የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
Open in Telegram
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Show more2 794
Subscribers
+124 hours
+87 days
+2030 days
Posts Archive
እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ አደረሰን !!
ዛሬ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ. ም.
የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ወርኃዊ በዓሉ ነው ።
ይኽንኑ በእየወሩ የሚከበረውን የጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስን በዓል አስመልክቶ በፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤታችን አሳታሚነት መልክዐ ጰራቅሊጦስና መልክዐ ቅዱስ ሚካኤል የጸሎት መጽሐፍ በግእዝና በአማረኛ ታትሞ ቀርቦልናል ።
እነሆ ጉባኤ ጰራቅሊጦስን እየተካፈልን :
በዚኹ የጸሎት መጽሐፍም
የቅዱስ ሚካኤልን አማላጅነት
የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስን
አዳኝነት እንማፀንበት ። በቅዱስ ወንጌል
"" መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ ። "" ተብለናልና ።
ዮሐ = 20 - 22 ።
የመጽሐፉ ዋጋ == 150 ብር ።
በብዛት ለሚወስድ = ስልክ
09 11 09 15 98
09 31 14 44 44
+3
የእለቱ የአገልግሎት ዜና
ነሐሴ ፲፯/፳፻፲፰
በዛሬው ዕለት የሰንበት ት/ቤታችን አዳጊ-ሀ ሕጻናል ክፍል በርዕሰ አድባራት መንበረ ጸሐይ እንጦጦ ማርያም እና በእንጦጦ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ወኤልያስ አብያተ ክርስቲያናት ዓመታዊ የአንድነት ጉዞዋቸውን አከናውነዋል።
ለጉዞው መሳካት የትራንስፖርት ወጪያቸውን በማዕከላውያን ክፍል አባላት ከቡሄ ዝማሬ ያገኙትን ገቢ ለታናናሾቻቸው ወጪውን በመሸፈን ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሲሆን፤ በቀጣይ ነሐሴ 30 የአዳጊ-ለ ሕጻናት ክፍልና የማዕከላውያን ክፍል የአንድነት ጉዞ የሚያደረግ በመሆኑ፤ ይህንንም ጉዞ በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ አባላትን በማስተባበር ከፍለው መሄድ የማይችሉ ወንድምና እሕቶቻችንን ለማገዝ የጉዞ ኮሚቴ ጥሪ እያደረገ ስለሚገኝ፤ አባላት እንደ አቅማቸሁ የተዘጋጀውን የድጋፍ ኩፖን በመግዛት እንድንተባበር ጥሪ አቅርበዋል።
እግዚአብሔር ማኅበራችንን ይባርክልን!
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
✨ሰላም እንደምን አመሻችሁ✨
ለፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት በሙሉውድ የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት በሙሉ የፊታችን ማግሰኞ ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም Calendar ዝግ የሆነ በመሆኑ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በሰ/ት/ቤታችን በጀትና ንብረት አስተዳደር አስተባባሪነት ለአገልግሎት የምንጠቀምበትን ልብሰ ስብሐት ለማጠብ መርሐግብር ይዘናል በመሆኑም በዕለቱ መምጣት የምንችል አባላት በሙሉ በመገኘት ይህን የትሩፋት ሥራ በመሥራት ከበረከቱ ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ በአምላከ ቅዱስ ሚካኤል ስም በአክብሮት ጠርተኖታል።
እግዚአብሔር ማኅበራችንን ይባርክ!ከበጀትና ንብረት አስተዳደር ክፍል
+1
በዛሬ ዕለትን የእናታችን የቅድስት ኪዳነ ምሕረትን ዓመታዊ የትንሣኤ እና የዕርገት በዓል የደብራችን ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ጸሐይ ቆሞስ አባ ብርሃነ ሥላሴ አስፋው፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሰበካ ጉባኤ አባላት እና በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል። ወቅቱ ክርምት እንደመሆኑ ዝናብ ቢጥልም፣ ምዕመናን ዝናቡን ታግሰው በዓሉን በታላቅ መንፈሳዊ ስነ ሥርዓት አክብረው ውለዋል።
የእናታችን የኪዳነ ምሕረት ጸሎት በረከቷ፣ ምልጃ ቃል ኪዳኗ፤ የልጇ ቸርነት አይለየን!
+9
ነሐሴ 13 በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትን በዓል ምክንያት በማድረግ የሰንበት ት/ቤታችን ማእከላውያን ክፍል አባላት በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የበዓሉን ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ በመጨረሻም በደብራችን በርካታ ምዕመናን በተገኙበት፤ ስለ በዓሉ ቃለ እግዚአብሔር ከተሰጠ በኋላ በችቦ ማብራት እና በዝማሬ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል። የማእከላውያን ክፍል አባላት በየዓመቱ ለምናካሂደው ጉዞ ከፍለው መጓዝ ለማይችሉ አባሎቻችን፤ ከቡሄ ዝማሬ የሚያገኙትን ገቢ ሙሉ በሙሉ ለጉዞ ኮሚቴ በማስረከብ ለጉዞው ድጋፍ የሚያደርጉ ሲሆን፣ ለዚህ በጎ አገልግሎታቸው አምላከ ሚካኤል ዋጋቸውን ይክፈልልን ለማለት እንወዳለን።
እግዚአብሔር ማኅበራችንን ይባርክ!
+1
📢 ደረሰ ደረሰ...
ውድ አባላቶቻችን ፤ ለጉዞው የቀረን ጊዜ በጣም አጭር በመሆኑ ሁላችሁም የጉዞ ትኬት በሰ/ትቤቱ ጽ/ቤት፣ ልማት ሱቅ እንዲሁም የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም እንድትቆርጡ ስንል በአክብሮት እናሳስባለን። በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች በመደወልም መመዝገብ ይችላሉ።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
