cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የቅዱሳን ታሪክ

በዚህ ቻናል ውስጥ፦ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብቻ የሚገኙ ስዕላትን የቤተክርስቲያን ትውፊት የጠበቁ ስዕላት የአድባራት እና የገዳማት ፎቶዎችን ያገኛሉ የተለያዩ ስዕለ አድዕኖ ለመላክ @kidanemiherat_bot

Show more
Advertising posts
9 218
Subscribers
-424 hours
-47 days
+4130 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
Media files
2410Loading...
02
#አነ #ውእቱ #ሩፋኤል #አሐዱ #እምሰብዓቱ #ሊቃነ_መላእክት ከሰባቱ የመላእክት አለቆች አንዱ እኔ ሩፋኤል ነኝ ( መጽ ቀሌምንጦስ) ጌታ በደብረዘይት ደቀመዛሙርቱን ሰብስቦ ጉባኤ ዘርግቶ እያሰተማረ ባለበት መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል መጣ ጌታም ስምህን ለደቀመዛሙርቴ ንገራቸው አለው የመጽሐፈ ቀሌምንጦስ ጸሐፊ ያንጊዜ ነው ስሙን እስከትርጓሜው የነገራቸው ይላል በረከቱ ይደርብን የቁስጥንጥንያው ሊቀጳጳስ ካሳነጻቸው ሰባት አቢያተ ክርስቲያናት አንዱ የቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ነው ቤተክርስቲያኑ የታነጸው ደሴት በሚመስለው በአሳ አንበሪው ጀርባ ላይ ስለነበር በቅዱሱ አባት አባ ቴዎፍሎስ ተባርኮ አገልግሎት ሲጀመር አጋጣሚው ተጠቅሞ አሳ አንበሪውን ሰይጣን እንዲናወጥ በማድረግ ሊያጠፋቸው ሲል ያዳናቸው መልአኩ እንደሆነ ድርሳኑ ይናገራል ቤተክርስቲያንዋን እና በውስጥዋ የነበሩትን አገልጋዮች ምዕመናን ከመሰጠም ታድጓቸዋል ዛሬም በውስጥም በውጭም ሁነው እንደ አሳ አንበሪው ቤተክርስቲያንን ከሚያናውጧት አገልጋይ ከሚመስሉ ቁማርተኞች አጋንንት ቤተክርስቲያንን ይታደግልን ቅዱስ ሩፋኤል ሰባት ዓመት ሙሉ እንደተራ ሰው ያገለገለው ከዓይነ ስውርነት የፈወሰው የእግዚአብሔር ሰው ቅዱስ ጦቢያ ስለቅዱስ ሩፋኤል ምልጃና ተራዳኢነት በሰፊው ጽፏል ጦቢያን የፈወሰ የቅዱሳን ባለሟል ቅዱስ ሩፋኤል ሁላችንም በአማላጅነቱ ይጠብቀን ከሚያናውጠን ከእርስ በእርስ የጦርነት ማዕበል ይታደገን! #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
2722Loading...
03
#ግንቦት_12 #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ባሕረ ምስጢራት የሆነ የሰውን ፊት አይቶ የማያደላ "መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ" (በርሱ ዘንድ ንጉሥ፣ ሐብታም፣ ደሃ፣ ነዳይ እኩል ነውና)፣ አፈ በረከት፣ አፈ መዐር (ማር)፣ አፈ ሶከር (ስኳር)፣ አፈ አፈው (ሽቱ)፣ ልሳነ ወርቅ፣ የዓለም ሁሉ መምሕር፣ ርዕሰ ሊቃውንት፣ ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)፣ የሐዲስ ኪዳን ዳንኤል፣ ሊቀ ጳጳሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)፣ ጥዑመ ቃል... እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እረፍቱ ነው። #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ሲናገር በአንድ ወቅት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡ከዕለታት አንድ ቀን በሀገረ ስብከቴ ሥር በነበሩ በሜዲትራኒያን ባሕር በሚገኙ ደሴቶች ውስጥ የሚኖሩ ምእመናንን  ለመጎብኘት አሰብሁ፡፡ ከእኔ ጋር ቀሳውስትንና ዲያቆናትን አስከትዬ በጀልባ ተሳፍሬ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ተጓዝሁ፡፡ በደሴቱ ውስጥ ስንዘዋወር የሰው ዱካ ብንመለከትም  ምንም ሰው ማየት አልቻልንም ነበር፡፡ በአሸዋው ላይ ታትሞ የነበረውን የሰው ዱካ ተከትለን ስንጓዝ ካልተፈለፈሉ ዐለቶች የተሠራ ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ዋሻ ላይ ደረስን፡፡ ዋሻው በርም ሆነ መስኮት የለውም፡፡ ወደ ውስጥ ስንገባ ልክ እንደ ሰባቱ ደማቅ ከዋክብት እጅግ በጣም አንጸባራቂ ብርሃን ቆመው ከሚጸልዩ ሰባት አባቶች ዘንድ ሲወጣ ተመለከትን፡፡ እኛም ከእነርሱ ጋር ለመጸለይ ባለንበት ቆምን። አባቶች ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ ወደ እኛ ዞሩና በፊቴ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ። በመቀጠልም ሰላምታ ሰጡን፡፡ እኔ ዮሐንስም ‘እኔ አባታችሁና ፓትርያርካችሁ ዮሐንስ ነኝ’ አልኳቸው፡፡ ቅዱሳኑ እንደገና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በፊቴ ሰገዱ እና እኔን ደካማውን እንዲህ አሉኝ፡- “የምንወደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትባርከንና እኛም አንተን በማየት እንድንበረታ ወደዚህ አመጣህ” አሉ። እኔም “እባካችሁ ታሪካችሁን ንገሩኝ” አልኋቸው፡፡ ሰባቱ አባቶችም “ከብዙ ዓመታት በፊት ሰባታችንም ከቍስጥንጥንያ ወጥተን በአንድነት ተሰባስበን ሕይወታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና በአምልኮ ብቻ ለማሳለፍ ወደዚህ ደሴት መጣን፡፡ ከዚህ ደሴት በደረስንበት ዕለት ከባሕሩ ከሚመጣው አስቸጋሪ ነፋስ ራሳችንን ለመከላከል ዋሻዎችን ለመገንባት ዐለቶችን ሰበሰብን፤ በሁለተኛው ቀን ደግሞ ይህን ቤተ ክርስቲያን መሥራት ጀመርን፡፡  በዐለቶች መካከል ከሚበቅለው ሣር እንበላለን፤ ውኃም ከባሕሩ እንጠጣለን፡፡ ቤተ ክርስቲያኑን የከበቡትን እነዚህን የአሸዋ ክምሮች ለማስወገድ ፈልገን ነበር፤ ግን አእምሯችንና አሳባችን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ስለተያዘ ጊዜ አጣን” በማለት ታሪካቸውን ነገሩኝ። እኔም “መንፈሳዊ አባታችሁ የት ነው?” ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ ይህን ጥያቄ ከመጠየቄ ወዲያውኑ አንድ ሽማግሌ በትሩን ተደግፎ ወደ እኔ ቀረብ አለና “እኔ የአንተ አገልጋይ ነኝ” አለኝ፡፡ አረጋዊው ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ራቁቱን ነበረና “ሰውነትህን የምትሸፍንበት ትንሽ ልብስ ትፈልጋለህ?” ስለው እሱም “ጌታ ከክረምቱ ቅዝቃዜ፣ ከበጋው ሙቀት ይከላከልልናል፤ ይጠብቀናልም” በማለት መለሰልኝ፡፡ “ምግብ ያስፈልጋችኋል?” ብዬ ስጠይቀው እርሱም “የሚበቃንን ያህል ከእነዚህ ዕፅዋት እንመገባለን ከዓለም የሆነ ምንም ነገር አያስፈልገንም” በማለት መለሰልኝ፡፡ እኔም “አባቶቼ እባካችሁ ለእኔ እና ስለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ጸልዩ” አልሁት። የእነዚያን ቅዱሳን ባሕታውያን አባቶች በረከት ከተቀበልን በኋላ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም ምሥጋና የሚገባውን የምንወደውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እያመሰገንን ወደ መጣንበት ተመለስን” ይለናል ቅዱሱ አባታችን ዮሐንስ አፈ ወርቅ። #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
4702Loading...
04
#ግንቦት_12 #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ባሕረ ምስጢራት የሆነ የሰውን ፊት አይቶ የማያደላ "መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ" (በርሱ ዘንድ ንጉሥ፣ ሐብታም፣ ደሃ፣ ነዳይ እኩል ነውና)፣ አፈ በረከት፣ አፈ መዐር (ማር)፣ አፈ ሶከር (ስኳር)፣ አፈ አፈው (ሽቱ)፣ ልሳነ ወርቅ፣ የዓለም ሁሉ መምሕር፣ ርዕሰ ሊቃውንት፣ ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)፣ የሐዲስ ኪዳን ዳንኤል፣ ሊቀ ጳጳሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)፣ ጥዑመ ቃል... እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እረፍቱ ነው። ምልጃውና የከበረች ጸሎቱ ከእኛ ጋር ትሁን!
4262Loading...
05
Media files
3111Loading...
06
#ቅዱስ_ሚካኤል #እስራኤል_ዘሥጋን • የመራቸውና የጠበቃቸው • ባህር የከፈለላቸው • ጠላት ፈርዖንን ከነሠራዊቱ ያጠፋላቸው • በአምላኩ ፈቃድ መና ከሰማይ ያወረደላቸው • በለዓም እንዳይረግማቸው ሰይፉን መዞ መርገማቸውን የመለሰላቸው • ለመራገም የሄደው እንዲመርቃቸው ያደረገው ....በዚህም መጋቤ ብሉይ ተብሎ የተጠራው • የባህራንን የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት የቀየረው • የቅድስት አፎምያን ፈታኝ በሥልጣን የረገጠው ... መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው!!! ቅዱስ ያሬድ "አስተምሕር ለነ ሰአልናከ በዐሠርቱ ወአርባዕቱ ትንብልናከ " ብሎ እንደለመነው.... እኛም እስራኤል ዘነፍስ በቅዱስ ያሬድ ቃል ♥ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ!♥ ተማጽነንሃል! በአሥራ አራቱ ምልጃዎችህ ማልድልን" እንደ አምላክህ በሆነው ርኅሩህነትህ ከፈጣሪያችን ጋር አስታርቀን ክፉዎን ሁሉ በምልጃህ ተቋቋምልን በጠላቶቻችን የተጻፈብንን የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት ቀይርልን በልዩ ልዩ ፈተና የሚፈትኑንን አጋንንትን ከአምላክህ በተሰጠህ ሥልጣን እርገጥልን .. እያልን እንለምነዋለን! የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ ሁላችንንም በያለንበት ይጠብቀን! #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
3551Loading...
07
. #ተክለ_ሃይማኖት . #የሃይማኖት_ተክል_ተክለ_አብ_ተክለ_ወልድ_ተክለ_መንፈስ_ቅዱስ ༺◉❖═───◉●◉🌹🌹🌹◉●◉────═❖◉༻ #ሐዲስ_ሐዋርያ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_ዘደብረ_ሊባኖስ እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ የመረጣቸው ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 11 97 ዓ.ም ተወለዱ ። ጸድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ❝ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ❞ ማለትም ❝ አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው ❞ በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነዋል ። #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ከልጅነታቸው ጀምሮ በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ዲቁናን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያጠኑ ቆይተው በ 15 እና በ 22 ዓመታቸው ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ከአቡነ ቄርሎስ ( ጌርሎስ ) ዲቁናንና ቅስናን ተቀብለዋል ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ቅድስት ቤ.ክ በወጣትነት ዕድሜያቸው ያገለግሉ እንደነበር በዚህ ይታወቃል ። ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዚህች ምድር በኖሩባት 99 ዓመት ውስጥ ለአገልግሎት የሚያበቃ ሃይማኖታዊ ትምህርታቸውን ከቀሰሙ በኋላ ወደ ተለያዩ ገዳማት በመዘዋወር ዕውቀታቸውን ያሰፉበትንና ለሐወርያዊ ተልዕኮዎች የተሰማሩባቸውን ጊዜያትና ቦታዎች እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስም የፈጸሙትን ተጋድሎ በአጭሩ የሚከተለውን ይመስላል ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1219-1222 ዓ.ም በተከታታይ ለሦስት ዓመታት ወንጌልን አስተማሩ ቀጥለውም ዘጠኝ ወር በዊፋት አገልግሎታቸውን ፈጸሙ ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ12 23-12 34 ዓ.ም ዳሞት በተባለው ስፍራ ወይም በወላይታ ሀገር ለ12 ዓመታት ሕዝቡን በማስተማር ከአምልኮተ ጣዖት ወደአምልኮተ እግዚአብሔር ከገቢረ ኀጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ መልሰዋል ። ቤተ ክርስቲያንንም አንጸዋል። በዚም ሀገር ዲያብሎስ በዛፍ ላይ አድሮ አምላክ ነኝ እያለ ለረጅም ዘመናት ሕዝቡን በማሳት የሚጠቀምበትን ዛፍ በተአምራት ከሥሩ ነቅለው አፍልሰውታል ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1234-1244 ዓ.ም ባለው ጊዜ ደግሞ በእግዚአብሔር ፈቃድና ትእዛዝ ወደ አማራ ሳይንት ወሎ በመሄድ ከአባ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ገብተው ሥርዓተ ምንኲስናን እየተማሩ ለ 10 ዓመታት የተለያዩ ገቢረ ታምራትን በማድረግ በጉልበት ሥራም ሲያገለግሉኖሩ #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1244-1254 ዓ.ም አባ ኢየሱስ ሞዐ ወደሚገኙበት ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም በቅዱስ ሚካኤል መሪነት ሐይቁን በእግራቸው እንደ ደረቅ መሬት በመርገጥ ወደ ደሴቱ በመግባት የአገልግሎትና የትሩፋት ሥራን በማብዛት የምንኲስናን ተግባራቸውን በመቀጠል ከፍጻሜ አድርሰዋል በአባ ኢየሱስ ሞዓ እጅም የንጽሕና ምልክት የሆነውን የምንኲስናን ቀሚስ ተቀብለዋል ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1254-1266 ዓ.ም ወደ ትግራይ ሄደው ከአቡነ አረጋዊ ገዳም ደብረ ዳሞ ገብተው በጊዜው ከነበሩት አበምኔት ከአባ ዮሐኒ ቆብና አስኬማ ተቀብለው ለ12 ዓመታት በገዳሙ በገድል በትሩፋት መንፈሳዊ ተጋድሎአቸውን ቀጠሉ ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1266-1267 ዓ.ም ለአንድ ዓመት ያህል የትግራይን ገዳማት በሙሉ በመጐብኘት ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ግብፅም በመሄድ በዚያ ያሉ ቅዱሳት መካናትን ጎብኝተው መጥተዋል ። ከዚህ በኋላ ዳዳ በተባለ ስፍራ ይመለክ የነበረውን 75 ክንድ የሚረዝመውን ዘንዶ በጸሎት ኃይል በመስቀል ምልክት አማትበውበት በተአምራት ገድለውታል ። በቦታው ላይ በአርባዕቱ እንስሳ ስም ቤተ ክርስቲያን አንጸው ታቦተ ሕግ አስገብተውላቸዋል ከሴቶችና ከልጆች ሌላ ሦስት ሺህ በጣዖት የሚያመልኩ ወንዶችን አስተምረው መልሰው አጥምቀው አቍርበዋቸዋል ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1267-1289 ዓ.ም ባለው ጊዜ ደግሞ በደብረ ሊባኖስ ካለችው ገዳመ አስቦ ዋሻ በመግባት 8 ጦሮችን ሁለቱን በፊት ፣ ሁለቱን በኋላ ፣ ሁለቱን በቀኝ ሁለቱን ደግሞ በግራ አስተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማምና ሞት ፣ ነገረ መስቀልን በማሰብ በተመስጦ ሌትናቀን ያለማቋረጥ በጾምና በጸሎት በአርምሞ ተወስነው ሲጋደሉ ከቁመት ብዛት የተነሣ ጥር 4 ቀን 12 89 ዓ.ም. አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰብራለች ቅዱስ አባታችን በመዓልትና በሌሊት በትጋትና በቁመት በተጋድሎ ብዛት አንዲት የአገዳ እግራቸው ስትሰበር ዕድሜያቸው 92 ዓመት ሆኗቸው ነበር ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1289-1296 ዓ.ም ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው በመቆም ያለምግብና ያለውኃ በትኅርምት ሌትና ቀን እንቅልፍ በማጣት እንደ ምሰሶ ጸንተው በተመስጦ በትጋት ለሰው ዘር ሁሉ ድኀነትን ሲለምኑ ኖረዋል ። ከሰባቱ ዓመታት ውስጥ ጥቂት ውኃ የቀመሱት በአራተኛው ዓመት ብቻ ነበር በዚህ ጊዜ ውስጥ ጌታችን ተገልጦላቸው በሰው አእምሮ ሊታሰብና ሊለካ የማይችል ትልቅና ልዩ የመንግሥት አዳራሽ ከሰጣቸው በኋላ የመለኮትን ነገር የሚናገር የእሳት አንደበት ያላቸው የመንግሥት ልብስ አለበሳቸው በመስቀል ምልክት የተጌጡት ሰባት የሕይወት አክሊላትን አቀዳጅቷቸዋል ። #ይኸውም ፦ ስለ ቀናች ሃይማኖትህ፣ሃይማኖትን ለማስተማር መላዋን ኢትዮጵያን ስለመዞርህ ። ከአረማውያን ሕዝብ ጋር በሃይማኖት ስትታገል ደምህን ስለማፍሰስህ ። ወደ ኢየሩሳሌም ወርደህ ልዩ ልዩ የቅዱሳን ቦታዎች ስለመሳለምህ ። በሰባት ዓመታት ቍመት የአንዱ አገዳ እግርህ ስለመሰበሩ። ስለብዙ ጾም ጸሎት ስግደትህ ስለልብህ ንጽሕናና ቅድስና ። በማለት የሕይወት አክሊላትን ካቀዳጃቸው በኋላ ዝክራቸውን በማዘከር መታሰቢያቸውን የሚያደርጉ ሁሉ በዚህ ዓለምም ሆነ በወዲያኛው ዓለም ፍጹም ዋጋና ፍጹም ክብር እንደሚሰጣቸው ጌታችን ታላቅ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል ። ሥጋቸውም ወዴት ይቀበር ዘንድ ሲነግራቸው ❝ እስከ 57 ዓመት ሥጋህ ከዚህ ይቀበራል ከ 57 ዓመት በኋላ ግን ይህች ዋሻ ትናዳላች በዚህም ገዳም አደባባይ በስምህ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ልጆችህ ሠርተው ሥጋህን አፍልሰው በውስጡ ያኖራሉ ❞ አላቸው ። በመጨረሻም አባታችን ለ10 ቀናት ያህል በተስቦ ሕመም ቆይተው ፈጣሪያቸው የገባላቸውን ቃል ኪዳን ለመነኰሳት መንፈሳውያን ልጆቻቸው ከነገሯቸው በኋላ ( ነሐሴ 24 )ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል ። #የቅዱስ_አባታችን_በዓላት_እነዚህ_ናቸው ✟ ኅዳር 24 ቀን ከ 24 ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር በሕይወተ ሥጋ እያሉ የሥላሴን መንበር ያጠኑበት ። ✟ ታኅሣሥ 24 ቀን 11 97 ዓ.ም ልደታቸው ። ✟ ጥር 4 ቀን 12 89 ዓ.ም ደግሞ በጸሎት ብዛት አንድ እግራቸው የተሰበረበት ቀን ነው ( ነገር ግን የዕረፍታቸውን ቀን ይዞ በዚሁ በጥር ወር በ 24 ይከበራ ) ✟ መጋቢት 24 ቀን 11 96 ዓ.ም ፅንሰታቸው ። ✟ በግንቦት 12 ቀን 13 53 ዓ.ም ፍልሰተ ዐፅማቸው ነው ✟ ነሐሴ 24 ቀን 12 96 ዓ.ም ዕረፍታቸው ። . #ጸሎታቸው_በረከታቸው_ረድኤታቸው_ምልጃቸው_በመላው_ሕዝበ_ክርስቲያን_አድሮ_ይኑር_ለዘለዓለም።
45411Loading...
08
Media files
3971Loading...
09
Media files
5472Loading...
10
Media files
4251Loading...
11
ስለ ቅዱስ ያሬድ ተናግሬ አልጠግብም አብዝቼ ወደዋለሁ............ #የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤት_ክርስቲያን መንዝራ ዘርዝራ አመሥጥራ የማትጨርሰው ከየዘመኑ ጋር አብሮ የሚጓዝ የዘመን ቅርስ ሀብቷ ነው ቅዱስ ያሬድ ። #ቅዱስ_ያሬድን ድንቅና ልዩ ከሚያሰኙት ምክንያቶች አንዱ በዓለማችን የመጀመሪያው የዜማ ምልክቶች ደራሲ በመሆኑ ነው ። ዜማን ቅርጽ በማስያዝ ሳይጠፋ ከትውልድ ትውልድ እንዲተላለፍ ያደረገ ለሌሎች የዜማ ሊቃውንት ፈር የቀደደ ሊቅ ነው ። #ቅዱስ_ያሬድ ገና የ12 ዓመት ልጅ እያለ በተፈጥሮዋ ትንሽ ከምትባለው ትል የጽናትን ውጤት ተገንዝቦ የሰው ልጅ እየወደቀና እየተነሣ ለውጤት መትጋት እንዳለበት እንዲሁም የሕይወት ስኬት የብዙ ልፋቶች ውጤት እንደሆነ በማመን ተስፋ ባለመቁረጥ በትዕግሥትና በጽናት ፍሬ ለማፍራት መታገል እንደሚገባው ተምሮ ያስተማረ ሊቅ ነው ። #ቅዱስ_ያሬድ ለዜማ ጥበባት ማኀፀን የሆነውን መተኪያ የማይገኝለትን ያሬዳዊ ዜማ ሰማያዊ ድርሰትን ለኢትዮጵያ ውበቷ የኩራት መቀነቷ የሆነውን የዜማ ድርሰቶችን ያበረከተላት ታላቅ ሊቅ ነው ። ቅዱስ እግዚአብሔር ያሬድንም ከብሔረ ሕያዋን ደምሮ ሞትን ሳይቀምስ በግንቦት 11 ቀን ሰወረው መታሰቢያውም በዚህ ዕለት ኾነ የሊቁ ቅዱስ ያሬድ ማሕሌታይ በረከቱና ረድኤቱ በአገራችን ኢትዮጵያና በመላው ሕዝበ ክርስቲያን ላይ ለዘላለም አድሮ ይኑር ። #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
5463Loading...
12
Media files
5072Loading...
13
ከሰው ፡ ዐይን ፡ ተሰወረ ፡ አኗኗሩም ፡ ከሰማይ ፡ መላእክት ፡ ጋር ፡ ሆነ #ቅዱስ_ያሬድ ደብረ ሐዊ ከተባለው በሰሜን ተራራና ጫካ ብዙ ዓመታትን በምናኔ ካሳለፈ በኋላ ግንቦት 11 ቀን ሞትን ሳይቀምስ ከዚህ ዓለም ተሠወረ ፣ በዚህ ዓለም የኖረበት ጠቅላላ ዕድሜው ሰባ ዐምስት ነበር ፡፡ በቅዱስ ያሬድ ታሪክ ውስጥ አከራካሪ ትረካዎች አሉ ይኸውም በዕረፍቱና በዕርገቱ መካከል የሚነገረው ትረካ ነው አንዳንድ ሊቃውንት ቅዱስ ያሬድ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየ መቃብሩም እንደተሠወረ ሲናገሩ ሌሎች ሊቃውንት ደግሞ እንደ ሄኖክና እንደ ኤልያስ ሞትን ሳይቀምስ እንደተሠወረ ይናገራሉ ፡፡ ሞቷል የሚሉት ሊቃውንት በስንክሣሩ ላይ ‹‹ በዚች ዕለት የሱራፌል አምሳያቸው የኾነ ማሕሌታይ ያሬድ ዐረፈ ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን ገዳም ሔዶ በዚያ ተቀመጠ በሰላምም ተቀመጠ ›› የሚለውን ገጸ ንባብ ይዘው ሞቷል የሚሉ አሉ ነገር ግን ይሄ ገጸ ንባብ በሞት መለየቱን አያመለክትም ። ምክንያቱም ‹‹ ጌታችን ከሥራው ሁሉ ዐረፈ ›› እንደሚለው ፤ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ‹‹ በጎዳና ካገኘኝ ድካም ሰውነቴ ዐረፈች ›› ብሎ በተናገረው መሠረት ሰው እንደሚያርፍ ቅዱስ ያሬድም ማስተማሩን ፤ ከሰው ጋር መለየቱን ፤ ከዓይነ ሞት መሠወሩንና ከተጋድሎው ማረፉን የሚያመለክት ነው እንጂ መሞቱን አያመለክትም ብለው የሚከራከሩ ሊቃውንት አሉ ። ስለዚህ ቅዱስ ያሬድ ሞቷል ብለው የሚከራከሩ ሊቃውንት ከሞተ መቃብሩ የት ነው ሲባሉ መቃብሩ ተሠውሯል ይላሉ ፤ የመቃብሩ መሠወር ለምን አስፈለገ ተብለው ሲጠየቁ ልክ እንደ ሙሴ መቃብር ተሠውሯል ይላሉ ነገር ግን የሙሴ መቃብር የተሠወረበት የራሱ የሆነ ዓላማና ምክንያት ነበረው ። እርሱም ምንድነው ቢሉ እስራኤላውያን ቅዱስ ሙሴን በብዙ ይወዱት ነበርና እንዳያመልኩት ምክንያት ለማሳጣት እግዚአብሔር ይህን እንዳደረገ ሊቃውንት ይናገራሉ ፤ የቅዱስ ያሬድ መቃብር መሠወሩ ግን ምሥጢሩ ምንድ ነው ? ለሚለው ጥያቄ በቂ መልስ ስለሌለ ሞትን ሳይቀምስ እንደነ ኤልያስ ተሠውሯል የሚለው አብላጫውን ድምፅ ይዞ በብዙ ቤተ ጉባኤዎች የሚነገረው መሠወሩ ነው ፡፡ ድርሳነ ዑራኤልም ‹‹ ከሰው ዐይን ተሰወረ ፤ አኗኗሩም ከሰማይ መላእክት ጋር ሆነ ›› በማለት እንደነ ኤልያስ ከነሥጋው ማረጉን አስረግጦ ይናገራል ፡፡( የሰኔ ድርሳነ ዑራኤል ምዕራፍ 2 ፥ 50 ) ስለዚህ ሊቁ ቅዱስ ያሬድን ከሃይማኖታዊ ሚዛን ወጥተን ስንመለከተው ሀገራዊ ፣ ባህላዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ሥልጣኔያዊ ፋይዳና ፍልስፍናዊ ድርሻ ያለው እንደሆነ እንገነዘባለን ፡፡ ቅዱስ ያሬድ ሃይማኖታዊ እሴት ያበረከተ ዘማሪ ብቻ ሳይሆን እጅግ ብዙ መጠነ ሰፊ ጉዳዮች የጻፈ የቀመረ ያረቀቀ ሊቅ ነው ፤ ስለሆነም ብሔራዊ መኩሪያችን ነው ። #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
5376Loading...
14
ሰንበትን ለቅ/ያሬድ -- አዲስ አበባና በዙሪያዋ ያላችሁ ጎተራ አካባቢ የሚገኘው ደብረ ይባቤ ቅ/ያሬድ ብትገኙ በረከት ነው። ሊቁ በዚያ ይነግሣል። ከሰዓት ደግሞ ሊቁን የሚዘክር መርሐ ግብር በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ተዘጋጅቷል። ዓመቱን ሙሉ ለልዑል እግዚአብሔርና እርሱ ላከበራቸው ቅዱሳን የሚሆኑ የምስጋና፣ የመማጸኛ፣ የታሪክና ተጋድሎ መንገሪያ፣ የመንፈሳዊ ሕይወት መመሪያ ዜማዎችን ለቀመረው ሊቅ አንዲት ቀን መስጠት በረከቱ ለራሳችን ነው። እርሱማ አንድ ጊዜ ቅዱስ ተብሏል፣ በእኛ ማክበር የሚጨመርለት፥ ባለማክበር የሚወሰድበት ክብር የለም። ብናከብረው ክብሩ በረከቱ ለራሳችን ነው። ማንገሥ ሲባል በእኛ ፈቃድ የሚነግሥ ሆኖ አይደለም፤ ስለእምነትና ትሩፋቱ ከፈጣሪው የተሰጠው ክብር ለመታሰቢያው በተሠራው መቅደስ መገለጡን መናገር ነው። ሰንበትን ለቅዱስ ያሬድ! መልካም በዓል!
6722Loading...
15
Media files
6271Loading...
16
ሁለተኛው ዐሳብ ደግሞ መንካቱን ነክታዋለች፤ እግሩንም ይዛ ወድቃ ሰግዳለታለች፤ እርሱ ግን እኔን መያዙን ተዪና ወደ ደቀመዛሙርት ሂደሽ ወደ አብ ዐርጋለሁ ብሏል በማለት ንገሪያቸው ማለትን ያመለክታል የሚል ነው። አትንኪኝ ሳይሆን ይዘሽኝ ብዙ አትቆዪ ፤ እኔን ልቀቂኝና ወደ ወንድሞቼ ሂደች የማርግ መሆኔን ንገሪ የሚል ነው። በዚህ ሰአት ለማርያም መላእክት ተገልጠው ነበር፤ "ስለምን ታለቅሻለሽ?" ብለው ለጠየቋት ጥያቄ የመለሰችው መልስ "ጌታዬን ወስደውታል፤ ወዴትም እንዳኖሩት አላውቅም" የሚል ነበር፤ ጌታም ወዲያው ተገለጠላትና ለጠየቃት ተመሳሳይ ጥያቄ "ጌታ ሆይ አንተ ወስደኸው እንደሆነ ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ፤ እኔም እወስደዋለሁ" የሚል ነበር። ረቡኒ ብላ የነካችው ማርያም ብሎ ከጠራት በኋላ ነው፤ እነዚህ ነገሮች የሚያስረዱን ማርያም ብሎ እስኪጠራት ድረስ የጌታን ትንሣኤ ማርያም ገና ያላመነች (ያልተረዳች) እንደነበረች ነው፤ ድምፁን ስትሰማ ትንሣኤውን የማወቅ፣ ሕያው መሆኑን የማመንና ትንሣኤውን የማስተዋል ኀይልን አገኘች። በነካችው ጊዜ አምናለች፤ ያመነችውን ማርያምን ላካት፤ ያላመነውን ቶማስን ጥርጥሩን ያርቅለት ዘንድ እንዲነካው አዘዘው፤ ሳያምኑ የትንሣኤውን ዜና ለመንገር መላክ የለምና ቶማስን ወደ እምነት ለመሳብ ይነካው ዘንድ አዘዘው፤ ማርያም ድምፁን ሰምታ አምና ነበርና ሰትነካው የዕርገቱን ነገር ለደቀመዛሙርት ትነግር ዘንድ ላካት። አላመነችም ነበር ብንል እንኳን አለማመንዋ ከመንካት ላያግዳት ይችላል፤ ቶማስም እየተጠራጠረ ሳለ ነክቶታልና፤ በማቴዎስ ወንጌል 28፥9 እንደተጠቀሰውም ሴቶች እግሩን ይዘው ደግውለታል፤ አንደኛዋም ራስዋ ማርያም መግደላዊት ነበረች፤ ስለዚህ አለማመንዋና ሴትነቷ እርሱን እንዳትነካ ይከለክላል ማለት አስቸጋሪ ይሆናል። የአንድምታ ትርጓሜው ለመሰናበት የተገለጠላት መስሏት እንደነበረ ያስረዳል፤ ይህም ማለት ማርያም ጌታን ከዚህ ሰአት በኋላ አላገኘውም ብላ ዐስባለች ማለት ነው፤ በዚህም ምክንያት አጥብቃ እንደያዘችውና ይዛውም እንደቆየች ያሳያል፤ ስለዚህ ጌታ ገና አላረግሁምና መልእክትን ወደ ወንድሞቼ ይዘሽ ሂጅ እንጂ እኔን በመያዝ አትዘግዩ አላት እንጂ አትንኪኝ ብሎ አልከለከላትም ማለትን ያስረዳል። ቀሌምንጦስ ዘሮም በእግሩ ላይ ወድቃ ሰገደችለት ይላል፤ ዮሐንስ አፈ ወርቅም ይህን ያጸናል፤ በዚህም እግሩን ይዛ እንደሰገደችለትና ይዛውም እንደቆየች መረዳት ይቻላል። ጌታም እያላት ያለው እኔን ይዘሽ አትዘግዪ፤ ገና ወደ አብ አላረግሁምና ታገኝኛለሽ፤ ይህ ሰአት የመጨረሻው አይምሰልሽ ነው። ለወንድሞቼ ፈጥነሽ ሂጅና መልእክቴን ንገሪ፤ ለመልእክት ፍጠኚ የሚል ዐሳብ ነው። ......... ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
1 1122Loading...
17
#ትንሽ_ረዘም_ትላለች_በጥሞና_በትዕግስት_አንብቧት "አትንኪኝ!" ማለት ምን ማለት ነው? ለምን አትንኪኝ አላት? "ኢየሱስም ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁም ዐርጋለሁ ብለሽ ንገሪያቸው አላት" ( ዮሐ. 20፥17) ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን! ብያለሁ። ይህ ንባብ (ዮሐንስ 20፥17) ለመረዳት አስቸጋሪ ከሚባሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባት አንዱ ነው፤ ለዛሬ "ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ" የሚለውን ንባብ ለማብራራት እሞክራለሁ፤ ቀጣይ ደግሞ ወደ አባቴ ወደ አባታችሁ ፣ ወደ አምላኬ ወደ አምላካችሁ የሚለውን ንባብ የሚያብራራ ዐሳብ ይዤ እመለሳለሁ። 1. አትንኪኝ ያላት ማርያም መግደላዊትን ነው፤ ጌታ ለማርያም መግደላዊት የተገለጠላት ኒሳን 16 ቀን እሑድ ሲነጋ ነበር፤ ጌታ ለማርያም ከመገለጡ በፊትም ገና ጨለማ ሳለ ወደ መቃብሩ መጣች፤ ድንጋዩ ተፈንቅሎ ዐይታ ለዮሐንስና ለጴጥሮስ ነገረች፤ እነርሱ ዐይተውና አምነው ሲመለሱ እርሷ እያለቀሰች ቆማ ነበር። ማርያም መግደላዊት ደግሞ ጌታ ሰባት አጋንንት ያወጣላት ሴት ነበረች (ማር.16፥9 ሉቃ. 8፥2) ። ማርያም መግደላዊት የጌታን ሥራ በራስዋ ሕይወት የምታውቅ፣ ክርስቶስን የምታምንና የምትወድ ሴት እንደሆነች ከታሪኳ መረዳት ይቻላል። ማርቆስ አስድሞ (ከሌሎች በፊት) እንደገለጠላት ይናገራል (ማር. 16፥9) ፤ በዮሐንስ ወንጌል ዘገባ መሠረት ደግሞ ገና ጨለማ ሳለ ብቻዋን ወደ መቃብሩ መጣች። 2. አትንኪኝ የሚለው ቃል ትርጉም "አትንኪኝ" የሚለው ቃል በግእዝ "ኢትልክፍኒ ተብሎ ተተርጉሟል፤ "ለኪፍ ለኪፎት" የሚለው የግእዝ ንኡስ አንቀጽ (infinitive) "መልከፍ፣ መለኮፍ፣ በጥቂት መንካት ፣ መድረስ ፣መቅመስ፣ ማግኘት" ማለት ነው ( ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ፣ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ ፣1948 ፣ ገጽ 566) ። ይህ ትርጉም እንደሚያመለክተን ጌታ ማርያም መግደላዊት እንድትነካው አለመፍቀዱን ያስረዳል። ሐፕቶማይ የሚለው የግሪክኛው ቃል "to attach oneself to" የሚል የእንግሊዝኛ ትርጉም አለው፤ ይዞ መቆየት መጣበቅ የሚል ግርድፍ ትርጉም ይሰጣል። ከዚህ ትርጉም በመነሣት ደግሞ ጌታ ለማርያም መግደላዊት ያላት ነገር አትንኪኝ ሳይሆን ይዘሽኝ አትቆዪ፣ ለረጅም ሰአት አትያዥኝ ዘይም አትጣበቂብኝ ነው። የግሪክኛው ቃል ወደ አማርኛ የተለያዩ ትርጉሞችን ይዞ ገብቷል፤ ለምሳሌ መንካት (ሉቃ.7፥14 ዮሐ.20፥17) ፣ መዳሰስ (ማቴ.8፥3) ፣ ማግኘት (1ቆሮ.7፥1) መንካት መቅመስ መያዝ (ቆላ.2፥21) ሊጠቀሱ ይችላሉ። በዚህም ምክንያት በእንግሊዝኛ ቅጅዎች የተለያየ ትርጉም ተሰጥቶታል፤ ኪንግ ጀምስ "do not cling to me" , New American standard Bible "stop clinging to me" , NIV "do not hold on to me" ይላሉ። cling ማለትም "hold on tightly to" ማለት ነው። ዐሳቡ ይዞ መቆየት፣ ቶሎ አለመልቀቅ እንጂ ፈጽሞ አለመንካትን አያመለክትም። ከትርጉሞች የምንረዳው አትንኪኝ የሚለው ቃል ሁለት ዐሳቦችን ሊገልጥ እንደሚችል ነው፤ አንደኛው "አትንኪኝ" የሚለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ይዘሽኝ አትቆዪ፤ አትዘግዪ፣ ልቀቂኝ" ማለት ሊሆን ይችላል፤ ስለዚህ ክርስቶስ ለማርያም መግደላዊት ያላት ምንድነው? ፈጽሞ አትንኪኝ ነው ወይስ ይዘሽኝ አትቆዪ? ይህን ነጥብ እንመረምራለን። 3. አትንኪኝ የሚለው ቃል ዐሳቡ ምንድነው? ምንስ ያመለክታል? አንደኛው "አትንኪኝ" በማለቱ እንዳትነካው ከልክሏታል የሚለው ዐሳብ ነው፤ በአንድምታ ትርጓሜም እንደተገለጠው ንግግሩ የተግሣጽ ቃል ነው፤ ምክንያቱ ብዙ ሊሆን ይችላል። ማርያም የመጣችው ሽቱ ይዛ የጌታን ሥጋ ሽቱ ለመቀባት ነበር፤ ሬሳን ሽቱ መቀባት የአይሁድ ልማድ ነው፤ ሽቱ የሚቀባው የሚፈርስና የሚበሰብስ ሥጋ ነው፤ የጌታ ሥጋ ግን ሙስና መቃብር (በመቃብር ፈርሶ በስብሶ መቅረት) አላገኘውምና ሽቱ መቀባት አያስፈልገኝም እያላት ነበር የሚለው አንድ ምክንያት ነው ( መጋቤ ሐዲስ ስቡሕ አዳምጤ ገጽ 361) ። አንድምታ ትርጓሜ ደግሞ ገና ያላመነችበት መሆኑን በመግለጥ የሃይማኖቷን ጉድለት "አትንኪኝ" ለመባሏ አንድ ምክንያት ያደርጋል፤ ማርያም መነሣቱን አላመነችም ነበርና አትንኪኝ አላት፤ አትንኪኝ ብሎ የከለከለበት ሁለተኛ ምክንያት ይህ ነው። ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ የጌታ ሥጋ ከትንሣኤ በፊት ቀድሞ እንደ ነበረው ሁኔታ የማይቀጥል መሆኑን ያስረዳል። አሁን ላይ የጌታ ሥጋ የትንሣኤ ሥጋ ነው፤ የትንሣኤ ሥጋ ደግሞ የከበረ ሥጋ (ሥጋ ስብሐት) ይባላል "ዘይሔድስ ሥጋነ ትሑተ ወይሬስዮ አምሳለ ሥጋ ስብሐቲሁ" እንዳለው (ፊል. 3፥21) ። "The Orthodox Study Bible" የተባለው ከማጥኛ ጽሑፍ ጋር የተዘጋጀ መጽሐፍ የሚከተለውን ጽፏል። "Christ does not prohibit the touching of His resurrected flesh , for we commune with His flesh in the Eucharist, and He even commands Tomas to touch Him (John 20:27) . Here, Christ is instructing Mary to understand and accept that His life is not merely continuing in the same state as before and that He will not remain with her as He did in the past,but is pressing forward to His ascension to the Father." (page 1405) ትርጉሙም "ከሙታን ተለይቶ የተነሣ አካሉን መንካትን ክርስቶስ አልከለከለም፤ ሥጋ ወደሙን በመቀበል ከእርሱ ሥጋ ጋር አንድ እንሆናለንና፤ ቶማስንም እንዲነካው አዝዞታል (ዮሐ.20፥27) ፤ በዚህ ስፍራ ክርስቶስ ለማርያም እያስተማራት ያለው ወደ አብ ለማረግ ይፈጥናል እንጂ ሕይወቱ በቀድሞው ሁኔታ ብቻ እንደማይቀጥል፣ ከዚህ ቀደም እንደነበረውም ከእርሷ ጋር እንደማይኖር እንድትረዳና እንድትቀበል ነው።" ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ይህን የሚደግፍ ቃል ተናሯል፤ "He did not want anyone to touch Him in order to show that this body was (already) glorified and magnified." ትርጉም "ይህ አካል በትንሣኤ ፈጽሞ የከበረ መሆኑን ለማመልከት ማንኛውም ሰው እንዲነካው አልፈቀደም" (Ancient Christian commentary, New Testament IVb, page 349) ከትንሣኤው በፊት ሁሉንም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመጥራት ከጻድቃንም ከኀጥኣንም ጋር ኖረ፤ በላ ጠጣም፤ ከትንሣኤው በኋላ ግን ያመኑበት ብቻ በእምነት የሚነኩት (በእምነት የሚያገኙትና የሚያዩት) እንጂ ሁሉም ሰው የማያገኘው እንደሆነ ያስረዳል። ምክንያቶቹ ምንም ይሁኑ የዚህ ዐሳብ ዋና ነገር እንዳትነካው ከለከላት የሚል ነው። ነገር ግን በሌላ ጊዜ ሴቶች እግሩን ይዘው ስለሰገዱለትና ቶማስም ስለነካው አትንኪኝ በማለቱ ፈጽሞ እንዳትነካው ከለከላት ለማለት አስቸጋሪ ይሆናል። ከዚህ አንጻር በሁለተኛነት የሚቀርበውን ዐሳብ መመርመሩ ጠቃሚ ነው።
8324Loading...
18
#አግብኦተ_ግብር ፤ #ዳግማይ_ትንሣኤ "ጊዜው ደረሰ" ዮሐ 17÷1 #ዳግማይ_ትንሣኤ ለሐዋርያት በጉባኤ ለሁለተኛ ጊዜ ቶማስ ባለበት የተገለጠበት ቀን ስለሆነ ዳግማይ ይባላል እንጂ ትንሣኤው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ #አግብኦተ_ግብር ዳግማይ ትንሣኤ ከመባሉ በተጨማሪ በሊቃውንት ምሥጢራዊ አጠራር "አግብኦተ ግብር" ይባላል፤ ቀጥታ ትርጉሙ "ሥራን መመለስ" ማለት ነው፤ ምሥጢሩ ግን "ግብረ ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ" ብሎ እንዲያመጣው እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነበትን ሥጋ የለበሰበትን ዓላማ በመስቀል የሚያጠናቅቅበት ጊዜው መድረሱን የሚያሳይ ነው፤መስቀሉ ላይ "ተፈጸመ ኩሉ" ብሎ መጮኹም የዚሁ የመጨረሻ ክፍል ነው፡፡ በዳግማይ ትንሣኤ ዕለት ጠዋት ከቅዳሴ በኋላ የዮሐንሰ ወንጌል 17÷1-ፍጻሜ ድረስ ሙሉው ይነበባል፡፡ በዓሉ የጸሎተ ሐሙስ ሲሆን በዕለቱ ብዙ የተደራረቡ በዓላት በመኖራቸው ምክንያት "አግብኦተ ግብሩ" ከዳግማይ ትንሣኤ ተደርቦ ይታሰባል፡፡ የዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ 17 ሙሉው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸሎት ነው፡፡ ይህም ጸሎቱ እንደ ብሉዩ ሊቀ ካህናት የኃጢአት መሥዋዕትን ተክቶ የቀረበ ጸሎት ነው፤ የብሉይ ኪዳኑ የካህናት አለቃ ለሕዝቡ የኃጢአት ሥርዬት የሚሆነውን መሥዋዕት ከማቅረቡ አስቀድሞ እሱ ራሱ ኃጢአተኛ ነውና ፤ ስለኃጢአቱ ስለ ጥንተ አብሶው ለራሱ መሥዋዕት ያቀርባል፤ ከዚያ በኋላ ስለ ሕዝቡ ሥርዬተ ኃጢአት የሚሆነውን መሥዋዕት አርዶ አወራርዶ ፤ደሙን ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባል፤ስለ ሕዝቡ ኃጢአትም ይለምናል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ምንም እንኳን ኃጢአት ባይኖርበትም ነገር ግን ሕግን ለመፈጸም ነውና የመጣው እንደ ብሉዩ ሥርዓት ኃጢአት ሳይኖርበት ወይም ኃጢአተኛ ሳይሆን የኃጢአት መሥዋዕት ያቀርባል ፤ ይህም ያለ ኃጢአት የሚቀርበው ጸሎቱና መሥዋዕቱ የሁሉ ነገር መዝጊያና ማብቂያ ነው፤ የአዳምና የልጆቹ የነቢያት እንባቸው ፤ኀዘናቸውና ትካዜያቸው ማብቂያ የሚያገኘው በጌታ እንባ፤ኀዘንና ትካዜ ነው፤ጸሎታቸው የሚታተመው በጌታ እንባ ጸሎት ነው፤የካህናቱ መሥዋዕታቸውና አገልግሎታቸው የሚታተመው በጌታ አገልግሎትና መሥዋዕት ነው፤ በአጠቃላይም የብሉይ ኪዳኑ አስተምሕሮ የሚጠናቀቀው በጌታ አስተምሕሮ ነው፡፡ የነቢያት አስተምሕሮ "በዘመንየኑ ትፌኑ ወልደከ…."፤ "አንሥእ ኃይለከ ፤ፈኑ እዴከ፤ኢትዝክር ለነ አበሳነ ዘትካት፤ወነዓ አድኅነነ፣ ፍጡነ ይርከበ ሣህልከ እግዚኦ፤እስመ ተመንደብነ ፈድፋደ፤አድኅነነ ወባልሐነ……" (መዝ 78÷8) እያሉ ነበር፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን "ጊዜው ደርሷል" ብሎ ነው የሚጀምረው ይኸውም የመዳን ዘመን ምሕረት የተደረገበት ዓመት መሆኑን ለማጠየቅ ነው “ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤” — ገላትያ 4፥4 አምላካችን ለሁላችንም ምሕረቱን ቸርነቱን አያጉድልብን #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
9524Loading...
19
#ዳግም_ትንሳኤ ዳግም ትንሣኤ ፣ክርስቶስ በልበ ቶማስ የተነሳበት ወይም ቶማስ የክርስቶስን መነሳት ጎኑን በመዳሰስ ያረጋገጠበት ቀን ነው እንኳን ለዳግም ትንሣኤ አደረሳችሁ በዋናው ትንሣኤ ሳምንት የምትመጣዋ ዕለተ እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብላ ትዘከራለች፡፡ ከላይ እንደ ተጠቀሰው ጌታችን በትንሣኤው ዕለት ማታ በዝግ በር ገብቶ፣ በቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ተገኝቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡ በኋላ ከሔደበት ሲመጣ ጌታችን እንደ ተነሣ እና እንደ ተገለጸላቸው ሐዋርያት በደስታ ሲነግሩት ‹‹ እናንተ ‹አየን› ብላችሁ ስትመሰክሩ፤ ስታስተምሩ፤ እኔ ግን ‹ሰምቼአለሁ› ብዬ ልመሰክር፤ ላስተምር? አይኾንም፡፡ እኔም ካላየሁ አላምንም›› አለ፡፡ ስለዚህም የሰውን ዅሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው የወዳጆቹን የልብ ዐሳብ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ልክ እንደ መጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በተዘጋ ቤት በአንድነት ተሰባስበው እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት በመካከላቸው ቆመ፡፡ ቶማስንም ‹‹ያመንህ እንጂ ተጠራጣሪ አትኹን፤ እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ፤›› ብሎ አሳየው፡፡ እርሱም ምልክቱን በማየቱ፣ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደ ፍላጎቱ በመረዳቱ ‹‹ጌታዬ፣ አምላኬ ብሎ መስክሮ›› የክርስቶስን ትንሣኤ አመነ፡፡ የሳምንቷ ዕለተ ሰንበት፣ የትንሣኤው ምሥጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት በመኾኑ የትንሣኤው ሳምንት እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብሎ ይጠራል፤ ይከበራል (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡ ብርሃነ ትንሣኤውን የገለጸልን አምላካችን ለብርሃነ ዕርገቱም በሰላም ያድርሰን!
7876Loading...
20
#ዛሬም_የሴቶች_ቀን_ይከበራል! የዛሬው ዕለት #ቅዱሳት_አንስት ወይም #አንስት_አንከራ ተብሎ ይጠራል 👉"አንስት አንከራ ትንሣኤሁ ነገራ" እንዲል ቅዱስ ያሬድ ፤ ሴቶች አደነቁ ትንሣኤውን ተናገሩ ማለት ነው ለጊዜው የጌታን ትንሣኤ ያበሠሩ ሴቶች መታሰቢያ ቢሆንም ፍጻሜው ግን ለክርስቲያን ሴቶች ሁሉ መታሰቢያ ቀን ነው። ዛሬም ብሥራተ ትንሣኤውን በዝማሬ በምስጋና በማስቀደስ በመቁረብ በሚዲያ በቃል በተግባር በማብላት በማጠጣት በማስተናገድ በጸሎት....በልዩ ልዩ አገልግሎት የሚፋጠኑ የሚመሰክሩ ሴቶች "ቅዱሳት አንስት" ይባላሉ (የተለዩ የተመረጡ የጸኑ ማለት ነው)። እግዚአብሔር እናቶችንና እህቶችን ይጠብቅልን!
8543Loading...
21
#ዕለተ_ዓርብ_ቅድስት_ቤተ_ክርስቲያን! በዕለተ ዓርብ ቀራንዮ ላይ የተወለደችው ቤተ ክርስቲያን ዛሬ በትንሣኤ ዓርብ መተሰቢያዋ ነው አዳም በዕለተ ዓርብ በመተኛትና በመንቃት ሰመመን ውስጥ ሆኖ ሳለ ሔዋን ከጎኑ እንደተፈጠረች ሁሉ ዳግማዊ አዳም ክርስቶስም በማዕከለ ሕይወት ወሞት ብዙ ጸዋትወ መከራ እንቅልፍ ላይ ሆኖ የፍጥረት ሁሉ መንፈሳዊት እናት የምትሆን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሰጠን። ቤተ ክርስቲያን የተወለደችው ቀራንዮ ላይ ስለሆነ በመከራ የታጀበ ጠባይ ነው ያላት ክርስቶስ ሲሰቀል በራሱ ላይ የእሾህ አክሊል፣ በጎኑ ጦር፣ በእግሮቹና በእግሮቹ ላይ ችንካር ነበር ይሄም ቤተ ክርሴቲያን በጉዞዋ ሁሉ መከራ እንደማይለያት ያሳያል ጠቢቡ ሰሎሞንም "ጽጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት ወከመ ጽጌ ደንጎላት በማእከለ አሥዋክ" በእሾህ መካከል የበቀለችና በበርሃ ውስጥ ያለች የሱፍ አበባ ብሎ ገልጿታል መኃ 2:1 የሱፍ አበባ ድርቅ አያጠቃውም በርሃ አያጠወልገውም ይህም ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን መከራ ጌጧና ውበቷ መሆኑን ያሳያል። እንኳን አደረሳችሁ
1 0061Loading...
22
Media files
8430Loading...
23
Media files
8520Loading...
24
©ተወለደችልን        ጥራዝ3.ቁ.91 ተወለደችልን ድንግል ማርያም የነቢያት ትንቢት ሕይወተ አዳም/፪/ ሐናና ኢያቄም በጸሎት ሲተጉ የአምላክን ስጦታ ፀንተው ሲፈልጉ በሕግ በሥርዓት ሆነው ሲማልዱ የፀሓይን እናት ሰማይን ወለዱ አባቶች ነቢያት ያደረጓት ተስፋ ምልክት የሆነች በሞት እንዳንጠፋ የቀረችልን ዘር የአምላክ መገኛ የሕይወት ውሃ ምንጭ ተወለደች ለእኛ የጥል ምክንያት ብትሆን ሔዋን በድንግል መወለድ እርቅ ሆነልን ለአዳም ዘር ኹሉ መድኃኒት ናትና እናቱን የሰጠን ይድረሰው ምስጋና
1 0843Loading...
25
የጨለማው ዓለም ብርሃን የሕይወት መሠረት የአበው ተስፋ የድህነታችን ምክንያት ለሆነችው ለድንግል ማርያም በዓለ ልደት ዋዜማ እንኳን አደረሳችሁ መተርጉማን ሊቃውንት በነገረ ማርያም ሚካኤል መልአክ በክነፍ ጾራ መንጦላዕተ ደመና ሰወራ ንጽህት በድንግልና አልባቲ ሙስና ወልድ ተወልደ እምኔሃ ቅዱስ ያሬድ በጥንተ ፍጥረት በቅዱስ ሚካኤል ክንፍ ላይ እመቤታችንን ስሎ ለመላእክት አሳያቸው እያዩአት ያንጊዜ በብርሃን መጋረጃ ተሰወረች ሲመለከቱዋት ነውር እንከን የለባትም መላእክት እጅግ ተደነቁ የመላእክት ጥያቄ ቅዱሳን መላእክት እግዚአብሔር ሆይ ይችን ቅድስት ፍጥረት በስዕል ብቻ አታስቀራት ፍጠራትና እንያት ብለው ጠይቀውታል እመቤታችን ከተወለደች በኋላም መላእክት አንድ ሰከንድ አልተለዩአትም ቅዱስ ያሬድ እንዘ ትትናዘዚ እም ሀበ መላእክት ይላል መላእክት እያነጋገሪሽ እያጫወቱሽ ማለት ነው መላእክት ለእመቤታችን እህት ወንድም ቤተሰብ ናቸው አደራ እናንተ እኮ ርህራሄ የላችሁም በመላእክት ጥያቄ ነው የተፈጠረችው እንዳትሉ ምስጢራዊ ትርጉሙን ነው የምነግራችሁ እግዚአብሔር እመቤታችን ከመፈጠሯ በፊት በስዕል ለቅዱሳን መላእክት ማሳየቱን እነሱም ለማየት መጓጓታቸውን ነው የሚያሳየው ሌላው እግዚአብሔር ለቅዱሳን ወዳጆቹ ምንም የሚሰውራቸው እንደሌለ ያሳያል ዘፍጥ 18:17: እግዚአብሔርም አለ፦ እኔ የማደርገውን ከአብርሃም እሰውራለሁን? እንዳለ ሰው ሲሆን ቅድሚያ ለነቢያት ምስጢረ ስጋዌን ገልጾላቸዋል ለነቢያት የተናገረው እውን መሆኑን በመላእክት አብስሯል ከዚህ ተንስተው የቤተክርስቲያን ሊቃውንት በዓለ ልደትዋን ሲያከብሩ ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም እም ሐና ወኢያቄም ከመ ትቤዙ ነቢያተ ጻድቃነ ይላሉ ይህ ማለት የነቢያት ትንቢት ትክክል እንደ ነበረ እና ምንም እንኳ ቅዱሳን ቢሆኑ ነቢያትም ጻድቃን በመንጸፈ ደይን ወድቀው ነበርና ነቢያትንና ጻድቃን ከመንጸፈ ደይን ለማዳን ከሐና እና ከኢያቄም በእመቤታችን መወለድ ዛሬ ታላቅ ደስታ ሆነ ብለው በዜማ ያመሰጥሩታል የእናታችን በረከት ይደርብን ድንግል ማርያም ልደትሽ ልደታችን ነው አማላጅነትሽ የእናትነትሽ በረከት ከሁላችንም ጋር ይሁን! #አባ_ገብረ_ማርያም #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
6121Loading...
26
#ልደታ_ለማርያም  ሰላም ለልደትኪ እማኀፀነ ድክምት ሥጋ ድኅረ ኀለፋ ውርዙት ወድኅረ ትክቶ ኃደጋ #የግንቦት_ልደታ_ለማርያም_ክብረ_በዓልና_የእመቤታችን_በዓላት በቀደመዉ ዘመን በዘመነ ብሉይ ‹‹የቤተ መቅደስ መታደስ በዓል›› ይከበር እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል፡፡ ይህ በዓል እስከ ጌታችን ዘመንም ይከበር ነበር፡፡ ዮሐ፡10፥22 በሐዲስ ኪዳን እውነተኛ የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤተ መቅደስ ለሆነችዉ እመቤታችን በስሟ በዓል ሊደረግላት ይገባል፤ ‹‹የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል›› እንዳለ ቅዱስ ዳዊት መዝ፡111፥7 በተአምረ ማርያም ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠዉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 33ት በዓላት አሏት፡፡ ከእነዚህ በዓላት ሁሉ አስበልጣ የምትወደዉ በዓለ ልደቷን እንደሆነ በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት ከዐረብኛ ወደ ግእዝ በተተረጎመዉ እመቤታችን በተለያዩ ሀገራት ያደረገቻችዉን ገቢረ ተአምራት በኢትዮጵያ ከተፈጸሙት ጋር አካቶ የያዘው ተአምረ ማርያም በዝርዝር ያስረዳል፡፡ #ልደቷ_መጽሐፍ_ቅዱስ_ላይ_ከሌለ_ተቀባይነት_እንዴት_ይኖረዋል? በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተካተቱና ምሉዕነት የሌላቸዉ ታሪኮች በአዋልደ መጻሕፍት እንደሚሟሉ ራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል ለምሳሌ ስለ ቅዱስ ዳዊት የሚናገረዉ መጽሐፈ ዜና መዋዕል ‹‹የንጉሡም የዳዊት የፊተኛዉና የኋለኛዉ ነገር በነቢዩ በናታን ታሪክ እንዲሁም በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ላይ ተጽፏል›› ይላል፡፡ 1ኛ ዜና 29፥29 #የእመቤታችን_የልደቷ_ታሪክ የእመቤታችን ወላጆች በአብዛኛዉ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ዮአኪን/ኢያቄም እና ሐና በሚለዉ ስም የሚጠሩ ሲሆን ሐና በቤተልሔም ተወልዳ እንዳደገች ታሪክ ያስረዳል፡፡ በናዝሬት ገሊላ ለመሥዋዕት የሚሆኑ በጎች የሚያቀርብ እንዲሁም እረኛ የነበረዉን ኢያቄምንም አግብታለች፡፡ ቅድስት ሐና ወደ ቤተ መቅደስ ስትሔድ ርግብን ዐይታ ታለቅስ ነበር፡፡ ከብዙ ልመና በኋላ ቅድስት ድንግል ማርያምን ግንቦት አንድ ቀን በደብረ ሊባኖስ ወልደዋል፡፡ ስለ ሐና መካንነት ወደ ቤተ መቅደስ ሄደዉ መባዕ ሲያቀርቡ ካህኑ ያልተቀበላቸዉ መሆኑን በብሥራተ መልአክ ልጅ እንደሚወልዱ እንደተነገራቸዉ በእኛ ቤተ ክርስቲያን የሚተረከዉና በሌሎች ኦርቶዶክሳዊያን አብያተ ክርስቲያናት የሚነገረዉ ታሪክ ተመሳሳይ ነዉ፡፡ #እመቤታችን_የት_ተወለደች? እመቤታችን ስለተወለደችበት ስፍራ በዓለም የተለያዩ ሐሳቦች ይስተጋባሉ፡፡ ሌላዉ ቀርቶ በዶግማ አንድነት ባላቸዉ አኃት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ በእንዲህ ዓይነት ታሪክ ነክ ጉዳዮች ላይ ልዩነት መኖራቸዉ የተለመደ ክስተት ነዉ፡፡ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ሐሳቦች የሚያነሱ ሲሆን፤ አንደኛዉ ‹‹ድንግል ማርያም ብስራተ መልአክ በሰማችበት ናዝሬት ተወልዳለች›› የሚል ነዉ፡፡ ሁለተኛዉ ሐሳብ ደግሞ ‹‹ከሦስተኛዉ ክ/ዘመን ወዲህ የማርያም መግቢያ ተብሎ በሚታወቀዉ ከኢየሩሳሌም የቅድስት ሐና የክሩሲድ ቤተ ክርስቲያን በታች ነዉ የተወለደችዉ የሚል ነዉ፡፡ የግብጽ ስንክሳር የእመቤታችን የትዉልድ ስፍራ በናዝሬት ነዉ ይላል፡፡ የኢትዮጵያ ስንክሳር ግን በቀደምትነታቸዉ ተጠብቀዉ የቆዩ ከመሆናቸዉ አንጻር ተአማኒነታቸዉ የጎላ መሆኑን ያሳያል፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት የእመቤታችን የትዉልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለዉ ተራራማ ሀገር ነዉ፡፡ ሊባኖስ ከገሊላ በስተ ሰሜንና ከፊንቄ በስተምስራቅ ይገኛል፡፡ ‹‹ሙሽራየ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ›› መኃ፡4፥7 የሚለዉ ቃለ ትንቢት ምሥጢርም የአመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ ስለመሆኑ የሚያጠይቅ እንደሆነ ምስክርነታቸዉ የታመነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃዉንት ያስረዳሉ፡፡ #የልደታ_ለማርያም_በዓል_መቸ_ነዉ? እንደተወለደችበት ሥፍራ የእመቤታችን የልደት ቀን እንዲሁ አወዛጋቢ ነዉ፡፡ በ6ኛዉ እና 7ኛዉ መቶ/ክ/ዘመን ነዉ የሚሉ የተለያዩ ሓሳቦች የተጻፉ ሲሆን Encyclopaedic of Christian antiquities ደግሞ በ431 ዓ/ም ከተካሄደዉና ንስጥሮስ ከተወገዘበት ከጉባኤ ኤፌሶን በኋላ ነዉ ይላል፡፡ በዓለም ቅዱሳንን የሚያከብሩ አብያተ ክርስቲያናት የቅዱሳንን በዓለ እረፍታቸዉን የሚያከብሩ ሲሆን ልደታቸዉ የሚከበረዉም በሦስተኛ ደረጃ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ፤ በሁለተኛ ደረጃ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ነዉ፡፡ በአንደኛ ደረጃ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባዉና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ነዉ፡፡ የአመቤታችን ልደት በምዕራባዊያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ በልዩ ክብር ያከብራሉ፡፡ #የድንግል_ማርያም_ልደት_ለምን_ይከበራል? ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ልደት በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል አንደበት ‹‹በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል›› በማለት ተነግሯል ሉቃ፡1-14፤ ምክንያቱም ቅዱስ ዮሐንስ የጌታ መንገድ ጠራጊ፣ የአዋጅ ነጋሪ በመሆኑ ነዉ፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ መወለድ ለብዙዎች ደስታ ምክንያት ከሆነ፤ የድንግል ማርያም ልደትማ ምንኛ የሚያስደስት ይሆን!? ስለሆነም ከጌታ ቀን ቀጥሎ የምንደሰትበት ትልቁ ቀን የእርሷ የልደት ቀን ነዉ፡፡ የቀርጤሱ ቅዱስ እንድርያስ ስለ ከበረ ልደቷ እንዲህ ብሏል ‹‹ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምሳሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌዉ በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነዉ፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነዉ፡፡››ብሏል እመቤታችን  ለፀሐዩ መምጣት የተዘረጋች ሰማይ፤ በቅድመ አያቶቿ በነ ቴክታና ጰጥሪቃ ሕልም እንደታየችዉ በሌሊት የምታበራ ጨረቃ፤ የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰዉ ልጅ ሁሉ ደስታ ነዉ፡፡ ነቢያት በብዙ ሕብረ አምሳል የተናገሩላት ‹‹መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራራዎች ናቸዉ››፤ ‹‹ከእሴይ ስር በትር ትወጣለች አበባዋም ከግንዱ ይወጣል››፤ ‹‹ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ነይ››፤ …. ብለዉ የተናገሩላት ቅድስት ድንግል ማርያም ልደቷ የትንቢታቸዉ ፍፃሜ ነዉና ታላቅ ደስታቸዉ ደስታችንም ነዉ፡፡ መዝ፡86፥1፣ ኢሳ፡11፥1፣ መኃ፡4፥7 በዓለም ላይ የብዙ ታዋቂ ሰዎች ልደት ከሞቱም በኋላም ጭምር በታላቅ ድምቀት ይከበራል፤ ታዋቂ ያልሆኑ ሰዎች ልደትም እንዲሁ ይታሰባል፡፡ ለሰዉ ልጅ መዳን ምክንያት የሆነች የአምላክ እናት የተወለደችበት ቀን ግን ምንኛ ሊከበር ይገባዉ ይሆን! #የግንቦት_ልደታ_በዓል_አከባበር ሐናና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር  እመቤታችንን ወለዱ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ ይኼንን ትዉፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ ሆኖም ግን በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መሃል መርዝን ከሚጨምርባቸዉ መንፈሳውያት በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ የእመቤታችን በዓል ነዉ፡፡ አንዳንዶች በድፍረት ለአድባር ለዉጋር ነዉ ፣ቆሌዉን ለመለመን ነዉ፣ እያሉ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ፈንድሻ የሚጥሉ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቂቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ አሉ ደግሞም በዘፈን እና በሥካርም ጭምር እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች እና በደለኞች ናቸዉ ከእንደዚህ አይነቱ አከባበር ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡
7606Loading...
27
« ስለ ቅዱስ ዮሐንስ በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል ››(ሉቃ 1፥ 14) ከተባለ እኔስ ጫማውን ልሸከም የማልችል ነኝ ብሎ የመሰከረለትን ጌታን የምታስገኝ የድንግል ማርያም ልደት ምንኛ የሚያስደስት ይሆን ? የነቢያቱ ትንቢት የተፈጸመበት ፣ በነቢያት የታየው ራእይ በገሀድ የተከናወነበት ፣ የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰው ልጆች ሁሉ #ለሕያዋን_ሁሉ ታላቅ የደስታ ቀን ነው ፡፡ እናም እንዲህ እንላለን #ድንግል_ሆይ_የልደትሽ_ቀን_ልደታችን_ነው !!!
8123Loading...
28
Media files
5752Loading...
29
Media files
6101Loading...
30
የትንሣኤ 4ኛዋ ቀን ዕለተ አልዓዛር ተብላለች በዚህም የክርስቶስ አምላክነቱ የተገለጠበት አይሁድ በገቢረ ተአምራት ሕዝብን እየነጠቀብን ነው ብለው ሊገድሉት የተዘጋጁበት ብዙ ሕዝብም በክርስቶስ ያመነበት ጊዜና ሰዓት ነበር በአልዓዛር ሞትም የእግዚአብሔር ክብር መገለጫ የሆነውም ለዚህ ነው ቅዱስ ኤፍሬም ስለ አልዓዛር ትንሣኤ ሲናገር" አምላክ ነህና ገና በሩቅ ሳለህ ለደቀመዛሙርትህ አልዓዛር መሞቱን አውቀህ ነገርሃቸው ከአራት ቀን በኋላም መጥተህ ከአንተ እንከንና ስሕተት ለሚፈልጉት ወዴት አኖራችሁት ብለህ ጠየቅህ በዚህም የተቀበረበትን ቦታ አያውቀውም ብለው ሲያፌዙ አልዓዛር ብለህ ጠርተህ ከመቃብር አስነሥተህ አስደነቅሃቸው መቃብር የምድር አልዓዛር የስንዴ ዘርዕ እንባህ የዝናብና ነጠብጣብ አልዓዛር አልዓዛር ብለህ የጠራህበት ድምፅ የነጎድጓድ ሆኖ ምድር ላይ የተዘራች ስንዴ በነጎድጓድና በዝናም በጠል በቅላና ምድርን ፈልቅቃ እንደምትወጣ አልዓዛርም ከመቃብር ወጣ አንተም አልዓዛርን ከመቃብር ስታሥነሳው ከሞትና ከመቃብር ጋር እየተዋወቅህ ነበር መቃብር ሲኦልና ሞት በአልዓዛር ትንሣኤ አንተን እየለመዱህ ነበር" ብሎ ቅዱስ ኤፍሬም ያደንቃል በሌላም መንገድ አልዓዛርን ከሞት ያስነሣ አምላክ ድንጋዩን አንሱለት መግነዙን ፍቱለት ለምን አለ ሞትን ያህል ነገር ፈንቅሎ ያስነሳ ድንጋዩን እርሱ እንኳን በቀራንዮ መስቀል ላይ ሆኖ መቃብራትን የከፈተ ሙታንን ያስነሣ አለቶችን የሰነጠቀ ጌታ የአልዓዛር መቃብር ላይ የተገጠመን ድንጋይ በቃሉ ማንሣት አልቻለም ነበርን ቢሉ ለእርሱ የማይቻል ሆኖስ አይደለም ነገ ምክንያት የሚፈልጉበት አይሁድ ትንሣኤ አልዓዛር ምትሐት እንዳይመስላቸው የመቃብሩን ድንጋይ ሲፈነቅሉ የሞተው አልዓዛር አካል እየሸተታቸው ድንጋይ አንሥተውለት በኋላ ሲነሣ አይተው እንዲደነቁ ነው። አንድም ድንጋዩና መግነዙ ምሳሌ ስላለው ነው የሞተው አልዓዛር በኃጢያት የወደቁ ሰዎች ሕይወት መቃብሩ ዓለም መቃብሩ ላይ የተገጠመ ድንጋይ ችግር፣ አለማመን ፣ኃጢያት መግነዙ የኃጢያት ድንጋይ የሚያነሱ የምዕመናን መግነዝ ፈቺዎች ጥንቱን ሐዋርያት ዛሬም ካህናት ድንጋዩን ማንሳት የእኛ ድርሻ ከኃጢያት ማሠሪያ ማላቀቅ የካህናት ድርሻ መሆኑን ያስተምር ዘንድ ይህንን አደረገ። አልዓዛር ሞቶ የተቀበረው መጋቢት 17 ቀን ሲሆን ከሞት የተነሣው ደግሞ መጋቢት 20 ቀን ነው ከዚህም በኋላ ከ72 አርድእትና ሐዋርያት ጋር ሆኖ በወንጌል አገልግሎት ብዙ ተጋድሎዎችን ፈጽሟል ቆጵሮስ በተባለች ሀገርም ከትንሣኤ በኋላ ለ40 ዘመን በወንጌል አገልግሎት ተጠምዶ ኖሮ በክብር አርፏል ከሞትና ከመቃብር በኋላ ያገኘውን ዘመን ፍቅረ እግዚአብሔርን እያሰበ በፍጹም ቅድሴና እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘ የተወደደች እድሜውን ፈጽሟል። እኛስ ለሞት ምሳሌ ከሆነ ኃጢአት ተመልሰን ንስሓ ከገባን ከብዙ ነገር ከዳንን በኋላ ዛሬ የተሰጠንን ተጨማሪ ዘመን በምን እያሳለፍነው ይሆን? ተወዳጆች ሆይ ውድ ዘመናችንን ከእግዚአብሔር ጋር በማሳለፍ አልዓዛርን እንምሰለው። #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
8803Loading...
31
Media files
6641Loading...
32
#ቅዱስ_ማርቆስ_ወንጌላዊ ማርቆስ ማለት ንህብ ማለት ነው ፤ ንህብ ከሁሉ እንዲቀስም አስቀድሞ ከከርስቶስ ኋላ ከሐዋርያት ተምሯልና፤ አንበሳ ማለት ነው ። አንበሳ ለላም ጌታው እንደሆነ እንዲሰብረው አምልኮተ ላሕምን ከግብጽ አጥፍቷልና ፤ አንድም ካህን ልኡክ ማለት ነው፣ በዚህች በከበረች ዕለት በሚያዝያ 30 ከ72ቱ አርድዕት አንዱ የሆነ ወንጌላዊ ሐዋርያ ሰማዕት ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የተባለ ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ግብፅ ውስጥ ዐርፏል። ረድኤት እና በረከቱ በሁላችንም ላይ አድሮ ይኑር ። "ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር "     "የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነዉ" መዝ፡ 115፥6
6662Loading...
33
#ቅዱስ_ማርቆስ_ወንጌላዊ በዚህች በከበረች ዕለት በሚያዝያ 30 ከ72ቱ አርድዕት አንዱ የሆነ ወንጌላዊ ሐዋርያ ሰማዕት ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የተባለ ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ግብፅ ውስጥ ዐርፏል። ረድኤት እና በረከቱ በሁላችንም ላይ አድሮ ይኑር ። "ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር "     "የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነዉ" መዝ፡ 115፥6
290Loading...
34
ከትንሳኤ በኃላ ያለው አራተኛዉ ቀን አልዓዛር ተብሎ ተሰይሟል ፡፡ በዚህ ዕለት የማርያምና የማርታ ወንድም የሆነው አልዓዛር ከሞተ አራት ቀን ሆኖት ሳለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት አስነሥቶታል፡፡ #ለትንሣኤ_ክርስቶስ_ምሳሌ_ነው፡፡ ለአይሁድ የአልዓዛር መነሣት ቅናት ፈጥሮባቸዋል፡፡እርሱ ሁሉ ትንሣኤና ሕይወት መሆኑን ገልጦ ይህንን ቀን ለአልዓዛር መታሰቢያ ይሆን ዘንድ አልዓዛር ተብሎ ተሰይሞ ታስቦ ይውላል፡፡ዮሐ 11፥1-42 በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን። አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያምና ማርታ ጋር ይኖር ነበር:: ማርያምም ጌታን ሽቱ የቀባችው እግሩንም በጠጕርዋ ያበሰችው ነበረች፤ ወንድምዋም አልዓዛር ታሞ ነበር። ስለዚህ እኅቶቹ ጌታ ሆይ፥ እነሆ የምትወደው ታሟአል ብለው ወደ እርሱ ላኩ። ኢየሱስም ሰምቶ፦ ይህ ህመም የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም አለ። ይህን ተናገረ፤ ከዚህም በኋላ ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፤ ነገር ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ አላቸው። ኢየሱስ በቢታንያ አቅራቢያ ከማርታ ከዚያም ከማርያም ጋር ከተገናኘ በኋላ ወደ አልዓዛር መቃብር አብረው ሄዱ። መቃብሩ ዋሻ ሲሆን መግቢያው በድንጋይ ተዘግቷል። ኢየሱስ “ድንጋዩን አንሱት”አለ። ማርታ፣ ኢየሱስ ምን ሊያደርግ እንዳሰበ ስላልገባት “ጌታ ሆይ፣ አራት ቀን ስለሆነው አሁን ይሸታል”አለች። ኢየሱስ ግን “ካመንሽ የአምላክን ክብር ታያለሽ ብዬ አልነገርኩሽም?”አላት። ስለዚህ ድንጋዩን አነሱት። ከዚያም ኢየሱስ ወደ ሰማይ እየተመለከተ እንዲህ ሲል ጸለየ፦ “አባት ሆይ፣ ስለሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ። እውነት ነው፣ ሁልጊዜ እንደምትሰማኝ አውቃለሁ፤ ይህን ያልኩት ግን እዚህ የቆሙት ሰዎች አንተ እንደላክኸኝ ያምኑ ዘንድ ነው።”ኢየሱስ በሕዝቡ ፊት መጸለዩ፣ ቀጥሎ ከዚያም በታላቅ ድምፅ “አልዓዛር፣ ና ውጣ!”አለ። አልዓዛር እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደተገነዙ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ ተጠምጥሞ ነበር። ኢየሱስም "ፍቱትና ይሂድ”አላቸው። አልዓዛር ማርያም እና ማርታ ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት ማርያምና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል። በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደ ነበር ተገልጧል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ አይደለም። ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደ ነበር ሲነግረን ነው እንጂ። ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን ። #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
6843Loading...
35
Media files
6380Loading...
36
#ዓለም_ቶማስ_ናት ትንሣኤ በዋለ በሶስተኛው ቀን ቶማስ በመባል ይታወቃል ከቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ ቶማስ ክርስቶስ ተነሣ ሲባል ሲሰማ ካላየሁኝ ካልዳሰስኩኝ አላምንም አለ ወዲያውኑ ክርስቶስ መጣ ቶማስ እጁን ሰዶ በጦር የተወጋው ጎኑን እዳስሳለሁ ሲል እንደ ጅማት ተኮማተረ ቶማስ ዋይ አለ አምላኬ ይቅር በለኝ አለ አመነ ዓለምም እንደዚሁ ነች እግዚአብሔር ዓለምን ለማስተማር የሚያደርጋቸውን ተአምራት ላለመቀበል ከቴክኖሎጂ ጋር ያያዙታል ነገሩ ጠንከር እያለ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ሲመጣ ያንጊዜ ሁሉም እጁን ያነሳል የምገድልም የማድንም የምቀስፍም ይቅር የምልም እኔ ነኝ ሲል እግዚአብሔር ዓለም ካላየሁ አላምንም ትላለች በዘመነ ኖኅ የሆነው እሱ ነው ኖኅ የጥፋት ውሃ ይመጣል የምትድኑበትን መርከብ ስሩ ሲል ያመነ የተቀበለው አልነበረም እግዚአብሔርን ያወቁት በፍል ውሃ ሲቀቀሉ ነው ኢየሩሳሌም ትጠፋለች እያለ ነቢዩ ሲናገር እስራኤላውያን እንደሟርት ይቆጥሩት ነበር እስራኤላውያን ማረን ያሉት የነቢዩ ትንቢት ተፈጽሞ ኢየሩሳሌም ከተወረረች ከአራት ዓመት የምርኮ የባርነት ጊዜ በኋላ ነው ዛሬም በእኛ ሕይወት ውስጥ የሚንጸባረቀው ይህ ነው መከራ ችግር ቅጣት ወዘተ ካልገጠመን እግዚአብሔር ያለ አይመስለንም ሁላችንም እግዚአብሔር ሆይ የምንለው የመከራ ቀን ነው ከአህዛብ ነገሥታት አንዱ አቤሜሌክ በመከራ በወደቀ ጊዜ አብርሃምን እባክህ ለእግዚአብሔር ንገርልኝ አስታርቀኝ ብሎአል ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ዓለም በነፈር በኮሮና እንደ በሶ ስትበጠበጥ ዓለም እግዚአብሔር መኖሩን ያወቀው ዓለም ቶማስ ናት የምንለው ለዚህ ነው የትንሣኤው ብርሃን ያሳየን ቸሩ አምላካችን ምስጋና ይድረሰው #አባ_ገብረ_ማርያም
9668Loading...
37
Media files
7340Loading...
38
#የትንሣኤው_ሦስተኛ_ቀን_ቶማስ_ይባላል የትንሣኤ ሦስተኛው ዕለት ቶማስ ይባላል፡፡ ቶማስ ማለት ፀሐይ ማለት ሲሆን ፣ዲዲሞስ ማለት ደሞ መንታ ማለት ነው፡፡ ማመኑ በፀሐይ ፤መጠራጠሩ በመንታነት ይመሰላል፡፡ ቶማስ ሰዱቃዊ ነው ሰዱቃውያን ትንሣኤ ሙታን የለም ብለው ያምናሉ ቶማስም ሰዱቃዊ ስለሆነ ትንሣኤ ሙታንን የማይቀበል የማያምን ሰው ነበር፤ የጌታን ትንሣኤ ለመቀበል የተቸገረው አእምሮውን ገድሎት የነበረው ሰዱቃዊው ሀሳብ ስላልተለየው ነበር፡፡ ይሄ ብቻ ሳይሆን ጌታ አልዓዛርን ለማስነሣት ሐዋርያትን እንሂድ ሲላቸው "ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት። ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ አለ" ይላል ዮሐ 11፡16፡፡ የጌታችንን ከሞት መነሣት እርግጥ ሆኖ ሲያገኘው ግን የሞተው አእምሮው/ሀሳቡ ተነሥቷል ፤ "ጌታዬ አምላኬ" ብሎ ጠርቶ ሕያውነትን ተቀላቅሏል፡፡ "አንሥአኒ በትንሣኤከ፤ በትንሣኤህ አንሣኝ" እንዲል ቅዱስ ያሬድ ቶማስን በትንሣኤው አንሥቶታል፤ ስለዚህ የትንሣኤው 3ኛው ቀን ለቶማስ መታሰቢያ ሆኗል፡፡ ቶማስም ከ 3 ዓመት ትምህርት በኋላ ከጥርጥር ሞቱ ተነሥቷልና። ቶማስ ጠያቂ ነው፤ ያልገባውን ይጠይቃል፤ ማየት የፈለገውን ልየው ይላል፡፡ በዚህም ፍጥረታዊ ወይም ሳይንሳዊ ሰውን ይመስላል፤ ፍጥረታዊ ሰው ተነግሮት አያምንም፤ካልጨበጠ ካልዳሰሰ እውነትነቱን አይቀበልም ፦ " ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም።" እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ 1ኛ ቆሮ 2 : 14፡፡ ቶማስ የጌታችንን ድርጊቶች በጥርጣሬ ይመለከት የነበረ ሐዋርያ ነበር ፡፡ ለምሳሌ ጌታችን አልዓዛርን ለማስነሣት ሲሄድ ደስተኛ አለመሆኑን በሞት ስጋት ገልጾ ነበር፦ "ስለዚህ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት። ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ አለ" በማለት እንደተጻፈ፡፡ ዮሐ 11 : 16፡፡ በሌላ ጊዜም ቶማስ መንገዱን የጠየቀው ለዚህ ነበር፤ ያ መንገድ ወዴትና የት የሚወስድ ነው? የሚል ጥያቄ በውስጡ ይመላለስ ስለ ነበረ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ እንደጻፈው፦ "ቶማስም። ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን? አለው" ዮሐ 14 : 5፡፡ በዚህ ሁሉ ጥያቄውና ጥርጥሩ ግን ጌታችን አንድም ቀን ሰልችቶት ተቆጥቶት ወይም በጥርጣሬ አትከተለኝ ብሎት አያውቅም ፤ ድካማችንን የሚያውቅ የሚሸከምልን አምላክ ነውና፤ ዛሬም ምንም ያህል ኃጢአት ብንሠራ ተጸጽተን በንስሐ ከተከተልነው አትከተሉኝ አይለንም፤ ከየትኛውም ክህደት ከየትኛውም ሃይማኖት ብንመለስ ወደ እውነተኛው ሃይማኖት ከገባን በኀላ አልፈልጋችሁም፡ውጡልኝ አይልም፤ "ወደኔ የመጣውን ወደ ውጪ አላወጣውም "ብሎናልና፤ ዮሐ 13፡32፡፡ ጌታችን ከሞት ከተነሣ በኀላ ለሁሉም ሲገለጥ ለቶማስ ግን አንድ ሳምንት ሙሉ አልተገለጠለትም ነበር፤ ቶማስም ጌታን በአካል ያዩት ሐዋርያት ሲነግሩት፦ • የችንካሩን ምልክት በእጆቹ ካላየሁ • ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ካላገባሁ • እጄንም በጎኑ ካላገባሁ አላምንም" ይላቸው ነበር። ዮሐ 20 : 25፡፡ ጌታችን ይህንን ያደረገበት ምክንያትም፦ 1. ቶማስ በውስጡ መንፈሳዊ ቅናት እንዲያድርበት፤ ሁሉም ስለ ትንሣኤው ሲናገር እየሰማ እንዲጓጓ ነው፤ ይህ መጎምጀት ወደ ፍጹም መንፈሳዊነት ይመራልና፤ እኛም ዛሬ ለመንፈሳዊ ነገር ስንጓጓና ስንቸኩል እግዚአብሔርን እናገኘዋለን፤ በውስጣቸው የሚቀጣጠለው ፍቅረ እግዚአብሔር እርሱን ራሱን ይጠራዋል፤ ቀድሞም ለሞት ያደረሰው ፍቅር ነውና፡፡ 2. ጌታችን የአንዲት ነፍስ ጉዳይ ጉዳዩ እንደሆነ ያጠይቃል፡፡ የተገለጠው ለቶማስ ሲል ነበር ለሱም ሲባልም አስቀድሞ በሌለበት የተገለጠበት ፦ • ዕለት • ሰዓት • ቦታ • በተዘጋ ደጅ መግባቱ • ሰላምታው (ሰላም ለሁላችሁ ይሁን) • ሁኔታው /መልኩ አልተቀየረም፡፡ ቶማስ ባለበት የተገለጠበትና ሳይኖር የተገለጠበት ልዩነት ቢኖረው በመጀመሪያ ቀንና በስምንተኛ ቀን መሆኑ ብቻ ነበር፡፡ ይህም የሚያሳየው ፦ • ለሰው ሁሉ ያለውን ክብር/ፍቅር/ግድ • ትንሣኤው እርግጥ መሆኑን • ፍጹም ቸርነቱን • መጀመሪያ ያዩትም መጨረሻ የሚያዩትም በአንድነት እንደሚወርሱት ያጠይቃል፡፡ የቶማስ የመጨረሻ እምነት፦ "ጌታዬ አምላኬም" ፤ዮሐ 20፡28፡፡ ይህ ቃል የመጨረሻው የእምነት ጥግ ቃል ነው፤ የምናምነው ይህን ነው ፤ የምንናገረው ይህን ነው፤ የምንሰብከው ይህንን ነው፤ ከዓለም የምንለየውም በዚህ ቃል ነው፡፡ ቶማስ ብዙ ቢጠይቅም፤ ቢጠራጠርም በመጨረሻ ግን "አምላኬ" ብሎ አመነ፤ ዛሬ "ኢየሱስን አምላክ " ብለው መጥራት የሚከብዳቸው ብዙዎች ናቸው፤ እኛ እንኳን የቶማስን ቃል የወንጌሉን ፍጥጥ ያለ እውነት ስንናገር ይጠሉናል፡፡ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድላቸው!!! ቶማስ ጌትነቱን አምላክነቱን ያመነው በመዳሰስና በማየት ከሆነ እኛስ ሳናይ እንዴት እናምናለን እንዳንል ጌታችን " ኢየሱስም። ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው" በማለት ወሳኝ መልእክት አስቀምጦልናል፡፡ ዮሐ20 : 29፡፡ ወንጌላዊውም ታሪኩን ሲጠቀልለው፦ " ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል" በማለት ይህን አንብበን፤ ሰምተን ብቻ እንድናምን አስገንዝቦናል፡፡ ዮሐ 20 : 31፡፡ እኛም የቶማስን እጅ እጅ አድርገን ዳሰነዋል የሐዋርያትን ዓይን ዓይን አድርገን አይተነዋል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም "ክብሩን አየን.." እንዳለ አባ ሕርያቆስም " ከእርሱ ጋር በላን ጠጣን.." እንዳለ እኛም እንደ ቶማስ " ጌታችን አምላካችን" እንላለን!!!!! በዚህም እኛ "ብፁዓን ነን"!!! እንድናምነው የረዳን አምላካችን ይመስገን!!!! በበጎ ሥራም ደስ እንድናሰኘው ይርዳን!!! በረከተ ሐዋርያት ይደርብን!!! አሜን!!! #መ_ሐ_ነቅዐጥበብ(ኢ/ር)     #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
7963Loading...
#አነ #ውእቱ #ሩፋኤል #አሐዱ #እምሰብዓቱ #ሊቃነ_መላእክት ከሰባቱ የመላእክት አለቆች አንዱ እኔ ሩፋኤል ነኝ ( መጽ ቀሌምንጦስ) ጌታ በደብረዘይት ደቀመዛሙርቱን ሰብስቦ ጉባኤ ዘርግቶ እያሰተማረ ባለበት መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል መጣ ጌታም ስምህን ለደቀመዛሙርቴ ንገራቸው አለው የመጽሐፈ ቀሌምንጦስ ጸሐፊ ያንጊዜ ነው ስሙን እስከትርጓሜው የነገራቸው ይላል በረከቱ ይደርብን የቁስጥንጥንያው ሊቀጳጳስ ካሳነጻቸው ሰባት አቢያተ ክርስቲያናት አንዱ የቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ነው ቤተክርስቲያኑ የታነጸው ደሴት በሚመስለው በአሳ አንበሪው ጀርባ ላይ ስለነበር በቅዱሱ አባት አባ ቴዎፍሎስ ተባርኮ አገልግሎት ሲጀመር አጋጣሚው ተጠቅሞ አሳ አንበሪውን ሰይጣን እንዲናወጥ በማድረግ ሊያጠፋቸው ሲል ያዳናቸው መልአኩ እንደሆነ ድርሳኑ ይናገራል ቤተክርስቲያንዋን እና በውስጥዋ የነበሩትን አገልጋዮች ምዕመናን ከመሰጠም ታድጓቸዋል ዛሬም በውስጥም በውጭም ሁነው እንደ አሳ አንበሪው ቤተክርስቲያንን ከሚያናውጧት አገልጋይ ከሚመስሉ ቁማርተኞች አጋንንት ቤተክርስቲያንን ይታደግልን ቅዱስ ሩፋኤል ሰባት ዓመት ሙሉ እንደተራ ሰው ያገለገለው ከዓይነ ስውርነት የፈወሰው የእግዚአብሔር ሰው ቅዱስ ጦቢያ ስለቅዱስ ሩፋኤል ምልጃና ተራዳኢነት በሰፊው ጽፏል ጦቢያን የፈወሰ የቅዱሳን ባለሟል ቅዱስ ሩፋኤል ሁላችንም በአማላጅነቱ ይጠብቀን ከሚያናውጠን ከእርስ በእርስ የጦርነት ማዕበል ይታደገን! #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

#ግንቦት_12 #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ባሕረ ምስጢራት የሆነ የሰውን ፊት አይቶ የማያደላ "መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ" (በርሱ ዘንድ ንጉሥ፣ ሐብታም፣ ደሃ፣ ነዳይ እኩል ነውና)፣ አፈ በረከት፣ አፈ መዐር (ማር)፣ አፈ ሶከር (ስኳር)፣ አፈ አፈው (ሽቱ)፣ ልሳነ ወርቅ፣ የዓለም ሁሉ መምሕር፣ ርዕሰ ሊቃውንት፣ ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)፣ የሐዲስ ኪዳን ዳንኤል፣ ሊቀ ጳጳሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)፣ ጥዑመ ቃል... እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እረፍቱ ነው። #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ሲናገር በአንድ ወቅት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡ከዕለታት አንድ ቀን በሀገረ ስብከቴ ሥር በነበሩ በሜዲትራኒያን ባሕር በሚገኙ ደሴቶች ውስጥ የሚኖሩ ምእመናንን  ለመጎብኘት አሰብሁ፡፡ ከእኔ ጋር ቀሳውስትንና ዲያቆናትን አስከትዬ በጀልባ ተሳፍሬ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ተጓዝሁ፡፡ በደሴቱ ውስጥ ስንዘዋወር የሰው ዱካ ብንመለከትም  ምንም ሰው ማየት አልቻልንም ነበር፡፡ በአሸዋው ላይ ታትሞ የነበረውን የሰው ዱካ ተከትለን ስንጓዝ ካልተፈለፈሉ ዐለቶች የተሠራ ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ዋሻ ላይ ደረስን፡፡ ዋሻው በርም ሆነ መስኮት የለውም፡፡ ወደ ውስጥ ስንገባ ልክ እንደ ሰባቱ ደማቅ ከዋክብት እጅግ በጣም አንጸባራቂ ብርሃን ቆመው ከሚጸልዩ ሰባት አባቶች ዘንድ ሲወጣ ተመለከትን፡፡ እኛም ከእነርሱ ጋር ለመጸለይ ባለንበት ቆምን። አባቶች ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ ወደ እኛ ዞሩና በፊቴ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ። በመቀጠልም ሰላምታ ሰጡን፡፡ እኔ ዮሐንስም ‘እኔ አባታችሁና ፓትርያርካችሁ ዮሐንስ ነኝ’ አልኳቸው፡፡ ቅዱሳኑ እንደገና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በፊቴ ሰገዱ እና እኔን ደካማውን እንዲህ አሉኝ፡- “የምንወደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትባርከንና እኛም አንተን በማየት እንድንበረታ ወደዚህ አመጣህ” አሉ። እኔም “እባካችሁ ታሪካችሁን ንገሩኝ” አልኋቸው፡፡ ሰባቱ አባቶችም “ከብዙ ዓመታት በፊት ሰባታችንም ከቍስጥንጥንያ ወጥተን በአንድነት ተሰባስበን ሕይወታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና በአምልኮ ብቻ ለማሳለፍ ወደዚህ ደሴት መጣን፡፡ ከዚህ ደሴት በደረስንበት ዕለት ከባሕሩ ከሚመጣው አስቸጋሪ ነፋስ ራሳችንን ለመከላከል ዋሻዎችን ለመገንባት ዐለቶችን ሰበሰብን፤ በሁለተኛው ቀን ደግሞ ይህን ቤተ ክርስቲያን መሥራት ጀመርን፡፡  በዐለቶች መካከል ከሚበቅለው ሣር እንበላለን፤ ውኃም ከባሕሩ እንጠጣለን፡፡ ቤተ ክርስቲያኑን የከበቡትን እነዚህን የአሸዋ ክምሮች ለማስወገድ ፈልገን ነበር፤ ግን አእምሯችንና አሳባችን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ስለተያዘ ጊዜ አጣን” በማለት ታሪካቸውን ነገሩኝ። እኔም “መንፈሳዊ አባታችሁ የት ነው?” ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ ይህን ጥያቄ ከመጠየቄ ወዲያውኑ አንድ ሽማግሌ በትሩን ተደግፎ ወደ እኔ ቀረብ አለና “እኔ የአንተ አገልጋይ ነኝ” አለኝ፡፡ አረጋዊው ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ራቁቱን ነበረና “ሰውነትህን የምትሸፍንበት ትንሽ ልብስ ትፈልጋለህ?” ስለው እሱም “ጌታ ከክረምቱ ቅዝቃዜ፣ ከበጋው ሙቀት ይከላከልልናል፤ ይጠብቀናልም” በማለት መለሰልኝ፡፡ “ምግብ ያስፈልጋችኋል?” ብዬ ስጠይቀው እርሱም “የሚበቃንን ያህል ከእነዚህ ዕፅዋት እንመገባለን ከዓለም የሆነ ምንም ነገር አያስፈልገንም” በማለት መለሰልኝ፡፡ እኔም “አባቶቼ እባካችሁ ለእኔ እና ስለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ጸልዩ” አልሁት። የእነዚያን ቅዱሳን ባሕታውያን አባቶች በረከት ከተቀበልን በኋላ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም ምሥጋና የሚገባውን የምንወደውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እያመሰገንን ወደ መጣንበት ተመለስን” ይለናል ቅዱሱ አባታችን ዮሐንስ አፈ ወርቅ። #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

Photo unavailableShow in Telegram