cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

️🌙ኢስላም የሰላም መንገድ🌙️

🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌 ወደ አላህ ከጠራና መልካምን ከሰራ <<እኔ ከሙስሊሞች ነኝ>> ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማነው? አል–ፉሲለት ምዕ41:33 t.me/MuslimNegnEneSul t.me/MuslimNegnEneSul 🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟 🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌

Show more
Advertising posts
316
Subscribers
No data24 hours
+17 days
-230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

             ┄┄┉┉✽‌»‌🌼»‌✽‌┉┉┄┄               💥💥 #የጁመዓ_ሱናዎች 💥💥 🌹 ገላን መታጠብ             🌹ሽቶ መቀባት ለወንድ 🌹ልብስ መቀየር             🌹ጥፍርን ማሳጠር 🌹በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ             🌹ሰለዋት ማብዛት 🌹ሱረቱል ካህፍን መቅራት             🌹ሲዋክ መጠቀም 🌹ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ              ┄┄┉┉✽‌»‌🌼»‌✽‌┉┉┄┄ https://t.me/MuslimNegnEneSul https://t.me/MuslimNegnEneSul •••••••🌟🌟 መልካም ጁምአ 🌟🌟••••••••
Show all...
ለመኖር አዲስ ቀን በተሠጠኝ ቁጥር ከራሴ ተስፋ የቆረጥኩበት ሁኔታ ዳግም ይለመልማል። ከትናንት ወዲያ አጠፋሁ ብዬ ዕድሜ ልኬን ስቆዝም አልኖርም ። ትናንት ወደቅኩ ብዬ ዘላለሜን ስተክዝ አልገኝም። አቧራዬን አራግፌ ጭቃዬኔ ተጣጥቤ እስቲ ልነሳና ዛሬን ልየው ደግሞ። አልሐምዱ ሊላህ ዐላ ኩሊ ሓል። የእስትንፋሴ ጌታ አላህ ሆይ አጠንክረኝ። ሶባሐል ኸይር ወዳጆቼ ! https://t.me/MuhammedSeidAbx
Show all...
ቁርአን ውስጥ የተጠቀሱ 7 ከንቱ ምኞቶች‼ ============================= ①) «ዋ ምኞቴ! ምነው አፈር በሆንኩ!» [አ-ን'ነበእ: 40] ②) «ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ!» [አል-ፈጅር: 24] ③) «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ!» [አል-ሐቀህ: 25] ④) «ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ አድርጌ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ!» [አል-ፉርቃን: 28] ⑤) «ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን፤ መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ!» [አል-አሕዛብ: 66] ⑥) «ዋ ምኞቴ! ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ!» [አል-ፉርቃን: 27] ⑦) «ወይ ምኞቴ! ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከነሱ ጋር በሆንኩ!» [አ-ን'ኒሳእ: 73] ሁሉም የሟቾች ምኞቶ ናቸው። ቀብር ውስጥ ያሉት ሰዎች ምኞታቸው ወደ ዱንያ አንዴ መጥተው ለአኺራቸው ጥሩን ነገር መስራት ነው። ግን ምን ዋጋ አለው! አልፏል ተቀድሟል! ቀብር ገብተህ አንተም ይህን ከምትመኝ ነፍስህ አካልህ ውስጥ እስካለች ድረስ ለአኺራህ አስቀድም።  ብልህ የሆነ ሰው ከመጸጸቱ በፊት ሥራውን ይሥራ አላህ ሆይ! ከነዚህ ከንቱ ምኞቶች በእዝነትህ ጠብቀን።
Show all...
አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ያ ጀመዓህ! "የተደበቀው እውነት" የሚለው ስድስተኛው መጽሐፌ በገበያ ላይ ውሏል። "የተደበቀው እውነት" የሚያውጠነጥነው ስለ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" መምጣት በተውራት እና በኢንጂል ተነግሮ የመጽሐፉ ሰዎች ይህንን እውነት እንዴት እንደደበቁት የሚገልጥ እና የሚያጋልጥ ነው። ዝርዝሩን መጽሐፉ ላይ ያንብቡ እና ለሎች የሂዳያህ ሠበብ እንዲሆን አስነብቡ! መጽሐፉን መርካርቶ አንዋር መሥጂድ ኢሥላማዊ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ያገኙታል፥ የበለጠ ለመረጃ +251920781016 ዐብዱ ብለው ይደውሉ! መጽሐፉ ተደራሽነት እንዲኖረው ባለው የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ሼር በማድረግ ሠበቡል ሂዳያህ ይሁኑ! ወጀዛኩሙላህ ኸይራ! ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
Show all...
እሷ ያን ሁሉ መስመር ጽፋልህ አንተ "እሺ" ብቻ ብለህ የምትመልስ ከሆነ ቀጥሎ የሚመጣዉን ጦርነት ጠብቅ። ምን እንደሚያናድደኝ ታውቃላችሁ ? ብዙዎቻችሁ ከሴት ልጅ ጋር እንዴት መኖር እንዳለባችሁ አታውቁም ። ትን ይበልህ አቦ https://t.me/MuhammedSeidAbx
Show all...
ABX

ወደ ቤታችሁ እንኳን መጣችሁ!!

ሁሉም ቢሞላለት ደስ ይለዋል፣ ሁሉም ሀብታም መሆን ይፈልጋል፣ ሁሉም መዝናናት ይፈልጋል፤ ሁሉም ገንዘብ ማግኘት ይፈልጋል፣ ሁሉም ጥሩ ኑሮ መኖር ይፈልጋል፣ ሁሉም ሰኞ በደስታ ማሳለፍ ይፈልጋል፡፡ ይህ ሀሳብ ያንተ ብቻ አይደለም፡፡  ስለዚህ ብቻህን አይደለህም አትፍራ ለማለት ነው እሺ፡፡ መልካም ዉሎ ሶባሐል ኸይር! https://t.me/MuhammedSeidAbx
Show all...
እንደ ቅሬታ ማቅረብ Complain ማብዛት ዝምድናን የሚበጥስ፣ ጓደኝነትን የሚሸረሽር፣ ወዳጅነትን የሚያደበዝዝ ... ነገር ይኖር ይሆን! በተለይ ሰው ከኑሮው እና ከሐጃው እየታገለ፣ ሕይወት ነፍስ ዉጪ ነፍስ ግቢ በሆነችበት በዚህ የትንቅንቅ ዘመን፡፡  አልደወልክልኝም፣ አልጠየቅከኝም፣ ምን ደረስክ አላለልከኝም …  እያሉ ነገር ማጋነን። ዛሬ ላይ ሰው ብዙ ነገር ጭንቅላቱን ይዞታል፡፡  ዛሬዉኑ ወደፊቱ፣ ኢማኑ፣ ሥራው፣ ኑሮው፣ ቤተሰቡ፣ ልጆቹ፣ አኺራው … ዛሬ ላይ ሰዎች የራሣቸው ችግርና አጀንዳ ራሱ በቂ ነው፡፡ ተጨማሪ ሀሳብና ሸክም አትሁኑባቸው፡፡ ወቀሳ አታብዙባቸው፣ ጥፋት አትቁጠሩባቸው፣ ምክንያት ፈልጉላቸው፣ ከሀሳብና ጭንቀት ነፃ ሆነው ይኖሩ ዘንድ ምክንያት ሁኗቸው፡፡ ሶባሐል ኸይር! https://t.me/MuhammedSeidAbx
Show all...
መልካም ስራህ ብቻውን በቂ አይደለም… ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لَا يُدْخِلُ أَحَدًا مِنْكُمْ عَمَلُهُ الْجَنَّةَ، وَلَا يُجِيرُهُ مِنَ النَّارِ، وَلَا أَنَا، إِلَّا بِرَحْمَةٍ مِنَ اللَّهِ﴾ “ከናንተ አንዳችሁ በመልካም ስራው ብቻ ጀነት አይገባም፤ ከእሳትም አይጠበቅም። እኔም ብሆን። በአላህ ራህመት (እዝነት) ቢሆን እንጂ።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል 2817
Show all...