en
Feedback
ፈለገ ጥበባት +++

ፈለገ ጥበባት +++

Open in Telegram

+++የቀደምት ኢትዮጵያውያን ስልጣኔን ማሳየት እንዲሁም ገዳማት እና አድባራትን ማሳወቅ፡፡+++ የተረሱ አድባራትና ገዳማትን ማስታወስ ፤የ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን ጥበብ እውቀትን በምንችለው ሁሉ መመርመር የአባቶቻችን ልጆች በመሆን ትላንት በዛሬ እና በነገ ውስጥ ማስቀጠል ማስቻል ነው።

Show more
7 163
Subscribers
-524 hours
-267 days
-7330 days
Posts Archive
ከደቂቃወች በኋላ አስደናቂው ከአለም የተሰወረው የአባቶቻችን ጥበብ እግልጥላችሁ አለሁ!

ከ ደቀቃውች በኋላ ያልተነገረው አስደናቂው የመጻሕፍ ቅዱስ ሚስጥር " the secret of Reproduction '' መለኮታዊ እውቀት የስነ ተዋልዶ ሚስጥር በጥንቷ የሶርያ ምድር የተደረገ ጥበብ ....ከደቂቃወች በኋላ በዩቲብ ቻናል ይተጠብቁን!

ሰላም! እንደሚታወቀው ፈለገ ጥበባት በተለያዩ ሃሳቦች ተንተርሶ ለአድማጭ ተመልካች አስደናቂ እውቀቶችን ያጋራል። ፈለገ ጥበባት ከዚህ ቀደም ከ ነበረው አቀራረብ እና ይዘቶች በተሻለ ለ አንባቢያን እንዲሁም ለተመልካቾች እጃግ አስደናቂ ፕሮግራሞችን ለማቅረብ ታስቧል። ከዚህ ቀደም ከነበሩት ይዘቶች በተሻለ ምን ምን ይካተቱ ለሚለው ሃሳብ የቤተሰቦቻችንን አስተያየትና ጥቆማወች አስፈላጊ ስለሆኑ ሃሳቦቻችሁን በሃሳብ መስጫ ሳጥቁ ወይም ደግሞ በውስጥ መስመር @Nabuti21 ላይ አድርሱን ። ለተሻለ ስራ እንተባበር!

ከ ደቂቃወች በኋላ እጂግ አስደናቂው ጥንታዊው የስነ ተዋልዶ እወቀት ከመጻሕፍ ቅዱስ አንጻር የተነገሩ እጂግ ሚስጥራዊ እውነቶች ይዠላችሁ እቀርባለሁ! በፈለገ ጥበባት የዩቲብ ቻናል ጠብቁን

  ከአያሌ ምዕተ አመታት ይኖርበት ከነበረው ከአንድ ታላቅ ገዳም ተዘርፎ በአውሮፖ ገቢያ የተሸጠው ልዩ ቅርስ! .... ለ 1400 አመታት በላይ ተጠብቆ የቆየውን ታላቅ አስደናቂ ሚስጥር ምንድን ነው? በርካቶች የአለም ተመራማሪወችን የገዳሙን የመግቢያ በሩን ቁልፍ ሊያገኙ ዋትተዋል...በጉዞ ማስታወሻየ ይህ ልዩ እጂግ አስደናቂ ሚስጥር እንፈታዋለን... በፈለገ ጥበባት የዩቲብ ቻናል ይጠብቁን!..

የሰው ልጆችን አመለካከት ይቀይራሉ ብየ ከማምንባቸው  እና በዩቲብ ለብዙሃኑ መልስ የሚሆኑ  ሃሳቦች ከሚተላለፊባቸው ቻናሎች ልጠቁማችሁ ወደድኩ! በእጂጉ የምታተርፉበት ከዚህ ቀደም ሰምተናቸው የማናውቃቸውን  አስደናቂ ሚስጥሮች የሚገለጥበት የዩቲብ ቻናል ነው። በእውቀት በእውነት  ለመራቀቅ ከፈለጉ ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ ዘንድ እመክራለሁ። የ ዩቲብ ቻናሉ ስም    ከሃሊ በቃሉ                              kehali bekalu https://youtu.be/hZ2nUhWl0x0

Watch "ጥንታዊዉ የሥነ ተዋልዶ እውቀት | The ancient knowledge of fertility | |kehali bekalu ||ክሃሊ በቃሉ |" on YouTube https://youtu.be/vN_-VqAosow

ይህንን black hole ለመረዳት በብዙ ሳይንሳዊ ጥናቶች እና መላምቶችን ተደርገዋል፡፡ ለዚህም የመጀመሪያዉን ፍንጭ ለመስጠት የሞከረዉ እዉቁ ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን ነዉ፡፡ ይህንንም ምርምሩን ደግሞ E=mc2 በሚል ፎርሙላ ነዉ የብረሃንን ፍጥነት በመጠቀም የጊዜና የስአት ግዝፈቱን ለማወቅ ሞክሯል፡፡ በዚህም የተነሳ ሳይንሳዊ ትንታኔወችን እንዲህ ሲሉ አስቀምጠዋል፡፡ ነገር ግን ከሳይንቲስቶች ንድፈ ሃሳብ በተሻለ መልኩ ታላቁ የሂወት መፃህፍ በመባል የሚታወቀዉ ራዛኤል የተባለዉ የብራና መፃህፍ በሰፊዉ አስቀምጦታል፡፡ ይህ መፃህፍ በአራቱ ሰማያት ወይም አለማት ያለዉን የሀይል የጊዜና የግዝፈት ልዮነት ያስረዳል፡፡ ይህ ታላቅ መፃህፍ የተፃፈዉ በአዳም ሲሆን አዳምን ያስተማሩት ሚስጥሩንም የገለጡለት በእሳት አለማት ዉስጥ የሚገኙ መላእክት ሲሆኑ አሁን ላይ የዚህ መፃህፍ መገኛ ከ አዲስ አበባ 47 km እርቃ ከምትገኘዉ ቢሾፍቱ ደብረ ዘይት በታላቁ የረር ተራራ በሚገኙት ገዳማት በሚስጥረ ተጠብቆ እንደሚገኝ ቅዱሳን አባቶች ይናገራሉ፡፡ አዳም በገነትና በምድር ላይ ኑሩዋልእና ፡፡ ስለዚህ ሰማያዊት በሆነችዉ ገነትና በምድር መሃከል የጊዜ የሃይል የግዝፈት ልዮነት አለ ማለትነዉ ፡፡ ነገር ግን አዳም በገነትና በምድር ያለዉን የጊዜ ልዮነት አስማምቶ ይኖር ዘንድ መላኩ ቅዱስ ገብረኤልና መላኩ ቅዱስ ኡራኤል ጥበብን አስተማሩት፡፡ ለብዙ ሰወች ጥያቆ የሚሆነዉ አዳም 7 አመት በገነት ኖረ ከዛም በምድር 930 አመት ኖረ ጥያቄ የሚሆነዉ ግን በገነትና በምድር ላይ የጊዜ ልዮነት አለ ካልን ይህም ማለት አንደ ቀን በገነትና አንደ ቀን በምድር የሚኖራቸዉ የጊዜ ክፍተት ብዙ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ አዳም በሰማይ 7 አመት ከኖረ በምድር የጊዜ ስሌት ላይ ስንት አመት ኖረ ማለት ነዉ ? ከዚህ ጋ ልብ በሉልኝ በቅዱስ መፀህፍ ላይ በሰማይ 1 ቀን በምድር 1 ሺ አመት ነዉ ይላል ፡፡ ይህም ማለት 7 አመት የአዳም የሰማይ ኑሮዉ በምድር ላይ ሲሰላ 7*365=2555, 2555 ቀናትን በሰማይ ኑሩዋል ማለት ነዉ ይህም በምድር የጊዜ ስሌት አዳም በገነት የኖረዉ 2555*1000=2555000 ቀናት ነው   ነዉ፡፡ 2.5 ሚሊየን ቀናት በላይ ማለት እኮ ነው..... ይህ ማለት የዘመኑ የሳይንስ ምርምር time travel በጊዜ ውስጥ የ መጓዝ ን ጥበብ አያሳየንም?    በዚህ ሃይማኖታዊ ፍልስፍና  ውስጥ  በሌላ ፕሮግራም የምንገለጠዎ እጂግ ረቂቅ የእግዚአብሔር ስራ እንመለከታለን .... ስለዚህ ነጮች እንደሚሉት ምድር ከተፈጠረች ሚሊየን አመት ሁኗታል ማለት ያስችለናል??? ነገር ግን አዳም ገነት ላይ በኖረበት 7 አመትና በምድር ያለዉን የሃይል የጊዜና የግዝፈት መጠን አመጣጥኖ መኖር ችሏል ማለት ነዉ:: ስለዚህ አዳም ምድር ላይ ሲመጣ የግዝፈት መጠኑ 7 አመት እንዳሳለፈ ሰዉ እንጂ በረካታ ሚሊዮን አመታት እንዳሳለፈ ሰዉ ሁኖ ወደ ምድር አልመጣም የሚል መላምት ይሰጣል ፡፡ ወደቀደመዉ ነገሬ ልመለስና ከላይ ከተመለከትናቸዉ 6ቱ Blach hole(የጥልቁ ጨለማ ሀገር) እና 6ቱ white hole (የቅዱሳን መላእክት ሀገር) በአራቱም አለማት ዉስጥ ከሚገኙት ማለትም ከመሬት ከሳት ከዉሃና ከነፋስ አለማቱ ጋ የጊዜ የግዝፈት ና የሃይል ተፅኖ ዉጭ ነዉ፡፡ለዚህም ይህ black hole በረባኖር ብዙ አስደንጋጭ ክስተቶችን የሚያሳይ አስደናቂ ቦታ ነው ። ዉድ የፈለገ ጥበባት ቤተሰቦቻችን ፡አንብቦ ዝም ማለት ሳይሆን ለጓደኛ ዘመድ ወዳጂ ለሆኑ ሁሉ አጋሩ፤ በአንድ ላይ ሰብሰብ እንበል፤ እንማማር እንመካከር... ከዚህው ከቴሌግራም ና የዩታቭ ማህበር አባላት ጋራ ወደ ፊት ተነጋግረን የጋራ የሚያደረገን ፈጣሪ ከፈቀደ ብዙ ስራወችን አብረን እንሰራለን፤ የሚገራርሙ የሀገራችንን ድንቅ ጥበብ እና ማንነቷን እንረዳለን የማህበሩ አባላት በቁጥር ከፍም ሲል ከመላ ኢትዮጵያ ከያለንበት ተሰባስበን የገዳማትና የአድባራት ጉዞ እንካሂዳለን፤ የተዘጉ ቅዱሳን መካናትንም እናስባለን ። ይህ ፈለገ ጥበባት ነዉ ያላችሁን ሃስብ አስተያየት @Nabuti21 ላይ ማድረስ ይቻላል...

የአለም ሃያላን በሚስጥር የሚፈልጉት የአለምን ሁለንተናዊ አሰራር  ሚስጥር የሚፈታ ድንቅ   የብራና መጻህፍ ! የአለማትን የሳይንሱን ዘረፍ የፈተነዉ ፍንጩ እንኳ ለመስጠት የሚያስቸግረዉ የጨለማ ድንኳን ምንድን ነዉ? የጥንት መዛግብቶቻችን ስለ አለማት ምን ይላሉ ምን ብለዋል? ብራናወቻችን አለም ተመራምሮ ስላልደረሰበት የሚስጥራት ሁሉ ሚስጥር ስለሆነዉ ስለ አለማት አፈጣጠርና አመሰራረት እንዲሁም ጥንተ ተፈጥሮ  ምን ይላሉ? ቀደምት ኢትዮጵያዉያን አባቶቻችን የእግዚአብሔርን ጥበብና ሚስጥር ተመግበዉ በዘመኑ ለሳይንስ ለቴክኒዎሎጂ እንቆቅልሽ የሆነ ምስጥራዊ እዉቀቶችን ና ጥበቦችን ትተዉልን አልፈዋል፡፡ እንዲሁም መለስ ብለን ታሪክን ስንመረምር፤ የተፃፉ ዶሴወችን ስናገላብጥ፤ የብራና መፃሆፍቶቻችንን ስንመረምር፤ አሁን ድረስ አለም ያልፈታቸዉ በረቀቀና በመጠቀ መልኩ ተብራርተዉና ተቀምጠዉ የሚገኙ አያሌ እዉቀቶች አሉ፡፡ ከነዚህም መካከል በምላት ና በስፋት ተብራርቶ የምናገኛቸዉ የአለማት አፈጣጠር ሚስጥራትን ነዉ፡፡ በዚህም የተነሳ የሚስጥር ማህበረሰብ የሚባሉት የምዕራቡ አለም ነገስታት አለምን አንድአድርጎ ለመግዛት ካላቸዉ ጉጉት የተነሳ የአዳም ልጆች ከሰለጠኑባት ከ ኢትዮጵያ ምድር ዉስጥ የሚገኙትን የአራቱን አለማት አፈጣጠር ሚስጥራትና ጥበባት ለመበዝበዝ ያላሰቡት ሀሳብ ያለፈነቀሉትም ድንጋይ አልነበረም፡፡ ከሰማያዊዉ ህብረት ሃይላት ጋራ ህብረት መፍጠር የቻሉት ኢትዮጵያዉያን በየዘመኑ ከአራቱም አለማት ሚስጥራትና በመረዳታቸዉ በዘመናቸዉ ብርቱና ሀያል ሁነዉ ከማለፋቸዉ ባሻገር በመንፈሳዊ ፅናትና አቋማቸዉ ምክኒያት ወደ ሀገራቸወ ሲመጡ ለነበሩት ቅዱሳን ይህኔን ጥበባት አስተምረዋል፡፡ በምዕራባዉያን ሳይንስና ቴክንሎጂ የህዋ ምርምር ተቋማት ሚስጥራቸዉ አልፈታም ብለዉ ከተዘረዘሩት አንዱና ዋናዉ አለማት  እና ይዘታቸው ሲሆን ፡ ስለዚህ ሚስጥራዊ ቦታ የተለያዩ ተመራማሪወች ሀሳባዊ መላምቶቻቸዉን አስቀምጠዋል ሁኖም ግን ከመላምታዊ ድምዳሜ የዘለለ አንዳችም ተጨባጭ ነገር ለመናገር አልቻሉም፡፡ ነገር ግን ቀደመት ኢትዮጵያዉያን ምሁራን በሚደንቅ እና በሚረቅ ትንታኔ አስቀምጠዉልን አልፈዋል፡፡ በአጠቃላይ አለማት 20 ሲሆኑ 14ቱ የሳትና የምድር ሲሆኑ 6 ደግሞ የነፍስና የዉሃ ናቸዉ፡፡ የሳት ፣የምድር፣ የነፋስ፣ እንዲሁም የዉሃ አለማት በመባል የሚታወቁ ጠቅለል ሲሉ አራት አለማት በመባል ይታወቃሉ፡፡ የሳት አለማት የሚባሉት 9 ሲሆኑ የምድር አለማት ደግሞ 5 ናቸዉ ፡፡ በ14 አለማት ዉስጥ የሚገኙት ፍጥረታት አንዳቸዉ ከአንዳቸዉ ግንኙነት የሚፈጠርባቸዉ ህቡዕ መንገዶች የሀይላቸዉ ማረፊያና ማደሪያ የሆኑ 12 የተለያዩ ቦታወች አሉ፡፡ እነዚህ የአለም ሀገራት black hool ብለዉ የሚጠሯቸዉ ከእነዚህ የተለያዩ ቦታወች 6ቱን ነዉ፡፡ የሳት አለማት የሚባሉት እጂግ በሚያንፀባርቅና በነበልባል በተከበበ ከፍተኛ በሆነ የሃይል መጠን የሚገኙባቸዉ አለማት ናቸዉ፡፡ እኒህ 20 አለማት በዝርዝር እንደሚከተለዉ ተቀምጠዋል፡፡ ዘጠኝ የእሳት: አምስት የመሬት: አራት የውሃና ሁለት የንፋስ ዓለማት ናቸው። ሀ. የእሳት ዓለም ( በቁጥር 9 ዘጠኝ ናቸው ) ከላይ ወደ ታች ሲቆጠሩ :- 1 ጽርሐ አርያም ( የእግዚአብሔር የምስጋናው አዳራሽ ) 2 መንበረ መንግሥት/ስብሐት ( የጌታ ዙፋን ያለባት ) 3 ሰማይ ውዱድ( በአራቱ እንስሳዎች ክንፎች ላይ የተዘረጋ ሰማይ ) 4 ኢየሩሳሌም ሰማያዊት/ ዛዶር ( በመጀመሪያ ሳጥናኤል የተፈጠረባት በኋላም ከእሱ ተነጥቃ ለአዳም ልጆች የተሰጠች ) 5 ኢዮር ( የአርባው ነገድ የመላእክት ከተማ ) 6 ራማ ( የሠላሳው ነገድ የመላእክት ከተማ ) 7 ኤረር ( የሠላሳው ነገድ የመላእክት ከተማ ) 8 ምጽናተ ሰማይ ( ባህረ እሳት ) 9 ገሀነመ እሳት ናቸው። አዳም አባታችን በዚች እኛ በምንኖርባት ምድር ከመሰልጠኑ አስቀድሞ ምድር ለሰባት ተቆርሳ ወይንም ተከፍላ ነበር። ይህ ማለት እንግዲህ ከምድራችን ጋር ተመሳሳይ የሀይል የጊዜና የግዝፈት መጠን ያላቸው ነገር ግን የማናውቃቸው ስድስት የመሬት ክፍሎች አሉ። እነዚህ በስድስት የተከፈሉ ሰባት የምድር ክፍሎች የሚከተሉት ናቸው:፡ 1,መሬት(እኛ አሁን የምንገኝበት) 2, ብሔሞት 3, አራዊት ብቻ የሚገኙበት 4, እሳት ብቻ የሚገኝበት 5, በረድ ብቻ የሚገኝበት 6, ሌዋታን 7, በርባኖስ (ጨለማ ስፍራና እስርቤት) የስነፍጥረት አንድምታ መፅሐፍ እንደሚያስረዳው ኢዮር ራማና ኤረር አሰራራቸዉ አራት ማዕዘን ሲሆን ሰባት የሳት ቅፅርና ሰባት የሳት መጋረጃ የጋረዳቸዉ የሳት አለማት ናቸዉ፡፡ እኒህ አለማት ከሰዉ በተሰወረና ከመላእክት እንኳ በረቀቀ መልኩ ይገናኛሉ፡፡ አራት ማአዘን ቅርፅ ይዛ የተፈጠረችው ምድር ለሰባት ከተከፈለች በኃላ ውሃ መላት። አንዳቸውን ከአንዳቸው እንዲሁ ውሃ ለያቸው። በዚህ የተነሳ መሬትን እኛ የምንገኝባትን ውሃ ከበባት በዚህ የተነሳ መሬት ክብ ናት የሚል ግንዛቤ ኖረን። ከአራቱ አለማት አንዱ የሆነው መሬት አምስት ሰማያትን ጠቅልሎ ይዟል እነርሱም ሲዖል ፣ መሬት፣ ብሔረ ብፁአን፣ ብሔረ ሕያዋን፣ ገነት ናቸው። ለዚህም ነው ገነት ምድር ላይ ናት የምትገኘውጨየሚባለው..... ከነዚህ መካከል መሬት ከላይ እንዳየነው የሰው ልጅ በቅጡ ያልተረዳቸው ስድስት ክፍሎችን ይዛለች። ከነዚህ አንዱ የሆነው በርባኖስ እስር ቤት ነው ! በዚህ ጥልቅ እስርቤት ሁለት መቶዎቹ የስማዝያ ጭፍሮች ታስረዋል። በአለመ እሳት ከሚገኙት ሶስቱ ማለትም ኢዮር፣ ራማ ፣ና ኤረር፣ ቅዱሳን መላዕክት የሚኖሩባቸዉ የመላእክት ከተሞች ናቸዉ፡፡ ኢዮር በተሰኘዉ የመላእክት ከተማ 4 የመላእክት ነገዶች ይኖራሉ፡፡ እነርሱም፦ ኣጋእዝት ፣ኪሩቤል፣ ሱራፎፌል፣ እንዲሁም ሃይላት በመባል ይታወቃሉ፡፡ የኣጋእዝቱ መላክት አለቃ ሳጥናኤል ይባላል ፡፡ እንዲሁም የኪሩቤል አለቃ ገፀ ሰብና ገፀ አንበሳ ሲሆን ፤የሱራፌል ደግሞ ገፀ ንስር ነዉ የሃይላት ቅዱስ ሚካኤል ነዉ፡፡ በራማ ደግሞ 3 ነገደ መላእክት ይገኛሉ ስማቸዉም መናብርት ፣አርባብ፣ ስልጣናት ይባላሉ፡፡ የመናብረቱ አለቃ መላኩ ቅዱስ ሩፋኤል ሲሆን የ አረባብ ደግሞ ቅዱስ ገብረኤል ነዉ፡፡ የስልጣናት ደግም ሱራኤል ነዉ፡፡ በሶስተኛዉ የእሳት አለም ዉስጥ የሚገኘዉ ኤረር ደግም 3 ነገደ መላዕክት ይገኛሉ፡፡ የነገዳቸዉም ስም መኳንት፣ ሊቃናትና ፣መላእክት ይባላሉ፡፡ የመኳንት አለቃ መላኩ ቅዱስ ሳዳካኤል ሲሆን የሊቃናት አለቃ ደግሞ መላኩ ቅዱስ ሳላታኤል ይባላል፡፡ የመላእክት ደግሞ መላኩ ቅዱስ አናንያኤል ነዉ፡፡ ምድራዊ ሰማያት ገነት ብሄረ ሄዋን ፣ብሄረ ብፁሀን ፣መሬትና ፣ሲኦል ናቸዉ፡፡ እኛ የምንኖርባት ምድር በማእከል ስትገኝ ገነት በስተምስራቅ ብሄረ ሄዋን ደግሞ በስተሰሜን ብሄረ ብፁሀን እንዲሁ በስተደቡብ እንዲሁም ሲኦል በምዕራብ በኩል ነዉ፡፡ ቀደም ሲል ለመግለፅ እንደተሞከረዉ 14 የሳት ና የምድር አለማት እርስ በርሳቸዉ ግንኙነት የሚፈጥሩባቸዉ እና የሀይላቸዉ ማደሪወች ከ12ቱ 6ቱ በርባንስ ወይም black hoel የአጋንት የክፉ መናፍስት ማደሪያ ሲሆኑ፤ የቀሩት 6 ደግሞ ቅዱሳን መላእክት የሚወጡና የሚወረዱባቸዉ የሀይላቸዉ ማደሪያ ነዉ፡፡

የአለም ሃያላን በሚስጥር የሚፈልጉት የአለምን ሁለንተናዊ አሰራር  ሚስጥር የሚፈታ ድንቅ   የብራና መጻህፍ ! ''Time trave'' በጊዜ የመጓዝ ጥበብ በአዳም ከ ገነትና ወደ ምድር ቆይታው የጊዜ ግዝፈት እንዴት ይለካል? E=MC² የአልበርት አንስታይን ቀመር የጨለማ ድንኳንን እንዴቴ ይፈታዋል? የአለማትን የሳይንሱን ዘረፍ የፈተነዉ ፍንጩ እንኳ ለመስጠት የሚያስቸግረዉ የጨለማ ድንኳን ምንድን ነዉ? የጥንት መዛግብቶቻችን ስለ አለማት ምን ይላሉ ምን ብለዋል? ብራናወቻችን አለም ተመራምሮ ስላልደረሰበት የሚስጥራት ሁሉ ሚስጥር ስለሆነዉ ስለ አለማት አፈጣጠርና አመሰራረት እንዲሁም ጥንተ ተፈጥሮ  ምን ይላሉ? ይህንን ድንቅ ሚስጥር ከደቂቃወች በኋላ በዩቲብ ቻናላችን ይቀርባል አስደኔቂ ምርምር አካፍላችሁ አለሁ ! ተዘጋጁ

የሰው ልጆችን አመለካከት ይቀይራሉ ብየ ከማምንባቸው  እና በዩቲብ ለብዙሃኑ መልስ የሚሆኑ  ሃሳቦች ከሚተላለፊባቸው ቻናሎች ልጠቁማችሁ ወደድኩ! በእጂጉ የምታተርፉበት ከዚህ ቀደም ሰምተናቸው የማናውቃቸውን  አስደናቂ ሚስጥሮች የሚገለጥበት የዩቲብ ቻናል ነው። በእውቀት በእውነት  ለመራቀቅ ከፈለጉ ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ ዘንድ እመክራለሁ። የ ዩቲብ ቻናሉ ስም    ከሃሊ በቃሉ                              kehali bekalu Link     https://youtu.be/YV35BaSLqGU

በዩቲብ መከታተል ለማትችሉ ይህንን ድንቅ እውነት በጹሑፍ ይዠላችሁ እቀርባለሁ!