cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat

"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ " በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን መዝሙሮች ከነግጥሞቻቸው እና ስብከቶች ይሰጡበታል፡፡ For more contact @eorthomazmur_Bot 👇👇👇👇 For Discussion👇👇👇👇 https://t.me/joinchat/Fe77ilHyDcn-td_xDU8Tkg

Show more
Advertising posts
3 013
Subscribers
No data24 hours
-87 days
-4030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ለመቀላቀል #ከታች #ሠማያዊውን #ይጫኑ             #JOIN #OUR #CHANNEL   👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇   👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏   👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏   👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏   ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
Show all...
#ለመቀላቀል #ከታች #ሠማያዊውን #ይጫኑ             #JOIN #OUR #CHANNEL   👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇   👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏   👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏   👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏   ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
Show all...
#ለመቀላቀል #ከታች #ሠማያዊውን #ይጫኑ             #JOIN #OUR #CHANNEL   👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇   👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏   👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏   👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏   ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
Show all...
ቅዱስ ገብርኤል 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ  አምላክ አሜን!! ✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ ገብርኤል (ቅዱስ ገብርኤል)  ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካልና፡፡ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል ጌታና አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱሳን ሰማእታት ገድላቸውን እንዲፈጽሙ እሳቱንና ስለቱን ተሳቀው ወደ ኋላ እንዳይመለሱ ይረዳቸዋል፡፡ ከግብሩ በመነሳትም የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ለቅዱስ ገብርኤል ሌሎች የተፀውኦ ስሞችን ሰተውታል፡፡ ከነዚህም መካከል ጥቂቶቹ:- 1ኛ - ብስራታዊው (አብሳሪው) መልአክ - እመቤታችንንና ዘመዷ ኤልሳቤትን አብስሮአልና፡፡ 2ኛ - የአርባብ አለቃ - 3ቱ አለመ መላእክት እየተባሉ የሚጠሩት ኢዮር ራማ ኤረር የየራሳቸው ክፍል ሲኖራቸው በራማ ካሉት 3 ክፍሎች (የመላእክት ከተሞች) አንዱ አርባብ እየተባለ የሚጠራው ሲሆን የዛ አለቃ ደግሞ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ 3ኛ - ጽኑው መልአክ - "ንቁም በበኅላዌነ እስከ ንረከቦ ለአምላክነ" በመጀመሪያው የመላእክት ጦርነት ጊዜ አምላካችንን እስክናውቅ ባለንበት ጸንተን እንቁም በማለት መላእክትን አጽንቶአቸዋልና፡፡ 4ኛ - ተራዳዩ መልአክ - ዳን 3÷19-27፣ ዳን 8÷15 ፣ ዳን 9÷21 – 27 5ኛ - ሊቀ መላእክ - ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ነውና ሐምሌ 19   ቅዱስ እየሉጣንና ልጇ ህፃኑ ቅዱስ ቂርቆስን ያዳነበት እለት ነው፡፡ ገድሉ የተፈፀመው በዘመነ ሰማዕተት ነው፡፡ በወቅቱ ቂርቆስና ኢየሉጣ የሚባሉ እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩ ቅዱሳን ነበሩ፡፡ ቅዱስ ቂርቆስ ሀገሩ ሮም አንጌቤን ነው አባቱ ቆዝምሶ ይባላል እናቱ ኢየሉጣ በትውልዷ ከአዝማደ ነገስት ነች፡፡      ዲዩቅልጥያኖስ በነገሰ በ20ኛው ዓመት በክርስቲኖች ላይ ‹‹ቤተክርስቲኖችና ቅዱሳት መጻህፍቶቻቸው ይቃጠሉ፣ ክርስቲያኖችም ይገደሉ!›› የሚል አዋጅ አውጥቶ ነበርና በመፍራት እናት ስለልጇ ስትል ወደ ኢቆንዩን ሸሸች፡፡ መስፍኑ ብሔሩ እለእስክንድሮስ ክርስቶስን ካጂ ለጣኦት ስገጂ አላት፡፡ እርሷ ግን አይን እያለው የማያይ ጆሮ እያለው ለማይሰማ አንተ ለቆምከው ምስል አልሰግድም አለች፡፡ ንጉሱም በሰይፍ ትቀጫለሽ ብሎ ቢያስፈራራት ሀሳቧን ልትለውጥ አልቻለችም፡፡ ህፃኑም ቢጠየቅ እንደ እናቱ መለሰላቸው፡፡ እሺ አለማለታቸውን ንጉስ ሲረዳ ለወታደሮቹ በብረት ጋን ውሃ አፍሉ ብሎ አዘዛቸው፡፡ የውሃው ፍላት እንደ ክረምት ነገድጓድ እስኪነድ ድረስ 42 ምዕራፍ ያህል ይሰማ ነበር፡፡ ወደውሃው ሊከቷቸው ባሉ ጊዜ ቅ.ኢየሉጣ ፈራች ነገር ግን አጠገቧ ያለው ህፃን ‹‹ቂርቆስ እናቴ አትፍሪ ዳግመኛ ሞት አንሞትም›› አላት አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ እኛንም ያድነናል ብሎ አፀናት፡፡ ከዚህ በኋላ በፍፁም ልብ ተያይዘው ከእሳቱ (ውሃ)ገብተዋል፡፡ በዚህ ጊዜ አናንያ አዛሪያ ሚሳኤልን የተራዳ ታላቁና ገናናው መልአክ ቅ/ገብርኤል በመካከላቸው ተገኝቶ የፈላውን ውሃ አቀዝቅዞላቸዋል፡፡ ከውሃ በወጡም ጊዜ ልብሳቸውና ሰውነታቸው አንዳች ሳይሆን ምዕመናን አዩ፡፡ እነርሱ በሚያመልኩት አምላክም አምነው ብዞዎቹ በሰማዕትነት አርፈዋል፡፡ ‹‹ቂርቆስ እየሉጣ ያወጣ ከሳት (2×)›› ‹‹እኛንም አድነን (2) ገብርኤል ሊቀ መላእክት›› ከእናታችን ከቅድስት ኢየሉጣና ከሰማዕቱ ቂርቆስ ከታደጋቸው ከቅዱስ ገብርኤል ረድኤት ፍቅር ያሳድርብን፡፡ አሜን 🙏🙏🙏🙏🙏 እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
Show all...
Repost from ETHIO-MEREJA®
ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተመደቡ!! ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሊቀ ጳጳስ የምዕራብ አርሲ (ሻሸመኔ) ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲያገለግሉ በቅዱስ ሲኖዶስ መዘዋወራቸው ተገለጸ። ብፁዕነታቸው የምዕራብ ሸዋ ፣ የሆሮ ጉዱሩ እና ምሥራቅ ወለጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ላለፉት ዓመታት ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወሳል። የዝውውሩ ምክንያት ቀደም ሲል በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አዳዲስ የሚሾሙት ኤጲስ ቆጶሳት የሚመደቡበት ሀገረ ስብከት ለውጥ የተደረገበት መሆኑን ተከትሎ ነው። የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ርዕሰ ከተማ ሻሸመኔ ከዚህ ቀደም በሕገወጦቹ አካላት በተደረገ ሢመት ቁጥራቸው ከ70 በላይ የሚሆኑ ምዕመናን ሰማዕትነት መቀበላቸው እና ከ450 በላይ የሚሆኑት ምዕመናን ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ይታወሳል። Via፣ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል      -ETHIO-MEREJA-     T.me/ethio_mereja
Show all...