en
Feedback
የፍቅር ታሪክ (seenaa jalaala)

የፍቅር ታሪክ (seenaa jalaala)

Open in Telegram

ማስተዋል(mastewal) Fikirr @AASH23

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
2 842
Subscribers
+224 hours
No data7 days
+230 days
Posts Archive
ጠፋ የሚለየን 👇👇👇👇👇 For fata 🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹 አየ ጊዜ ስንቱን አየን እኔና አንቺን ጠፋ የሚለየን አኩርፈሽኝ አኩርፌያለሁ ግን ሳይሽ ደሞ ረሳዋለሁ 🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼 በቃ ከእንግዲህ አታኋት ስል ቆይቼ ለስንቱ ገላጋይ የሌለውን አውርቼ በጣም የራኩ ይመስል ከቤቴ ጠፍቼ ኡ..ዎ.. ና ና ና ና ናፍቆትሽ ገና ከጅምሩ ሲገርፈኝ እያሮጠ ካንቺ ደጃፍ ሲመልሰኝ ያስገባኛል ልብሽ ምንም ሳይል እያቀፈኝ 🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼 በልብሽ በልቤ ያለው ፍቅር ፅናቱ ስንት ዘመን የሚያሻግር ሳናቀው ስንገኝ አጥፍተን መለሰን ወደቤት ፍቅራችን እኔ ካንቺ አንቺ ደሞ ከኔ ሌላ ማን አለን እስኪ ሚሆነን ከለላ ምን ቢሄድ ምን ቢመጣ አውቀዋለሁ አንቺን ብቻ ነው እኔማ ምወደው 🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼 አንቺን ነው አንቺን ነውው.... እኔማ ምወደው አንቺን ነው አንቺን ነውው.... እኔማ ምወደው አንቺን ነው አንቺን ነውው.... እኔማ ምወደው አንቺን ነው አንቺን ብቻ ነው እኔማ ምወደው 🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼 ፍቅርን አየሁ በኛ ላይ እያጀበን ሲያኖረን ሳይ ስንት ያሉለት የኛ ነገር መጨረሻው ሁሌም ሲያምር 🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼 እኔም ሮጬ አንቺም ወደኔ መተሻል ሁለታችንም እርስ በእርስ ተያይተናል ያያ ላፍታ ያለፈውስ ትዝ ይለናል ኡ...ዎ... ና ና ና ና ቃልም የለ ካንደበቴ ካንደበትሽ ፈዘን ቀርተናል እያየሽኝ እያየሁሽ አንድ ሆኗል ይቅርታዬ ለይቅርታ... 🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼 በልብሽ በልቤ ያለው ፍቅር ፅናቱ ስንት ዘመን የሚያሻግር ሳናቀው ስንገኝ አጥፍተን መለሰን ወደቤት ፍቅራችን እኔ ካንቺ አንቺ ደሞ ከኔ ሌላ ማን አለን እስኪ ሚሆነን ከለላ ምን ቢሄድ ምን ቢመጣ አውቀዋለሁ አንቺን ብቻ ነው እኔማ ምወደው 🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼 አንቺን ነው አንቺን ነውው.... እኔማ ምወደው አንቺን ነው አንቺን ነውው.... እኔማ ምወደው አንቺን ነው አንቺን ነውው.... እኔማ ምወደው አንቺን ነው እመቤቴን ነው እኔማ ምወደው ናናናና ናና ናና 🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼 በፅናት ልጠብቅ ከእንግዲህስ አወኩት በፍቅርሽ ነው ለካ እስከዛሬ የዳንኩት 🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼 አንቺን ነው አንቺን ነውው.... እኔማ ምወደው አንቺን ነው አንቺን ነውው.... እኔማ ምወደው አንቺን ነው አንቺን ነውው.... እኔማ ምወደው አንቺን ነው እመቤቴን ነው እኔማ ምወደው ናናና ና ናና ናና ... @libmalet @libmalet

. . . ሂድልኝ . . . ሂድልኝ ማለቴ እውነት አልነበረም አትምጣብኝ ሥልክ ፍፁም ሀቅ አደለም አፌ ብቻ ነበር ልቤ አልተባበረም እደምትሄድ ሲያቅ ልቤ ከመሥማቱ አልነበረም ሄዷል ከማደሪያው ቤቱ ተከትሎ ወቷል እግርህ ከመውጣቱ እደወጣ ቀርቷል እንጃ መመለሡን ሠውነቱን ከርቷል ቀጥሏል መሮጡን አንተ እኮ እደሄድክ ሂወቴ እንኲ ቆሞል አቀጥልም በቃ እዳልነበር ሆኗል ብርሀን የለኝም ጨለማን ተላብሣል አያይም ደብዝዟል አይኔ ብሌን አቷል አንተ የሄድክ ቀን ማንነቴ ጠፍቷል ውበቴ ደብዝዟል ሠላሜ ደፍርሷል ውሃ እዳጥ አበባ እኔነቴ ረግፏል የኔ ማንነቴ የህልሜ ጒደኛ የኑሮዬ ሚሥጥር የልቤ ላይ ዳኛ ሂድልኝ ማለቴ እውነት እልነበረም ያለአንተ እኮ አለሜ በፍፁም አይደምቅም እናም የኔ ፍቅር ሂወቴን አድማቂ የውበቴ ፍካት የኔ ተናፋቂ የአፌን ወለምታ ሂድ ማለቴን ረሥተህ ልቤን ብቻ ሠምተህ ናልኝ ተመልሠህ፡፡ @libmalet @libmalet

. . . ትዝታሽ . . . እንዴት ልግለፅልሽ ሀሳቤን በዝርዝር? እሩቅ ስለሆነ ያለሽበት ሀገር ትዝታሽ ብቻ ነው ሁሌም ሚጠይቀኝ አንዴ ልይሽና የያዘ ይልቀቀኝ ሲመሽም ሲነጋ አንቺው ነሽ ናፍቆቴ ከደጅሽ ካልመጣው ካልደረሽ ከቤቴ ዘንድሮን እንጃ ክረምቱም በረታ መዝለቁ ተሳነኝ በቁሜ መኝታ እንዴት ነህ ለሚሉኝ እለሁኝ በትዝታ ካንቺ ጋ ደርሼ በሀሳብ ጨዋታ መድረሻም የለው ይገሰግሳል ልቤ መምጣቴ አይቀርም ከደጅሽ ጋልቤ፡፡ @libmalet @libmalet

ልንገርህ ወንድሜ የኔ የምትላትን ሴት / # ሚስት/ ማግኘት የምትፈልግ ከሆነ ከዚችም ከዚያችም መተዋወቅና ስልክ መለዋወጥ አቁም እናም ለራስህ ጊዜ ስጠው… የምታገኛቸው ሴቶች ሁሉ ሚስት አይሆኑህም ምክንያቱም አንተም ለምታገኛቸው ሴቶች ሁሉ ባል መሆን አትችልማ። ፍቅር ለገበያ አይቀርብም ላንተ ያላትን መቼም ከግርግር መሃል ማግኘት አትችልም ምክንያቱም አስር ያባረረ አንድ አይዝም! በቃ ዳር ሆነህ ጠብቃት ላንተ ያላት ብትዘገይ እንጂ ፈፅሞ አትቀርምና። ግን ልብ በል መልካም ሴት በእድል እምጂ በትግል አትገኝም ስልህ የምታያቸውን ሁሉ ለማግኘት አትሞክር እንጂ ሁሉንም ላለማየት አይንህን ጨፍን እያልኩ እንዳልሆነ ተረዳኝ። ላመንክባትና የኔ ናት ብለህ ላሰብካት ሔዋንህ ግን እስከመጨረሻው ታገልላት። ከሁሉም ግን መልካም ሚስት ስትፈልግ መልካም ባል ሆነ ተገኝላት በቃ። ከተስማማችሁበት በ 👍 አሳዮኛ @libmalet @libmalet

👉ጥቂት መረጃ ስለ ሴቶች 1⃣ አንዳንድ ሴቶች አስመሳይ ናቸው በዚህ ግራ አይግባህ ተጠንቀቅ 2⃣ ሴቶች አብዛኛውን ጊዜ ቁመና ባላቸው ወንዶች ይሳባሉ ምንም ቆንጆ ባይሆንም 3⃣ ሴቶች ሲደነቁ ይወዳሉ እናም የሚያምረውን ክፍሉአን አድንቅላት 4⃣ ሰቶች ንዴታቸውን በስርት ከገልፁልህ ይወዱሃል 5⃣ ሴቶች የሚወዱት ወንድ ሳያያቸው ያዩታል 6⃣ ሴቶች ጥፍት የሚሉት ወንዶች የሆነ ነገር ከሴቶች ሲፈልጉ ነው 7⃣ ሴቶች የሚወዱትን ወንድ ማታ ሁሌ ከመተኛታቸው በፊት ያስቡታል ምንም አንኩዋ ከሌላ ወንድ ጋር ቢዉሉም 8⃣ ሴቶች በወንድ ልጅ በቀላሉ በፍቅር ይያዛሉ 9⃣ ሴቶች የሚወዱት ወንድ ከሌላ ሴት ሲሆን ያብሰልስላቸዋል 1⃣0⃣ ሴቶች የሚወዱት ወንድ በአጠገባቸው ሲያልፍ ይደሰታሉ 1⃣1⃣ ሴቶች ሌላ ሰው ለመምሰል የሚሞክር ወንድን ይጠላሉ 1⃣2⃣ ሴት አንደወደድካት ታውቅባሃነች ነገር ግን ካልነገርካት አርግጠኛ አትሆንም 1⃣3⃣ ሴቶች የሚወዱት ወንድ ሲቀልድ ባያስቅም ምን አልባት ውሃ ፈላ ቢላት ት ስቃለች 1⃣4⃣ ሴት ፍቅረኛህ ከወንድ ጉዋደኛህ ፍቅር አንዳይዛት ትጠነቀቃለች 1⃣5⃣ ሴት ስለ ውንድ ትጉአጉአለች ለምን በትል ወንዶች ለሴቶች አስፈላጊ ናቸው 1⃣6⃣ ስለሷ ማወቅ ከፈለክ ጓደኛዋን ጠይቃት እሷ እራሱዋ የማታቀውን ሁላ ትነግርሃለች አረ ላይክ እያነሰ ነው 👍 በማረግ ያበረታቱን @libmalet @libmalet

ፍቅር ማለት ? ፍቅር ማለት ዉበትን ፍለጋ አይደለም፣ ፍቅር ማለት ጥቅምን ፍለጋ አይደለም፣ ፍቅር ማለት ዝሙትን ፍለጋ አይደለም፣ ፍቅር ማለት በደስታ ጊዜ መተቃቀፍ አይደለም፣ ፍቅር ማለት ስለተወደዳችሁ መዉደድ አይደለም፣ # ፍቅር ማለት ከማንነት የፀዳ # ፍቅር ከማዳላት የራቀ # ፍቅር ከመፍረድ እጁን ያወጣ በመከራም በሀዘንም በደስታም መተሳሰብ መረዳዳት እናንተ ያላገኛችሁትን ነገር ለሌሎች መመኘት ፤ጠላትህን መዉደድ ፣ በናንተ እንዲፈፀም የማትፈልጉትን በሌላ ሠዉ አለመፈፀም፣ ነገ ተመልሶ በራሳችን መፈፀም አይቀርምና፣ # ፍቅር ማለት ይኸ ነዉ ለመስዋት የማይሠሥት ፍቅር መስዋትን ድል የሚያደርግ ፍቅር ይኑር በቤታችሁ ! @libmalet @libmalet

"ድሀ ማለት ሀብት ንብረት ገንዘብ የሌለው ማለት አይደለም! ድሀ ማለት . . . ተስፋ የሌለው! ፣ህልም የሌለው! ፣አላማ የሌለው! ፣ራእይ የሌለው! ፣እምነት የሌለው! ፣ሰብአዊነትን ያጣ! ፍቅር የማይገባው! ነው፡፡ እንደሰው አስብ. . . ጤናማ ጭንቅላት! ብሩህ ተስፋ! ጠንካራ እምነት! መልካም ስብእና! ትልቅ አላማ!ንፁህ ልብ! እውነተኛ ፍቅር! ካለህ አንተ የዘለአለም ሀብታም ነህ፡፡" @libmalet @libmalet

•••!ያማል!••• . እና እንደ ነገርኩሽ የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ የነብሰጡርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ ከተስፋ ጉልላት ተገፍቶ እንደመውደቅ ታምር በበዛበት በዚች ቧልተኛ አለም ከዚህ የበለጠ ምንም ህመም የለም አውቶብሱ ያማል ሚኒባሱ ያማል ላዳ ታክሲው ያማል የማይጎል የሰው ጎርፍ ደራሽ ማዕበሉ የዕንባ ቅጥልጥሉ ምንብዬ ልንገርሽ ? ያማል ይሄ ሁሉ እና እንደ ነገርኩሽ የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ የሚያፈቅሩትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ ነገር ተበላሸ ህመም ተወለደ ጨጓራ በገነ እሳት በዕንፋሎት መልክ በእህታ ተነነ የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ ሁሉም ተቀይሮ ተተካ በሲቃ ምንብዬ ልንገርሽ? ይሄም ያማል በቃ ወጪ ተራማጁ አስመሳይ ሰጋጁ ፀሀዩ ዝናቡ የለምን ምክንያት የለምን ሰበቡ ተቆራጭ አበባ ሊቆረጥ ማበቡ ውል የለሽ ደመና ተራራ መክበቡ እልፍ አዕላፍ ኮከብ ጨረቃን ማጀቡ ደሞ ለሷ ግጥም እናቷን ጨረቃ ምንብዬ ልንገርሽ ይህም ያማል በቃ እና እንደ ነገርኩሽ ጉንጭ የማትሞላ ኬክ አስር ብር የሸጠ የካፌ አሳላፊ ወደኔ አፈጠጠ ዘይት የነካውን መንታ እጁን አጣምሮ ምን ልታዘዝ ይላል ቁልቁል አቀርቅሮ ምን ልታዘዝ ይላል…?? እንዴት ቅጥሉ ሰው ቅጥሉን ሰው ያዛል ማኪያቶ ልዘዝ? ካፑችኖ ልዘዝ? ጥቁር ቡና ልዘዝ? ለምን ሰው አላዝም? መታዘዝ መናዘዝ እርግማን የሆነው ካፌውን ሊያሳልፍ እራሱ ግን የሚያልፍ ቁልቁል አቀርቅሮ ሞቱን ባንገት ቀብሮ ምን ልታዘዝ? ይላል አንድ ማኪያቶ ካንድ እሷ ጋር ልዘዝ? አንድ ካፑችኖ ካንድ እሷ ጋር ልበል? ከጥቁር ቡና ጋር እሷን አምጣልበል? ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል የላስቲክ አበባ ያርቲ ቡርቲ ስዕል የ`ጭቃ እሾህ ወግቶት እዥ ያወጣ ቁስል ትልቁ ነቀዝ ሰው የማንቀዙን ያህል ብዙ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል እና እንደ ነገርኩሽ ላንቺ የያዝኩት አበባ መጠውለግ አመጣ ፀሀይ ገባ ወጣ ዝናብ ቀረ መጣ ጨረቃም የለችም እናቷን ስላልኳት ደግሜ ሰድቤ ሺህ አመት እንዳይገርማት እ. . . .ና. . . .ቷን ! እናቷን ጨረቃ ተይ አታስለፍልፊኝ ይህም ያማል በቃ ግን አንቺን ስወድሽ ይህን ሁሉ ችዬ - ነው ም'ጠብቅሽ ቢሆንም ግን ያማል !!!! @libmalet @libmalet

💋💋💋💋💋 ሚስት-: የኔ ቆንጆ የቤታችን በር ተሠብሯል እስኪ ስራዉ ባል-: ስታዪኝ አናፂ መስላለዉ? በማለት ወደ ስራ ይ ሔድና ማታ ተመልሶ ሢመጣ ተሠርቶ ያገኘዋል ባል-: ማነዉ በሩን የሠራዉ? ሚስት-: ጎረቤታችን ባል-: ለሠራበት ምን ሠጠሽዉ? ሚስት-: አንሦላ እንጋፈፍ ወይም ዳቦ ጋግረሽ ስጪኝ አለኝ ባል-: እና ዳቦ ጋግረሽ ሠጠሽዉ ማር? .... ሚስት-: ስታየኝ ዳቦ ጋጋሪ መስላለዉ !!! ብቻችሁን አትሳቁ ሼር አርጉ እንጂ 😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂 @libmalet @libmalet

ልቤ ልቤ ነበር ዛፍ ባ‘ለት የሰደደ በንፋስ በጎርፉ ጭራሽ ያልተናደ። : ውሀ ማያጠፋው ልቤ ነበር እሣት ካመድ ሚቀላቅል ስንቱን ባለብርታት። : ልቤ ነበር ወንዝ የማይጥሰው አዞ ዐለም የማይበቃው ተጉዞ ተጉዞ። : አንበሳ ማይደፍረው ልቤ ነበር ደን ጥልፍልፉ ብዙ የማይመች ለአደን። : ማህበል የሚያስነሳ ልቤ ነበር ሞገድ ካምላክ ትዛዝ በቀር በሌላ የማይበርድ። : ልቤ ነበር ሰማይ የጠራ የኮራ ሲያስገመግም ግርማው እጅጉን ሚያስፈራ። : ዛሬ ግን ግን ዛሬ ሁሉ ሲቀር ቀርቶ በፍቅር አንካሴ መሀል ላይ ተወግቶ ልቤ ደም ፈሰሰው ደንዳና እንዳልነበረ ፍቅር ገብቶ አረሰው። ዛሬ ግን ልቤ ተሸነፈ ወኔው ተነቀለ ብርታቱ እረገፈ። : አሳዘነኝ ልቤ ያኔ እንዳልተኩራራ እሣት ነኝ እያለ እንዳልደባለቀ ... ...ስንቱን ካ‘መድ ጋራ ደን ነኝ እያለ ብዙ እንዳልተወሳ ሞገድ ነኝም ብሎ ፈጥኖ እንዳልተነሳ ዛፍ ነኝ እንዳላለ ባለት የሰደደ ወንዝ ነኝ እያለ ግድብ እንዳልናደ ሰማይ ነኝም ብሎ ዶፉን አከታትሎ... ...እንዳላወረደ ዛሬ ተቀልብሶ በፍቅር እርሶ ዐለቱም ፈራርሶ ማንነቱን አጣ በናፍቆት ተቀጣ። : : አይ ልቤ አይ ልቤ : : ትናንት እንዳልኖረ ዘራፍ ብሎ እንዳሻው : : : ፍቅር ማርኮ ጣለው በስተመጨረሻው። @libmalet @libmalet

🍁🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ፍቅር በተላላቆች እይታ 🌿❣"ፍቅር ያለ እምነት ነፋስ ላይ እንደተቀመጠ ሻማ ነው!" (ቶማስ ሚድልተን) 🌿❣ "በፍቅር ለሚወድቁ ሰዎች የመሬት ስበት በፍፁም ተጠያቂ አይደለም!" (አልበርት እንስታየን 🌿❣"ፍቅር በተፈጥሮ የሚታደሉት ሲሆን ፣ የተሳካ የሚሆነው በቅንነት ጠበቅ አርገው ሲገፉበት ነው (አሪስቶትል) 🌿❣" ፍቅር በእልህ ፣ በችኮላ ፣ በንትርክና በግዴታ የሚያሸንፉት ቀላል ስሜት አይደለም !!!" (አጋታ ክርስቲ) 🌿❣"በፍቅር ውስጥ ያለው ድል ማሸነፍ ነው!!" (ናፖዎሊዩን ቦናፓርት) 🌿❣"ፍቅር የቡድን ስራ አይደለም!!!"(አሰፉ ጉያ) 🌿❣"ፍቅርን ፍቅር የሚያሰኛት አብረው ያሳለፉት ረዥም ጊዜ አይደለም ፣ ፍቅር የምንላት የአንድ ደቂቃ ጉዳይ ቢሆንም ጣዕሟ ለዘላለም የማይረሳ ከሆነ ፣ እስዋን ነው ፍቅር የምንላት !!!!!" (ደራሲ በዓሉ ግርማ) 🌿❣"ፍቅር ገንዘብ ማስቀመጫ ኪስ የሌለው ራቁቱን የሆነ ልጅ ነው!! "(አቪድ) 🌿❣"ፍቅር ጥልቅ ቦታ እንጂ በከንፈር ውስጥ ብቻ ሊኖር አይችልም!!!" (ቴኔሰን) 🌿❣"ፍቅር ውሻ እንኳን በግጥም እንዲጮኽ የሚያረግ ኃይል አለው!!" (ፍራንሲስ ቦም) @libmalet @libmalet

«ልብ ብለው ያንብቡ» ውበትሽን አይቶ የተመኘሽ እና ከውበትሽ ጀርባ ያለውን ማንነትሽን አውቆ ያፈቀረሽ ሰው የተለያዩ ናቸው። ለምን ነገርከኝ እንዳትይ? እኛ ወንዶች የፈለግነውን እስክናገኝ ሴትን ንግስት ማድረግ እናውቅበታለን። ያፈቀረ ግን ተብታባ ነው፤ ውበትሽን ለመግለፅ እንኴን አንደበት የለውም፤ ነገር ግን በውስጣዊ ማንነትሽ እሱነቱን አጥቶ ሌት ተቀን አንቺን በምናቡ ሲያወጣና ሲያወርድ፣ የአንቺን ህይወት ለማድመቅ የራሱን ሲያፈዝ፣ ከሰው በላይ የነበረው መቀመቅ ሲወርድ........ያኔ ላንቺ ያንስብሻል። እናም ፍቅርሽን ገላሽን ለተመኘው ትሰጪና ደግመሽ ብትፈጠሪ እንኴን የማታገኝውን ንፁህ አፍቃሪሽን ልብ አንኮታኩተሽ ትሰብሪዋለሽ። እሱም ለዘለዓም ልቡ ታሞበት እንደማቀቀ ፍቅሩን ተቀምቶ አዝኖ አፈር ይሆናል። አንቺ ሳታውቂ ራስሽን የሰጠሽው ግን አውቆ ይተውሻል። በቃላት ድርደራ በስጦታ ጋጋታ ንግስት ያስመሰለሽ.......ያሻውን ፈጽሞ ሲያበቃ ከጥፍሩ ቆሻሻ እንኴን አይቆጥርሽም። ለዚ ነው የተመኘሽ እና ያፈቀረሽ የተለያዩ ናቸው ያልኩሽ። ምርጫው ግን ያንቺ ነው። «ልብ ብለው አነበቡ? 👍 ካደረጉ በዋላ ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ Join us form more. 👇👇👇👇👇👇👇 @libmalet @libmalet

♨️♨️♨️ሴቶች ከወንዶች የሚጠብቋቸዉ ሰባት መገለጫዎች♨️♨️♨️ 1💝የትም ብትሆን ሁሌም ያማረ አለባበስ ይኑርህ:: 2💝ጠብ አጫሪ አለመሆንህን-የፍቅር ሰው መሆንህን አሳይ:: 3💝ተረጋጋ ፣ ዘና ብለህ አሽኮርምማት 4💝ከማዉራት ባሻገር ማድመጥም እንደምትችል አሳያት 5💝ድምፅህን ዝግ አድርገህ ተናገር (ድምፅህ የማማለል ዋነኛ መሳሪያ መሆኑን አትርሳ) 6💝ስሜቷን ጠብቅላት (እንደሙዳቸዉ ሁን) 7💝ሙሉ ትኩረትህን እሷ ላይ አድርግ (በተለይ እሷ እያወራች ከሆነ ዐይኗን መሸሽ የለብህም) @libmalet @libmalet

💞#የፍቅር_ግንኙነትን_ረጅም_ጊዜ_ለማቆየት_ሚረዱ_ነጥቦች💞 🗝አንደኛውና ዋነኛው ነገር #ኩርፊያን 😒ማቆም ነው ትንሽዋ ነገር ምትገነው በኩርፊያ ም/ክ ነው በምንም ነገር ከማኩረፍም ሆነ ከመበሳጨት በፊት ተነጋገሩ። 🔑ሁለተኛው ነገር ምንም ነገር አትመዝኚ/ን ለምን አይደውልም ለምን ቴክስት አይፅፍም ……………ለምን ሚለውን ነገር ባጠቃላይ ከአይምሮዋቹ አሶጡት ምንም ነገር አትመዝኑ ሁሉም የሆነበት የራሱ ም/ክ አለ። 🗝ሶስተኛው እና ግን ቀዳሚዊ ነገር ለሁሉም ነገር አትቸኩሉ በአንዴው ስለ አንድ ሰው ማንነት ሳታውቁ አበድንልህ ሞትንልህ አትበሉ በስተመጨረሻ ስለ አፍቃሪያቹ ስሰሙ መጨረሻው መዘዙ ለናተው ነው። 🔑ለወሲብ አትቸኩሉ ከስጋዊ እርካታ በፊት ልባዊ ፍቅራቹን ማጠንከር አለባቹ ወሲብ አስቀድማቹ ኃላ ፍቅራቹን ረስታቹ ሁሌም ለስጋዊ እርካታቹ ብቻ መገናኘት ትጀምራላቹ በመጨረሻም ግንኙነታቹ ይፈርሳል። 🗝ሌላው ደሞ ሁሌም እንደምለው #ትኩረት #ትኩረት #ትኩረት ትኩረት አስፈላጊው ነገር ነው ለአጋራቹ ትኩረት እና ጊዜ ስጡ። 🔑ካለሱ ወይም ካለስዋ መኖር አልችልም ብላቹ አስቡ ባሰባቹ ቁጥር ለአፍቃሪያቹ ትልቅ ቦታ እየሰጣቹት ትመጣላቹ 🗝ቅናትን አጥፉ❌ ወሬ አትስሙ❌ በሆዳቹ ቂም ከመያዛቹ በፊት መነጋገር ልመዱ💯 🔑ይሄ ቢሄድ ያይመጣል ምትሉትን ሁሉ ከሀሳባቹ አውጡ ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም ዝም ብላቹ 10ፍቅረኛ ከመያዝ ይልቅ ለህይወታቹ ሚያስፈልገውን ሰው መርጣቹ መስዋት ብትከፍሉለት ይሻላል። ወንድሜ እህቴ መለያየትን እንደመፍትሄ አትውሰጂ/ድ መለያየት መፍትሄ አይደለም ፍቅር እንደ ህፃን ልጅ ነው በትግስትና በእንክብካቤ ነው ማደግ ያለበት ትግስት ይኑራቹ ያለፈውን አታስታውሱ ባለፈ ሚዛን አትመዝኑ @libmalet @libmalet

❤️ሴት ልጅ እንዳፈቀረችህ የምታቅበት መንገድ❤️ ክፍል5⃣ 9. ከንፈሯን ከበላች በመሳሳም ወቅት ከንፈርህን ከነከሰችህ ፍፁም አታቋርጣት፡፡ ምንም መጥፎ የሆነ ነገረ የለም፡፡ ግን እሷ በራሷ የራሷን የምትነክስ ከሆነ ለመጨናነቋ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ለምን? ለሚለው መልስ ምናልባት በጥያቄ አይን አፍጥጠህባት ይሆን? 10. ነፍሷን አዳምጠው እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ መደበኛ ወንድና ሴት ግንኙነት ውስጥ ያሉ እንቅስቃሴዎች ሲሆኑ በወሲብ ላይ ጤናማ የሆነ መልዕክት ያላቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህን መልዕክቶች አንብቦ መተርጎምና በእንቅስቃሴው ውስጥ የራስህን ድርሻ መውሰድ ያንተ ፋንታ ነው፡፡ ሌላው ግን በደንብ እሷን መከታተልና ነፍስያዋ ማዳመጥ ዋናው ነገር ነው፡፡ አንድን ሴት አይተህ ከአንተ ምን እንደምትፈልግ ወሲብ፣ ፍቅር ወይስ ጥልቅ ቅርርብ የሚለውን ነገር ለማወቅ እነዚህን ከታች የተዘረዘሩትን ነገሮች ማስተዋልና ነፍሷን ማወቅ ትችላለህ፡፡ ጮክ ብላ የምትስቅ ከሆነ፣ ከንፈሯን ካረጠበች፣ በጡቷ ወይም በዳሌዋ ከገፋችህ፣ በጥልቅ ካዳመጠችህ፣ በኩራት ከተራመደች፣ ዳሌዋን ካማታች፣ የአይን አሰባበሯ፣ እግሯን አጣምራ ወደኋላ ከገፋችው፣ ፊቷን ከሸፈነች፣ በጣቶቿ ፀጉሯን ካበጠረች፣ የማይነኩ የሰውነት ክፍሎችህ ውስጥ እጆቿን ከሰደደች፣ እስቶኪንጓን ካስተካከለች ወይም በሹራቧ ቁልፍ ስትጫወት፣ በጣም ከዘነጠች ከተኳኳለችና ሽቶ ከተጋነነ፣ በጆሮህ በተደጋጋሚ በመምጣት የምታንሾካሹክ ከሆነ ወይም ደግሞ ፍቅራዊ የሆነ ሌላ መንገድ ከተጠቀመች፣ በጥልቀት ካፈጠጠችብህ፣ እንዲሁም በአይኗ መዝናህ ካንተጋር የበለጠ ሰዓት ለማሳለፍ ከፈለገች በነገሮች ላይ እርግጠና ልትሆንና የራስህን ውሳኔና እንቅስቃሴ ልታሳልፍ ትችላለህ፡፡ End @libmalet @libmalet

❤️ሴት ልጅ እንዳፈቀረችህ የምታቅበት መንገድ❤️ ክፍል4⃣ 7. እግር ማወዛወዝ እግር ማወዛወዝም ሆነ በፍጥነት ማጣጠፍ ሴቷ ለወሲብ ያላትን ተነሳሽነት ያሳያል፡፡ ይህን አጋጣሚ ደግሞ የበለጠ የሚያበረታታው እግሯን በማንቀሳቀስ ላይ እያለች ሳታስበው የምትከፍት ከሆነ ነው፡፡ በሲግመንድ ፎርይድ ክላሲካል ቲዮሪ መሰረት ይህ አጋጣሚ ለወሲብም ክፍት መሆኗን ጠቋሚ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ሳይነሳ የማይታለፈው የምታደርገው የጫማ አይነት ነው፡፡ የጫማው አይነት ለማውለቅ የበለጠ ቀለል ያለ ከሆነ ለነገሮች ያላትም ተነሳሽነት ቀላል መሆኑን የበለጠ አመላካች ነው፡፡ ለዚህ እንደ ምሳሌ የሚጠቀሰው በቤዚክ ኢንስትኒክት /Basic Instinct/ ፊልም ላይ የሻሮን ስቶን እግር አከፋፈት ነው፡፡ 8. የጣቶች አይነት አንድ ሴት ለእጇ ያላት አመለካከት የበለጠ ነገሮችንገላጭ ሲሆን በደንብ የተሰሩ ረጃጅም ጣቶች በጥንቃቄ የተቀለሙ ጥፍሮች መልካም የሆኑ አነቃቂ ነገሮች ናቸው፡፡ ይሁንና ሴቷ እጆቿን የምታንቀሳቅስበት መንገድ የበለጠ ጥንቃቄ ሊደረግበት የሚገባው ነው፡፡ ለረጅም ሰዓት እጆቿ ላይ በመፍጠጥ ከቆየች መናደዷንመረዳት ትችላለህ /ምናልባት ባንተ?/ ጠረጴዛውንም በጥፍሮቿ የምትመታ ከሆነ ተመሳሳይ መልዕክት ስለያዘ ብታስብበት ይሻላል፡፡ ይቀጥላል... @libmalet @libmalet

❤️ሴት ልጅ እንዳፈቀረችህ የምታቅበት መንገድ❤️ ክፍል3⃣ 3. በክንዷ ስትደገፍ አሪስቶትል እንዳለው ከሆነ የሴት እጅ ብዙ ነገር ያወራል፡፡ በአካል እንቅስቃሴ ላይ ጥናት አድራጊዎች ደግሞ ሴቶች በእንቅስቃሴያቸው የበለጠ ነገሮችን እንደሚገልፁ ያብራራሉ፡፡ በክንዷ ደገፍ ብላ እጇን አገጯ ስር በማስቀመጥ አይኗ በሀሳብ ከዋለለ ተመስጣብኛለች ብለህ በማሰብ እንዳትሳሳት እንደውም በዛ ሰዓት ላይ እራሷን በመጠየቅ ላይ ስለምትገኝ ትንሽ ታገሳት፡፡ እሷም በዛ ሰዓት እያሰበች ከምትሆናቸው ጥያቄዎች አንዱ ‹‹ለዚህ ሰው እገባዋለሁ?›› ሊሆን ም ወይም አልተማመነችብህም ማለት ነው፡፡ ይህ ሲሆን ታዲያ የተዘጋጀህበትም ቀልድም ሆነ ፈርጣማ ሰውነትህ ትርጉም ስለሌላቸው ባትለፋ ይሻላል፡፡ አይ ካልክ ደግሞ ቀለል ያለ የወሬ መጀመሪያ መንገድ ብትፈልግ ያዋጣሃል፡፡ 5. ከንፈሯን ስታረጥብ አንድ ሴት ከአንተ ጋር እያወራች በተደጋጋሚ ከንፈሯን የምታረጥብ ከሆነ ለፍቅር ያላትን ተነሳሽነት ይገልፃል፡፡ የስነ ባህል ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ሴቶች እንደዚህ አይነት ምልክት የሚሰጡት ከንፈራቸው ላይ ሌላ ነገር እንዲቀመጥ ሲፈልጉ ነው፡፡ ምን ሊፈልጉ እንደሚችሉ መቼም ላንተ መንገር የለብኝም፡፡ 6.ሽፋሽፍቶቿን የምትነካካ ከሆነ ነፃነት ያላት ሴት መሆኗን መናገር ይቻላል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ውስጥ መቀለድም ሆነ በትልቁ መሳቅ ላይጠበቅብህ ይችላል፡፡ ተነሳሽነቱን እሷ መውሰዷ ካልደበረህ በሁኔታዎቹ አብራችሁ ልትዝናኑ ትችላላችሁ፡፡ ይቀጥላል... @libmalet @libmalet

❤️ሴት ልጅ እንዳፈቀረችህ የምታቅበት መንገድ❤️ ክፍል2⃣ - በምታወሩበት ጊዜ እጇን ካጣመረች መጨናነቋን ወይም በሁኔታው ምቾት እንዳልተሰማትአመላካች በመሆኑ እስትራቴጂህን ወይም ስልትህን በፍጥነት መቀየር ይኖርብሃል፡፡ ሌላው ከዚሁ ከማጣመር ጎን የሚያያዘው የእግር ማጣመር ነው፡፡ እግር ማጣመር ልክ እጅን የማታመር ያህል መጥፎ ሲሆን ይህን አጋጣሚ የበለጠ መጥፎ የሚያደርገው ደግሞ አንድ ጊዜ እግሯን ካጣመረች እጇንም የማጣመር ሁኔታ ከፍተኛ መሆኑ ነው፡፡ ይሁንና እግሯን አጣምራም ቢሆን ጉልበቶቿ ወደ አንተ ከዞሩ ትንሽ ከመጨነቋ ውጪ ከአንተ ላይ ፍላጎት እንዳላት ያመላክታል፡፡ ተቃራኒው ሆኖ ጉልበቷ በሌላ አቅጣጫ ከዞረ ግን ችግር ውስጥ ነህ ማለት ነው፡፡ ወደኋላ መሸሽ ወይም መለጠጥ፡- ወንበር ላይ ከአንተ ራቅ ብላ ወይም ተለጥጣ የምትቀመጥ ከመሆን በደንብ የሚስተዋል አንተን ያለመሻቷ መገለጫ ነው፡፡ ስለዚህ የእኔ ምክር የሚሆነው የዚህ አይነት አካላዊ እንቅስቃሴዎችን በምታይበት አጋጣሚ ጨዋታውን ጥሎ መውጣት ብቻ ነው መፍትሄ የሚሆነው በእንደዚህ አይነት አጋጣሚ ሴቷን የራሳቸው ማድረግ የሚችሉት ልምዱ ያላቸው ብቻ ናቸው፡፡ የአካላዊ እንቅስቃሴ ማታለያዎች አንድ ሴት አንተን እየተከታተለችህ መሆኑንና ያለመሆኑን ለማወቅ አንድ የሚያስቅና የሚሰራ ማታለያ ልንገርህ፡፡ እሷ አንተን በምታይበት ሁኔታ ላይ ሆነህ ሰዓትህን እያየህ በዝግታ ከ1-3 ቁጠርና ቀና ብለህ እያት፡፡ እሷም ሰዓቷን እያየች ከሆነ አንተን ስታይህ እንደነበር እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡ ይህ ተፈጥሯዊ የሆነ አንተን የሚወድ ሰው ባህሪ ነው፡፡ ልክ አንተ ሰዓትህን ማየት ስትጀምር እሷም ምን እየጠበክ እንደሆነ በማሰብ ሰዓቷን ታያለች፡፡ ተጨማሪ የአካላዊ እንቅስቃሴ መረጃዎች 1. ፀጉር ማፍተልተል አብዛኛውን ጊዜ ፀጉሯን የምታስተካክል ወይም የምታፍተለትል ሴት የወንዶችን አይን ለመማረክ የምትሞክረው ናት፡፡ ፀጉር ማፍተልተሏንም ሆነ መነካካቷን በደቂቃ ውስጥ ሶስት ጊዜ የምታደርገው ከሆነ መያዝም ሆነ መታየትን የምትፈልግ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡ ሌላው ደግሞ ፀጉሯንየምትነካበት መንገድም የራሱ የሆነ መልዕክት እንዳለው መዘንጋት የለብህም፡፡ ይህም ፀጉሯን በቀስታ የምትነካካ ከሆነ የፍቅር ጥበብ እንዳላት ማወቅ የምትችል ሲሆን ከፈጠነች ደግሞ ማፈሯንና ትዕግስት አልባ መሆኗን ማየት ትችላለህ፡፡ 2. የብርጭቆ ጠርዝ ላይ እጅን ማሽከርከር በሲግመንድ ፎርይድ ቲዎሪ መሰረት ይህ ምልክት ለወሲብ የመጋበዝ ያህል ነው፡፡ ይህ አባባል ታዲያ በብዙ ሴቶች ተደግፏል፡፡ ይህን ጊዜ ታዲያ የጣቶቿን እንቅስቃሴ ልብ ማለት አለብህ፡፡ በዝግታ ጣቶቿን የምታሽከረክር ወይም የምታንቀሳቅስ ከሆነ ጥልቅ የሆነ እርጋታን፣ እራስ መቆጣጠርንና ጥበቃን አመላካች ስለሆነ ከጎኗ ልትቀመጥ ትችላለህ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ በጥፍሯ ብርጭቆውን መምታት ከጀመረች ለነገሮች ትዕግስት ማጣቷንና መቸኮልን ወይም በሌላ መልኩ በወንድ ጓደኛዋ መናደዷን አመላካች ነው፡፡ ይቀጥላል ... @libmalet @libmalet

❤️ሴት ልጅ እንዳፈቀረችህ የምታቅበት መንገድ❤️ ክፍል one የቅርብ ጊዜ የስነ ልቦና ጥናታዊ ሪፖርቶች… ሴት ልጅ ለአንተ ልዩ ፍቅርና መውደድ እንዳላትና እንደሌላት አዕምሮዋን በአካላዊ እንቅስቃሴዎቿ በኩል በቀላሉ እንድታነብ ያስችሉሃል!! አካላዊ እንቅስቃሴዎች ዋነኛዎቹ የመግባቢያ መንገዶች ናቸው፡፡ እነዚህ እንቅስቃሴዎች ግልፅ አካላዊ እንቅስቃሴና ዝግ አካላዊ እንቅስቃሴ ይባላሉ፡፡ አካላዊ እንቅስቃሴዎች በራሳቸው ቋንቋ በመሆን ከንግግርም በላይ በሆነ መልኩ መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡ እንዲህ አይነት ተግባቦት በአብዛኛው በተቃራ ፆታ ግንኙነት ውስጥ በተለይም በሴቶች ላይ ይስተዋላሉ፡፡ ግልፅ አካላዊ እንቅስቃሴ አንድ ጊዜ ከሴት ጋር አይን ለአይን ከተገጣጠምክ ፊቷን ካዞረች በኋላ ያላትንም እንቅስቃሴዎች አስተውል፡፡ አይናች በመጋጨቱ አፍረት ወይም መጨናነቅ ነገር ከታየበት ተመችተሃታል ወይም ወዳሃለች ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ፀጉሯን እንደማፍተልተል፣ ልብሷን ወይም ጌጣጌጧን ማስተካከል ወይም ደግሞ እጇ ላይ ባለው ነገር መጫወት ከጀመረች እነዚህ ግልፅ የሆኑ ማረጋገጫዎችህ ናቸው፡፡ - ውስጥ እጇን አንብብላት፡- በአጋጣሚዎች እና አንድ ላይ በምትሆኑባቸው ሁኔታዎች ውስጥ እጇን ብትመለከት እሷም አሳልፋ ውስጥ እጇንና የእጇን አንጓ እንድትነካ ከፈቀደችልህ ሌላው ያንተ እሷን የመመቸት የአዕምሮ ፍቃድ ማሳያ አንዱ መንገድ ነው፡፡ ይህም ሁኔታ ‹‹ከፈለከኝ ያንተው ነኝ›› እንደማለት ነው፡፡ - ማጎንበስ፡- በምታጎነብስበት ጊዜ ትከሻዋን ወደ አንተ በመስበቅ ካጎነበሰች ዕድል በእጅህ ገብታለች ማለት ነው፡፡ - እግሮቿን ከፍታ በምትቀመጥባቸው አጋጣሚዎች ካሉ አንተ ጋር በመሆኗ ምቾት ተሰምቷታል ማለት ነው፡፡ - አንድ ሴት አንድን ሰው በምታይበት ጊዜ የአይን ብሌኗ ከሰፋ ያንን ሰው እንደምትወደው በተቃራኒው ደግሞ የአይን ብሌኗን ካጠበበች ለዛ ሰው ጥሩ ስሜት እንደሌላት አንድ መገለጫ ነው፡፡ አይን ለአይን በምትጋጩበት ጊዜ ፈገግታን ከቸረችህ ወደ እሷ ሂድና አነጋግራት፡፡ ሌላው እንደ መልካም ነገር መገለጫ የሚወሰደው አንተ በምታወራበት ጊዜ ለረባ ባልረባው ፈገግ የምትል ወይም ሳቅ የምታበዛ ከሆነ በእርግጠኝነት በደንብ ተመችተሃታል ይሄ ደግሞ የበለጠ የተሻለ ነው፡፡ ይቀጥላል..... @libmalet @libmalet

በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ መምህሯ ክፍል ገብታ ስታስተምር ከተማሪዎቹ አንዱ ይነሳና "መምህር እቃ ተሰርቂያለሁ" ይላል ። መምህሯም የተሰረቀው እቃ ምን እንደሆነ ካጣራች ቡኃላ ተማሪዎች ለፍተሻ እንዲዘጋጁ አደረገችና ፍተሻዋን ቀጠለች ። ፣ በፍተሻው ሰአት ታዲያ አንዲት እድሜዋ 10 አመት እማይሞላ ተማሪ ተራዋ ደርሶ ቦርሳዋን እንድትከፍት ስትጠየቅ አሻፈረኝ ትላለች ። መምህሯም በንዴት ጦፋ አንቺ ሌባ አንቺ ነሽ የሰረቅሽው ፓሊስ ነው ምጠራልሽ እያለች ስትጮህ የሰሙት ዳይሬክተሯ ከተፍ ይላሉ ። ፣ ይህን ጊዜ ልጅቷ የባሰ ድንጋጤና ፍርሃት እያንቀጠቀጣት እባክሽ ይቅር በይኝ እኔ ሌባ ኣደለሁም ከፈለግሽ እንኪ ፈትሽኝ ግን እዚህ ተማሪዎች ፊት አደለም እያለች መምህሯ እግር ስር ወድቃ ልመናዋን ቀጠለች ። መምህሯ ግን እየደነፋች ነው ። ፣ በዚህ ጊዜ በእድሜ ጠና ያሉት ሴት ዳይሬክተር ቆይ እስቲ መምህር ምን እንደተፈጠረ ንገሪኝ ብለው ዳይሬክተሯ ወደቢሮ ወሰዷቸው ። ከዛም ልጅቷን በተረጋጋ ሁኔታ እንድትቀመጥ ቢያደርጉም መምህሯ ግን እስካሁን መረጋጋት አልቻለችም ። ዳይሬክተሯ መምህሯን ከገላመጡና ዝም እንድትል ካደረጉ ቡኃላ ልጅቷን እረጋ ብለው "ቦርሳው ውስጥ ምንድነው ያለው" ብለው ጠየቋት ። ፣ ልጅቷም "ቦርሳው ውስጥ ያለው ተማሪዎች በልተው የጣሉት ትርፍራፊ ነው ያለው" አለች በህፍረት እየተሸማቀቀች። ሴትዮዋም በመገርምና ባለማመን ስሜት "እንዴት እንዲህ ይሆናል" ሲሉ ጠየቋት ። ፣ እሷም "ለወንድሞቼ ልወስድላቸው ብየ ነው" አለች አንገቷን ደፍታ በሚያሳዝን ሁኔታ ቅስሟ ተሰብሮ ። ይህን ጊዜ ዳይሬክተሯ ከመቀመጫቸው ተነስተው ተጠጓትና ፀጉሯን እየደባበሱ "አይዞሽ የኔ ልጅ ተረጋግተሽ ስለ አባትሽና ስለ እናትሽ ንገሪኝ ኣሏት ። ፣ ይቺ አንዲት ፍሬ ልጅ እንባዋ እየወረደ እንዲህ አለች" አባቴ በሹፍርና ነበር የሚያስተዳድረን በኋላ ግን በአደጋ ተለይቶናል ። እናቴም ብትሆን ምንም ገቢ ያልነበራት ስትሆን ያባቴን ሞት ስትሰማ እራሷን ስታ ሆስፒታል ገባች ። በዛው የተነሳ ሽባ ሁና ቀረች ። ታዲያ ሁለት ጨቅላ ወንድሞች አሉኝ ቤት ነው ጥያቸው የመጣሁት ዘመድ ስለሌለን ዘወር ብሎ እሚያየን የለም ። ፣ እሚላስ እሚቀመስ የለንም ። ታዲያ ይችን ፍርፋሪ ወስጄ ሂወታቸውን ብታደጋት ብየ ነው ። እባካችሁ ለተማሪዎች እንዳትነግሩብኝ ። ትምህርቴንም ቢሆን አቋርጣለሁ ። ብቻ አትናገሩብኝ እያለች አንጀት በሚያላውስ ሁኔታ ችግሯን ስትናገር ዳይሬክተሯ ልጅቷን አቅፈው አነቡ ። ስለዚህ ከመፀፀት ይልቅ የሰዎችን ሁኔታ በእርጋታ ለመረዳት መሞሞከር ታላቅነት ነው ። @libmalet @libmalet