cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethio Fm 107.8

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Show more
Advertising posts
19 308
Subscribers
-924 hours
+537 days
+27430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የአስፓልት መንገድን በአፈርና በጠጠር አንዲሁም በጭቃ ያበላሹ 91 የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ተቀጡ፡፡ በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አምስት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የጫኑትን ጭነት ሳይሸፍኑ እንዲሁም የተሸከርካሪ ጎማ ሳያጸዱ በማሽከርከር በመንገድ ላይ ጠጠርና አፈር ያንጠባጠቡና በጭቃ አስፓልት ያበላሹ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎችን በልዩ ኦፕሬሽን እንዲቀጡ አድርገዋል፡፡ በተለይም በ90 ቀናት የተግባር ክንውን ወቅት የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ አፈርና ጭቃ ከጎማ ላይ ሳያፀዱ ወደ መንገድ እንዳይወጡ እንዲሁም ከመጠን በላይ ትርፍ አፈርና ቆሻሻ እንዳይጭኑ ተገቢውን ቁጥጥር እዲደረግ በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት በየቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከ ግንቦት 1 እስከ 10 ባሉት ቀናት በለሚ ኩራ 38 በቦሌ 36 በአዲስ ከተማ 7 በልደታ 4፣ በቂርቆስ 4 በየካ 2 በድምሩ 91 አሽከርካሪዎች ተቀጥተዋል፡፡ በአጫጫን ጥንቃቄ ጉድለት ጭነትን ሳይሸፍኑ ያንጠባጠቡ እና ከተሸከርካሪዎች ጎማ ላይ ጭቃ ሳያጸዱ አስፓልት መንገድን ያበላሹ እነዚሁ አሽከርካሪዎች የተቀጡት በደንብ 395/2009 በእርከን 1/14 መሰረት ሲሆን ቁጥጥሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅንመንት ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም
Show all...
👍 9😱 1
ጓደኛቸውን በመግደል ሲያሽከረክረው የነበረውን መኪና ወስደው ተሰውረዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ *** የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሰሜን ማዘጋጃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ገ/ሚካኤል ሰይፉ የተባለው ሟች የወንጀል ፈፃሚዎቹ የቅርብ ጓደኛ በመሆኑ በየዕለቱ እየተገናኙ አብረው የሚውሉ፣ የሚዝናኑ እና በእጅጉ የጠነከረ የጓደኝነት ግንኙነት ያላቸው የሱሉልታ ከተማ ነዋሪዎች እንደሆኑ ተጠርጣሪዎቹ ለፖሊስ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል። በዕለቱ ሟች በወንጀሉ ከተጠረጠሩት ከሁለቱ ጓደኞቹ ጋር አብሮ ሲዝናና እንዳመሸ ታውቋል። ተጠርጣሪዎቹ ቴዎድሮስ ታከለ እና ሲሳይ ጥላሁን ከምሽቱ 5 ስዓት ገደማ የጓደኛቸውን አንገት በማነቅ ህይወቱ እንዲያልፍ ካደረጉ በኋላ አስክሬኑን መንገድ ላይ በመጣል ሞባይል ስልኩንና መታወቂያውን ጨምሮ በወቅቱ ሲያሽከረክረው የነበረውን የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 4-15624 ኢት መኪና ወስደው ተሰውረዋል ተብሏል፡፡ ፖሊስ የወንጀሉ ሪፖርት ከደረሰው በኋላ ባደረገው ያልተቋረጠ ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ለይቶ በማወቅ በ24 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡ አንደኛው ተጠርጣሪ ከአየር ጤና አካባቢ የተያዘ ሲሆን ሁለተኛው ተጠርጣሪ ደግሞ ሱሉልታ ከተማ ውስጥ ሊገኝ ችሏል፡፡ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተከናወነ ምርመራ የማስፋት ስራ የሰረቁትን ተሽከርካሪ በሸገር ከተማ ወለቴ ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ በመውሰድ እንዲሸጥላቸው ለአንድ ግለሰብ እንደሰጡት በማረጋገጥ መኪናው ከቆመበት በምሪት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ ተሽከርካሪውን ለመሸጥ ተስማምቶ ከተጠርጣሪዎቹ የተቀበለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የክትትል እና የምርመራ ስራው የቀጠለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። የከተማችንን እና የነዋሪዎቿን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆ በከተማችን የተፈጸሙ አንዳንድ ወንጀሎችን መነሻ በማድረግ የበሬ ወለደ ይዘት ያላቸውን የተዛቡ እንዲሁም የተጋነኑ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ግለሰቦችና ተቋማት መኖራቸውን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ የከተማችንን የፀጥታ ጉዳይ በተመለከተ ትክክለኛውን መረጃ ከትክክለኛ ምንጭ የማግኘት ልምድን ሊያዳብር እንደሚገባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፎ ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ ፖሊስ ጨምሮ አሳስቧል። ምንጭ፡- የአዲስ አበባ ፖሊስ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም
Show all...
👍 4👏 2

የነገ የግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ስብስቡን ይፋ ሆነ ! በአሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት የሚመራው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ለቀጣዩ የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር የሚጠቀመውን ስብስብ ይፋ አድርጓል። ማርከስ ራሽፎርድ ከስብስቡ ውጪ የሆነው በእሱ ቦታ የተሻለ አመት ያሳለፉ ተጨዋቾች መኖራቸውን ተከትሎ መሆኑን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ገልጸዋል። ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ ከሚያደርጋቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች በኋላ ሰባት ተጨዋቾችን በመቀነስ ወደ አውሮፓ ዋንጫው ያመራል። ጃደን ሳንቾ በዲሲፒሊን ምክንያት ነው ከዛሬው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ውጪ የሆነው። በጋዲሳ መገርሳ ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም
Show all...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
በሲንጋፖር አየር መንገድ አዉሮፕላን በረራ ላይ ባጋጠመ የአየር ለዉጥ አንድ መንገደኛ መሞቱ ተገለጸ፡፡ ከለንደን ወደ ሲንጋፖር ሲበር የነበረዉ ቦይንግ 777-300 አዉሮፕላን ባጋጠመዉ የአየር ለዉጥ አንድ መንገደኛ ህይወቱ ሲያልፍ ሌሎች 30 መንገደኞች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸዉ ተገልጿል፡፡ ብዙም በማያግጥም ክስተት የአንድ ሰዉ ህይወት ማለፉን እና አዉሮፕላኑም ባንኮክ ላይ ለማረፍ መገደዱን የሲንጋፖር አየር መንገድ አስታዉቋል፡፡ የዘርፉ ባለሙያዎች እንደዚህ ዓይነት አደጋዎች ብዙ ጊዜ የሚከሰቱት ተጓዦች የመቀመጫ ቀበቷቸዉን በማያስሩበት ወቅት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በአየር ሁኔታ መከታተያዉ ላይ ምንም ዓይነት ለዉጥ ባለመታየቱ አብራሪዉ አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ መስጠት አለመቻሉንም አንስተዋል፡፡ ቦይንግ 777-300 ኢ አር የበረራ ቁጥር ኤስ-ኪዉ 321 አዉሮፕላን በዉስጡ 2መቶ11 ተሳፋሪዎችን እና 18 የበረራ ሰራተኞችን ይዞ ነበር ከለንደን ሄዝሮዉ አየር መንገድ የተነሳዉ፡፡ ባለፈዉ ዓመት ግንቦት ወር ላይ ከህንድ ዴልሂ ተነስቶ ወደ አዉስትራሊያ ሲድኒ ሲጓዝ የነበረ የህንድ አዉሮፕላን ላይ እንደዚህ ዓይነት የአየር ለዉጥ ተከስቶ ብዙ ተጓዦች ጉዳት እንደደረሰባቸዉ ሲኤንኤን አስታዉሷል፡፡ በእስከዳር ግርማ ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም
Show all...
👍 1
#መዋሸት ከአዕምሮ ጤና ችግር ጋር ምን ያገናኘዋል ? መዋሸት ከልጅነት ዕድሜ ይጀምር እና እስከ እድሜ አመሻሽ ድረስ ሊቀጥል እንደሚችልም ይነገራል። ውሸት የህመም ምልክት ሊሆን እና የስብዕና መለያ ተደርጎ ይታሰባል፡፡ ለውሸት ምክንያት የሚሆኑ ጉዳዮችን እና የመፍትሄ ሃሳችን በተመለከተ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ ያደረጉት የአእምሮ ሀኪም የሆኑት ዶክተር እስጢፋኖስ እንዳላማው ውሸትን ህመም ነው ማለት ባይቻልም ሲደጋገም ግን እንደ ህመም ባይወሰድም የህመም ምልክት ግን ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡ ሰዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ውስጥ ሊዋሹ የሚችሉ ሲሆን፤ ጊዜ እና ቦታ እየመረጡ የሚዋሹ እና በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ መዋሸትን የሚመርጡ በማለት ዋሾዎችን በሁለት መልኩ ከፍሎ መመልከት እንደሚቻል ይገለጻል፡፡ #ለመዋሸት እንደ ምክንያት የሚነገሩ መላምቶች • የአእምሮ ጭንቀት • የጤና እክል • ዝቅተኛ በራስ መተማን • በሰዎች ዘንድ ተፈላጊነትን ለመጨመር በማሰብ • የናርስሲሲት ስብዕና ያላቸው ሰዎች (አፍቅሮ ራስ) • ከዚህ በተጨማሪም በቤተሰብ ውስጥ የሚዋሽ ሰው ካለ ህጻናት ውሸትን እየተለማዱ እንዲያድጉ ያደርጋል፡፡ በመዋሸት ሌሎች ለመጉዳት የሚሞክሩ ሰዎች ቢኖሩም እንኳን ያለፈ የህይወት ታሪካቸው በሚያሳድርባቸው አሉታዊ ተጽዕኖ ብቻ ሰዎች ሊዋሹ ይችላሉ ተብሏል፡፡ አንዳንዶች ለምን እንደሚዋሹ ምክንያቱን ባይቁትም ፍላጎታቸው መዋሸት ብቻ ሆኖ ሊያገኙት ይችላሉ፡፡ የመዋሸት ፍላጎታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ ይጨምር እና በመዋሸታቸው ደስተኛ እንደሆኑ እንዲሰማቸው ሲናገሩም እንደሚስተዋል ተነግሯል፡፡ ሰዎችን ያለ ምክንያት ማታለል፣ አመለካከታቸውን ማሳት የስብዕና እክል ተደርጎ ይታሰባል፡፡ በህይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ ጉዳቶች ሰዎች እንዲዋሹ እንደ ምክንያትም የሚነሳ ሲሆን ፍርኃትም ለመዋሸት ምክምያት ሊሆን እንደሚችል ተመላክቷል፡፡ ሆን ብሎ መዋሸት፣ ሀላፊነትን አለመውሰድ፣ እንደ ታመሙ ማስመሰል፣ ግልፍተኛ መሆን እና የሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ በሚዋሹ ሰዎች ይስተዋላል ተብሏል፡፡ #እንዴት መዋሸትን ማቆም ይቻላል፤ በሰዎች እንዋሻለን የሚለው አመለካከት አለመሩ ለሚዋሹ ሰዎች በስነ ልቦና ባለሞያ የሚደረግላቸውን ህክምና አስቸጋሪ እንደሚያደርገው ተነግሯል፡፡ ሰዎች በቅድሚያ ስለ ውሸት እራሳቸውን መጠየቅ እንደሚገባቸው የተገለጸ ሲሆን፤ በንግግር ህክምና የመዋሸት ባህሪን ማከም ይቻላልም ተብሏል፡፡ በህክምናው ሰዎች የሚዋሹበትን ምክንያት እንዲረዱ ማድረግ እና ሌሎች ተጓደኝ የአእምሮ ህመሞችን ካሉ ማከምን ያካተተ መሆኑ ተነግሯል፡፡ በእሌኒ ግዛቸው ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም