en
Feedback
ፍቅሬን በግጥም 💞

ፍቅሬን በግጥም 💞

Open in Telegram

✍️ለምን ወደድኩህ/ሽ? እንጃ።🤷‍♀️‍ ✍️ምንህ /ምንሽ ተመቸኝ ? እንጃ🤷‍♀️ ✍️እንዴት ማረከኝ/ሺኝ? እንጃ🤷‍♀️ ♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር💟 ማለት፤ ➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤ ➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤ ➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟 👉comet ena malt yemet felguti ngr kal @Erazatube_bot

Show more
4 788
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-5230 days
Posts Archive
💔💔 ሁለቴ ከዳሺኝ 💔💔 ጥቂት በማይባለው ያሳለፍነው ጊዜ፣ ባንቺ የውሸት ምላስ ምንኛ መያዜ፣ ታፈቅረኛለች ብዬ ብዙ አውርቻለው፣ እንደማታፈቅሪኝ የገባኝ አሁን ነው፣ እስኪ አንዴ ስሚኝ ልምከርሽ ፍቅርዬ፣ ይህው ቃል ገባሁልሽ አልጠላሽም ብዬ፣ ጥሩ አፍቃሪ ሆነሽ እስኪ ልመልከትሽ፣ የድሮ ማንነትሽን ጣይው አሳፍረሽ፣ ሁለቴ ከድተሺኝ ልቤ ቢሠበርም፣ ቂም ባሊዝብሽም ዐይኔን ግን አታይም፣ ለአዲሱ ሕይወቴ እስክዘጋጅ ድረስ፣ ፍቅርን አውቀሽ ልይሽ መንፈሴም ይታደስ ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ካወኳቸው ሁሉ ልቤ አንችኑ መርጧል ማንነትሽ ማርኮት ማፍቀሩን አጋልጧል ምን ቆንጆ ቢሞላ ቢትረፈረፍ በዝቶ አይኔም ሌላ ላያይ ምሏል ተገዝቶ እግሮቼም ካንቺ ውጭ ከቶውን ላሄዱ ወስነው ቆርጠዋል ተዘግቷል መንገዱ ከንግዲ ለኔ ጎን ያለሽው አንቺ ነሽ ብዬ ምፅፍልሽ የኔ ሴት ወዴት ነሽ🤔😔 ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

❤️አልልም ❤️‍🔥 """""""""" ላንቺ ልቤን ሰጠሁ አምኜሽ 😕 አመልሽን #ቻልኩት ወድጄሽ ፣ ስለተከዳሁኝ አልል ሴት አላምንም ፣ ፆታ ውልደት እንጂ እድገት አይወስንም ። #ተከዳሁኝ በቃ በኔ አዲስ #አይደለም ፣ እኔ ግን አልልም የእውነት #ፍቅር_የለም😒 እርግጥ #ጎድተሽኛል ጨካኝ አልልሽም 💔 ቀንም ቢሆን እንኳ #ሳይነጋ አይመሽም ። ሰው ሙሉ አይደለም ከአዳም ጀምሮ ፣ ሁሉም ድክመት አለው የሚቀርፈው አድሮ ተስፋ አለኝ አንድ ቀን 🙏 የወንድ ልጅ እንባ  #በሴት እንደማይፈስ በወንድ ልጅ #መካድ ትዳር እንደማይፈርስ ‼️ አይወጣኝ ክፉ ቃል #አረግምሽም ከቶ ፣ ሰው ተዋዶ እንጂ አይኖርም ተጣልቶ ፣ ሊቃረን ይችላል አመሉ #ላይገጥም#ከቢጤው ጋራ ነው ሰው ውሎውም የሚጥም🤦‍♂ ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

#ምኗ_ነው? : : : ምኗን ነው ግን የወደድከው አልፎ አልፎ ይለኛል ሰው፤ እንዲ ብሎ ሚጠይቀኝ የሆነ ብቃት እንዳነሰው፤ መጠይቁ ያሳብቃል፤ የልቡ ዓይን ያልበራለት ወትሮስ ፍቅርን እንዴት ያውቃል። : : ብዙ ማዕረግ ብዙ ገድል የቀለም ቀንድ ጥልቅ ሀሳቡ፤ እስካልበራ እውር ልቡ፤ ፍቅር ወርሶ እስካልቋጨው፤ ሰው አይሆንም የምድር ጨው። : : ሆነሽልኝ ዝርግፍ ጌጤ ወርቀዘቦ ተክህኖ፤ አዋቂው ሰው ለጋ ሆኖ፤ እንዲያ ብሎ ሲጠይቀኝ ያደርገኛል ደርሶ ብግን፤ የሚጠላው ምኗ ነው ግን? ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

😀➿➿➿➿➿😭➿➿➿➿➿😀 ፈጣሪ አምላኬ ~ ይቅር በለኝ ዛሬ ህግህን ሳፈርሰው አትፍረድ ብትልም ~ እኔ ግን አልቻልኩም ፈርዳለው በዚህ ሰው። የክፋትን ጥጉን ~ የመቆሸሽ ጥጉን ገደቦች ላለፈ ያንዲት
😀➿➿➿➿➿😭➿➿➿➿➿😀 ፈጣሪ አምላኬ ~ ይቅር በለኝ ዛሬ          ህግህን ሳፈርሰው አትፍረድ ብትልም ~ እኔ ግን አልቻልኩም         ፈርዳለው በዚህ ሰው። የክፋትን ጥጉን ~ የመቆሸሽ ጥጉን         ገደቦች ላለፈ ያንዲት ምስኪን ህፃን ~ ክብሯን በግፍ ገፎ          ነፍሷን ለቀጠፈ የእጁን እንዲያገኝ ~ ስቃይ እና ሞቱን           ለሱ መመኘቴ የጨቅላዋን ህመም ~ ማሰብ ቢያቅተኝ ነው        ባይችል ነው አንጀቴ ፧ ፧ ፧ የቆሰለ ውስጧን ~ የእናቲቱን እምባ     ሚያብሰው ሲጠፋ ፍትህ እየተዛባ ~ ተበዳይ ሲበደል       ውስጣችን ቢከፋ አቤቱ ፈጣሪ ~ አነባን ወዳንተ        አነባን ወደላይ ፍርድህን አሳየን ~  ክፉዎች ቀጥተህ           በምድርና በሰማይ። ፧ ፧ #ፍትህ_ያለእድሜዋ_በግፍ_ለተነጠቀች_ነፍስ #ፍትህ_ለሔቨን ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

#ፍትህ_ሳትኖር_ለተገደለችው_ህጻን_ሄቨን 😢😢😢😢😢 ፌቨን የ7 ዓመት ህፃን ነች።እናቷ ነርስ ስለሆነች የተከራዩበት ቤት ትታት ትሄዳለች።ነገር ግን ቤት ያክራያቸውና አሁን በማረሚያ ቤት የሚገኘ
+2
#ፍትህ_ሳትኖር_ለተገደለችው_ህጻን_ሄቨን 😢😢😢😢😢 ፌቨን የ7 ዓመት ህፃን ነች።እናቷ ነርስ ስለሆነች የተከራዩበት ቤት ትታት ትሄዳለች።ነገር ግን ቤት ያክራያቸውና አሁን በማረሚያ ቤት የሚገኘው ጌታቸው የተባለ የ3 ልጆች አባት ህፃኗን በአሰቃቂ ሁኔታ አስገድዶ ደፍሮ ገድሏት ተገኘች። የ7 ዓመት ህፃኗ ልጅን ግቢ ውስጥ ወደ ሽንት ቤት ስትሄድ ጠብቆ አፏ ውስጥ አሽዋ በመጨመር ለመግለፅ በሚከብድ ሁኔታ አሰቃይቶ እንደገደላት እናት አስረድታለች።25 ዓመት ተፈርዶበት ማረሚያ ቤት ቢሆንም በይግባኝ ለማስወጣት እየሠሩ ነው።እኔን አስፈችው በማለት ዛቻና ማስፈራሪያው ከአቅሜ በላይ ሆኗል።ህዝብ ይፍረደኝ እያለች ነው። እናንተ ኢትዮጵያውያን ይህ ነገር በደንብ እንዲሸራሸር ፊስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ቲክቶክ ላይ * ሼር እያደረጋችሁ ተባበሯት ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ያጣናቸው ሰዎች ከላያችን ላይ ቦጭቀው የሚወስዱብን ነገር አለ።በመሄዳቸው ያጎሉብናል። እነዚህ ጉድለቶች ቀን በገፋ ቁጥር ልብ ላይ ዘልቀው የሚፈጥሩት ህመም በቀላሉ አይሽርም። ወደ ውስጥ በተመለከትን ቁጥር ጎዶሎነታችን ላይ የምንደርስበት ሰዎች አለን። በራሱ ጨለማ ተውጦ የማያውቅ ማነው?.... አመታት ቢያልፉም እንደ አዲስ የምናለቅስለት ሰው አናጣም። ይህ ስቃያችን በጎጇችን ሰላም፤ በመኝታችን ደግሞ እንቅልፍ ይከለክለናል ....   ፀሐይ ከጨለማዬ ምን አለሽ? ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ልብን እንደ መሰጠት መልሶ መቀበልም ቀላል ቢሆን ኖሮ😔 ልቦች ባልተሰበሩ ነበር አይኖችም ባላነቡ ነበር ምሽቶች የሀዘን ማራገፊያ ባልሆኑ ነበር💔 ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

🦋🦋   መውደድ ስለጋረደው  ልብሽ እናውጋ እስኪ?. . . የትኛው የትእግስት ጥበብሽ ነው እንዳሻቸው እየሆኑብሽ ካለነሱ ያስባለሽ? ....የትኛው ጥንካሬሽ ነው ለሺ በደሎቻቸው ይቅርታን በነፃ የሚያሳድልሽ?. .  .  የቱስ የተለየ ቃል ይዞሽ ነው አንዱን ቃላቸውን ሚሊዮን ጊዜ እያጠፉ ለአንዱ ቃልሽ ፀንቶ ያስኖረሽ?? ምንስ ይሆን እንዲ በተስፋ የሞላሽ?  ... . . ብቻ ምንም ይሁን ያለፍሽባቸውን መንገዶች አቅልዬ በቃሽ አልልሽም ግን ዛሬሽን ልብ በይ ያለሽን አስተውይ ምናልባት ያጣሽው ከሚመስልሽ በላይ ያለሽ ይበልጥ ይሆናል. . . . እንደዛ ይሰማኛል...🦋 🦋🦋 #. . . ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ሳልፈልግ ልርሳሽ💔😭 ወራቶች አልፈዋል እኔ አንችን ሳፈቅርሽ❤️ ድፍረትን አጥቼ በአካል ባልነግርሽ🙊 በቴክስት ፃፍኩልሽ ፍቅሬ ቢገባሽ🌹 ግን አሁን አዘንኩኝ መልስሽን ሳነበው😢 አንቺን አላገኝም
ሳልፈልግ ልርሳሽ💔😭 ወራቶች አልፈዋል እኔ አንችን ሳፈቅርሽ❤️ ድፍረትን አጥቼ በአካል ባልነግርሽ🙊 በቴክስት ፃፍኩልሽ ፍቅሬ ቢገባሽ🌹 ግን አሁን አዘንኩኝ መልስሽን ሳነበው😢 አንቺን አላገኝም ሁሉንም ሳስበው😔 ለኔ ላትሆኝ ነገር ለምን ላስቸግርሽ😓 በዱአ በፆም ሳልፈልግ ልርሳሽ😭                  ✍Eraza ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

😍 ከአቅም በላይ ስለወደድኩሽ 🙏 ይቅር በይኝ! 💞ከማንም በላይ ከአንቺጋ መሆን በመፈለጌ 🙏 ይቅር በይኝ! ❤️በህይወትሽ ውስጥ ትልቅ ቦታ እንድትሰጪኝ በመጠየቄ 🙏 ይቅር በይኝ! 💘መካድ እስ
😍 ከአቅም በላይ ስለወደድኩሽ       🙏 ይቅር በይኝ! 💞ከማንም በላይ ከአንቺጋ መሆን በመፈለጌ       🙏 ይቅር በይኝ! ❤️በህይወትሽ ውስጥ ትልቅ ቦታ እንድትሰጪኝ በመጠየቄ       🙏 ይቅር በይኝ! 💘መካድ እስከማልችል ድረስ ስላፈቀርኩሽ      🙏 ይቅር በይኝ! 💔መውደዴ ስላልገባሽና በእኔ ውስጥ ያለሽን ቦታ ስላላወቅሽ     🙏ይቅር እልሻለሁ! ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

​​​​​​ #ብቻዬን_ላፍቅርሽ ባልኖረ ሌላ አዳም ከምድር በጠፋ፣ የኔ ብቻ እንድትሆኝ ቢደላም ቢከፋ፣ ♠ በሰፊው አለም ላይ ለጥ ባለው ምድር፣ ምናለ አምላክ ፈቅዶ ብቻችንን ብንቀር፣ ሌላ አዳሞች ቀር
​​​​​​ #ብቻዬን_ላፍቅርሽ ባልኖረ ሌላ አዳም ከምድር በጠፋ፣ የኔ ብቻ እንድትሆኝ ቢደላም ቢከፋ፣ ♠ በሰፊው አለም ላይ ለጥ ባለው ምድር፣ ምናለ አምላክ ፈቅዶ ብቻችንን ብንቀር፣ ሌላ አዳሞች ቀርተው ብቻዬን ባፈቅር፣ መሬት ባዶ ትሁን ማንም አይኑርባት ከኔና አንቺ በቀር፣ 💎 ሆንሽና ስስቴ የነፍሴ ጥም አርኪ፣ ቀኔን ምታበሪ ዘወትር ስትስቂ፣ 💌 እንዳትሆኝ የሌላ ልቤ ስለፈራ፣ አዳሞችን ጠላው ስላንቺ ስራራ፣ 💍 ብቻዬን ላፍቅርሽ ማንም ሳይጋራኝ፣ ከሄዋኔ በቀር አዳም አያሳየኝ፣ 🍬 አደለም በውን ተኝቼ በህልሜ፣ ከሌላ አዳም ባይሽ ይብሳል ህመሜ፣ አልድነውም እንኳ በቅጡ ታክሜ፣ 🌼 አዳሞች ራቁ ሽሹ ከኔ ሄዋን፣ ደርሶ የነካትን አልምረውም ነፍሱን፣ 🌹 ድርድር አላውቅም እኔ በሷ ጉዳይ፣ ጦሬን እመዛለው ባልሆንም ሺ ገዳይ፣ 🍊 የኔ ብቻ እንድትሆን አምላክ ባክህ እርዳኝ፣ ከኔ ሌላ አዳም በምድር አይገኝ፣ ልሁን ከሷ ጋራ ተጋፊ ሳይኖረኝ፣ ተው አትንካት ብሎ የሚከለክለኝ፣ 🌺 የውበትሽ ማማር እጅግ ስለ በዛ፣ ሁሉም ይመኙሻል አይተውሽ በዋዛ፣ 💞 ሲረባረቡብሽ እጅግ አፈራለው፣ አዳም ከኔ ሌላ ባላይ እመርጣለው፣ ♥ ከሰዋራው ልቤ ውዴ ልደብቅሽ፣ ማንም ሳይነካብኝ ብቻዬን ላፍቅርሽ!!! ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

•• ስወድሽ ውደጅኝ •• ..... . ውዴ ... እኔ አንቺን መውደዴ፤ መጥፎ እድል አይደለም ችግር የሚያመጣ ወንጀልም አይደለም በህግ የሚያስቀጣ፤ ሀጢያትም አይደለም አንገት የሚያስደፋ ሰማይ ቤት አ
•• ስወድሽ ውደጅኝ ••      ..... . ውዴ ... እኔ አንቺን መውደዴ፤ መጥፎ እድል አይደለም ችግር የሚያመጣ ወንጀልም አይደለም በህግ የሚያስቀጣ፤ ሀጢያትም አይደለም አንገት የሚያስደፋ ሰማይ ቤት አትቆምም ነብሴ ተጠይቃ-ትዕዛዝ ተላልፋ፤ ታድያ አንቺን መውደዴ ምን ላይ ነው ጥፋቱ? ወደድኩሽ ማለቴስ ምንድነዉ ክፋቱ? ጠልተሺኝ እንዳይሆን ቁርጡን እንዳላውቀው  እንደምትወጂኝ ነው ውስጥሽ ሚያሳብቀው፤ ታድያ እየተዋደድን አንድ ሆኖ ውስጣችን ለምን እንራራቃለን እንሁን ለብቻችን፤ ስለዚህ ውድዬ....... ባንቺ ፍቅር ጨርቅ ሳልጥል ወይ ሳታሳብጂኝ በፍፁም ተማምነን ሳልከዳሽ ሳትከጂኝ ሳልጎዳሽ ሳትጎጂኝ፤ መራራቁን ትተሽ ስወድሽ ውደጂኝ❤️😍። ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

🇼 🇪 🇱 🇱 🇨 🇴 🇲 🇪 በሀገራችን አሉከሚባሉ ምርጥ የ TG ግሩፕ ነው። 👉#እመኑኝ እኔ 100% ኧረ እንደውም 200% አምኜበት እንድትቀላቀሉት የምጋብዛቹ GROUP... ይህግሩፕ ለየትየሚያደርገው 👌በየወጎቻችች መሀል እርሶን ያዝናናሉ ተብለው የታሰቡ ምርጥቀልዶች😁 👉 ልብ የሚነኩ የፍቅር ግጥሞች ትኩስመረጃዎችን የምናካፈልበት 👌ሁሉም የሚሳተፉበትና ራስዎን የሚገምቱበት የጥያቄናመልስ ውድድሮች። 👌 ✍ በዚህ ግሩፕ የማውቀውየሌም ማንንላውራ ተብሎ አይታሰብም😳  👉ከርስዎየሚጠበቀው ከ CoNTACT ዎ ጎድኞቾን👉 Add 👈 በማድረግ የዚህ ቤተሰብ አባልእድሆኑ በመጋበዝ ዘና ማለትነው። 🔔 🔆60 ሰው add ላደረገ ለ 👉1 👈 ሳምንት ፎቶው የ #GROUP Profileና   በ GROUPው እውቅና እሰጣለን ✍      ⚠️👉ህጎች👈❗️ 🙌No ዘርመቁጠር❌❌ 💁No ጭንቀት😠😂 💁No ዝምታ😷😁 💁No ፖለቲካ ❌❌ 💁No ስድብ 😡❌❌ No Tata Just ፈታ😂። 🙌link post አይቻልም❌❌እቢካልክ #Spam 💁መጀናጀን👌👫በአሪፍ ሙድ መቀወጥ😝 💁ምርጥ የሙዚቃ ግብዛዎች🎧 😳ወንዶች ይቦጨቃሉ😜 👌ሴቶች ይናቆራሉ 💁በሴቶች የበላይነትና በፍቅር የሚመራ 💪 💁ያበደ ቀውጢግሩፕ😘 አሁኑ Serch በመጠቀም 👉@public_Groupppp Join👈 ያድርጉ።👇👇 @public_Groupppp

​🌹🍃🕊...✍ዐይኔ ይነግርሻል 'አትንገራት' አሉኝ ማፍቀርህን ገልፀህ😍 መውደድህን አውቃ እንዳትኮራብህ😏 ብትኮሪ ኩሪ ልክ እንደ ንግሥት👸 በልቤ አንድደሻ የማይከስም እሳት ልደብቅ አልችልም አንቺዬን ማፍቀሬን ዐይኔ ይነግርሻል የህይወት ሚስጥሬን መኩራት አይጠቅምሽም ከኔ መሸሸት ቅረቢ እንቋደስ የመውደድን ህብስ ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

የኔ ፍቅር..አንድ ቃል ህይወቴን ልዩ የሆነ ደስታ ሊሰጠዉ እንደሚችል ታዉቂያለሽ? ይህን ቃል ለመስማት ማንኛዉንም መስዋዕት አደርጋለሁ..በጆሮዎቼ ስር ሆነሽ በሚነዝረዉ ድምፅሽ < እወድሃለሁ > በይኝ✨💞💜 ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

​​​​​          💞  ቃል ብዬ ጠራሁሽ  💞 ስላንች ለመፃፍ ብእር እቀርፅና ቀለሙን አቅልሜ ፈቅፍቄ ብራና ፊደልና ቃላት እንደልጅ እያማጥኩ ሀረግ እየመዘዝኩ ምሳሌ እየጠቀስኩ ቃል ባጣው ልሳኔ ስፅፍ ውዬ አድሬ ገልጨሽ ሳይበቃኝ ትደርቃለች ብእሬ ደግሞ ተመልሼ................ ደሜን አንጠፍጥፌ ቀለሙን አቀለምኩ አጥንቴን ፈቅፍቄ ላንች ብእር ቀረፅኩ ብእሬን በደሜ ነክሬ ሳወጣው አንችን እገልፅበት ቅንጣት ቃላት አጣው ለካንስ ቃልዬ!!! በፍቅር ነሁልሎ መንፈስ ከደከመ ናፍቆት አገርጥቶት ልብ ከታመመ እንኳን ቃል ተዋቅሮ ቅኔ ሊመሰጠር ደግሞ ስንኝ ሁኖ ግጥም ሊደረደር ደህና አደርክ ሲባል ለእግዚአብሄር ይመስገን አንደበት ቃል ያጣል ሲመርቁት ለአሜን ለዛ ነው ቃልዬ!!! መግለጫ ቃል ባጣ እልፍ ዘመን ሙሉ የብራናዬ ገፅ ግራ ገብቶት ውሉ እየደጋገምኩኝ የፃፍኩት አንድ ቃል እ ን ዲ ህ ብቻ ይላል ሌላ ቃል ተገኝቶ ወይ ልሳንህ ፈቶ ህቡእ በሆነ ቃል እስከምትገልፃት ቃልህ እሷ ነችና ቃሌ ብለህ ጥራት እናም አንች ቃሌ ነሽ ሀረግና ስንኝ ካጠገቤ ሁነሽ ሰርክ የምትርቢኝ እናም የኔ ንግስት ገፅሽን አድምቄ በልቤ መዝገብ ላይ ቃሌ ብዬ ፃፍኩሽ ቃል አጣው ቃሌ ላይ ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

#ናፈከኝ💓 ♥ያልዋልንበት ጊዜ ውሎዬ ሲመስለኝ ያላለፍነው መንገድ መንገዴን ሲመራኝ❤‍🩹 ያላየነው ሁሉ ትውስታ ሲሆነኝ ባልኖርኩት ትላንት ውስጥ ኖሬ ተገኘሁኝ💕 💗የኖርኩት ካልኖርኩት ገጥሞልኝ ባየው ያልነበረው ሁሉ ተፈጥሮ ባገኘው በልቤ መዝገብ ውስጥ ሰፍሮ ብመለከት ያበድኩ መሰለኝ እራሴን ፈራሁት❤‍🔥 💗ውስጤ ሰላም ሆኖ አይኔ ቢያማትር💞 ያልነበረን ሊያይ በስሜት ቢታትር የሰፈነን ሰላም ሊያሸብር ቢጥር አልገለጥ አለኝ የብዥታው ሚስጥር❣ ባልሄድኩት ጎዳና ሄጄ 💖ባስተውለው ባልኖርኩት ህይወት ውስጥ ህይወቴን ባኖረው ባላሰብኩት ማእበል ሰምጦ ቢገኝ ነፍሴ❤ ሊቋረጥ ቢጣጣር ትንሹ እስትንፋሴ አየሁት እራሴን የኖርኩት መሰለኝ ባልኖርኩት ትላንት ውስጥ ትዝታህ መለሰኝ የህይወቴ ዋሻ አንተን አስታወሰኝ💞 ዛሬ ሀቁን ላውራ በብዙ ናፈከኝ💖💔💞 ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ ባትለኝ ንገሪኝ ካልክ ዛሬም እንደዛው ነኝ የኔ ደህና መሆን ምን #ያሳስብሀል😏 ፍቅር ነው እንዳልል #ትተከኝ ሂደሃል😔 ደግሞ ድንገት መጠክ #አዛኝ ያደርግሀል🫤 እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ ባትለኝ ንገሪኝ ካልክ ግን አንተን እያሰብኩኝ ዘመናት ቆጠርኩኝ❤️‍🔥 እኔነቴን ትቼ ባንተ ውስጥ አለሁኝ አመታቶች አልፈው ዘመናት ቢመጣ አንተን #ከማፍቀር ውጭ ለውጥም አላመጣ😣 ህመሜን ብነግርህ መጠህ #ላታድነኝ ድንገት እየመጣህ ምነው #ባታደማኝ🤦‍♀️💔 ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

 👩‍❤️‍👨                 💋 ሳሚኝ እና ልንቃ💋                        ነግረውሽ እንደሆን… መጎዳቴን አይተው ህመሜን በዝርዝር ጤናዬን እንዳጣው ለክፎኝ ያንቺ ፍቅር የመኖር አኳኋን ውሉ ተዛብቶብኝ ቀንና ለሊቱ እንደተምታታብኝ ሰምተሽ እንደሆነ… አንቺን ካየሁ ወዲህ ሰላም እንደራቀኝ ፍቅርሽ ውስጤ ገብቶ እንደሚያስጨንቀኝ ውበትሽ በልቤ ደምቆ እንደተሳለ የኔ አካል በሀሳብ ካንቺጋ እንደዋለ ሰምተሽ እንደሆነ… ብቻ መዋተቴን እራሴን ማጣቴን ውሎ አዳር መተከዝ አለፍ ሲል መፍዘዝ ለብቻ መፈገግ ዝም ብሎ መበርገግ ሆኗልና ግብሬ ሰርክ የማይቀየር መጥተሽ አንድ በዪኝ ተይ ነገሩ ሳይከር ባንቺ እንደታመምኩኝ ባንቺው ልዳን በቃ በውብ ከንፈሮችሽ ሳሚኝና ልንቃ  ━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━ ━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━ #ሼር ♥️    ♥️ ♥️ ✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨ ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━     🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ @getemi _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ