ከ2019 በጀት ዓመት ጀምሮ የሚተገበሩ 11 የጭብጥ ተኮር ምርምር ፕሮፖዛሎች ግምገማ ተካሄደ
ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም
በወልድያ ዩኒቨርሲቲየምርምር፣ ህትመት፣ ሥነ-ምግባርና ሥርዓት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ከነሐሴ 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት በዩኒቨርሲቲው መምህራንና ተመራማሪዎች የተዘጋጁ ጭብጥ ተኮር የምርምር ትልመ-ጥናቶችን (ፕሮፖዛሎችን) ለመገምገም የተዘጋጀው ወርክሾፕ ተካሂዷል።
የከፍተኛ ትምህርትተቋማት ከሚያከናውኗቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል አንዱ ከአካባቢው ችግሮች በመነሳት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን የሚጠቁሙ እና የማህበረሰቡን ኑሮ ሊያሻሽሉ የሚችሉ ምርምሮችን ማካሄድ እንደሆነ የአካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ማርዬ በለጠ ገልጸዋል።
ምርምር ሌሎችንምየዩኒቨርሲቲውን ተልዕኮዎች ለማሳካት ያለው ሚና የጎላ በመሆኑ ከፍተኛ በጀት ተመድቦለት እየተሰራ እንደሚገኝ የጠቀሱት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ ተቋሙ የብዙ ወጣት ምሁራን ስብስብ በመሆኑ የጭብጥ ተኮር ምርምር ሥራ የትብብርና የቡድን ሥራን የሚያጠናክር ነው ብለዋል።
የምርምር፣ ህትመት፣ሥነ-ምግባርና ሥርዓት ዳይሬክተር ዶ/ር እንዳልካቸው ፍቃዱ በበኩላቸው፤ የወርክሾፑ ዋና ዓላማ በዩኒቨርሲቲው የሚተገበሩ ምርምሮች ማህበረሰብ አቀፍ ፋይዳ ያላቸውና አሁናዊ ችግሮችን የሚፈቱ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንዲሁም የጥናቶቹን ማስፈጸሚያ ስልቶች ጥንካሬና ሳይንሳዊ ይዘት መገምገም መሆኑን ተናግረዋል። አክለውም የዝግጅቱ ሌላው ዓላማ የተመራማሪዎችን አቅም በማሳደግ ለሀገራዊ የምርምር አጀንዳዎች ያላቸውን ተሳትፎ ማጎልበትና የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች በምርምር አተገባበር ላይ ንቁ አስተዋጽኦ እንዲኖራቸው ማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል።
በግምገማ ሂደቱ11 የጭብጥ ተኮር ምርምር ፕሮፖዛሎች የቀረቡ ሲሆን፤ ሂደቱም በ12 የውስጥ እና በ24 የውጭ ገምጋሚዎች (ከአዲስ አበባ፣ ከጎንደር፣ ከወሎ፣ ከደብረ ታቦር፣ ከባህር ዳር እንዲሁም ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በተውጣጡ ልምድ ባላቸው ምሁራን) አማካኝነት በበይነ-መረብ (Online) ተካሂዷል።
በዚህም ሰፊ ልምድና ጠቃሚ ሙያዊ አስተያየቶች የተንጸባረቁበት እንደነበር ተመልክቷል።
በልዩ ልዩ የትምህርት ዘርፎች የቀረቡት እነዚህ ትልመ-ጥናቶች በባለሙያዎች ከተገመገሙ በኋላ የተሰጡ ጠቃሚ ግብዓቶችንና ገንቢ አስተያየቶችን በማካተት በቀጣይ ወደ ዋናው የጥናት ትግበራ ምዕራፍ እንደሚሸጋገሩ ይጠበቃል።
-------------------------------------------------
Evaluation of 11 Thematic Research Proposals to be Implemented Starting from the 2019 Fiscal Year Conducted August
28,2026
Organized by the Directorate of Research, Publication, Ethics, and Standards at Woldia University, a four-day evaluation workshop washeld starting August 24, 2026, to review thematic research proposals authored by university academic staff and researchers.
Dr. Marye Belete, Vice President for Academic, Research, Technology Transfer, and Community Service, stated that one of the core functions of higher education institutions is to conduct research that addresses local challenges, provides solutions, and improves community livelihoods.
Highlighting that research plays a pivotal role in achieving the university's overall mission, the Vice President noted that substantial funding has been allocated to support these endeavors.
He added that as the institution brings together many young scholars, thematic research serves to foster collaboration and team work.
Dr. Endalkachew Fekadu, Director of Research, Publication, Ethics, and Standards, explained that the workshop primarily aimed to ensure that research projects implemented at the university deliver tangible community impact and solve real-world problems.
It also served to evaluate the methodology, scientific rigor, and feasibility of the proposals.
Furthermore, Dr. Endalkachew emphasized that building research capacity, bolstering contributions to national research agendas, and involving postgraduate students in practical research implementation are key objectives of the initiative.
During the evaluation, 11 thematic research proposals were reviewed. The process was conducted online by 12 internal and 24 external reviewers—seasoned scholars drawn from Addis Ababa, Gondar, Wollo, Debre Tabor, Bahir Dar, and Adama Science and Technology Universities.
The directorate noted that the sessions were highly enriching and filled with valuable scholarly discourse.
Following expert review, the project leads will incorporate the constructive feedback and insights provided, after which the research proposals will advance to full implementation.
ዘገባውየወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለም ዓቀፍ ግንኙነት ነው፡፡
----------------------------------------------------------
‹‹አእምሮ ሲከፈት፤ ዓይኖች ማየት ይችላሉ!›› ‹‹ Open Mind, Open Eyes!››
For latest updates, please follow the university official pages:
Web site:
https://www.wldu.edu.et/
Facebook =
https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel =
https://t.me/Woldia_University
Linkedin =
https://t.me/Woldia_Unive
rsity/2985YouTube:
https://www.youtube.com/@woldiauniversityofficial
Tiktok=