en
Feedback
Endod + እንዶድ +

Endod + እንዶድ +

Open in Telegram

www.endod.net በአስተውሎት ንጽህና፣ በአብሮነት መድህን፣ ከተፈጥሮ በተቀዳ ጽናት ኃላፊነት የሚሰማው ሰው ሆኖ መገኘት መቻል እና ሌሎችን ማስቻልን መነሻው አድርጎ ወደ ወድ አድማጮቹ በFM Addis 97.1 የሚደርስ የራድዮ መሰናዶ ነው።

Show more
1 226
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ውድ እንዶዳውያን፣ የአፍሪካ ዋንጫ ሲጠናቀቅ የምጥን ተከታታይ መሰናዷችን "ማለፊያችን-፪: ጀባ"ን አራተኛ ክፍል እናስደምጣችዃለን! ከዚያም "የጠፋ ይገኛል" ይከተላል፤ እስከዚያው የምዕራፍ ፪ ቀዳሚ
ውድ እንዶዳውያን፣ የአፍሪካ ዋንጫ ሲጠናቀቅ  የምጥን ተከታታይ መሰናዷችን "ማለፊያችን-፪: ጀባ"ን አራተኛ ክፍል እናስደምጣችዃለን! ከዚያም  "የጠፋ ይገኛል" ይከተላል፤ እስከዚያው የምዕራፍ ፪ ቀዳሚ ተከታታይ መሰናዶ የነበረውን "ሰው እና ሰው" ተጋበዙልን! አንዳች ረብ ያለው ነገር እንደማታጡበት በማመን በሞላ ልብ ጋበዝናችኹ! ደግሞም "እንዶድ"ን እና ይዘቱን የምትወዱ ኹሉ የእንዶድ ዘር ይድረስ ዘንድ ለሌሎች በማጋራት ፍቅር እና እምነታችኹን ትገልጹ ዘንድ እናበረታታችዃለን! ለሌሎች የጋበዛችኹባቸውን "ስክሪን-ሻቶችን" ብታጋሩንም ልባችንን ታሞቁታላችኹ! እነሆ ማስፈንጠርያው! https://youtube.com/playlist?list=PLTqdaZz7JE0UXy6idVFN8Wd-fV1-dm6Bm&si=-c63ttiv_QZ8ZjkB

ውድ እንዶዳውያን፣ የአፍሪካ ዋንጫ ሲጠናቀቅ የምጥን ተከታታይ መሰናዷችን "ማለፊያችን-፪: ጀባ"ን አራተኛ ክፍል እናስደምጣችዃለን! ከዚያም "የጠፋ ይገኛል" ይከተላል፤ እስከዚያው የምዕራፍ ፪ ቀዳሚ ተከታታይ መሰናዶ የነበረውን "ሰው እና ሰው" ተጋበዙልን! https://youtube.com/playlist?list=PLTqdaZz7JE0UXy6idVFN8Wd-fV1-dm6Bm&si=-c63ttiv_QZ8ZjkB

ለምሽታችኹ! https://youtu.be/LT7nmdSZDTY

ሰብስክራይብ የማታደርጉስ? አድርጋችኹ የማታበረቱንስ? የምር... ጥሩ ነገር ለማበሳሰል ጊዜ ወስደናል! ሰብስክራይብ አድርጎ ስክሪንሻት ኮሜንት ላይ ማያያዝ የጥሩ ወዳጃዊ አለኝተኝነት ማሳያ ሆኖ ያገለግላል! ድጋፋችኹ ያሻናል! የምትሰሙት ሙዚቃ በወንድም ጌታ Kidanemaryam Admasu ተከሽኗል፤ በርትቶ ማበርታት የማይደክመው ታናሽ ወንድም Tadee Masee ለሙከራችን እዚህ መድረስ እጁ አለበት! መላው የእንዶድ ቤተሰብም በ'ደጀን-ጦር' ነት በ"ሐሳብ-ወለድ ሐሳቦች" ተሰልፏል! https://youtube.com/@endodplus?si=uJNDfEQm5wdMWBpk

በሕይወት መንገድ የሰው ልጆች ዋጋ ከሚገለጥባቸው የሕይወት እጥፋቶች ውስጥ መለያየት አንዱ ነው፤ እናም ይህ መለያየት የከበደ ስቃይ እና ሥነ-ልቦናዊ ጫና ያስከትላል። በእርግጥ እንዲህ ካለው ስቃይ ማገገም ይቻላል? ከተቻለስ እንዴት? የባልደረቦቻችንን የአበባው ፍሰሃን(በቅርቡ በሞት የተነጠቅነው ወንድማችን) እና የዮፍታሔ ማን ያዘዋልን ቆይታ ታደምጡት ዘንድ ጋበዝናችኹ። https://youtu.be/ua9jv-zwhhM

ይኸው አዲሱ ነገር... "ሐሳብ-ወለድ ሐሳቦች" - ዕለታዊ የጠዋት ፖድካስት! በቅርብ ቀን በ እንዶድ+ የዩትዩብ ቻናል ይጀመራል፤ እስከዛው ሰብስክራይብ እያደረጋችኹ ቆዩማ! ስለቀናነታችኹ ልብ ይመርቅ
ይኸው አዲሱ ነገር... "ሐሳብ-ወለድ ሐሳቦች" - ዕለታዊ የጠዋት ፖድካስት! በቅርብ ቀን በ እንዶድ+ የዩትዩብ ቻናል ይጀመራል፤ እስከዛው ሰብስክራይብ እያደረጋችኹ ቆዩማ! ስለቀናነታችኹ ልብ ይመርቅ! https://youtube.com/@endodplus?si=uw7cyFJlZUaIngkU

photo content

አዲስ ነገር በቅርቡ... በዩትዩብ ሜዳ፤ እስከዛው ሰብስክራይብ እያደረጋችኹ ቆዩማ! እነሆ ሊንኩ ፤ ስለቀናነታችኹ ልብ ይመርቅ! https://youtube.com/@endodplus?si=uw7cyFJlZUaIngkU

"ጀባ" የተሰኘው ምጥን ተከታታይ መሰናዷችን ክፍሎች አምልጠዋችኹ ቅር ለተሰኛችኹ፤ እነሆ "ጀባ" 2- "ትዝ አለኝ"፡ ትዝታ | ዝምታ | ወግ "በአገር ቁጭ ብሎ አገርን መናፈቅ!"

ሸጋ ነገር ለአዲሱ ሳምንታችኹ! "ነፃነት፡ ቀንበር ወይስ መንበር?" -2: "በእርግጥ ነፃነት ምንድር ነው?" ኮሜዲያን ማሜ ከባልደረባችን መኮንን ሞገሴ ያደረገውን ቆይታ ተጋበዙልን! ማስፈንጠሪያውን ኮሜንት መስጫው ላይ ያገኙታል፤ ሰብስክራይብ፣ ላይክ እና ሼር በማድረግ ለብዙዎች እንድንደርስ ድጋፍዎን እንሻለን! https://youtu.be/09YZPWsn_1Y?si=8HHsPCNHqNVVH1YJ

photo content

በእንዶድ ምዕራፍ ፩ ከሰውመሆን ይስማው (ሶሚክ) ጋር የተደረገውን ሸጋ ቆይታ አድምጠዋል? - "8፡ 62"፣ "የፀሃይ መውጫ ልጆች" ፣ "ዓለሜ" ፣ "እውር አሞራ ቀላቢ" (DocuDrama) ፣ "ሰውነ
በእንዶድ ምዕራፍ ፩ ከሰውመሆን ይስማው (ሶሚክ) ጋር የተደረገውን ሸጋ ቆይታ አድምጠዋል? - "8፡ 62"፣ "የፀሃይ መውጫ ልጆች" ፣ "ዓለሜ" ፣ "እውር አሞራ ቀላቢ" (DocuDrama) ፣ "ሰውነቷ"ን ጨምሮ ከ15 በላይ ፊልሞች ላይ በድርሰት፣ በዝግጅት፣ በሲኒማቶግራፊ እና በፕሮዲውሰርነት ተሳትፏል። - የቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ "ማር እስከ ጧፍ" እንዲሁም የእሱባለው ይታየው "ዘፈን ማሞቂያ አይደለም" እና " ይቻትና ልጅት" የሙዚቃ ቪድዮዎችም የዚሁ ባለሙያ ሸጋ አበርክቶዎች ናቸው። - በተከታታይ ድራማ ዘርፍም "አደይ" ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማን በስሙ በተሰየመ የፊልም አምራች ኩባንያ ለኪነጥበብ አፍቃሪው እያቀረበ ነው። ብዙዎችም ወደው ይከታታሉት ከያዙ ከረምረም ብለዋል። - በእንዶድ መሰናዶ "ነገን አብዝቶ የሚናፍቅ ሰብዕና ዛሬን በድል ይሻገራል!" ፫ በመኮንን ሞገሴ Mekonnen G Mogessie አጋፋሪነት "የማያልቀው፣ ግን የማያ'ደቀው ናፍቆት..." በተሰኘ ገዢ ርዕስ ነውያደረገውን ቆይታ ክፍል 1 ተጋበዙልን። https://www.youtube.com/watch?v=JveelzYZOvs linktr.ee/shegafuture ለተሻለ ነገ እናዋጣለን!

ከዲበኩሉ ጋር ያደረግነውን ቆይታ አድምጣችኹታል? ተጋበዙልን! https://youtu.be/IQ5WVPFkL0s
ከዲበኩሉ ጋር ያደረግነውን ቆይታ አድምጣችኹታል? ተጋበዙልን! https://youtu.be/IQ5WVPFkL0s

እነሆ "ማለፊያችን!" -2 : “ጀባ” ያሳያችኹንን ፍቅር እና አክብሮት ይሸከም ዘንድ የደከምንበት ልዩ ምጥን ተከታታይ መሰናዶ “ማለፊያችን”-2 እነሆ ሁለተኛ ክፍል እነሆ በቅርቡ “ጀባ” የሚል መጠሪ
እነሆ "ማለፊያችን!" -2 : “ጀባ” ያሳያችኹንን ፍቅር እና አክብሮት ይሸከም ዘንድ የደከምንበት ልዩ ምጥን ተከታታይ መሰናዶ “ማለፊያችን”-2 እነሆ ሁለተኛ ክፍል እነሆ በቅርቡ “ጀባ” የሚል መጠሪያ የሰጠውን EP ያበረከተልን ወጣቱ ድምጻዊ አብነት ባላ “ትዝ አለኝ” መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ ልዩ መሰናዶ፤ መኮንን ሞገሴ እና ተሻለ ከበደ አብረዋችኹ ያመሻሉ። ጸጋ ካሕሳይ እናንተን ያስተናግዳል። የእልፍኝ አስከልካያችኹ ጥንቅርም በ0931717191 የሰደዳችኹልንን የቸር ልቦቻችሁን ረጢብ ስንቆች መልሰው ወደ እናንተ ይደርሱበት ዘንድ ተሰናድቷል። ሸጋ ሸጋ ጥያቄዎች የተሰደሩበት መሰናዶ ነውና ያድምጡ፣ ይሳተፉ፣ ሸጋ ጥያቄዎች ይሸምቱ ስንል ጋበዝንዎ! ዛሬ ረቡዕ ጥር 01 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ በFM Addis 97.1 በመላው ኢትዮጵያ እንዲሁም በቀጣዩ ማስፈንጠሪያ በመላው ዓለም መደመጥ ይጀምራል። https://zeno.fm/radio/ebc-fm-addis-97-1/... ኑ! ለተሻለ ነገ 'አብ'ረን' እናዋጣ!

በገና ዋዜማ መንፈሳዊ ይዘት ወዳላቸው፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከብርሃነ-ልደቱ ጋር ግንኙነት ወዳላቸው የተመረጡ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች የምናቀናበት ልዩ መሰናዶ፤ “ከአራራት እስከ ናዝሬት!” አቤል
በገና ዋዜማ መንፈሳዊ ይዘት ወዳላቸው፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከብርሃነ-ልደቱ ጋር ግንኙነት ወዳላቸው የተመረጡ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች የምናቀናበት ልዩ መሰናዶ፤ “ከአራራት እስከ ናዝሬት!” አቤል ብርሃኑ የወይኗ ልጅ፡ ያለ ፓስፖርት እና ቪዛ ወደ ቱሪስት መዳረሻዎቹ ወስዶ ያጎበኘናል፤ በእነዚህ ቦታዎች ኢትዮጵያን እና የአገሩን ቋንቋዎች ሲያገኝ ምን ተሰምቶት ይሆን? ያጋራናል፤ መኮንን ሞገሴ መሰናዶውን ያጋፍራል። አቤል ኢንተርቴንመንት እና ሸጋ ሶሻል ኢንተርፕረነርስ ከ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል። ዛሬ ምሽት በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ይጠብቁን።

photo content