፊት የምንቀርብበት ልዩ ጊዜ ይኖረናል። ስለሆነም ሁላችንም በአንድነት ተሰብስበን ይህን ቀን አብረን እንድናሳልፍ በፍቅር እንጋብዛችኋለን። እንዲሁም ለህብረታችን ያመጣችሁትን መጽሐፍ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን። በዚህ የተባረከ ቀን አብረውን እንዲሰበሰቡ የምትወዷቸውን ጓደኞቻችሁንም እንድትጋብዙና አብራችሁ እንድትመጡ ይሁን:: #ማርፈድም ሆነ መቅረት አይታሰብም #እግዚአብሔር ይባርካችሁ!❤
543
ሰላም ውድ ቅዱሳን👋🤗❤️
እንዴት ናችሁ? እንኳን ወደ ግቢያችሁ በደህና መጣችሁ፣ ወደ ውዱ ህብረታችንም በሰላም ተመለሳችሁ!🥰
እንደገና አብረን ልንሰባሰብ፣ ልንጸልይ፣ ቃሉን ልንማር እና እርስ በርስ ልንበረታታ የምንጀምርበት ጊዜ መድረሱ በጣም ደስ ይላል።❤️
ዛሬ ግን የፌሎሺፕ ፕሮግራም አይኖረንም።ብዙዎቻችን ወደ ግቢ እየገባንና እየተሰባሰብን ያለንበት ጊዜ ስለሆነ፣
ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮበሙሉ ልብ እንደገና አብረን እንጀምራለን።🥰 🙏 እስከዚያ ድረስ ግን እባካችሁ ለህብረታችን ጊዜ ስጡ፤ በጸሎት አስቡን። እግዚአብሔር ህብረታችንን እንዲባርክ፣ ፍቅራችንንና አንድነታችንን እንዲያጸና እና በዚህ ዓመት በመካከላችን በልዩ ሁኔታ እንዲሰራ እንጸልይ።🙏❤️ በቀጣዩ ሳምንት ደግሞ እንደ አንድ ቤተሰብ ተሰብስበን፣ በደስታ ፌሎሺፓችንን እንጀምራለን። የምንጋራው ደስታ፣ የምንማረው ቃል እና አብረን የምናሳልፈው ጊዜ ይባረክልን።❤️ እግዚአብሔር በዚህ አዲስ የትምህርት ዓመት ይጠብቃችሁ፣ ይምራችሁ፣ በጸጋውና በሰላሙ ይሙላችሁ።🙏 በቀጣዩ ሳምንት እንገናኝ!🥰❤️ ተባረኩ 🤗❤️
543
እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! ❤️🙏
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የመተሳሰብ ይሁንላችሁ።
እግዚአብሔር በጸጋው ጠብቆ ወደዚህ አዲስ ዓመት ስላደረሰን እናመሰግነዋለን። ይህ ዓመት እንደ ፈቃዱ የምንኖርበት፣ መልካም ፍሬ የምናፈራበት እና በእርሱ ዘንድ የምንጠነክርበት ዓመት ይሁንልን።
ከእግዚአብሔር ጋር ይበልጥ የምንቀርብበት፣ ቃሉን በጥልቀት የምንረዳበት፣ በጸሎት የምንተጋበትና በመንፈስ ቅዱስ እለት በእለት የምንሞላበት ዓመት ይሁንልን።
በቅድስና የምንመላለስበት፣ በእምነት የምንጸናበት፣ ተስፋችንን በጽናት የምንጠብቅበት፣ እቅዶቻችንም በእግዚአብሔር ፈቃድ የሚሳኩበት ይሁንልን።
በሥራና በትምህርት የምንጠነክርበት፣ በፍቅርና በአንድነት የምንኖርበት፣ እርስ በርሳችን የምንተጋገዝበትና ለሌሎችም በረከት የምንሆንበት ዓመት ይሁንልን።
ከሁሉም በላይ ራስ ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ ይበልጥ የምናድግበት፣ ሕይወታችንም ለእርሱ ክብር የሚሆንበት የተባረከ ዓመት ይሁንልን።
እግዚአብሔር እኛን፣ ቤተሰቦቻችንን፣ ፌሎሺፓችንንና ማኅበረሰባችንን በሰላሙ ይጠብቅ፤ በጸጋው ይሙላን፤ በረከቱንም ያብዛልን።
መልካምና የተባረከ አዲስ ዓመት! ❤️🙏
አሜን!
543
Greetings All
For any student interested there is an upcoming screening program. It will be carried out on Saturday, Sept 5 (Nehase 30) in Harar Ammanuel Church from 3 - 6LT.
Any interested student is welcome to join!
Harar Medical Mission Team.
543
📣 3 ሳምንት ቀረው ....
✨መዝሙረ ዳዊት 133:1
ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው።
🖐ሰላም ቅዱሳን ከዚህ በፊት እንደተናገርነው የሃረማያ ሃረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ክርስትያን ተማሪዎች ሕብረት አባል የሆንን እና ሆነን ያለፍን በአንድነት በጸሎት : በዝማሬ : ቃሉን በመስማት በጌታ ፊት የምንሆንበት ፤ እርስ በእርስ የምንጨዋወትበት ፤ ስለ ቀጣይ እርምጃዎች በአንድነት የምንመክርበት የምናመልክበት ፕሮግራም እለተ ቅዳሜ ነሃሴ 23 በአዲስ አበባ ተዘጋጅቷል ።
ስለዚህ እስከ ፕሮግራሙ ቀን ድረስ እየጸለይን ፣ እንዲሁም ወዳጆቻችን እየጋበዝን፣ በዚህ ፕሮግራም ላይ የምንችል ሁላችንም እንደንገኝ ጥሪ እናቀርባለን ።
543
ሰላም የጌታ ውዶች! 👋🤗
"ከማማረር ወደ መዘመር" በሚል ርዕስ በፌሎሺፓችን የተዘጋጀው የትንቢተ ዕንባቆም ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በዚህ ሳምንት ቅዳሜ፣ ነሐሴ 2 ይቀጥላል።
📖 የዕለቱ ርዕስ፦
"የእግዚአብሔር መልስ፣ የነቢዩ ዝምታ"
"ጻድቅ ግን በእምነቱ ይኖራል።" (ዕንባቆም 2፥4)
ከእግዚአብሔር ቃል በመማር አብረን እንባረክ።
📚 መጽሐፍ ቅዱሳችሁን፣ ማስታወሻችሁን እና ክፍት ልባችሁን ይዛችሁ በሰዓቱ ተገኙ።
📢 ይህን የተባረከ ጊዜ ለሌሎችም በማካፈል ወዳጆቻችንን እንጋብዝ፤ ከላይ ያለውን ፖስተር በProfile እና Story ላይ በማጋራት ፕሮግራሙን እናስተዋውቅ።
🙏 እንጠብቃችኋለን! ጌታ ይባርካችሁ።
543
ሰላም የጌታ ውዶች 👋🤗
“ከማማረር ወደ መዘመር” በሚል ርዕስ በFellowshipኣችን የተዘጋጀዉ የትንቢተ ዕንባቆም ተከታታይ ትምህርት በዚ ሳምንት ቅዳሜ ሐምሌ 25 ይቀጥላል።
በባለፈዉ የነበረዉ introduction ስለነበር በዚ ሳምንት ክፍል አንድን አብረን እንማራለን።
📌 የዕለቱ ርዕስ፦ “የነብዩ መልስ ያጣላቸዉ ጥያቄዋች እና የእግዚአብሔር ዝምታ”
• በዚህ የተባረከ ትምህርት ጊዜ ላይ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
•ከእግዚአብሔር ቃል በመማር አብረን እንባረክ።
📖 መጽሐፍ ቅዱሳችሁን እና ማስታወሻችሁን ይዛችሁ በጊዜ አንደትገኙ ይሁን።
• እንዲሁም ይህን የተባረከ ጊዜ ለሌሎችም በማካፈል ወዳጆቻችንን እንጋብዝ።
ከላይ ያለዉን Poster በProfile እና Story ላይ በማድረግ ፕሮግራሙን እናስተዋውቅ።
ተባረኩ 🙏
543
ሰላም የጌታ ውዶች 👋🤗
“ከማማረር ወደ መዘመር” በሚል ርዕስ በFellowshipኣችን የተዘጋጀ ተከታታይ ትምህርት በዚ ሳምንት ቅዳሜ ሐምሌ 11 ይጀምራል።
📌 የዕለቱ ርዕስ፦ “የነብዩ ጥያቄ የእግዚአብሔር ዝምታ”
• በዚህ የተባረከ ትምህርት ጊዜ ላይ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
•ከእግዚአብሔር ቃል በመማር አብረን እንባረክ።
📖 መጽሐፍ ቅዱሳችሁን እና ማስታወሻችሁን ይዛችሁ በጊዜ አንደትገኙ ይሁን።
• እንዲሁም ይህን የተባረከ ጊዜ ለሌሎችም በማካፈል ወዳጆቻችንን እንጋብዝ።
ከላይ ያለዉን Poster በProfile እና Story ላይ በማድረግ ፕሮግራሙን እናስተዋውቅ።
ተባረኩ 🙏
543
የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን! 🕊️ የ2014 ዓ.ም. ተመራቂዎች ለኅብረታችን ያበረከቱትን ልዩ ስጦታ ላበስራችሁ እወዳለሁ🎁; እሱም ከዚህ ጽሑፍ ጋር ተያይዞ የሚታየው አኮስቲክ (ቦክስ) ጊታር ነው🎸.
እግዚአብሔር ይባርካችሁ🙏, በሄዳችሁበት ሁሉ ይምራችሁ, ሁልጊዜም ከእናንተ ጋር ይሁን✨. የምንወዳችሁ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን, አብረን ላሳለፍነው ድንቅ ጊዜ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን
📖 መዝሙር 65፥4📖
“አንተ የመረጥኸው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልኸው ምስጉን ነው፤ ከቤትህ በረከት እንጠግባለን።”
543
ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በዕንጨት መስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቍስል እናንተ ተፈውሳችኋል። 1ኛ የጴጥሮስ 2:24 (NASV)🎧 | Listen 👂 & Blessed 🙌🥰 👉Join&Share @SERVANTJOHN
543
#ስለእኛ✝️
He himself bore our sins in his own body on the tree, so that we, being dead to sins, should live for righteousness. By his wounds you were healed.
1 Peter 2:24
Blessed🙌🥰
Share&Join 👉 @SERVANTJOHN
543
የ21 ቀን የፆም ጸሎት ጥሪ 🙏
ሰላም ለእናንተ ይሁን ቅዱሳን!
የፊታችንን ሦስት ሳምንታት (21 ቀናት) በፌሎሺፓችን የታወጀ የፆም እና የጸሎት ጊዜ እንደሚኖረን ስንነግራችሁ በደስታ ነው። በእግዚአብሔር ፊት የምንቆይበት መሪ ርዕሳችን፦ "እግዚአብሔርን መፈለግ" የሚል ስሆን። ይህን በሶስቱ ሳምንታት ከፋፍለን ፀሎታችንን የሚንቀጥል ይሆናል።
📌 የመጀመሪያ ሳምንት፦
እግዚአብሔርን መፈለግ በመመለስ 🙇♂️📌 ሁለተኛ ሳምንት፦
እግዚአብሔርን መፈለግ በቅድስና 🕊️📌 ሦስተኛ ሳምንት፦
እግዚአብሔርን መፈለግ በመታመን ❤📌 የዚህ ሳምንት ጸሎት ነገ ቅዳሜ መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም የሚጀምር ስሆን፣ ቅዳሜና እሁድን በግል ካሳለፍን በኋላ፣ ከሰኞ ጀምሮ በጋራ እንጸልያለን። 🤝 የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 🙌
543
ሰላም የጌታ ቤተሰቦች፤
ባለፈው ሳምንት በገለጽነው መሠረት፣ የ2014 ባች ተመራቂ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን የምንሸኝበት ፕሮግራም ነገ ይካሄዳል። 🎓✨
በመሆኑም ሁላችሁም በተባለው ሰዓት ከቀኑ 11:00 ጀምሮ እንድትገኙ በጌታ ፍቅር እናሳስባለን። 🕒
ጌታ በኅብረታችን መካከል ይገኝ!
ነገ እንገናኝ! 🙏✨
📖 መዝሙር 65፥4📖
“አንተ የመረጥኸው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልኸው ምስጉን ነው፤ ከቤትህ በረከት እንጠግባለን።”
543
ሰላም ወዳጆች ከዚህ በታች የሚገኘው የፌሎው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ነው ።
አስራታችሁንና ስጦታችሁን እንድታስገቡበት ይሁን ።
ተባረኩ🙌
1000634424109
Eshetu and eden
543
ሰላም የተወደዳችሁ በትናንቱ ማስታወቂያ እንደሰማችሁት የፀጋ ስጦታዎች እና አጠቃቀማቸው በሚል ርዕስ እየተማርነው ያለ የትምህረት ክፍለ ጊዜ የፊታችን ቅዳሜ ይጠናቀቃል። የዚያ ቀን መርሃ ግብር የጥያቄ እና መልስ ክፍልን ያካትታል ስለዚህ ጥያቄያችሁን እስከ ማክሰኞ ምሽት 2፡00 ድረስ ማስገባት ትችላላችሁ።
ጥያቄ ለመላክ: 0904790081
0960479442
ተባረኩ🙏
📖 መዝሙር 65፥4📖
“አንተ የመረጥኸው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልኸው ምስጉን ነው፤ ከቤትህ በረከት እንጠግባለን።”
543
ሰላም ለእናንተ ይሁን የተወደዳችሁ ቅዱሳን ✋
ዛሬ በተለመደው ሰኣታችን የህብረት/የትምህርት ግዜ ስለሚኖረን ሁላችንም #ማስታወሻ እና #መጽሓፍ ቅዱስ ይዘን እንምጣ ተባረኩ።👐
