Ethiopian Customs Clearing Agents
Open in Telegram
6 613
Subscribers
+424 hours
+427 days
+23430 days
Posts Archive
June_2023_ትራንዚት_ተፈቅዶላቸው_በወቅቱ_ወደ_ሀገር_ስላልገቡ_ጭነቶች_ሠርኩላር.pdf8.68 KB
If Interested...........
⚜ወደ ሀገራችን ከሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መካከል በቻይና ሀገር ተገጣጥሞ ወደ ኢትዮጲያ እየገባ የሚገኘው ቮልስ ዋገን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ህጋዊ የሆነ ፍቃድ የሌለው መሆኑን የጀርመን ኩባንያ በኢንባሲው በኩል ለሚኒስቴር መ/ቤቱ በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡
ስለሆነም ይህ ቻይና ሀገር የሚመረተው የቮልስ ዋገን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ከኩባንያው ህጋዊ ፈቃድ ያለው መሆኑ እስኪረጋገጥ ድረስ በጊዜያዊነት ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ የታገደ መሆኑን እወቁልኝ ብሏል፡፡፡፡
Source:
👉የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር
🚢 ከቻይና /China/
Nansha, Shekou, Xiamen, Ningbo, Qingdao, Shanghai, Xingang/Tianjin, Huangpu, Yantian, Nanjing ወደቦች
⚜ለ20 ጫማ ኮንቴይነር ከ37.5% እስከ 47.91 % ቅናሽ
⚜ለ40 ጫማ ኮንቴይነር ከ50.96% እስከ 64.71% ቅናሽ
🚢 ከህንድ /India/
Nhavasheva (JNPT) Mumbai, Mundra, Ennore, Tuticorin, Hazira, Culcatta, Chennai (Madras) ወደቦች
⚜ ለ20 ጫማ ኮንቴይነር ከ20.21% እስከ 66.38% ቅናሽ
⚜ለ40 ጫማ ኮንቴይነር ከ36.71 እስከ 183.08% ቅናሽ
🚢 ከቱርክ /Turkey/
Izmit/Korfezi/Evyap/Yarimca, Mersin, Istanbul/Ambarli/Kumport/Hudrapassa ወደቦች
⚜ለ20 ጫማ ኮንቴይነር ከ16.1% እስከ 21.58 % ቅናሽ
⚜ለ40 ጫማ ኮንቴይነር ከ31.44% እስከ 61.60% ቅናሽ
🚢 ከቤልጂም /Belgium/ Antwerp ወደብ
⚜ለ20 ጫማ ኮንቴይነር የ24.45% ቅናሽ
⚜ለ40 ጫማ ኮንቴይነር የ59.94% ቅናሽ
🚢 ከኔዘርላንድ/ Netherlands/ Rotterdam ወደብ
⚜ለ20 ጫማ ኮንቴይነር የ24.45% ቅናሽ
⚜ለ40 ጫማ ኮንቴይነር የ57.60% ቅናሽ
🚢ከጣሊያን /Italy/ Genoa ወደብ
⚜ለ20 ጫማ ኮንቴይነር የ46.96% ቅናሽ
⚜ለ40 ጫማ ኮንቴይነር የ88.92% ቅናሽ
🚢ከግብፅ /Egypt/ Alexandria ወደብ
⚜ለ20 ጫማ ኮንቴይነር የ33.92% ቅናሽ
⚜ለ40 ጫማ ኮንቴይነር የ43.70% ቅናሽ
🚢 ከሳኡዲአረቢያ /S.Arabia/ Jeddah እና Dammam ወደቦች
⚜ለ20 ጫማ ኮንቴይነር የ18.31% እና የ49.39% ቅናሽ
⚜ለ40 ጫማ ኮንቴይነር የ15.29% እና የ50.66% ቅናሽ
🚢 ከኢንዶኔዥያ /Indonesia/ Belawan እና Jakarta ወደቦች
⚜ለ20 ጫማ ኮንቴይነር የ38.25% እና የ40.00% ቅናሽ
⚜ለ40 ጫማ ኮንቴይነር የ81.49% እና የ70.82% ቅናሽ
🚢 ከማሌዥያ/Malaysia/ Port Klang ወደብ
⚜ለ20 ጫማ ኮንቴይነር የ42.47% ቅናሽ
⚜ለ40 ጫማ ኮንቴይነር የ56.91% ቅናሽ
🚢 ከታይላንድ /Thailand/ Laem Chabang ወደብ
⚜ለ20 ጫማ ኮንቴይነር የ38.14% ቅናሽ
⚜ለ40 ጫማ ኮንቴይነር የ51.84% ቅናሽ
🚢 ከደቡብ ኮሪያ /South korea/ Busan ወደብ
⚜ ለ20ጫማ ኮንቴይነር የ41.15% ቅናሽ
⚜ለ40 ጫማ ኮንቴይነር የ82.23% ቅናሽ
⚜ In Case You Missed the News:
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ እ.ኤ.አ ከኤፕሪል 01 ቀን 2023 ጀምሮ ተግባራዊ በተደረገው የባሕር ትራንስፖርት ታሪፍ ቅናሽ መሰረት ለባለ ሃያ ጫማ ኮንቴይነር ከ16% እስከ 66.38% እንዲሁም ለባለ 40 ጫማ ኮንቴይነር ከ15.29% እስከ 183.08% ቅናሽ ማድረጉን እወቁልኝ ብሏል፡፡
በመሆኑም ስትራቴጂክ ለሆኑ 32 የመጫኛ ወደቦች የተደረገውን ቅናሽ በመቶኛ ከታች መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
If Interested .......
⚜️የንግድ፣የቁም እንስሳት ግብይት እና የጥራት ረቂቅ ፖሊሲ
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በሀገራችን ግልፅ፣ፍትሃዊ እና ዘመናዊ እና በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ የሆነ የንግድ ስርአት የመገንባት ተልዕኮውን ለመወጣት በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት የንግድ፣የቁም እንስሳት ግብይት እና የጥራት ረቂቅ ፖሊሲ አውጥቷል፡፡
ረቂቅ ፖሊሲው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተመልክተውት እና አስተያየት ከተሰጠበት በኋላ ሀሳቦቹ እንዲካተቱ የሚደረጉ ይሆናል፡፡
በመሆኑም ማንኛውም አስተያየት ያለው destaw-mequanint@motri.gov.et በሚለው ኢሜይል አድራሻ እስከ ግንቦት 10/2015 ድረስ እንዲላክልን በማለት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጠይቋል፡፡
If Interested...........
⚜የቤት ግብር ማሻሻያ
⚜Rental Income Tax Ammendment
የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ በቁጥር ፋ/ቢ/2/64/2249 በቀን 3/3/2015 በተፃፈ ደብዳቤ መነሻነት አሁን ያለውን ዓመታዊ የቤት ግብር ግምት ለማሻሻል የዳሰሣ ጥናት በማቅረብና በተገኘው የጥናቱ ውጤቶች ላይም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አቅጣጫ የተሰጠበት በመሆኑ የገቢዎች ቢሮ የመሬት ተቋማት በሚልኩት የግብር ግምት መሠረት የቤት ግብሩ እንዲሰበስብ የተወሰነ በመሆኑ ተግባራዊ እንዲደረግ በማለት በቁጥር 10/1/9357/15 በቀን 5/8/2015 ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የተላለፈ ሠርኩላር
⚜የገንዘብ ሚኒስቴር በቁጥር ማኢ 30/07/9880 በቀን 29/05/2015 የጉምሩክ ታሪፍ ምጣኔ ማሻሻያ እንዲደረግ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ማሻሻያው ተግባራዊ እንዲደረግ የካቲት 09 ቀን 2015 በደብዳቤ ቁጥር 6.3/0109/15 ከጉምሩክ ኮሚሽን የተላለፈ ሠርኩላር
⚜አዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ረቂቅ_ English Version
⚜New VAT Proclamation Draft
⚜አዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ረቂቅ_ Amharic Version
⚜New VAT Proclamation Draft
⚜EFDA Circular Issued on February 09, 2023 to all Medicine Manufacturers, Importers and Wholesalers regarding Medicines Promotional Material Approval
⚜ኒዶ ፎርቲፋይድ 400 ግራም ፉል ክሬም የዱቄት ወተት የመለያ ቁጥሩ 0000039688 በተመለከተ የተሰጠ ማሳሰቢያን ማንሳትይመለከታል።
የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1112/2011 መሰረት ከተሰጡት ኃላፊነቶች በምግብ ደህንነት ላይ ችግር መኖሩን ሲጠረጥር ጊዚያዊ እርምጃን በመውሰድ አስፈላጊን ማጣራት በማድረግ ጥሰት መፈጸሙን ሲያረጋግጥ እርምጃ የመውሰድ ወይም የተፈጸመ ጥሰት የሌለ እንደሆነ የወሰደውን ጊዚያዊ እርምጃ የማንሳት ተግባር አንዱ ነው። በዚሁ መሰረት ኒዶ ፎርቲፋይድ 400 ግራም ፉልክሬም የዱቄት ወተት የመለያ ቁጥሩ 0000039688 የሆነ ምርት መያዣ ዕቃው (ጣሳው) ላይ የተጻፈው ድብቅ ጽሑፍ (Barcode) ሲነበብ የምርቱ መጠቀሚያ ጊዜ እ.እ.አ 09/2021 የሚል ሲሆን ከምርቱ መያዣ ዕቃው (ጣሳው) ላይ የተጻፈው ደግሞ እ.አ.አ 01/2024 እንደሆነ ያሳያል በሚል ጥቆማ ለባለስልጣኑ በመድረሱ ህብረተሰቡ ከላይ የተጠቀሰውን ምርት እንዳይጠቀም ማሳሰቡ ይታወቃል።
ባለስልጣኑ ጥቆማው ከደረሰው ጊዜ ጀምሮ ምርቱን በተመለከተ ምርመራና ማጣራት ሲያደርግ ቆይቷል። የላብራቶሪ ምርመራን ጨምሮ በተደረገው ምርመራና ማጣራት የኒስሊ ምርት በሆነው ኒዶ ባለ 400 ግራም የመለያ ቁጥሩ 0000039688 የሆነ የመጠቀሚያ ጊዜው ያላለፈ እና የጥራትም ሆነ የደህንነት ችግር የሌለበት መሆኑን ለማረጋገጥ ችሏል። ለጥቆማ መነሻ የሆነው የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበት መሆኑ ድብቅ ጽሑፍ (Barcode) ያሳያል የሚል ቢሆንም፤ ምርቱ ይህን ጊዜ እንዲያሳይ የተደረገው Addisber.com በተባለ ይህን ለማድረግ (ለማስቀመጥ) የማይመለከተው ሰው ሲሆን ተግባሩም ባለስልጣኑን ጨምሮ ህብረተሰቡን ያሳሳተ በመሆኑ ጉዳዩ በሚመለከተው የፍትሕ አካል ተይዞ የወንጀል ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል። ባለስልጣኑም የምርቱ የመጠቀሚያ ትክክለኛ ጊዜ ድብቅ ጽሑፍ (Barcode) ላይ ያለው ሳይሆን በምርቱ ገላጭ ጽሑፍ ላይ ያለው መሆኑን አረጋግጧል።
ስለሆነም ባለስልጣኑ ከዚህ ቀደም ህብረተሰቡ እንዳይጠቀመው ያሳሰበው ኒዶ ባለ 400 ግራም የምርት መለያ ቁጥሩ 0000039688 የሆነ በህጋዊ መንገድ ወደ አገር ውስጥ የገባ መሆኑን ያረጋገጠና የመጠቀሚያ ጊዜው ያላለፈ ስለሆነ ህብረተሰቡ ምርቱን መጠቀም የሚችል መሆኑን ለማሳወቅ ይወዳል።
በዚህ አጋጣሚ ጥቆማ በመስጠትም ሆነ በማጣራት ሂደቱ ለባለስልጣኑ አስፈላጊውን መረጃ በመስጠት የተባበሩትን ሁሉ ለማመስገን ይወዳል።
የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን
#EFDA
