GLOW STAR KG AND PRIMARY SCHOOL ADDIS ABABA ETHIOPIA.
Open in Telegram
1 615
Subscribers
No data24 hours
+57 days
+6230 days
Posts Archive
1.ሐሙስ ሰኔ 22/2015 ዓ.ም ለጣቢያ ሀላፊ ፣ለሱፐርቫይዘሮች፣ ለፈታኝ እና ጤና ባለሙያዎች በተመደቡበት የፈተና ጣቢያ ኦረንቴሽን ይሰጣል
2.አርብ ሰኔ 23/2015 ዓ.ም ለ8ኛ እና 6ኛ ክፍል ተማሪዎች በተመደቡበት የመፈተኛ ጣቢያ ኦረንቴሽን ይሰጣል
3.ከሰኔ 26-27/2015 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ይሰጣል፡፡
4.ከሰኔ 28-30/2015 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ይሰጣል፡፡
✅በመሆኑም ሁሉም የግል እና የመንግስት ት/ቤቶች እና ወላጆች ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት የፈተና ጣቢያ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት ተገኝተው ፈተናቸውን በአግባቡ እንዲወስዱ በማድረግ የበኩላቹህን አስተዋጽኦ እንድታበረክቱ አደራ እንላለን
በጋራ እርብርብ የተማሪዎቻችንን ውጤት እና ስነምግባር እናሻሽላለን!!
የ2016ዓ.ም ምዝገባ መረጃ
ከትምህርት በሮ በተላለፈ የምዝገባ መመሪያ መሠረት የነባር ተማሪዎች ምዝገባ፡-
👉ከሐምሌ 03-20/2015 ዓ.ም
ይካሄዳል ::
👉ሐምሌ 20/2015 ዓ.ም ለነባር
ተማሪዎች የመጨረሻ የምዝገባ ቀን
ይሆናል ::
👉ለምዝገባ ሲመጡ የ2015 የት/ት
ዘመን ሪፖርት ካርድና ሁለት ጉርድ ፎቶ
ግራፍ ይዘው መምጣትዎን አይርሱ::
ማሳሰቢያ:- ከላይ ከተጠቀሰው ቀን አሳልፎ
ወይም ዘግይቶ የሚመጣን ወላጅ የማናስተናግድ መሆኑን አውቃችሁ በወቅቱ ልጆቻችሁን እንድታስመዘግቡ ከወድሁ እናሳስባለን።
ግሎው ት/ቤት
> Sis:
በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች!
========================
👉ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው::ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤
ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዘዴዎች፤
------------------------------------------------
☝️ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።
☝️ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡
👌ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ።
☝️ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።
☝️ ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል።
☝️ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።
ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤
👉 ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።
👉አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ።
👉ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።
👉 በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ። ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር::
👉 ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤
👉በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።
👉ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ።
👉በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ።
👉መጭው ወቅት የፈተና ወቅት ነውና ለተፈታኞች በሙሉ መልካም ጊዜ ተመኘን👏👏👏👏
📝ሰሞነኛ 📝
ልጆችና👧🧒 ዝናብ🌧
ልጆች በዝናብ እንደመጫወት በውሀ እንደመንቦራጨቅ የሚያስደስታቸው ነገር የለም አልፈንበታልና መቼም ሁላችንም እናውቀዋለን ግን ምን ያደርጋል የሚያስደስት ሁሉ መልካም አይደለም አደጋ አለው እናም ጥንቃቄዎችን ለኛም ለልጆቻችንም እናድርግ።
"አይሆንምን ትተሽ ይሆናልን ያዢ" 👵ትለኝ ነበር አያቴ ምክሩ ቀላል ይመስላል ብዙዎቻችን ምንም አይመጣም ችግር የለውም ብለን የምናልፋቸው ነገሮች ደርሰው ጎድተውናልና ቅድመጥንቃቄን መተግበር መልካም ነው ስለዚህ?ስለዚህ...
⛈ የአየሩን ሁኔታ አይቶ ለልጆች ከደንብ ልብስ (ከዮኒፎማቸው)ስር የሚሞቁ ልብሶችን ማልበስ🧥🥼
⛈ በዝናብ ውስጥ እንዳይሯሯጡ እና በውሀ እንዳይንቦራጨቁ መምከር።
⛈ በዝናብ ወቅት የተቆፈረ ወይም ያልተደፈነ ጉድጓድ በውሀ ስለሚሸፈን ልጆቻችን ከእጃችን ሳይወጡ ግልፅ ሆኖ በሚታይ መንገድ መጓዝ ይኖርብናል።
⛈ እንደሚታወቀው ዝናብ ለመኪናም አስቸጋሪ ስለሆነ ስናሽከረክርም🚗 በጥንቃቄ እግረኛም ከሆንን ልጆቻችንን እጃቸውን ይዘን እራሳችን ብንወስዳቸው ይመረጣል።
⛈ ዝናቡ አባርቶ እንኳን ከሌላ ቦታ በዘነበ ዝናብ ምክንያት ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል ልጆችን በቤት ውስጥ ማቆየት
⛈ ከዚህ በፊት በምናውቀው በዝናብ ወቅት ድንገት የኤሌትሪክ መቋረጥ፣ የኤሌትሪክ ⚡️ገመድ መርገብ፣ የኤሌትሪክ እንጨት መውደቅ፣ በገመዶቹ መነካካት የሚፈጠር እሳት🔥 እና ሌሎችም አደጋዎች ስለሚኖሩ በዚህም ጉዳይ የተቻለንን ጥንቃቄ ማድረግ መልካም ነው።
የልጆቼ ወላጆች👨👩👧👦 አይሆንምን ትተን ይሆናልን እንያዝ ጨርሻለሁ።
ት/ቤትዎ
✍የ2015 ትምህርት ዘመን 2ኛው ሴሚስተር አጋማሽ ፈተና ፕሮግራም ከላይ የተያያዘ ሲሆን ልጅችዎ በፕሮግራሙ መሰረት እንዲያጠኑ እገዛ ያድርጉላቸው፡፡
# ስለሚደረገው ክትትልና ድጋፋ እናመሰግናለን!!👍👍👍👍👍
ት/ቤትዎ
የ2015 ትምህርት ዘመን 2ኛው ሴሚስተር አጋማሽ ፈተና ፕሮግራም ከላይ የተያያዘ ሲሆን ልጅችዎ በፕሮግራሙ መሰረት እንዲያጠኑ እገዛ ያድርጉላቸው፡፡
# ስለሚደረገው ክትትልና ድጋፋ እናመሰግነለን!!
ት/ቤትዎ
ሚያዚያ 19/ 2015 ዓ.ም
የተከበራችሁ የትምህርት ቤታችን
ወላጆች
# ከነጌ ሚያዚያ 20 - 21/2015 ዓ.ም በመምህራን ስልጠና ምክንያት ትምህርት የማይኖር መሆኑን እና
# ሚያዚያ ሰኞ 23/2015 ዓ.ም የላብ አደሮች ቀን ታስቦ ስለሚዉል ትምህርት አይኖርም።
# ሚያዚያ ማክሰኞ 24/2015 ዓ.ም መደበኛ ትምህርት ይቀጥላል።
ለ1444ኛዉ ኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።
ግሎው ት/ቤት
Eebla 12/2015 ALH
Maatiiwwan manan barumsaa keenya hundaaf / Maraaf
Duran dursa hordoftoota Amantaa Musliimota maraaf baga ayyaana waggaa 1444ffaa IId Alfaxiriif isin gahe Jenna.
Haa ta’u malee sababa ayyaana kanaan walqabatee Eebla 13/2015 ALH manni barumsaa cufaa ta’uu isaa isin beeksifna.
Dabalataanis Sambata Eebla 14/2015 ALH sababa ayyaana kanaan barumsi gargaarsaaf/ Tutor Class/ kennamu kan hin jiraanne ta’uu isaa isin beeksifna.
Wixata Eebla 16/2015 ALH barnootni idilee guyyaa guutuu itti fufa.
Mana Barumsaa Glow
ሚያዚያ 12/ 2015 ዓ.ም
የተከበራችሁ የትምህርት ቤታችን ወላጆች
ለእስልምና እምነት ተከታዬች እንኳን ለ1444ኛዉ ኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።
በኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት ነገ ዓርብ ሚያዚያ 13 /2015ዓ.ም ትምህርት ቤት ዝግ ሆኖ ይውላል፡፡
ቅዳሜ ሚያዚያ 14/2015 ዓ.ም በበዓሉ ምክንያት የማጠናከሪያ ት/ት የማይኖር መሆኑን እየገለፅን።
ሰኞ ሚያዚያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም መደበኛው ትምህርት ይቀጥላል፡፡
ግሎው ት/ቤት
ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!! አደረሰን!
መልካም ዓመት በዓል!
ግሎው ት/ ቤት
