cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የቅዱሳን ታሪክ

በዚህ ቻናል ውስጥ፦ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብቻ የሚገኙ ስዕላትን የቤተክርስቲያን ትውፊት የጠበቁ ስዕላት የአድባራት እና የገዳማት ፎቶዎችን ያገኛሉ የተለያዩ ስዕለ አድዕኖ ለመላክ @kidanemiherat_bot

Show more
Advertising posts
9 200
Subscribers
+224 hours
+67 days
+5330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሥርዓተ ዑደት ዘሆሣዕና የሚጀምረው በቤተ መቅደስ ነው ዲያቆኑ በመቅደሱ ፈት ለፊት ይህንን ምስባክ ከዳዊት መዝሙር ለዕለቱ የተመደበውን ይዘምራል ምስባክ መዝ ፻፲፯፥፳፮፡፳፯ ብሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር፤ ባረክናክሙ እምቤተ እግዚአብሔር እግዚአብሔር እግዚእ አስተርአየ ለነ ትርጉም በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፤ ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ። እግዚአብሔር አምላክ ነው፥ ለእኛም በራልን፤ እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ የበዓሉን መሥዋዕት በገመድ እሰሩት። ወንጌል ሉቃ ፲፱፥፩ አቡን አርእዩነ ፍኖቶ ሃሌ ሃሌ ሉያ ፣ አርእዩነ ፍኖቶ፣ ወንሑር ቤቶ፣ እስመ እምጽዮን ፣ይወጽእ ሕግ ፣ወቃለ እግዚአብሔር እምኢየሩሳሌም፣ ንሣለማ ለመድኃኒትነ፣ በትፍሥሕት፣ ተቀበልዋ ለታቦት፣ እስመ ዋካ ይእቲ ወብርሃን ምልጣን ንሳለማ ለመድኃኒትነ በትፍሥሕት ተቀበልዋ ለታቦት እስመ ዋካ ይእቲ ወብርሃን ምዕዋድ እስመ ዋካ ይእቲ ወብርሃን ዋካ ይእቲ ወብርሃን ትርጉም ቅድመ ዓለም የነበረ አሁንም ዓለምን አሳልፎ የሚኖረውን የእግዚአብሔርን መንገድ አሳዩን መድኃኒታችን የሆነችውን የርሱን ጎዳና እንከተላት እርሷ ብርሃን ናትና በምዕራብ ምስባክ መዝ ፱፥፲፩ ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘየኀድር ውስተ ጽዮን፣ ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ ። እስመ ተዘከረ ዘይትኃሠሥ ደሞሙ ትርጉም በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ በአሕዛብም መካከል አደራረጉን ንገሩ፤ ደማቸውን የሚመራመር እርሱ አስቦአልና፥ የድሆችንም ጩኸት አልረሳምና። ወንጌል ዘማቴዎስ ማቴ ፳፩፥፩፡፲፯ አቡን ሰመያ አብርሃም ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፣ ሃሌ ሃሌ ሉያ፣ ሃሌ ሃሌ ሉያ፣ሰመያ አብርሃም፣ ወይቤላ፣ ዛቲ ዕለት በዓለ እግዚአብሔር፣ ንፍሑ ቀርነ ፣በዕለተ ሠርቅ፣ በዕምርት ዕለት፣ በዓልነ፣ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን ትርጉም ቅድመ ዓለም የነበረ አሁንም ዓለምን አሳልፎ የሚኖረውን አብርሃም ጠራት እንዲህም አለ ይህች የእግዚአብሔር በዓል ናት መድኃኒታችን የሆነችውን እንሳለማት ቀርነ ምስዋዑን ለምስጋና አዘጋጁ ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ ምልጣን ንፍሑ ቀርነ ፣በዕለተ ሠርቅ፣ በዕምርት ዕለት፣ በዓልነ፣ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን ምዕዋድ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን በደቡብ ምስባክ መዝ.፰፥፪ “እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሓተ፡፡ በእንተ ጸላዒ፡፡ ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ፡፡” ትርጉም “ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ስለ ጠላትህ፥ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።” ወንጌል ማር ፲፩፥፩፡፲፩ አቡን ወትቤ ጽዮን ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፣ ሃሌ ሃሌ ሉያ፣ ሃሌ ሃሌ ሉያ፣ወትቤ ጽዮን፣ አርኅው ሊተ አናቅጸ ፣ይባኡ ሕዝብ ብዙኃን፣ ወያዕትቱ፣ ዕብነ እምፍኖት፣ ለንጉሥ ለወልደ ዳዊት፣ ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ፣ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ምልጣን ወያዕትቱ፣ ዕብነ እምፍኖት፣ ለንጉሥ ለወልደ ዳዊት፣ ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ፣ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ትርጉም ቅድመ ዓለም የነበረ አሁንም ዓለምን አሳልፎ የሚኖረውን ጽዮን እንዲህ አለች በሩን ክፈቱ አለች ከመንገድ ዲንጋዩን ያንከባሉት ንጉሥ ለሆነው ለዳዊት ልጅ የእስራኤል ንጉሥ እርሱ ነው በዓለም ሁሉ መድኃኒት አቤቱ አድን ይላሉ ምዕዋድ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ይብሉ ሆሣዕና በአርያም በምሥራቅ ምስባክ መዝ ፵፱፥፩ እምሥራቀ ፀሐይ እስከነ ዓረብ ይትአኰት ስሙ ለእግዚአብሔር ልዑል እግዚአብሔር መልዕልተ ኵሉ አሕዛብ። ትርጉም “የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ፥ ከፀሓይም መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ምድርን ጠራት።” ወንጌል ሉቃ ፲፱፥፳፰ አቡን ባርኮ ያዕቆብ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ፣ሃሌ ሃሌ ሉያ ፣ሃሌ ሃሌ ሉያ፣ ባረኮ ያዕቆብ፣ ለይሁዳ ወልዱ ወይቤሎ፣ሀሎ ንጉሥ ዘይወጽ እምኔከ ፣ዘየሐጽብ ፣በወይን ልብሶ፣ወበደመ ፣አስካል ሰንዱኖ ፣ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ ፣ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ምልጣን ዘየሐጽብ ፣በወይን ልብሶ፣ወበደመ ፣አስካል ሰንዱኖ ፣ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ፣ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ምዕዋድ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ትርጉም ቅድመ ዓለም የነበረ አሁንም ዓለምን አሳልፎ የሚኖረውን ያዕቆብ ልጁን ያዕቆብን ባረከው እንዲህም አለው ካንተ የሚወለድ የሚወጣ ንጉሥ አለ ልብሱን የሚያጥብ መጎናጸፊያውንም በደም የሚያጥብ ይህ የእስራኤል ንጉሥ ነው ይላሉ አቤቱ አሁን አድን በሰሜን ምስባክ መዝ.፹÷፫ ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ በእምርት ዕለት በዓልነ እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ ትርጉም “ለእስራኤል ሥርዓቱ ነውና፥ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ።” ወንጌል ዮሐ ፲፪፥፲፪፡፲፱ አቡን ባኡ ውስተ ሀገር ሃሌ ሃሌ ሉያ ባኡ ውስተ ሀገር ወበዊአክሙ ትረክቡ ዕዋላ አድግ እሱረ ፍትህዎ ወአምጽእዎ ሊተ። ምልጣን ፍትህዎ ወአምጽእዎ ሊተ።ፍትህዎ ወአምጽእዎ ሊተ። ትርጉም ቅድመ ዓለም የነበረ አሁንም ዓለምን አሳልፎ የሚኖረውን ወደ አንዲት ሀገር ግቡ ገብታችሁም የታሰረ አህያ ታገኛላችሁ ፈታችሁ አምጡልኝ ምዕዋድ ፍትህዎ ወአምጽእዎ ሊተ ፍትህዎ ወአምጽእዎ ሊተ። ካህናት ወደቤተ መቅደስ ሲመለሱ አቡን ሃሌ ሉያ አልጺቆ ኢየሱስ ኢየሩሳሌም ርእያ ለሀገር፤ ወይቤላ ሶበ ተአምሪ ጽዮን ነዋ ንጉሥኪ በጽሐ ብርሃነኪ ዮም ሰላምኪ። ምልጣን ወይቤላ ሶበ ተአምሪ ጽዮን ነዋ ንጉሥኪ በጽሐ ብርሃነኪ ዮም ሰላምኪ በሕዝብኪ ዮም ሰላምኪ ይትሐፈሩ ጸላእትኪ ዮም ሰላምኪ፤ሰላምኪ ሰላምኪ ዮም ሰላምኪ ትርጉም ቅድመ ዓለም የነበረ አሁንም ዓለምን አሳልፎ የሚኖረውን ኢየሱስ ክርስቶስ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ሀገሪቱን አያትና አለቀሰላት ኢየሩሳሌም ሆይ ብታውቂ ሰላምሽ ዛሬ ነበረ ብርሃንሽ ደርሶ ነበረ አላት
Show all...
#ተጽዒኖ <<ተጽዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሤት ይሁቦሙ ኃይለ ወስልጣነ።>> ጾመ ድጓ ዘሆሳዕና በዓለ ሆሣዕና ሳይደርስ አስቀድሞ በረቡዐ ኒቆዲሞስ ሆሣዕናን ማንሳቱ ስለምን ነው ቢሉ ኢየሱስ መጋቢት ፲፰ ቀን ረቡዕ ዕለት ሁለት ደቀ መዛሙርቱን በመንደር ላይ የታሰረች አህያ ታገኛላችሁ ፈትታችሁ አምጡልኝ ማን አላችሁ የሚላችሁ ቢኖር ጌታዋ ይፈልጋታል በሉ ያለበት ቀን ነው ማቴ.፳፩፣፩፤ሉቃ.፲፱፣ ፴፬:: በ፫ኛው ቀን መጋቢት ፳ ቀን ምሕላ ሆሣዕና አድርጎ ዲበ ዕዋል እየተባለ በጸናጽል መታወዱ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መጋቢት ፳፪ ቀን በመጣለት አህያ ተቀምጦ ቤተ መቅደሱን ሲያውድ አዕሩግና ሕፃናት ተከትለው ሆሣዕና በዓርያም እያሉ በቃለ ቀርን እያመሰገኑ ማወዳቸውን አስቀድሞ ለህዝበ ክርስቲያኑ ማብሰር ማወጅ መንገር ማለት ነው ስለምን በፈረስ በበቅሎ ሳይሰቀል በአህያ ተሰቀለ ቢሉ አህያ መከራ ቻይ ናት የደረሰው ሁሉ ይደበድባታል ሩጣም አታመልጥም እኔም በዕለተ ዓርብ መከራን እቀበላለሁ የደረሰው ሁሉ ይደበድበኛል አንድም አህያ ከጫንቃዋ ላይ መስቀልኛ አለባት በዕለተ ዓርብ በመስቀል ላይ እሰቀላለሁ ሲል ነው፡፡ ማቴ 21፥1፤ሉቃ 19፥29 ሰሙነ ሕማማትን በቤተ ክርስቲያን አሳልፉ በቻናላችን የምንገናኘዉ በትንሳዔ ይሆናል መልካም የስግደት፤ የጸሎት ሳምንት ያድርግልን።
Show all...
Show all...
♦️ቀጥታ♦️በካራ ቆሬ ደብረ ገነት ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን

#ethiopia​ #orthodox​  #natanimtube ተዋህዶ #ethiopian​ orthodox mezmur #Tinsae​ #Fasika​ #Easter​ Ethiopia #ዘኪ​ ቲዩብ #ethiopian​ mezmur #የትንሳኤ​ መዝሙር #ከትንሳኤ​ እስከ ዳግም ትንሳኤ #Dagim​ Tinsae #ከትንሣኤ​ ስብስብ ►የትንሳኤ መዝሙሮች ስብስብ #Mezmur​ ምርጥ መዝሙር , የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር ►Ethiopian Easter 2021 ►Easter mezmur collection ►Yilma Hailu ►Marta Hailesilasie ►Nebiyu samuel ►Chernet Senai ►Hiwot Teferi #ፅዋ_ቲዩብ​​ #TsiwaTube​​ #newmezmur2020​​ #tewahdomezmur​ #orthodoxmezmur​​ #mahtottube​​ #omegatube​​ #aryam​​ #mihretab​​ #mehreteab​ #sibket​​ #gubae​​ #Lideta​​#Bata​​#Yohannis​​#Abuye​​#Abune​​ gebremenfes kidus#Arsema​​#Eyesus​​#silase​​#sositu​​ silasochi# #Aba​​ kiros#estinfase​​ kirstos#hana​​ mariam#abunehara​​# dingil# kidus mikael#mikael​​#melaku​​ mikael#egizhaber​​ abe#ab​​#welde​​#menfes​​ kidus#abune​​ aregawi#qirqos​​#hitsahu​​ kirqos#kidanemihret​​#enate​​#kidane​​ mihret#semaetu​​ estifanos#estifanos​​#kidus​​ gebrial#gebrial​​#melaku​​ gebrial#mariam​​#dingil​​ mariam#deginesh​​#tsiyon​​#tsige​​#soliyan​​#tsadikane​​#urael​​#kidus​​ urael#kidus​​ giorgis#giorgis​​#teklehaimanot​​#aba​​ tekilehaimanot#cherqos​​#kidus​​ qirkos#medihaniyalem​​#amilak​​#eyesus​​#hosahina​​#lemariam​​#amanual​​#bale​​ egizhabiher#yohannis​​#markos​​#ልደታ​​ #ባታ​​ #ዮሃኒስ​​ #አቡዬ​​ #አቡነ​​ ገብረመንፈስ ቅዱስ#አርሴማ​​#ቅድስት​​ አርሴማ#እየሱስ​​#ስላሴ​​#ስላሶች​​፣ሶስቱ ስላሴ#አባ​​ ኪሮስ#እስትንፋሰ​​ ክርስቶስ#ሃና​​ ማርያም#ማርያም​​#አቡነሃራ​​ ድንግል#አቡነ​​ ሐራ#ሚካኤል​​#ቅዱስ​​ ሚካኤል#መላዕኩ​​ ሚካኤል#እግዚሃብሔር​​ አብ#አብ​​#አቡነ​​ አረጋዊ#ኪዳነምህረት​​#እናቴ​​#ኪዳነ​​ ምህረት#ሰማዕቱ​​ እስቲፋኖስ#እስቲፋኖስ​​#መላዕኩ​​ ገብርኤል#ገብርኤል​​#ቅዱስ​​ ገብርኤል#ቅድስት​​ ማርያም#ድንግል​​ ማርያም፣ፂዮን#ሶልያና​​#ፃድቃኔ​​ ማርያም#ዑራኤል​​#ቅዱስ​​ ዑራኤል#መዕላኩ​​ ዑራኤል#ቅዱስ​​ ጊዎርጊስ#ጊዮርጊስ​​#ተክለ​​ ሃይማኖት#አቡነ​​ ተክለሃይማኖት#ቂርቆስ​​#ጨርቆስ​​#መድሃኒያለም​​#አማኑኤል​​#አምላክ​​#ባለእግዚሃብሔር​​#ማርቆስ​​#ዮሐንስ​​#መጥምቀ​​ ዮሐንስ #መስቀል​ አደባባይ #Abel​ Birhanu #Rama​ Tube #Rama​ Media #Rama​ tube # ll ራማ ቲዩብ Zemari Tadewos

+ ኪዳነ ምሕረት + "ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ፦ ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ" ብሎ እንደተናገረ ከብዙዎች ጋር ቃል ኪዳን አለው ። (መዝ ፡89-3) ምድርን ዳግመኛ በንፍር ውኃ ላይመታ ፣ ሥጋ ለባሽንም አንድ ጊዜ ፈጽሞ ላያጠፍ ለኖህ ቃል ኪዳን ገብቷል ። (ዘፍ፡9፥1-17) የምድር አሕዛብ በዘሩ እንዲባረኩ ለአብርሃም ቃልኪዳን ገብቷል ።( ዘፍ ፡22-18 ) ለይስሐቅና ለያዕቆብ ተስፍቸውን ነግሮአቸዋል ። ( ዘፍ፡26-4) ለቅዱስ ዳዊትም ምሎለታል ። (መዝ ፡89-3) የእነዚህ ሁሉ ቅዱሳን ኪዳን ፍፃሜ ያገኘው ግን በአምላክ ሰው መሆን ነው ። #የእመቤታችን ቃል ኪዳን ግን የለየት ያለ ነው ። ለየት የሚለው በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ነው ። የመጀመሪያው እርሷ ምልዕተ ፀጋ መሆኗና ፍጽምት ርኅርኂተ ኅሊና ከመሆኗ የተነሳ ስለሰው ልጅች አብዝታ የማለደችና ክርስቲያኖች ሁሉ ይድኑ ዘንድ ከሌሎች በተለየ የለመነች በመሆኗ ነው ። እንኳን እግዚአብሔር ጨካኙ ዳኛ እንኳን አብዝታ ለለመነችው መበለት ያደረገውን እናውቃለን ። (ሉቃ 18-1-8) ሁለተኛ ምክንያት ደግሞ ወላዲተ አምላክ ለመባል የበቃች ከእርሷ በቀር ሌላ የሌለ በመሆኑ  በዚህም መልዕልተ ፍጡራን ትሆን ዘንድ አምላክ ያከበራት በመሆኗ ልዩ ቃል ኪዳን ይገባላት ዘንድ የተገባት ናት ። ( "በዓላት" ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ገጽ 146-147 ) የኪዳነ ቃሏ እመ ምሕረት ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን።
Show all...
#ኪዳነ_ምህረት_ሆይ እንዲህ እያልሽ ለምኝልኝ « ልጄ ሆይ የኃጢአቱን ቁጥር አታስብ እንደበደሉም አታድርግበት ስለ ኃጢአቱም አትበቀለው በሰውነቱም ቢበድል በገቢርም በሐልዮም ቢሆን ስለ ፍዳ እኔ ጸሎትን ማማለድን እከፍላለሁ ይቅርታህ ያባትህም ቸርነት የመንፈስ ቅዱስም ምሕረት በዘመኑ ሁሉ ባርያህን ይጎብኘው ይርዳው ዘለዓለም » አሜን ።
Show all...
Show all...
TikTok · SADOR SISAY

Check out SADOR SISAY’s video.

"እስጢፋኖስም ጸጋንና ኀይልን ተመልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር" ሐዋ፡ 6፥8 የተከበራችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ ባላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ። እነሆ የፊታችን ሐሙስ በፎቶዉ እንደምታዩት ጉባዔ ተሰናድቷል በቅርብ ያላችሁ መገኘት ብትችሉ በብዙ ታተርፉበታላችሁ በርቀት ያላችሁ ደግሞ በዚሁ ቻናላችን በድምጽ፤ በመምህር ሳዶር የፌስቡክ ገጽ እና ቲክቶክ እንዲሁም በናታኒየም ፕሮሞሽን ዩቲዩብ ገጽ በቀጥታ በምስል የምናሰራጭ መሆኑን በአክብሮት እየለጽን ሊንኮቹ በዚሁ ቻናል ላይ የምናገኛቸዉ መሆኑን እናሳስባለን የዩቲዩብ ገጻችንን እባካችሁ ሰብስክራይብ አድርጉልን #አምኀ_ተዋኅዶ_ዘኦርቶዶክስ ይሰኛል
Show all...
#ጌታ_ሆይ_ሩፋኤል_ደስ_ይበለው_ብለህ_ማረን "በእንተ #ሩፋኤል መልአክ ዓቃቤ ትእዛዝከ ወዑራኤል ገባሬ ሥምረትከ ወበእንተ ኪሩቤል አፍራሲከ ወሱራፌል ላዕካነ ቤትከ በእንተ ሚካኤል ምእመንከ ወገብርኤል አብሣሬ ትስብእትከ" ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ሕግህን ወዶ የሚጠብቀው መልአክ #ሩፋኤል ደስ ይበለው ብለህ። ውድህን የሚሠራ #ዑራኤል ደስ ይበለው ብለህ። ነበልባላዊት ዙፋንህን የሚሸከሙ #ኪሩቤል ደስ ይበላቸው ብለህ. ነበልባላዊት ማደሪያህ የምትሆን ሕዝብህን የሚጠብቁ #ሱራፌልም ደስ ይበላቸው ብለህ። ሀልዎትህን ያልዘነጋ #ሚካኤል ደስ ይበለው ብለህ። ሰው መሆንህን በትጋት የነገረን #ገብርኤልም ደስ ይበለው ብለህ። ይቅር በለን ማረን ራራልን። #አሜን "በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል እግዚአብሔርን፦ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ" መዝ 91 #ፓንዋማንጦን
Show all...
✞ ኒቆዲሞስ ✞ ኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ ክቡር ሌሊቱን በብርሃን የሚማር መምህር(፪) በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ በመከራው ፅናት ይህን ዓለም ናቀ መምሕር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ የትዕቢትን ጅረት በትሕትና ተዋርዶ አደረቀ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የአቢ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ ፍርሃትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ የመግነዙን በፍታ በሽቱ ያከበረ ከመቅደሱ አንቀጽ ላይረሳ አምድ ሆኖ ታጠረ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የአቢ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ነገረች ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች ከጨለማው ኃጢአት ነቅታ ብርሃን ካየች እንደ ኒቆዲሞስ ነፍስህም ተምራ ተመለሰች ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የአቢ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ በሌሊት አጋማሽ መምህር ለመምህር ሰገደ፤ ጣትስ ከጣት ይልቅ አይደለምን? መዝሙር ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ "ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ" ዮሐ፫፥፩-፴፮
Show all...