Ethio ድንቃድንቅ
Open in Telegram
📌Let's have fun together 👉 ይገረሙ 👉 ይደነቁ 🌍 ለማመን የሚከብዱ አስገራሚ እውነታዎችን እዚህ ያገኛሉ። 🏁 @denkadink join እና share ማወቅ መሰልጠን ነው እየሳቁ 😂 ይወቁ 📚 @denkadink
Show more1 129
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
1 129
Repost from ሰሌዳ | Seleda
አሜሪካ የDV-2025 አመልካቾችን መቀበል ጀመረች።
⚡️የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመታዊውን የዲይቨርሲቲ ቪዛ (#ዲቪ) ፕሮግራም / " ግሪን ካርድ ሎተሪ " በመባል የሚታወቀውን በአሜሪካ ለመኖር እና ለመስራት ለሚፈልጉ አመልካቾች ዛሬ ክፍት አድርጓል።
⚡️እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ መርሃ ግብሩ ከትናንት ሩቡዕ ጥቅምት 4 ተጀምሮ ማክሰኞ ህዳር 7 ቀን 2023 ይጠናቀቃል።
⚡️አሜሪካ አሁን ባለው ፕሮግራም 55000 ለሚደርሱ የውጭ ዜጎች የግሪን ካርድ እድል ትሰጣለች።
⚡️የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዲቪ ፕሮግራም ለመመዝገብ / ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ እንደሌለው አሳውቋል።
⚡️ነገር ግን ወደፊት ለቃለ መጠይቅ ቀጠሮ የተያዙ ተመራጮች መደበኛ የቪዛ ማመልከቻ ከማቅረባቸው በፊት የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ። እነዚህ ተመራጮች በቆንስላ ኦፊሰር አማካኝነት ለቪዛ ብቁ መሆን አለመሆናቸውን የሚወሰንላቸው ናቸው።
⚡️በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዲቪ ለመሙላት ብቁ ከሆኑ በርካታ ሀገራት 55,000 አመልካቾች በዘፈቀደ በውስጥ ስርዓት ይመረጣሉ።
⚡️አስፈላጊ መመሪያዎችን ፣ መስፈርቶችን እንዲሁም ለማመልከት ይህን ትክክለኛ ድረገፅ ይከተሉ፦ https://dvprogram.state.gov/
⚡️አመልካቾች ዲቪ ለማመልከት #ክፍያ_የማያስፈልግ ስለሆነ ከአጨባርባሪዎች እንዲጠነቀቁ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል።
1 129
መስቀል ኃይልነ፤ መስቀል ጽንዕነ፤ መስቀል ቤዛነ፤ መስቀል መድሀኒተ ነፍስነ፤ አይሁድ ክሕዱ ንሕነሰ ኣመነ ወእለ አመነ በኃይለ መስቀሉ ድኅነ። እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ።
1 129
ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ፤ ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም፤ ወይረውዩ አድባረ በድው።
በቸርነትህ አመታትን ታቀዳጃለህ፤ ምድረበዳውም ስብን ይጠግባል፤ የምድረበዳ ተራራዎች ይረካሉ፤ ኮረብታዎችም በደስታ ይታጠቃሉ።
መዝ 64:11
መልካም አዲስ አመት ይሁንልን።
1 129
ይህንን ያውቃሉ🤔
Brunei በምትባል እስያዊት ሀገር ከ 400,000 በላይ ሰዎች የምኖርባት ስትሆን በዚህች ሀገር አንድ የሚያስደንቅ ተግባር አለ እሱም በአገሪቱ የሚኖሩ ዜጎች ካለምንም ክፍያ ነጻ የትምህርት እና ህክምና አገልግሎት እንዲሁም ሩዝ በነፃ እንዲያገኙ በማድረግ የሀገሪቱ ዜጎች ስለ ኑሮ ውድነት በዜና እንዲሰሙ ብቻ አድርጓል::
1 129
"ጳጉሜን"
⚡️ጳጉሜን ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ዮሐንስ ጳጉሜ ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ በመባል ትታወቃለች ፡፡
1 129
አውደ አመት አመት!
ድገምና አመት ድገምና!
ባዲሱ አመት
ሰላም በረከት
ይትረፈረፋል በእውነት።
አመት ድገምና....
አመት ድገምና....
መልካም የቡሄ በአል እንመኛለን።
1 129
አውደ አመት አመት!
ድገምና አመት ድገምና!
ባዲሱ አመት
ሰላም በረከት
ይትረፈረፋል በእውነት።
አመት ድገምና....
አመት ድገምና....
መልካም የቡሄ በአል እንመኛለን
1 129
#ዒድ_አልፈጥር
ውድ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆናችሁ ቤተሰቦቻችን በሙሉ እንኳን ለ1444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ዒድ ሙባረክ !
በዓሉ የሰላም ፣ የአንድነት ፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።
በዓሉን ስታከብሩ የተቸገሩት ፣ ያጡትን ፣ በችግር ላይ የወደቁትን ፤ በሰላም እጦት የሚሰቃዩትን ፣ በጦርነት እና በግጭት ወገን ዘመዶቻቸውን ከጎናቸው የተነጠቁትን ፣ ከሞቀው ቄያቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የቀሩ ወገኖቻችን በማሰብ ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን።
ሀገራችንን ፈጣሪ ይጠብቅልን!!
መልካም በዓል !
1 129
#ትንሳኤ
እንኳን አደረሳችሁ !
ውድ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።
በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።
በዓሉን ስናከብር ፤ የተቸገሩ ወገኖቻንን አለንላችሁ በማለት ፣ የወደቁትን በማንሳት ፣ በሀዘን ላይ ያሉ ወገኖችን በማፅናናት፣ ከክፉ ድርጊትና ሀሳብ ርቀን ሊሆን ይገባል።
በተጨማሪም ፤ በዓሉን በሰላም እጦት ፣ በግጭት ፣ በጥቃት፣ በድርቅ ክፉኛ የተጎዱ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በገዛ ቄያቸው ከሞቀው ቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የወደቁትን ፤ በፀሃይና ዝናብ የሚንከራተቱትን ፤ የሚወዱትን ተነጥቀው በጥልቅ ሀዘን ላይ የሚገኙትን ፣ ታመው በየሆስፒታሉ የተኙትን ፣ በየሰው ሀገር በስደት ስቃያቸውን እያዩ ያሉ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በግልም ፤ በሀገርም ላለብን ችግር ሁሉ አምላክ መፍትሄ እንዲያበጅልን እየተማፀንን እንድናሳልፍ አደራ እንላለን።
የሰላም፣ የመተሳሰብና የበረከት በዓል ያድርግልን !
ፈጣሪ ሀገራችን ሰላም ያድርግልን !
መልካም በዓል !
1 129
#ትንሳኤ
እንኳን አደረሳችሁ !
ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የቲክቫህ አባላት በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።
በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።
በዓሉን ስናከብር ፤ የተቸገሩ ወገኖቻንን አለንላችሁ በማለት ፣ የወደቁትን በማንሳት ፣ በሀዘን ላይ ያሉ ወገኖችን በማፅናናት፣ ከክፉ ድርጊትና ሀሳብ ርቀን ሊሆን ይገባል።
በተጨማሪም ፤ በዓሉን በሰላም እጦት ፣ በግጭት ፣ በጥቃት፣ በድርቅ ክፉኛ የተጎዱ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በገዛ ቄያቸው ከሞቀው ቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የወደቁትን ፤ በፀሃይና ዝናብ የሚንከራተቱትን ፤ የሚወዱትን ተነጥቀው በጥልቅ ሀዘን ላይ የሚገኙትን ፣ ታመው በየሆስፒታሉ የተኙትን ፣ በየሰው ሀገር በስደት ስቃያቸውን እያዩ ያሉ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በግልም ፤ በሀገርም ላለብን ችግር ሁሉ አምላክ መፍትሄ እንዲያበጅልን እየተማፀንን እንድናሳልፍ አደራ እንላለን።
የሰላም፣ የመተሳሰብና የበረከት በዓል ያድርግልን !
ፈጣሪ ሀገራችን ሰላም ያድርግልን !
መልካም በዓል !
1 129
" ስቅለት "
ዕለቱ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ዂሉ መድኀኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የሚታሰብበት ታላቅ ቀን ነው።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን #በስግደት እና #በጾም የሚታሰብ ሲሆን በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረትም በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ታስቦ ይውላል፡፡
በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከንጋታው ጀምሮ እስከ ማምሻው በዕለቱ የተፈጸሙትን ክስተቶች በሰዓት ከፍላ በልዩ መንፈሳዊ ሥርዓትና በስግደት ታከብረዋለች
✝ ዓርብ ጠዋት
ዓርብ ጠዋት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት በፍርድ አደባባይ መቆሙ ይታሰባል። የካህናት አለቆችና ሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ፤ አስረውም ወሰዱት ፥ ለገዢው ለጰንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።
✝ በ3 ሰዓት
ጲላጦስ በወቅቱ በነበረው ሕዝብ ግፊት መሠረት ወንጀለኛውን በርባንን ከእስር አስፈትቶ በምትኩ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠበት፤ አካሉ እስኪያልቅም 6,666 የገረፉት ከሊቶስጥራ - ቀራኒዮ እርጥብ መስቀል አሸክመው የወሰዱበት ነው።
✝ በ6 ሰዓት
ኢየሱስ ክርስቶስን እጆቹን እና እግሮቹን ቸንክረው በቀራንዮ ጎልጎታ ተራራ በ2 ወንበዴዎች መካከል የተሰቀለበት ነው።
✝ በ9 ሰዓት
በእምነቱ አስተምሮ ይህ ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ከሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ የለየበት ወደ ሲዖል ወርዶም የታሠሩትን ሁሉ ያስፈታበት ነው።
✝ 11 ሰዓት
ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብር እና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር የቀበሩበት ነው።
#Repost
Credit @tikvahethiopia
1 129
Jordan Kinyera ይባላል የዩጋንዳ ዜግነት ያለው ሲሆን በ6 ዓመቱ አባቱ ይህንን የራሱን የነበረ መሬት በሕጋዊ መንገድ አቶት ነበር ይህ ልጅ 18 ዓመት በትምህርት ህይወት ካሳለፈ በዋላ በጠበቃ ሰራተኝነት ተቀጥሮ ከ23 ዓመት በዋላ አሸንፎ የአባቱን መሬት የግሉ አድርጎታል!
@denkadink
1 129
የሚፈልጉትን መፅሃፍ በነፃ አውርደው ለማንበብ የሚጠቅሙ ምርጥ 5 ዌብሳይቶች
*******
1. Project Gutenberg -
www.gutenberg.org
2. Book Boon -
www.bookboon.com
3. Many Books -
www.manybooks.net
4. Free Ebooks -
www.free-ebooks.net
5. Open Library -
www.openlibrary.org
@denkadink
1 129
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን
ለኢየሱስ ክርስቶስ
የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
ብርሀነ ጥምቀቱ የሠላም,የፍቅር,የአብሮነት,የመቻቻልና የጤና እንዲሆንልን እንመኛለን።
መልካም በዓል
1 129
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን
ለኢየሱስ ክርስቶስ
የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
በዓሉ የሠላም,የፍቅር,የአብሮነት,የመቻቻልና የጤና እንዲሆንልን እመኛለሁ።
መልካም በዓል
1 129
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
መስቀል ሀይልነ ፣መስቀል ፅንህነ ፣
መስቀል ቤዛነ፣ መስቀል መድሀኒተ ነፍስነ
አይሁድ ይክህዱ ለእለ አመነ በሀይለ መስቀሉ ድህነነ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ እያልን መልካም የደመራ በዓል እንመኝላችኋለን!!
We wish you a Happy Holiday!!!
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1 129
ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1443ኛው ዒድ አል ፊጥር በዐል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ።
ዒድ ሙባረክ መልካም በዓል
@denkadink
